TG Telegram Group Link
Channel: Islamic Pic Quotes
Back to Bottom
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
كل عام وأنتم بخير وعيدكم مبارك، تقبل الله منا ومنكم صالح الأعمال وأن يعيده علينا بالخير أعواماً عديدة، وندعو الله أن يكمل أعيادنا بالتفريج عن كل المسلمين
Forwarded from የኛ ለምን⁉️
🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺

ህይወት የምትሰጠን ፈተናዎች እምብዛም ከሩቅ የሚመጡ አይደሉም ከጉያችን እንጂ ... ጠላታችን እራሳችን ነን… ወይ ስንፍናችን አልያም ለሰዎች የሰጠነው ግምት ... ሁለቱም ለስኬታችን መሰናክል የሆኑ ፈተናዎቻችን ናቸው:: ቅርብ በመሆናቸው የሚዘነጉ ነገር ግን ደስታችንን ቀስ በቀስ እየሸረሸሩ የሚሄዱ ጉዳዮች ናቸው እና ልብ ብለን ልንሰራባቸው ግድ ይለናል::

የተዋበ ጁምዐ ተመኘሁ!

📍 @yourstressfreezone
ይግቡ ቤተሰብ እንሁን ያማረ ነገን እንፍጠር::

ለሀሳብ አስተያየቶ @stressfreezonebot መጠቀም ይችላሉ::

🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺
Forwarded from የኛ ለምን⁉️
🍥🍥🍥🍥🍥🍥🍥🍥🍥🍥🍥🍥

አላህን ማመን የሚፈተንበት ጊዜ ይመጣል... ለምን ማለትም የሚያምርህ ጊዜ ... የሰው ልጅ ባህሪ ሆኖ ለስሜት ህዋሶች ቅርብ ለሆኑ ነገሮች መታመን አይከብደውም ምክንያቱም የአእምሮ እንዲህ ቢሆን እንዲ ይሆናል የሚል ስሌት ነገሮችን ለማቅለል ስለሚረዳ... አንዳንዴ ግን የትኛውም ስሌትህ መልስ የለውም:: አቅምህ እጅ መስጠት ብቻ ይሆናል በደህና ጊዜህ አምነዋለው ያልከውን አላህ እምነትህን ምታፀናበት ጊዜ ይሆናል:: ማፅናቱ ግን ቀላል አይደለም እጅግ የሚያሙ ሁነቶችን ከማለፍ ጋር ነው የማትፈልጋቸውን እውነቶች መስማትና መጋፈጥም ሊሆን ይችላል:: .. በዚህ ሰዐት ከእኔ በላይ ስለእኔ ታውቅልኛለህ ብለህ እጅ መስጠት, ስለሚሆነው ሁሉ እያየህ እምባህንም ጭንቀትህንም በመንገር ውስጥ የሚሆነውን ማየት ... ስታየው ከላዩ መጥፎ በሚመስለውም ጥሩ በሆነውም... በጠየቅክበት መልኩ ባይመጣም ባላሰብከው መልኩ ቢገለፅም… ዝም ብሎ ማመን… እዚህ ሰዐት ላይ የሚኖርህ በአላህ ላይ መተማመን ትክክለኛው መታመን ነው ሰውኛ ነገርህን ሁሉ ትተህ ለሱ ምትሰጥበት... መሰጠትህን የምር ካደረከው በምትፈልገውም ባይሆን በሚሻልህ መልኩ ውጤቱን አሳይቶ ይክስና መስካሪ ያደርግሃል ... መስካሪ ለመሆን ግን ትላንት ላይ ምታልፋቸው ህመሞች እና በእርሱ ላይ የሚኖርህ ትዕግስት ወሳኝነት አለው!

መልካም ቀን!

📍 @yourstressfreezone
ይግቡ ቤተሰብ እንሁን ያማረ ነገን እንፍጠር::

ለሀሳብ አስተያየቶ @stressfreezonebot መጠቀም ይችላሉ::

🍥🍥🍥🍥🍥🍥🍥🍥🍥🍥🍥🍥
Forwarded from የኛ ለምን⁉️
🪷🪷🪷🪷🪷🪷🪷🪷🪷🪷🪷🪷

ለራስ መታመን ትልቁ የህይወት ዳገት ይመስለኛል... በተለይም ራስህን ለመፈተሽ ከራስህ ጋር ቁጭ ስትል በሚከፈቱ ያንተ የማይመስሉህ ምዕራፎች እና መልስ አልባ ጥያቄ አዘል ገፃች ጋር መፋጠጥ እጅጉን ከባድ ነው:: ላለመፋጠጥም ስትል ብዙ ርቀቶችን ልትጏዝ ትችላለህ:: ... ጀግንነትህን ማረጋገጥ ከፈለክ ግን ከማትፈልጋቸው ማንነቶች ጋር ራስህን አጋፍጥ, ከራስህ ጋር እውነቱን አውራ, መቀየር ያለበትን ቀይር, መቀጠል ያለበትን አስቀጥል ይሄኔ ከራስህ አልፎ ወደ ሰዎች የሚጋባን ሰላም ይዘህ መኖር ትችላለህ :: ቢያንስ የራስህን የአኩኩሉ ጨዋታ ንጋት ታበስራለህ ከፍ ሲል የተደበቁትን ሰዎች ራሳቸውን እንዲያገኙ በር ትከፍታለህ!

መልካም ጁምዐ!

📍 @yourstressfreezone
ይግቡ ቤተሰብ እንሁን ያማረ ነገን እንፍጠር::

ለሀሳብ አስተያየቶ @stressfreezonebot መጠቀም ይችላሉ::

🪷🪷🪷🪷🪷🪷🪷🪷🪷🪷🪷🪷
Forwarded from የኛ ለምን⁉️
🕐🕑🕒🕓🕔🕕🕖🕗🕘🕙🕚🕛

መኖር ማለት ዛሬን ማጣጣም መቻል ይመስለኛል... ብዙ ጊዜ መኖርን ስናስብ የተሻሉ ብለን የምናስባቸው ነገሮችን መሳካት ብሎም ማግኘትን መሰረት እናደርጋለን:: የምናስባቸው ነገሮች የሚመጡት ግን በምንኖራቸው ዛሬ እና ነገዎች ጥርቅም መሆኑን እንዘነጋለን:: ዛሬ ማጣጣም ያልቻልነው የህይወት መንገድ ማግኘት ያልነው ላይ ስንደርስ ጣዕም አልባ መሆኑ አይቀርም… እናም የዛሬ ምኞታችን ጥርቅም ውጤት የሆነን ነገ ላይ ከመድረሳችን በፊት የዛሬዋን እያንዳንዷን ሁነት ለመኖር እንሞክር በዚህ መልኩ ስንደርስበት ከትላንት እስከዛሬ የሆነ የኑሮ ሂደት ይኖረናል::...ዕድሜያችንስ የሚቆጠረው ከትላንት እስከ ዛሬ ባለው አይደለምን?

መልካም ጁምዐ!

📍 @yourstressfreezone
ይግቡ ቤተሰብ እንሁን ያማረ ነገን እንፍጠር::

ለሀሳብ አስተያየቶ @stressfreezonebot መጠቀም ይችላሉ::

🕐🕑🕒🕓🕔🕕🕖🕗🕘🕙🕚🕛
Forwarded from የኛ ለምን⁉️
🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆

ለብዙዎቻችን መኖር እና አለመኖር ልዩነቱ ከመቃብር በላይ እና ታች መዋል ነው:: ያልተረዳነው እውነት ግን እየኖርን የመሰለን መኖር ያቆምን ብዙዎች መኖራችን ነው:: መብላት መጠጣት ሲመሽ ደሞ መተኛት ብቻውን መኖር አይባልም ምናልባትም ማኗኗር እንጂ... አንተ እንደ አንተ ለተፈጠርክለት አላማ የማትለፋ ከሆነ መኖርህ ምን ላይ ነው? ምድር አንተን በመያዟ ከሸክም ውጭ የምታተርፈውስ ምንድነው?... ሁሌም ራሳችንን መጠየቅ እና መልሱን መረዳት ያለብን ጥያቄ ነው ... ያለምክንያት አልመጣንም :: የመጣንበት አላማ ፈልጎ አግኝቶ ለተፈጠርንበት ነገር መኖር መጀመር ደግሞ የእኛ ሀላፊነት ነው::

ፍክት ያለ ጁምዐ ተመኘሁ!

📍 @yourstressfreezone
ይግቡ ቤተሰብ እንሁን ያማረ ነገን እንፍጠር::

ለሀሳብ አስተያየቶ @stressfreezonebot መጠቀም ይችላሉ::

🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆
Forwarded from 🎁 Yamy wraps 🎁
Orders for remedan are getting accepted… hurry to order yours … some exciting things are also on the way 😊

A combination of
- ተስቢህ
- ቁርዐን
- መስገጃ

👉🏽 @yamywraps1
🎁A place where u buy emotions 🎁
Forwarded from HIRFA DECORATIONS
💫🌙💫⭐️

ረመዳን መምጣቱን ለማብሰር ከምንጠቀማቸው ነገሮች መሃል የቤታችንን ይዘት ለመቀየር መሞከር ነው:: ረመዳንን የሚያስናፍቁ እና ቤታችንን የሚያስውቡ እቃዎችን በማቅረብ የሚታወቀው ድርጅታችን  Hirfa decoration ዘንድሮም ለእናንተ ይመጥናሉ ያላቸውን የተለያዩ የዲኮር አይነቶች አዘጋጅቶ ለእናንተ ለማድረስ ዝግጅቱን ጨርሷል ... ከርሶ የሚጠበቀው በሚከተሉት አድራሻዎች ጎራ ብለው መሸመት ብቻ... ብዛት መረከብ የምትፈልጉ ደንበኞች ካላችሁ በስልካችን ሃሎ ይበሉ::

ለበለጠ መረጃ፦

💫በስልክ ቁጥር
    📞 0908888585
https://hottg.com/hirfa_Deco

🌷Hirfa decoration💫🌾
Forwarded from 🎁 Yamy wraps 🎁
የእናት ዱዐ ያማረው ... ለአክስትም የሚሆን...አያትም ካሉ ይቻላል.... ዱዐ ፈላጊ በውስጥ ብቅ ይበል

@yami49 or 0913201486

👉🏽 @yamywraps1
🎁 A place where u buy emotions 🎁
Forwarded from 🎁 Yamy wraps 🎁
አባት በደስታ የሚያደርገው ዱዐ ብዛት ያውም የረመዳን ዱዐ ... ገዝተህ ሀጃህ ይውጣ የሚልን ዱዐ መስማት አትፈልግም ... እና ምን ትጠብቃለህ?... ማዘዝ ብቻ

@yami49 or 0913201486

👉🏽 @yamywraps1
🎁 A place where u buy emotions 🎁
HTML Embed Code:
2024/06/03 08:09:58
Back to Top