TG Telegram Group Link
Channel: Hiba_Jemea
Back to Bottom
ውድ የሂባ ቤተሰቦች

ወደ ጅማ መስመር ግቤ ድልድይ አልፎ ሳጃ ከተማ አካባቢ ለሚገኝ መስጂድ የቁርዓን እርዳታ ከተደረገላቸው መሳጂዶች አንዱ እንደሆነ ይታወቃል:-

ቁርሀኖቹንም በምናበረክትበት ግዜ ለመስጂዱ እንደ ቁርዓን ድጋፍ ሊደረጉለት የሚገቡ በርካታ ነገሮች እንዳሉ በጠየቁን መሰረት ሂባ ጀምዓም የአቅሙን ድጋፍ ለማድረግ በማሰብ 100,000ብር የሚጠጋ ድጋፍ ከስር እንደተቀመጠው ዝርዝር በአላህ ፍቃድ አበርክተናል:-

3000ሊትር ውሃ ታንከር (ሮቶ)
100ካሬ ምንጣፍ እና ሸራ
የውጪ እስፒከር እና የውስጥ ማይክራፎን
ናቸው አልሃምዱሊላህ።
እቃዎቹንም መስጂዱን በማሰራት እዚህ ደረጃ ላደረሱት እናት ሶፍያ አበርክተንላቸዋል።

በቀጣይም በአላህ እርዳታ እና በሁላችንም ትብብር በሂባ ጀምዓ ስም አንድ መስጂድ እንደምንሰራ እንተማመናለን ኢንሽ አላህ።
Forwarded from Minber TV
ሶሻል ሚዲያን ለበጎ አላማ በመጠቀም ከፍተኛ ብር በቻሌንጅ በማሰባሰብ ለተቸገሩ ወገኖች በመርዳት ላይ ከሚገኙት "ሂባ ጀመዓ" ጋር ልዩ ቆይታ አድርገናል።
#መወዳ መዝናኛ
የፊታችን እሑድ ከቀኑ 8:00 ጀምሮ በመወዳ መዝናኛ ይጠብቁን

🌙🌙🌙🌙
★★★★★
በናይል ሳት ለመከታተል:–
ፍሪኩዌንሲ 12521
27500
ቨርቲካል
★★★★★

YouTube👉 https://www.youtube.com/channel/UCQQWZ1IeswjheSTSEXKcQsA

Facebook👉
https://www.facebook.com/minbertv/

Telegram👉
https://hottg.com/minbertv

#ሚንበር_ቲቪ
#ሁለንተናዊ_ከፍታ
የአላህ ሰላም እና ራህመት በናንተ ላይ ይሁን

ሂባ ጀምዓ
በትንሽ ሰደቃ የሰዎችን ደስታ እንመልስ
እጅ ለሌላቸው እጅ እንሁን
አይን ለሌላቸው አይን እንሁን
ፍቅር ላጡት ፍቅር እንስጥ
ትንሽ ብንሆንም ትልቅ ልብ አለን

በአላህ እርዳታ እና በእኛ ትብብር ካሰብንበት እንደርሳለን
አማራ ክልል ሰሜን ወሎ ላሊበላ ወረዳ ግራኝ አምባ ከተማ (መቄት)መስጂድ ራህማ 250 ካሬ ምንጣፍ አበርክተናል

"የተቋም ውጤቱ ስራው መታየቱ ሲሆን የግለሰብ ውጤቱ ስራው መደበቁ ነው"
የግለሰብ ተሳትፎ አደብዝዘን የተቋማችንን ስራ አጉለተን ለሌሎች አርአያ እንሆን ዘንዳ እና ለምንሰራቸው ኸይር አድራጎቶች ስራችን በማስተዋወቅ ወደኸይር ስራ ምንጣራበት አንዱ የዳዕዋ መንገድ ነው አላህ ኸይር ስራችንን ይቀበለን !!!
ውድ የሂባ ጀምዓ አባላት እና ቤተሰቦች

ክረምቱን በአልባሳት:-

ለአቅመ ደካሞች እና ምስኪን የተቸገሩ ወገኖቻችንን በገንዘብ እና በአስቤዛ እንደ ጀምዓችን አቅም በአላህ ፍቃድ ስናግዝና ስንንቀሳቀስ የነበረ መሆኑ ይታወሳል:-

አሁን ባለንበት የክረምት ወቅት ቅዝቃዜው እጅግ ከፍተኛ እና ብርዱም ከባድ መሆኑንን በመገንዘብ ለአቅመ ደካሞች እና ምስኪን የተቸገሩ ወገኖቻችንን ካለን አልባሳት ላይ በማካፈል አንድም ለህሊናችን አንድም ለወገናችን ምንደርስበት ትልቅ የእርዳታ መድረክ አዘጋጅተናል እና በቀጣይ ሁለት ሳምንት ውስጥ ሰብስበን ስለምናስረክብ ሁላችንም በዚ ኸይር ስራ ላይ እንሳተፍበት ስንል በአላህ ስም እንጠይቃለን።

በዚህም ሁላችንም ለወዳጅ ዘመድ በማስታወስ እና አልባሳትና ጫማዎችን ሐላፊነት ወስደን በማሰባሰብ ከስር በምናስቀምጣቸው አድራሻዎች እንድታደርሱልን እንጠይቃለን።

*ቦሌ አካባቢ- ቦሌ ዴንታል የጥርስ ህክምና ሚሊኒየም አዳራሽ ፊት ለፊት ከናታኒ ካፌ አጠገብ
ስልክ 0911943141

*ገርጂ Alfoz Plaza ቃተኛ አጠገብ
Elegance Flower and Gift Shop
ስልክ ቁጥር 0911225268

*ቤተል ተቅዋ መስጂድ በሴቶች በር በኩል አል ቡካሪ ቡቲክ:-ስልክ ቁጥር 0911252997/0920730753

"መርካቶ ሚሊተሪ ተራ 0911487390 /0966798540

*ሳርቤት ማሞካቻ ፊትለፊት JFK አፓርትመንት ውስጥ Elegance Flower and Gift Shop
ስልክ ቁጥር 0911225268
Forwarded from حمودي
አሰላም ወአለይኩም ውድ የሂባ ጀምዓ ቤተሰቦች:-

እንደሚታወቀው ሂባ ጀምዓ በተለያዩ በጎ አድራጎቶች በመከወን ከእንናንተ ቤተሰቦቹ ጋር 2 ዓመታትን ለሚጠጋ ግዜ መዝለቅ ችሏል። አልሀምዱሊላህ

በዚህ ረመዳንም ከናንተ ከቤተሰቦቹ ጋር በመሆን የተለያዩ በጎ አድራጎቶች ላይ መሳተፍ ይፈልጋል ከነዛም ውስጥ የመስጂድ ግንባታ አንዱ ነው።

ይህንንን ለማሳካት በሂባ ጀምዐ አባላት እና ወዳጅ ቤተሰቦች በግል 560ሺ ብር አካባቢ አሰባስበን ወደ አፋር ክልል በማምራት ከአፋር ክልል መጅሊስ ሰመራ ከተማ ላይ መስጂድ መስራት የምንችልበት 2300ካሬ ስፋት ያለው ቦታ ተበረከተልን።

በአቅራብያው የሚኖሩ ሰዎች በሳጠራ እና ቆርቆሮ ሰርተው መስጂዱን እየሰገዱበት ይገኛልይ:: ቢላል መስጂድ

እኛም 300ካሬ ላይ ያረፈ መስጂድ ለማስገንባት እጃችን ላይ ባለው ገንዘብ ግንባታው ተጀምራል ።

እንደ ከዚህ ቀደሙ ተግዳሮቶቻችን በጋራ የአላህን ቤት እንገነባዋለን። ኢንሻአላህ

ከፊታችን ሀሙስ ጀምሮም የላይቭ ቻሌንጅ ፕሮግራም በመስጂዱና በሌሎች ኸይር ስራዎች ላይ የLive ፕሮግራም ይኖረናልና ሁላችንም በምንችለው አቅም እንሳተፍ ኢንሻአላህ
Forwarded from حمودي
Forwarded from حمودي
Forwarded from حمودي
Forwarded from حمودي
በሂባ ጀምዓ እየተገነባ ላለው መስጂድ Final stage ማሰሪያ መዋጮ #challenge

1 ሰው በዙሩያው ካሉ 10 ሰዎች,instagram ላይ ካሉት ጏደኞች አልያም ከቤተሰብና ወዳጆች በነብስ ወከፍ 1000ሺ ብር በመሰብሰብ በድምሩ 10,000 ብር ሰብስቦ በሂባ ጀምዓ አካውንት ማስገባት ይሆናል::
በአላህ ፍቃድ 100 ሰዎች ይሳተፉበት ዘንድ ያዘጋጀነው #challenge ነው:: 100 አህለል ኸይሮች በ10000ሺ ብር ከ ተሳተፉ 1 ሚሊዮን ብር የመስጂዱን Finishing Work ምንሰራበት ገንዘብ ማግኘት እንችላለን::
በአላህ እገዛና በሁላችንም ተሳትፎ እንደጀመርነው በቅርቡ እንጨርሰዋለን ኢንሽ አላህ🤲🤲🤲
HTML Embed Code:
2024/06/08 06:16:09
Back to Top