TG Telegram Group Link
Channel: ቅዱሳን ኅሩያን የዲ°ን ዮርዳኖስ ትምህርቶች
Back to Bottom
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
#ግንቦት_23_ቀን_በቅዳሴ_ሰዓት_የሚነበቡት_መልእክታት👇
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
ሮሜ 16
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
⁷ በሐዋርያት መካከል ስመ ጥሩዎች ለሆኑ፥ ደግሞም ክርስቶስን በማመን ለቀደሙኝ፥ አብረውኝም ለታሰሩ ለዘመዶቼ ለአንዲራኒቆንና ለዩልያን ሰላምታ አቅርቡልኝ።
⁸ በጌታ ለምወደው ለጵልያጦን ሰላምታ አቅርቡልኝ።
⁹ በክርስቶስ አብሮን ለሚሠራ ለኢሩባኖን ለምወደውም ለስንጣክን ሰላምታ አቅርቡልኝ።
¹⁰ በክርስቶስ መሆኑ ተፈትኖ ለተመሰገነው ለኤጤሌን ሰላምታ አቅርቡልኝ። ከአርስጣባሉ ቤተ ሰዎች ላሉት ሰላምታ አቅርቡልኝ።
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
ይሁዳ 1
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
²⁰ እናንተ ግን፥ ወዳጆች ሆይ፥ ከሁሉ ይልቅ በተቀደሰ ሃይማኖታችሁ ራሳችሁን ለማነጽ እየተጋችሁ በመንፈስ ቅዱስም እየጸለያችሁ፥
²¹ ወደ ዘላለም ሕይወት የሚወስደውን የጌታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን ምሕረት ስትጠባበቁ በእግዚአብሔር ፍቅር ራሳችሁን ጠብቁ።
²² አንዳንዶች ተከራካሪዎችንም ውቀሱ፥ አንዳንዶችንም ከእሳት ነጥቃችሁ አድኑ፥
²³ አንዳንዶችንም በሥጋ የረከሰውን ልብስ እንኳ እየጠላችሁ በፍርሃት ማሩ።
²⁴ ሳትሰናከሉም እንዲጠብቃችሁ፥ በክብሩም ፊት በደስታ ነውር የሌላችሁ አድርጎ እንዲያቆማችሁ ለሚችለው
²⁵ ብቻውን ለሆነ አምላክና መድኃኒታችን ከዘመን ሁሉ በፊት አሁንም እስከ ዘላለምም ድረስ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ክብርና ግርማ ኃይልም ሥልጣንም ይሁን፤ አሜን።
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
ሐዋርያት 21
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹⁵ ከዚህም ቀን በኋላ ተዘጋጅተን ወደ ኢየሩሳሌም ወጣን።
¹⁶ በቂሣርያም ከነበሩ ደቀ መዛሙርት አንዳንዶች ደግሞ ከእኛ ጋር መጡ፥ እነርሱም ወደምናድርበት ወደ ቀደመው ደቀ መዝሙር ወደ ቆጵሮሱ ምናሶን ወደሚሉት ቤት መሩን።
¹⁷ ወደ ኢየሩሳሌም በደረስን ጊዜ ወንድሞች በደስታ ተቀበሉን።
¹⁸ በነገውም ጳውሎስ ከእኛ ጋር ወደ ያዕቆብ ዘንድ ገባ ሽማግሌዎችም ሁሉ መጡ።
¹⁹ ሰላምታም ካቀረበላቸው በኋላ በእርሱ ማገልገል እግዚአብሔር በአሕዛብ መካከል ያደረገውን በእያንዳንዱ ተረከላቸው።
²⁰ እነርሱም በሰሙ ጊዜ እግዚአብሔርን አመሰገኑ አሉትም፦ ወንድም ሆይ፥ በአይሁድ መካከል አምነው የነበሩት ስንት አእላፋት እንደ ሆኑ ታያለህ፤ ሁላቸውም ለሕግ የሚቀኑ ናቸው።
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️

#ግንቦት_23_ቀን_የዕለቱ_የቅዳሴ_ምስባክ👇
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
"ወትቀውም ንግሥት በየማንከ። በአልባሰ ወርቅ ዑጽፍት ወኊብርት። ስምዒ ወለትየ ወርእዪ ወአጽምዒ ዕዝነኪ"። መዝ44፥9-10።
የንጉሦች ሴት ልጆች ለክብርህ ናቸው፤ በወርቅ ልብስ ተጐናጽፋና ተሸፋፍና ንግሥቲቱ በቀኝህ ትቆማለች። ልጄ ሆይ፥ ስሚ እዪ ጆሮሽንም አዘንብዪ፤ ወገንሽን ያባትሽንም ቤት እርሺ፤ መዝ44፥9-10።
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️

#ግንቦት_23_ቀን_የእለቱን_ወንጌል_እናንብብ📖👇
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
ሉቃስ 10
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹⁷ ሰብዓውም በደስታ ተመልሰው፦ ጌታ ሆይ፥ አጋንንት ስንኳ በስምህ ተገዝተውልናል አሉት።
¹⁸ እንዲህም አላቸው፦ ሰይጣንን እንደ መብረቅ ከሰማይ ሲወድቅ አየሁ።
¹⁹ እነሆ፥ እባቡንና ጊንጡን ትረግጡ ዘንድ፥ በጠላትም ኃይል ሁሉ ላይ ሥልጣን ሰጥቻችኋለሁ፥ የሚጐዳችሁም ምንም የለም።
²⁰ ነገር ግን መናፍስት ስለ ተገዙላችሁ በዚህ ደስ አይበላችሁ፥ ስማችሁ ግን በሰማያት ስለ ተጻፈ ደስ ይበላችሁ።
²¹ በዚያን ሰዓት ኢየሱስ በመንፈስ ቅዱስ ሐሤት አደረገና፦ የሰማይና የምድር ጌታ አባት ሆይ፥ ይህን ከጥበበኞችና ከአስተዋዮች ሰውረህ ለሕፃናት ስለ ገለጥህላቸው አመሰግናለሁ፤ አዎን አባት ሆይ፥ ፈቃድህ በፊትህ እንዲህ ሆኖአልና።
²² ሁሉ ከአባቴ ዘንድ ተሰጥቶኛል፥ ወልድንም ማን እንደ ሆነ ከአብ በቀር የሚያውቅ የለም፥ አብንም ማን እንደ ሆነ ከወልድ በቀር ወልድም ሊገልጥለት ከሚፈቅድ በቀር የሚያውቅ የለም አለ።
²³ ወደ ደቀ መዛሙርቱም ዘወር ብሎ ለብቻቸው፦ የምታዩትን የሚያዩ ዓይኖች ብፁዓን ናቸው።
²⁴ እላችኋለሁና፥ እናንተ የምታዩትን ብዙዎች ነቢያትና ነገሥታት ሊያዩ ወደዱ አላዩምም፥ የምትሰሙትንም ሊሰሙ ወድደው አልሰሙም አለ።
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️#ሚቀደሰው_ቅዳሴ የእመቤታችን የማርያም ቅዳሴ ነው። መልካም የሐዋርያው የቅዱስ ዮልዮስና የእመቤታች የደብረ ምጥማቅ በዓል ሰሞን። ለሁላችንም ይሁንልን።
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
Audio
🕊መንግሥተ ሰማያት ቀርባለችና ንስኅ ግቡ🕊 (ማቴ ፫:፫)

ርዕስ፦📝 "" ትወደኛለህን ? ""  (ዮሐ. ፳፩:፲፭)

"ትምህርት በወቅታዊ ጉዳይ ላይ"

"በዓለ ደብረ ምጥማቅ"

📅ግንቦት 21 - 2016

🎤 በመምህር ዲ/ዮርዳኖስ አበበ

ዝክረ ቅዱሳን ማኅበረ ቅዱስ ዳዊት

🌿ፍቅር ያጌብረኒ ከመ እንግር ዜናሆሙ ለቅዱሳን! (የቅዱሳንን ዜና እንድመሰክር ፍቅር ያስገድደኛል)

🌿አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ (መጽሐፈ ምሥጢር)

🔗https://hottg.com/zikirekdusn
▶️
https://www.youtube.com/@ZikereKedusan
††† እንኩዋን ለእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ዓመታዊ የስደት
በዓል በሰላም አደረሳችሁ †††

=>የአርያም ንግሥት: የፍጥረታት ሁሉ እመቤት ድንግል ማርያም የባሕርይ
አምላክ ልጇን አዝላ በዚህች ቀን ወደ ምድረ ግብፅ ወርዳለች::

+በወንጌል ላይ (ማቴ. 2:1-18) እንደተጻፈው ጌታችን በተወለደ በ2 ዓመቱ
የጥበብ ሰዎች (ሰብአ ሰገል) ወደ ቤተ ልሔም መጥተው ሰግደውለት: ወርቅ
እጣን ከርቤውን ገበሩ: አገቡለት::

+ንጉሥ ተወልዷል መባሉን የሰማ ሔሮድስ 144,000 ሕጻናትን ሲፈጅ በቅዱስ
ገብርኤል ትዕዛዝ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም 1 አምላክ ልጇን
አዝላ: በአንዲት አህያ ጥቂት ስንቅ ቁዋጥራ: ከዮሴፍና ከሰሎሜ ጋር ስደት
ወጣች::

+ከገሊላ ተነስታ በጭንቅ በመከራ: በረሃብና በጥም: በሐዘንና በድካም:
በላበትና በእንባ ተጉዛ በዚሕች ቀን ምድረ ግብፅ ገብታለች::

+የአምላክ እናቱ
*እሳትን አዝላ በብርድ ተንገላታለች::
*ለእኛ የሕይወት እንጀራን ተሸክማ እርሷ ተራበች::
*የሕይወትን ውሃ ተሸክማ ተጠማች::
*የሕይወት ልብስን ተሸክማ ተራቆተች::
*የሕይወት ፍስሐን ተሸክማ አዘነች::
*እመ አምላክ ተራበች: ተጠማች: ታረዘች: ደከመች: አዘነች: አለቀሰች:
እግሯ ደማ: ተንገላታች::

+ለሚገባው ይሕ ሁሉ የተደረገው ለእኛ ድኅነት ነው:: በእውነት ይህንን
እያወቀ ለድንግል ማርያም ክብር የማይሰጥ ሰይጣን ብቻ ነው:: አራዊት:
ዕፀዋትና ድንጋዮች እንኩዋ ለአመላክ እናት ክብር ይሰጣሉ::

+አረጋዊው ቅዱስ ዮሴፍና ቅዱስ ሰሎሜ ደግሞ የክብር ክብር ይገባቸዋል::
ከአምላክ እናት ከድንግል ማርያምና ከቸር ልጇ ጋር መከራ መቀበልን
መርጠዋልና::

=>መድኃኔ ዓለም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለምን ተሰደደ?
ለምንስ ስደቱን ወደ ግብፅና ኢትዮዽያ አደረገ?

1.ትንቢቱን ይፈጽም ዘንድ:: በፈጣን ደመና ወደ ግብፅ እንደሚወርድ
ተነግሯልና (ኢሳ. 19:1, ዕን. 3:7)

2.ምሳሌውን ለመፈጸም:: የሥጋ አባቶቹ እነ አብርሃም: ያዕቆብ (እሥራኤል):
ኤርምያስ ወደዚያው ተሰደዋልና::

3.ከግብፅ ጣዖት አምልኮን ያጠፋ ዘንድ:: (ኢሳ. 19:1)

4.የግብፅና የኢትዮዽያ ገዳማትን ይቀድስ ዘንድ::

5.ሰው መሆኑ በአማን እንጂ ምትሐት እንዳልሆነ ለማጠየቅ:: ሰው ባይሆን
ኑሮ አይሰደድም ነበርና:: ሔሮድስ ቢያገኘው ደግሞ ሊገድለው አይችልም::
ያለ ፈቃዱና ያለ ዕለተ ዐርብ ደሙ አይፈስምና::

6.ስደትን ለሰማዕታት ባርኮ ለመስጠት:: እና

7.የአዳምን ስደት በስደቱ ለመካስ ነው::

=>ቸሩ መድኃኔ ዓለም የድንግል እናቱን ስደት አስቦ ከመንግስተ ሰማያት ስደት
ይሠውረን:: ከስደቱ በረከትም ያድለን::

=>ግንቦት 24 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.ቅዱስ ዕንባቆም ነቢይ
2.ቅዱስ ዮሴፍ አረጋዊና ቅድስት ሰሎሜ
3.ቅዱስ አብቁልታ ሰማዕት
4.ቅዱስ አልዓዛር ካህን (የአሮን ልጅ)

=>ወርኀዊ በዓላት
1.ቅዱስ አቡነ ተክለ ሃይማኖት
2.ቅዱስ አጋቢጦስ (ጻድቅ ኤዺስቆዾስ)
3.ቅድስት ክርስቶስ ሠምራ
4.ቅዱስ ሙሴ ፀሊም
5.ቅዱስ ቶማስ ዘመርዐስ
6.ቅዱስ አብላርዮስ ታላቁ
7."24ቱ" ካኅናተ ሰማይ (ሱራፌል)
8.አቡነ ዘዮሐንስ ጻድቅ (ኢትዮዽያዊ)

=>+"+ ዘንዶውም ሴቲቱ በወለደች ጊዜ ሕጻኑዋን እንዲበላ ልትወልድ ባላት
ሴት ፊት ቆመ:: አሕዛብንም ሁሉ በብረት ዘንግ ይገዛቸው ዘንድ ያለውን ልጅ:
ወንድ ልጅ ወለደች:: ልጇም ወደ እግዚአብሔርና ወደ ዙፋኑ ተነጠቀ::
ሴቲቱም ሺህ ከሁለት መቶ ስድሳ ቀን በዚያ እንዲመግቧት በእግዚአብሔር
ተዘጋጅቶላት ወደ ነበረው ሥፍራ ወደ በረሃ ሸሸች:: +"+ (ራዕይ. 12:4-7)

https://hottg.com/zikirekdusn
#ግንቦት_28

አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም
ግንቦት ሃያ ስምንት በዚህችም ዕለት ተጋዳይ የሆነች ዓለምን ንቃ የተወች #ቅድስት_አመተ_ክርስቶስ አረፈች፣ ከአባ ጳኵሚስ ገዳም #አባ_መርቆሬዎስ አረፈ፣ #የቅዱስ_ኤጲፋንዮስ ሥጋ ወደ ቆጵሮስ ደረሰ፣ ዳግመኛ በዚህች ቀን አባ #ጌርሎስና_አርባ_አምስቱ_ልጆቹ በሰማዕትነት አረፉ፣ ደግሞም የከበሩ አባቶች የ #አብርሃም#ይስሐቅና#የያዕቆብ መታሰቢያቸው ነው፣ ደግሞም በዚህች ዕለት የአባ #ስንጣ የሰማዕት #አጋቦስ መታሰቢያቸው ነው በረከታቸው ይደርብን።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#ቅድስት_አመተ_ክርስቶስ

ግንቦት ሃያ ስምንት በዚህችም ዕለት ተጋዳይ የሆነች ዓለምን ንቃ የተወች አባ ዳንኤል ስለርሷ እንደተናገረ የዓለምን ፍላጎት ሁሉ ድል የነሣች ቅድስት አመተ ክርስቶስ አረፈች። ሀገሯ ልዩ ስሙ ተጉለት ሲሆን በተጋድሎዋ በእጅጉ ትታወቃለች፡፡ መጽሐፍ ተሐራሚት ገዳማዊት ይላታል፡፡ በበረሃ ውስጥ በተሰነጠቀ ዓለት ውስጥ 38 ዓመት ብቻዋን ማንም ሳያያት የኖረች ታላቅ እናት ናት፡፡ አባ ዳንኤል ስለርሷ እንዲህ አለ በበረሀም ሳለሁ በሌሊት ተነሥቼ በጨረቃ ብርሃን ተጓዝኹ በተራራ ላይ የተቀመጠ ሰውንም አየሁ ጠጉሩም ሁለመናውን ሸፍኖታል በልቤም ወደርሱ ሔጄ ይህ ምን እንደሆነ ልወቅ ብዬ ወደርሱ ሔድሁ።

በአየችኝም ጊዜ ወደ ተሠነጠቀ አለት ውስጥ ገባች ሰው እንደሆነ አውቄ የእግዚአብሔር ሰው ሆይ ወደ እኔ ትመጣ ዘንድ በረከትህን እንድቀበል እማልድሃለሁ አልሁ እጅግም አብዝቼ ለመንሁ። ከዚህም በኋላ አባት ሆይ አልወጣምና ይቅርታ አድርግልኝ አለችኝ። ስለምን አልኋት እኔ ሴት ነኝ ራቁቴን ስለሆንኩ አለችኝ። ይህንን ሰምቼ የለበስኩትን ዐጽፍ ጣልሁላት ለብሳም ወጣች በአንድነትም ጸለይን።

ከዚህ በኋላ እናቴ ሆይ ከዓለም ወደዚህ ስለመውጣትሽ ይኸንን የተሠነጠቀ ዐለት እንዴት እንዳገኘሽ ንገሪኝ አልኋት። እርሷም እንዲህ ብላ መለሰችልኝ በወላጆቼ ቤት ድንግል ሁኜ በኢየሩሳሌም የምኖር ነኝ ሁል ጊዜ የሚጎበኘኝና ከእኔ ጋራ የሚነጋገር አንድ መነኰስ ነበረ።

ከጥቂት ቀኖችም በኋላ ወደርሱ ሔድኹ በእግዚአብሔር ፊትም ኃጢአቱን እየታመነ ሲአለቅስ አገኘሁት። ደጁንም በአንኳኳሁ ጊዜ አልከፈተልኝም እየተጸጸተ ልቅሶን አበዛ እንጂ። በዚያን ጊዜ በልቤ እንዲህ እልኩ እኔስ ስለ ጕስቊልናዬና ስለ ኃፍረቴ የማላለቀስና የማልጸጸት ለምንድነው ወደ ማደሪያዬም ፈጥኜ ሔድኹ ማቅ ለበስኩ በዘንቢልም ሽምብራ በጽዋ ውኃን ያዝሁ። በክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መቃብር ዘንድ እንዲህ ብዬ ጸለይኩ አቤቱ ጽኑዕ ኃያል ለዘላለሙ ድንቅ የሆንክ የጠፉትን የምታድን የወደቁትንም የምታነሣቸው ወደ አንተ የሚጮኹትንም የምትሰማቸው የታመነችብህ ባሪያህን ታድናት ዘንድ ይቅርታህንና ምሕረትህን ላክ። ከምግባር ድኃ የሆንኩ ባሪያህን ጐብኘኝ ንስሓዬንም ተቀበል። ለረጅም ዘመን ስንቅ ይሆነኝ ዘንድ ይህን ሽምብራና ይህን የጽዋ ውኃ ባርከው ስለ ነፍሴ ድኅነት የአሰብኩትን እንዳላቃልል ለሆዴ ምግብ ስለሚአሻኝ።

ከዚህ በኋላም ነፍሴን በእግዚአብሔር ላይ በመጣል ወጥቼ ወደ በረሀ ሔድኹ እስከ ኤርትራ ባሕርም ደረስኩ። ከዚያም ወደዚህ በረሀ መጥቼ ይህን የተሠነጠቀ ዐለት አገኘሁ ይህ እግዚአብሔር ያዘጋጀልኝ መኖሪያዬ ነው አልሁ።

እነሆ በዚህ በረሀ ውስጥ ሠላሳ ስምንት ዓመት ሆነኝ ያለ አንተ ሰው አላየሁም። ይህም የዘንቢል ሽምብራና የጽዋ ውኃ ሠላሳ ስምንት ዓመት ከእሳቸው ስመገብ አልጐደሉም ልብሴ ግን አለቀ ነገር ግን ይህ ቦታ ስለ ልብስ መከለያ ሆነኝ። የበጋ ፀሐይ ትኩሳትም አላስቸገረኝም ቁር ቢሆንም በዕድሜዬ ዘመን ሁሉ አላስጨነቀኝም።

ከዚህ በኋላም ከዘንቢል ካለው ሽምብራ እንድመገብ ማለደችኝ ከሽምብራውም በላሁ ከውኃውም ጠጣሁ። ግን አልጎደለም እግዚአብሔርንም አመሰገንሁት ልብሴንም ልተውላት ወደድሁ እርሷም ከዚህ የተሻለ አምጣልኝ ብላ ይህን እምቢ አለችኝ።

ከዚህ በኋላም ከእርሷ ዘንድ ሔድኩ ወደ ገዳም ደርሼ ስለርሷ ለአበ ምኔቱ ነገርኩት። እርሱም ሁለት ልብስ ያለው ለሌለው አንዱን ይስጥ ብሎ ጮኸ ፈቃደኞች የሆኑም አመጡለት ያን ጊዜም ይዤ ሔድኩ ለአመተ ክርስቶስ ልስጣት ብዙ ደከምኩ እርሷን በመፈለግ ዞርኩ አላገኘኋትም።

ከጥቂት ቀኖች በኋላም አረጋውያን ወደ እኔ መጡ እንዲህም አሉኝ ወደ ኤርትራ ባሕር የሚያደርሰውን መንገድ ይዘን በጣኔዎስ በረሀ ስንጓዝ ከዋሻ ዘንድ ሴት ተቀምጣ አይተን ከእርሷ በረከት ለመቀበል ሮጥን ሸሽታ ከዋሻው ገባች ወደ ዋሻውም አፍ ቀረብን ግን አላየናትም። ሽምብራ በዘንቢል ውኃም በጽዋ አግኝተን በላን ጠጣን ያን ጊዜም አለቀ እስከ ንጋትም አደርን።

በነጋም ጊዜ በረከቷን ለመቀበል ቅድስቲቱን ፈለግናት ሙታም አገኘናት ጠጉሯም ሥጋዋን ሁሉ ሸፍኖአል። በዚያም ሰገድን በበዓቷም ውስጥ ቀበርናት የዋሻውንም አፍ በደንጊያ ዘጋን የቅድስቲቱን በረከት እንድንቀበል አድሎናልና እግዚአብሔርን እያመሰገን ወደ በዓታችን ገባን።

በሰማሁም ጊዜ አስቀድሜ ያገኘኋት እንደሆነች አወቅሁ የነገረችኝንም ሁሉ ነገርኳቸው። ጠላት ዲያብሎስን ድል ያደርገው ዘንድ ክፉዎች አጋንንትንም ደካማውን ድኃ የሚረዳ የተመሰገነ እግዚአብሔርን ፈጽመን አመሰገን ነው።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#አባ_መርቆሬዎስ_ገዳማዊ

በዚችም ዕለት ከአባ ጳኵሚስ ገዳም አባ መርቆሬዎስ አረፈ። እንጦንዮስም እንዲህ አለ ለእኔ ገዳም አለኝ ይኸውም የወንድማችን የመርቆሬዎስ ዕረፍቱ ቀረበ እያሉ ወደእኔ መነኰሳት የመጡበት ነው እኔም በረከቱን ለመቀበል ወደርሱ በሔድኩ ጊዜ ነፍሱ ከሥጋው ሳትለይ በተመሥጦ ላይ አገኘሁት።

ከመነኰሳቱ ጋራ በእርሱ ዘንድ ሦስት ሌሊቶች ኖርን በሦስተኛዪቱም ዕለት ነፍሱ ተመልሳ ዐይኖቹን ገለጠ በአየንም ጊዜ ከእኔ ዘንድ ምን ሰበሰባችሁ አለን። እኛም የሆነውን ሁሉ ነገርነውና ከዚህም በኋላ ያየውን እንዲነግረን ለመንነው እርሱም የሚአስፈራ ሰው ወደርሱ መጥቶ ነፍሱን እንደወሰደ የኃጥአንን ሥቃይ እንዳሳየው የጻድቃንንም ዋጋቸውንና ተድላቸውን እንዳሳየው ነገረን።

ከዚህ በኋላ ወዮ ብሎ በማልቀስ በግምባሩ ከምድር ላይ ተደፋ እንዲህም አለን ወንድሞቼ ሆይ ወደ ሐራጺት ገዳም ወደ አባ ጊዮርጊስ ማደሪያ ሒዱ። ከእኔ ጋራ የነበረውን መልአክ መርቆሬዎስን መልሳችሁ በትንሽ በዓት ውስጥ ሲጋደል የኖረ ጊዮርጊስን አምጡት ሲል ሰምቼዋለሁና ይቺም ሥጋው እስቲቋጠር የተጋደለባት የጨው በረሀ ናት።

ወንድሞች መነኰሳትም በሔዱ ጊዜ ሙቶ አገኙት ወደዚህ ገዳምም አምጥተው ቀበሩት። ይህም ወንድም መርቆሬዎስ እንደ ደረቀ እንጨት እስቲሆን ሥጋውን እጅግ አሠቃየ።

ከዚህም በኋላ ወደ ገዳም ይሔድ ዘንድ ተሰናበተኝ። ደግሞ ግንቦት ሃያ ስምንት ቀን ወደኔ ና ታገኘኛለህና አለኝ። በቀጠረኝም ቀን ወደርሱ ሔጄ አገኘሁትና እኔ ወደ አባቶቼ እሔዳለሁ። ወደ አንተም ሦስት አጋዘኖች ይመጣሉ ሥጋዬንም በጀርባቸው ላይ ጫን እነርሱም ወደ ቦታዬ በእግዚአብሔር ፈቃድ ይመሩሃል።

በዚያም በማደሪያዬ ውስጥ ድፈኑኝ አለኝ። እንደ ቃሉም ሆነለት ከመቃብሩም ቁጥር የሌላቸው ድንቆች ተአምራት ተገለጡ።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#ቅዱስ_ኤጲፋንዮስ

በዚህችም ዕለት የቅዱስ ኤጲፋንዮስ ሥጋ ወደ ቆጵሮስ ደረሰ። ይህም እንዲህ ነው ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ወደ መንበረ ሢመቱ እንደማይደርስ ትንቢት እንደተናገረበት ወደ ቆጵሮስ ሳይደርስ በመርከብ ውስጥ ሳለ ግንቦት ዐሥራ ስድስት ቀን አረፈ።
በአረፈም ጊዜም በመርከብ ጭነው ወደ ቆጵሮስ ከተማ አደረሱት። ካህናቱና ሕዝቡ ሁሉ መጡ ከሳቸውም ጋር ወንጌሎች መስቀሎች መብራቶችና ማዕጠንቶችም ይዘው ነበር የሐዋርያት ጉባኤ ከታላቂቱ ቤተ ክርስቲያን እስኪያደርሱት በዝማሬና በማኅሌት በሚገቡት ጸሎቶች ሁሉ እያመሰገኑ ሥጋውን ተሸከሙ። ካህናቱም መቃብሩን በቤተ ክርስቲያኑ ውስጥ ሊያዘጋጁ ወደዱ። ቀድሞ ስለ ክፉ ሥራቸው ቅዱስ ኤጲፋንዮስ አውግዞአቸው የነበሩ ሁለት ዲያቆናት ተቃወሟቸው።

ስለዚህም አርባ ቀን ተቀመጠ ነገር ግን ሽታው እንደ ሙታኖች ሽታ አልተለወጠም እንደ አንቀላፋ ሰው ሆነ እንጂ። ከዚህም በኋላ አንድ ደግ ዲያቆን ወደ ቅዱሱ ሥጋ ቀርቦ አባቴ ሆይ በእግዚአብሔር ዘንድ አንተ ባለሟልነት እንዳለህ እኔ አውቃለሁ። ብትፈቅድስ ክፉዎች ተቃዋሚዎችን ልታሸንፋቸው ትችላለህ አለ። የቅዱስ ኤጲፉንዮስንም እጅ ይዞ ምድሩን መታባት በዚያንም ጊዜ ሁለቱ ዲያቆናት በግምባራቸው ተደፉ። ለመሞትም ደረሱ ወደ ቤታቸውም ወስደዋቸው ሞቱ።

ቅዱስ ኤጲፋንዮስንም ካህናቱ በሚጣፍጡ ሽቱዎች ገነዙት። በከበሩ ልብሶችም ጠቅልለው ከከበረ ደንጊያ በተሠራ ሣጥን ውስጥ ጨምረው በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ቀበሩት። ቀድሞ በሕይወቱ ሳለ እንደሚሠራው ከሥጋው ድንቆች ተአምራት ተገለጡ።

ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳኑ ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን።

(#ስንክሳር_ዘወርኀ_ግንቦት_28)
✞✞✞ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ አሐዱ አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡ ✞✞✞

❖ እንኳን አደረሳችሁ ❖

❖ ግንቦት 29 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት

+"+ አባ አፍፄ ወአባ ጉባ +"+

=>አባ አፍፄና አባ ጉባ ቁጥራቸው ከተስዓቱ (ዘጠኙ)
ቅዱሳን ነው::

+"+ አባ አፍፄ +"+

=>ጻድቁ የተወለዱት እስያ ውስጥ በ5ኛው መቶ ክ/ዘመን
ሲሆን ወላጆቻቸው አቡሊዲስና አቅሌስያ ይባላሉ:: ገና
በሕጻንነታቸው
ብሉይ ከሐዲስ ጠንቅቀው ወደ ግብፅ ወርደዋል:: በዚያም
በአባ መቃርስ እጅ መንኩሰዋል:: አባ አፍፄ ወደ ኢትዮዽያ
የመጡት
በአልዐሜዳ ዘመን ከ8ቱ ባልንጀሮቻቸው ጋር ነው::

+ጻድቁ ጸበል እያፈለቁ ብዙ ድውያንን ፈውሰዋል::
ትግራይ ውስጥ የሐ የተባለው ቦታም ማረፊያቸው ነበር::

❖ለጻድቁ በጥቂቱ እነዚሕን እንጠቅሳለን:-

1.ከ100 ዓመት በላይ አበ ምኔት ሆነው በኖሩበት
ገዳማቸው በፍጹም ትጋት: በጾምና በጸሎት
አገልግለዋል::

2.በመጀመሪያ ያስከተሏቸውን 366 ደቀ መዛሙርት
ጨምሮ ብዙ መናንያንን አፍርተው በሃገራችን ገዳማዊ
ሕይወትን አስፋፍተዋል::

3.ቅዱሳት መጻሕፍትን ከሱርስትና ከጽርዕ ቋንቋ ወደ
ግዕዝ ተርጉመዋል::

4.በስብከተ ወንጌል ለሃገራችን ብርሃን አብርተዋል::
ሕዝቡ በጣዕመ ስብከታቸው ይገረም ስለ ነበር "አፍፄ
(አፈ-ዐፄ)"
ብሏቸዋል:: "የዐፄ (የንጉሥ) አንደበት ያለው" ወይም
"ንግግር አዋቂ" ማለት ነው::

+ጻድቁ ከ200 ዓመታት በላይ ቤተ ክርስቲያንን
አገልግለው በዚሕች ቀን በ684 ዓ/ም ተሠውረዋል::
እግዚአብሔርም
በስማቸው ለተማጸነ: ገዳማቸውን ለተሳለመ የምሕረት
ቃል ኪዳን ሰጥቷቸዋል::

+"+ አባ ጉባ +"+

=>ጻድቁ የተወለዱት ታሕሳስ 29 ቀን በ336 ዓ/ም
በመንፈቀ ሌሊት ነው:: አባታቸው ጌርሎስ: እናታቸው
ቴዎዶክስያ ደጐች
ነበሩ::

+አባ ጉባ ("ባ" ጠብቆ ይነበብ) በተወለዱ ቀን ጌታችን
ከመላእክቱ ጋር በመውረዱ ቤታቸው ለ7 ቀናት በብርሃን
ተሞልቶ
ነበር:: ሕጻኑ ጉባም ፈጣሪያቸውን ሃሌ ሉያ ብለው
አመስግነዋል::

+በልጅነታቸው መጻሕፍትን አጥንተው: ወደ ገዳመ
አስቄጥስ ገብተው መንነዋል:: ለበርካታ ዓመታት ከተጋደሉ
በኋላ ሊቀ
መላእክት ቅዱስ ገብርኤል "ወደ ቅድስት ሃገር ኢትዮዽያ
ሒድ" ብሏቸው ከ8ቱ ቅዱሳን ጋር ወደ ሃገራችን
መጥተዋል::
በወቅቱ ዕድሜአቸው ከ140 በላይ ነበር::

+ጻድቁ አባ ጉባ እንደመሰሎቻቸው በስብከተ ወንጌል:
መጻሕፍትን በመተርጐም: ገዳማትን በማስፋፋትና አብያተ
ክርስቲያናትን
በማነጽ ቆይተዋል:: በተለይ ራማ ኪዳነ ምሕረት
የእርሳቸው ናት ይባላል::

+ጻድቁ ቅዳሴ ሲቀድሱ ከመሬት ከፍ ብለው ነበር:: ብዙ
ጸበሎችን አፍልቀው ድውያንን ፈውሰዋል:: ሙታንንም
አንስተዋል::
እመቤታችንም የብርሃን መስቀል ሰጥታቸዋለች:: ጻድቁ
ከበርካታ የቅድስና ዘመናት በኋላ በዚህች ቀን ዐርፈው
በገዳማቸው
ተቀብረዋል::

+በዘመኑ ትኩረት ካጡ ታላላቅ ገዳማት አንዱ ይሔው
ትግራይ ውስጥ የሚገኘው የአባ ጉባ ገዳም ነው::
(በነገራችን ላይ "ጉባ" ማለት "አፈ-መዐር: ጥዑመ-
ልሳን" ማለት ነው)

❖ቸሩ መድኃኔ ዓለም ክርስቶስ የጻድቃኑን በረከት
ያድለን::
በጸሎታቸውም በደላችንን ይቅር ይበለን::

❖ግንቦት 29 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.አባ አፍፄ (ከዘጠኙ ቅዱሳን)
2.አባ ጉባ (ከዘጠኙ ቅዱሳን)
3.አባ ስምዖን ገዳማዊ (በ7 ዓመታቸው መንነው ለ81
ዓመታት በተጋድሎ የኖሩ ሶርያዊ)
4.አባ ይስሐቅ ጻድቅ

❖ወርኃዊ በዓላት
1፡ በዓለ ልደቱ ለክርስቶስ
2፡ ቅድስት አርሴማ ድንግል
3፡ ቅዱስ ጴጥሮስ ተፍጻሜተ ሰማዕት
4፡ ቅዱስ ማርቆስ ዘሮሜ
5፡ ቅድስት ፍቅርተ ክርስቶስ
6፡ ቅዱስ ዘርዐ ክርስቶስ
7፡ ቅዱስ ቀሌምንጦስ ሐዋርያ
8፡ ጉባኤ ሰማዕታት

++"+ ነቢይን በነቢይ ስም የሚቀበል የነቢይን ዋጋ
ይወስዳል:: ጻድቅን በጻድቅ ስም የሚቀበል የጻድቁን ዋጋ
ይወስዳል::
ማንም ከእነዚህ ከታናናሾቹ ለአንዱ ቀዝቃዛ ውሃ ብቻ
በደቀ መዝሙር ስም የሚያጠጣ እውነት እላቹሃለሁ
ዋጋው አይጠፋበትም::
+"+ (ማቴ. 10:41)

<<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>

https://hottg.com/zikirekdusn
Audio
🕊መንግሥተ ሰማያት ቀርባለችና ንስኅ ግቡ🕊 (ማቴ ፫:፫)

ርዕስ፦📝""መንገዱን እንዴት እናውቃለን?""  
   (ዮሐ. ፲፬:፭)

"ተግሣጽ ለኲሉ፥ ወቅዱስ ቶማስ ሐዋርያ"

📅(ግንቦት 26 - 2016)

🎤 በመምህር ዲ/ዮርዳኖስ አበበ

ዝክረ ቅዱሳን ማኅበረ ቅዱስ ዳዊት

🌿ፍቅር ያጌብረኒ ከመ እንግር ዜናሆሙ ለቅዱሳን! (የቅዱሳንን ዜና እንድመሰክር ፍቅር ያስገድደኛል)

🌿አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ (መጽሐፈ ምሥጢር)

🔗https://hottg.com/zikirekdusn
▶️
https://www.youtube.com/@ZikereKedusan
HTML Embed Code:
2024/06/16 19:39:07
Back to Top