TG Telegram Group Link
Channel: ✝ሃይማኖተ አበው✝
Back to Bottom
በወንጌል ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ጌቴሴማኒ ወደሚባል ቦታ ሄዶ በጸለየበት ጊዜ ጴጥሮስንና ሁለቱን የዘብዴዎስን ልጆች እንዲህ አላቸው፤ ‹‹ነፍሴ እስከ ሞት ድረስ እጅግ አዘነች፤ በዚህ ተቀመጡ፤ ከእኔ ጋርም ትጉ፤›› ከዚያም ጥቂት ፈቀቅ አለና በግንባሩ ሰግዶ ጸለየ፤ እንዲህም አለ፤ ‹‹አባቴ ሆይ፥ የሚቻልስ ከሆነ ይህች ጽዋ ከእኔ ትለፍ፤ ነገር ግን ፈቃድህ ይሁን እንጂ የእኔ ፈቃድ አይደለም፡፡›› ወደ ደቀ መዛሙርቱ በሄደ ጊዜ ግን ተኝተው አገኛቸው፤ ጴጥሮስንም እንዲህ አለው ‹‹አንድ ሰዓት እንኳ ከእኔ ጋር መትጋት እንዲህ ተሳናችሁን? ወደ ፈተናም እንዳትገቡ ተግታችሁ ጸልዩ፤ መንፈስ ይሻልና፤ ሥጋ ግን ደካማ ነው፡፡›› ጌታችን ይህን ቃል ለሐዋርያቱ የተናገራቸው እርሱ ከእነርሱ ጋር በማይኖርበት ጊዜም ብቻ ሳይሆን ሁልጊዜም ወደ ፈተና እንዳይገቡ በትጋት መጸለይ እንደሚያስፈልግ ለማሳወቅ ነው፡፡ (ማቴ.፳፮፥፴፮-፵፩)

በክርስትና ሕይወት ውስጥ ጸሎት ተቀዳሚ ተግባር ነው፤ ወደ እግዚአብሔር አምላካችን የምንቀርብበት፣ ከእርሱ ጋር የምንንነጋገርበት እና የምንፈልገውን ነገር ለማግኘት የምንማጸንበት ክርስቲያናዊ ምግባር ነው፤ እናም ዘወትር ልንጸልይ ይገባል፡፡

ይህች ምድር በችግር፣ መከራና ፈተና የተሞላች በመሆኗ በአሁኑ ጊዜ ሃይማኖታችንና እምነታችን እየተፈተነ ነው፤ ዓለማችን ወስጥ ስቃይ፣ በሽታና ጦርነት በመብዛቱ ይህን አስቸጋሪ ጊዜ ለማለፍ ተግተን ልንጸልይ ይገባል፡፡ ሰዎች በሕይወታቸው ውስጥ ችግርና መከራ ሲያጋጥማቸው የዕለት ጉርሻቸውን ለመሙላትም ማድረግ የሌለባቸውን ነገር ማድረግ ወይንም የእግዚአብሔርን ሕግ መተላለፍ ይጀምራሉ፤ በሐሰት እና በአቋራጭ መንገድም ምድራዊ ሕይወታቸውን ይኖራሉ፡፡ ሆኖም ዘወተር እግዚአብሔርን በመፍራት ስንኖርና አምላካችን ከእኛ ጋር ሲኖር ከክፋት እንዲሁም ከፈተና ይሰውረናል፡፡ ይህንም ማድረግ የምንችለው ሥርዓቱን ጠብቀን ስንጸልይ ነው፡፡

በተዋሕዶ እምነታችን እኛ ክርስቲያኖችም በ፳፬ ሰዓት ውስጥ ፯ ጊዜ መጸለይ እንዳለብን እንረዳለን፡፡ ይህም እግዚአብሔር አምላክ ሁሉን በምክንያት ያደረገው በመሆኑ ሁል ጊዜ ወደ እርሱ እንጸልይና እንቀርብ ዘንድ ነው፡፡

የሰባቱ የጸሎት ጊዜያትም ጸሎተ ነግህ (፲፪)፣ ጸሎተ ሠለስት (፫ ሰዓት)፣ ቀትር (፮ ሰዓት)፣ ተሰዓቱ ሰዓት (፱ ሰዓት)፣ ጸሎተ ሰርክ (፲፩ ሰዓት)፣ ጸሎተ ንዋም (የመኝታ ጊዜ ጸሎት) እና መንፈቀ ሌሊት (እኩለ ሌሊት) ናቸው፡፡ (መዝ. ፻፲፰፥፻፷፬)

ጸሎተ ነግህ

ቅዱስ ዳዊት ‹‹አምላኬ አምላኬ በማለዳ ወደ አንተ እገሰግሳለሁ›› እንዳለ ሌሊቱ አልፎ ቀኑ ሲተካ፣ ከመኝታችን ተነስተን የምንጸልየው ጸሎተ ነግህ ነው፡፡ አምላካችን እንደቸርነቱ ሌሊቱን በሰለምም አሳድሮ ለብርሃነ ቀኑ ስላደረሰን በማመስገን፣ ወጥተን እስክንገባ ከክፋት ጠብቆ ወደ ቤታችን በሰላም እንዲመልሰን እና ከፈተና እንዲሰውረን እንጸልያለን።

ነግህ አዳም የተፈጠረበትም ሰዓት በመሆኑም ያንን እያሰብንም እና የሰውን ልጅ በመዓልትና በሌሊት የሚጠብቁን መላእክት የሚገናኙበት ሰዓት በመሆኑ እንጸልያለን፡፡ ሌሊቱን ሲጠብቀን ያደረው መልአክ የቀኑን ሲተካ ስንተገብረው የነበረውን ለቀኑ ያስረክባል፤ እንደዚህ እየተቀባበሉ ይጠብቁናል፡፡ ስለእኛ ምግባር ያውቁ ዘንደ ነውና፡፡

ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስለ ሰው ልጆች በደል በጲላጦስ አደባባይ የቆመበት ሰዓት በመሆኑ በነግህ እንጸልያለን።

ጸሎተ ሠለስት

እናታችን ሔዋን የተፈጠረችበት፣ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የቅዱስ ገብርኤልን ብሥራት የሰማችበት፣ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስለ ሰው ልጆች ሲል በጲላጦስ አደባባይ የተገረፈበት፣ ነቢዩ ዳንኤል ፊቱን ወደ ኢየሩሳሌም አቅጣጫ መልሶ የቤቱን መስኮት ከፍቶ የጸለየበት፣ ለአባቶቻችን ሐዋርያት መንፈስ ቅዱስ የወረደበት /በኢየሩሳሌም ጸንተው በመቆየታቸው ከእግዚአብሔር ዘንድ ይህንን ታላቅ ጸጋ የተቀበሉበት /ሰዓት በመሆኑ በሦስት ሰዓት እንጸልያለን፡፡

ቀትር

ቀትር ሰይጣን አዳምን ያሳተበት እና በዕፀ በለስ ምክንያት ለስሕተት የተዳረገውን አዳምን ለማዳን ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በቀራንዮ አደባባይ መከራና ስቃይ የተቀበለበት ጊዜ ነው፡፡ በዚህም ሰዓት የፀሐይ ሙቀት የሚያይልበት፣ የሰው ልጅ ለድካም የሚዳረግበት ስለሆነ አጋንንት ይበረታሉ። ስለዚህ የአዳምን ስሕተት፣ የኢየሱስ ክርስቶስ መሰቀልና መሞት፣ እያሰብን፣ በዚያም ሰዓት ሥጋዊ ድካማችንን ሰበብ አድርጎ አጋንንት እንዳይሰለጥንብን እየለመንን እንጸልያለን፡፡ ጴጥሮስም በቀተር ጊዜ ሊጸልይ ወደ ሰገነት ወጣ እንዲል፡፡ (ሐዋ. ፲፥ ፱)

ተሰዓቱ ሰዓት

የተሰዓቱ ጸሎት ዘጠኝ ሰዓት ላይ የምናደርሰው ጸሎት ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አዳምን ነጻ ለማውጣት በፈቃዱ ቅዱስ ሥጋውን ከቅድስት ነፍሱ የለየበት ሰዓት በመሆኑ ነው።
ቅዱሳን መላእክት የሰው ልጆችን በጎም ሆነ ክፉ ተግባር ወደ ፈጣሪ የሚያሳርጉበት፣
ቆርኖሌዎስ የተባለ መቶ አለቃ በጸሎት ጸንቶ ደጅ ሲጠና ከሰነበተ በኋላ ከፈጣሪው ምላሽ ያገኘበት ስለሆነም ዘጠኝ ሰዓት ላይ እንጸልያለን፡፡ በዚህ ጊዜ የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስን መከራ እና ሞት አያሰብን ቅዱሳት መላእክት ከፈጣሪያቸው እንዲያስታርቁን እየለመንን የቆርኖሌዎስ እድል እንዲገጥመን እየተማጸንን እንጸልያለን፡፡

ጸሎተ ሰርክ

‹‹ጸሎቴን በፊትህ እንደ ዕጣን ተቀበልልኝ፥ እጆቼ የሠርክ መሥዋዕትን አነሡ›› ብሎ ቅዱስ ዳዊት እንደተናገረው በዚህ የጸሎት ሰዓት በቤተ ክርስቲያን ሁላችንም ተሰባስበን ጸሎታችን እናደርሳለን፤ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ዓለምን ለማዳን በፈቃዱ ነፍሱን ከሥጋው ከለየ በኋላ ወደ መቃብር የወረደበት ሰዓት ነውና፡፡ (መዝ. ፻፵፥፪፣ ማቴ. ፳፯፥፶፯)

ጸሎተ ንዋም

ቀኑን እንደ ፍቃዱ ያዋለንን እግዚአብሔር አምላክን እያመሰገንን፤ ሌሊቱንም በሰላም ያሳድረን ዘንድ እንማጸናዋለን፡፡ እርሱ የማይተኛ አምላክ ነውና ሌሊቱን ሁሉ ከክፋት ጠብቆ ያሳድረናል ነው፡፡

በዚህ ጊዜም ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ደቀ መዛሙርቱን ጸሎት አስተምሯቸዋል፡፡ ስለዚህ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስለጸሎት ማስተማሩን እያሰብን እንጸልያለን፡፡

መንፈቀ ሌሊት

መንፈቀ ሌሊት ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በቤተልሔም ዋሻ የተወለደበት፣ ሞትን ድል አድርጎ በታላቅ ኃይልም የተነሳበት እንዲሁም ጌታችን ዳግመኛ ለፍርድ የሚመጣበትም ሰዓት ነው። ቅዱሰ ዳዊት ‹‹መንፈቀ ሌሊት እትነሣእ ከመ እግነይ ለከ በእንተ ኵነኔ ጽድቅከ፤ ስለ ጽድቅህ ፍርድ በእኩለ ሌሊት አመሰግነህ ዘንድ እነሳለሁ›› በማለት ይህ ሰዓት ከእግዚአብሔር ጋራ የሚነጋገርበት እንደሆነ እንደገለጸው ያንን በማሰብ ለፍርድ ሲመጣ በቀኙ ከሚያቆማቸው ወገን እንዲያደርገን እየለመንን በዚህ ሰዓት እንጸልያለን፡፡ (መዝ.፻፲፰-፷፪)

ነገር ግን እነዚህን ሰባቱ የጸሎት ሰዓታት የሚጸልዩባቸው በገዳም ያሉ መነኮሳት በየበረሃው የሚዞሩ ባሕታውያን ብቻ መሆን የለባቸውም፤ ምንም እንኳን በሥራ ምክንያት ሁሉንም ሰዓታት ጠብቀን መጸለይ ባይቻለን ቢያንስ በነግህ እና በመኝታ ሰዓት መጸለይ አለብን። ይህም በሕይወታችን ውስጥ የሚያጋጥመንን ችግር መከራ እንድንቋቋም ይረዳናል፤ አምላካችን እግዚአብሔርም ከፈተና ያወጣናል፡፡

እግዚአብሔር አምላክ ከፈተና ይሰውረን ዘንድ ተግተን እንጸልይ
ሕገ ወጡ ቡድን ወደ ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ቦንጋ ለመግባት ቢሞክርም በሕዝበ ክርስቲያኑ እና በጸጥታ ኃይሎች ቅንጅት ዕቅዱ መክሸፉ ተገለጸ።

በከፋ ሀገረ ስብከት ሥር የሚገኙት 12 ወረዳ ቤተ ክህነቶች የቅዱስ ሲኖዶስን ውሳኔ በመደገፍ ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ እንቅስቃሴ ላይ ሳሉ ቅዱስ ሲኖዶስ ጥያቄያችን ካልተመለሰ የካቲት 5 ቀን ዓለም አቀፍ ሰላማዊ ሰልፍ ይደረጋል ብሎ መናገሩን ተከትሎ ለዛሬ የታሰበው ሰልፍ እንዲቀር ነገር ግን ሁሉም በተጠንቀቅ እንዲጠብቅ ተነጋግረው ቆይተዋል።

ነገር ግን ዛሬ ከቀኑ 9:00 ሰዓት አካባቢ ሕገ ወጡ ቡድን እየመጣ ነው መባሉን ተከትሎ በቦንጋ ከተማ በአሥሩ አድባራት የሚገኙ ካህናትና ምእመናን በነቂስ ወጥተው የኦሮሚያ እና ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል አዋሳኝ ወደ ሆነችው ጎጀብ ወደ ተባለችው ኬላ ደርሰው ከክልሉ የጸጥታ ኃይሎች ጋር በመሆን ኬላውን ዘግተው በመጠበቅ ላይ ሳሉ ሕገ ወጡ ቡድን ይደርሳል።

ሕገ ወጡ ቡድን በኦሮሚያ ፖሊስ ታጅቦ የመጣ ቢሆንም ግር ግር በመፍጠር ለመግባት ቢሞክሩም የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የፖሊስ፣ ልዩ ኃይልና የሚሊሻ አባላት ከምእመኑ ጋር ሆነው በመከላከላቸው ወደ ጅማ መመለሳቸውን የደረሰን መረጃ ያመለክታል።

ወደ ቦንጋ የሚያስገቡ መንገዶች ሁሉ ተዘግተው የመኪና እንቅስቃሴ ቆሟል። ሕዝበ ክርስቲያኑም በከፋ በሚገኙት በአሥሩም አድባራት ሆኖ ቤተ ክርስቲያንን በመጠበቅ ላይ ይገኛል። ተሚማ
ብርሃናተ አለም ጴጥሮስ ወጳውሎስ።
ከብዙ በጥቂቱ ከግዕዝ እና አማርኛ ቋንቋ ወደ ኦሮምኛ ቋንቋ የተተረጎሙ መጻሕፍት
+++++++++++++++++++++++++++++++++
በኢትዮጵያ ኦርቶዶከስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንና በልጆቿ የተዘጋጀ ከግዕዝ እና አማርኛ ቋንቋ ወደ ኦሮምኛ ቋንቋ የተተረጎሙ መጻሕፍት በከፊል እንዘረዝራለን የተተረጎመልንን እናንብብ፡፡ ቤተክርስቲያንናችን በቋንቋ መገልገልን ከልክላ አታውቅም እያገለገለችም ትገኛለች ያለስሟ ስም ለየሚለጥፉ አላዋቂዎች ምስክር ይሆን ዘንድ እነሆ !

1. ውዳሴ ማርያም (Galata Maariyaam)
2. ዓምደ ሃይማኖት (Utubaa Amantaa)
3. የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን (Seenaa Mana Kiristaanaa Ortodooks Tawaahidoo Itiyoophiyaa)፣
4. ፍኖተ ቅዱሳን (Daandii Qulqullootaa)፣
5. ክርስቶስ ኢየሱስ ማን ነው? (Kiristoos Iyyesuus Eenyudha?)፣
6. ወላዲተ አምላክ በመጽሐፍ ቅዱስ (Deessuun Waaqaa Kitaaba Qulqulluun)፣
7. ነገረ ቅዱሳን (Dubbii Qulqullootaa)፣
8. ውዳሴ አምላክ (Galata Waaqaa)፣
9. ፍኖተ አሚን /ቁጥር-1 እና ቁጥር-2) (Daandii Amantii)፣
10. ነገረ ሃይማኖት (Dubbii Amantaa)፣
11. የቤተ ክርስቲያን ታሪክ በዓለም መድረክ (Seenaa Mana Kiristaanaa Sadarkaa Addunyaatti)፣
12. ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን (Sirna Mana Kiristaanaa)፣
13. መንፈሳዊ አገልግሎት፣ ስብከትና ሐዋርያዊነት (Tajaajila Afuuraa, Lallabaafi Duuka Bu’ummaa)፣
14. የመጽሐፍ ቅዱስ መዝገበ ቃላት (Galmee Jechoota Kitaaba Qulqulluu)፣
15. ቃል ኪዳን በነገረ ድኅነት (Waadaa Dubbii Fayyinaa Keessatti)፣
16. ጸሎትና የጸሎት ሥርዓት (Kadhannaafi Sirna Kadhannaa)፣
17. ክብረ ቅዱሳን (Kabaja Qulqullootaa)፣
18. ክብረ ታቦት (Kabaja Taabotaa)፣
19. መንፈሳዊ ሕይወት (Adeemsa Jireenya Hafuuraa)፣
20. የምስጋና ሕይወት (Jireenya Galata Qabu)፣
21. ሰይፈ ሥላሴ (Seefii Sillaasee)፣
22. የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት መግቢያ (Seenaafi Seensa Qu’annaa Kitaaba Qulqulluu)፣
23. ሃይማኖት ለልጆች (Amantaa Ijoolleef)፣
24. ድርሳነ ሚካኤል (Dirsaana Mikaa’elii)
25. መጽሐፈ ቅዳሴ (Kitaaba Qiddaasee)
26.) ዐምደ ሃይማኖት
27.) ነገረ ቅዱሳን ቁ_፩
28.) ተአምረ ማርያም
29.) ድርሳነ ሚካኤል
30) kitaaba sinkisaaraa
31) መጽሐፈ ቅዳሴ(ክታበ ቅዳሴ)
32) መጻሕፍትን ባለማወቅ ትስታላችሁ (yeeyyiiwwaan)
33) ቃለ አዋዲ (JECHA LABESI)
34.) ሕማማት (DHUKKUBBII)
35.) ግንጊልቻ
36.)ተግባራዊ ክርስትና
37.) የብርሃን እናት

በዋናነት ደግሞ መጽሐፍ ቅዱስን የሥልሳ ስድስቱን ትርጉም አገልግሎት እየሰጠ ሲሆን ሲሆን 80 አሐዱ እየተዘጋጀ ይገኛል፡፡
Channel photo removed
Channel photo updated
🔴አዲስ ዝማሬ በተስፋ ኢየሩሳሌም ሰ/ት/ቤት🔴 ምስጋና የሚገባህ @Wedase_melaekt
https://youtu.be/vhCAo114vlg

ምስጋና የሚገባህ
ምስጋና አምልኮ ስግደት የሚገባህ
ውዳሴ እልልታ ክብር የሚገባህ
የአምላኮች አምላክ እግዚአበሔር አንተ ነህ

ከዓለም አስቀድሞ በዙፋንህ ያለህ
እረቂቅ ግዙፉን ፈጥረህ ትገዛለህ
በመላእክት እና በሰው ልጅ ልሳን
ትመሰገናለህ የያዝከው ሁሉን

ተመስገን በሰማይ በምድር/2/
የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር
አዝ።።።።።።

ከደመናት በላይ ከአርያም ከፍ ያልክ
በመንገድህ ሁሉ የተመሰገንክ
ፍፁም አሸናፊ በምድር በሰማይ
ከአእምሮ የምትረቅ ኤልሻዳይ አዶናይ

ተመስገን በሰማይ በምድር/2/
የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር
አዝ።።።።።

ቁጥር የሌለብህ ለዘመንህ ርዝመት
ወሰንም የሌለው የግዛትሀ ስፋት
የተሰወርክ ነህ ከመላእክት ሕሊና
ዓለም ሳይፈጠር ያለህ በምስጋና

ተመስገን በሰማይ በምድር/2/
የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር
አዝ።።።

በችሮታህ ብዛት ሁሉን የመታኖር
ዓለምን የወደድህ በዘለዓለመ ፍቅር
በመዳፍህ ላይ ነው ፍጥረትህ በሙሉ
ተመስገን ተመስገን እግዚአብሔር ኃያሉ

ተመስገን በሰማይ በምድር/2/
የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር
አዝ።።።
🔴ጥዑም ዝማሬ | ሰብሕዎ ለአምላክነ | ቀሲስ መኮንን ፍስሐ🔴 @Wedase_melaekt #መዝሙር #ኦርቶዶክስ #ኢትዮጵያ #ውዳሴ_መላእክት

ሰብሕዎ ለአምላክነ ሃሌ ሉያ ለእግዚአብሔር
ሰብሕዎ ለአምላክነ ሃሌ ሉያ ለእግዚአብሔር
በሰማይ በምድር/3/

ሰማዩን ያለምሶሶ አጽንቷል በቃሉ
መሬትን በውሆች መሃል መስርቷል ጥበቡ
ይታያል ያበራል ጌታ ዛሬም በስራው
ምስጉን ነው ሰራዊት ሁሉ ያመሰገነው

ሰብሕዎ ለአምላክነ ሃሌ ሉያ ለእግዚአብሔር
ሰብሕዎ ለአምላክነ ሃሌ ሉያ ለእግዚአብሔር
በሰማይ በምድር/3/

ምሕረቱ ይቅርታው ብዙ ከወሰን የሰፋ
አባት ነው ብርቱ መጠጊያ የሰው ልጆች ተስፋ
መጋቢ ለፍጥረት ዓለም ታላቅ ባለጸጋ
ያብባል ይለመልማል እርሱን የተጠጋ

ሰብሕዎ ለአምላክነ ሃሌ ሉያ ለእግዚአብሔር
ሰብሕዎ ለአምላክነ ሃሌ ሉያ ለእግዚአብሔር
በሰማይ በምድር/3/

ተመስገን ተመስገን ይላል የተጎበኘ ሰው
ከጥፋት ከጉስቁልና ከሞት የመልሰው
ይቀባል ከታች አንስቶ ከእረኝነት ቦታ
ይቅርታው ጸጋው ብዙ ነው ምህረቱ የጌታ

ሰብሕዎ ለአምላክነ ሃሌ ሉያ ለእግዚአብሔር
ሰብሕዎ ለአምላክነ ሃሌ ሉያ ለእግዚአብሔር
በሰማይ በምድር/3/

መላእክት በላይ በሰማይ ይዘምሩለታል
ዳዊትም ከበገናውጋር ለቅኔተነስቷል
በምድርም እኛ ልጀቹ እንበል ንሴብሆ
ይገባል ለአምላከ እስራኤል ውዳሴ አንክሮ

ሰብሕዎ ለአምላክነ ሃሌ ሉያ ለእግዚአብሔር
ሰብሕዎ ለአምላክነ ሃሌ ሉያ ለእግዚአብሔር
በሰማይ በምድር/3/

https://youtu.be/KwK7-4MIUek
🔴እግዚአብሔር ተዋጊ ነው ስሙም | ገብረ ዮሐንስ ገብረ ፃድቅ🔴 @Wedase_melaekt #መዝሙር #ኦርቶዶክስ #ኢትዮጵያ
https://youtu.be/MtDu-WJwczg

እግዚአብሔር ተዋጊ ነው ስሙም እግዚአብሔር ነው
ጉልበቴም አንደበቴም እርሱ ነው

በክብር ከፍከፍ ብሏል
ኃያሉን ከባህር ጥሏል
ለህዝቡ መድኃኒት ሆኗነ
ከሳሹን ቀላይ ከደነ

ምስጉን ነው የተመሰገነ
ልጆችሁን ከሞት ያዳነ
ፈርኦን ከጥልቁ ሰጥሟል
በክንዱ ኃይልን አድርጓል

ታወጀ የምህረት ዘመን
ከድንግል አመላክ ሰው ሆነ
ሲገለጥ የአለም መድኃኒት
ተሻገርን ገባን ከገነት

መለኮተ ስጋን ተዋሀደ
ዲያቢሎስ ሲኦል ወረደ
ተዋጊው እግዚአብሔር ቀድሟል
የሞት ኃይለ በሞት ተሽሯል
🔥🎰 EXPLOSIVE START AT FORBOOM.COM! 🎰🔥

🎁 +300% on Your First Deposit! 🎁
💸 Promo Code: FORBOOMNEW 💸
📈 Don't miss your chance to TRIPLE your start! 📈

⚡️ Want quick cash and a thrill? This is YOUR chance to win big! ⚡️
🎯 Deposit $50 or more, enter the promo code, and GET +300% BONUS INSTANTLY! 🎯

💣 Jump on Forboom.com and start winning RIGHT NOW! 💣
💥 Promo code valid for a LIMITED TIME! 💥

🚀 Ready to blow up the jackpot? Click here 👉 Forboom.com and use the promo code FORBOOMNEW! 🚀

💰 Your first deposit is your first step to a big win! 💰
🎲 FORBOOM – Play and win big! 🎲
HTML Embed Code:
2025/06/27 07:07:36
Back to Top