TG Telegram Group Link
Channel: hawassa City sport club
Back to Bottom
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ5ኛ ሳምንት ጨዋታ ውጤቶች ፣ የደረጃ ሰንጠረዥ ፣ የከፍተኛ ጎል አግቢዎች እና ሊጉ ከኢንተርናሽናል ጨዋታዎች እና ከኢትዮጵያ ዋንጫ ጨዋታዎች በኋላ ህዳር 20 በስድስተኛ ሳምንት ጨዋታዎች ሲመለስ ያሉትን መርሀግብር ከላይ ይመልከቱ ☝️

© Soccer Ethiopia
የክለባችን ተጫዋች ለብሔራዊ ቡድን ጥሪ ተደርጎለታል።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ ገብረመድህን ኃይሌ በዓለም ዋንጫ ማጣርያ ብሔራዊ ቡድናችን ከሴራ ሊዮን እና ቡርኪና ፋሶ ጋር ለሚያደርጋቸው ጨዋታዎች ዝግጅት ለ30 ተጫዋቾች ጥሪ አስተላልፈዋል።

በዚህም መሰረት የክለባችን የተከላካይ ስፍራ ተጫዋች ማሊዮን ሰለሞን ጥሪ ተደርጎለታል።

@hawassakenemafc
@hawassakenemafc
የኢትዮጵያ ዋንጫ ሁለተኛው ዙር ድልድል ይፋ ሆኗል።

በዚህም መሰረት ሀዋሳ ከተማ ከ ቤንች ማጂ ቡና ጋር ተደልድሏል።


ውድድሩ ከህዳር 15-17 ባሉት ቀናት ወደፊት በሚገለፅበት ከተማ ይደረጋል።

ቀሪ ድልድሎችን በምስሉ ላይ ይመልከቱ።

@hawassakenemafc
@hawassakenemafc
የኢትዮጲያ ሴቶች ፕሪሜር ሊግ ዛሬ ይጀምራል

ሀዋሳ ከተማ ከ ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ

4:00 ሰዓት

ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም

@hawassakenemafc
@hawassakenemafc
hawassa City sport club
የኢትዮጲያ ሴቶች ፕሪሜር ሊግ ዛሬ ይጀምራል ሀዋሳ ከተማ ከ ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ 4:00 ሰዓት ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም @hawassakenemafc @hawassakenemafc
የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪምየር ሊግ የ1ኛ ሳምንት የመክፈቻ ጨዋታ ውጤት

ሀዋሳ ከተማ 2-1 ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ

48' ቱሪስት ለማ | 72' አሪያት ኦዶንግ
51' እሙሽ ዳንኤል

@hawassakenemafc
@hawassakenemafc
የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪምየር ሊግ የ2ተኛ ሳምንት ጨዋታ ውጤት

ሀዋሳ ከተማ 3-1 ቅዱስ ጊዮርጊስ

39'ፀሀይነሽ ጁላ | 90+2 ምስራቅ ዛቶ
55' እሙሽ ዳንኤል
76'ቱሪስት ለማ

@hawassakenemafc
@hawassakenemafc
ለሀዋሳ ከተማ እግር ኳስ ክለብ ደጋፊዎች በሙሉ

የሀዋሳ ከተማ ደጋፊዎች ማህበር ከተቋቋመ ረዘም ያሉ ዓመታትን ያስቆጠረ ሲሆን በርከት ያሉ ስራዎችንም ሲሰራ ቆይቷል። ያለፉትን ዓመታት በአቶ ባዩ ባልጉዳ ፕሬዝዳንትነት እንዲሁም በስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት ተዋቅሮ እጅግ አበረታች ስራዎችን ሲሰራ የነበረው ይህ ማህበር በቀጣይም ያሉትን ደካማ እና ጠንካራ ጎን ገምግሞ ካለፉት ዓመታት በተሻለ ደረጃ ላይ እንዲገኝ ለማድረግ ማህበሩ አዳዲስ ሀሳቦች እና ስራዎችን አቅዶ እየተንቀሳቀሰ ሲሆን ለእነኚህም ተግባራት የስራ አስፈፃሚ ምርጫ እና በተጓደሉ አባላት ላይ ተተኪዎችን ለመምረጥ በማሰብ በቅርቡ ማህበሩ ጠቅላላ ጉባኤን ለማድረግ የወሰነ ሲሆን በስብስባውም ላይ ለመገኘት የክለባችን ደጋፊ ሆናችሁ የማህበሩ አባል በመሆን ክፍያን ፈፅማችሁ መታወቂያ የያዛችሁ አባሎቻችን በቀጣይ የስብሰባውን ቀን እና ቦታ እስክናሳውቅ ድረስ እንድትጠብቁን በአክብሮት እንገልፃለን !

ማሳሰቢያ - ከማህበራችን አሰራርና ደንብ ውጪ በማህበራዊ ሚዲያ የሚለቀቁ የማህበሩን ስም ለማጉደፍ ታስቦ ተልዕኮ አዘል የሚመስሉ የውስን ግለሰቦችን አላስፈላጊ ተግባር የሚያሰራጩትን ማህበሩ እንዲሁም ሰፊው የሀዋሳ ህዝብ እና መላው የክለባችን ደጋፊ የማይታገስ መሆኑን እና ይህንንም ድርጊት ከበስተጀርባ ሆነው ገንዘባቸውን መከታ በማድረግ ለከፋፋይ ተግባር አጋር የሚሆኑትን እንደደረስንባቸው እና ህዝቡ እንደማይታገሳቸው ከወዲሁ ልናሳውቅ እንወዳለን

የሀዋሳ ከተማ እግር ኳስ ክለብ ደጋፊዎች ማህበር !

ዝርዝር መረጃ 👉 https://m.facebook.com/story.php?story_fbid=pfbid02hLZJad34Nhpj1YcS5rAjmkj2k4kSgjD41J1u8VhtEJRjDwM5zimMv27HaxuKyrRdl&id=100063473539789&mibextid=2JQ9oc
ሀዋሳ ከተማ እግር ኳስ ክለብን ይወዳሉ ?

ስመ ገናና ከክልል ክለቦችም ቀዳሚ የሆነውን በ1950ዎቹ ተጠንስሶ በ1970ዎቹ በክለብ ደረጃ የተቋቋመውን ሀዋሳ ከተማ እግር ኳስ ክለብን ከወደዱ አሁኑኑ የደጋፊ ማህበሩ አባል በመሆን መታወቂያዎትን ይያዙ አንጋፋውን ክለብም ይደግፉ !

"የሀዋሳ ከተማ እግር ኳስ ክለብ ደጋፊዎች ማህበር"
የክለባችን ደጋፊዎች መልካም ተግባርን ፈፅመዋል...ዝርዝር 👉 https://www.facebook.com/100063473539789/posts/pfbid02FKPFufGnkgcCc5ED8mAkDxwq1kWxFbHQ2HXsnjN5a514FDKu49Vbt9EdTejC2oHhl/?mibextid=Nif5oz
በሀዋሳ የሚገኙ ሜዳዎች ግንባታቸው ምልከታ ተደርጎበታል

በሀዋሳ ከተማ የሚገኙ የእግር ኳስ መጫወቻ ሜዳዎችን የከተማ አስተዳደሩ እያደረገ ያለውን ግንባታ እና የሳር ንጣፍ የምልከታ መርሀግብር በዛሬው ዕለት ተደርጓል። የሀዋሳ ከተማ ከንቲባ አቶ መኩሪያ መርሻዬን ጨምሮ ስፖርቱን የሚመሩ አካላት በተገኙበት ዛሬ ከሰዓት በነበረው ሂደት በቀጣይ በሁለተኛው ዙር የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግን እንደሚያስተናግድ የሚጠበቀውን የሀዋሳ ዩኒቨርስቲ ስታዲየም የተደረገውን የሳር ማንጠፍ ተግባር መጠናቀቁን አስቀድመው ከንቲባውን ጨምሮ ከፍተኛ አመራሮች ታዝበዋል።

ለቀጣዩ የፕሪምየር ሊግ ዝግጅት ታስቦ የተወሰነው የሜዳ ክፍል በጋዜጠኛ መኳንን በሪሄ ከሀንጋሪ ቡዳፔስት ባመጣው የእግር ኳስ መጫወቻ ሳር የለበሰ ሲሆን የከተማ አስተዳደሩ ከንቲባም እንዳሉት በቀጣዮቹ ቀናት የሀዋሳ ከተማ እግር ኳስ ክለብ የመጫወቻ ሜዳ የሆነው አርቴፊሻል ሜዳውን ሙሉ በሙሉ በማንሳት በጋዜጠኛ መኳንንት በርሄ አማካኝነት ዘመናዊ የመጫወቻ ሳር እንደሚለብስ ከንቲባው በጉብኝት ፕሮግራሙ ላይ ተናግረዋል። በመቀጠል በሀዋሳ ከተማ የሚገኙ የተለያዩ ሜዳዎች በመዟዟር ምልከታ የተደረገ ሲሆን የማሻሻያ ስራ የሚጠይቀ ሜዳዎች በቀጣይ ስራዎቻቸው ተፈፃሚ እንደሚሆን እና በተለምዶ ጨፌ ተብሎ የሚገኘው ሜዳን ለክለቡም ሆነ ለሌሎች ከተማዋ ላይ ለሚመጡ ክለቦች ምቹ ይሆን ዘንድ የግንባታ ሂደቱ መከናወን ጀምሯል።
በወንዶችም በሴቶችም የኢትዮጲያ ፕሪሜር ሊግ ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪነትን እየመሩ የሚገኙት የክለባችን ሀዋሳ ከተማ ተጫዋቾች ናቸው።

አሊ ሱሌይማን በ11 ጎሎች
እሙሽ ዳንኤል በ12 ጎሎች

👏🔥

የማትጠቀሙበት ጉሩፕ ካላችሁ ለመሸጥ @ermias_ks አዋሩኝ
ተጠናቀቀ #ኢትዮጲያ ፕሪሜር ሊግ

ሀምበርቾ 0⃣ - 1⃣ ሀዋሳ ከነማ
#ዲንክ_ኪያር በራሱ ላይ

@hawassakenemafc
@hawassakenemafc
HTML Embed Code:
2024/04/24 00:27:22
Back to Top