አንዲት ምስኪን ሀገር
.
.
.
ሙሾ እያወረደች ነጠላ አዘቅዝቃ፤
ኩርማን ስትለምን ከማጀቷ ርቃ፤
መኖር ታክታ ክንዷ ዝሎ፤
በእንባ ብዛት ፊቷ ከስሎ፤
ሰላምን ተርባ ተሰብሮ መንፈሷ፤
በላይዋ አለቀ የዝን ጥቁር ልብሷ፤
ቀኝ ጎኗ ሲድን ግራዉ ይታመማል፤
መዳንን ስትሻ ሀኪሙ ይጠፋል፤
መድሀኒት ቀማሚ በሀገሩ ጠፍቶ፤
ቁስሏ ሲያመረቅዝ ህመሟ በርትቶ፤
ከቤቷ እየመጡ ይማርሽ ይሏታል፤
መድሀኒቷን ነፍገዉ ፈዉስ
ይመኙላታል።
በዔደን ታደሰ
@ediwub
@getem
@getem
>>Click here to continue<<