የአብስራ ሳሙኤል
ከቤትሽ በር ላይ
ትንሽ ዘምበል ብሎ ቅጠሉ የረገፈ
አንቺ ስትወጪ የተንዘፈዘፈ
በአራራይ ዜማ
ጎንበስ ቀና ብሎ ውዳሴ የሚያሰማ
ዛፍ ካየሽ.......እኔ ነኝ
ደሞ ጮራ ከቦሽ
የጸሀዪ ንዳድ ገላሽን አልቦሽ
ማረፊያ ፍለጋ የተቀመጥሽበት
ስራ የፈታ ድንጋይ የዱርዬ መንበር
የኔ ገላ ነበር
ወይም ባለፈው 'ለት
በዕለተ ሰንበት ልደታን ስትስሚ
የተሽኮረመምሽው ምርቃት ስትሰሚ
ምንም ሳትሰጪ ሳትመጸውቺ
ህይወት ህይወት ጸዳል ለምትሸቺው ላንቺ
አሜን ሳትይ እንኳ የመረቀሽ ለማኝ
እኔ ነኝ
እናልሽ መቅደሴ
ሴያሻሽ እንደ ታዛ ሲያሻሽ እንደ ወንበር
ደጀ ሰላም ወድቆ ሲመርቅ የነበር
ከጎጆሽ ባይመጥን ከልብሽ ባይሞላ
በሄድሽበት ሁሉ በአምሳል እያጠላ
እንደ ንፍቀ ክበብ ሲዞርሽ የሚገኝ
እኔ ነኝ
@getem
@getem
@paappii
>>Click here to continue<<