TG Telegram Group & Channel
ግጥም ብቻ 📘 | United States America (US)
Create: Update:

---

የአብስራ ሳሙኤል 
*・꙳・꙳・꙳・꙳・・*

እጠራሀለው 
በስምህ አቤት በለኝ ከሰማኀው
"ጠይቁ?" ብለህ አልነበር 
እጠይቃለሁ አንተ እንዳልከው 

ከፀሀይ ጀርባ  ምን አለ?
ከህይወት አድማስ ባሻገር 
ሞት የህይወት ፍጻሜ ነው? 
ወይስ ድልድይ የሚሻገር? 
አላዛር ያኔ ቢጠየቅ 
የሞተ ግዜ የት ነበር? 

ወዴት ነው 
የመኖር ማብቂያው? 
ወዴት ነው መጠናቀቂያው? 
ነፍሴን የማጽናናበት 
ምኞቴን የምዳኝበት 
ምን አለ ከጸሀይ ጀርባ? 
ወዴት ነው ነፍሴ የምትሸሸው? 

ይብቃህ እረፍ ተብዬ 
የስቃይ ቀኔ የሚያመሸው 
አውቃለሁ እንደ ነገርከኝ 
ብረዳም ከድርሳን ቅጽህ 
ማ? በለኝና ማን ልመን 
ብዙ ነው ስምና ገጽህ 

*"ጠይቁ?" ብለህ አልነበር・・・ራባይ* 
―☾―

አየሁኝ 
እውር አንበሣን 
አንካሳ ነብር ሲመራው 
እንዲህ ነው መንግስት የሚዘልቅ 
እንዲህ ነው ፍጡር የሚመራው 

ካልተማመነ 
መንገዱን በነብር አይን ተረድቶ 
መጠራጠር ይገላል 
አንዱን ከአንዱ አባልቶ 
ይኀው ነው የነፍሴ ጣሯ 
አታምነኝ ወይም አላምናት 
ማ? በለኝና ማን ልበል 
በየቱ ቃልህ ላባብላት 

ማመን ነው 
የተስፋ ምርኩዝ 
መከተል የአይኑ ብርሀን 
ወዴት ነው የመኖር ማብቂያው? 
ወዴት ይሆን የመራኀን? 
―✦―

እጠራሀለው 
በስም አቤት በለኝ  ከሰማኀው
ጠይቁ ብለህ አልነበር 
እጠይቃለሁ አንተ እንዳልኀው 

ከጸሀይ ጀርባ  ምን አለ?
ኦና'ነት ወይ ፍጻሜ 
የት ይሆን ጅምር መቋጫው? 
ስንት ይሆን የመኖር እድሜ? 
ወዴት ነው የመኖር ማብቂያው? 
ወዴት ነው መጠናቀቂያው? 

አውቃለሁ 
እንደ ነገርከኝ 
ብረዳም ከድርሳን ቅጽህ 
ማ? በለኝና ማን ልመን 
ብዙ ነው ስምና ገጽህ 

*・☽・・・☾・・・*

@getem
@getem
@paappii

---

የአብስራ ሳሙኤል 
*・꙳・꙳・꙳・꙳・・*

እጠራሀለው 
በስምህ አቤት በለኝ ከሰማኀው
"ጠይቁ?" ብለህ አልነበር 
እጠይቃለሁ አንተ እንዳልከው 

ከፀሀይ ጀርባ  ምን አለ?
ከህይወት አድማስ ባሻገር 
ሞት የህይወት ፍጻሜ ነው? 
ወይስ ድልድይ የሚሻገር? 
አላዛር ያኔ ቢጠየቅ 
የሞተ ግዜ የት ነበር? 

ወዴት ነው 
የመኖር ማብቂያው? 
ወዴት ነው መጠናቀቂያው? 
ነፍሴን የማጽናናበት 
ምኞቴን የምዳኝበት 
ምን አለ ከጸሀይ ጀርባ? 
ወዴት ነው ነፍሴ የምትሸሸው? 

ይብቃህ እረፍ ተብዬ 
የስቃይ ቀኔ የሚያመሸው 
አውቃለሁ እንደ ነገርከኝ 
ብረዳም ከድርሳን ቅጽህ 
ማ? በለኝና ማን ልመን 
ብዙ ነው ስምና ገጽህ 

*"ጠይቁ?" ብለህ አልነበር・・・ራባይ* 
―☾―

አየሁኝ 
እውር አንበሣን 
አንካሳ ነብር ሲመራው 
እንዲህ ነው መንግስት የሚዘልቅ 
እንዲህ ነው ፍጡር የሚመራው 

ካልተማመነ 
መንገዱን በነብር አይን ተረድቶ 
መጠራጠር ይገላል 
አንዱን ከአንዱ አባልቶ 
ይኀው ነው የነፍሴ ጣሯ 
አታምነኝ ወይም አላምናት 
ማ? በለኝና ማን ልበል 
በየቱ ቃልህ ላባብላት 

ማመን ነው 
የተስፋ ምርኩዝ 
መከተል የአይኑ ብርሀን 
ወዴት ነው የመኖር ማብቂያው? 
ወዴት ይሆን የመራኀን? 
―✦―

እጠራሀለው 
በስም አቤት በለኝ  ከሰማኀው
ጠይቁ ብለህ አልነበር 
እጠይቃለሁ አንተ እንዳልኀው 

ከጸሀይ ጀርባ  ምን አለ?
ኦና'ነት ወይ ፍጻሜ 
የት ይሆን ጅምር መቋጫው? 
ስንት ይሆን የመኖር እድሜ? 
ወዴት ነው የመኖር ማብቂያው? 
ወዴት ነው መጠናቀቂያው? 

አውቃለሁ 
እንደ ነገርከኝ 
ብረዳም ከድርሳን ቅጽህ 
ማ? በለኝና ማን ልመን 
ብዙ ነው ስምና ገጽህ 

*・☽・・・☾・・・*

@getem
@getem
@paappii


>>Click here to continue<<

ግጥም ብቻ 📘




Share with your best friend
VIEW MORE

United States America Popular Telegram Group (US)