TG Telegram Group Link
Channel: ግጥም እና ጥበብ
Back to Bottom
ቻይ ስትሆን
==+====

ከናፈርሕ ደርቆ፥
                    ውስጥሕ ተጨናንቆ፤
ሲገርፉት ዝም ቢል፥
                      ፈርቶ ተሸማቆ፤
ነገ ስትስል ስታልም፥
                      ተስፋን ስትሸከም፤
አርቀሕ ስታስብ፥
                    ብራን ስትሆንብሕ ፍም፤
ቀኑን ከሌቱ መለየት ሲቅትሕ፤
ከሜዳ ተነስቶ ነገር ሲጠምብሕ፤
እሕል በሞላበት ሲርብሕ፤
ወንዘ በሞላበት ሲጠማሕ፤
ቻይ ስቶን ሁሉን ታልፈዋለሕ።

ምንተስኖት ሱሌይማን
ቀን፦24/05/2016
#ናፍቆት_እኔን_ሳያሰቃየኝ

ከመሄዷ
በፊት እሷ 
ምን አለችኝ
ያደረግከው  ፥  እንዳስከፋኝ
እስክነግረህ ፥  አትጠብቀኝ
እንደግጥምህ
እንደህይወትህ 
ስታዝን ብቻ  ...  የምታነሳት
ለሳቅ ጊዜ የምትረሳት
ሰው ጨቅጭቀህ
ስሙኝ ብለህ  ፥  የምታነባት
በየቦታው  የምትለጥፋት
ከቀነህ ውስጥ
ከአንድ ሰዓት ... የማትበልጥ ... የምትሰጣት
የምትኩላት ... የምትቀባባት ... ለመሸሽ ሂስ
"ምን ተሰማኝ" ቀርቶ  ፥  "ከምን ላውራ" የሚፀንስ
እንደግጥምህ
እንደህይወትህ
ተው አትይኝ  ...  ሆኜ ሚስትህ።


✍️ተጽፎ በ Safi Abde
ግጥም እና ጥበብ pinned «https://vm.tiktok.com/ZMMYR4moS/»
🇪🇹ጦቢዊነት🇪🇹
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
የዋሕ ነበሩ
              ከልብ ከነፍቅሩ፤
ጀግናም ነበሩ
             ጣልያንን ያባረሩ፤
ኩሩም ነበሩ
              ከነ ሙሉ ክብሩ።

ታድያ በአሽዋ ዘመን አፈር ይረክሳል፤
የምንበላው የለ የምንከናነብ ያምረናል።
እምዬ ሚኒሊክ የጦቢያ ብራን፤
በብልሀታቸው ከነጭ በታደጉን፤
ስማቸው ሲጠራ ለምን እንጠላለን?
ማርያምን ብለዋል፤
ሊዋጉም ዘምተዋል፤
ፊት አውራሪ ሆነው ጀነራል ማርከዋል፤
በጦር በጎራዴ ጠመንጃን ነጥዋል፤
እነሱ ተዋግተው እኛን አኩርተዋል።
በአረንጓዴ ቢጫ በቀዩ ባንዲራ፤
ስንቱ ተዋደቀ ሀገሩን ሊያኮራ።
ከራቱም አቅጣጫ ከመላ ሀገሩ፤
እነሱ ሞተው አኝን ግን አኮሩ።
ጦቢዊነት ደም ነው ቢቀዳ የማያልቅ፤
ከዘር ከጎሳ የሰፋ የሚልቅ።

ምንተስኖት ሱሌይማን
ቴክስት ብልክልሽ
ዘመናት ቆይተሽ ኮርተሽ ስትመልሺ
ለሳምንት ስዘጋሽ
ሀኒ፣ቤቢ እያልሽ ስታለቃቅሺ
.
ዕርሜን የደወልኩ' ዕለት
ጥሪው ተመችቶሽ ደግመሽ እንዳልሰማሽ
የኔ ተራ ሲደርስ እንደው ምን ተሰማሽ?
.
አየሽ!!
የተጣለ ሁሉ ወድቆ ላይቀር ደርሶ
ምንም አይበጀኝም ያአንቺ ያሁን ለቅሶ
.
የተናቀ አስማጠ የተገፋም ወጣ
እኔም አልቀረሁም ይኸው ቀኔ መጣ

ይድረስ ላማረሩዋቹ ሴቶች🙌


♡ ㅤ    ❍ㅤ      ⎙         ⌲
ˡᶦᵏᵉ   ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ    ˢᵃᵛᵉ  𝑠ℎ𝑎𝑟𝑒
  💡💡💡💡💡💡💡💡
    ✍️📝  https://hottg.com/tibepil
     📝✍️ https://hottg.com/tibepil
  💡💡💡💡💡💡💡💡
🌹.................................🌹
Forwarded from ዜመኞቹ - Zemegnochu (HR tube)
ነገ ማታ 2 ሰዓት በ ዜመኞቹ YouTube Channel ይጠብቁን link 👇👇👇

https://youtube.com/shorts/bb4k9Rvx338?feature=share
#የኔ_ልብ_ንግሥት..

ማነሸ? ማን ልበልሸ? በምን ቃልሰ ልጥራሸ ፍደል ብደረድር አጣምሬ ብቀምር አጠሩኛ ቃላት ጠፉብኝ ፍደላት እና አንቺን ለመግለጽ ልበደር ወይ አንቀጽ በዜማ በቅኔ የምትበልጡ ከኔ እሰቲ ፍደል አምጡ ቃላትን መሰርቱ እኔንስ ከብዶኛል እናንተ ሰም አወጡ
ማሰተዋለ ከሰጣት፣ ውበትን ካደላት ለሰው ልጅ አሳቢ፣አርጎ ከፈጠራት የሷ ምክር ገብቶ፣በልቤ ከረፈ ምታወጣው ቃላት ፣ ሞልቶኝ ከተረፈ ለዚች ለምትመክረኝ፣ የድካሜ ብርታት እሰቲ ማን ልበላት፣ የትኛው ሰም ልሰጣት ለሰሟ ስያሜ፣ ጠፉቢኝ ፍደላት
እንግዲህ ከጠሩኝ፣ ቃላት ከጠፉቢኝ የፍደላት ጥምረት ፣ትርጉሟን ካልሰጡኝ የኔ ባቶን እንኳን ዝምብዬ ልውደዳት እንዲሁ በድፍኑ....የኔ ልብ ንግሥት ብቻ ብዬ ልጥራት

Safi Abde
Forwarded from Quality button
🎸🎧የፍቅር ሙዝቃ🎧🎸 ምትፈልጉ ብቻ ይሄን ቻናል ተቀላቀሉ። የምር ትወዱታላችሁ ገብታችሁ እዩት❤️‍🩹❤️‍🩹
#አንቺን_ካጣሁ_ወዲህ

የነካሁት ሁሉ በ'ጄ እየቆሸሸ
ፈጣሪን ስረግመው
ተስተካክሏል ያልኩት  እየተበላሸ

ያለማንነቴ
ማንነት ሰጥተውኝ በብሶት ስባዝን
እንዳረጀ ውሻ
በየመንገዱ ዳር በብሶት ሳላዝን
ይኸው ዘመን ነጉዶ
በጊዜ ሀዲድ ላይ አመታት አለፉ
እኔ አንቺን መውደዴ
ኪሳራ ባይሆንም መገመት ነው ትርፉ፡፡

አቃተኝ አልቻልኩም
እራሴን አጥቼ በስካር መደበቅ
በይሆናል ተስፋ
በሌለ ማንነት አለሁ ብሎ መድረቅ፡፡
ብቻ ግን ጠጣለሁ
መርሳቱ ቀርቶብኝ በእጥፍ ላስብሽ
ባዶ ሆኖ ሳለ
የኔ ልብ ያን ይላል ምን ይልሻል ልብሽ?

✍️ Safi Abde
Forwarded from Haymanot Nigusie (HR tube)
አዲስ ቪዲዮ ተለቀቀ
ግጥም እያላችሁ ዜማ ለተቸገራችሁ
አቀናባሪ መለመን ላሰለቻችሁ
ጀማሪ ድምፃዊያንሞክሩት
Not Forget Like,Share,Subscribe

https://youtu.be/Rdd9YfE7Jug
ግጥም በእንባ የተሞላ፣ በሽግግር መንገድ ተዘጋጅቶ በውበት እና በግጥም ቋንቋ የሚቀርብ የስነ-ጽሁፍ ዘርፍ ነው። በግጥም ውስጥ, ጠንካራ ትርጉም ለማስተላለፍ ቋንቋ, ግጥም, ፈሊጥ እና ቃላት ይጠቀማሉ. ግጥሞች ብዙውን ጊዜ ትኩረትን በመጠየቅ ይጀምራሉ. ከዚህ በታች ባለው ምሳሌ ይጀምራል.

ያለ ለውጥ የብሔርተኝነት ውዳሴ

የድህነትን ጥይት በጀርባቸው ይሸከማሉ

በህልም ይዘምራሉ እናም ፍልስፍናን ይከላከላሉ

የአዕምሮ መስክ የሃሳብ ክፍልን ይከብባል

የዱሪጉላሊ ዘመን

እንደ ሶቅራጠስ ገለጻ፣ ግጥሞች በዙሪያችን ያሉ እና በአለም ዙሪያ ያሉትን ነገሮች እውነተኛ ተፈጥሮ ያሳያል። ፍልስፍና፣ ቅኔ ከአብዮት ይልቅ የሀገርና የህዝብ ሞራል፣ የሀገር ሞራል ውድቀት ነው ይላል። ስለዚህም ህብረተሰቡ ወደ ገሃዱ ዓለም መግባት የለበትም ሲል ጽፎ ተከራከረ። አርስቶትል ግጥም ከስሜታዊው ስኳር ፈውስን ያመጣል, ፍርሃትን እና ሀዘንን ያነሳል እና ያጠፋል.

የግጥም ባህሪያት

ግጥም ተግባራዊ ነው። ከገሃዱ አለም በመነሳት ግጥም ሀሳቡንና አስተያየቱን ይገልፃል እና ተጨባጭ ነገሮችን በመጠቀም ጉዳዩን ለአንባቢ ያቀርባል። ግጥም ምስል ሰሪ ግጥም ሲሆን ይህም ማለት ጥቅም ላይ የሚውሉት ቃላት በአንባቢው አእምሮ ውስጥ ምስል ሊፈጥሩ ይችላሉ. ግጥም የቃላት እና የሃሳብ ምርጫን ይጠይቃል። ሀሳቦችን በብቃት ለማስተላለፍ የሚያምሩ ቃላትን እና ኃይለኛ ቃላትን ተጠቀም። ቁጠባዎች የሚመጡት ሀሳቦች በአንድ ቦታ ላይ ስለሚከማቹ ነው. ግጥም በቋንቋ ቀርቧል ስለዚህም ግጥም አለው። ከስሜታችን ሁሉ ለጆሮ ቅርብ የሆነው ይህ ዘፈን አሳዛኝ፣ ደስተኛ፣ አስደሳች እና ተስፋ አስቆራጭ ሊሆን ይችላል።
#የምናብ_እስረኛሽ


አልገባሽም እንጂ አንቺን ሳስብ እኔ፣
ሳላውቀው ያልፈኛል ሰዓትና ቀኔ፣

ብዕሬን አድምቼ ልከትብ ስላንቺ፣
ቃላት ተቆላልፈው ያጡብኛል ፍቺ፣

ዕውቀት አጥሮኝ ሳይሆን ስሚኝ እታለሜ፣
ላ'ንዷ በተፃፈው ላንቺ አልፅፍ ደግሜ፣

እኔ ያንቺ አላሚ የምናብ እስረኛሽ፣
አንዴም ላላገኝሽ እልፍ የተመኘሁሽ፣
ባልታሰረ ሸራ አስውቤ የነደፍኩሽ፣
ቀለም ባጣ ብሩሽ ውበት የለገስኩሽ፣
ውል ባጣ አዛዚያም ውበት የሰጠሁሽ፣
አንቺ ያላወቅሽኝ የምናብ እስረኛሽ፣

እኔው ነኝ

አቅም የለኝ ከቶ ችዬም አልበረታ፣
አንደበቴ ልጉም እስር ያልተፈታ፣
ወጉን የጠበቀ ቃል ካፌም አይወጣ፣

የትልቅ ህፃን ነኝ ሲፈጥረኝ ፈጣሪ፣
የሰለለ አካል ተደግፌ ኗሪ፣

እኔ ያንቺ ታማሚ የምናብ እስረኛሽ፣
በዚ ፍጥረቴ ላይ የእውነት አፈቀርኩሽ፣

እንዳልነግርሽ ነገር የአንደበት እዳ፣
አይወጣም ከውስጤ የፍቅርሽ ዱብዳ፣

ወይ ነግሬ አይነግሩሽ አማላጅ አልሰድም፣
ማንስ ከቶ ያምነኛል አፈቀርኩሽ ብልም፣

በዘገመ አይምሮ በሰለለ ገላ፣
በትልቅ ልጅነት ፊት በሌለው ሗላ፣
በማፍቀር አለም ውስጥ የኔ ህልም ላይሞላ፣
ተመኘሁሽ አንቺን ሞኝ ነኝ ተላላ፣

አንቺማ፣

ፈላጊሽ ብዙ ነው በዜማ በቅኔ የሚያወዳድስሽ፣
ፍቅሩን ካ'ንደበቱ አውጥቶ ሚነግርሽ፣
ክንደ ብርቱ ፍርጥም ጋሻ የሚሆንሽ፣

ታድያ ምን ያደርጋል የኔ አንቺን ማፍቀር፣
በዚ ሙት አካሌ ባልገባው ወደ አፈር፣

አንቺም አታውቂውም እኔ እንደው አልነግርሽ፣
ሆኜ ልኑር እንጂ የምናብ እስረኛሽ፣



✍️Safi Abde
Forwarded from Haymanot Nigusie (HR tube)
https://hottg.com/tapswap_mirror_1_bot?start=r_453240043 🎁 +2.5k Shares as a first-time gift

በአንድ ቀን ማግኘት ይቻላል
HTML Embed Code:
2024/06/03 10:40:33
Back to Top