TG Telegram Group Link
Channel: ግጥም እና ጥበብ
Back to Bottom
Forwarded from Haymanot_siliver
አድራሻ : ልደታ #ዶን_የጥርስ_ህክምና_ክሊኒክ
ፊት ለፊት

ስልክ : +251973076559
         : +251993709655

በመረጡት ዲዛይን በጥራት እና በፍጥነት ሰርተን እናስረክባለን።

#በግሩፕ_እና_በብዛት_ለሚያዝዙ_ደንበኞች_ልዩ_ቅናሽ

ለማዘዝ ሱቃችንን ይጎብኙ
ወይም ይደውሉ
ሌላም አማራጭ
👉 @haymanot6 ን ይጠቀሙ

Check Out
@haymanot_siliver
#ሌባና_ሌባ
        ፧
ምን ሊጠቅምሽ ነው? ልቤን ሰረቅሺው፣
እኔን ልበ ቢስ አደረግሽና ላንቺ ደረብሽው፣
ላይጠቅምሽ ነገር መንታ ልብ ሆነሽ፣
     ስለምን ሲባል?
ልቤ በጠፋው በባዶነቴ ትጨነቂያለሽ፣
ልሞት ሳጣጥር ሀኪም ሆነሺኝ፣
ልቤን ስፈልግ ያንቺን ሰጠሺኝ፣
ሌባ ነሽ እኮ ለዛውም የልብ የሰው ሙሉ አካል፣
ልብ የሌለው ሰው እንዴት አስቦ በምን ይለካል፣
ሩህሩህ ሌባ የኔን ቀምተሽ ያንቺን ሰጠሽኝ፣
ልብ ለሌለኝ ልቤ ሆንሽና ሌባ አደረግሺኝ፣
ሌባና ሌባ አሪፍ ፍቅረኞች ለክፉ አንዘምትም፣
በፍቅር ዓለም ሌባና ፖሊስ አንጫወትም።


✍️Safi Abde
#የመፃፍ_ቅምሻ 📖📚


ሂትለር የአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት መምህር ነው።ሰይጣን ሰፈር መጠጥ የማይጠጣና
የማይሰክር ሰው በመብራት ፈልጎ ማግኘት ባይቻልም ፤ ሂትለር ግን ወደር የማይገኝለት
ጠጥቶ ንቅንቅ የማይል ፤ ጠጥቶ በቃኝ የማያውቅ ሽንቁር ገንቦ በመሆኑ ነው። ሚስቱ አንድ ልጁን ቡቾን አስታቅፋው ከሄደች ወዲህ ደሞ ብዙ ይጠጣል። እቤቱ ሲገባ ዋነኛ ተግባሩም ቡቾን ማሰቃየት ነው። በቀበቶ ይተለትለዋል፤ ቁልቁል አንጠልጥሎ በበርበሬ ያጥነዋል፤እጅና እግሩን አስሮ ያሳድረዋል። ይሄን ሁሉ የሚያደርገው ሚስቱን ለመበቀል ነው።

" አንተ ተኩላ ! እናትህም በልታ የማትጠግብ የሰው አሳማ ነበረች። በቀን ሁለት ዳቦ በልተህ ራበኝ ብለህ ታለቅሣለህ!" ሂትለር ይጮሃል።

" አላለቅስም አባዬ፣ ሁለተኛ አላለቅስም!" ቡቾ ያላዝናል።

" አባቴ - አትበለኝ- አባት ይንሳህና! የናትህን ጉድ ያልሰማውልህ መሰለህ? አንተ የኔ ልጅ
ሣትሆን የጣልያኑ የሲኞር ፖውሎ ዘበኛ ልጅ ነህ። ይሄን የጥንቸል ጆሮ የመሰለ ሾጣጣ
ጆሮህን ስመለከት ሁል ጊዜም ይደንቀኝ ነበር- ገና ልጅ ሣለህ ጀምሮ። የዚያ የመንደሩ
አውደልዳይ ኮርማ፤ የሲኞር ፖውሎ ዘበኛም ጆሮው እንዳንተ ሾጣጣ ነበር። ቀበሮ፣ የሰው
ቀበሮ! . . ."

ግርፊያው ቀጥሏል፤ የልጅ ጀርባ ይጮሃል፤ አፉ ይለማመጣል።

" እናትህ የት እንዳለች ታውቃለህ?"

"አላቅም፣ አባይዬ"

" አንድ ሸማኔ አግብታ ጥበብ ለብሳለች አሉ። ጧት ላይ ያጠለቀችው ጌጥ ቢሸጥ እኔና
አንተን ይገዛል አሉ። አንተም እንደ እናትህ ብልጥ ነህ?"

"አይደለሁም አባዬ"

"እንግዲህ በአባትህ ወጥተህ ይሆናል። የሲኞር ፖውሎ ዘበኛም እንዳንተው ነጉላ ነበር።
ለመሆኑ ከትምህርት ዓይነቶች የትኛውን ትመርጣለህ?"

"ሣይንስን አባዬ"

" ውሸታም ልጅ ውሸታም ትምህርት ቢመርጥ አይደንቀኝም። ሣይንስ ውሸት ነው። ዝንብ
የጤና ጠንቅ ነች ይላል። የዚህ የሰይጣን ሰፈር ሕዝብ በሚሊዮን ከሚቆጠሩ የዝንብ አብሮ
አደግ ወዳጆቹ ጋር በመከባበርና በመተባበር ሲኖር እንጂ፣ ተቅማጥና ሞት ቀርቶ ቁርጠት
ይዞት አይተሃል?"

"አላየሁም አባዬ!"

"ታዲያስ? እንዳንተ ውሸታም ሣይንስ ግን 'ብርድ የኒሞኒያ መንስኤ ነው' ይላል። እስኪ
በዚህ መንደር እርቃናቸውን ከሚንጦለጦሉ ህፃናት አንድ እንኳን ታሞ የተኛ አይተሃል?!"

"አላየሁም አባዬ"

"ሣይንስ ለዚህ ምን መልስ ይሰጥሃል? የህፃናቱ ቆዳ ከአዞ የተሠራ ነው ሊልህ ነው?
የሣይንስ ውሸት በዚህ ብቻ አያቆምም። 'ጉንፋን ከቆሻሻና ከመጥፎ ሽታ ይመጣል'
ይልሃል። ለመሆኑ እዚሁ ሰይጣን ሰፈር ጠላ ቤቱ አጠገብ የተከመረው ቆሻሻና የሽንት ፍሳሽ
ይታይሃል? ጠላ ነጋዴዋ አሮጊት እንኳን ጉንፋን ሊይዛቸው ሲያስነጥሳቸው ሰምተሃል?!"

"አልሰማሁም አባዬ!" ይላል ቡቾ እየተንቀጠቀጠ

"ሣይንስ ውሸት ነው! አንተም ውሸታም ነህ! የፖውሎ ዘበኛም ውሸታም ነበር"

" ልክ ነህ አባዬ"

"ሌላ የምቶደው ትምህርት ምንድን ነው?" ግርፋቱን ቀጥሏል።

"ህብረት! አባዬ ህብረት!"

ሂትለር ከትከት ብሎ ይስቃል። " 'ከድጡ ወደ ማጡ' አሉ። ህብረት? ይሄም ለኛ ሀገር
አይሠራም። በወፈረ በቀጠነው ለሚጯጯህ፣ አጥንት ላይ እንደ ሰፈረ የውሻ መንጋ እርስ
በእርሱ በሚናጭ ህዝብ መሃል ህብረት ብሎ ትምህርት ውሸት ነው! አንተም ውሸታም ነህ፤
ልክ እንደ ዘበኛው! ሌላ አምጣ!"

"እሽ - ታሪክ አባዬ"

ሂትለር ድምጹን ከፍ አድርጎ ከጣራ በላይ ይስቃል። " ታሪክም ውሸት ነው! እንደኔ፣
እንዳንተ፣ እንደ ሰይጣን ሰፈር ላሉ ነዋሪዎች አይሠራም። ቀድሞ ነገር ደሃ ምን ታሪክ
አለው? የድሃ ታሪክ ቀን ከሌት የማይተኛ ሆዱን ለማሸነፍ የሚያደርገው ተጋድሎ ነው።
ታሪክን ለባለ ታሪኮች ተውላቸው። የሰው አሳማ! ሠርተህ ሆድህን የምትሞላበት ትምህርት
አትመርጥም?!"

"ሂሣብ!" አለ ቡቾ ሲፈራ ሲቸር። ሂትለር ይስቃል።

"አሁን ገና ልክ እንደ እናትህ ጦጣ
ሆንክ። ሂሣብ ምን ጊዜም ትክክል ነው። አንድ ብርና አንድ ብር ዘለዓለሙን ያው ሁለት ብር
ነው። እንደ ሣይንስ አይዋሽም። እንደ ህብረት አያፌዝም፣ እንደታሪክ ጀንበር ስትጠልቅ
አይለዋወጥም"

"ልክ ነህ አባዬ"

"ብራቮ ቡቾ ! አራቱን የሂሣብ መደቦች አጣርተህ ካወቅህ ይበቃሃል። እውነቱን ይዘሃል
ማለት ነው። አራቱን የሂሣብ መደቦች አውቀህ ስትጨርስ ንገረኝ። ከዚያ በኋላ ወደ
ትምህርት ቤት አትሄድም። ተምረህ ከምታብድ፣ ደንቁረህ ብትራብ ይሻላል! እሺ ቡቺ?!"

"እሺ አባዬ"

ሂትለር ይኸኔ ልጁን አቅፎ ይስማል። ራሱንም እያሻሸና ከጉያው እያስገባው "ይሄ ሾጣጣ
ጆሮህ ባይኖር እወድህ ነበር ቡቾ" ይለዋል።

"ታዲያ ለምን ሁልጊዜ እሱን እያየህ ከምትደበድበኝ በምላጭ ከርክመህ
አታስተካክልልኝም? ያንተን ሊመስሉ ይችሉ የለም?" የሚል ምላሽ ሲሰጠው ሂትለር ደረቱን
ደግፎ ትንፋሽ እስኪያጥረው ይስቃል።

/ከደረጄ በቀለ
"ህያው ፍቅር"
ገፅ 42-44/



✍️Safi Abde
HTML Embed Code:
2024/06/03 11:00:48
Back to Top