TG Telegram Group Link
Channel: የሆሄያት ህብር📝📝
Back to Bottom
#እኔ_እንጃ



«ፍቅር አይቀናም» ይላል፣
ከፈጣሪ የተሰጠን የማይሻረው ቅዱሱ ቃል፣
አንድ ልቤም ይህን ያውቃል።
እኔ ግን ...
ቆሽቴ ድብን እስኪል ድረስ ጨጓራዬም እስኪከስል፣
ፊቴም አመድ እስኪመስል፣
ሰርክ ባንቺ እቀናለሁ በማይረባ ተራ ነገር፣
ቢሆንም ግን አልታከትኩም አፈቀርኩሽ ብዬ ላንቺ ሁሌ እንዳዲስ ከመናገር።


«ፍቅር አይታበይም» ይላል፣
ፅኑ ወንጌል ቅዱሱ ቃል፣
እርግጥ ልቤም ይህን ያውቃል።
እኔ ግን ...
ባደባባይ አብረን ስንዞር እቅፌ ውስጥ አስገብቼሽ ቸርችሬያለሁ እልፍ ጉራ፣
አንቺን የኔ በማድረጌም ደረት እና ትከሻዬን ሰብቄአለሁ በየተራ፣
ሰው እንዲያየን ተመኝቼም ተጓደድኩኝ ተጎብሬ፣
አፈቅርሻለሁ ግን እላለሁ ተመልሼ ደግሞ ዞሬ።


«ፍቅር ቸርነት ያደርጋል»፣
ይላል የፈጣሪ ቅዱስ ቃል፣
ይህም እውነት ልቤ ዘልቋል።
እኔ ግን አንቺን ብቻ ስል ግራ ቀኜን ፊት ነስቼ፣
ሁሉን ላንቺ ለመስጠት ስል ወዳጅ ዘመድ ወዲያ ትቼ፣
ቸር ማድረግን እረስቼው ተቆራኝቶኝ ንፉግነት፣
ላፍታም ቢሆን አልቦዘንኩም አፈቅርሻለሁ ግን ከማለት።


«ፍቅር በ እውነት ደስ ይለዋል»፣
ቅዱሱ ቃል እንዲያ ይላል፣
ልቤም ይህን ያስተውላል።
እኔ ግን ላንቺ ደስታ ስል ያልሆንኩትን ሆኜ አውቃለሁ፣
እየከፋኝ እስቃለሁ፣
እንዳላጣሽ እየሰጋው እየዋሸው ስንቴ አለፈ፣
አፈቅርሻለሁ ግን ከማለት ልቤ ዛሬም አላረፈ።


«ፍቅር አመፅን ይጠላል» ይላል፣
የተሰጠን የ ሕይወት ቃል፣
በልቤም ውስጥ ተሰንቋል።
እኔ ግን ...
በክፉ ያዩሽ ሲመስለኝ ምኑንም ገና ሳልይዘው ጥላቻ ውስጤ እየሞላ፣
አስሼ ፀብ በደላላ፣
ባንቺም ላይ ዓይኔ እየቀላ፣
ተጋጨው ካላፊ አግዳሚ፣
ቢሆንም ነግቶ አይመሽም አፈቅርሻለሁ የሚል ቃል ከኔው አንደበት ሳትሰሚ።


ሲጋጭብኝ ብታዘበው ላንቺ ያለኝ ጥልቅ ስሜት፣
ከማይሻረው ቃለ ህይወት፣
ይጨንቀኛል ይጠበኛል ይጠፋኛል ምገባበት።
ማቅ ለብሼም ተክዛለሁ ላንቺ እስካሁን ባይታይሽም፣
ፍቅር ከቃል በላይ ነው እንዴ? ወይንስ አላፈቅርሽም?
                             እኔ እንጃ!
#ሄኖክ_ብርሃኑ
@gGetem
@gGetem
@leoyri
#በርግጥ እንደ እህት ናት
ፍቅሯ ግን ነው ሚስጥር
አይነኳት ነገር
እሾህ የሷ አጥር !
ወደድኩሽ ልበላት?
ቀልድ ነው 'ሚመስላት
እርሷ እየሳቀች
ወንዱን እየራቀች
ነፍሷ ግን ለብቻ ጮሀ ትጣራለች
ለዛ ልስልስ ገላ ከለላ ትሻለች ።
ይገርማል
ያስፈራል !
ወደድኩሽ አትባል ...
ያ ጥርሷ  ይቀድማል።

(ሚካኤል• አ)
@gGetem
@leoyri

ህብረ ቀለማት ግጥሞች
#የወፈፌው ቃላት!!
(ሚካኤል አስጨናቂ)
።።።።።።።።።።።።።።።
ደግሞ ተነሳብኝ!
የአምና ካቻምናው ፥ የፊቱ እብደቴ
አንቺን ባየው ቁጥር.. .
ወፈፈ ሚያስብለኝ ፥ ህመም ምልክቴ።
ይኸው ፌስታል ሸረብሁ !
ቡልኮዬን ቀደድሁ
ገረባዬን ሸከፍሁ
ካላፊ ካግዳሚው ...
ቅጥሬን ለይቼ ፥ በፅኑ ተኳረፍሁ።
ብልሀት በራቀው ፥ መላ በሌለበት
ህመምን የሚያብስ...
ከንፈር መጣጭ ሀኪም ፥ ደጁን በሞላበት
ከተማ ሸሽቼ ...
ብቻዬን ወጥቼ...
ለሚሰግር ፍቅር ፥ መንገድ ላበጅለት
አበድሁ ስላንቺ ...
ያለ አንዳች ከልካይ ፥ ተመላለሺበት ።
ይኸው እንኪ ሰበዙን
የልምዱ እብደቴን...
በወስፌ ለይተሽ ፥ መሶቡን አበጂ
ተቀበይ ህመሜን!
አንጀትሽ እንዲርስ...
ከዳሩ ላይ ጨልፈሽ ፥ ወይንሽን ቅጂ ።
እንኪ ንሽማሽን!
ዘርጊው መዳፍሽን ...
ጠያቂው በተርታ ፥ በሰልፍ ተሰድሮ
ምን ክፉ አጊንቶህ
ከጤናህ ተሽረህ ፥ ሆንህ እንደ ድሮ ?
ብለው ሳይጠይቁኝ ....
#እኔም በተራዬ
"አዎን እንደዚህ ነው !
ሰው ፍቅርን ሊያነግስ ፥
ልቡን ተሸክሞ ፥ ሲወርድ ከገበያ
አቅልን የመሳት ፥ የእብደት መጀመርያ
ደግሞም የእውነት ህመም ...
መላወሻ አልባው ፥ ሀቀኛው በሽታ
ሰው ልቡን አቅርቦ ፥ ዘርግቶ በፎጣ
ሸማች ሲርቀው ነው ፥ የሚገዛው ሲያጣ "
ብዬ ሳልመልስ ፥ ሳይገለጥ ምክንያቴ
ፈጥነሽ ድረሽልኝ ፥ ተሿሚ ልዕልቴ ።
@leoyri
hottg.com/gGetem
ዓለም እድሜውን
(ሊዮ ማክ®)
አንድ ፥ሁለት ...አስር
ያለ --ምንም ስሌት ቀረሽ
አበቅቴ ቢገለበጥ
የኃሊዬሽ ዘመን ቢፈተሽ
እንደ ወጣ"የወጣ"
እንደ "ቀረ " የቀረ
እንደ ታለመ የሰመረ
እንደ--ሰመረ--የዘመረ
እንዳለ --ኖሮ
እንደኖረ --የኖረ
አንዳችም ነገር የለ
አለ፥ነበረ
ተብሎ ---የተነገረ።
ጠላት :---ሆኖ ያረጀ
ወዳጅ:---ሆኖ ያፈጀ
እንደ---በጀ፥እንደ --ጎዳ
እንደ---ጎዳ እንደ--በጀ
ሣይኖር ነው የኖረ
ዓለም እድሜውን የፈጀ።
----------------------
@leoyri
hottg.com/gGetem
የይቅርታ መሐልይ👐
ገጣሚ፦ በእውቀቱ ስዩም
አንባቢ፦ ሊዮ ማክ
የሆሄያት ህብር
#የጥበብ_ማዕድ
#ማጀቢያ፦ሲታ አዳም 👩
😍በየቀኑ አዳዲስ የግጥም ስራዎችን ለማግኘት ቤተሰብ ይሁኑ!!!
@gGetem
Comment_
@sirak6
ከወደዱት ያንሸራሽሩት (Share)
📶Medium Quality🆓
እንኳን ለ128ኛው የአድዋ ድል በዓል በሰላም አደረሰን አደረሳቹ!!!!
@gGetem
@leoyri
💚💛
አድዋ
#ገጣሚ_ሊዮ_ማክ
የሆሄያት ህብር💙💙💙
#የጥበብ_ማዕድ
#ማጀቢያ_ኤደን_ሙላት
እንኳን ለ128ኛው የአደዋ ድል መታሰቢያ በዓል በሰላም አደረሰን!!!
#አድዋ
#አድዋ
#አድዋ
💚💛💚💛💚💛💚💛💚💛💚💛💚💛
@gGetem
@gGetem
hottg.com/leoyri
የኦቶማን ንጉስ አህመድ ወደ ጦርነት ከመሄዱ በፊት ሚስቱን (ቆንጆዋን ንግሥት) በአንድ ክፍል ውስጥ ቆልፎባት ቁልፉን ለቅርብ ጓደኛው ሙሳ ሰጠው እና "በአራት ቀን ውስጥ ካልተመለስኩ ክፍሉን ክፈት እና ሚስቴን አግባት…”ብሎት ፈረሱ ላይ ወጥቶ ወደ ጦር ሜዳ ሄደ። ከግማሽ ሰዓት በኋላ ንጉሱ ከኋላው አቧራማ ንፋስ እንዳለ አየ። ቆም ብሎ ጓደኛው ወደ እሱ በፍጥነት እየሮጠ ሲመጣ አየ።

"ምነዉ ምን ሆንክ ?" ብሎ ንጉሱ ጠየቀ። በጣም ከመሮጡ የተነሳ ትንፋሹ እየተቆራረጠ ጓደኛው ሙሳ “የተሳሳተ ቁልፍ ነው የሰጠኸኝ” ሲል መለሰ።

ምንድን??? ብሎ አይቶት በድንጋጤ እና በመገረም አየዉ
ቁልፎቹን ከመሞከሩ በፊት ለ4 ቀናት ይቅርና ለ1ሰአት እንኳን አልጠበቀም።

እንደ “ጓደኞችህ” ከምትቆጥራቸው ሰዎች ጋር ተጠንቀቅ እና በትጋት ለምታገኘው ሃብት አደራ ልትሰጣቸው ትችላለህ - እነሱ በቅርቡ እንድትሞት እየተመኙልህ ሊሆን ይችላል እና እራስህን ከጓደኛህም ቢሆን መጠበቅህን አትዘንጋ።

ምክር ብቻ ነዉ።
Have a Beautiful day
💛 💕 😍

#ለመታመን_እንኑር!!!!
@gGetem
@leoyri
Forwarded from የሆሄያት ህብር📝📝 (Sirake peterøs ☞Ye Yerijo)
👫ግጣም አልባው ገጣሚ📖📚
☔️ #ገጣሚ_ሊዮ_ማክ
የሆሄያት ህብር🦋🦋🦋🦋
#የጥበብ_ማዕድ
@leoyri
@leoyri
@gGetem
@gGetem
@gGetem
👁💚💛❤️
#ተፃፈ_12_06_2012_ዓ_ም
💯 quality 😍🥰
Plc share
ልማዱ ሆኖበት
ሰው እንዴት ነህ ብሎ ሰውን ይጠይቃል
ሰውም በምላሹ ደህና ነኝ በሚል ቃል ህመም ይደብቃል
እሳት ....ወይ.....አበባ
ገጣሚ፦ ሎሬት ፀጋዬ ገብረ መድህን
አንባቢ፦ ሊዮ ማክ
የሆሄያት ህብር
#የጥበብ_ማዕድ
#ዝግጅት፦ሲፈን
😍በየቀኑ አዳዲስ የግጥም ስራዎችን ለማግኘት ቤተሰብ ይሁኑ!!!
@gGetem
Comment_
@sirak6
ከወደዱት ያንሸራሽሩት (Share)
📶 High Quality🆓
#ስለ ስህተቶቻችን ልባዊ ይቅርታቹ አይለየን!!!
ውድ የየሆሄያት ህብር ቤተሰቦች እንደምን ከረማቹ??
    ህይወት እና ቀኖቻችሁን ረቂቃን ከሆኑ ጥበባዊ ሀሳቦች እና ስራዎች በየ ዕለቱ እየቃኛችሁ እና እብረንም እየተማማርን እነዚህን ሁሉ አመታት ሳትሰላቹ  ከምክርና ከቀና ልብ ከሚፈስ መልካም አስተያየታቹ ሳይለየን ለዚህ መድረሳችንን ምክንያት በማድረግ ልባዊ ምስጋናችንን ልናቀርብ እንወዳለን ቤተሰብነታቹ ይቀጥል ዘንድ እየጠየቅን!!
......እናም እርሶም ስራዎቻችንን ከማዳመጥ ባለፈ የመስራት ፍላጎት ያላቹ ሁሉ ያለ እድሜ ገደብ አብራችሁን ...
>>በግጥም
>>በወግ
>>በትረካ
>>በፊልም (በትወና)
>>በስዕል
>>በዝግጅት
>>በፅሁፍ
>>በዜማ ለመስራት ማመልከት ትችላላቹ።
መገኛችን፦0946951761
            ፦0974901793
ወይም፦ @sirak6
         ፦ @yosikeman
በተሻለም በአካል ለምትመጡ ቢሮችን ክፍት ነው።
#ኑ_አብረን_ጥበብን_እንኑራት
የሆሄያት ህብር
#የጥበብ_ማዕድ
@sirak6
hottg.com/gGetem
Forwarded from የሆሄያት ህብር📝📝 (Sirake peterøs ☞Ye Yerijo Leጅ)
...አንድ ሰው ፈልጉ
የሆሄያት ህብር🦋🦋🦋🦋
#የጥበብ_ማዕድ
@leoyri
@gGetem
🗣
የሚስኪን አፍቃሪዋ ትግፃፅ.aac
744 KB
የሚስኪን አፍቃሪዋ ተግሳፅ
ገጣሚ፦ ሊዮ ማክ
አንባቢ፦ ቤቲ
የሆሄያት ህብር
#የጥበብ_ማዕድ
#አዘጋጅ፦ሲታ አዳም 👩
😍በየቀኑ አዳዲስ የግጥም ስራዎችን ለማግኘት ቤተሰብ ይሁኑ!!!
@gGetem
Comment_
@sirak6
ከወደዱት ያንሸራሽሩት (Share)
አስተያየታቹ አይለየን!
ተመስገን
(ሚካኤል .አ)
ለውሀ ቢቀረጥ ለማየት ቢከፈል
ለጠሀይ ቢቆጠብ አየር ቢከለከል
ለመስማት ቢያስጨንቅ ለማሽተት ቢቀጣ
አቤት የእኛ እጣ!
ዋጋ ቢወጣለት እያወሩ መስማት
በደረሰኝ ቢሆን መራመድ መተኛት
እግዚኦ የኮመቴው የህግ አውጭው መዓት!
ይህን ሳይ ብቻ ነው ወደ ላይ ማንጋጥጥ
የዓለም ማጣቴን ... በስድብ የማለውጥ
ውድ መነፅር ሳጣ ከጎኔ ማተርኩኝ
መኪና አልባ ስሆን አቀርቅሬ አየሁኝ
ማየት የተሳነው እግር አልባም አለ
እንዴት ብዬ ላማር ሁሉ ኖሮኝ ሳለ?
ስድብ ከቶ አልክም ለዝምታው ዳኛ
ጤና ቢሰጠኝ ነው ሰርቼ ምተኛ
አላማርረውም ቤት ሳልገዛ ብዬ
የጎዳናውን ጉድ እያየሁኝ ባይኔ
ባለ መፅናናት ነው በፀጋው ማመስገን
ያለን ነው የሚበዛ ለእኛ ካልተሰጠን
ተመስገን ተመስገን
ይሄ ነው ክፍያው ደግሞ ለቀጣይ ቀን🙏

@gGetem
@gGetem
@leoyri
7232a0221ee2450f159ea3f893415f10.mp4
6.6 MB
ሰላም ውድ የዚህ ቻናል ቤተሰቦች ሊያደምጡት የሚገባ ድንቅ ግጥም
ለሃሳብ አስተያየት
@yosikeman
@leoyri
ለመቀላቀል==@gGetem
@gGetem
HTML Embed Code:
2024/03/29 05:49:25
Back to Top