TG Telegram Group Link
Channel: የሆሄያት ህብር📝📝
Back to Bottom
ትወደዋለች!!!
ገጣሚ፦ ሚካኤል አስጨናቂ
አንባቢ፦ ሊዮ ማክ
የሆሄያት ህብር
#የጥበብ_ማዕድ
#ማጀቢያ፦ ሔለን ክፍሉ(ሔለና)
😍በየቀኑ አዳዲስ የግጥም ስራዎችን ለማግኘት ቤተሰብ ይሁኑ!!!
@gGetem
Comment_
@sirak6
#የሳምንቱ ገፅ🕤
#ከድንቅ አቀራረብ ጋር....😘😢
ደስታ
ሃምሳ የሚሆኑ ሰዎች ስልጠና እየወሰዱ ነው...አሰልጣኙ በመሃል ላይ ለእያንዳንዱ
ሰልጣኝ ኳስ አደላቸውና ስማቸውን እንዲጽፉበት ጠየቃቸው.....በመቀጠልም ኳሶቹ
ተሰብስበው ወደ ሌላኛው ክፍል ተቀመጡ...ከትንሽ ገለጻም በኋላ
አሰልጣኙ
"ሁላችሁም የሚቀጥለው ክፍል ውስጥ ሄዳችሁ የራሳችሁ ስም የተጻፈበትን ኳስ
በአምስት ደቂቃ ውስጥ ይዛቹ ኑ.." ሲል ጠየቃቸው
ሁሉም ክፍሉ ውስጥ መተረማመስ ጀመሩ...ነገር ግን በአምስት ደቂዎች ውስጥ ማንም
የራሱን ኳስ ማግኘት አልቻለም።
አሰልጣኙም ትርምሱን ካስቆመ በኋላ "እያንዳንዳችሁ በእጃችሁ ያገኛችሁትን የሌላ
ሰው ኳስ ለሚመለከተው ሰው መልሱለት.." ሲል ጠየቃቸው....በሚገርም ፍጥነት
ሁሉም የየራሱን ኳስ አገኘ።
አሰልጣኙም እንዲህ በማለት ምሳሌውን አጠናቀቀ
"በህይወታችንም ውስጥ እየሆነ ያለው ይሄው ነው....ሁሉም ሰው ደስታን
ይፈልጋል...የት እንዳለ ግን አያውቀውም...ነገር ግን የእኛ ደስታ የሚገኘው የሌሎች
ሰዎች ደስታ ውስጥ ነው...ደስታቸውን መልሱላቸው....የእናንተንም ደስታ ታገኛላችሁ።"
እኛም እንላለን "እውነተኛ ደስታ ማግኘት የሚቻለው የሌሎችን ደስታ በመጨመር እና
የወሰድንባቸውን ደስታ በመመለስ ነው#

መልካም ምሽት ቤተሰቦቼ🥰


                                          @gGetem
@leoyri
👧መላዬ👩
አዘጋጅ፦ጆሲ &ሊዮ
ተውኔት፦ተካ፣እድል&ማሂ(የሆሄ ልጆች)
የሆሄያት ህብር
#የጥበብ_ማዕድ
@gGetem
@leoyri
@yosikeman
👂የመድረክ ስራ
#ሸጋ_ቅዳሜ
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የጆሲ እና የሊዮ ጥምረት የታየበት
በየሆሄያት ህብር የYOUTUBE እና TIkTOK አካውንት ይጠብቁን።
#አድቬንቸር ዘውግ ያለው😲😎
@leoyri
@yosikeman
@gGetem
በቅርብ ቀን ይጠብቁን...
እጅግ አስተማሪ መልዕክት!!!
★★★★★★★★★★
ባልና ሚስት ወደ ጣልያን እየበረሩ ሳለ የአውሮፕላኑ ካፒቴን በድምፅ ማጉያ አንድ ነገር ተናገረ፦
" ክቡራንና ክቡራት ይህን ስናገር ባጣም አዝናለው። 1ኛው የአውሮፕላኑ ሞተር አይሰራም። 2ተኛውም ቆሟል። በጥቂት ደቂቃዎች ውስጥ የመከስከስ አደጋ ይደርስብናል።ጊዜው የመናዘዝ እና የይቅርታ ጊዜ ነው። ፀልዩ ንስሃ ግቡ ማስተካከል ያለባችሁን ነገር አስተካክሉ" አላቸው።

አቶ ዳኒ የሚስቱን የኤልሲን እጅ ይዞ " የኔ ማር ይቅር በይኝ። ለመናገር እጅግ ይከብዳል። ታውቂያለሽ እህትሽ ሳምራዊት ከእኛ ጋር የምትኖረው አብሬያት እተኛ ነበር። አሁንም ነፍሰ ጡር ናት። ብዙ ጊዜም አስወርዳለች። ከጣልያን ስንመለስ አንቺን በመርዝ ገድላ ወደ አሜሪካ ሄደን አብረን እንድንኖር አቅዳለች። እባክሽ ይቅር በይኝ" አላት።

ኤልሲም እንባ እየተናነቃት " ምንም ማለት አይደለም። ይቅር ብዬሃለሁ። ግን እኔም የምናዘዘው ነገር አለኝ " አለች። እርሱም የምትለውን ለመስማት አሰፈሰፈ። እንዲህም አለች "እባክህ ይቅር በለኝ? ካሉን ሦስት ልጆች መሃከል ሁለቱ ማለትም ዮሐንስና አስቴር ያንተ ልጆች አይደሉም። ያንተ ልጅ ቪክቶሪያ ብቻ ናት። የቀሩት የውድ ጓደኛህ የኤርሚያስ ናቸው። ይህ ብቻም አይደለም የኔ ማር። ታስታውሳለህ አንዴ ሌቦች አልዘረፉህም ?"
አቶ ዳኒ... "አዎ የኔ ማር አስታውሳለው"
ኤልሲ.. ...." ሌቦች እንዲዘርፉህ ያደረኩት እኔ ነኝ። ምክንያቱም ቦይ ፍሬንዴ አሌክስ የትምህርት ክፍያ አልነበረውም። የተዘረፍከውንም ገንዘብ ለእርሱ የትምህርት ክፍያ አውሎታል። ታውቃለህ ከጣልያን እንደተመለስን እኔም አንተን ለማስገደል ሰው ቀጥሬያለውና ይቅር በለኝ" አለች።

አቶ ዳኒም በሁኔታው እጅግ በጣም አዝኖ "ምንም ማለት አይደል ይቅር ብዬሻለሁ" አላት። ከቆይታዎች በኋላ ድንገት የአውሮፕላኑ ካፒቴን በድምፅ ማጉያው "እናንተ ክቡራን ተሳፋሪዎች በጣም ዕድለኞች ናችሁ። ፈጣሪ ፀሎታችሁን ሰምቷችኋል። ለማመን በሚያዳግት ሁኔታ ሁለቱም ሞተሮች በትክክል መስራት ጀምረዋል። እናም በሰላም እናርፋለን " አለ።

ሁሉም ተሳፋሪዎች ከመደሰት ይልቅ ፀጥ አሉ። አንድ ተሳፋሪ በድንገት ብድግ አለና፣ " አብራሪ ስማ ማረፍ የለብንም! አውሮፕላኑን ከስክሰው! ጣለው! ጣለው! " በማለት ሲጮህ ማንም የተቃወመው አልነበረም። ይልቁንም ሁሉም ተሳፋሪዎች በአንድ ድምፅ " ፈጥፍጠው! ከስክሰው! " በማለት ከሰውየው ሀሳብ ጋር ተባበሩ ይባላል።
★★★★★★★★★★★★★★★★★★★★
ምን ተሰማችሁ ?? ሃጥያት አስቀያሚ ነው አይደል?? መቼም እኛ ሰዎች ከዚህም የባሰ ሃጢያት እንሰራለን!! ፈጣሪ ይቅር ይበለን እንጂ! ከዚያ በፊት ግን እንዳንሰራ እሱ ያርቀን!!! የትጋ ነህ/ነሽ ሲሉን ለመናገር የምናፍርበት ቦታ አንሁን !!!!!
@leoyri
@gGetem
#አንድ_አዝማሪ_ነበር.......
.
.
ማሲንቆውን 'ሚገርፍ ስንኝ እያጀበ
የከበበው ጠጪ ብሶት ገረበበ
ሚስቱ የፈታችው ተቀበል በሚል ቃል
ብሶቱን ሲያበርደው ቤቱ ግን ይሞቃል
  
  ተቀበልልል
.
.
ሚስቴ የሰው ገፊ መሄድ ነው ሚደላት
እንደ ቀልድ ፈታችኝ አርግዢልኝ ብላት
ከጎኑ ሚገችም አንድ ቀለም ቀቢ
ደግሞ ያሽሟጥጣል ምን ጉድ ነው በረቢ
          
እሱም እንዲህ አለ

ክብር ጠለቀብን አዳም ደበዘዘ
ሄዋን በምትሰራው ወንዱ እያረገዘ
(ህመም አይደል ፅንሱ )
.
.
ስካር የጀመረው ሳይገባው ይስቃል
ከሆደ ከደረሰ ብቅል ያሳቅቃል
ከቀቢው ፊት ለፊት ስራ የፈታ ወጣት
ተበድሮ ይጠጣል ቀፋፊ ነው ማጣት
   
እሱም አቀበለ...
.
.
ሆዴን ይብሰኛል ብሶቴን ስደግመው
     እኔን መሳይ የታል
ተመረኩኝ ቢልም ትምህርት የረገመው
.
.
ትካዜን ሲያጣጥም ከእንባው ተናንቆ
ችግር ያስተጋባል ቢቸገር ማሲንቆ
ያንሳል አትልቆ!
.
እኔ እንዳለሁ አለ

አንዴ ሰካራሙን ሲልም አዝማሪውን
ስገረም ስታዘብ መከራ ሲተውን
ወጣት ሽማግሌው ቃል እየተራጨ
ስንቱ ነው ያለፈው
ባ'ለም መቅጫ እድሜው ባ'ለም 'የተቀጨ

#እኔ_እንዳለሁ_አለሁ....


@leoyri


@gGetem
@gGetem
@gGetem
ኑረት
የተፈጥሮ መገብርሽ
ህላዌያዊ ጡዘትሽ
በእኩሌታዊ እውነታ
እስትንፋስን ለዘራበት
መኖሩ ቢዳኝ በሽረት
ተዘሎ ወጣ ከኑረት።
ላየው...
ለኖረው...
ወለልሽ ጉድጓድ
በደከመው ላይ የሚናድ
ተስፋ ቢስ ጭላንጭል
ላ'ፍታ ከድካም የሚያስጠልል
ቅንጣት ቢታጣ
ያርምሽ ጀመር በብሂል
"ህይወት ብርቱ ሰልፍ ናት"
የ'ፎይታ ዳስ መዳረሻ የሌለባት፤
ሲል ይሰማል በትዝብት
ሰርክ እየሮጠ ያለ እረፍት።
፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡።።።\\\////።።።።።።
ገጣሚ፦ሊዮ ማክ
ለሌሎች ስራዎች፦ hottg.com/gGetem
@leoyri
እኔ ምልህ?
አገኘሀት?
:
ያቺን ምጥን
የሰው ምታ'ት!
.
ምናለችህ - ስታወጉ ?
ምን ብላለች ~ ስትጫወት ?
ያምና ውድህ ~ ያይንህ ውበት !
.
ትዝ ይላታል ስላለፈው ?
በዛ ቀሚስ ~ ስስ ነፍስህን ስትንጠው?


ትዝ ይላታል ~ ያንተ ሳቅህ ?
ታወሳት ወይ ~ ያ ደረትህ ?
የክንድህ ላይ ~ ንቅሳትህ
ስሟን ያተምክበት
..............ጥቁር ምልክትህ
ትዝ አላት ወይ?
ጥርስ ገላጭ ~ ለዛ ቀልድህ?

ምን ትላለች
ስለ ትናንት —-
ከንፈርህ ዳሳ - ተኩሳህ እንደ እሳት
ልብህን አድብናት…
ቀልብህን አጉናት ...
ስትነጥልህ ፦  ከሰው መንጋ
ለሌላው ጨልመህ ለርሷ ስትነጋ፤

ታወሳት ፦ ትዝ አላት?
.
ተበድረህ ለልደቷ
የአንገት ሀብል ስትገዛላት?
ለብርቋ ቀን ስትደርስላት
.
ውዴ ብላ
ተንጎማላ
ውዱ ብላ
ተገማሽራ
ስትሸጎጥ ስርህ
ተሞልታ ~ በኩራት
ከእናቷ ለጥቆ
በፍቅር ወልደሀት..
ሞገስ ሆነህ
ቅባት ሆነህ
እንደ ጣይቱ አንግሰሀት
ጓዶቿ ፊት ጌጥ ሆነሀት

እንደው ምናለችህ ?
ስታገኛት ፣ ስትቀርባት
ያቺ ምጥን
የሰው ምታ’ት?
.
ምን ብላለች ስትጫወት?
ያምና ውድህ ያይንህ ውበት !

.
ብዬ ብጠይቀው
እየተናነቀው...
.
"ሳቄ አይደል ጠረኔ
ምኑም የላት ከኔ
ይልቅ ስጠይቃት
የታወሳት የገረማት...
ከቀን መርጦ የመጣላት
የኔ ችጋር ~ የኔ ማጣት
ለዓይኗ እንኳ ጠገነንኳት ።"

ብሎ መለሰልኝ...

(ሚካኤል አ)
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
፨፨፨፨፨፨፨
፨፨፨፨፨
፨፨፨

@gGetem
@leoyri
ቅዱስ መስዋዕት
ገጣሚ፦ ሚካኤል አስጨናቂ
አንባቢ፦ ሊዮ ማክ
የሆሄያት ህብር
#የጥበብ_ማዕድ
#ማጀቢያ፦ ቤርሳቤህ 👩
😍በየቀኑ አዳዲስ የግጥም ስራዎችን ለማግኘት ቤተሰብ ይሁኑ!!!
@gGetem
Comment_
@sirak6
#የሳምንቱ ገፅ🕤
#ከድንቅ አቀራረብ ጋር....😘😢
ከወደዱት ያንሸራሽሩት (Share)
#እምነት!

(ሚካኤል አስጨናቂ)

።።።።

ከእልፍ የቀለም ቀንድ ፥ መጥሀፍ አዋቂ

አንደበተ ርቱዕ ፥ ቃላትን አርቃቂ 

ወጎች ተነጥላ.. .

ሽሙጥ ቧልታቸው ጫንቃዋ ላይ አዝላ 

መሬት የወደቀች ...

በእንባዋ ተማፅኖ ፥ ይቅር በለኝ ብላ

የእየሱስን እግር በጠጉሯ ያበሰች 

አንዲት እንስት አለች!

።።።።

ወዲያ ማዶ ግድም.. .

መጎተት አዝሎት ፥ ሰንፎ የማይለግም

አንድ አባት ይጮሀል ፥ ድምፁን አሰምቶ 

ልጄን ማራት ይላል ፥ መሲሁን ተጣርቶ

።።።። 

ደግሞ ሌላ እናት.. .

የመንጋው ሁካታ ፥ ግርግር የረታት

ደዌዋን ልታሽር ፥ በአማኑኤል ሸማ

እጇን ዘርግታለች ፥ ከጠርዝ ዳር ቆማ 

።።።።።።።

ኢየሱስ ዞር አለ !

በዛች በቀድሞ ሴት ፥ ሀፍረት ተሸብበው 

ሀጥያተኛ ሳለች ፥ ዝም ያላት ለምን ነው?

ብለው ለመጠየቅ እያጉረመረሙ

በእምነቷ መዳኗን ተናግሯቸው ሰሙ።

።።።።።።።።።።

ደግሞም ወዲያ ግድም

ልጅህ ስለሞተች መምህሩን አታድክም 

ብለው የሚመክሩ አዋቂዎች ቆመው 

ሙት ልጁ ተነስታ ጉንጮቹን ብትስመው 

እነርሱ አፈሩ ፥ ከእምነት ተናንሰው ።

።።።

ያቺም አንዲት እናት.. .

መጮህ ባትችልም ፥ ማረኝ ማረኝ ብላ 

ፊቱ ባትቆምም ፥ በግፊያ ተሽላ 

ሸማውን ስትነካ ፥ ምህረቱን ዘርግቶ

ደዌዋን ሽሮታል ፥ ስር እምነቷን አይቶ ።

።።።።

ኢየሱስ ዞር አለ !

ከስቅለቱ በፊት ፥ ከስሩ የማይርቅ 

ህጉን እያፀና ፥ ምግባሩን የሚያርቅ

የእግሩ ስር ተማሪ ቶማስ ተጠራጥሯል

መዳፉን ሊዳስስ እጆቹን ዘርግቷል

ዳሰሰ መዳፉን!

እሳት አነፈረው የዘረጋው እጁን...

ቶማስ ማረኝ አለ ፥ ዳግም ምህረት ሽቶ

ጌታችን አነፃው ፥ ይቅርታውን ሰጥቶ 

ደግሞም ለማስረጃ ፥ አንድ ሀቅታ ሊተው

ገፄን ያልዳሰሱኝ ፥ እኔን ተጠራጥረው

በቃሌ የሚያድሩ ፥ መፈተንን ትተው

ሳያዩ የሚያምኑ ፥ ብፁአኖች ናቸው

ብሎ ተናገረው !

@gGetem
@leoyri
#ከጥበብ በላይ !!
(ሚካኤል አስጨናቂ)
።።።።።።።።።።።።።።።
አጃኢብ ያረቢ!
አጃኢብ ያ ጎፍታ !
መገን ያንቺ ውበት
መገን ያንቺ ዝና...
የገላሽ ፍምነት ፥ የቁንጅናሽ ፋና
ደግሞ ተለኮሰ!
ጠዳል ብርሀንሽ ፥ ባገር ተዳረሰ።
ይኸው መጣን ደግሞ!
ጠበብት ተሰብስበን
ብዕር ተሸክመን...
ቀለማት በጥብጠን..
አንደኛው ሊፅፍሽ
ሌላኛው ሊስልሽ
ውበት ቃኙ ብለን ፥ ልናውጅ ለ'ዓለሙ
ነጋሪት ልንጎስም ፥ ስላንቺ ላልሰሙ።
እንችል ይመስል.. .
በብራና ጥራዝ ፥ በቅርፆች ማህደር
ስላንቺ መናገር!
እንችል ይመስል.. .
በሸራ ላይ ስዕል ፥ በሙዚቃ ቃና
መንገር ያንቺን ዝና!
እንዲያው ለሙከራ
እንዲያው ስለደንቡ
እንያዝ ብለን ወጉን
የገጣሚ ልኩን...
ስንኝ ልንቋጥር ፥ ሆሄያት ልንመታ
እንገልፅሽ ይመስል ፥ በቃላት ጋጋታ
እንዲያው ለሙከራ
እንይ ብለን ወጉን
የአዝማሪ ልኩን...
"ቀይ የወደደና ፥ እባብ የነደፈው"
እያልን በዜማ ፥ ውበትሽን ልንገልፀው
እንዲያው ለሙከራ
እንዲያው ስለደንቡ
እንያዝ ብለን ወጉን
የሰዓሊ ልኩን...
በውድር ሸራ ላይ ፥ ስለናታል ልንል
ገፅታሽ በቀለም ፥ ይገለፅ ይመስል
ይኸው መጣን ጠበብት!
ይኸው መጣን ሊቃን !
ሞልቶልን ባንገልፅሽ...
ሞከሯት ለመባል ፥ የፈጠረሽ ያብቃን ።
አሜን 🙏
@gGetem
@leoyri
ሐረግ የወረረው የህንፃ ቅሪት ሳይ

(በእውቀቱ ስዩም)

ሐረግ የወረረው የህንፃ ቅሪት ሳይ
አንቺን አስባለሁ
የረገፈ ቅጠል፤ ከትልልቅ ዛፍ ላይ
አንቺን ያሳስባል
እኮ ለምን ቢባል
ምናቃለሁ እንጃ
ያለ ሰበብ ማሰብ ፤ የመለከፍ ፍርጃ

ግን ብፈልግ አጣሁ ያለ ሰበብ መርሻ
ትዝታሽ ወጌሻ
ሳይጠሩት የመጣ
ያለ ማደንዘዣ ራስ የሚበጣ
ልብን እንደ ሙዳይ  ከፍቶ የሚገጥም
ብቻ
ላያስችል አይሰጥም!

ግንቡን አስረጅቶ ለሀረግ አውርሶ
ከትልቁ ዛፍ ላይ ቅጠሉን አፍልሶ
የሰጠውን ወስዶ ዘመኑ፤ ይነጉዳል
ብቻ
ባይድን ወይ ባይገድል ፤ ህመም ይለመዳል
@gGetem
@gGetem
ብቸኝነት  (በድሉ ዋቅጅራ)

እልፍኝህ እንዳʽብርሀም ቤት፣
አደባባይህ እንደጥምቀት፤
የሰው አሸን ቢወረው፣ ጠጠር መጣያ ቢገድም፤
ለመሀላህ ካስማ ʽሚሆን፣ ሲያነቅፍህ የምʽጠራው ስም፤
ከልቦናህ ሲነጥፍ፣ አንደበትህን ሲያንቀው፤
ብቻህን ነህ፣ ያኔ እወቀው፡፡

-----------
@gGetem
@leoyri
መጅ ደባቂ
(ሚካኤል አስጨናቂ)
.
መንገድ ለማበጀት መሬት ለሚንዱ
በሚንዱት መሬት ፍጥረት ለማገዱ
ፍጥረቱ ሲማገድ ታዝበው የሚያልፉ
ከመታዘብ ልቀው ለጩኸት ሰነፉ።
።።
እነርሱ.. .
ለጩኸት ሲሰንፉ
ዘመንን ሲገፉ
በሚገፉት ዘመን
ተስፋን እየቋጩ
ራዕይ ሲያጠፉ
በዝምታ ለምድ ውስጥ
አብዮት ሲጠልፉ
.
ተመልክተን ነበር ዓይናችን ተገልጦ
ከገቢረ ስጋ.. .
የነፍሳችን ቆቡ ከፍ እንዲል ተመርጦ።
።።።
እኛም.. .
ለጩኸት ስንከንፍ
የተገፋን ዘመን
ጎትተን ልናቀርብ
በጊዜ ባህር ላይ
ልንሻገር ስንቀዝፍ
.
ከሰውኛ ላንሸሽ
ላንመስል ቀንዳውጣ
ሲጮህ ተሸሽገን
ሲበርድ ላንወጣ
.
ለመከነ ራዕይ
ለከሰመ ተስፋ
ሲበርድ አጉረምርሞ
ሲጮህ ለሚጠፋ
.
ቀድሞውኑ ለራደ
ሙቁ ለበረደ
ታሪክን ሊገርፍ
እብለት ለገመደ
.
ያንን ሀሞት አልባ ፥ ደርሰን ለማታከት
በቀደደው ሱሪ.. .
ዙሪያ እየጠቀምን ልጣፍ ስንጥልበት
።።።
ሌሎች!
ከሚምሱት ምድር ፍጥረት ሊማግዱ
መንገድ ለማበጀት መሬት ስለናዱ
ቦላሌ ተርትረው እርቃን ስለሄዱ
.
የእነርሱን ቀዳዳ ለመጥቀም ስንታትር
ቱባ እያፍታቱ እንደማቀበር ክር
ፋሽን ናቁ ብለው.. .
ቁልቁል ወረወሩን ከሚምሱት ምድር ።
@gGetem
@leoyri
እሱ ነው - እሱ!
(ደበበ ሰይፉ)
።።።
እሱ ነው ~ እሱ
ዐይን ባይኖረው
ለምን ብርሀን ኖረ? የሚለው
እግር ባይኖረው
ለምን መንገድ ኖረ? የሚለው
.
እሱ ነው ~ እሱ
ከቀናቴ
ፀሀይቱን የሰረቀ
በመንገዴ
አሜኬላ ያፀደቀ።
@gGetem
@leoyri
ያለ ጥላ ልቁም!!!
ገጣሚ፦ ሚካኤል አስጨናቂ
አንባቢ፦ ሊዮ ማክ
የሆሄያት ህብር
#የጥበብ_ማዕድ
#ማጀቢያ፦ ቤርሳቤህ 👩
😍በየቀኑ አዳዲስ የግጥም ስራዎችን ለማግኘት ቤተሰብ ይሁኑ!!!
@gGetem
Comment_
@sirak6
#እኔ_አክሱምን_ልሁን !!!!
#ሰንበታት😍
#ከድንቅ አቀራረብ ጋር...
ከወደዱት ያንሸራሽሩት (Share)
ከአምስት አራት ኪሎ አንድ ሺህ እርምጃ ነው
(ሰለሞን ሳህለ ትዕዛዙ)

ሁሌም ቀኑ ሲመሽ እንዲህ ወደ ማታ
ስካርን አግብቼ
ባገኘሁት መጠጥ ራሴን ሞልቼ
በቀዝቃዛው ሌሊት እራፊ ለብሼ
ብርድ ያስጥል ይመስል ሲጋራ ለኩሼ
በአምስት ኪሎ መንገድ
አራት ኪሎድረስ
እመላለሳለሁ
እርምጃ ‘ቆጥራለሁ
ደ‘ሞ ቆም እላለሁ
እሷን አስባለሁ

"አንቺ ልጅ አንቺ ልጅ
አንቺ ልጅ አንቺዬ
ሰመመን የሆነን ናፍቆትሽን አዝዬ
ከአምስት አራትኪሎ እመላለሳለሁ
መፍትሄው ምን ይሆን ይሄን ካንቺ እሻለሁ"
ደግሞ እንዲህ እልና እሷን አስባለሁ

በቀደም ሶስት ሆነው ትናንት አራት ሆነው
የምወዳትን ልጅ ከመሃል አጅበው
በዚህ ነው ያለፉ
አሁን እዚህ የሉም…
ጭር ብሏል ጎዳናው…
በረንዳ አዳሪዎች
የጎዳና ውሾች
ማጅራት መቺዎች ሁሉም እዚህ የሉም
እምጥ ይግቡ ስምጥ ይግቡ ማንም አላወቀም
ማንም አልጠየቀም

ጭር ብሏል ጎዳናው…
ጭርር ብሏል ጎዳናው!
እንጀራ ፈላጊ ሹፌር የሚነዳው
ላዳ ታክሲ ብቻ ሽውው ይላል እንዳሻው
የሹፌሩም የኔ የሁለታችን መንገድ ትርጉሙ ልዩ ነው

እርሱ እንጀራ ብሎ እኔ ፍቅሬን ብዬ
እመላለሳለሁ
የሄደችበትን መንገድ ተከትዬ

ይመስክር ጎዳናው
የስካር እርምጃን ስንት‘ግዜ እንደቆጠርኩ
ይመስክር ጎዳናው
የቆመችበት ጋር ስንት ቀን እንደቆምኩ

እዚህ ቦታ ነበር
ድህረ— ምረቃ ውቅያኖስ ፊትለፊት
ሳቂ ጓደኛዋ አንድ ቀልድ ነግራት
ስትስቅ የነበረው
እዚህ ቦታ ነበር
ጥቁር ጓደኛዋ በሳቋዋ የሳቀው

ወይኔ ሳቋ ደግሞ
መለዓክት ስመውት
ስመው አውግተውት ፍልቅልቅ እንደሚል
የስድስት ወር ጨቅላ
ይህን ሳቅ እኮ ነው ያፈራ ይመስል
እልቤ ላይ ተክላ
ቀልቤን የነሳቺኝ በሳቅ እኔን ገድላ

ወይኔ ሳቋ!
አሁን በዚህ ሰዓት…
ቀጭን ጓደኛዋን በስካር ደፍሬ
ደውዬ ላናግራት?
ቀልዱን ድገሚልኝ ባክሽ እኔም ልሳቅ
ብዬ ልለምናት?

ሳቋን እያሰብኩኝ
ቆሜያለሁ በብርዱ ቆሜያለሁ በሌሊት
ድህረ— ምረቃ ውቅያኖስ ፊትለፊት

መቆሜን እንዳየ ላዳ ታክሲ መጣ
ጠየቀኝ ኮንትራት
እባክህን ሹፌር ምንድነው ኮንትራት?
ይልቅ እሱን ትተህ
የምወዳትን ልጅ የትም ቦታ ሂደህ ለኔ ብለህ አምጣት!?

ይህ የላዳ ሹፌር እንጀራ ፈላጊው
ስካሬን 'ረስቶ እብደቴን እንዳየው
ከንፈሩን መጥጦልኝ ሄደ ባለታክሲው

ውይ ከንፈሯ ደግሞ!
አንድ የዋህ አፍቃሪ በእሷ ፍቅር ታምሞ
ወድያው ነው የሚድን በከንፈር ተስሞ
ስም የለሽ ከንፈሯን ባ‘ሳቤ እየሳልኩኝ
ያለቀ ሲጋራ ጥዬ እየለኮስኩኝ
በስካር እርምጃ መንገዱን ቀጠልኩኝ

ከአምስት አራት ኪሎ አንድ ሺህ እርምጃ ነው
‘ሚወዱትን ማጣት ግን ምን የሚሉት እርግማን ነው?

በቀደም እሮብ‘ለት
ሙዚየሙ ፊትለፊት
ለአንድ የኔቢጤ መፅውታው ነበረ
ምነው እርሱን በሆንኩ
በአስማተኛ ዓይኖቿ እንደዘበት አይታ
በሳንቲሙ ፈንታ መፅውታኝ ፈገግታ
ምነው ድኜ ባደርኩ የዛኑ‘ለት ማታ!

ዓይኗ ያው ዓይን ነው ከዓይን የተለየ
ከብርሃን ጎልቶ ወግቶ ያሰቃየ
"ወይ ተዓምር!" ይላል ሰው እንደኔ ያላየ
ወይ ተዓምር!!

በዓይኗ በከንፈሯ በሳቋ ሰክሬ
በፍቅር በናፍቆት በመጠጥ ሰክሬ
ክዋክብት የፃፉት የሕይወት መስመሬ
እንዲህ ነው የሚለው ዕጣ ፈንታ ክፍሌ?
ይህ ነው ክፉ እድሌ?

ወይኔ!
ደግሞ…
እኔ እሷን እንዳልሳለም በቃል እየደለለች
በዓይኗ እያሳመመች
በሳቅ እየገደለች
እሷ ግን እዚህ ስትመጣ
ማርያምን ትሳለማለች!

እኔም እሳለማለሁ መሳለም አይበለውና
በሷ ፍቅር ተጸብዬ አገኝ እንደው ብፅዕና

እና…
የሰከረ ሰው ጸሎት ተሰማ ሲባል ባልሰማም
እኔ ግን እጸልያለሁ ተሰምቶ የማያውቅ ጸሎት
እግዜሩ ጸሎቴን ሰምቶ ለ‘ኔ ለአፍቃሪው ቢያመጣት

"አባት ሆይ...
እንድወድዳት ፈቅደህልኝ
የወደዱትን አለማግኘት እንደምን ያለ ፍትህ ነው?
ኧረ በማርያም የማርያም ልጅ
እንዲሆን እንዲሆን አርገው?
እሷንም ምንድነው በላት የ‘ኔንም ልብ አጠንክረው
በስካርና በሲጋራ ተቃጥዬ‘ኮ ልሞት ነው!
አገልጋይህ ያንተ ባርያ የምለምንህ እንዲህ ነው
ታውቃለህ የ‘ኔን ሁኔታ ታውቃለህ የልቤን ሚስጥር
ድምፅ የለኝ እንዳላወድስ ቃል የለኝ እንዳልናገር
እኔ እንደሁ ብኩን ምስኪን ነኝ በፍቅር የምቸጋገር!?"

እንዲህ እላለሁ… እንዲያ እላለሁ
ከዚያም እንደገና እሷን አስባለሁ
ያለቀ ሲጋራ ጥዬ አዲስ እለኩሳለሁ
በስካር እርምጃ ቁልቁል እወርዳለሁ
ገጣሚ
ሰዓሊ
አፍቃሪ
ቆማሪ
የሚቃጠሩበት ሮሚና ካፌን
ማለዳን አልፌ
ጆሊ ባር አጠገብ ባ‘ዘን እደርሳለሁ
ፍቅር ያሳመመው
መጠጥ ያሰከረው
ስካር ያደከመው እኔን አገኛለሁ

በዛ በውድቅት ሌሊት ሚኒባስ ታክሲ ባይኖርም
ድምፅ ግን ይሰማል
ረዳት  ይጮኻል
"ሜክሲኮ ሜክሲኮ? አንድ ሰው ሜክሲኮ?"
እያለ ይጣራል
በዛ ውድቅት ሌሊት በሌለ ሚኒባስ
እኔ ግን አያለሁ
እሷ ስትገባ እመለከታለሁ
ሚኒባስ ይሄዳል እኔ እመለሳለሁ
አንቺ ሆዬ እያልኩኝ አንጎራጉራለሁ

"አንቺ ልጅ አንቺ ልጅ
አንቺ ልጅ አንቺዬ
ሰመመን የሆነ ናፍቆትሽን አዝዬ
ከአምስት አራት ኪሎ እመላለሳለሁ
መፍትሄው ምን ይሆን?
ይህን ካንቺ እሻለሁ!"
ከአምስት አራት ኪሎ
አንድ ሺህ እርምጃ ነው
የሚወዱትን አለማግኘት
ምን የሚሉት እርግማን ነው?!
@leoyri
@gGetem
እንግጫ ጎዝጉዘን
በአሪቲው ቃና ጎጆዋችንን ሞልተን
ከባንክ እንደወጣ ወርቃማ ፈራንካ
የተዋበች ጠሀይ ታዛችን ስር ሞቀን፤
በአዲስ መሻት አዲስ ተስፋ...
የህይወት ወስከንባ ጀምረን ልንሰፋ
በወስፌ ቀዳዶች አክርማ እየዶልን
በአለላ ቆለምሸሽ ሊቀርብ እንጀራችን
ጀመርን መወጠን ዛሬ በዋዜማው
"ከህልማችሁ በፊት ሀገርን አብጁ"
የሚለውን ነብይ የለም የሚሰማው !
ነብዩ ይጮሀል አደባባይ ቆሞ
ዙሪያ ገባው ሁሉ ተሞልቷል ባታሞ
ድው ነው!      ድው.. .ድው
ድም ነው!       ድም.. .ድም
ወዲያም ሲማትሩ ወደዚህም ግድም።
አንዳንዱ ሲደክር...
ለአዲሱ ተስፋ ... ትከሻውን ሰብቆ
አንዳንዱ ያለቅሳል.. .በጦር መንደር ወድቆ።
"ኸረ ይቆይ መጨፈር.. . ይቅር ይሄ እስክስታ
ሀገር ካልተሰራ ... ቅርብ ላይ ነው ዋይታ
ግዴየለም.. .
ግድየለም.. .
ይደርሳል ዘፈኑ ... ይደርሳል ጭፈራ
እርቅን አስቀድሙ.. . ይቅር አታካራ
እዚህ ደጅ ቄጠማ.. .እዛ ማዶ ጅማት
እዚህ ማዶ ውስኪ... እዛ የደም መዓት
በሆነበት ቀዬ ... በሆነበት መንደር
በለቅሶ ውስጥ ዘፈን ... እንባ ላይ መጨፈር
እንዲህ ባለ ነገር ...
ህልም አይታለምም ... ተስፋም አይሳካም "
ብሎ የሚጮህን ያ ስጉ ፈላስፋ
አልነው  'አይነፋም' !!
በአዲስ ቀን ለአዲስ ህልም
ድም.. . ድም
ነብይ አናከብርም።

@gGetem
hottg.com/gGetem
የዘመነኛው ኑዛዜ!!

(ሚካኤል አስጨናቂ)

።።።።።

እንኳን አንተ አባቴ!

ጨለማው ምናብ ላይ ~ ፋኖስን ለኩሰህ

ከመሀል እስከ ጫፍ ~ የዞርከው ጀግነህ

ሀገርን በሌማት.. .

ለመቋደሻችን ~ ዘርግተህ የሰጠህ

ስንቱ ታሪክ አባሽ

ስንቱ አዳም አስለቃሽ

ገሀዱ እውነታው ~ ሀቅታው ታብሎ

ሀውልቱ ይቆማል.. .

ኧኸተማ መሀል ~ ዠግና ነው ተብሎ።

።።።።

እምዬ ሚኒልክ

የፅናታችን ልክ

ሀላፊ አግዳሚው ~ ታሪክህን ቢሰማ

አረሙን መንግሎ...

የባርነትን ጥግ ~ የሀሳቡን ጥሻ ~ መንጥሮ ቢያለማ

ለባንዳ ህመም ሆነህ ~ መቅደሱ ፊትለፊት ~ ቁምልን በግርማ።

።።።።

ቁምልን አባቴ!

በአክሊል አጊጥህ ~ ተውበህ በካባ

ልጓምህን አንቀህ ~ ኸፈረስህ ጀርባ

ማነው? ብለው ሲሉን ~ ንጉስ ነው እንድንል

ሸማችን ሲሳሳ...

ሀገር እንዳይበርዳት ~ ታሪክ እንድንፈትል

ወኔያችን ሲላላ...

ዳግም ዘራፍ ብለን ~ በስምህ እንድንምል

በዓለም ጎዳና ላይ...

ግዞተኛ ሆነን ~ እንዳንቆርጥ ተስፋ

ለምልክት ቆመህ...

የአርነት መለከት ~ በኩራት ይነፋ ።
@leoyri
hottg.com/gGetem
#ከምኞት_ባሻገር
የምስኪን አፍቃሪዋ ተግሳፅ..
         (በሊዮሪ)

ተመልክቼህ በሸራፋ ቀኔ
ቢሰወረር እኔነቴ
ጀመርኩ
ምኞቴን እየመዘንኩ!!!!!
ላልፈታ ገባው ከፍቅርህ ሉጋም፤
አሰሳዬ እጥግ ደርሶ ብደክም።

  እንደ መንገደኛ...

በ'ይታ ሰርጌ ከባህሩ እንብርት፤
አድማስ አልፎ አይኔ አንተ ባትኖርበት።
ቀለሜን አፍስሼ ብሩሹን ሰቀልኩት!!!!!!

እንደ ሰዓሊ...

ዜማ ስደረድር ከቅኔ 'የወጣው
የግጥሜ ድምፀት ጥል ሆኖ__ ቤቴንም ቢያፈርሰው፤
ብኩን እንጉርጉሮዬ አውንታሩን በጠሰው!!!!!!

እንደ አዝማሪ....

ከሌላኛው የነብስ ዋጋ ከሚታፈስበት፤
ሰማይን ዘወትር በአይኖቼ ዳስሴ ከማማትርበት።
አንተ ካለህበት ከስምህ ጉባዬ፤
ልቤ መልስን ሽቶ ከተመ ሱባዬ።
ናፍቆት  የከለለው ከፍቅርህ ገዳሜ፤
ልታቀብ ወሰንኩኝ ሲገባኝ ከርሜ።

በዚም...

ደግሞ እንደመናኝ....
ላንተ ካልታደልኩኝ አለም ሙሉ በቃኝ።

በቃኝ!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!
ሊዮሪ
21/12/2013ዓ.ም
የሆሄያት ህብር🦋🦋🦋🦋
#የጥበብ_ማዕድ
🦋🦋🦋🦋
@leoyri
@gGetem
@gGetem
HTML Embed Code:
2024/04/29 03:11:18
Back to Top