Channel: Fuad Muna (Fuya)
አልሀምዱሊላህ!
.
በፉአድ ሙና ቻናል ቤተሰቦች ስም ለኢፋዳ ኢስላማዊ ድርጅት የአንድ የውሀ ጉድጓድ ገንዘብ አሰባስበን የነበረ መሆኑ ይታወቃል። የውሀ ጉድጓዳችን በጉራጌ ዞን ጉመር ወረዳ አርሟ ቀበሌ ቆቶ መንደር ቁፋሮው ተጀምሮ ውሀ ተገኝቷል። አልሀምዱሊላህ!
ኢንሻአላህ ግንባታው ለውጥ ሲኖረው ከቦታው የሚላኩልኝን መረጃዎች አደርሳችኋለሁ።
አንድ ላይ ችለናል። አልሀምዱሊላህ!
.
@Fuadmu

የመጨረሻዎቹ መፅሀፍት
ኢፋዳ መፅሀፍ እኛ ጋ አልቋል። በፒካፕ ሎኬሽኖቻችን ጥቂት መፅሀፎች ቀርተዋል። @ifadasales ላይ ጎራ በሉና የእትሙን የመጨረሻ መፅሀፍ የራሳችሁ አድርጉ!
ኢፋዳን ግዙ!
.
@Fuadmu
ኢፋዳ መፅሀፍ እኛ ጋ አልቋል። በፒካፕ ሎኬሽኖቻችን ጥቂት መፅሀፎች ቀርተዋል። @ifadasales ላይ ጎራ በሉና የእትሙን የመጨረሻ መፅሀፍ የራሳችሁ አድርጉ!
ኢፋዳን ግዙ!
.
@Fuadmu
እሷ
(ፉአድ ሙና)
.
ይፈሳል እንባዋ ፣ ትማፀነዋለች ሀዘን ተቀልፃ፣
"ወዴት ነው ‘ምትሄደው?" ትጠይቀዋለች ድንጋጤ ለብሳ።
አይመልስም እርሱ ፣ የያዘው ይዞታል ፣ ቃል አይወጣም ከአፉ፣
"ለማን ነው ‘ምትተወን?" አታውራ ቢለው ነው ለመልስ መስነፉ።
በአስፈሪ በረሀ ፣ ጡት ያልጣለን ህፃን የሚያስተው ጭካኔ፣
ታሰላስላለች ፣ ከየት አመጣ ወኔ?
"አላህ ነው ያዘዘህ?" አይኖቿ ዋተቱ ምላሹን ፍለጋ፣
"አዎ" ሲል መለሰ ፣ ልቧ ተረጋጋ!
"እርሱማ ከሆነ ጥሎ አይጥለንም!" ስትል ተናገረች በኢማን ተውባ፣
የአላህ እርዳታ እንደሚደርስላት በፅኑ አስባ።
.
ትቷቸው ሲመለስ
ልቡን ሊያረጋጋ ፣ ጌታውን ለመነ እጆቹን ዘርግቶ፣
በልጁ ስቅይት ፣ በሚስቱ ተማፅኖ አንጀቱ ተበልቶ።
"ጌታችን ሆይ!
ከቤትህ አቅራቢያ ፣ አንተን ይገዙ ዘንድ፣
አዝመራ ከሌለው ፣ ከሸለቆው ንዳድ፣
ትዕዛዝህን ብዬ ፣ ዘሮቼን አስቀመጥኩ፣
ፍላጎቴን ገደብኩ ፣ መሻትህን ፈፀምኩ።
ጌታችን ሆይ!
የሰዎችህን ልብ ፣ አስናፍቅ ወደነርሱ፣
ከፍሬህ ስጣቸው ፣ ያመስግኑህ ለሱ።
ጌታችን ሆይ!
ድብቁን ታውቃለህ ፣ የምንሰውረውን፣
ተለየሁ ከእነርሱ ፣ ጌታዬ አደራህን!"
.
ከሄደ በኋላ
ስንቋም ተራገፈ ፣ ውሀም ለአመል ጠፋ፣
ጥሙ ጠበሳቸው ፣ ረሀቡም ከፋ።
ስትሮጥ ከጋራው ላይ ፣ ሶፋና መርዋን ስትመላለሰው፣
ቃሏን አሟላላት ፣ ቃሉን የማይጥሰው።
በመልዓኩ ክንፍ ፣ ሲቆፈር አፈሩ፣
"ዙሚ ዙሚ" አሰኛት ፣ ቀናላት ነገሩ።
"ጥሎ አይጥለንም!" ተወዶ እምነቷ፣
ለዓለም ፈውስ ሆነ ፣ ሀጀር ትሩፋቷ።

ንግስት
(ፉአድ ሙና)
.
ከበረሀ መሀል
እንዳለች፣ አንዲት ዛፍ፣
ብርቅነቷ በዝቶ
በድርሳናት ሁሉ፣ ታሪኳ እንደሚፃፍ፣
ከድርቅ በኋላ
ህይወት እንደሚያበስር፣ የዝናብ ጠብታ፣
የናፈቀው ሁሉ
እንደሚያለቅስለት፣ በጠዋት በማታ፣
ከወንጀል በኋላ
ማርታን እንደመልበስ፣ በአላህ ይቅርታ፣
ከአፋፍ እንደመትረፍ
ህያው እንደመሆን፣ ሞት የጠራ ለታ፣
ከዚህም ብዙ ብዙ
ትልቂያለሽ ለኔ፣ ቃል የለውም ወስፉ፣
በሞተ ልቤ ላይ
በፍቅርሽ ተዓምር፣ ህይወት መንሳፈፉ።
ፍቅር አልባ እኔን
በሳቅ በቁምነገር፣ የማረክሽው ለታ፣
ሰቀቀኔ አባራ፣
የታረዘ ነፍሴን፣ አለበስሽው ደስታ።
ይኑርልኝ ጥርስሽ
በፈገግታው ጨረር፣ ሀዘን የሚያስረሳ፣
የሞተ ስሜትን
የታመመ ገላን፣ አክሞ `ሚያስነሳ።
አጀብ ውብ አይኖችሽ
ትክ ያልሽብኝ ለታ፣ ይነዝረዋል ነብሴ፣
ሁሌም ይደንቀኛል
በሁረልአይን አይኖች፣ ሳልሞት መጠቀሴ።
ተክቢር ለትንፋሽሽ
እንደ ዘምዘም ውሀ፣ ተናፍቆ ተጠጪ፣
ልብ ፈታይ ሙቀት
በተማገ ቁጥር፣ አዲስ ስሜት ሰጪ።
ስሜሽ እንኳን ባላውቅ
አይቼ አይጠፋኝም፣ የጀነት ጣዕሙ፣
ዱነዊይ አይደለም
የጥፍጥናው ልኬት፣ የከንፈርሽ ስሙ።
ዘርዝሬ አልችለውም
የደዌ ፈውስ ነው፣ አንቺነትሽ ሁሉ፣
ውብ ነሽ አይገልፀውም
ላንቺ ይልፈሰፈሳል፣ አይችለውም ቃሉ።
እናልሽ ስስቴ
ሀውልት አልቀርፅልሽ፣ ሀራም ነው ድርጊቱ፣
በይ ጉዴን ልንገርሽ
ንጋ ብለው አይሰማም፣ ስትቀጥሪኝ ለሊቱ።
የኔ የብቻዬ...
የልቤ መርጊያ ነሽ
እሱን እወቂልኝ፣ አትዘንጊ ለአፍታ፣
በዱዓ አግዢኝ
በአንድ ጎጆ እንድናድር፣ የማታ የማታ።
መጨረስ ከበደኝ
በልክሽ አይደለም፣ ውዳሴዬ ላንቺ፣
አደራሽን ውዴ
እኔ አፈቅርሻለሁ፣ እኔን መውደድ በርቺ።
እኔን ብቻ!
.
@Fuadmu
(ፉአድ ሙና)
.
ከበረሀ መሀል
እንዳለች፣ አንዲት ዛፍ፣
ብርቅነቷ በዝቶ
በድርሳናት ሁሉ፣ ታሪኳ እንደሚፃፍ፣
ከድርቅ በኋላ
ህይወት እንደሚያበስር፣ የዝናብ ጠብታ፣
የናፈቀው ሁሉ
እንደሚያለቅስለት፣ በጠዋት በማታ፣
ከወንጀል በኋላ
ማርታን እንደመልበስ፣ በአላህ ይቅርታ፣
ከአፋፍ እንደመትረፍ
ህያው እንደመሆን፣ ሞት የጠራ ለታ፣
ከዚህም ብዙ ብዙ
ትልቂያለሽ ለኔ፣ ቃል የለውም ወስፉ፣
በሞተ ልቤ ላይ
በፍቅርሽ ተዓምር፣ ህይወት መንሳፈፉ።
ፍቅር አልባ እኔን
በሳቅ በቁምነገር፣ የማረክሽው ለታ፣
ሰቀቀኔ አባራ፣
የታረዘ ነፍሴን፣ አለበስሽው ደስታ።
ይኑርልኝ ጥርስሽ
በፈገግታው ጨረር፣ ሀዘን የሚያስረሳ፣
የሞተ ስሜትን
የታመመ ገላን፣ አክሞ `ሚያስነሳ።
አጀብ ውብ አይኖችሽ
ትክ ያልሽብኝ ለታ፣ ይነዝረዋል ነብሴ፣
ሁሌም ይደንቀኛል
በሁረልአይን አይኖች፣ ሳልሞት መጠቀሴ።
ተክቢር ለትንፋሽሽ
እንደ ዘምዘም ውሀ፣ ተናፍቆ ተጠጪ፣
ልብ ፈታይ ሙቀት
በተማገ ቁጥር፣ አዲስ ስሜት ሰጪ።
ስሜሽ እንኳን ባላውቅ
አይቼ አይጠፋኝም፣ የጀነት ጣዕሙ፣
ዱነዊይ አይደለም
የጥፍጥናው ልኬት፣ የከንፈርሽ ስሙ።
ዘርዝሬ አልችለውም
የደዌ ፈውስ ነው፣ አንቺነትሽ ሁሉ፣
ውብ ነሽ አይገልፀውም
ላንቺ ይልፈሰፈሳል፣ አይችለውም ቃሉ።
እናልሽ ስስቴ
ሀውልት አልቀርፅልሽ፣ ሀራም ነው ድርጊቱ፣
በይ ጉዴን ልንገርሽ
ንጋ ብለው አይሰማም፣ ስትቀጥሪኝ ለሊቱ።
የኔ የብቻዬ...
የልቤ መርጊያ ነሽ
እሱን እወቂልኝ፣ አትዘንጊ ለአፍታ፣
በዱዓ አግዢኝ
በአንድ ጎጆ እንድናድር፣ የማታ የማታ።
መጨረስ ከበደኝ
በልክሽ አይደለም፣ ውዳሴዬ ላንቺ፣
አደራሽን ውዴ
እኔ አፈቅርሻለሁ፣ እኔን መውደድ በርቺ።
እኔን ብቻ!
.
@Fuadmu
ክፍት የስራ ቦታ
የስራ መደብ: ‐ ፀሀፊ
የስራ ቦታ: ‐ ታጠቅ
ተፈላጊ ችሎታ: ‐ አማርኛና ኦሮምኛ መፃፍ የምትችል
ደመወዝ: ‐ በስምምነት
መስፈርቱም የምታሟሉ @step7352 ላይ ያናግሩን!
የስራ መደብ: ‐ ፀሀፊ
የስራ ቦታ: ‐ ታጠቅ
ተፈላጊ ችሎታ: ‐ አማርኛና ኦሮምኛ መፃፍ የምትችል
ደመወዝ: ‐ በስምምነት
መስፈርቱም የምታሟሉ @step7352 ላይ ያናግሩን!
የአምስተኛ አመት የኮሌጅ ተማሪ ናት
ትምህርት የጀመረችው በ2012 ነው። ከ18 አመት በላይ አልጋ ላይ የቀረችባትን እናቷን ለማስታመም እንዲሁም ባሉባት የተለያዩ ችግሮች ትምህርቷን አቋረጠች። ነገሮች የተሻሉ ሲመስሏት ያቆመችውን ትምህርት በ2013 ቀጠለች የራሷ እና የእናቷ ህመም ግን ትምህርቷን ባሰበችው መልኩ ከመከታተል አገዳት።
ያን ሁሉ ህመም ያን ሁሉ መከራ አልፋ ብዙ መስዋትነትን ከፍላ የምርቃቷን ቀን በጉጉት ስትጠብቅ እናቷን እንዲሁም እራሷን ስታስታምም የቀረችባቸው ኮርሶች ከ 15 በላይ እንደሆኑና የእነሱን ክፍያ መፈፀም የማትችል ከሆነ በዚ አመት መመረቅ እንደማትችል ይነገራታል።
አብረዋት የሚማሩ ልጆች ከሁለት ወር በኋላ እንደሚመረቁ አውቀው ሽር ጉድ ሲሉ እሷ ግን...........
ያሉባትን ኮርሶች add ለማድረግ ከ 16,000 ብር በላይ ያስፈልጋታል። አጠቃላይ ትምህርቱ የሚፈጀው 5 አመት ነው። በዚ አመት መመረቅ ካልቻለች 7 አመት ይወስድባታል።
አላህ ያገራላችሁን ያህል አግዟት!
ልጅቷን ማገዝ የምትፈልጉ @fuadmuna ላይ አካውንቷን መውሰድ ትችላላችሁ።
.
@Fuadmuna

ኢፋዳን ቅናሹ ሳይጠናቀቅ ይግዙ!
ኢፋዳ @ifadasales ላይ በመቶ ብር ቅናሽ 400 ብር ትሸጣለች።
መፅሀፉ የት የት አለ?
● አዲስ አበባ
● ሀዋሳ
● ጅማ
● ሻሸመኔ
● አዳማ
@ifadasales ላይ በመሸመት ባሉበት ከተማ መፅሀፉን ይረከቡ!
ፈጥናችሁ እድሉን ተጠቀሙ!
.
@Ifadasales
ኢፋዳ @ifadasales ላይ በመቶ ብር ቅናሽ 400 ብር ትሸጣለች።
መፅሀፉ የት የት አለ?
● አዲስ አበባ
● ሀዋሳ
● ጅማ
● ሻሸመኔ
● አዳማ
@ifadasales ላይ በመሸመት ባሉበት ከተማ መፅሀፉን ይረከቡ!
ፈጥናችሁ እድሉን ተጠቀሙ!
.
@Ifadasales
የመጨረሻ ዕድል!
ኢፋዳን ቅናሹ ሳይጠናቀቅ ይግዙ!
ኢፋዳ @ifadasales ላይ በመቶ ብር ቅናሽ 400 ብር ትሸጣለች።
መፅሀፉ የት የት አለ?
@ifadasales ላይ በመሸመት ባሉበት ከተማ መፅሀፉን ይረከቡ!
ፈጥናችሁ እድሉን ተጠቀሙ!
.
@Ifadasales
ኢፋዳን ቅናሹ ሳይጠናቀቅ ይግዙ!
ኢፋዳ @ifadasales ላይ በመቶ ብር ቅናሽ 400 ብር ትሸጣለች።
መፅሀፉ የት የት አለ?
@ifadasales ላይ በመሸመት ባሉበት ከተማ መፅሀፉን ይረከቡ!
ፈጥናችሁ እድሉን ተጠቀሙ!
.
@Ifadasales
HTML Embed Code: