TG Telegram Group Link
Channel: ፍቅር እና ጠበሳ
Back to Bottom
ድምፅዋ ብቻውን - የመኖር ሰበብ
ሳቋ ቢሰላ - የአመታት ቀለብ
ወተት ይፈሳል ጥርሷ ቢታለብ ።

አጀብ !

ውይ ከንፈሯ ሲያምር !
የደጋ ዐሰል ፥ የበርሃ ቴምር ።

መዐዛ ወዟ የአደስ የአሪቲ
አምራ 'ምትታይ በድሪያ ሺቲ
ዑመተ ፈናን ፥ ዑመተ ቀሽቲ ።

ርግብ አይነ-ርግብ ፥ ልበ ስግብግብ
ወዳ 'ማትሰለች ፥ ወዳ 'ማትጠግብ ።

አዛኝ አንጀቷ ከማርያም ባይልቅ
በእጇ እየሰጠች በአይኗ ምትመርቅ
ትሁት ናት ፃድቅ ።

መጻተኛው ሊቅ በቀን በፋኖስ ያፈላለጋት
የሰው ልጅ ትርጉም ፥ የሰው ልጅ ንጋት
ጎልታ ባትታይ የማያሰጋት
የአበባ ስር ናት ።

የነፍስ ቅኔ ፥ የምታዳግት ለቃል ለምናብ
የልብ መዝሙር ፥ የአዕምሮ ተዐብ
ኧረ በስመአብ !


@fonkabcha1
@fonkabcha1
ከነበብሁት ላካፍላችሁ 🥰👇

የደራሲ ቅጣት…

የሆነ ሰውዬ ይሞትና ገነትንም፣ ሲዖልንም ይጎበኛል። ገነት ሲደርስ በጎ ምግባሮች እንደቀጠሉ ናቸው። መልካም ሰርተው የፀደቁትንም አስተዋለ። ይልቅ የገረመው አንዲት ዛፍ ስር ቁጭ ብሎ የሚፅፍ ሰው ተመለከተ። ገረመውና ምን እንደሆነ ቢጠይቅ "ደራሲ ነው" አሉት። እየተደነቀ "አይ ደራሲ ፀድቆም አያርፍ፣ አሁኑም ይፅፋል" ሲል ተደመመ።

ከሚንቀለቀል የእሳት እቶትን ውስጥ የሲዖልም ሕይወት ቀጥላለች። አመፅ፣ ግርግሩ፣ ጦርነቱ…ኃጥያቱ አናት ባናቱ ይደራረባል። አሁንም አንድ ሰውዬ ከእሳት ዛፍ ስር አረፍ ብሎ በእሳት ብዕር፣ በእሳት ወረቀት ይቸከችካል። ተመልካቹ ሰውዬ ግራ ተጋባም ምን ሊሆን ይችላል ሲል እያሰበ ጠየቀ "ደራሲ ነው፣ ይከትባል" አሉት።

እየተገረመ፣ እየተደነቀ መልዓኩን "ቆይ ደራሲ እዚህም ሲፅፍ አይቼዋለሁ…እዛም ሲቸከችክ ተመልክቼዋለሁ ካዲያ ገነትም ገባ፣ ሲዖልም ወረደ ምን ቀረበት? ምንድነው ቅጣቱ? ምን ተጎዳ?" ሲል ጠየቀው።

መልዓኩም መለሰለት "ገነት ያሉት ይታተምላቸዋል"



ዓለማየሁ ገላጋይ


@fonkabcha1
@fonkabcha1
​​​​​


የፍቅር ደብዳቤ

ለውዷ ፍቅሬ

የኔ ፍቅር ከህወሃት ሴራ የገዘፈ ሰላምታዬ ይድረስሽ። ካየሁሽ እለት ጀምሮ ሀሳቤን እንደ ሜቴክ ሰርቀሽ፤ ልቤን እንደ ጌታቸዉ አሰፋ በቀዝቃዛ እስር ቤት አስረሽ እያሰቃየሽኝ ነዉ። የኔ ማር በተለይ ደግሞ እንደ ዶክተር አቢይ የሚማርከዉ ንግግርሽ፣ እንደ ህወሃት አገዛዝ በማንአለብኝነት የሚንጎማለለዉ ዳሌሽ፣እና አባይ ፀሀየ ከሰረቀዉ ስኳር በላይ የነጣዉ ጥርስሽ እኔን እንደ ክንፈ ዳኘዉ እጅ በፍቅር ካቴና አስሮኛል። የኔ ፍቅር እኔ ያላንቺ መኖርእንደማልችል እያወቅሽ አንቺ ግን እንደ ዶክተር ደብረጽዮን መጣሽ ስልሽ መሄድ፣ ሄድሽ ስልሽ ደግሞ መምጣት የዘወትር አመልሽ ሆኗል። ዉዴ በፍቅርሽ እንደ ያሬድ ዘሪሁን አንገቴን ብታስደፊኝም አንቺን እንደ ህዳሴዉ ግድብ በተስፋ መጠበቅ ሳይታክተኝ፤ እንደ በረከት ስምዖን በስጋት ሳይሆን እንደ ኢትዮጵያ ህዝብ በተስፋ ዉጭ ዉጭዉን አያለሁ። የኔ ስጋት ግን እንደጠፋዉ አዉሮፕላን እስከመጨረሻዉ ተሰዉረሽ ልቤን እንደ ተሰረቀችዉ መርከብ በባህር ላይ አንሳፍፈሽ እንዳታጉላዪዉ ነዉ። በተረፈ እንደ ኢትዮ-ኤርትራ በፍቅር ተደምረን እንደ ኢሳያስና አቢይ ዘወትር ለመገናኘት ያብቃን እላለሁኝ።

ከአፍቃሪሽ...... 🤗

@fonkabcha1
@fonkabcha1
አርቲስት ማዲንጎ አፈወርቅ ከዚህ አለም በሞት ተለየ #ነብስ_ይማር 😢😢😢
ለዝች አጭር እድሜ ለዝች ከንቱ ዓለም
እድሜያችን ተመዞ ላንኖር ዘላለም
በድንገት ተጠርተን ላይቀር መሄዳችን
መልካም ጥሩ ይሁን ሁል ጊዜ ስራችንም
አግኝቶ ላያገኝ ወይ ጠቅሞ ላይጠቅመው
ሰው ለምን ይኖራል ትዝታ ሲያደክመው

ትርጉሙ ምንድነው ምንድነው ትዝታ
ምንድነው ሰው ማሰብ ምንድነው ትዝታ
ባክህ ተው የማይሉት የሁሉም ሰው ጌታ

ይሀው ሰው ይኖራል በትዝታ ሰበብ
የኋሊት ሲጋልብ ትናንትን በማሰብ
ሰው እንዴት ባለፈው በትናንት ይኖራል
ዛሬን በእጁ ይዞ ለነገው መሰላል.....



#ድምጻዊ ማዲንጎ አፈወርቅ ነፍስህ በሰላም ትረፍ።

@fonkabcha1
@fonkabcha1
መጽሐፍ ጥቆማ
"ሜሎሪና"
በናሁሰናይ ፀዳሉ አበራ
🚢🚢🚢
"መሸበርና መፍራት የነገን ችግር አያስወግድልንም ይልቁኑስ የዛሬን ደስታ ያሳጣናል ።" "ሕይወት፣ የመዘጋጃና የመኖሪያ ዕድሜ የሌላት፣ ከአፈር ለተሠራ ሰው የተሰጠች ስጦታ ነች ፡፡ የሰው ልጅም ከተፈጠረ ጀምሮ ሕይወትን በውስጡ ለማሰንበት በትግል የሚኖር፣ ሲያጣትም እጅግ ጠሊቅ ሐዘን ውስጥ የሚገባ ፍጡር ነው፡፡ሰዉ የራሱንና የሚወዳቸውን እስትንፋስ ለማቈየት፣ ከሰከንድ እስከ ሰዓታት ከዛሬው እየተበደረ ለማያውቀው ነገ ሲገብር፣ ለማያውቀው ነገ ደስታ ዛሬ ሲያለቅስ፣ ለማያውቀው ነገ ጥጋብ ዛሬ ሲራብ ሲታረዝ፣ ከማያውቀው ነገ ተበድሮ ዛሬ ሲጨነቅ የሚኖርና መኖሩን ሳያውቅ የሚሞት ፍጡር…፡፡"
🎄🎄🎄
ከማያውቀው ነገ ተበድሮ ዛሬ ሲጨነቅ የሚኖርና መኖሩን ሳያውቅ የሚሞት ፍጡር - ሰው፡፡ ...በሕይወት ትልቁ ቁም ነገር ትምህርት መውሰድ ነው፡፡ መቼም በስለንም አውቀንም አንጨርስም። ባወቅን ቊጥር ብዙ ቀዳሚ አላዋቂነታችን ይታወሰናል፡፡ሁሌም እንማር፣ ሁሌም ለመለወጥ ዝግጁ እንኹን፣ ሁሌም ብሩሕ ተስፋ ይኑረን፡፡ ብልህ ሰው ዛሬ ላይ ዐዋቂ ነኝ፣ ትክክል ነኝ፣ እኔ ብቻ የሚል ሳይኾን ዛሬ ላይ የሕይወትን ትምህርት ከሕፃናት ሳይቀር ለመማር የተዘጋጀ ነው፡፡ስለ ዛሬ ማንነቱ ሲያስብ ሙሉነት የሚሰማው ብቻ ሳይኾን፣ ነገ ላይ ለመሙላት የሚሰናዳ ነው፡፡ ብልህ ሰው ትናንትናንና ነገን አስታርቆ ዛሬን በእረፍት በርጋታና በደስታ የሚኖር ሲኾን፣ በሰው ሁሉ ለመወደድ ሳይኾን ሰውን ሁሉ ለመውደድ የሚጥር ነው፡፡

@fonkabcha1
@fonkabcha1
"ማንበብ ፋሽን ነው።"
ከወደድኩት ላካፍላችሁ

🕯ፍቅር ማለት 1 ሚሊዮን ሴት ማፍቀር አደለም 🙅‍♂ ፍቅር ማለት አንድን ሴት በአንድ ሚሊዮን መንገድ ማፍቀር ❤️ ነው!

ወንድነት ማለት ሁሉም ሴቶች ስለወደዱት አደለም ወንድነት መለኪያው አንድዋ ሴት ከሌሎች አብልጣ ስትወደው እና ለስዋም ታማኝ እና ፍፁም መሆን ነው።

ነጥቡ መፈቀር ላይ ሳያሆን አፍቅሮ ተፈቅሮ መቆየት ላይ ነው

SHER❤️
@fonkabcha1
@fonkabcha1
🥀.....አንቺ'ና ቁንጅናሽ.....👱‍♀
      
        እኔም ለኔ❤️‍🔥 ስልሽ
   ሌላም ሠው😌 ሢመኝሽ
    ተወዳድርኩ🥹 እኔም
      የግሌ 🥰ላደርግሽ
    ግና ምን😔 ያደርጋል
    መስፈርትሽ🤷 ይከብዳል
    እንኩዋን 🙋እኔ ቀርቶ
  እብዱም ደግሞ ያብዳል💔

 
@fonkabcha1
@fonkabcha1
🤕ድምፅ አልባ ፊደላት💔

ፀጉሩን #አንጨብርሮ ፂሙን #አጎፍሮ
#ጥግ ተቀምጦ ለሚታየኝ ወጣት
ሂድና ታዘዘዉ #ስጠዉ አንድ ድራፍት
ቅዳለት ደብል ጂን ሀሳቡን #ይርሳበት‼️

በፂሙ #መጎፈር በፀጉሩ #መንጨብረር
ቁጥር ፈታ በሚል በግንባሩ መስመር☹️
ይታየኛል ቋንቋ ይታየኛል #ነገር!
.
.
እዚያምከጨለማዉ #ብቸኝነት ዉጧት💔
ሲጋራዋን ይዛ ለቆመችዉ ወጣት🤒
ሂድና #ታዘዛት የሚጠጣ ስጣት!
.
.
ምጋ #በተፋችዉ በጭሶቹ መሀል
ሴትነት #ሲበደል ‼️💔
እህትነት #ሲጣል ‼️
አናትነት #ሲጎል 😔
ይታየኛል ቋንቋ ይታየኛል ፊደል....

@fonkabcha1
@fonkabcha1

👪 እናትነት 👪


💞 እውነተኛ_ታሪክ 💞

ገነት አራት ልጆች አሏት ሁሉም ወንዶች ናቸው የመጀመርያ ልጇ ቢንያም 24 አመቱ ነው ሁለተኛ ልጇ ሱራፌል 22 አመቱ ሦስተኛ ልጇ ሳሚ16 አመቱ የመጨረሻ ልጇ አሜን ግን ገና 3 አመቱ ነው። ገነት ና ባለቤቷ ኪሮስ የሚያስቀኑ ደስ የሚሉ ባል ና ሚስት ናቸው። ኑሮአቸውን የሚያስተዳድሩት አንድ ሬስቶራት ከፍተው እየተጋገዙ በመስራት ነው ። በሳምንቱ የመጀመርያ ቀን ጥዋት ቤታቸው ተንኳኳ ፖሊሶች ነበሩ ኪሮስን ይዘዋቸው ሔዱ ምክንያቱም እሳቸው ትግሬ ስለሆኑ ሰሞኑን በሚሰራው ወንጀል ፓሊሶች ጥርጣሬ ስላደረባቸው ነው። ገኒ ባለቤቷ ስለታሰረባት ብቻዋን ቤት በማስተደደር ተጠምዳለች ለልጆቿ ሚያስፈልጋቸውን ነገር ካሰናዳችላቸው በኋላ ባለቤቷን እስር ቤት ሔዳ ካየችው በኋላ ወደ ሬስቶራንቱ የሦስት አመት ልጇን አሜንን ይዛ ትሔዳለች አሜንም አጠገቧ መጫወችያ ሰታው በአይኗ እየተቆጣጠረችው ሲያለቅስ እያባበለችው ሲተኛ በጀርባዋ አዝላ ስትሰራ ቆይታ ማምሻዋን ወደ ማደርያዋ ትመለሳለች። በባለቤቷ አለመኖር ብትከፋም ብታዝንም ደከመኝ ሰለቸኝ ሳትል ትሰራለች። ኪሮስ ከታሰረ ሦስት ቀን ሆኖታል ገኒ እደተለመደው ተነስታ ልጇን ይዛ ወደ ስራ ቦታ ሔዳ ለአሜን መጫወቻውን ሰታው በስራ ተጠምዳለች ይሔኔ ነበር አሜን ከ አይኗ የተሰወረው ገኒ ስራዋን ጨርሳ ቀና ስትል ልጇን ታጣዋለች ወዴት እንደሔደ ለማጣራት ተጣራች አሜን አሜን የት ነህ አሜን ግን መልስ የለም ደግማ ተጣራች አባ አባቴ የት ሔድክብኝ አሁንም መልስ የለም ትንሽ ዞር ዞር ብላ ስታጣው ምናልባት ከተስተናጋጅ ጋር ከሆነ ብላ ወደ ፊት ለፊት ሰው ላከች ግን የለም አሁንም ደግማ ተጣራች አሜን አባቴ ግን መልስ የለም። ገነት ደነገጠች ምናልባት ወደ ጓሮ ሔዶ ይሖን ሩጫ ወደ ጓሮ እየተጣራች ገሰገሰች። ጓሮ ቆሻሻውን ለማስመጠጥ ብለም የከፈቱት 5ሜ ያልተከደነ ጉድጓድ አለ ከ ዛሬ ነገ አስከድነዋለው እያሉ ረስተውታል ገነት ሮጣ ከደረሰች በኋላ ወደታች ለማየት ብትሞከርም ሩቅ ከመሆኑ የተነሳ ሊታያት አልቻለም ባትሪ አስመጥታ ስታይ ልጇ በጭንቅላቱ ተደፍቶ ታየዋለች በዕንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ ይሉታል እንዲ ነው ። ገነት አልቻለችም ጮኸች ኸረ ልጄ ኡኡኡ ልጄን አድኑልኝ ምትይዘው ምትጨብጠው ጠፋት አብረዋት የነበሩ ሰራተኞች ተደናገጡ ሰፈሩ በጩኸት ተናጋ እናት ግን ደቅቃ መጠበቅ አልቻለችም ከመቅስፈት ዘላ ወደ ጉድጓዱ ገባች በሷ መግባትም እንደገና ሌላ ጩኸት ኡኡኡ ድረሱልን ።ገኒ እንደገባች በፍጥነት ልጇን ከተደፋበት አነሳችው ምታደርገውን አታቅም በደመ ነብስ ልጇን አቅፋዋለች በህይወት ነበር ግን ትንፋሹ ይቆራረጣል ልጄን ልጄን አድኑልኝ ብላ ጮኸች ደጋግማ ልጄን አድኑልኝ ትላለች ልጇ አሜን በትንፋሽ ማጠር ና ቆሻሻም በመጠጣቱ በጣም ደክሟል። አብረዋት ልጇን ሲያፋልጓት የነበሩ ሰራተኞች በናት ና ልጅ ቆሻሻ ጉድጓድ ውስጥ መግባት ቢደናገጡም በፍጥነት ተጨማሪ ሰው ጠርተው እንዲሁም ጩኸቹን የሰሙ ሰዎች ተሰብስበው አሶጧቸውና የህክምና አርዳታ እንዲያገኙ ወደ ሆስፒታል ወሰዷቸው። ገነት በወገቧ ና በእጇ ላይ ጉዳት ቢደርስባትም የሷ መጎዳት አልታያትም ለዶክተሮቹ በልቧ ደሞ ፈጣሪን ልጇን እዲያድኑላት ተማፅናቸዋለች እዳሳቧ ፈጣሪም አላሳፈራትም ልጇ ሰላም ሆኖላታ በእግዚአብሔር ቸርነት ልጇ ተርፎላታል አሁን ደስተኛ ናት ።
በአሁን ሰአት እግዚአብሔር ይመስገን አናትም ልጅም በመልካም ጤንነት ላይ ናቸው።
ምን አይነት መሰዋትነት ነው? ምን አይነት እናት ናት ነብስ እስከመስጠት ልጇን የምትወደው? ፈጣሪ ለናቶች የሰጣቸው ልብ ምን አይነት ነው? ይሔ የኔ ጥያቄ ነው። ድንቅ እናት የምትወደድ ለነብሷ ያልሳሳች እኔ መቼም አረሳትም ፈጣሪ አድሜሽን ያርዝመው።
🙏🙏👉ክብር💓 ፣እድሜ ና ምስጋና ለእናቶች💓🙏🙏



@fonkabcha1
@fonkabcha1
ለምን
የተረገመ ሂወት የተረገመ ማቅ
ውስጡ ቆሽሾ ጠውልጎ ውጪው እጂግ ደማቅ
መታየት ሰልችቶት መታማት አጥፍቶት እንዲ ለሚባክን
ሰሚ የሌለው ጩኸት እየጮኸ እንዲው ለሚኳትን
እየኖረ ላለ መፈቀር እርቆት ማጣትም በዝቶበት
ለመቅረብ ሳይችል እያገኘ እያጣ ደስታውም ጠፍቶበት
ለምን ቢል ቢሳለቅ እብድም ቢያረገው አቅሉን ቢያሳጣው
በሱሶች ቢደበቅ አለው የሚል አቶ ውድቀቱ ቢከብደው
ለምን ቢል ድጋሚ አምላኩን ቢጠይቅ
እንደሰው ለመቆም ጥፋቱን ለማወቅ
እንዲው መባከኑን ሁሉም እንደራቀው
መንገድ እንደሌለው መኼጃ እንደጠፋው እራሱን እየጠላ በበደል ቢቀጣ
ማነው ሚረዳው ሰላሙን እንዳጣ
የፈጠረው እንኩዋን እንደዘነጋው ሰው እንዲ ሲሆን አይቶ እሱም ፀጥ ካለው
ማን ይሆን ለዚ ሰው አለውልህ ሚለው
እና ይሄ ሰው ለምን ቢል ማን ሊመልስለት
ልቡ እንደቆሰለ ጠጋ ብሎ ማን ጥቂት ሊያይለት
ግን ይሄ ሰው አሁንም በተስፋ ለምን ይላል ቆሞ መልስ እየፈለገ
እየኝ ይላል ደጋግሞ ለሁሉም ጥያቄ መልስ እየፈለገ
መጥቆሩን መክሳቱን ከሰውነት ማረግ እጅጉን መውጣቱን ለምን ቢያስብለው
የሚያየው ፈጣሪ እንደሚያነሳው ተስፋ ስላለው ነው

አሚር አደም

@fonkabcha1
@fonkabcha1
❣️🌹❣️🌹❣️🌹❣️🌹❣️🌹❣️🌹
" አንድን ሰው ለማየት ሰከንዶች ይፈጃል ፣
ያየኸውን ሰው ለመቅረብ ሰአታት ይፈጃል ፣
የቀረብከውን ለመግባባት ቀናት ይፈጃል ፣
የተግባባከውን ለመውደድ ሳምንታት ይፈጃል ፣
የወደድከውን ለማፍቀር ወራት ይፈጃል ፣
ያፈቀርከውን ለመርሳት ግን እድሜ ልክ ይፈጃል


@fonkabcha1
@fonkabcha1
💋💋 እኔኮ ስወድሽ 💋💋

እኔኮ ስወድሽ ቃላት ይደክማሉ፣
ፊደላት ሰልለው ድጋፍን ይሻሉ፣

ምን ቃል አለኝና ፍቅሬን ነግርሻለሁ፣
በልቤ ወድጄሽ ለፍቅርሽ ሞቻለሁ፣

አንቺን መተው ለኔ ይገርምሻል ውዴ፣
ከሞት ከቶ አያንስም እወቂው እንግዴ፣

አረ እንደውም መሞት ሳይሻል አይቀርም፣
የማፍቀር ሰቀቀን ጠባሳው አይሽርም፣
የናፍቆትን እከክ ጥፍር አያከውም፣
የመውደድን መሞት አይኖች አያዩትም፣

እናምልሽ ውዴ እራቀኝ ስትዪኝ፣
በቁም ሳለሁ በድን እንደሆንኩ እወቂኝ፣

በፍቅርሽ ሰንሰለት እግረ ሙቅ ታስሬ፣
አቅም የተቀማሁ የማልቆም ዳክሬ፣
የመከነ ልፋት ሰርክ ምድርን ዞሬ፣
የድጋይ ላይ ተክል የማይበዛ ዘሬ፣
እንዲ ነኝ አለሜ ካጣሁሽ አፍቅሬ፣

ዓሳ ከውሃ ወጥቶ ይኖር ዘንድ እንዳይችል፣
ንስር ምድር ወርዶ እንደማይሄድ ቁልቁል፣
እየተገረፈ እንደማይድን ቁስል፣
ለመርዶ ነጋሪ እንዳይባል እልል፣
እኔም አንቺን ካጣሁ ፍቅሬ ይከብደኛል፣

እኔኮ ስወድሽ ከገደቡ አልፌ፣
ጧት ማታ ሳልምሽ መውደድሽን ታቅፌ፣
ሌላ ምንስ አለኝ ፍቅርሽ ነዋ ትርፌ፣
ልተውሽ አልችልም ልቤ ላይ ሸክፌ፣

ውሰጂው ያለኝን ልሁን ነጭ ደሃ፣
ወይኑንም ተጎንጪ ለኔ ደሞ ውሃ፣

ከጮማው ቁረጪ አማርጪ ያሻሽን፣
እኔ ውዬ ልደር እየራበኝ ጦሜን ;;
ላንቺ ነው

@fonkabcha1
@fonkabcha1
❤️💙 አሁን ስንት ገባሽ

አፍቅሬሽ ከልቤ ያኔ ስጠይቅሽ
አሻፈረኝ ያልሽው ብር የለህም ብለሽ
እድሜ ላንቺ ውዴ አሁን ብር ይዣለው
አሁን ስንት ገባሽ ይሀው ልገዛሽ ነው..

💘💘❤️‍🔥
@fonkabcha1
@fonkabcha1
ግን እኮ የለሽም
ከደመና በላይ እጅጉን እንደራቀ ልኬት የለሽ ፀሀይ
ከሰዎች ሳይገናኝ ምድርን ሊያበራ ከሩቁን የሚታይ
እንደዛ ነው ማሬ እሩቅ ሆነሽ እንኳን ባንቺ ብርሀን ማይ
ተስፋ እንደሌለው ሰው ሞት እንደናፈቀው አንድ ነገር አቶ
በጨለማ ሂወት ኑሮው ተናግቶበት በሀሴት ተሞልቶ
ሲኳትን ሲኳትን ከሰው ሁሉ እርቆ እድሜ ዘመኑን እንደኖረ ሰው
በሌላም በሌላም በሁሉም ብትመስሉኝ እኔን በማይገልፀኝ ብትስሉኝም እንዲው
እኔ ምን ሊደንቀኝ ባልበላ ባልጠጣ አንቺን እያሰብኩ ቁጭ ብዬ ባነጋ
ምንም ብመፃደቅ ምንም ላላመጣ ለምን እደክማለው ስሜን አልመነትፍ ከሰዎች መንጋጋ
ግን እኮ የለሽም
እኔ እቀጥላለሁ አንቺን ማፍቀሬን ብዙ ብትሪቂኝም ሁልግዜ ማሰቤን
ከሰው ኋላ ብቀር እጅ እግር ባይኖረኝ መች አቆማለሁ አንቺን መናፈቄን
ለማኝ ተብያለሁ አንቺን ሳባብል ህልሜን እንድኖረው
ውሻ ተብያለሁ በሄድሽበት ቦታ ሁሌ ስከተልሽ መሄጃ እንደሌለው
እድሜ ዘላለሜን ላንች እታገላለው ዘብም እቆማለሁ
ግን እኮ የለሽም እርቀሽ ሄደሻል
ላትመለሽ አይንሽ እንዳያይ ጆሮሽ እንዳይሰማ ወደፊት ነጉደሻል
ምን አረጋለሁ ስጨነቅ እውላለሁ አስብሻለሁ
እዚ ባትሆኚም ከተሜው እንዲያማሽ መች እፈቅዳለሁ
ግን እኮ የለሽም

አሚር አደም

@fonkabcha1
@fonkabcha1
💋💋 እኔኮ ስወድሽ 💋💋

እኔኮ ስወድሽ ቃላት ይደክማሉ፣
ፊደላት ሰልለው ድጋፍን ይሻሉ፣

ምን ቃል አለኝና ፍቅሬን ነግርሻለሁ፣
በልቤ ወድጄሽ ለፍቅርሽ ሞቻለሁ፣

አንቺን መተው ለኔ ይገርምሻል ውዴ፣
ከሞት ከቶ አያንስም እወቂው እንግዴ፣

አረ እንደውም መሞት ሳይሻል አይቀርም፣
የማፍቀር ሰቀቀን ጠባሳው አይሽርም፣
የናፍቆትን እከክ ጥፍር አያከውም፣
የመውደድን መሞት አይኖች አያዩትም፣

እናምልሽ ውዴ እራቀኝ ስትዪኝ፣
በቁም ሳለሁ በድን እንደሆንኩ እወቂኝ፣

በፍቅርሽ ሰንሰለት እግረ ሙቅ ታስሬ፣
አቅም የተቀማሁ የማልቆም ዳክሬ፣
የመከነ ልፋት ሰርክ ምድርን ዞሬ፣
የድጋይ ላይ ተክል የማይበዛ ዘሬ፣
እንዲ ነኝ አለሜ ካጣሁሽ አፍቅሬ፣

ዓሳ ከውሃ ወጥቶ ይኖር ዘንድ እንዳይችል፣
ንስር ምድር ወርዶ እንደማይሄድ ቁልቁል፣
እየተገረፈ እንደማይድን ቁስል፣
ለመርዶ ነጋሪ እንዳይባል እልል፣
እኔም አንቺን ካጣሁ ፍቅሬ ይከብደኛል፣

እኔኮ ስወድሽ ከገደቡ አልፌ፣
ጧት ማታ ሳልምሽ መውደድሽን ታቅፌ፣
ሌላ ምንስ አለኝ ፍቅርሽ ነዋ ትርፌ፣
ልተውሽ አልችልም ልቤ ላይ ሸክፌ፣

ውሰጂው ያለኝን ልሁን ነጭ ደሃ፣
ወይኑንም ተጎንጪ ለኔ ደሞ ውሃ፣

ከጮማው ቁረጪ አማርጪ ያሻሽን፣
እኔ ውዬ ልደር እየራበኝ ጦሜን ;;
ላንቺ ነው
@fonkabcha1
@fonkabcha1
❤️አልጠረጥራትም❤️

ትድመቅ እንደፀሃይ ትታይ አሸብርቃ ❤️
ብርሃን ታምጣልኝ ጨለማን አርቃ ❤️

ትሂድ በዚም በዚያም ትጓዝ በሰፈሩ 💖
ነፃነት ማግኘቷ ምንድነው ችግሩ 💖

ባምባ ገነን ሃይል ወሰን አልሰጣትም 💞
እንዳሻት ትሁን -አልጠረጥራትም💞
@fonkabcha1
@fonkabcha1
ቤትሽ እየመጡ መንገድ እያስቆሙ
ስለአብሮነታችን ለጠየቁሽ ሁሉ
እንደዚህ አልሽ አሉ
የኔንማ አታንሱ የሱን አታስታውሱ
እኔማ ልጅት ሞኝ ለፍቅር እኮ ስል
ቲማቲም መስዬ ኳ ብዬ እስክበስል
እንደ ቡሄ ዳቦ እሳት ነዶብኛል
ከታችና ከላይ
እናሳ ምን ልሁን እስቲ ከዚህ በላይ
ማለትሽን ሰማሁ አይደበቅ ወሬ
እርግጥ እውነትሽን ነው
አልዋሸሽም ፎቅሬ
ግንስ ከላይ ከታች ያለውን የእሳት ጠል
ወደውስጡ ዘልቆ ዳቦ እንዳይቃጠል
ይለብስ የለ ወይ ሙሉ የኮቦ ቅጠል
ታድያ እኔስ ብሆን አንቺ እንዳትጎጂ
ኮቦሽ እንደነበርኩ ተናገሪ እንጂ
እንዲያውም ፍቅሬ ሆይ አንቺ ታድለሻል
ገማጭ እንዳታጪ በልኩ በስለሻል
እኔ ኮባሽማ ልውል ስለማችል
ከአንድ ጊዜ በላይ ለድፎ ጋገራ
ከአንቺ ላይ ተልጬ ተጥዬልሻለሁ
      ከቆሻሻ ጋራ.....


@fonkabcha1
@fonkabcha1
፨፠፨ 'ትዝብት' ፨፠፨


በተቀመጥኩበት በሃሳብ ተውጬ
የዚህ አለም ነገር ገርሞኝ ተመስጬ
እንዲህ አስብ ነበር በዚህ ምድር ያለ
የሚርመሰመሰው ወዲህ ወዲያ እያለ
ቢሆን ምን አለበት ሁሉ ሰው አንድ አይነት
ተስተካክሎ ፍጥረት ቢኖር በእኩልነት
እንዲህ ምናያቸው ትንሽና ትልቅ
ባይበላለጡ ባይሉ ከፍና ዝቅ
አንዱ ቤት ተራቁቶ ጠፍቶ የሚጎረስ
ሌላው እጅግ ተርፎት ምግብና አልባሳት
አንዱ ቤት ልጅ በዝቶ የሚቀምሰው ጠፍቶ
መሃኑ ለመውለድ አይኑ ተንከራቶ
አገር የሚጠቅመው ታላቁ ሰው ሞቶ
የመንገድ ላይ እብድ እድሜው እጅግ ገፍቶ
እናት አባት ሞተው ሲፈርስ ቤታቸው
ጎዳና ሲወጡ ብዙ ልጆቻቸው
እውቀት ያለው አጥቶ ለስራው መነሻ
ገንዘብ ያለው ሰው አርጎት መንተራሻ
ውሸት በአለም ነግሶ ተሸፍና እውነት
ሰው በአፉ ብቻ በሽንገላ ሲበልጥ
አንደኛው ሲደሰት በሳቅ ተፍለቅልቆ
ጎረቤቱ በሃዘን በለቅሶ ገርጥቶ
አስተዋልኩኝና ሆኖብኝ ድንግርግር
አስገርሞኝ የዚች አለም ነገር
ግና....
ብርሃን ለማየት ጨለማ ግድ ነው
ጨለማ ካልኖረ ብርሃን ምንድነው
ፍቅር ሚታወቀው ጥላቻ ሲኖር ነው
ስለዚ ይጉዋዛሉ አብረው ልዩነቶች
በብዙ ታጅበው በተወዳዳሪዎች
ለሚበልጠው ነገር በፍጥነት በአላማ
ሰውም ይራመዳል በተስፋ ጎዳና


@fonkabcha1
@fonkabcha1
HTML Embed Code:
2024/05/16 13:25:03
Back to Top