TG Telegram Group Link
Channel: ጠቅላላ እውቀት
Back to Bottom
#በ2023_እንደ_TasteAtlas_በአፍሪካ_ውስጥ_10_ምርጥ_ምግቦች_ደረጃውን_እነሆ

1️⃣ አልጄሪያ 🇩🇿
2️⃣ ሞሮኮ 🇲🇦
3️⃣ ግብፅ 🇪🇬
4️⃣ ደቡብ አፍሪካ 🇿🇦
5️⃣ ቱኒዚያ 🇹🇳
6️⃣ ኢትዮጵያ 🇪🇹
7️⃣ ሊቢያ 🇱🇾
8️⃣ ጋና 🇬🇭
9️⃣ አንጎላ 🇦🇴
🔟 ናይጄሪያ 🇳🇬

╭══•|❀:✧๑♡๑✧❀|: ══╮
@ewentesfa
╰══•ೋ•✧๑♡๑✧• ══╯
#10_አስገራሚ_እውነታዎች_ስለአፍሪካ_ሀገራት

ኢትዮጵያ 🇪🇹 በአለም ላይ እጅግ ጥንታዊ እና ቀጣይነት ያለው የክርስትና ባህል ባለቤት ስትሆን በላሊበላ ምድር ስር የተሰሩ ውቅር አብያተ ክርስቲያናት አሏት።

ግብፅ 🇪🇬 ከአፍሪካ ከፍተኛ ቁጥር ያለው የኖቤል ተሸላሚዎች አላት::

ደቡብ አፍሪካ 🇿🇦 በአለም ላይ ሶስት ዋና ከተማዎች ያላት ብቸኛ ሀገር ናት ኬፕታውን (ህግ አውጪ)ፕሪቶሪያ (አስተዳደር) እና ብሎምፎንቴን (ዳኝነት) ናቸው።

ኬንያ 🇰🇪 በዓለም ላይ ትልቁን ጥቁር ሻይ ላኪ ነች።

ናይጄሪያ 🇳🇬 በመላ አገሪቱ የሚነገሩ ከ500 በላይ ቋንቋዎች አሏት።

ታንዛኒያ 🇹🇿 ጎብኚዎች የታላቁን የዱር አራዊት ፍልሰት የሚያዩበት በዓለም ታዋቂ የሆነው የሴሬንጌቲ ብሔራዊ ፓርክ መኖሪያ ነው።

ሞሮኮ 🇲🇦 በአለም ትልቁ የፀሐይ ኃይል ማመንጫ በሰሃራ በረሃ ይገኛል።

ጋና 🇬🇭 በ1957 ከቅኝ አገዛዝ ነፃ የሆነች የመጀመሪያዋ አፍሪካዊት ሀገር ነች።

ቱኒዚያ 🇹🇳 በአለም ውስጥ ብቸኛው ከመሬት በታች ያለው መስጊድ በዱዝ ከተማ ይገኛል።

ዚምባብዌ 🇿🇼 ከ90% በላይ ህዝቧ ማንበብና መፃፍ ከአፍሪካ ቀዳሚ ስትሆን።

╭══•|❀:✧๑♡๑✧❀|: ══╮
              @ewentesfa
╰══•ೋ•✧๑♡๑✧• ══╯
#በ2024_ከዶላር_አንጻር_ደካማ_ገንዘብ_ያላቸው_10_የዓለም_ሀገራት

💰 የአንድ ሀገር ገንዘብ በሌላ ሀገር ገንዘብ ሲመነዘር ያለው ዋጋ ጥንካሬውን እና ድክመቱን ያሳያል የተባለ ሲሆን፤ ኤፍ.ኤክስ.ኤስ.ኤስ.አይ ድረ ገጽ ከሰሞኑ ከከዶላር አንጻር ገንዘባቸው ደካማ የሆነ 10 የዓለም ሀገራትን ይፋ አድርጓል።

💰 የአንድ ሀገር ገንዘብ በሌላ ሀገር ገንዘብ ሲመነዘር ያለው ዋጋ ጥንካሬውንና ድክመቱን ያሳያል

የኢራን 🇮🇷 ሪያል ቀዳሚ ሲሆን፤ 1 የዶላር በ42 ሺህ 45 የሀገሪቱ ገንዘብ (ሪያል) ይመነዘራል

የቬትናም🇻🇳 ገንዘብም ከዶላር አንጻር ደካማ ከሚባሉት ውስጥ 2ኛ ደረጃ ለይ የተቀመጠ ሲሆን፤ 1 የአሜሪካ ዶላር በ24 ሺህ 469 የቬትናም ገንዘብ (ዶንግ) ይመነዘራል።

የሴራሊዮን🇸🇱 ገንዘብም ከዶላር አንጻር ደካማ ከሚባሉት ውስጥ 3ኛ ደረጃ ለይ የተቀመጠ ሲሆን፤ 1 የአሜሪካ ዶላር በ22 ሺህ 418 ሴራሊዮን ገንዘብ (ሊዮን) ይመነዘራል።

➍ 4ኛ ደረጃ ላይ የተመቀጠው የላኦ🇱🇦 ወይም ላኦቲን ኪፕ ገንዘብ ሲሆን፤ አንድ የአሜሪካ ዶላር በ20 ሺህ 594 ላኦቲን ኪፕ እየመተመነዘረ መሆኑ ነው የተነገረው።

የኢንዶኔዢያን🇮🇩 ደግሞ 5ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል የተባለ ሲሆን፤ 1 የአሜሪካ ሶላር በ15 ሺህ 619 የኢንዶኔዢያን ሩፒያህ ይመነዘራል ነው የተባለው።

የኡዝቤኪስታን🇺🇿 ገንዘብ 1 የአሜሪካ ዶላር በ12 ሺህ 335 የኡዝቤክ ሰም ነው የሚመነዘረው ይላል መረጃው።

የጊኒ🇬🇳 ገንዘብም በ7ኛ ደረጃን የያዘ ሲሆን፤ 1 የአሜሪካ ዶላር በ8 ሺህ 583 የሀገሪቱ ገንዘብ (ጊኒ ፍንክ እንደሚመነዝርም ተመልክቷል።

የፓራጓይ🇵🇾 ገንዘብ 8ኛ ደረጃ ላይ የተቀመጠ ሲሆን፤ 1 የአሜሪካ ዶላር በ7 ሺህ 280 የፓራጓይ ጓራኒ እንደሚመነዘር ነው መረጃዎች የሚያመለክቱት።

የካምቦዲያ 🇰🇭 ገንዘብ ሲሆን፤ 1 የአሜሪካ ዶላር በ4 ሺህ 86 የካምቦዲያን ሬይል እንደሚመነዘርም ተነግሯል።

የኮሎምቢያ🇨🇴 ገንዘብ 10ኛ ደረጃ ላይ የተቀመጠ ሲሆን፤ በዚህም 1 የአሜሪካ ዶላር በ3 ሺህ 915 የኮሎምቢያን ፔሶ እንደሚመነዘርም ነው የተገለጸው።

╭══•|❀:✧๑♡๑✧❀|: ══╮
@ewentesfa
╰══•ೋ•✧๑♡๑✧• ══╯
ከአፍሪካ አየር መንገዶች በአውሮፕላን ብዛት ቀዳሚዎቹ የትኞቹ ናቸው?

1ኛ የኢትዮጵያ አየር መንገድ


✈️ ከስምንት አስርት ዓመታት በፊት በአጼ ኃይለ ሥላሴ የተመሠረተው የኢትዮጵያ አየር መንገድ በፈጣን እድገቱ በአፍሪካ ስመ ጥር ነው።

✈️ አፍሪካን ከዓለም፤ ዓለምን ከአፍሪካ በማስተሳሰርም ስሙን ገንብቷል።

✈️ ዋና መናኸሪያውን አዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ላይ አድርጎ፤ በቶጎ ሎሜ፣ በማላዊ ሊሎንፍዌ፣ በዛምቢያ ሉሳካ ተጨማሪ መናኸሪያዎችን ከፍቷል።

✈️ የአፍሪካን መንገደኞች እና ጭነቶችን በማጓጓዝ ከአህጉሪቱ የአየር ትራንስፖርት ገበያ የአንበሳውን ድርሻ የሚይዘው አየር መንገዱ፤ ዘመናዊ በሆኑ አውሮፕላኖች በአምስት አህጉራት ከ150 በላይ ወደ ሆኑ መዳረሻዎቹ ይበራል።

✈️ የቦይንግ፣ የኤርባስ እና የቦምባርድኤር ምርት የሆኑ የተለያዩ አውሮፕላኖች ያሉት የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአጠቃላይ 148 አውሮፕላኖችን በአየር ላይ በማሰማራት በአፍሪካ ውስጥ ተፎካካሪ የሌለው ለመሆን ችሏል።

✈️ አየር መንገዱ ሙሉ በሙሉ በኢትዮጵያ መንግሥት ባለቤትነት ስር የሚተዳደር ሲሆን፣ በየዓመቱ በቢሊዮኖች ዶላር የሚቆጠር የውጭ ምንዛሪን ለአገሪቱ ያስገኛል።
︎ 20 ኤርባስ ኤ350
      ︎ 44 ቦይንግ 737
     ︎ 20 ቦይንግ 777
     ︎ 29 ቦይንግ 787
     ︎ 32 ቦምባርዴር ኪው400
     ︎ 3 ቦይንግ 767

2ኛ ኢጅብት ኤር

✈️ እ.አ.አ በ1932 በመመሥረት ከዓለም ቀደምት አየር መንገዶች ተርታ የሚመደበው የግብፁ አየር መንገድ ኢጅብት ኤር፤ እዚያው በአገር ውስጥ ከካይሮ ወደ አሌክሳንዲሪያ በመብረር ነበር አገልግሎት የጀመረው።

✈️ በአገሪቱ መንግሥት ባለቤትነት የሚተዳደረው አየር መንግዱ፤ 100 ዓለም አቀፍ መዳረሻዎች አሉት። የግብፅ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያን ዋነኛ ማዕከሉ አድርጎም ይበራል።

✈️ በአፍሪካ ግዙፍ የአየር የጭነት አገልግሎት (ካርጎ) የሚሰጠው አየር መንገዱ፤ በመጪዎቹ ዓመታት የአውሮፕላኖቹን ቁጥር እንደሚያሳድግ ይጠበቃል።

✈️ የኤርባስ እና የቦይንግ አውሮፕላኖችን በአብዛኛው የያዘው ኢጅብት ኤር፤ 82 አውሮፕላኖች አሉት።

     ︎ 12 ኤርባስ ኤ220
     ︎ 10 ኤርባስ ኤ320
     ︎ 7 ኤርባስ ኤ321
     ︎ 11 ኤርባስ ኤ330
     ︎ 29 ቦይንግ 737
     ︎ 6 ቦይንግ 777
     ︎ 7 ቦይንግ 787

3ኛ ኤር አልጄሪያ

✈️ እ.አ.አ በ1946 አልጄሪያ የፈረንሳይ ቅኝ ግዛት አካል እያለች የተመሠረተው ኤር አልጄሪያ ወደ አውሮፓ መንገዶኞችን ለማጓጓዝ የተመሠረተ ነው።

✈️  በ1962 ነጻነቷን ስታገኝ በመንግሥት ቁጥጥር ስር የገባው አየር መንገዱ፣ በ28 አገራት 78 የአገር ውስጥ እና ዓለም አቀፍ መዳረሻዎች አሉት።

✈️  መንገዱ በቅርቡም ኢትዮጵያን አዲስ መዳረሻው በማድረግ አገልግሎት መስጠት ጀምሯል።

✈️  አልጄሪያ ሰፋ ያሉ ቅርጽ ያላቸውን የአውሮፕላን ሞዴሎች በመጠቀም የሚታወቅ ሲሆን፣ በአጠቃላይ የ55 አውሮፕላኖች ባለቤት ነው።

     ︎ 8 ኤርባስ ኤ 330
     ︎ 25 ቦይንግ 737-800
     ︎ 2 ቦይንግ 737-700
     ︎ 5 ቦይንግ 737-600
     ︎ 15 ኤአርቲ 72-2012 ኤ
     ︎ 1 ሄርኩሌ ኤል 100-30 (ካርጎ)

4ኛ ሮያል ኤር ሞሮኮ

✈️  ሰንደቅ ዓላማ ስር የሚበረው ሮያል ኤር ሞሮኮ እ.አ.አ በ1957 ነው የተመሠረተው።

✈️  በአብላጫው በሞሮኮ መንግሥት ባለቤትነት የተያዘም ሲሆን፤ በካዛብላንካ መሐመድ አራተኛ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ማዕከሉን አድርጎ ይበራል።

✈️  በአብዛኛው ጉዞውን በአገር ውስጥ እና በቀጣናው አገራት ያደረገው አየር መንገዱ 89 መዳረሻዎች ሲኖሩት፣ ለእነዚህ ጉዞዎቹም ድብልቅ የአውሮፕላን ዓይነቶችን ይጠቀማል። በአጠቃላይ 51 አውሮፕላኖች አሉት።

     ︎ 4 ኢምባሪየር E190
     ︎ 30 ቦይንግ 737-800
     ︎ 4 ቦይንግ 787-9
     ︎ 5 ቦይንግ 737-800
     ︎ 2 ቦይንግ 737-ማክስ 8
     ︎ 1 ቦይንግ 767-300 (ካርጎ)
     ︎ 6 ኤአርቲ72-600

5ኛ የኬንያ አየር መንገድ

✈️  የምሥራቅ አፍሪካ አየር መንገድ መፍረሱን ተከትሎ እ.አ.አ 1977 የተመሰረተው የኬንያ አየር መንገድ 44 ዓለም አቀፍ መዳረሻዎች አሉት። ከእነዚህም ውስጥ 35ቱ በአፍሪካ የሚገኙ ናቸው።

✈️  በ2020 በዓለም የጉዞ ሽልማት የአፍሪካ መሪ አየር መንገድ የተባለው የኬንያ አየር መንገድ በዓመት አራት ሚሊዮን መንገደኞችን ያጓጉዛል።

✈️  የአየር መንገዱ 48.9 በመቶው የባለቤትነት ድርሻ የኬኒያ መንግሥት የሆነው አየር መንገዱ የተለያየ ዓይነት ያላቸው 32 አውሮፕላኖች አሉት። እሱም

     ︎ 9 ቦይንግ 787-8
     ︎ 8 ቦይንግ 737-800
     ︎ 2 ቦይንግ 737-300F
     ︎ 13 ኢምባሪየር E190

© ቢቢሲ አማርኛ

╭══•|❀:✧๑♡๑✧❀|: ══╮
              @ewentesfa
╰══•ೋ•✧๑♡๑✧• ══╯
#ቀይ_ሥር_ለጤና_ከሚሠጠው_ጥቅም_ምን_ያህሉን_ያውቃሉ?

♧ ለጤና ከፍተኛ ጥቅም ከሚሠጡ አትክልትና ሥራሥር ተክሎች አንዱ ቀይ ሥር ነው፡፡

♧ ቀይ ሥር በርካታ የጤና ጥቅሞች እንዳሉትም የሥነ-ምግብ ባለሙያዎች ይናገራሉ፡፡

♧ ከበርካታ ጥቅሞቹ መካከልም÷ ዕይታን ለማሻሻል፣  የጉበት ሥብን (ኮሌስትሮል) ለማስወገድ፣  የሆድ ድርቀትን ለማስወገድ፣ የደም ግፊትን ለመከላከል እና የሆድ ቁስለትን ለማስታገስ የሚሉትን ለአብነት ያነሳሉ፡፡

1.  ዕይታን ለማሻሻል ፡- በተለይም ሰዎች ዕድሜያቸው እየጨመረ ሲሄድ ቀይ ሥር ቢመገቡ የዕይታቸውን ሁኔታ ባለበት ለመጠበቅ ብሎም ለማሻሻል እንደሚያግዝ ባለሙያዎች ይመክራሉ፡፡

2.  የጉበት ሥብን ለማስወገድ ፡- የጉበት የሥብ መጠን ከሚፈለገው በላይ መሆን ውስብስብ የጤና ዕክሎችን እንደሚያስከትል ይታመናል፡፡

በመሆኑም ቀይ ሥር መመገብ የጉበትን ሥብ ለማስወገድ እና ጤናማነቱን ለመጠበቅ እንዲሁም ጉበታችን ሥራውን በአግባቡ እንዲሠራ ለማስቻል ይረዳል፡፡

3.  የሆድ ድርቀትን ለማስወገድ ፡- በቀይ ሥር ውስጥ የሚገኘው ንጥረ ነገር የምግብ መፈጨትን ለማፋጠን፣  ምግብ በሚመገቡበት ወቅትም ምቾት እንዲሰማና የሆድ ድርቀት እንዳያጋጥም ይረዳል፡፡

4.  የደም ግፊትን ይከላከላል ፡- ቀይ ሥርን መመገብ ጤናማ የደም ዝውውር እንዲኖር ያስችላል ይላሉ ባለሙያዎች፡፡
ይህም የልብ ሕመምን ጨምሮ በሌሎች ተያያዥ ችግሮች ከመጋለጥ እንደሚታደግም ነው የሚገልጹት፡፡

5.  የሆድ ቁስለትን ያስታግሳል ፡- ቀይ ሥር “ቤታላይን” በተሰኘ ንጥረ-ነገር የበለጸገ በመሆኑ የሰውነት ክፍሎችን ሥርዓት ለማስተካከል እንዲሁም የሆድ ቁስለትን ለማስወገድ ያግዛል መባሉን ኸልዝ ላይን አስነብቧል፡፡

♧ አንድ 80 ግራም የሚመዝን ቀይ ሥር÷ 29 ኪሎ ካሎሪ፣ 1 ነጥብ 4 ግራም ፕሮቲን፣ 0 ነጥብ 1 ግራም ሥብ፣ 6 ነጥብ 1 ግራም ኃይል ሠጪ፣ 2 ነጥብ 1 ግራም ፋይበር፣ 304 ሚሊ ግራም ፖታሺየም እንዲሁም 120 ማይክሮ ግራም ፎሌት እንደሚይዝ መረጃው አመላክቷል፡፡

መልካም ጤንነት!!

╭══•|❀:✧๑♡๑✧❀|: ══╮
              @ewentesfa
╰══•ೋ•✧๑♡๑✧• ══╯
#የዓለማችን_ረጅም_በረራዎች

1. ከፐርዝ ወደ ለንደን 17ሰዓት ከ20ደቂቃ

2. ከሂዩስተን ወደ ሲድኒ 17ሰዓት ከ30ደቂቃ

3. ከኦክላንድ ወደ ዶሃ 17ሰዓት ከ40ደቂቃ

4. ከሲንጋፖር ወደ ኒውዮርክ 18ሰዓት ከ45ደቂቃ

╭══•|❀:✧๑♡๑✧❀|: ══╮
              @ewentesfa
╰══•ೋ•✧๑♡๑✧• ══╯
#በዓለም_ላይ_በብዛት_የተጎበኙ_20_አገሮች
➊ ፈረንሳይ 🇫🇷  82.6 ሚሊዮን ጎብኝዎች

➋ አሜሪካ 🇺🇸  75.6 ሚሊዮን ጎብኝዎች

➌ ስፔን 🇪🇸  75.6 ሚሊዮን ጎብኝዎች

➍ ቻይና 🇨🇳 59.3 ሚሊዮን ጎብኝዎች

➎ ጣሊያን 🇮🇹 52.4 ሚሊዮን ጎብኝዎች

➏ እንግሊዝ 🇬🇧 35.8 ሚሊዮን ጎብኝዎች

➐ ጀርመን 🇩🇪35 .6 ሚሊዮን ጎብኝዎች

➑ ሜክሲኮ 🇲🇽  35 ሚሊዮን ጎብኝዎች

➒ ታይላንድ 🇹🇭  32.6 ሚሊዮን ጎብኝዎች

➓ ቱርክ 🇹🇷  30 ሚሊዮን ጎብኝዎች

ለተጨማሪ ምስሉን ይመልከቱ።

╭══•|❀:✧๑♡๑✧❀|: ══╮
              @ewentesfa
╰══•ೋ•✧๑♡๑✧• ══╯
ልዩ የኢድ በዓል አሸላማ ጥያቄና መልስ ውድድር

📆 ቀን፡ በኢድ ዋዜማ ምሽት 2 ሰዓት

☞ ለተጨማሪ 50 ሰዎች👨‍🦳👨‍🦳 ይህንን መልዕክት ሲያጋሩ ተጨማሪ 40 MB🎁

ውድድሩን ለመደገፍ  @keyeferju ላይ ያነጋግሩን፡፡

🗣#ይመልሱ_ይሸለሙ
🗣#መፅሐፍትን_ያውርዱ
          👇👇👇👇👇👇
              @ewentesfa
#የኢድ_በዓል_አሸላሚ_ጥያቄዎች
➊ ቁርኣን በየትኛው ወር ወረደ?

➋ በዓለም ላይ ረዥሙ ፏፏቴ የት ሀገር ይገኛል?

➌  በእስልምና የመጀመሪያው ሙአዚን ማነው?

➍ የዓለማችን ትልቁ ዋሻ የት ሀገር ይገኛል?

➎ በዩኔስኮ የዓለም ቅርስ መዝገብ ላይ የምትገኝ ብቸኛ ሀገር ማነች?

ጉርሻ:

➏ የእስልምና መሰረቶች ስንት ናቸው ? ምንድን ናቸው?


🚫 መልሳችሁን ስትልኩልን ሙሉ ስማችሁን እንዳትረሱ፤መልሱን እስከ ነገ ማታ2 ሰዐት (02/08/2016ዓ.ም) ድረስ ብቻ አድርሱን!

⭕️ መልሳችሁን @keyeferju ላይ ላኩልን!

ማስታወሻ፡ቀድመው ለሚመልሱ #ሶስት ተሳታፊዎች ሽልማታቸው ይደርሳቸዋል፡፡

           ኢድ_ሙባረክ

     🗣#ይመልሱ_ይሸለሙ!

                @ewentesfa
#የኢድ_በዓል_አሸላሚ_ጥያቄ_መልሶች
➊ ቁርኣን በየትኛው ወር ወረደ?

በረመዳን ወር

➋ በዓለም ላይ ረዥሙ ፏፏቴ የት ሀገር ይገኛል?

ኤንጅል ፏፏቴ - ቬንዙዌላ 🇻🇪

➌  በእስልምና የመጀመሪያው ሙአዚን ማነው?

ቢላል

➍ የዓለማችን ትልቁ ዋሻ የት ሀገር ይገኛል?

ቬትናም 🇻🇳

➎ በዩኔስኮ የዓለም ቅርስ መዝገብ ላይ የምትገኝ ብቸኛ ሀገር ማነች?

ቫቲካን 🇻🇦

ጉርሻ:-

➏ የእስልምና መሰረቶች ስንት ናቸው ? ምንድን ናቸው?

አምሥት ናቸው እነርሱም፦
ሀ. የእምነት ምስክርነት (ከአላህ በስተቀር ማንም ሊመለክ አይችልም እና ሙሐመድ የአላህ መልእክተኛ ናቸው)
ለ. ሰላት (ሶላት) መስገድ
ሐ. ዘካ (ምጽዋት) ማድረግ
መ. የረመዷን ፆምን ማክበር
ሠ. የጉዞ አቅም ከቻለ ሀጅ (የተቀደሰ ቤት ጉዞ) ማድረግ


           መልካም የኢድ በዓል

     🗣#ይመልሱ_ይሸለሙ!

                @ewentesfa
#የኢድ_በዓል__አሸላሚ_ጥያቄዎችን_በሙሉ_የመለሱ_ተሳታፊዎች_የሚከተሉት_ናቸዉ 

1. ሳለአምላክ ምሕረቴ 8:07
2. ልዑል ዛሬ 8:19
3. አረፈዐይኔ ዳመነ  8:24
4. ስራው አርጌ ታደለ 8:40
5. አንተነህ ጌታቸው 8:41
6. ዳዊት 9:00
7. ይትባና አቤል 9:15
8. ካሊድ ኢብኑ 9:35
9. ታደለ 10:37
10. ዳዊት 10:41
11. ወርቁ ጥበቡ Apr 10 7:33
12. መለሠ ተስፋዬ Apr 10 8:00
13. የማርያም Apr 10 8፡45
14. ሰሚራ መሐመድ Apr 10 11:21
15. ዱባለ አባተ Apr 10 4፡02
16.  ሆሜር አለማየሁ Apr 10 4፡09

#ሳለአምላክ_ምሕረቴ#ልዑል_ዛሬ እና #አረፈዐይኔ_ዳመነ የኢድ ጥያቄዎችን ሙሉ በሙሉ በመመለስ  አሸንፈዋል እንኳን ደስ ያላችሁ👏👏

በውድድሩ ላይ #27ሰዎች ተሳትፈው #16ሰዎች ሙሉ በሙሉ መልሰዋል

       ➹ይመልሱ፤ይሸለሙ፤ይሸልሙ
                     👇🏾👇🏾👇🏾
               @ewentesfa
#የአለማችን_አስር_ብዙ_ሰማይ_ጠቀስ_ህንፃዎች_ያላቸው_ሐገሮች

♧ እንደ ሰማይ ጠቀስ ሴንተር ድረ-ገጽ በ150m+፣ 200m+፣ 300m+ ከፍታ የተከፋፈሉ ሰማይ ጠቀስ ፎቆች ያሏቸው 70 አገሮች አሉ። ደቡብ ምስራቅ እስያ 7 አገሮችን ለዚህ ዓለም አቀፋዊ ዝርዝር አስተዋውቋል።

1. ቻይና 🇨🇳
2. አሜሪካ 🇺🇸
3. ዩናይትድ አረብ ኤምሬትስ 🇦🇪
4. ማሌዥያ 🇲🇾
5. ጃፓን 🇯🇵
6. ደቡብ ኮሪያ 🇰🇷
7. አውስትራሊያ 🇦🇺
8. ካናዳ 🇨🇦
9. ኢንዶኔዥያ 🇮🇩
10. ታይላንድ 🇹🇭

ማሳሰቢያ: የተጠናቀቁ ሕንፃዎች ብቻ ናቸው, በግንባታ ላይ ያሉ ሕንፃዎች በዝርዝሩ ውስጥ አይካተቱም.

ምንጭ፡ ሰማይ ጠቀስ ህንጻ ማእከል

╭══•|❀:✧๑♡๑✧❀|: ══╮
@ewentesfa
╰══•ೋ•✧๑♡๑✧• ══╯
ልዩ የፋሲካ(የኢየሱስ ክርስቶስ ትንሣኤ) ጥያቄና መልስ ውድድር

📆 ቀን፡ ቅዳሜ ሚያዚያ 26 2016 ዓ.ም ምሽት 2 ሰዓት

☞ ለተጨማሪ 50 ሰዎች👨‍🦳👨‍🦳 ይህንን መልዕክት ሲያጋሩ ተጨማሪ 40 MB🎁

ውድድሩን ለመደገፍ  @keyeferju ላይ ያነጋግሩን፡፡

🗣#ይመልሱ_ይሸለሙ
🗣#መፅሐፍትን_ያውርዱ
          👇👇👇👇👇👇
              @ewentesfa
#የትንሣኤ_አሸላሚ_ጥያቄዎች
➊ በመጽሐፍ ቅዱስ የእድሜ ባለፀጋ የሆነው ማነው? ስንት ዓመትስ ኖረ?

➋ መሰረታዊ ቀለሞች የሚባሉት ምን ምን ናቸው?

➌ ጎለጎታ ማለት ምን ማለት ነው?

➍ ሞናሊዛን የሣለው ማነው?

➎ ኤሌክትሪክን ማን አገኘው?

ጉርሻ:

➏ በመፅሐፍ ቅዱስ ሳይወለድ የሞተው ወይም ወደመቃብር የወረደው ብቸኛው ሰው ማን ነው?


🚫 መልሳችሁን ስትልኩልን ሙሉ ስማችሁን እንዳትረሱ፤መልሱን እስከ ነገ ማታ2 ሰዐት (27/08/2016ዓ.ም) ድረስ ብቻ አድርሱን!

⭕️ መልሳችሁን @keyeferju ላይ ላኩልን!

ማስታወሻ፡ቀድመው ለሚመልሱ #ሶስት ተሳታፊዎች ሽልማታቸው ይደርሳቸዋል፡፡

         መልካም_ የትንሣኤ_በዓል

     🗣#ይመልሱ_ይሸለሙ!

                @ewentesfa
#የትንሣኤ_አሸላሚ_ጥያቄ_መልሶች
➊ በመጽሐፍ ቅዱስ የእድሜ ባለፀጋ የሆነው ማነው? ስንት ዓመትስ ኖረ?

ማቱሳላ የኖረበት ዘመን 969

➋ መሰረታዊ ቀለሞች የሚባሉት ምን ምን ናቸው?

ቢጫ፣ ሰማያዊ፣ ቀይ

➌ ጎለጎታ ማለት ምን ማለት ነው?

የራስ ቅል

➍ ሞናሊዛን የሣለው ማነው?

ሊዮናርዶ ዳ ቪንቺ

➎ ኤሌክትሪክን ማን አገኘው?

ቤንጃሚን ፍራንክሊን

ጉርሻ:

➏ በመፅሐፍ ቅዱስ ሳይወለድ የሞተው ወይም ወደመቃብር የወረደው ብቸኛው ሰው ማን ነው?

አዳም፤ ተፈጠረ እንጅ አልተወለደም

         መልካም_ የትንሣኤ_በዓል

     🗣#ይመልሱ_ይሸለሙ!

                @ewentesfa
#የትንሣኤ_በዓል__አሸላሚ_ጥያቄዎችን_በሙሉ_የመለሱ_ተሳታፊዎች_የሚከተሉት_ናቸዉ 

1. ግዛቸው የሻምበል 8:09
2. ተመስገን ዮሐንስ 8:10
3. ሳለአምላክ ምሕረቴ 8:10
4. ታደለ 8:16
5. መለሠ ተስፋዬ 8:17
6. ሚኪያስ አለማየሁ 8:20
7. ተስፋዬ አስረስ 8:20
8. ልዑል ዛሬ 8:22
9. ቻላቸው መስፍን 8:23
10. ኢየሩሳሌም ዱባለ 8:26
11.አሌ  አበበ 8:34
12. ኢዩኤል አረጋ 8:36
13. ዳዊት 8:40
14. ግዛ ተሜ 9:02
15. ሃይሉ ተስፋዬ 9:33
16. ዘሪሁን በላይ 10:04
17. ከበደ መንገሻ 10:05
18. እውነቱ ካሳ 10:27
19. የአብሥራ በቀለ 11:18
20. ሠላም ኢትዮጵያ 11:34
21. እንደሻው ተካበ 11:43
22. የማርያም 11:50
23. አገዘ ታደሠ May 5 10:48
24. ወርቅነህ ጥበቡ May 5 1:23
25. ካብታሙ ፀጋዬ May 5 5:18

#ግዛቸው_የሻምበል #ተመስገን_ዮሐንስ እና #ሳለአምላክ_ምሕረቴ  የትንሣኤ ጥያቄዎችን ሙሉ በሙሉ በመመለስ  አሸንፈዋል እንኳን ደስ ያላችሁ👏👏

በውድድሩ ላይ #50ሰዎች ተሳትፈው #25ሰዎች ሙሉ በሙሉ መልሰዋል

       ➹ይመልሱ፤ይሸለሙ፤ይሸልሙ
                     👇🏾👇🏾👇🏾
               @ewentesfa
#ጥንታዊ_የአፍሪካ_አየር_መንገዶች

1. የግብፅ አየር መንገድ በ1932 ተመሰረተ 🇪🇬

2. የደ/አፍሪካ አየር መንገድ በ1934 ተመሰረተ 🇿🇦

3. የአንጎላ አየር መንገድ በ1938 ተመሰረተ 🇦🇴

4. የኢትዮጵያ አየር መንገድ በ1945 ተመሰረተ🇪🇹

5. የምስራቅ አፍሪካ አየር መንገድ በ1946 ተመሰረተ

6. የሱዳን አየር መንገድ የካቲት1946 ተመሰረተ🇸🇩

7. የመካከለኛው አፍሪካ አየር መንገድ በ1946 ተመሰረተ 🇨🇫

8. የላይቤሪያ አየር መንገድ፣ ቱኒስኤር (ሁለቱም በ1948 ተመስርተዋል) 🇱🇷

╭══•|❀:✧๑♡๑✧❀|: ══╮
              @ewentesfa
╰══•ೋ•✧๑♡๑✧• ══╯
#የአለም_ጥንታዊ_አየር_መንገዶች

KLM አየር መንገድ በጥር 7, 1919 ተመሰረተ

አቪያንካ አየር መንገድ በታህሳስ 5,1919 ተመሰረተ

ኳንታስ አየር መንገድ በህዳር 16,1920 ተመሰረተ

ኤሮፍሎት አየር መንገድ በመጋቢት 17, 1923 ተመሰረተ

ቼክ አየር መንገድ በጥቅምት 6, 1923 ተመሰረተ

ፊንኤር አየር መንገድ በህዳር 1, 1923 ተመሰረተ

ዴልታ አየር መንገድ በግንቦት 30, 1924 ተመሰረተ

ታጂክ አየር መንገድ በመስከረም 3, 1924 ተመሰረተ

ሰርቢያ አየር መንገድ በሰኔ 17, 1927 ተመሰረተ

አይቤሪያ አየር መንገድ በሰኔ 20, 1927 ተመሰረተ

╭══•|❀:✧๑♡๑✧❀|: ══╮
              @ewentesfa
╰══•ೋ•✧๑♡๑✧• ══╯
#ሽንታችን_ስለጤናችን_ምን_ይነግረናል?

♧ ሽንት በምንመገበው ምግብ፣ በምንወሰደው መድኃኒት እንዲሁም በምንጠጣው የውኃ መጠን ምክንያት ቀለሙ፣ ጠረኑ እንዲሁም ዓይነቱ ይቀያየራል።

♧ ሽንት ሰውነታችን በፈሳሽ መልክ ቆሻሻን የሚያስወግድበት አንዱ መንገድ ሲሆን በዋናነት ውኃ፣ ጨው፣ ኤሌክትሮላይቶች እንደ ፖታሺየም እና ፎስፈረስ፣ ዩሪያ እና ዩሪክ አሲድ የሚባሉ ኬሚካሎች በውስጡ ይዞ ይገኛል።

♧ እነዚህም ኩላሊት መርዛማ ንጥረ ነገሮችን እና ሌሎች መጥፎ ነገሮችን ከደም ውስጥ ሲያጣራ የሚከሰቱ ሲሆኑ፤ መድኃኒት፣ የተለያዩ ዓይነት ምግቦች እና ሕመሞች የሚወገደው የሽንት ዓይነት ላይ ለውጥ እንዲኖረው ያደርጋሉ።

♧ ጤናችን ያለበትን ሁኔታ የሚነግሩን የቀለም ዓይነቶች እንዳሉ ስንቶቻችን እናውቃለን?

ጤናማ የሽንት ቀለም ምን ዓይነት ነው?

♧ ሽንት ፈዛዛ ቢጫ ወይንም ወርቃማ ቀለም ሲኖረው ሰውነት በቂ ውኃ አግኝቷል፤ ጤናማ ነው እንላለን።

♧ ሽንት ምንም ዓይነት ቀለም ከሌለው (ውኃ ቀለም) ከሆነ ደግሞ ሰውነታችን በብዛት ውኃ እንዳገኘ እና እንዳበዛን ያመላክታል።

♧ ከልክ በላይ ውኃ ማብዛት በሰውነታችን ወስጥ የኤሌክትሮላይት መዛባት ያስከትላል፤ በመሆኑም የምንወስደውን የውኃ መጠን በመቀነስ በቀን ውስጥ ከ6 እስከ 8 ብርጭቆ ውኃ እንድንጠጣ ይመከራል።

♧ ቀላ ያለ ሮዝ ቀለም ለኩላሊት እና ለተለያዩ በሽታዎች  መጋለጥን ሊያመላክት ይችላል።  
                                                            
♧ አረንጓዴ ወይም ሰማያዊ የሽንት ቀለም በዘር ምክንያት የሚመጡ በሽታዎች እና የሌሎች በሽታዎች ምልክት ሊሆን ይችላል።
                                       
♧ ደማቅ ቢጫ ጤናማነትን የሚያሳይ ቢሆንም ይበልጥ ውኃ መጠጣት እንደሚያስፈልግ ግን ያመላክታል።

♧ ቡናማ ቢጫ ከፍተኛ የሆነ የውኃ እጥረት እንዲሁም የጉበት በሽታ ምልክት ሊሆን ይችላል።

♧ እንደ ካሮት፣ ቀይ ስር እና የተለያየ ቀለም ያላቸው ምግቦች ሽንትን ወደ ቀይ ወይም ሮዝ ቀለም ይቀይሩታል። አንዳንድ መድኃኒቶች እንዲሁ የሽንት ቀለምን እና ጠረንን የመቀየር አቅም አላቸው።

♧ ከነዚህ ጋር በተያያዘ የሚፈጠሩ የሽንት ቀለም ለውጦች በአጭር ቀናት ውስጥ ተመልሰው የሚስተካከሉ ናቸው።

♧ ከዚህ ባለፈ የሰውነታችን ጤና ያለበትን ሁኔታ የሚያመላክቱ ከጤናማው ቀለም ለየት ያሉ ምልክቶች ሲኖሩ በአቅራቢያ ወደሚገኝ የጤና ተቋም በመሄድ ሐኪም ማማከር ያስፈልጋል።

ምንጭ: ኢቢሲ

╭══•|❀:✧๑♡๑✧❀|: ══╮
              @ewentesfa
╰══•ೋ•✧๑♡๑✧• ══╯
HTML Embed Code:
2024/06/15 06:09:28
Back to Top