TG Telegram Group Link
Channel: ኢትዮጵ
Back to Bottom
Forwarded from Peka Tube - ፔካ ቲዩብ (ኃይለሚካኤል ዘኢትዮጵያ ' ተዘከር አንተ ቅድመ አበሳከ፤ ከመ ኢይዘክርብከ ፈጣሪከ ')
እንኳን ለቅድስት ሥላሴ ዓመታዊ በዓል አደረሳችሁ፤ አደረሰን።

ሥሉስ ቅዱስ ሀገራችንን ኢትዮጵያን በምህረት ዓይን ይመልከትልን። 🙏

" አሐዱ አብ ቅዱስ
አሐዱ ወልድ ቅዱስ
አሐዱ ውእቱ መንፈስ ቅዱስ"

" እንደ #አብርሃም እንደ #ይስሐቅ እንደ #ያዕቆብም ሦስት የምንል አይደለም፤ #በገጽ_ሦስት ሲሆን #በባሕርይ_አንድ ነው እንጂ።
ከፍጥረት ሁሉ እንደሚቀድም እንደ #አዳም አንድ የምንል አይደለም፤ #በባሕርይ_አንድ ሲሆን #ሦስት ነው እንላለን እንጂ። " ቅዳሴ ማርያም

📌 #ለቅድስት_ሥላሴ እሰግዳለሁ።

👉 #በሥላሴ እታመናለሁ።
👉 ብወድቅ #በሥላሴ እነሣለሁ።
👉 ብንገዳገድ #በሥላሴ እደገለሁ።
👉 ብራብ #በሥላሴ እጠግባለሁ።
👉 ብጠማም #በሥላሴ ከሚሰጠኝ ወይን ጠጅ እረካለሁ።
👉 ብደኸይ #በሥላሴ እበለጽጋለሁ።
👉 ብራቆት #በሥላሴ እለብሳለሁ።
👉 ብታመም #በሥላሴ እድናለሁ።
👉 ብቆስል #በሥላሴ እፈወሳለሁ።
👉 ኃዘን ቢያገኘኝ #በሥላሴ እደሰታለሁ።
👉 ትካዜም ቢያገኘኝ #በሥላሴ እጽናናለሁ።
👉 ብታመምም #በሥላሴ ቸርነት እድናለሁ።
👉 ብሞትም #በሥላሴ ተስፋ አድርጌ እነሳለሁ።

@EthiopeTowoderos
The best speech in the world!
“If the world goes against the truth,then atinatious goes against the world” /the 1st pop atinatious/
“ዓለም እውነቱን ለመቃወም ከተነሳ አትናቴዎስ ዓለምን ለመቃወም ይነሳል!"ይላል!
ብቻውንም ቢሆን እንደማለት!
እና ምን ለማለት ነው....?
"ምኒልክ ዛሬም ንጉስ ነው!
ባልቻ ዛሬም ይነፍሳል...!
አብይ አህመድ ዛሬም ይዋሻል..!
ነገም ይዋሻል! እስከመቃብር ይዋሻል!
አጀንዳ አድርጎ የተነሳበት ነውና ሃሰተኛ ምላሱ እስከ ሞት ድረስ ሳይታጠፍ ይቀጥላል....! በሂደቱም የብዙዎች እልቂትም ይቀጥላል...! ስለዚህ
ይህን እውነት መላው ህዝብ ቢክድና ቢቃወም እንኩዋ እኔ ብቻየን እናገረዋለሁ ለማለት ነው!
ለማንኛውም አብይን አምናችሁ ለዘመቻው የተነሳችሁ የኢትዮጵያ ብሄርብሄረሰቦችና ጀዝኦች ህወሃትን ካሸነፋችሁ በሁዋላም ይሁን በፊት ብቻ ግን በነካ እጃችሁ ከኢትዮጵያ ድንበር 85 ኪ.ሜ ዘልቃ የገባችውን ታሪካዊ ጠላታችንን ሱዳንንም አስወጥታችሁልን ብትመለሱ ጥሩ ነው::
የቀድሞ የኢትዮጵያ ነገሥታት የስልጣን ጸብ ውስጥ ገብተው እርስ በርስ እየተዋጉ በድንገት የውጭ ወራሪ ጦር ሲመጣ የራሳቸውን ጸብ አቆይተው በጋራ ዘምተው ጠላትን ካባረሩ በሁዋላ ነበር እንደገና ወደራሳቸው ጦርነት ይመለሱ የነበረው::
ይህ አካሄድ በራሱ ሃሪፍ ነገር አለው:: ከውጭ ጠላይ የማረኩትን መሳሪያ የርስ በርስ የስልጣን ጸቡን ለማካሄድ ጥቅም ላይ ያውሉታል!
ይህ ሁሉ የኢትዮጵያ ጉዋንዴና ምንይሽር እንዲሁም አብራራው በዚያ መንገድ የተሰበሰበ ነው...!
ችግሩ ግን እንዲህ ያለው እውነት የሾርት ሜሞሪ ባለቤት ለሆኑ ሰዎች የሚገባቸው አለመሆኑ ነው!
ብቻ ግን አብይ አህመድ እየተዋጋና እያዋጋ ያለው ለስልጣኑና ለስልጣኑ ብቻ ነው!የአማራና የትግራይ ህዝብ መቸም ቢሆን እንዳይስማሙና እንዳይታረቁ አድርጎ ለማንኮታኮት ነው! ሱዳን የኢትዮጵያን መሬት እንጂ ስልጣኑን ስለማትቀማው ሊዋጋት አይፈልግም!ህወሃት ግን በስልጣኑ ስለመጣች ሊዋጋት ይፈልጋል! ይሄን ደግሞ እኔ አይደለም ያልኩት!እራሱ አብይ አህመድ ያለውን ነው የደገምኩት! ይሄው ስሙት!
*************
ትንሳኤዋን ማን ነው የሚገታው ከ ከፍታዋስ ማን ይሆን ዝቅ የሚያደርጋት ?

አይዟችሁ የጨለማው በርኖስ ይገለጥ ዘንድ ድቅድቁ ጨለማ ይበረታል!

ይህ ክፉ ቀን ፣ይህ ጭንቅ፣ ይህ መከራ ፣ ይህ ሁሉ ግዞት የሚመጣ መሆኑን ቀደመን በ አባቶቻችን ስለተረዳን እስካሁን በሆነው ከዚህ በኋላም በሚሆነው ነገር ሁሉ አንገረምም።

የ አለም የፖለቲካ ርዕዮት የሚንጣት ፤የግራ ና ቀኝ ዘመም የፖለቲካ እሳቤ ብቻ የሚያምሳት፤ ከስጋዊ ና ደማዊ ሰወች ብቻ የሚወረወር የፖለቲካ ሸክም የተሸከምች ምንዱብ አገር መስላ ትታየና ይሆናል። ግን ጦርነቱ ከስጋዊያኑ ጋር ብቻ ሳይሆን በስጋዊ እሳቤ በሚመሩት ጥሉቁ ከሚጋልባቸው ፈረሶች ጋር ነው።

የኢትዮጵያ መፍትሔ መዳኛዋ ከታሰረችበት አዚም መላቀቂያዋ የእግዚአብሔር መንገድ ብቻ ነው። ይህ የተሰራው የጠላት አዚም ከ ኢትዮጵያ ምድር የሚነሳበት ጊዜ አለው ።
አወን ኢትዮጵያ ትንሳኤ አላት ከ ገባችበት ቅርቃር ከዘር ፖለቲካ ተላቃ ከፍ ከፍ የምትለበት ዘመን ከፊቷ አለ።
ታላቅነቷ የሚገለጥበት፣ የተዳፈኑ የመሰሉ ድንቅ ማንነቶቿ ለአለም ይፍ የሚሆንበት፣ ልጆቿ ከተ ሰደዱበት አገር የሚመለሱበት አምሳለ ከንአን የምትሆንበህ ጊዜ አላት።

ያ ዘመን በተስፍ እንጠብቀዋለን!

ይህ ባዶ ምኞት ፣የማይገለጥ እውነት፣ አይደለም። አወ አገሬ ትንሳኤ አላት ስንል በ ቀቢጸ ተስፊ ተሞልተን እንዲሆን የፈለግነውን ሳይሆን አበው የነገሩን ወደ ፊት የሚገለጥ እውነት ነው።
ከፍ ከፍ የምትልበታ ያ ጊዜ ይመጣል።

በዙወቹ ትንሳኤዋን ሊቀብሩ ይዳዳቸዋል፤ በፖለቲካ ጫና የሚቀር ትንሳኤ ያላት ይመስል ብኩን የፉኝት ልጆች ሊጥሏት ይታገሏታል።
የመንፈሱ አለም ምኞት በጠንካራ አምልኳ በእምነትና ሃይማኖት የማትገለጥ ደካማ ኢትዮጵያን መፍጠር ነው።

እውነት ነው ከሆነብን ይልቅ ወደ ፊት የሚሆነው ይብሳል፤
ከተደረገብን ይልቅ ሊደርግ የታሰበው ያስፈራል።
እውነት ነው ኢትዮጵያ የተጫነባት ቀንበር ከብዷታል ፤ ትክሻወቿ ተዳክመዋል ፤ ከዚህም የባሰ ዘመን ሊመጣ ይችላል።
ግን ተስፋ አለን በእግዚአብሔር የተስፋ ቃል ውስጥ እውነተኛ ሰላም ፣ ፍትህ ፣ ጥበብ እና ተስፋ አለ ና ።

ትንሳኤውን አሻግረው ለተመለከቱ ትንሳኤው በፈቃደ እግዚአብሔር ጊዜውን ጠብቆ ይገለጥላቸዋል ። እስኪገለጥ ግን ጽኑ ተጋድሎ እና ብርቱ የሃይማኖት ጽናት ያስፈልጋል ።

ይህ ፈለገ ጥበባት ነው ሀሳብ አስተያየት ጥቆማ @Nabuti21 ላይ አድርሱኝ።

10/12/7513
Forwarded from ኢትኤል ዘ ተዋሕዶ (Bereket)
የአባታችን_አለቃ_አያሌው_ታምሩ_ስለ_ኢትዮጵያ_ትንቢታዊ_ንግግር

አሁን_ስላላለውና_ወደፊት_ስለሚሆነው
...እግዚአብሔር አምላካችን አኹንም እሱ ከወደቅንበት አንስቶ የዓለም ጥፋት የማይቀር ነው፡፡ አኹን በያዝነው ሰልፍ ዐይነት ቅዱሳን የተናገሩት እየደረሰ ስለሆነ #ሦስተኛው_የዓለም_ጦርነት የማይቀር ነው፡፡ አኹን የሰው ዘር ይተርፋል የሚባለው በኢትዮጵያ ስለኾነ ይኽንን እድል እንዳያስቀርብን ፈጣሪያችን ቤተክርስቲያናችን አስቀድማ ከወደቀችበት እንድትነሳ ነው መጸለይ ያለብን፡፡ የሰው ዘር ማትረፍ እንድትችል ይኽች ሀገር እግዚአብሔር አምላካችን በቸርነቱ እርሱ ላሰበው ለጸጋው ያዘጋጀን #ብርሃን_ትንሳኤውን በሰላም ለማየት ያብቃን ፡፡»
➲ መጋቢት 22/1999 ዓ.ም በመኖሪያ ቤታቸው ካስተማሩን ትምህርት የተወሰደ።
በእውነት የአባታችን አለቃ አያሌው ታምሩ በረከታቸው ይደርብን!!
እግዚአብሔር ይመስገን!!!
Forwarded from Tadele Tibebu - ታደለ ጥበቡ (Tadele Tibebu)
#አድዋን_ስታወሱ_ጊዮርጊስን_አትርሱ! #ሼር

በክብረ ነገሥት መረጃ መሠረት የቅዱስ ጊዮርጊስ ጽላቱ ወደ ኢትዮጵያ የገባው በ13ኛው መክዘ በዐፄ ዓምደ ጽዮን (1307-1336 ዓ.ም.) ነው።

በኢየሩሳሌም የኢትዮጵያ ገዳም ውስጥ ለብዙ አመታት የነበሩት አባ ልዑለ ቃል የተባሉ መነኩሴ ከደማስቆ (ሶርያ) ደብረ ይድራስ ከሚባለው ገዳም አምጥተው ለዐፄ ዓምደ ጽዮን እንዳስረከቡና ንጉሡም ቤተ ክርስቲያን እንዳሰሩ፤ ገድሉም ከዐረብኛ ወደ ግእዝ እንደተተረጎመ ማስረጃዎች ይጠቁማሉ።

ከዐፄ ዓምደ ጽዮን በኋላ ከ1422-1425 ዓ.ም.
የነገሠው የቀዳማዊ ዳዊት ልጅ የሆነው ተክለ ማርያም (ሕዝብ ናኝ) የቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን አሰርተው ነበረ። ይኼ ቤተ ክርስቲያን የተሰራው ሰሜን ሸዋ፣ ሞረትና ጅሩ ከእነዋሪ ከተማ አጠገብ “ደይ” እየተባለ ከሚጠራው ጠረጴዛማ ተራራ ላይ ሲሆን ቤተ መንግሥቱም እዚሁ ተራራ ላይ ነበረ። ዛሬም የቤተ መንግሥቱ ፍርስራሽ ይገኛል።

ዐፄ ዓምደ ጽዮን ከአስር በላይ ታላላቅ ጦርነቶችን አድርጓል። አስሩንም ጦርነቶች በድል አድራጊነት ሲያጠናቅቅ የቅዱስ ጊዮርጊስ ፅላት ተለይቷቸው አያውቅም።

በ1426 ዓ.ም. "ቆስጠንጢኖስ ንጉሠ ነገሥት ዘኢትዮጵያ" ተብሎ ተጉለት ደጎ ላይ የነገሰው የቀዳማዊ ዳዊት የመጨረሻ ልጅ ዘረዓ ያዕቆብ በ1437 ዓ.ም. አሕመድ በድላይን ድል ያደረገው የቅዱስ ጊዮርጊስን ፅላት ይዞ ነበረ።

ዳግማዊ ዐፄ ምኒልክም ጥቅምት 2 ቀን 1888 ዓ.ም. ወደ አድዋ ሲዘምቱ የቅዱስ ጊዮርጊስ ታቦት ይዘው ነበረ።

የካቲት 22 ለ23 አጥቢያ ከጧቱ 11:00 ሰዓት አድዋ ላይ ጦርነቱ ጀመረ። በዚህን ጊዜ በጦርነቱ መሀል ድንቅ ተአምር ታዬ። ይኸውም ቀይ፣ ቢጫና አረንጓዴ ቀስተ ደመና ነው። በቀስተ ደመናው ውስጥ ደግሞ መልኩ አረንጓዴ የሚመስል ጢስ ወጣ። ጢሱም ውስጥ የነጎድጓድ ድምጽ ተሰማ። ታላቅም ሽብር ሆነ። ቅዱስ ጊዮርጊስ በነጭ ፈረስ ላይ ተቀምጦ ተገለጠ።

ከዚህን በኋላ የኢጣሊያን ወታደሮች መዋጋት አልሆነላቸውም። መሳሪያ የያዙበት ሰይፍ የጨበጡበት ክንዳቸው ዛለ። በግንባራቸውም ፍግም እያሉ ወደቁ። ምድር ጠበበቻቸው። የኢትዮጵያ አርበኞች ፈጇቸው። የተረፉትንም ማረኳቸው። ቀኑም የካቲት 23 1888 ዓ.ም. ዕለተ ጊዮርጊስ ነበር።

ተርፈው ወደ ሀገራቸው የተመለሱት የኢጣሊያ ወታደሮችም ከኢትዮጵያ አርበኞች መሀል አንድ ወጣት በነጭ ፈረስ ተቀምጦ ሰራዊታቸውን እንደፈጀባቸው ገለጡ። የድሉ ምንጭም የእግዚአብሔር ሀይልና ኢትዮጵያዊን ለሃይማኖታቸው ለነጻነታቸው የነበራቸው ቀናዒነት እንደሆነ የራሳቸው የኢጣሊያ ታሪክ ጽሐፊ የነበረው ኮንቲ ሩስኒ በሮም አደባባይ መሰከረ።

የኢትዮጵያ ሠራዊት ጠቅላይ አዛዥ ዳግማዊ ዐፄ ምኒልክም ለፈረንሣዊው ሙሴ ሞንዶን ከጻፉለት የምሥራች ደብዳቤ እንዲህ ብለው ነበር፣

" የምሥራች በእግዚአብሔር ቸርነት የየካቲት ቅዱስ ጊዮርጊስ ዕለት ኢጣልያንን ድል አድርጌ መታሁት፡፡ በጨረቃ ሲገሰግስ አድሮ እሰፈሬ ድረስ መጥቶ ገጠመኝ፡፡ አምላከ ኃያላን ረድቶኝ ፈጀሁት፡፡ ደስ ብሎኛል ደስ ይበልህ"

እንደገና መጋቢት 23 ቀን 1888 ዓ.ም ዐፄ ምኒልክ ለሩሲያው ንጉሥ ት‘ዛር ኒቆላዎስ 2ኛ በጻፉት ደብዳቤያቸው

"እንደ አውሮፓ ነገሥታት ሥራት ሁሉ ጠብ መፈለጋቸውን ሳያስታውቀኝ፣ እንደ ወምበዴ ሥራት ሌሊት ሲገሰግስ አድሮ ሲነጋ ግምባር ካደረው ዘበኛ ጋር ጦርነት ጀመረ፤ ጥንት ከአሕዛብና ከአረመኔ አገራችን ጠብቋት የሚኖር አምላክ ከእኛ ባይለይ በእግዚአብሔር ኃይል ድል አደረግሁት" በማለት ድሉ የእግዚአብሔር መሆኑን አስረግጠው ተናግረው ነበር፡፡

ለሀሳብ ለአስተያየት በዚህ ሊንክ @Tadeletibebut
ETHIOPIA(ኢትዮጵያ) 🇪🇹🇪🇹

➊ በአፍሪካ በቀኝ ግዛት ያልተገዛች ብቻኛ ሀገር ናት።
➋ ከሌሎች በተለየ አስራ ሶስት ወር ያላት ሀገር ናት።
➌ ከ80 በላይ ቋንቋ ይነገርባታል።
➍ የቡና ተክል ለመጀመሪያ ጊዜ የተገኘው ኢትዮጵያ ውስጥ ነው።
➎ 13 ቅርሶችን በ UNESCO በማስመዝገብ ከአፍሪካ ቀዳሚ ናት።
➏ ኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኘው መርካቶ የፍሪካ ትልቁ የገበያ ማእከል ነው።
➐ በአሁጉራችን በህዝብ ብዛት ናይጄሪያን በመከተል ሁለተኛውን ስፍራ ይዛለች።
➑ በዓለማችን የባህር ወደብ ከሌላቸው ሀገራት በህዝብ ብዛት ቀዳሚ ናት።
➒ በአፍሪካ የራሷ ፊደልና ቁጥር ያላት ብቸኛዋ ሀገር ናት።
➓ በዓለማችን ብዙ ርቀት በመጓዝ ቀዳሚ የሆነው የአባይ ወንዝ መነሻ ናት።
➊➊ የኢትዮጵያ ዋና ከተማ የሆነችው አዲስ አበባ የአፍሪካ ህብረት መቀመጫ ናት።
➊➋ ከ200 በላይ የቋንቋ ዘዬ ይነገርባታል።
➊➌ የሀገሪቷ ሰም በመጽሐፍ ቅዱስ(42+)ና በቁራን በርካታ ጊዜ ተጠቅሷል።
➊➍ በአፍሪካ የመጀመሪያው የኦሎምፒክ ወርቅ ሜዳልያ ያስገኘው ኢትዮጵያዊው አበበ በቂላ ነው።
➊➎ ከሌሎች ሀገራት የተለየ የሰዓት እና የካላንደር አቆጣጠር አላት።
➊➏ ከአርመንያ በመቀጠል ክርስትና ብሔራዊ ሃይማኖቴ ነው ብላ የተቀበለች ሁለተኛዋ ሀገር ናት።
➊➐ በአፍርካ የመጀመሪያው መስጊድ መገኛ ናት።
➊➑ በቀንድ ከብት ብዛት ከአሁጉራችን ቀዳሚናት።
➊➒ ክርስቶስ የተሰቀለበት መስቀል የቀኝ ክፍሉ የሚገኝባት ሀገር ናት።
➋0 በኢትዮጵያ ውስጥ 924 የአእዋፍ ዝርያ ያሉ ሲሆን 23 ያህሉ በሌላ ዓለማት የማይገኙ ናቸው።

🗣➹share &Join
Forwarded from ፈለገ ጥበባት +++ (ናቡቴ)
የዓመቱ መስከረም 1 ቀን መቼ መቼ ትውላለች?
መስከረም አንድ ቀን መቼ እንደምትውል ለማወቅ ዓመተ ዓለምን ከመጠነ ራብዒት ጋራ ደምረን በእለታቱ መጠን በ7 አካፍለን
ቀሪው 1 ከሆነ ማክሰኞ ፤ቀሪው 2 ከሆነ ረቡእ፤ቀሪው 3 ከሆነ ሐሙስ፤ቀሪው 4 ከሆነ አርብ፤ቀሪው 5 ከሆነ ቅዳሜ፤ቀሪው 6 ከሆነ እሑድ፤ ያለ ቀሪ ከተካፈለ ሰኞ ይውላል።


የ2015 ዓ.ምየኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር 🌏
     
                       =========
👉በኢትዮጵያ ዘመን  አቆጣጠር ከክርስቶስ ልደት በፊት ዘመን የተቆጠረበት ጊዜ 5,500 ዓመት ነው ።
👉ይህም ዘመን ዘመነ ፍዳ፣ዘመነ ኩነኔ፣ ዘመነ ብሉይ ይባላል ።
👉ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ልደት ጀምሮ  ያለው ዘመን 2,015 ዓመት ሲሆን ይህም ዓመተ ምህረት ፣ዘመነ ሥጋዌ ፣ዘመነ ሀዲስ ፣ዘመነ መሲሕ  ይባላል ።
👉ዘመነ ብሉይ እና ዘመነ ሐዲስ  ሲደመሩ ውጤታቸው  ዐመተ ዓለም ተብሎ ይጠራል ።
👉5,500ዓመተ ፍዳ+2,015 ዓመተ ምሕረት
                =7,515 ዓመተ ዓለም
👉የዓመተ ዓለም  ጥቅም  ዓመተ ወንጌላውያንን ለማውጣት  ይጠቅመናል።
👉የ2,015 ዓ.ም ወንጌላውያኑን ለማወቅ ዓመተ ዓለምን  ለአራት ማካፈል ነው ።
               ሲካፈል ቀሪው
1ከሆነ ማቴዎስ  2ከሆነ ማርቆስ 3ከሆነ ሉቃስ ያለቀሪ ከተካፈለ ዮሐንስ ነው።
👉የ2,015 ዓ.ም ወንጌላውያኑን ለማግኘት
ዓመተ ኩነኔ+ዓመተ ምህረት =ዓመተ ዓለም
                   5,500+2,015 =7515
      7515÷4 =1878  ቀሪው 3️⃣ነው ።
ምክንያቱም 1878×4=7512 ሲሆን
              7515-7512=3️⃣ነው ።
ስለዚህ  የ2015ዓ.ም ወንጌላዊ  ቅዱስ ሉቃስ ነው።
👉4️⃣ተካፍሎ የሚደርሰው 1878 ቁጥር መጠነ ራብዒት ይባላል ።
👉መጠነ ራብኢት ማለት  ለ4️⃣ተካፍሎ የደረሰ ማለት ነው ።
        
👉ለኢትዮጵያውያን የዘመን መለወጫ መስከረም አንድ ቀን ነው።
👉መስከረም 1️⃣ቀን ለማግኘት ዓመተ ዓለምን እና መጠነ ራብኢትን እንደምራለን ።
👉የተደመረውን ቁጥርለሰባት ቀናት ማካፈል ።
በዚህም  መሠረት ለ7️⃣ቀናት ተካፍሎ የሚቀረው 1ከሆነ  ማክሰኞ 2ከሆነ ረቡዕ 3ከሆነ ሐሙስ 4ከሆነ ዓርብ 5ከሆነ ቅዳሜ 6ከሆነ እሑድ ያለቀሪ ከተካፈለ ሰኞ ይሆናል ።
👉ስለዚህ የ2,015ዓ.ም መስከረም 1️⃣ቀን
7515+1878=9393 //9393÷7=1341ቀሪ 6️⃣ነው
ምክንያቱም 1341×7======9387ይሆናል ።
                     9393-9387===6 ነው
ስለዚህ የ2,015 ዓ.ም መስከረም 1️⃣ቀን በዕለተ ዕሑድ ይውላል ።


መስከረም 1 በዋለበት ሚያዝያ 1 ይውላል
ጥቅምት 1 በዋለበት ግንቦት 1 ይውላል
ህዳር 1 በዋለበት ሰኔ 1 ይውላል
ታሕሣሥ 1 በዋለበት ሐምሌ 1 ይውላል
ጥር 1 በዋለበት ነሐሴ 1 ይውላል።



ይህም ማለት ለምሳሌ መስከረም 1 ቀን እሁድ ከዋለ ሚያዝያ 1 ቀንም እሁድ ይውላል ማለት ነው።
Channel photo updated
#የፈራ_ይመለስ
#አንዲት_ቤተክርስቲያን

ጉዟችን እስከቀራኒዮ ነው።
† † †† † †† † †† † †
ደሜን ሁሉ ጠጡት ስጋዬንም ብሉት፤
ማዕተቤን ከአንገቴ መቼም አትበጥሱት።
እኛ አንናወጽም ያም አለ ያም አለ፤
ትንሳዔን ለመድረስ ጥንትም ስቅለት አለ።
ይህም ቀን ያልፋል
ፈርኦንን ከነወታደሩ በቀይባህር ያሰጠመው የራሄል እንባ ነው። ቀይባህርን የከፈለው የሙሴ ጸሎት ነው።
ዳዊት ጎልያድን የጣለው አምላኩን ስለተማመነ ነው። ፍየል ነብር ሲያንቃት ትጮኻለች ። ጓደኞቿም ይጮኻሉ።
ስለጮኹ ነብሩ አይተዋቸውም። በገደላቸው ቁጥር ወኔ ይሰማዋል። ሌላ ይገድላል። ይጮኻሉ፤ ይሞታሉ ። አሁንም ይጮኻሉ ፤ይሞታሉ።
ከዚህ ለመዳን እንደ ራሄል ማንባት፣ እንደ ሙሴ መጸለይ፣ እንደ ዳዊት በእግዚአብሔር ማመን።
እግዚአብሔር እንባችንን ያብስልን
ከሱ ውጪ መፍትሄ የለንም🙏
Forwarded from Tadele Tibebu - ታደለ ጥበቡ (Tadele Tibebu)
"ከየትኛውም ብሄር ተወለድ የትኛውንም ዕምነት ተከተል ኢትዮጵያዊ ሆነህ በኢትዮጵያዊያን ባህልና ስረዓት አድገህ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ
ቤተ ክርስቲያን እንድትፈርስ እንድትከፋፈል
በምንም አይነት መንገድ አስተዋፆ
አታድርግ።" አቡሽ ዘለቀ
ጸሎተ ምህላ በባሕርዳር መስቀል አደባባይ (ምስካየ ኅዙናን መድኃኔዓለም)🙏🙏

ሄኖክ የኖላዊ ኄር ልጅ

ጥር 30/2015 ዓ.ም
በዚህ ወቅት ኢትዮጵያዊ ሆኖ ከኦርቶዶክስ ጎን አለመቆም ራስን እንደመካድ ይቆጠራል:: ኦርቶዶክስ ለኢትዮጵያና ለኢትዮጵያውያን ሐይማኖት ብቻ አይደለችም:: ኦርቶዶክስ ታሪክ ናት! ባህል ናት! ማንነት ናት! ፊደል ናት!ቁዋንቁዋ ናት! ኦርቶዶክስ ኢትዮጵያ ናት! ኢትዮጵያ ያለ ኦርቶዶክስ ምንም ናት! ኦርቶዶክስ መላውን የኢትዮጵያ ሕዝብ በታሪክ በባህል በልማድ በአኑዋኑዋር ዘይቤና በማንነት በስነምግባር በወዘተ...መላውን ኢትዮጵያዊ ዜጋ ያስተሳሰረች ገመድ ናት! ይህን ገመድ በፖለቲካዊ ሸፍጥ እና በአፈሙዝ መበጣጠስ አይቻልም! መንግስት ተብየው አካል በማይቻል ነገር ላይ ነው ጊዜውን እያጠፋ ያለው::
መንግስት ተብየው አካል ግጭቱን እና ደም መፋሰሱን ብሎም አገር ማፍረሱን እንደ ጥቅም ካልቆጠረው በቀር በዚህ ሴራ የሚያገኘው አንዳችም ትርፍና ጥቅም የለም:: በዚህ ሴራ የሚያገኘው ድልም ሆነ ፖለቲካዊ ትርፍ የለም! ይልቁንም ውድቀቱን ያፋጥናል::
ይህንን ዕውነት በየካቲት 5 ቱ ሐይማኖታዊና ፍጹም ሰላማዊ ሰልፍ ላይ ለመስዋዕትነት የቆረጠውን የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ምዕመን ሲያይ ይረዳዋል ብለን ተስፋ እናደርጋለን:: የካቲት 5 መንግስት የማይነካ ነገር እንደነካ የሚረዳበት ዕለት እንደሚሆን እንጠብቃለን! ወሳኝ ዕለት!!!
HTML Embed Code:
2024/03/28 00:54:35
Back to Top