TG Telegram Group & Channel
Channel: ኢትዮጵ
Back to Bottom
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#የሐሙስ_ውዳሴ_ማርያም

ዘር ምክንያት ሳይኾናት አምላክን የወለደች ድንግል፣ የማኅፀንዋ ሥራ ምን ይረቅ? ምን ይጠልቅ? አንድም ለድንግል ለማኅፀኗ ሥራ አንክሮ ይገባል፡፡ ለዮሴፍ የነገረው መልአክ ሳይለወጥ ሰው የኾነ አካላዊ ቃል ከርሷ የሚወለድ በግብረ መንፈስ ቅደስ እንደኾነ መስክሯልና /ማቴ.፩፡፳/፡፡ ማርያም የዚህ ደስታ ዕፅፍ ድርብ የሚኾን ጌታን ወለደችው፡፡ ሴቶች ልጅ ትወልዳላችሁ ሲባሉ ደስ ይላቸዋል፤ ይልቁንም ወንድ ትወልዳላችሁ ሲሏቸው ደስ ይላቸዋል፡፡ እመቤታችን ግን ከዚሁ ኹሉ ያለፈ አምላክን ወልዷለችና ደስታዋ ዕፅፍ ድርብ ኾነላት፡፡ መልአኩ፡- “ልጅ ትወልጃለሽ፤ ስሙም አማኑኤል ይባላል” አላት፡፡ አማኑኤልም ማለት እግዚአብሔር ከሥጋችን ሥጋ ከነፍሳችን ነፍስ ነሥቶ ከኛ ጋራ አንድ ባሕርይ ኾነ ማለት ነው፡፡ ዳግመኛም ወገኖቹን ከኃጢአታቸው ፍዳ የሚያድናቸው መድኃኒት ይባላል አላት /ማቴ.፩፡፳፩/፡፡ በመኾኑም በክሂሎቱ (በከሃሊነቱ) ያድነን ዘንድ፣ ኃጢአታችንን ያስተሠርይልን ዘንድ (እስከ ዕለተ ምፅአት ድረስ ክብር ይግባውና) ሰው የኾነ እርሱ አምላክ እንደኾነ በተረዳ ነገር አወቅነው፡፡ አምላክ ብቻ ቢኾን ባልታመመ ነበርና፤ ሰውም ብቻ ቢኾን ባላደነን ነበርና፡፡ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅም ከዚህ ጋር አያይዞ ፡- “ፍቁራን ሆይ! ምንም እንኳን ለዚህ ክብር የተገባን ኾነን ባንገኝም አባታችን በከኀሊነቱ እንዲሁ ከኀጢአታችን አድኖናልና ይህን ክብር፣ ይህን ጸጋ በፍጹም ልናክፋፋው (ልናቆሽሸው) አይገባንም፡፡ ልጅነት እንዲሁ ሳይሰጠን ለምረረ ገሃነም የተገባን የቁጣ ልጆች ከነበርን፤ ይህ ከኅሊናት በላይ የኾነ ጸጋ ከተቀበልን በኋላማ ፍዳችን እንደምን የበዛ አይኾን? ልጆቼ! ይህን የምለው እንዲሁ ለመናገር ያህል አይደለም፡፡ ዳግም ከአብራከ መንፈስ ቅዱስ ከማኅፀነ ዮርዳኖስ ከተወለዱ በኋላ ብዙ ክርስቲያኖች በኀጢአት፣ በስንፍና፣ ለምግባርና ለትሩፋት ሳይሽቀዳደሙ ታክተው ስለምመለከት ነው እንጂ” ሲል ይመክረናል /St. John Chrysostom, Homily on the Gospel of St. Matthew, Homily IV/፡፡

ወዮ! ንዕድ ክብርት ከምትኾን ከእመቤታችን ይህ የአምላክ መወለድ ምን ይረቅ? ምን ይጠልቅ? ቃልን ወሰነችው፡፡ ለልደቱም ዘርዕ ምክንያት አልኾነውም፡፡ በመወለዱም ማኅተመ ድንግልናዋን አልለወጠውም፡፡ ከአብ አካል ዘእምአካል ባሕርይ ዘእም ባሕርይ ድካም ሳይሰማው የተወለደ እርሱ ፭ ሺሕ ከአምስት መቶ ዘመን ሲፈጸምም ከድንግል ሕማም ሴቶች የሚሰማቸውን ሕማም ሳይሰማት እርሱን ሕፃናትን የሚሰማቸው ሕማም ሳይሰማው ተወለደ እንጂ፡፡
ሰብአ ሰገል ሰገዱለት፡፡
አምላክ ነውና አምላክ እንደኾነ ለማጠየቅ ዕጣን አመጡለት፡፡ ንጉሥ ነውና ንጉሥ እንደ ኾነ ለማጠየቅ ወርቅ አመጡለት፡፡ ማኀየዊ የሚኾን የሞቱ ምሳሌ ከርቤንም አመጡለት፡፡

#አንድም “ይኸን ወርቅ እንገብርላቸው የነበሩ ነገሥታት ቀድሞም ፍጡራን ኋላም ኀላፍያን ናቸው፤ አንተ ግን ቀድሞም ያልተፈጠርህ ኋላም የማታልፍ ነህ” ሲሉ ወርቅ አመጡለት፡፡ “ይኽን ዕጣን እናጥናቸው የነበሩ ጣዖታት ቀድሞም ፍጡራን ኋላም ኃላፊያን ናቸው፤ አንተ ግን ቀድሞም ያልተፈጠርህ ኋላም የማታልፍ ነህ” ሲሉ ዕጣን አመጡለት፡፡ “ምንም ቀድሞ ያልተፈጠርህ ኋላም የማታልፍ ብትኾን በሰውነትህ መራራ ሞትን ትቀምሳለህ” ሲሉ ከርቤ አመጡለት፡፡

#አንድም ወርቅ ጽሩይ ነውና “ጽሩየ ባሕርይ ነህ” ሲሉ ወርቅ አመጡለት፡፡ ዕጣን ምዑዝ ነውና “አንተም ምዑዘ ባሕርይ ነህ” ሲሉ ዕጣን አመጡለት፡፡ ዳግመኛም “ከርቤ የተሰበረውን ይጠግናል፤ የተለያየውን አንድ ደርጋል፡፡ አንተም ከማኀበረ መላእክት የተለየ አዳምን አንድ ታደርገዋለህ፤ ጽንዓ ነፍስ ሰጥተህ ታጸናዋለህ” ሲሉ ከርቤ አመጡለት፡፡

#አንድም ወርቅ ጽሩይ ነውና “ባንተ ያመኑ ምዕመናን ጽሩያነ ምግባር ወሃይማኖት ናቸው” ሲሉ ወርቅ አመጡለት፡፡ ዕጣን ምዑዝ ነውና “ባንተ ያመኑ ምእመናንም ምዑዛነ ምግባር ወሃይማኖት ናቸው” ሲሉ ዕጣን አመጡለት፡፡ ዳግመኛም በዕለተ ሞቱ ያቀምሱታልና ከርቤ አመጡለት፡፡ ቸርና ሰው ወዳጅ የኾነ አንድ እርሱ ብቻ ነው፡፡ ቸርና ሰው ወዳጅ ከኾነ ልጅሽ ጽንዕት በድንግልና ሥርጉት በቅድስና እመቤታችን ጸጋውን ክብሩን እንዳይነሣን ለምኚልን፡፡
++ ዛሬ ነገ ነው? ++

‘‘አባዬ ዛሬ ነገ ነው?’’ አለ አቡሽ አባቱን ከተኛበት እየቀሰቀሰ

አባት እየተበሳጨ ‘ምንድን ነው የምትለኝ?’ አለ፡፡
ልጅ ‘ዛሬ ነገ ነው ወይ?’
አባት እንቅልፉ ስላልቀቀው ‘ሂድና እናትህን ጠይቃት በቃ ልተኛበት’ አለና እየተበሳጨ ፊቱን ሸፈነ፡፡

ልጅ ወደ እናት ሔዶ ያንኑ ጥያቄ ደገመላት
‘’እማዬ ዛሬ ነገ ነው?’’ እናት ፈገግ አለች
‘ምን ማለት ነው ደግሞ ዛሬ ነገ ነው? ማለት?’’ አለች የልጅዋን የተጋለጠ ደረት እየሸፈነች
‘ትናንት አስተማሪያችን ‘ነገ ትምህርት የለም’ ብላን ነበር ፤ ዛሬ ነገ ነው?’’
እናት ‘እ እ አዎ ልክ ነህ ዛሬ ነገ ነው’ አለች እየሳቀች፡፡

ይህ ለሕጻኑ ጥያቄ የተሰጠ መልስ ለእኛም ሳያስፈልገን አይቀርም፡፡ ብዙዎቻችን የምንኖረው ለነገ ነው፡፡ ለነገ እንማራለን ፣ ለነገ እንሠራለን ፣ ለነገ እንገነባለን፡፡ የተፈጠርነው ለዘላለማዊነት ነውና እንደምንኖር አስበን ማቀዳችን ባልከፋ፡፡ ነገር ግን ላላየነው ነገ ስናስብ ያየናትን ዛሬ እንዘነጋታለን፡፡ ለነገ ደመና የዛሬን ፀሐይ እንገፋታለን፡፡ እንዳቀድን እንዳለምን ለመኖር ስንዘጋጅ እንሞታለን፡፡ መጽሐፍ ‘’ነገ ወደዚህ ከተማ እንሄዳለን በዚያም ዓመት እንኖራለን እንነግድማለን እናተርፍማለን የምትሉ እናንተ፥ ተመልከቱ፥ ነገ የሚሆነውን አታውቁምና’ ‘ነገ ለራሱ ያስባልና ለነገ አትጨነቁ! ይላል፡፡ /ያዕ 4፡15 ፤ ማቴ 6፡34/

ሰይጣን ከሚጠቀምበት ሰውን ማጥቂያ መሣሪያም አንዱ ‘ነገ’ በሚል ቃል ማዘናጋት ነው፡፡ ነገ እማራለሁ ፣ ነገ እሔዳለሁ ፣ ነገ የታመመ እጠይቃለሁ ፣ ነገ ንስሓ እገባለሁ ፣ ነገ ወደ እግዚአብሔር እመለሳለሁ ፣ ነገ ይሄንን መልካም ነገር እሠራለሁ ነገ ነገ ነገ
ፈርኦን የሚባለው ጨካኝ ንጉሥ በመቅሠፍት ጓጉንቸር ተወርሮ ነበር፡፡ በመጨረሻም እስራኤልን እለቃለሁ ሲል ሙሴ ፦ ጓጉንቸሮቹ ከቤትህ እንዲጠፉ መቼ ልጸልይልህ? አለው፡፡ ፈርኦንም ፦ ነገ አለ፡፡

እንግዲህ ዛሬን ከጓጉንቸሮች ጋር ማደር ፈልጓል ማለት ነው፡፡ ወዳጄ በሕይወትህ ውስጥ ጓጉንቸሮች ምንድን ናቸው? ምን ዓይነት ክፉ አመል አለብህ ፣ ምን ዕረፍት ያሳጣህ ፣ ሰላም የነሳህ ነገር አለ? አልላቀቅ ያለህ ሱስ ፣ አልስተካከል ያለህ ድክመት ፣ አልድን ያለህ ቁስል ምንድን ነው? እርሱን መቼ ትላቀቀዋለህ? መቼ መዳን ትሻለህ? ነገ ካልከኝ ፈርኦን መሆንህ ነው? ‘አቤቱ አሁን አድን’ ካልክ ደግሞ እንደ ዳዊት ትሰማለህ

ነገ ይህንን ሱስ እተዋለሁ ፣ ነገ ይህን ልማድ እላቀቃለሁ ፣ ነገ ይህን መልካም ነገር አደርጋለሁ የሚል ቀጠሮ ሠርቶ አያውቅም፡፡ ነገ እንላለን እንጂ የሚገርመው በማግሥቱም መልሳችን ነገ ነው፡፡ ‘ዱቤ ዛሬ የለም ነገ ነው’ እንደሚለው የብልጥ ባለሱቅ ማስታወቂያ ነገ ስንሔድ ነገ እየተባለ የምንፈልገውን ሳንሠራ የማንፈልገውን እየሠራን እንኖራለን፡፡ ወዳጄ ነገ የአንተ አይደለችም ‘የተወደደው ሰዓት አሁን ነው’ መኖርህን ሳታውቅ ቀጠሮ አትሥጥ፡፡ ኃይልህ በአሁን ላይ ብቻ ነው፡፡ ማንም ሊሠራባት የማይችላት ሌሊት ሳትመጣ አሁንን ተጠቀምባት፡፡

አሁኑኑ ተነሥ ያሰብከውን መልካም ነገር ለመሥራት ፣ ክፉውን ነገር ለመተው ነገ አደርገዋለሁ አትበል
ትናንት ኅሊናህ ሲጠይቅህ ‘ነገ አደርገዋለሁ’ ብለህ ነበር ፤ ዛሬም ‘ነገ’ አትበል ምክንያቱም ሕጻኑ እንዳለው ‘ዛሬ ነገ ነው’

ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ

👉እርሶ ያወቁትን እውቀት ሌሎች ያውቁ ዘንድ ቻናላችንን ሼር በማድረግ ጓደኛዎን ይጋብዙ

ቻናላችንን ይቀላቀሉ
👇👇👇👇👇 👇👇👇👇👇
@ethiopianissm @ethiopianissm
@ethiopianissm @ethiopianissm
@ethiopianissm @ethiopianissm
እንኳን ለእመቤታችን ለቅድስት ድንግል ማርያም በዓለ ትንሣኤና ዕርገት በሰላም
አደ ረሳችሁ።ይህን ክብረ በዓል አስቀድመው ያከበሩት፦የትንሣኤዋ እና የዕርገቷ
የዓይን ምስ ክሮች የሆኑት ቅዱሳን መላእክት እና ቅዱሳን ሐዋርያት
ናቸው።በዚህች ዕለት ልጇ ወዳጇ ኢየሱስ ክርስቶስ ቅዱሳን መላእክትን እና
ቅዱሳን ነቢያትን አስከትሎ በመውረድ ሠራኢ ካህን ሆኖ
ቀድሶአል፥እመቤታችንም በልጇ እጅ ቆርባለች።ከዚህ በኋላ በዕርገት ወደ ራሱ
ወስዶአታል።እግዚአብሔር እንኳን እናቱን ባሮቹን ሄኖክን እና ኤልያስን እንኳ
መላእክቱን ልኮ ወደ ሰማይ ወስዶአቸዋል።ዘፍ፡፭፥፳፬፣፪ኛ፡ነገ፡፪፥፲፩።ለእርሷ
ሲሆን ግን እርሱም ጭምር ወረደ።"ወአልቦ ዘዓርገ ውስተ ሰማይ ዘእንበለ
ዘወረደ እምሰማይ ወልደ ዕጓለ እመሕያው።ወደ ሰማይ የወጣ የለም፥ወደ ሰማይ
የወጣው ከሰማይ የወረደው ክርስቶስ ነው እንጂ።"የሚለው፦"የወጣውም
የወረደውም አንድ አካል አንድ ባሕርይ ነው፤" ለማ ለት ነው። አንድም ሰማያዊ
ሀብትን፥ሰማያዊ ዕውቀትን ገንዘብ ያደረገ የለም።ሰማያዊ ሀብትን፥ሰማያዊ
ዕውቀትን ገንዘብ ያደረገው ከሰማይ የወረደው ክርስቶስ ነው እንጂ፤" ለማለት
ነው።ዮሐ፡፫፥፲፫።የበዓሉን በረከት ያሳድርብን።መጪውን ዘመን ዘመነ ማቴዎስን
መከራችን የሚያበቃበት ዘመን ያድርግልን፥አሜን።


👉እርሶ ያወቁትን እውቀት ሌሎች ያውቁ ዘንድ ቻናላችንን ሼር በማድረግ ጓደኛዎን ይጋብዙ

ቻናላችንን ይቀላቀሉ
👇👇👇👇👇 👇👇👇👇👇
@ethiopianissm @ethiopianissm
@ethiopianissm @ethiopianissm
@ethiopianissm @ethiopianissm
"ለበጎ ነው"

"አንድ ንጉስ ከአጃቢው ጋር በመሆን ለአደን ይወጣል። ለአደን ሲወጡ ንጉሱ ወጥመድ እያጠመደ እያለ ወጥመዱ አምልጦት እጁን ቆረጠው። በዚህም አጃቢው በማዘን "አይዞህ ንጉስ ሆይ ሁሉ ነገር ለበጎ ነው!" ይለዋል። በዚህም ንጉሱ በንዴት እየጦፈ "የኔ እጅ መቆረጥ ነው ለበጎ?" ይለውና እስር ቤት አሳሰረው።

ከብዙ ጊዜ በኋላ ንጉሱ ብቻውን ሀገሩን ሲዞር ሰው አርደው ለጣዖት መሰዋት የሚያደርጉ ጨካኝ ሰዎች ያዙትና አርደው መሰዋት ሊያደርጉት ሲሉ ቆራጣ እጁን አዩት። በእነሱ ህግ መሰዋት የሚያደርጉት ሰዉ ሙሉ ጤነኛ መሆን ስላለበት ለቀቁት።

ንጉሱ አጃቢው 'ሁሉ ነገር ለበጎ ነው!' ያለው ትዝ አለውና እስር ቤት ሄዶ ስላሰርኩህ ይቅርታ አርግልኝ! ብሎ ታሪኩን አጫወተው። አጃቢውም "ማሰርህ ለበጎ ነበር! እኔም መታሰሬ ጠቅሞኛል።" አለው። ንጉሱ "እንዴት?" አለው አጃቢውም "ባልታሰር ኖሮ ከአንተ ጋር እሄድና አንተ ቆራጣ መሆንህን ሲያውቁ ይለቁህና አኔን ይገሉኝ ነበር" አለው።

ስለዚህ ሁላችንም ስለተደረገልንም ሆነ ስላልተደረገልን እንዲሁም ስለሆነውም ሆነ ስላልሆነው ነገር ሁሉ "ለበጎ ነው" ማለት ይልመድብን፡፡
ገብርኤል ማለት የአምላክ አገልጋይ ማለት ነው::
ቅዱስ ገብርኤል ለብስራትና ለድህነት የሚላክ ከሰዎች ጋር ታላቅ ግንኙነት ያለው
ተወዳጅና ፈጣን መልአክ ነው::
ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን እንደምትወልድ እመቤታችንን ያበሰራትና
ለመጀመሪያ ጊዜ ከሰዎች በፊት ያመሰገናት ቅዱስ ገብርኤል ነው::
ሰለስቱ ደቂቅን ናቡከደነፆር በእሳት ላይ በጣላቸው ጊዜ
ፈጥኖ በመድረስ ከእሳት ያዳናቸው ቅዱስ ገብርኤል ነው::
እንዲሁም ኢየሉጣና ቂርቆስ በፈላ ውሀ ውስጥ በተጣሉ ጊዜ
ውሃውን በማቀዝቀዝ ያዳናቸው መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ነው::
መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል አሁንም ቢሆን የሰዎችን ጭንቀታቸውንና ችግራቸውን
በማስወገድ ስሙን ለጠራ ሁሉ ፈጥኖ በመድረስ ታላላቅ ተዓምራትን ሲያደርግ
ይታያል::
የኛንም የተለያየ ችግር ያስወግድልን::
አንድነትና ሰላም ለቅድስት ቤተክርስቲያን:

👉እርሶ ያወቁትን እውቀት ሌሎች ያውቁ ዘንድ ቻናላችንን ሼር በማድረግ ጓደኛዎን ይጋብዙ

ቻናላችንን ይቀላቀሉ
👇👇👇👇👇 👇👇👇👇👇
@ethiopianissm @ethiopianissm
@ethiopianissm @ethiopianissm
@ethiopianissm @ethiopianissm
የድንግል ማርያም አስደናቂው ስብዕና
[ በብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊ ]
በቤተ መቅደስ ውስጥ በንጽሕናና በቅድስና ኖረች ፤ ከቤተ መቅደሳችን ውጪልን
በማለት ሰዎች እርሷን የሚያስገድዱበት ጊዜ መጣ ግን እርሷ ይህንንም
አልተቃወመችም። ፈቃዷ ያለ ጋብቻ መኖር ነበር ፤ በሰው ልጅ ጥበቃ ትሆን ዘንድ
ግድ አሏት ፥ ይህንንም አልተቃወመችውም። ይህም እንደ ጊዜያቸው ሥርዓት
ይጓዙ ነበርና ለአረጋዊ ዮሴፍ እንድትታጭ ሆነ ፤ ይህንንም ሳትቃወም ከመቅደስ
ውጪ መኖርን እንዳልተቃወመች ሁሉ ይህንንም ሁኔታ ባለመቃወም ፈጸመችው ፤
የኖረችው ሕይወት የመታዘዝ ሕይወትን ነውና።
ያለመቃወም ፣ ያለማጉረምረም ፣ ያለማንገራገር ሕይወት ፤ ነገር ግን በእርጋታ
የሯሷን ፈቃድ አሳልፋ ለእግዚአብሔር ፍቃድ ሰጠች እንጂ። የድንግልና
ሕይወትን ለመምራት ቆረጠች ፣ እናት እሆናለሁ የሚል ሀሳብ በእርሷ ውስጥ
ፈጽሞ አልነበረም። እግዚአብሔር እናቱ ትሆን ዘንድ ፈቃዱ ሲሆን ግን
የሚከተለውን ነገር ተናገረች "እነሆኝ የጌታ ባሪያ እንደ ቃልህ ይደረግልኝ" አለች
(ሉቃ. ፩፥፴፰)። ለዚህም ትህትናዋ እግዚአብሔር አምላክ የእናትነት ዘለዓለማዊ
ትሕትናን አጎናጸፋት። ይህችም ጸጋ ለዘለዓለም በእርሷ ላይ ጸንታ ትኖራለች።
እናቱ ትሆን ዘንድ በድንግልና አጸናት ፤ ስለዚህ ምክንያት ቅድመ ፀኒስ ጊዜ ፀኒስ
ድኅረ ፀኒስ ፣ ቅድመ ወሊድ ጊዜ ወሊድ ድኅረ ወሊድ በድንግልና ሀብታት ከብራ
እንድትኖር አደረገ እናትም ሆነችው።
ፈጽማ እሆናለሁ ብላ ያላሰበችው ምሥጢር ነበር ፤ ነገር ግን በመታዘዝ የጌታ
እናት ሆነች። ወደ ግብጽ እንድትመጣ ታዘዘች ሄደች ፣ በዚያም ኖረች። እርሷ
በስብዕናዋ ምሳሌ የምትሆን እመቤት ናትና። ለዚህ ነው "ብርቱ የሆነ እርሱ
ታላቅ ነገርን አድርጎልኛልና" በማለት ያመሰገነችው። በዚህ ነው ትሑትነቷንም
የገለጠችው የባሪያውን ትሕትናና መታዘዘ በእርግጥም እግዚአብሔር
ከማደሪያው ተመለከተ በማለት ብጹዕነታቸው አቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊ የግብጽ
ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፻፲፯ተኛ ጳጳስ በብዕራቸው ከትበውላታል።
የአምላክ እናት እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም አማላጅነት ፣
የብጹዕነታቸው ጸሎት በረከት አይለየን!!!
ሰዓሊ ለነ አእምሮውን ልቡን ሳይብን አሳድሪብን ፥ ጸጋውን ክብሩን እንዳይነሣን
ለምኝልን!!!
ነሐሴ 24

ድካም በማብዛት እንደ ነቢያት፣ ወንጌልን በማስተማር እንደ ሐዋርያት፣ በመገረፍ እንደ ሰማዕታት፣ አጥንቱ ከስጋው ጋር እስኪጣበቅ ከሰውነቱ ማለቅ ብዛትና የሚያቃጥለውን ላብ እንደ ደም ዥረርታ በማፍሰስ፥ ከስግደቱ የተነሳ የሰውነቱ መለያ እስኪቆጠር ድረስ ተባህትዎን በመያዝ እንደ መነኮሳት ሆኖ መንፈሳዊ መገዛቱን ለመጨረስ ቆርጦ የተነሳ።

አይን እያለው እንደማያይ፣ ጆሮ እያለው እንደማይሰማ፣ ክረምትና በጋን ሳያያቸው 8 ጦር ዙሪያው ተክሎ የእግሩ አገዳ እስኪቆረጥ ድረስ ያለ ምግብ ያለ ውሃ ቅጠል እንኩአን ሳይቀምስ በፅኑ ተጋድሎ እንባውን እያፈሰሰ በብዙ የደከመ። ብጹዕ አባታችን በህመም በተያዘ ጊዜ በመንፈስ ልጆቹ የሆኑ ሁሉ ወንዶችም ሴቶችም ተሰብስበው ብዙ አለቀሱለት፡፡

አባታችንም ‹‹ልጆቼ አታልቅሱ ነገር ግን የሽማግሌውን ቃል ስሙ ከሁሉ አስቀድሞ እምነታችን በእግዚአብሔር ላይ ይሁን፡፡ ልጆቼ ሆይ ሰላም ለእናንተ ይሁን እንግዲህ ወዲ ግን ተሰናበትኳችሁ የእግዚአብሔር ፍቅሩ የክብሩም ባለቤትነት የረዳትነቱም ሀብት ዘወትር ከእኔና ከሁላችሁም ጋር ለዘላዓለሙ በእውነት ይኑር፡፡›› በማለት እንደዚህች ባለች እለት በምግባር ፍጹም የሆነ ተጋድሎው የበዛ ትሩፋቱ ያማረ፣ ሌሊትና ቀን በመቆም እግሩ የተሰበረ፣ በክረምትና በበጋ ውርጭ መልኩ የጠቆረ፣ በጌታችን ስም ደም ተቀብቶ ሰማዕት የሆነ፣ የዓለም ፀሐይ የትምህርት ብርሃን #ብጹዕ_አባታችን_አቡነ_ተክለሃይማኖት በተወለዱ በ 99 ዓመት ዐረፉ፡፡
የአባታችን ረድኤት በረከት አይለየን፡፡
👉በሀገረ እስራኤል የራሷ ቦታ ያላት (ዴር ሡልጣን) ብቸኛዋ ሀገር ሀገረ እግዚአብሄር ኢትዮጵያ ብቻ ነች።
"ነሐሴ 26፦ ይህች ዕለት የታላቁ ቅዱስ አቡነ ሀብተማርያም በዓለ ፅንሰታቸው ናት” በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!

ታላቁ ጻድቅ አቡነ ሀብተማርያም የተወለዱት በመንዝ አውራጃ ልዩ ስሙ የራዊ በተባለ ቦታ ሲሆን የአባታቸው ስም ፍሬ ብሩክ የእናታቸው ስም ዮስቴና ይባላል፡፡ ከታላቁ የተጋድሎ አርበኛ ፃድቅ አባታችን ቅዱስ ሀብተማርያምና በዚህች ዕለት ከሚታሰቡ ሌሎች ቅዱሳንና ሰማዕታትም ቃልኪዳን ፣ ረድኤት ፣ በረከት ያሳትፈን! አሜን!
➙ አልፋና ዖሜጋ ዘተዋሕዶ ◈ hottg.com/christian930
#ዴቪልስ_ትሪያንግል ወይም በሌላኛው አጠራሩ #ቤርሙዳ_ትሪያንግል በጥቂቱ

በምድር ላይ ካሉት ሚስጥራዊ ስፍራዎች አንዱ የቤርሙዳ ትሪያንግል ነው ቤርሙዳ ትሪያንግል ነው ፡፡ ቤርሙዳ ትሪያንግል በአትላንቲክ ውቅያኖሶች ውስጥ ይገኛል ፤ ከአሜሪካ ፍለሎሪዳ ግዛት ዝቅ ብሎ የሚገኝ ሲሆን በስተደቡብ በኩል ካሪቢያን ደሴት ያዋስነዋል ፡፡

ቤርሙዳ ትሪያንግልን ለመጀመሪያ ጊዜ ያየው ክርስቶፈር ኮሎምበስ ሲሆን ዘመኑም በ1449 ነበር ፡፡ ተጓዡ ክርስቶፈር ዓለምን በሚያስስበት ወቅት በዚህ ስፍራ ደርሶ አንድ ነገር ተመለከተና በማስታወሻው እንዲህ ሲል ፃፈ

"በአድማስ ላይ የሚደንስ እንግዳ የሆነ የብርሃን ጮራ ፤ በሰማይ ላይ የነገሰ የእሳት ነበልባል ፤ የአቅጣጫ መጠቆሚያን ኮመምፓስን የሚያመሰቃቅል ሀይል" ብሎት ነበር ፡፡

እንደ ብዙዎች አነጋገር ከዛ ከቤርሙዳ ትሪያንግል ቡሃላ ያለውን የምድር ክፍል አዲስ አለም ወይም አዲስ ምድር ብለው ይጠሩታል

ቤርሙዳ ትሪያንግል ባለልታወቀ ሚስጥር በርካታ መርከቦች እና የሰውን ልጅ ህይወት እና ሀብት እንደያዙ ለአንዴ እና ለመጨረሻ ጊዜ ጠፍቷል ! በአለማችን ላይ ከፍተኛ የመርከብና የአየር ትራንስፖርት እንቅስቃሴ የሚደረግበት በዚህ ስፍራ ላይ እንዲ አይነት እንቅስቃሴ ወይም እንግዳ የሆነ እና ሁሉን ውጦ የሚያስቀር ገደል መገኘቱ የሰውን ልጅ እስካሁን ግራ አጋብቷል ፡፡

በቤርሙያ ትሪያንግል አካባቢ እንደ ወጡ ከቀሩት ውስጥ በጥቂቱ በ1812 ቲዎዶስያ በር አልስተን የተባለች የወቅቱ የአሜሪካን ም/ፕሬዝደንት የነበሩት የአሮን በር ልጅ ዲሴምበር 30 በተጠቀሰው አመት ፓትሮዎት በተባለች መርከብ ስትጓዝ በዚያው ቀርታለች ፡፡ በ1945 ፍላይት 19 የተባለች አውሮፕላን ከ14 ተጓዥ ጋር ጠፍታለች ፡፡ በዛኑ ወቅት ፍላይት 19 ፍለጋ የተላኩ 6 አውሮፕላኖች እና 27 ሰዎች እንደወጡ በዛው ቀርተዋል ፡፡ በ1948 ስታር ታይገር 19 የተባለች አውሮፕላን ከ6 አብራሪዎች እና ከ25 ተሳፋሪዎች ጋር ልትጠፋም ችላለች ፡፡ ከ65 አመታትቶች በፊት በዚ በቤርሙዳ ተትሪያንግል በየእለቱ 5 አውሮፕላኖች በዚህ አካባቢ ላይ ሲያልፉ የመስመጥ አደጋ ደርሶባቸዋል መስመጥ ብቻ ሳይሆን ደብዛቸውም ጠፍቷል ብዙ መርከቦች ከነተሳፋሪያቸው ላይመለሱ ቤርሙዳ ትሪያንግል ውስጥ ሊሰምጡ ችለዋል !!

ለቤርሙዳ ትሪያንግል እንዲ መሆን ብዙ መላምቶች ተቀምጠዋል በጥቂቱ

1, ከፍተኛ የማግኔት እና የኤሌክትሮኒክስ ሃይል ያለው ደመና በአካባቢው ሰማይ ላይ መኖር የመርከቦችንና የአውሮፕላኖችን እንቅስቃሴ ያግዳል

2,ያልታወቁ በራሪ ፍጥረታት (UFO) በአካባቢው ሰፍረዋል

3, ሁሪካን የሚባለው ሃይለኛ አውሎ ንፋስ በአካባቢው ሊኖር ይችላል

4,በውቅያኖሱ ውስጥ በከፍተኛ ፍጥነት የሚጓዝ አደገኛ ወንዝ ስላለ መርከቦችን እና ፕሌኖችን ጠራርጎ ይወስዳል

5, ሚቴን ሃይድሬት የተባለ ንጥረ ነገር በባህር ውስጥ በከፍተኛ መጠን ስላለ የውሃውን እፍጋት (ዴንሲቲ) ይቀንሰዋል የውሃው ዴንሲቲ በሚቀንስበት ወቅት መርከቦችን የመሸከም አቅሙ ስለሚወርድ መርከቦቹ በቀላሉ ይሰምጣሉ ፡፡

6,ሰይጣናዊ ቦታ ነው ተብሎም ይገመታል ! ! !
ዝክረ ዘርአ ያዕቆብ.....#share

*ዐፄ ዘርዓ ያዕቆብ.በረራ (አዲስአበባን) የቆረቆሯት የቀዳማዊ ዳዊት አራተኛ ልጅ ነው።የተወለደው ፈጠጋር ውስጥ ጥልቅ ከሚባለው ሥፍራ ነው።ከአባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ ዘንድ ተምሯል።በግሼን ብሉይና ሐዲስን መጻሐፍት ትርጓሜ በመማር እንዲሁም ሲኖዶስን በማጥናት አሳልፏል።

*.በ1426 ዓ.ም ዐፄ አምደ እየሱስ ሲያርፍ በግዝት ከነበረበት ግሽ አምጥተው ተጉለት ውስጥ "ደጎ"ላይ "ዐፄ ቆስጠንጢኖስ ንጉሠ ነገሥት ዘኢትዮጵያ "ብለው አነገሡት።
ዐፄ ዘርዓያዕቆብ በነገሠ በሰባት ዓመቱ ከአምሐራ መጥቶ ተጉለት ውስጥ እጉባ በሚባል ቦታ ከተመ።ሰሜን ሸዋ ሰላ ድንጋይ የምትገኘውን ደብረ ምጥማቅ ያሰሯት በዚህን ጊዜ ነበር።የአሕመድ በድላይን አመጽ የሰማውም ታኅሣሥ 21 ቀን በደብረ ምጥማቅ የእመቤታችንን በዓል እያከበረ እያለ ነበረ።(Les chronuques da zar'a Yaeqob et de Ba'ede maryam,88፤ encyclopedia Aethiopica,vol.ll,34-35)

*በዐፄ ዘርአ ያዕቆብ 3 ሃይማኖታዊ ችግሮች ነበሩ።እነርሱም፦

ሀ~ኤዎሳጣቴዎሳውያን፦ ቅዳሜን እንደ እሁድ ካላከበርን የሚሉ፣

ሁ~ደቂቀ እስጢፋ፦ቀደም ብሎ በዐፄ ያግብዐ ጽዮን ዘመን የነበረውን ጭቅጭቅ እንደገና አንሥተው ለሰውና ለማላእክት፣ለሥዕል እና ለመስቀል አንሰግድም የሚሉ እና

ሂ~ዘሚካኤላውያን፦አምላክ መንፈስ እንጂ እንደፍጡር መልክ የለውም የሚሉ ናቸው።

*.ዐፄ ዘርያ ያዕቆብ መጽሐፍ አዋቂና ለሃይማኖቱ ቀናተኛ ከመሆኑ ባሻገር እነዚህ ሰዎች ሕዝቡን በተለይም መንግሥቱን የሚከፋፍሉት መስሎት ትልቅ ሥጋት አደረበት።ጉዳዩን ትኩረት በመስጠት ከኤዎስጣቴዎሳውያን ጋራ የቅዳሜን መከበር ፈቅዶ ሌሎቹን ግን በካህናት በጉባኤ እየሰበሰበ ስሕተታቸውንአሳያቸው፤አስፈረደባቸው፤አጠፋቸው።ተዓአምረ ማርያምን ወደ ግዕዝ አስተረጎመ።በዓመት 33 ቀኖች በቅድስት ማርያም ስም ዓመት በዓል ሆነው እንዲከበሩ ዐወጀ።እምነቱን የሚያንጸባርቁ ብዙ መጻሕፍትንም ደረሰ፤ዋና ዋናዎቹ መካከል፦

1.መጽሐፈ ብርሃን፣ 7.መጽሐፈ ሚላድ፣
2.መጽሐፈ ሥላሴ፣ 8.መጽሐፈ ባሕርይ፣
3.ተዓቅቦ ምሥጢር፣ 9.ጦማረ ትስብእት፣
4.ስብሐት ፍቁር፣ 10.መልክአ ፍልስታ
5.ተአምራተ ማርያም 11. ድርሳነ መላእክት....
6.እግዚአብሔር ነግሠ

*በእግዚአብሔር ነግሠ ግጥም ውስጥ ይኩኖ አምላክን፣ዐምደ ጽዮንን እና ቴዎድሮስን ያነሳል።
"የባህር ዕንቁ ለሆነው፤
ምርጡን ይኩኖ አምላክን ሰላም እላለሁ።
ኢትዮጵያን እንደ ፀሐይ አበራት።
ጌታ ሆይ ከአሸበረቀችው ሀገርህ፥
የበጉ ውበት ከሚያበራባት አስገበው።"

*በሰሜን እስከ ምፅዋ ደሴት በምሥራቅ እስከ ዘይላ ወደብ አመፀኞችን ዘምቶ ስላስገበረው ዐምደ ጽዮን እንዲህ ሲል ገጥሞለታል።
"የአመፀኞች ጎማጅ የሆነውን፥
ዐምደ ጽዮንን ሰላም እለዋለሁ።
በሁሉ ቦታ አብያተ ክርስቲያናት ሠራ፤
ንግሡን ለአምላክ በትክክል ባስገዛ ጊዜ፥
ከባሕር እስከ ባሕር ፈረሱን አስኬደ።"

7.ዐፄ ዘርአ ያዕቆብ ዋና ሥራ የኢትዮጵያን የቤተመንግስት የሹም ሽር አወቃቀር፥ የፍርድ ስርአቱን ማሻሻል እና ወታደራቸውን በዝርዝር መከፋፈል ነበር።በዝርዝር የተከፈሉ ወታደሮች ስማቸው፦

1.በፀር ዋጀት፣ 11.በድል ደመና፣
2..በድል ሾተል፣ 12.በፀር ሾተል፣
3.ድብ ምልዓት፣ 13.ዣን ምልዓት፣
4.በድል መብረቅ፣ 14.በድል መስቀል፣
5.በአዳል ዣን፣ 15.አቄት በአምባ፣
6.በአዳል ዋዠት፣ 16.ጸመና አምባ፣
7.በባሕር ዋገት፣ 17.በአዳል መብረቅ፣
8.ዣን አሞራ፣ 18.ዣን ጸገና፣
9.ዣን ገደብ 19.ዣን ቀንጠፋ...

*በዚህ በተደራጀ ፈረሰኛ እግረኛ ባለጦር፥ባለቀስት፥ ባለ ሰይፍ ጀሌ ዐፄ ዘርዓያቆብ የዓምደ ጽዮንን የአገር ግምባታ ፖሊስና ተግባር የበለጠ በማጠናከር አገሮችንና ክፍለ ሀገራትን በሙሉ በአንድ ማዕከላዊ መንግሥት ስር አደራጀ፥በዘመኑ የቀይ ባህር የዳህላክ ደሴት፣በአዴን ባህረሰላጤ የዜላ ወደብ ጨምሮ በአፍሪካ ቀንድ በአዴን ባህረሰላጤ ጠረፍና በሕንድ ውቅያኖስ ዳርቻ የበርበሮች ምድር ጨምሮ በማዕከላዊ መንግሥት ሥር አደረገ።የአዳሎችን በድላይ ተዋግቶ አሸነፋቸው።

*ዘርዓ ያዕቆብ የቤተክርስቲያን ሥርዓት አቋቁመዋል፣የሳታት ጸሎት አስጀምረዋል፣መካነ ጎልጎታ፤መካነ ማርያምን፤በሰሜን ሸዋ የሚገኘው ደብረ ብርሃን ሥላሴ፣በሰሜን ሸዋ ተጉለት ይገኝ የነበረው ደብረ ምጥማቅ፣በአምሐራ ዳሕያ በሚባል ቦታ የመሠረተው ደብረ ነጎድጓድ አሠርተዋል።

*በሰሜን ሸዋ ተጉለት ይገኝ የነበረው ደብረ ምጥማቅ የተሰራችው በዚህ ምክንያት ነበረ።ላይላይ ግብፅ ክርስቲያኖቹ ሰንደፋ ከሚባል ቦታ ደብረ ምጥማቅ(ዴር አል-መግጠስ) በምትባል ቦታ ላይ በሡልጣን በርስበይ (1422-1438) ትእዛዝ ቤተ ክርስቲያኗን አፈረሷት።የዘመኑ ሊቀ ጳጳሳት አባ ዮሐንስ (1422-1438) በክርስቲያኖቹ ላይ የደረሰባቸውን በደል ለዐፄ ዘርዓ ያዕቆብ ላኩበት።ዘርዓ ያዕቆብ ለሡልጣኑ "አዚህ ኢት ያሉትን እስላሞች ማንም አይነካቸውም።ሌላው ቀርቶ እንደ ሌላው ሕዝብ ግብር እንኳን አናስገብራቸውም እናንተ ግን የሃይማኖት ነፃነት ትገፍፋላችሁ"የሚሉ ቃላትና ሡልጣኑ የማይሰማ ከሆነም ለመበቀል እንደሚችል የሚያመላክት ጠንካራ ደብዳቤ ጻፈለት።ለግብጻዊያን ክርስቲያኖች ማጽናኛ ትሆን ዘንድም በፈረሰችው ቤተ ክርስቲያን ስም እዚህ ኢትዮጵያ እጉባ ላይ "ደብረ ምጥማቅ" የምትባል ቤተ ክርስቲያን ሠራ።በዚያ ላይ በዚያን ጊዜ የአደሉን ንጉሥ በድላይን ድባቅ መምታቱ በክርስቲያኑ ዓለም ስለተሰማ ሡልጣን ጀቅማቅ ተደናግጦ ከሊቀ ጳጳሳቱ ጋር ቶሎ ታረቀ።(ጌታቸው ኃይሌ,ደቂቀ እስጢፋኖስ፣52-53)

*ባጠቃላይ ዐፄ ዘርዓያዕቆብያ ስርዓትና ደንብ"፣የመንግስት አወቃቀር፣የጦር አደረጃጀት፣የሹማምንት አሿሿምና ተግባር፣የመንፈሳዊ ክብረ በአላትና የጸሎት አይነቶችን ጨምሮ፤በርካታ ነገሮች ከነበሩበት ጨምረውና አሻሽለው በ34 አመታቸው ልክ በዛሬዋ ቀን ጳጉሜ 3 ቀን 1460 ዓ.ም. አረፉ።በኋላ ላይ አስክሬናቸው በጣና ሐይቅ ደሴተ ዳጋ እንዲያርፍ ተደርጓል።

*ከታደለ ጥበቡ የተወሰደ

👉እርሶ ያወቁትን እውቀት ሌሎች ያውቁ ዘንድ ቻናላችንን ሼር በማድረግ ጓደኛዎን ይጋብዙ

ቻናላችንን ይቀላቀሉ
👇👇👇👇👇 👇👇👇👇👇
@ethiopianissm @ethiopianissm
@ethiopianissm @ethiopianissm
@ethiopianissm @ethiopianissm
"ፈተና ሲገጥመን ውስጣችን ሊረበሽ ወይም በቀቢጸ ተስፋ ሊያዝ አይገባውም፡፡ ወርቅን የሚያነጥር ሰው በእሳት ውስጥ የጨመራትን የወርቅ ቅንጣት እዚያ ውስጥ ምን ያህል ጊዜ መቆየት እንዳለባት ያውቃል፤ መቼ ከእሳቱ ሊያወጣት እንደሚገባውም ያውቃል፡፡

እንዲሁ እስከ መጨረሻው በእሳቱ ውስጥ ተጥላ እንድትቀርና በዚያ እንድትቃጠል አይፈቅድም፡፡ እግዚአብሔር ደግሞ ይህን ከወርቅ አንጣሪው በላይ ያውቃል፡፡ መቼ ከርኩሰታችን እንደምንነጻ ያውቃል፡፡ በመኾኑም ራሳችንን በመጣልና ተስፋ በመቁረጥ በክፋት ላይ ክፋት እየጨመርን እንዳንኼድ ሽቶ መቼ ከዚያ ፈተና እንደሚያወጣን ያውቃል፡፡

ስለዚህ ድንገት ያላሰብነው ነገር ቢገጥመን በፍጹም የምናማርር፣ ወይም ተስፋ የምንቆርጥ ልንኾን አይገባንም፡፡ ከዚህ ይልቅ የእነዚህ ነገሮች ምንነትን የሚያውቅ እግዚአብሔርን መጠበቅ፣ እርሱ እስከ ፈቀደው ጊዜ ድረስም ልቡናችንን በእሳት እንዲፈተን ማድረግ ይገባናል፡፡ ምክንያቱም ይህ ነገር በእኛ ላይ እንዲኾን (እንዲመጣ) የፈቀደው ለእኛ ጥቅምና በዚያ ውስጥ ኾነን በምናሳየው ጥረት ይበልጥ ሊያከብረን ስለሚወድ ነው፡፡"

(#ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ - #ወደ_ኦሎምፒያስ)
የኢያሪኮ መንገደኛ፤ (በዲያቆን ብርሃኑ አድማስ)፤ *********አቤቱ በእኔ
በኵል እለፍ። ጌታዬ ሆይ አቤቱ በአዲስ ዘመን ዋዜማ በአጠገቤ እለፍና አንሣኝ፡፡
ዘይትና ወይን ባልካቸው የመሥዋዕት ደምህ ቁስሌን ጥረግልኝ፡፡ ጨርቅ በተባለ
ፍቅርህም ግጥም አድረገህ እሰርለኝና ከጥላቻ፣ ከከንቱነት፣ ከግብዝነት፣
ከለፍላፊነት፣ ከኩራትና ከትዕቢት፣ ከዝሙትና ከርኩሰት ቁስሌ ማገገምን ስጠኝ፡፡
በአገልጋይህ በኩል ስበህ የእንግዶች ማደሪያ ወዳልካት ቤትህ አስጠጋኝ፡፡
ጌታዬ ሆይ እባክህን ለእኔ ለምስኪኑ ዛሬም ዲናርህን ክፈልልኝ፤ አቤቱ ሁለቱ
ዲናሮችህ በተባሉ በብሉይና በሐዲስ እጅግ የደከመች ቁስለኛ ነፍሴን መግበህ
አድንልኝ፡፡ የነፍሴ እረኛ ሆይ በአንተ ዘንድ ዝለት መሰልቸት የለምና የእኔ
መቅበዝበዝ አይተህ ቸል አትበለኝ፤ ጠባቂዬ ሆይ በኃጢአቴ ምክንያት ካገኘኝ
ደዌ ሥጋ ደዌ ነፈስ ፈውሰህ ሰው አድርገህ አቁመኝ፡፡
ስለእኔ የእሾህ አክሊል የደፋኸው ጌታ ሆይ የአንተ ራስ ስለእኔ ተወግቷልና
ኅሊናዬን ከሚወጋኝ የሀሳብና የኃጢአት እሾህ አድነኝ፡፡ በውኑ አንተ ለእኛ ብለህ
ካልሆነ በከንቱ ተወግተሃልን? ስለዚህ ጌታ ሆይ ቤተ መቅደስ ውስጥ ቆሜ
እየጸለይኩ እያስቀደስኩ ሳይቀር እሾህ ነገር እያሰወጋ ከሚያቆስለኝ ክፉ ሀሳብ
ስለደፋህልኝ የእሾህ አክሊል ብለህ እኔን አድን፡፡ አቤቴ እረኛዬ ሆይ በዘመነ
ሥጋዌህ ኃጢአትህ ተተወልህ፣ ኃጢአትሽ ተተወልሽ እንዳልካቸው ኃጢአትህ
ተትቶልሃል የሚለውን ድምጽህን አዲሱ ዘመን ከመግባቱ በፊት አሰማኝ፡፡
የልጆችን ለውሾች መስጠት አይገባም እንዳልካት ሴት ፈውስ ባይገባኝ እንኳ
ጌታ ሆይ ውሾችም ከጌቶቻቸው ማዕድ የወደቀውን ፍርፋሪ ይበላሉ ስትለህ
እምነቷን አይተህ እንደፈወስክላት እኔንም በእምነት ፍጹማን ከሆኑት የተረፈውን
የፈውስ ፍርፋሪ አቅምሰኝ፡፡ ቤዛዬ ሆይ ስለእኔ ተገርፈሃልና በመገረፍህ ቁስል
ፈውሰኝ፡፡ በሙሴ ፊት ብርሃን በሳልከበት በአንተ ፊት ላይ አይሁድ የረከሰ
ምራቃቸውን ሲተፉብህ የተጋሰከው ቤዛዬ ሆይ ዛሬም እኔ በየቀኑ በአንተ ፍጡር
ላይ የምተፋውን አይተህ አላጠፋኸኝም፣ ነገር ግን ርኩሱን ምራቅ በብርሃናዊ
ፊትህ ላይ ስለመቀበልህ እኔን ከርኩሰቴ አንጻኝ፡፡
አንተ ስለእኛ ስለሁላችን ተከሰህ በጲላጦስ ፊትህ ቀርበህልናልና አቤቱ ጌታ ሆይ
እኛ ስለኃጢአታችን አንከሰስ አንወቀስ፤ በአንተ መከሰስ እኛ እንፈወስ እንጂ፡፡ ጌታ
ሆይ ስለአንተ መንገላታታ የምእመናን መንገላታት ይበቃ፡፡ ስለአንተ መናቅ እኛ
በድነቁርናና ባለማሰብ፤ ባለማቀድና ባለመሥራት የገጠመን መናቅና መገፋት
በአዲሱ ዐመት ይከልከልልን፡፡ ጌታ ሆይ ስለእኛ መስቀል ተሸክመህ ሦስት ጊዜ
ወድቀሃልና፣ በግል በሠራነው ኃጢአት ከወደቅንበት ውድቀት፣ እንደተቋምም
ተሰነካክለን ከወደቅንበት አዘቅት፣ የአባቶችን ገድልና ትሩፋት ይዘን
ስለወደቅንበትም ታሪካዊ ውደቀት የአንተ መውደቅ ቤዛ ሆኖን እንነሣ፤ አቤቱ
አንሣን፣ ቀጥ አድርገህም አቁመን፡፡ ተነሣ አልጋህን ተሸክመህ ተመላለስ
እንዳልከው፤ ተነሡ ወንጌል እውነት ይዛችሁ፣ የተኛችሁበትን የታሪክ፣ የገድልና
የፍቅር አልጋ ይዛችሁ በአገልግሎት ተመላለሱ ብለህ በኃጢአትና በድከመት
የሰለሉ እግሮቻችንን አጽና፡፡ ጌታ ሆይ ስለእኛ ተቸንከረሃልና ከተቸነከርንባቸው
የጎሰኝነት፣ የድንቁርና የጥቅመኝነትና የአድሎ ችንካሮች አልላቀን፡፡ አቤቱ ጌታ
ሆይ ስለእኛ የሆምጣጤውን መራራ ጽዋ ቀምሰሃልና በምትኩ ከፍቅርና
ከይቅርታ፣ ከዕወቀትና ከምሕረት ጽዋ እኛን አቅምሰን፡፡ ሳይገባህ ስለእኛ
ተገንዘህ ተቀብረሃልና አቤቱ ከድንዛዜ መግነዝ ፍታን፣ ከጥልቅ የድንቁርና
መቃብርም አውጣን፡፡ ስለ ልዩ ትንሣኤህ ትንሣኤ ልቡና ወኅሊና አድለን፡፡ ስለ
ቅድስት ዕረገትህም ዕርገተ ኅሊናና አልዕሎ ልቡናን አሳድርብን፡፡ ስለ ዳግም
ምጽአትህም በቀኝህ የሚቆሙ ወዳጆችህ የሚሠሩትን ምግባረ ሃይማኖት
ለመሥራት አብቃን፡፡
ጌታ ሆይ በዚህች በዿግሜ ኢዮብን በዮርዳኖስ ወንዘህ አጥበህ እንደፈወስነው
እኛን ኢትዮጵያውያንን ከሚያጸይፍ ቁስለ ነፍሳችን ፈውሰን፡፡ እጠበን እንጠራለን፤
አንጻንም እንነጻለን፡፡ ጌታ ሆይ ስለእኛ አይደለም መምጣትህን አስቀድመው
ይነግሩ ዘንድ ስለነገርሃቸው አርእሰተ አበውና ነቢያት፣ መርጠህ አስተምረህ
ሾመህ ዐለምን ወደአንተ ይመልሱ ዘንድ መስቀል መከራ ሞትን አሸክመህ
ስለላክሃቸው ሐዋርያት፣ ኑፋቄ ዘርቶ መንጋውን ከአንተ ለመለየት የተጋውን
የዲያብሎስን ሽንገላ ተቃውመው ሃይማኖትን በንጽህ ስለጠበቁ ሊቃውንት፣
ፍትወታትን ድል ነሥተው በተጋድሏቸው ያለደም መፍሰስ ሰማዕትነትን
ስለተቀበሉ ጻድቃን፣ የነገሥታትን ማስፈራራትና የሚያደርሱባቸውን መከራ
ሳይሰቀቁ ነገሥታተ አሕዛብን ድል ስለነሡ ሰማዕታት፣ በንጽሕ እና በትጋት ሆነው
ያለመታከት አንተን ስለሚያገለግሉ ሊቃነ መላእከትና ሠራዊተ መላእክት ብለህ
ይልቁንም ደግሞ ከሁሉም በላይ ስለሆነች ከእርሷ ሰው ትሆን ዘንድ
ስለመርጥካት የንጽሕና መሠረት የባሕርየ አዳም መመኪያ ስለሆነች ስለንጽሕተ
ንጹሐን ቅድስተ ቅዱሳን ድንግል እናትህ ብለህ ጌታ ሆይ በወደቅሁበት አዘቅት
እለፍና እኔን ምስኪኑን ቁስለኛ የዲያብሎስ ምርኮኛ ከወደቅሁበት አንሣኝ፤
በሚቀጥለው ዐመትና በመጪዎቹ ዘመናትም አንተን በመከተል ሕግህን
በመጠበቅና ፈቃድህን በመፈጸም አንሣኝ፡፡ ለፈቃዴ አሳልፈህ አትሰጠኝ፣
ይልቁንም ለፈቃድህ የምገዛበትን ልቡና ሥጠኝ፡፡ አቤቱ አትተወኝ አትጣለኝም፣
አሜን፡፡

👉እርሶ ያወቁትን እውቀት ሌሎች ያውቁ ዘንድ ቻናላችንን ሼር በማድረግ ጓደኛዎን ይጋብዙ

ቻናላችንን ይቀላቀሉ
👇👇👇👇👇 👇👇👇👇👇
@ethiopianissm @ethiopianissm
@ethiopianissm @ethiopianissm
@ethiopianissm @ethiopianissm
እንኳን ለቅዱስ ሩፋኤል አመታዊ በአል በሰላም አደረሳችሁ
ጳጉሜ፦3
ቅዱስ ሩፋኤል
ሥንክሳር፦
1)የስሙ ትርጉም፦ "የእግዚአብሔር መድኃኒት"
2)ምድብ፦ ከ7ቱ ሊቃነ-መላእክት እንዱ።
3)ትውልድ፦ መላእክት የሥጋ ልደትና ሞት የለባቸውም(ለመጠቆም ያክል ነው)
4)ዓቢይ ተልእኮ፦ ፈታሄ ማህፀን፣ ሕክምና፣ የቀንና የዓመታዊ የሰዎችን ሥራ
ለእግዚአብሔር ዘገባ ማቅረብ፣ የሌሊት 3ሰዓት ተረኛ ጥበቃ፣ ከአውሬዎች
ጥበቃ፣ መንገድ መምራትና ሌሎችም፤
5)ተኣምር፦"ከከበሩት ከሰባቱ ሊቃነ መላእክት አንዱ እኔ ሩፋኤል ነኝ" እንዳለ::
ጦቢት 12፥13
እንግዲህ ከባህሪው ቅድስና ፍጥረቱን በጸጋ ቅድስና መርጦ የሚለይ
እግዚአብሔር አክብሮ እንዲህ ያለ ሰማያዊ ፀጋ ከሰጣቸው ቅዱሳን መላእክት
መካከል በስልጣኑ ሊቀመናብርት (የመናብርት አለቃ) የሆነ በሹመት ፈታሔ
ማኅጸን (ማሕጸን የሚፈታ) ከሳቴ እውራን (የእውራንን ዓይን የሚያበራ) ሰዳዴ
አጋንንት (አጋንንትን የሚያባርር) ፈዋሴ ዱያን (ድውያንን የሚፈውስ)፣ አቃቤ
ኆኅት (የምህረትን ደጁ የሚጠብቅ) ተብሎ የተገለጠ ከሊቃነ መላእክቱ ቅዱስ
ሚካኤልና ቅዱስ ገብርኤል ተከትሎ የሚነሳ መልአክ ራሱን እንዲህ በማለት
ገለጠ « የቅዱሳንን ጸሎት ከሚያሳርጉ ወደ ከበረ ወደ ገነነ ወደ እግዚአብሔር
ጌትነት ከሚያገቡ ከከበሩ ከሰባቱ አለቆች አንዱ አለቃ እኔ ሩፋኤል
ነኝ» (ጦቢ.12÷15)
ይህ የከበረ ታላቅ መልአክ ሰሙ ሩፋኤል የሚለው ከአምላክ ለሰዎች የተሰጠ
ፈውስ የሚለውን ይተካል «በሰው ቁስል የተሾመ ከከበሩ ከመላእክት አንዱ
ሩፋኤል ነው፡» (ሄኖ.6÷3)
ይህ መልአክ እንደሌሎቹ ሊቃነ መላእክት ሁሉ የሰው ልጆችን ይጠብቃቸዋል
(ዳን.4÷13 ዘጸ. 23÷20 መዝ. 90÷11-13 )
ያማልዳል፣ ከፈጣሪ ያስታርቃቸዋል፡፡(ዘካ.1÷12)
በፈሪሀ እግዚአቤሔር እና በአክብሮተ መላእክት ያሉትን ያድናቸዋል
(ዘፍ.49÷15 መዝ.3÷37)
« እግዚአብሔር ሃይሉን የሚገልጥበትን ቅጣቱን ሊያሳይ ቢወድ አስቀድሞ
መርጦ በወደዳቸው ለይቅርታ የተዘጋጁ የይቅርታ መላእክትን
ያመጣል» (ሮሜ.9÷22)
የወላድ ማኅፀን እንዲፈታ ስለተሸመ ከጌታ አዋላጅ ብትኖርም ባትኖርም ሐኪም
ሩፋኤል አይታጣም በምጥ ጊዜ ሲጨነቁ ሴቶች ሁሉ የመልአኩን መልክ
አንግተው ማርያም ማርያም ይላሉ ማየጸሎቱን ጠጥተው ቶሎ ፈጥነው
ይወልዳሉ እያሉ ደጅ ጠንተው ይማጸኑታል፡፡
ዜና ግብሩን ሊቁ ዮሐንስ አፈወርቅ ከተናገረለት በመነሳት በቅዱሳን ላይ ድንቅ
የሆነ እግዚአብሔር በመልአኩ አድሮ ያደረጋቸውን ተግባራት አበው የበረከት
ምንጭ በሆነ ድርሳኑ ላይ አኑረው የበረከቱ ተካፋይ እንድንሆን ሰጥተውናል፡፡
በጉልህ ሠፍረው ከምናገኛቸው ብዙ ድንቅ ሥራዎች መሀል ጥቂቶቹን እነሆ፦
~> በሥነ-ስዕሉ የተማጸኑ፣ በምልጃው ታምነው የጸኑ ቴዎዶስዮስንና
ዲዮናስዮስን በገሃድ ተገልጾ ለንግስናና ለጵጵስና ክብር አብቅቷቸዋል፡፡
~> የንጉስ ቴዎዶስዮስ ልጅም ጻድቁ አኖሬዋስም በፈጣሪው ህግ እየተመራ
የሊቀ መናብርቱን መታሰቢያ ቤተ መቅደስ አሳንጾ ሲያስመርቅ ለበለጠ ክብር
ልቡን አነቃቅቶ ለታናሽ ወንድሙ ለአርቃዴዋስ የነጋሢነት ስልጣኑን ትቶ መንኖ
በስውርና በጽሙና እዲኖር ረድቶታል፡፡
~> በሊቀጳጳሳት ቴዎፍሎስ ዘመን አባቶች ለሊቀመናብርቱ ክብር በአሣ አንበሪ
ጀርባ ላይ ያሳነጹትን መታሰቢያ ቤተ መቅደስ በወደቡ አጠገብ በእስክንድሪያ
ሳለች ጠላት ዲያቢሎስ አነዋውጾ ለምስጋና የታደሙትን ምዕመናን ሊያጠፉ አሣ
አንበሪውን ቢያውከው ወደ ሊቀመናብርቱ ተማጽነው እርዳን ቢሉ ፈጥኖ ደርሶ
በበትረ መስቀሉ (ዘንጉ) ገሥጾ ከጥፋት ታድጓቸዋል፡፡
በቅዱስ መጽሐፍም እንደተገለጠው
~> ሣራ ወለተ ራጉኤልን አስማንድዮስ ከተባለው የጭን ጋንኤን ሲታደጋት
የጦቢያን አባት የጦቢትን ዓይን አበራለት (መጽሐፍ ጦቢት)
ከዚህም አልፎ የይስሐቅን እናት ሣራን፣ የሶምሶንን እናት (እንትኩይን)
ምክነታቸውን የቆረጠ ወልዶ ለመሳም ያበቃቸው ይኸው ፈታሔማኅጸን የልዑል
እግዚአብሔር መልአክተኛ ቅዱስ ሩፋኤል ነው፡፡
የመልአኩ ጥበቃና የክንፎቹ መጋረድ ከተዋህዶ ምእመናን ጋር ይኑር አሜን።

👉እርሶ ያወቁትን እውቀት ሌሎች ያውቁ ዘንድ ቻናላችንን ሼር በማድረግ ጓደኛዎን ይጋብዙ

ቻናላችንን ይቀላቀሉ
👇👇👇👇👇 👇👇👇👇👇
@ethiopianissm @ethiopianissm
@ethiopianissm @ethiopianissm
@ethiopianissm @ethiopianissm
🗣2013 ዓ.ም ምን ይዛ ትመጣ ይሆን 😳
ከታች ባለው ሊንክ በመግባት ሊቀ ትጉሃን መ/ር ገ/መስቀል ኃ\መስቀል ያስተላለፉትን የእግዚአብሔር መልእክት ትንቢት ያዳምጡ 👇🏿👇🏿👇🏿
https://www.hottg.com/EthiopeTowoderos/2982
💚💛❤️
ወደኋላ ቲዩብን ሰብስክራይብ ለማድረግ
https://www.youtube.com/channel/UCmdQNLIJU8JqXNCd1s3LOqg/featured?sub_confirmation=1
👇🏿👇🏿👇🏿
ቀደምት ጥበብና ጠቃሚ ሃይማኖታዊ ትምሕርቶች የሚተላለፍበት የቴሌግራም ቻናሎች ከፈለጉ ደግሞ ከነዚህ መካከል ይምረጡ 👇🏿
💚💛❤️
"በቸርነትህ ዓመታትን ታቀዳጃለህ ምድረ በዳውም ስብን ይጠግባሉ'' መዝ 65÷11
🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼
እንኳን ከዘመነ ዮሐንስ ወደ ዘመነ ማቴዎስ በሰላም አሸጋገረን!
🌼እንኳን አደረሳችሁ🌼
🌼መልካም አዲስ አመት🌼


🌼መስከረም ፩/፪፲፩፫ ዓ.ም🌼

🌼 @ethiopianissm 🌼
የበረኸኞቹን የትንቢት ቃል
ለመስማት እንዘጋጅ።
*~★★~*

• እፎይ የእረፍት ጊዜዬን በሰላም ፈጸምኩ። እንደ ንስርም ታድሼ እንደ አንበሳ እያገሳሁ፣ እንደፈረደብኝ ደግሞ ልንጫጫብህ፣ ልሟገትህ፣ ነጭ ነጯንም ልግትህ ልመጣ ነኝ። ጠብቀኝ። ሰምተሃል።

#ETHIOPIA | ~ ዘንድሮ በ2013 እና በቀጣዩ በ2014 ዓም በዋናነት በኢትዮጵያችን የሚጠበቁ ዋና ዋና ክስተቶች ዓለሙ ሁሉ ይሰማው ዘንድ በበረኸኞቹ ተዘጋጁ ተብላችኋል። ለመስማት እንዘጋጅ። ሲጨንቅ።

•••
አስቀድሞ እንደተነገረ ቀጣዮቹ ሁለት ዓመታት “ለኢትዮጵያ የከባድ ምጥ ዓመታት” እንደሆኑ ተነገሯል። ከአንድ ዓመት በፊት ጀምሮ መጪዎቹ ሦስት ዓመታት ለኢትዮጵያ እጅግ አስጨናቂ ዓመታት ይሆናሉ ተብሎ በ2011 ዓም ማብቂያ ላይ በበረኸኞቹ የተነገረው ትንቢት ዓምና በ2012 ዓም ቃል በቃል መፈጸሙም ይታወሳል። በበረኸኞቹ ከተናገሩት የትንቢት ቃሎች አንዳችም የቀረ የለም። በሙሉ ተፈጽሟል።

•••
አምና ገና መስከረም ወር ላይ ዘንድሮ በ2012 ዓም ማለት ነው ምርጫ የሚባል ነገር በኢትዮጵያ የለም። አይደረግምም በማለት ለህዝቡ ሁሉ እነገር ዘንድ ያዘዙኝና የነገርኳችሁ የትንቢት ቃል በሙሉ ዓይናችን እያየ አንድ በአንድ መፈጸሙን ታስታውሳላችሁ። ይህንን የበረኸኞች ቃል በእኔ በኩል ላለመናገር የነበረብኝን ጭንቀትም መድኃኔዓለም ብቻ ነበር የሚያውቀው።

•••
መንግሥት የምርጫ ቀን ቆርጦና ወስኖ እያየሁ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች ክርክርና የምረጡኝ ቅስቀሳ ጀምረው እያየሁ፣ የአውሮጳ ኅብረትና የአማሪካ መንግሥት ለምርጫው ማስፈጸሚያ ገንዘብ ለግሰው ወደፊት ሲሉ እያየሁ፣ አገር ምድሩ ምርጫ ምርጫ እያለ ሲራወጥ እያየሁ እኔ ይህን የአባቶች ትንቢት በድፍረት “ ዘንድሮ ምርጫ የለም” ብሎ መናገሩን ፈርቼ ላለመናገር የተጨነቅኩትን ጭንቀት ፈጣሪዬ ብቻ ነበር የሚያውቀው። እነሱ ግን ዘመዴ ንገር ያልህን ንገር፣ አክሊለ ገብርኤል አትፍራ፣ መልእክቱ በአንተ በኩል ያልፍ ዘንድ የተፈቀደ ስለሆነ አትስጋ። ማን ያውቃል የኢትዮጵያን ትንሳኤ አብሳሪ ሆነህስ እንደሆን። ብቻ ራስህን እየመረመርክ ንገር። እኛ የምንልህን፣ የምንልክልህንም በራስህ የአገላለጽ ፀጋ ለህዝቡ ሁሉ ንገር ብለው ወጥረው ሰቅዘው ያዙኝ።

•••
ቀጠሉና የቻይናው የወፍ ጉንፋን የመሰለ ጉንፋን በኢትዮጵያም፣ በመላው ዓለምም ይከሰታል። የኢትዮጵያው ከአፋር በሚነሱ ወፎች አማካኝነት ነው የሚገባው። እሱንም ንገር አሉኝ። ነገርኳችሁ። ያው የሆነው ሁሉ ሆነ።

•••
በ2012 ዓም መንገዶች ሁሉ ይዘጋሉ። የዐቢይ ጾም ዘንድሮ አይጾምም። ዓለም ጭንቅ ትሆናለች በል አሉኝ። እሱንም ነገርኳችሁ። የሆነው ሁሉ ሆነ።

•••
በወርሃ መስከረም በትግራይ የመስቀለ ክርስቶስ ህንፃ ቤተ ክርስቲያን ተሠርቶ ፍጻሜውንም አግኝቶ ይመረቃል። የቤተ ክርስቲያኑ መሥራች የሆኑት አባ ዘወንጌል የተባሉ ደገኛ አባት ከቤተ ክርስቲያኑ ምርቃት ማግሥት እንደሚያርፉ፣ ከእረፍታቸው ማግስትም በኢትዮጵያ የኦርቶዶክሳውያን መከራ በከፋ ሁኔታ እንደሚጀምር፣ ብዙዎች በሰማዕትነት እንደሚያልፉ ንገር የተባልኩትንም የነገርኳችሁ። በ2011 ዓም በወርሃ ነሐሴና በወርሃ መስከረም በ2012 ዓም ነግረኳችሁ። የዚህ የበረኸኞቹ የትንቢት ቃልም በወርሃ ጥቅምት ከአባ ዘወንጌል ባረፉ በማግስቱ “ ዐቢይ አህመድ ወደ ራሺያ በሄደ ጊዜ፣ ጃዋር መሐመድ “ ተከበብኩ” የሚል ኮድ በመስጠቱ ምክንያት በኦሮሚያ ክልል ያሉ ንጹሐን ኦርቶዶክሳውያን የተዋሕዶ ልጆች እንደበግ ታረዱ፣ እንደ እባብም ተቀጠቀጡ። ይሄም ተፈጸመ።

•••
ዐቢይ ጾምም በቴሌቪዥን ተቀደሰ። ቤተ ክርስቲያን ተዘጋች። የዓለም ሀገራት የየብስም፣ የባህርም፣ የአየርም መንገዶችም ተዘጉ። ተጠረቀሙ። የኢትዮጵያ ምርጫም ከግንቦት 7 ወደ ነሐሴ 10 ተዘዋወረ። እኔ መደንገጥ ጀመርኩ። ቀጥሎ ወደ ነሐሴ 23 ተዘዋወረ። አሁንም ደነገጥኩ። የበረኸኞቹ ቃል ላይፈጸም ነውን ብዬም ሰጋሁ። በመጨረሻም ዐብይ አህመድና ብርቱካን ሚደቅሳ እግዚአብሔር ይስጣቸውና “ ዘንድሮ ምርጫ የለም።” ብለው ገላገሉኝ። እፎይ እንዴት እንደሚጨንቅ። የነቢየ እግዚአብሔር ዮናስ ጭንቀት የገባኝ ባለፈው ዓመት ነበር። መጻኢውን ዘመን ቁልጭ አድርገው አይተው የሚሆነውን፣ የሚፈጸመውን ሁሉ የሚነግሩን አባቶቻችን ግን ምንኛ የታደሉ ናቸው? ይደንቀኛል። ከምር ስለ እውነት ዝም ብሎ ይደንቀኛል። እንኳንም ኦርቶዶክስ ሆንኩኝ። እንኳንም የተዋሕዶ ልጅ ሆንኩኝ። እንኳንም ኢትዮጵያዊ ሆንኩኝ። ታድዬ።

•••
ዘንድሮም እንደተለመደው የበረኸኞቹ መልእክት መጥቷል። ለሁሉም እነግር ዘንድ መልእክቱ መጥቷል። የዘንድሮው ግን ጫን ያለ ነው። እንዴት አድርጌ እንደማቀርበው ሁላ ጨንቆኝ ብቻዬን መንበጫበጭ ከጀመርኩ 15 ቀናት አለፉኝ። አሁን ግን የግድ ነው። የትንቢቱ መፈጸሚያ ቀናት እየተቃረቡ ስለሆነ መንገሬ ግድ ነው። እናም ተዘጋጅታችሁ ጠብቁኝ። ለመስማት ራሳችሁን አዘጋጅታችሁ ጠብቁኝ።

•••
ምንአልባት ዛሬ ማታ ላይ በዩቲዩብ ቻናሌ ላይ ማድረግ ስላለብን ነገሮች አስቀድሜ ትዘጋጁ ዘንድ በመጠኑም ቢሆን የመግቢያ ቃል እነግራችኋለሁ። እናም እንደተለመደው፣ እንደወትሮው ሁሉ ልክ በተለመደው ሰዓታችን በዩቲዩብ ቻናሌ ላይ እንገናኝ።

•••
የሚነገረውን ቃል ሰምተህ የታዘዝከውን፣ የታዘዝሽውን የማትፈጽሚ የማትፈጽመውም ከሆነ መስማቱ ምንም አይጠቅማችሁም። የበረኸኞቹ ቃል የሚነገረው ሰምተው የትእዛዝ ቃሉን ለሚፈጽሙ ነው። የትንቢት ቃሉን ሰምተህ ስትጨነቅ፣ ስትጠበብ፣ ስታለቅስ ስታነባም የምትውል ቢሆን ምንም ዋጋ የለውም። አንዳንዶች ይሰማሉ፣ ያለቅሳሉ፣ ነገር ግን እንዲህች ብለው ንስሃ አይገቡም። እንደ ጠንቋይ ትንቢት ማድነቅ ብቻ ነው ሥራቸው።

•••
የሚሰሙ ብዙዎች ናቸው። የሠሙትን ተግብረው እንደቃሉ የሚኖሩ ግን ጥቂቶች ናቸው። ከካህናት ወገን፣ ከዲያቆናት ከመነኮሳት፣ ከመምህራን ከዘማርያን ወገን፣ ወንድም ሴትም ቢሆኑ አብዛኛው የኖህ ዘመን ስሜትና ጠባይ ነው ያለን። ፒፕሉ እንደሆን በሚሰማውም በሚያየውም ነገር ሁሉ ያሾፋል፣ ያላግጣል፣ ይቀልዳል፣ ብዙ ምስጢር የተከደነበት፣ የተዘጋበትም ነው። ኋላ ላይ ግን መርከቡ ከተዘጋ በኋላ፣ የንፍር ውኃው አንገቱ ጋር ሲደርስ ወደ መርከቧ ለመግባት፣ ይራወጣል፣ ይንፈራገጣልም። ጥቂቶች ግን ልባቸውን ከፍተው ይሰማሉ። ይወስናሉ። በመጨረሻም ይድናሉም። ይኸው ነው።

•••
“እንዲሁ ኋለኞች ፊተኞች፥ ፊተኞችም ኋለኞች ይሆናሉ፤ የተጠሩ ብዙዎች፥ የተመረጡ ግን ጥቂቶች ናቸውና።” ማቴ 20፥16

•••
ፌስቡክ ምክንያቱን ሳይነግረኝ በሰጠኝ ፔጅ ላይ እንዳልጽፍ ከልክሎኛል። ሙግት ላይም ነኝ። እኔን ብቻም አይደለም። ዲን አባይነህ ካሴንም በአንደኛው አካውንቱ እንዳይጽፍ አግዶታል። እናም ሁኔታውን፣ ድርጊቱን ስናጤነው ነገርየው ጤናማ አይመስልም። የሆነ በእኛ ላይ የተመደበ ፀረ ኦርቶዶክስ ሰውም በቦታው የተመደበ ይመስላል። ሆኖም ግን እኔ የምነግራችሁ ነገር ቢኖር ሰባክያኖችም የተለያዩ አማራጮቹን መጠቀሙን አትርሱ። በተለይ የቴሌግራም ቻናሌንና፣ የዩቲዩብ ቻናሌን ሰብስክራይብ አድርጉ አስደርጉ። በፌስቡክ መንደር ያለውንም ህዝብ ወደ እዚህ ማፍለስ ነው። የአድማጭ ተመልካች የአንባቢንም ቁጥር ከፍ እንዲል አድርጉ። አስደርጉም።

•••
👉 ዩቲዩብ ፡https://www.youtube.com/c/ZemedkunBekele

👉ቴሌግራም: http://hottg.com/ZemedkunBekeleZ

•••
የማታ ሰው ይበለን።
•••

ሻሎም !
2020/09/21 18:29:34
Load New Feed
Back to Top