TG Telegram Group Link
Channel: ኢትዮጵ
Back to Bottom
❖ ‹ፍልሰት› የሚለው ቃልም “ፈለሰ ሔደ፤ ተሰደደ” ካለው የግእዝ ግስ የተገኘ ሲኾን ትርጕሙም ከአንድ አገር ወደ ሌላ አገር መሔድን ያመለክታል፡፡

❖ ‹ፍልሰታ ለማርያም› ሲልም እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ካረፈች በኋላ ከጌቴሴማኒ ወደ ገነት መወሰዷን የሚያስረዳ መልእክት አለው ።

❖ በጾመ ፍልሰታ ባሕታውያን ብቻ ሳይኾኑ ዓለማውያንም በእግዚአብሔር ቸርነት፣ በእመቤታችን አማላጅነት የሰይጣንን ፈተና ድል ለማድረግ እንዲቻላቸው ከቤተሰቦቻቸው ተለይተው በየገዳማቱና በየአብያተ ክርስቲያናቱ በዓት አዘጋጅተው፣ ሱባዔ ገብተው፣ ፈቃደ ሥጋቸውን ለፈቃደ ነፍሳቸው አስገዝተው ይጾማሉ፤ ይጸልያሉ፤ እንደዚሁም ቅዱስ ሥጋውን ክቡር ደሙን ይቀበላሉ፡፡

❖ እኛም የእመቤታችንን ዕረፍትና ትንሣኤ በማሰብ ከልጇ ከወዳጇ የሚገኘውን ጸጋና በረከት ተስፋ በማድረግ የአባቶቻችንንና የእናቶቻችንን ፈለግ ተከትለን በየዓመቱ ጾመ ፍልሰታን እንጾማለን፤ የምንችል ደግሞ አስቀድሰን ቅዱስ ሥጋውን ክቡር ደሙን እንቀበላለን፡፡

❖ በተጨማሪም ይህ ጾም ለእመቤታችን ያለንን ፍቅርም የምንገልጽበት ወቅት ነው፤ በተለይ ኦርቶዶክሳውያን ሕፃናት በአብዛኛው ትምህርተ ወንጌል የሚማሩት፤ ቅዱስ ሥጋውን ክቡር ደሙን የሚቀበሉት በዚህ በጾመ ፍልሰታ ነው፡፡

ጾሙን ጾመን ቅዱስ ሥጋውን ክቡር ደሙን ተቀብለን ለድኅነት እንድንበቃ፤ የእመቤታችንን ረድኤት በረከት እንድናገኝ አምላካችን እግዚአብሔር ይርዳን፡፡

የእግዚአብሔር አብ ጸጋ፣ የእግዚአብሔር ወልድ ቸርነት፣ የእግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ አንድነት፣ የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም አማላጅነት፣ የቅዱሳን ጸሎትና ምልጃ ከሁላችንም ጋር ይሁን አሜን


"ልብህን በእርጋታ አኑረው፤ የሁሉም መጨረሻ እና የሁሉም አገልጋይ ለመሆን በጣም ትጋ ለከንቱ ንግግር ዘገምተኛና ሰነፍ ሁን፤ ነገር ግን የቅዱሳት መጻህፍትን ቃል በማወቅ በመስማት ድኅነትን የሚሰጡ ናቸውና ብልህ ሁን"
📚ታላቁ ባስልዮስ ዘቂሳሪያ

               ወስብሐት ለእግዚአብሔር
#ሼር
👉 @ort_mezmur
🌻🌻🌻እንኳን ለፍልሰታ ለማርያም ጾም በሰላም አደረሳችሁ!!!🌻🌻🌻

✥✥✥"ፆም ጸሎታችንን ተቀበልልን፣
ደስ የሚያሰኝህ ይሁንልን።
እንድናሸንፍ ኃይልህን ስጠን፣
አፍሮ ይመለስ ይውደቅ ሰይጣን።"✥✥✥

«ሞትሰ ለመዋቲ ይደሉ ሞታ ለማርያም የሐጽብ ለኲሉ፤ ሞት ለማናቸውም ሰው ሁሉ የተገባ ነው የማርያም ሞት ግን ሁሉን ያስደንቃል» ቅዱስ ያሬድ  

✟✟✟ፆሙን ለሀገራችን የሰላም የፍቅር፤ ለእኛም በረከት ፆም ይሁንልን!✟✟✟

@ethiopianissm
@ethiopianissm
"#ከትዕቢተኛ_ሰው_በላይ_ጎስቋላ_ሰው_የለም!"

እንዲያውም ትዕቢት ከዝሙት ወይም ከማመንዘር በላይ እኛን ያቆሽሻል። #ለምን? ያልከኝ እንደሆነም....
👉ምንም እንኳን ዝሙት ንስሐ ካልገቡበት ሥርየተ ኃጢአት የሌለው በደል ቢኾንም በዝሙት የቆሸሸ ሰው ንስሐ ለመግባት ቅርብ ነው። በትዕቢት የታመመ ሰው ግን እንዲህ እንደ ዘማዊው ያለ ዓቅምን አያገኝም። ስለዚህ ትዕቢት እጅግ አደገኛ ደዌ ዘነፍስ ነው ብዬ እነግርሃለሁ።

✦ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ✦
#የእሑድ_ውዳሴ_ማርያም_ትርጓሜ

በዚህ ዕለት እመቤታችን ከወትሮው ይልቅ ቀደም ብላ መጥታለች፡፡ “ዛቲ ዕለት ተዓቢ እምኩሎን ዕለታት፤ ወውዳሲያቲሃኒ የዓብያ እምኵሉ ውዳሴያት - ከዕለታት ኹሉ ይህቺ ዕለት ታላቅ ናት፤ ከውዳሲያቱም ኹሉ የዚች ዕለት ውዳሴ ታላቅ ነው” አለችውና ባረከችው፡፡ እርሱም በቤተ መቅደስ ባሉ ንዋያት ማለትም፡- በመሶበ ወርቅ፣ በተቅዋመ ወርቅ፣ በማዕጠንተ ወርቅ፣ በበትረ አሮን እየመሰለ ሲያመሰግናት አድሯል፡፡

፩. ንዕድ ክብርት ሆይ! ከሴቶች ተለይተሽ የሥላሴ ባለሟል ተባልሽ፡፡ ከተለዩ የተለየሽ፣ ከከበሩ የከበርሽ፣ ቅዱሳን ኪሩቤል የተሣሉብሽ፣ ቅዱሳን ካህናት የሚያመሰግኑሽ ኹለተኛ ክፍል አንቺ ነሽ /ዘጸ.፳፮፡፩-፴/፡፡
ሕግ የተጻፈባት ጽላት ያለብሽ የምትባዪ አንቺ ነሽ /ዘጸ.፴፪፡፲፭-፲፱/፡፡ ኪዳንም ያልኹት በእግዚአብሔር ጣቶች የተጻፉ (በግብር አምላካዊ የተገኙ) ዐሥሩ ቃላት ናቸው፡፡ ዐሥርቱ ቃላትን በጽላቱ ጽፎ እንዳኖረ ኹሉ ዋሕድ ቃለ እግዚአብሔርም በአፃብዐ መንፈስ ቅዱስ (ያለ ወንድ ዘር፣ በግብረ መንፈስ ቅዱስ) በማኅፀንሽ እንዲቀረጽ ኾኗልና የሙሴ ጽላት አንቺ ነሽ /ቅዳ.ማር. ቁ.፴፫/፡፡ ዐጤ ዘርዐ ያዕቆብም በነገረ ማርያም መጽሐፉ፡- “… ወማኅፀናሰ ለማርያም ድንግል በክልኤ ይትሜሰል በጽላት ዘተጽሕፈ ውስቴታ ዐሠርተ ቃላት፡፡ ወዐሠርተ ቃላት ቀዳሜ ስሙ ለወልዳ ውእቱ ዘውእቱ የውጣ ዘተሰምየ በኈልቄ ዐሠርተ ቃላት - … በኹለት ወገን ድንግል የምትኾን የማርያም ማኅፀንስ ዐሥሩ ቃላት በውስጧ በተጻፈ ጽላት ይመሰላል፡፡ ዐሥሩ ቃላትም የልጇ የኢየሱስ ክርስቶስ የመዠመርያ ስሙ ነው፤ ያውም የውጣ በዐሥሩ ቃላት የተጠራ ነው” ብሏል /ነገረ ማርያም በብሉይ ኪዳን፣ ክፍል ፩፣ ገጽ ፻፳፰፣ በመጋቤ ሐዲስ ሮዳስ ታደሰ/፡፡
ከአንቺ ሳይለወጥ ሰው ኾነን፡፡ ለኦሪት ሳይኾን ለወንጌል ሊቀ ካህናት ኾነን፡፡ ለምድረ ርስት ሳይኾን ለመንግሥተ ሰማያት አስታራቂ ኾነን፡፡ ሐዋርያው ጳውሎስ፡- “በውድ ልጁም፥ እንደ ጸጋው ባለ ጠግነት መጠን፥ በደሙ የተደረገ ቤዛነታችንን አገኘን፤ እርሱም የበደላችን ስርየት ነው” እንዲል በከበረ ደሙ ፈሳሽነት በዓለመ ሥጋ በዓለመ ነፍስ ያሉትን አዳናቸው /ኤፌ.፩፡፯/፡፡ ሊቁ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅም የኤፌሶንን መልእት በተረጐመበት በአንደኛው ድርሳኑ ላይ፡- “ከእግዚአብሔር ዘንድ ያገኘነው ሥርየተ ኃጢአት በርግጥ ታላቅ ነው፡፡ ተቀዳሚ ተከታይ በሌለው በልጁ ደም መኾኑ ግን ከምንም በላይ ታላቅ ነው” በማለት የእግዚአብሔር ከኅሊናት የሚያልፈውን የማዳን ምሥጢር (ፍቅር) በመደነቅ ተናግሯል፡፡ በከበረ ደሙ ፈሳሽነት በዓለመ ሥጋ በዓለመ ነፍስ ያሉትን ካዳነ ልጅሽ ጽንዕት በድንግልና እመቤታችን ጸጋውን ክብሩን እንዳይነሣን ለምኚልን፡፡

፪. ኹል ጊዜ ንጽሕት የምትኾኚ አምላክን የወለድሽ እመቤታችን ሆይ! ስለዚህ ነገር ኹላችን እናከብርሻለን፤ እናገንሻለንም፡፡ ሰውን ከሚወድ ሰው ከሚወደው ከርሱ ይቅርታን እናገኝ ዘንድ ኹል ጊዜ ዓይነ ልቦናችንን ወዳንቺ እንሰቅላለን፡፡ ሸምሸር ሰጢን ከሚባል ከማይነቅዝ (በአምልኮተ ጣዖት ከማይለወጥ) እንጨት የተቀረጸ በአፍአ በውስጥ በወርቅ የተለበጠ ታቦት አካላዊ ቃልን ይመስልልናል /ዘጸ.፳፭፡፱-፳/፡፡ ይህ ንጹሕ የሚኾን፣ መለወጥ የሌለበት እርሱ ባለመለወጡ አለመለወጧን ነገራት፤ ከአብ ዕሪና ባለመለየቱም አለማለየቷን ነገራት (አምላክ ወሰብእ ኾኖ እርሷም እም ወድንግል መኾኗን ነገራት)፡፡ ከጥበብ በሚበልጥ ጥበብም ዘር ምክንያት ሳይኾነው እንደ እኛ ሰው ኾነ፡፡ አበው፡- “ዓለሙን ከፈጠረበት ጥበብ ይልቅ ሰው ኾኖ ዓለሙን ያዳነበት ጥበብ ይበልጣል” የሚሉትም ስለዚሁ ነው፡፡ አደፍ ጉድፍ ሳያገኝሽ መለኮቱን አዋሕዶ ከሥጋሽ ሥጋ ከነፍስሽ ነፍስ ነሥቶ ሰው ኾነ፡፡ መለኮቱን አዋሕዶ ሰው ከኾነ ልጅሽ ጽንዕት በድንግልና እመቤታችን ጸጋውን ክብሩን እንዳይነሣን ለምኝልን፡፡
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ከ1700 ዓመት በኋላ ከግእዝ ቋንቋ ወደ ዐማርኛ ቋንቋ በመጋቤ ሐዲስ ዶክተር ሮዳስ ታደሰ የተተረጎመው የእንስሳት፣ የአራዊት የሥነ ሕይወት ምሳሌ የያዘው አስደናቂው
💥"መጽሐፈ ፊስአልጎስ" እና
💥"መጽሐፍ ቅዱስና የሕክምና ሳይንስ" የተሰኘው የምርምር መጽሐፍ ከገበያ መጥፋታቸውን ተከትሎ 60 ብር የነበሩት ተሠርዘው 160 እየተሸጡ መኾናቸውን አንባብያን አሳውቀውናል።
በመኾኑም ይህንን ለማስቀረት ለአንባብያን ሲባል በድጋሚ በ60 ብር መሸጫ ብቻ የተወሰነ ኮፒ ታትሟል። መጻሕፍቱ ሳያልቅ የምትፈልጉ
0913422447 አቶ ብርሃን ጋር ታገኛላችሁ።
# የሰኞ_ውዳሴ_ማርያም_ትርጓሜ
ሊቁ ቅዱስ ኤፍሬም እመቤታችን ከባረከችው በኋላ ምስጋናውን የጀመረው
#“ፈቀደ እግዚእ…” ብሎ ነው፡፡
፩. በመቅድመ ወንጌል “ወአልቦቱ ካልእ ሕሊና ዘንበለ ብካይ ላዕለ ኃጢያቱ -
በኃጢአቱ ከማዘን፣ ከማልቀስ በቀር ሌላ ግዳጅ አልነበረውም” እንዲል ጌታ ፭
ሺህ ከ፭፻ ዘመን በግብርናተ ዲያብሎስ ያዝን ይተክዝ የነበረ አዳምን ነጻ
ያደርገው (ያድነው) ዘንድ ወደደ፡፡ ምድራዊ ንጉሥ የተጣላውን አሽከር
“ሰናፊልህን (ልብስህን) አትታጠቅ፤ እንዲህ ካለ ቦታም አትውጣ” ብሎ ወስኖ
ያግዘዋል፡፡ በታረቀው ጊዜ ግን ርስቱን፣ ጉልበቱን፣ ቤቱን፣ ንብረቱን
እንደሚመልስለት ኹሉ ንጉሠ ሰማይ ወምድር እግዚአብሔርም “ጥንቱንም
መሬት ነህና ወደ መሬት ተመለስ” /ዘፍ.፫፡፲፱/ ብሎ ፈርዶበት የነበረ አዳምን
ይቅር ብሎ ወደ ቀደመ ቦታው ወደ ገነት፣ ወደ ቀደመ ክብሩ ወደ ልጅነት
ይመልሰው ዘንድ ወደደ /ሉቃ.፳፫፡፵፫/፡፡
# ሊቁ (ቅዱስ ኤፍሬም) በኦሪ. ዘፍ ፫፥፱ ያለውን ኃይለ ቃል ሲተረጕምም እንዲህ
ይላል፡- “ቸር ወዳጅ የኾነው እግዚአብሔር አዳምና ሔዋን ወዲያው እንደተሳሳቱ
ፍርዱን አላስተላለፈባቸውም፤ ታገሣቸው እንጂ፡፡ ይኸውም ምኅረት ቸርነቱን
ይለምኑት ዘንድ ነው፡፡ እነርሱ ግን አልለመኑትም፡፡ እግዚአብሔርም ምንም
ሳይናገራቸው በገነት ውስጥ በእግር እንደሚመላለስ ሰው ኾኖ በድምፅ ብቻ
መጥራቱን ቀጠለ፡፡ አዳምና ሔዋን ግን አሁንም አልመለስ አሉ፡፡ በመጨረሻም
አምላክ ድምፁን ማሰማት ጀመር፡፡ ‘አዳምን ወዴት ነህ?’ ይላቸው ጀመር፡፡
አስቀድሞ በእግር እንደሚመላለስ ሰው ኾኖ በድምፅ ብቻ መጥራቱ መንገድ
ጠራጊው ዮሐንስን እንደሚልክላቸው፣ ቀጥሎ ድምፅ አሰምቶ ወዴት ነህ ብሎ
መፈለጉም ወልደ እግዚአብሔር ራሱ በተዋሕዶ ፍጹም ሰው ኾኖ ሊያድናቸው
እንደ ፈቀደ ያጠይቃል” ይላል /St. Ephrem the Syrian, Commentary on
Genesis/፡፡
# ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅም ኦሪት ዘልደትን በተረጐመበት በ፲፯ኛው ድርሳኑ
ላይ፡- “በዚህ ንግግሩ የእግዚአብሔር ከአእምሮ የሚያልፈውን ፍቅሩን
እንመለከታለን፡፡ አንድ አባት ልጁ የማይረባውን ነገር በማድረግ ከክብሩ
ቢዋረድም አባቱ እጅግ እንዲወደውና ወደ ቀደመ ክብሩ ይመልሰው ዘንድ
እንዲደክም፤ እግዚአብሔርም ከሰው ልጆች ጋር ይህን የመሰለ ፍቅር ሲያሳይ
እናስተውላለን፡፡ አንድ ሐኪም ወደ ታማሚው አልጋ ጠጋ ብሎ በሽተኛውን
እንዲጠይቀውና አስፈላጊውን ኹሉ እንደሚያደርግለት፣ ሰው ወዳጁ
እግዚአብሔርም ወደ አዳም ጠጋ ብሎ ሲያነጋግረው እንመለከታለን” ይላል፡፡
ዳግመኛም # በሌላ አንቀጽ “አዳም ሆይ ወዴት ነህ” ማለቱ፣ ለአቅርቦት መኾኑን
ሲገልጥ፡- “አዳም ሆይ! ምን ኾንክብኝ? በመልካም ቦታ አስቀምጬህ ነበር፤
አሁን ግን ቦታህ ተለወጠብኝ፡፡ ብርሃን ተጐናጽፈህ ነበር፤ አሁን ግን ጨለማ
ውስጥ አይሃለሁ፡፡ ልጄ! ወዴት ነህ? ይህ ኹሉ እንደምን ደረሰብህ? በአንተ
ውስጥ ያኖርኩት መልኬ ማን አበላሸብኝ? በዚህ ያህል ፍጥነት የጸጋ ልብስህን
ገፎ የጽልመት ልብስ ያከናነበህ ማን ነው? ውዴ! ባለጸጋ አድርጌ ፈጥሬህ
አልነበረምን? ታድያ አሁን ድኽነት ውስጥ የከተተህ ማን ነው? ያን የግርማ
ልብስህን ሰርቆ ዕራቆትህ ትኾን ዘንድ ያደረገህ ማን ነው? እኮ የጸጋ ልብስህን
እንድታጣ ያደረገህ ማን ነው? ይህን የመሰለ ቅጽበታዊ መለወጥ ከወዴት
መጣብህ? የከበረ ዕንቁህን እንድትጥል ያደረገህ ምን ቢገጥምህ ነው?
አክብሮ በተወደደ ቦታ ካስቀመጠህና ኹል ጊዜ በስስት ዐይን ሲያነጋግርህ
ከነበረው አምላክህ ተደብቀህ እንድትሸሸግ ያደረገህ ምንድነው? ማንም
የወቀሰህ ሳይኖር፣ እንዲህ እንዲህ አድርገህ በድለሃል ብሎ የመሰከረብህ
ሳይኖር ይህን ያህል በፍርሐት መናጥ ከወዴት አገኘህ?” ይላል /Daily
Readings of St. John Chrysostom/፡፡
# ጽንዕት በድንግልና እመቤታችን ሆይ! ፭ ሺሕ ከ፭፻ ዘመን በግብርናተ
ዲያብሎስ የነበረ አዳምን ነፃ ካደረገው ልጅሽ ጸጋውን ክብሩን እንዳይነሣን
ለምኝልን፡፡ #“ቅድስት” ማለቱ ንጽሕት፣ ጽንዕት፣ ክብርት ልዩ ሲል ነው፡፡
ይኸውም፡-
· ሌሎች ሴቶች ከነቢብ ከገቢር ቢነጹ ከሐልዮ አይነጹም፡፡ እሷ ግን የዕንቆራው
# ኤጲስ ቆጶስ ቅዱስ ቴዎዶጦስ “ወኢረኩሰት በምንትኒ እምዘፈጠራ ድንግል
በሕሊናሃ ወድንግል በሥጋሃ- ከፈጠራት ጀምሮ በምንም በምን (በሕሊናዋም
በሥጋዋም) ከድንግልናዋ አልተለወጠችም” /ሃይ.አበ.፶፫፡፳፪/ እንዲል ከነቢብ፣
ከገቢር፣ ከሐልዮ ኃጢአት ንጽሕት ናትና፡፡
· # ጽንዕትም አለ፡፡ ሌሎች ሴቶች ቢጸኑ ለጊዜው ነው፤ ኋላ ተፈትሖ አለባቸው፡፡
እሷ ግን ቅድመ ፀኒስ ጊዜ ፀኒስ፤ ቅድመ ወሊድ፣ ጊዜ ወሊድ፣ ድኅረ ወሊድ
ጽንዕት (ወትረ ድንግል) ናትና፡፡
· # ክብርትም አለ፡፡ ሌሎችን ሴቶች ብናከብቸው ጻድቃንን፣ ሰማዕታትን፣
ጳጳሳትን፣ ሊቃውንትን ወለዱ ብለን ነው፡፡ እሷን ግን ወላዲተ አምላክ
ወልዳልናለች ብለን ነውና፡፡
· # ልዩም አለ፡፡ እናትነትን ከድንግልና፣ አገልጋይነትን ከእናትነት፣ ወተትን
ከድንግልና ጋር አስተባብራ የተገኘች፤ በድንግልናም እያለች ከጡቶቿ ወተት
ተገኝተው በዝናም አብቅሎ በፀሐይ አብስሎ የሚመግብ መጋቤ ፍጥረታት
አምላክን የወለደች፤ እሳታውያን የሚኾኑ ኪሩቤል ሱራፌልም በፍርሐት በረዐድ
ኹነው ዙፋኑን የሚሸከሙት እሳተ መለኮት ጌታን ፱ ወር ከ፭ ቀን በማሕፀኗ
የተሸከመች፣ በክንዷ የታቀፈች፣ በዠርባዋ ያዘለች ከእመቤታችን በቀር ሌላ ሴት
የለችምና፡፡
#“ለምኚልን” ሲልም ልክ በዚህ ምድር እንደነበረው ዓይነት ልመና ከዚያ በኋላ
ኖሮባት አይደለም፡፡ ስንኳን በሷና በሌሎችም የለባቸውም፡፡ በቀደመ ልመናዋ
የምታስምር ስለ ኾነ እንዲህ አለ እንጂ፡፡ ይኸውም በቃል ኪዳኗ ማለት ነው፡፡
አንድም በቁሙ ይተረጐማል፡፡ ማዘከር (ማሳሰብ) አለና፡፡
#“ሰአሊ ለነ ቅድስት” የሚለው ቅዱስ ኤፍሬም የተናገረው አይደለም፡፡ “ታድያ
ይህን የጨመረው ማን ነው?” በሚለው ላይም ኹለት ዓይነት አመለካከለት አለ፡፡
“ቅዱስ ያሬድ ለዜማ መከፈያ ተናግሮታል” የሚሉ አሉ፤ “የኋላ ሊቃውንት
ተናግረውታል” የሚሉም አሉ፡፡

👉እርሶ ያወቁትን እውቀት ሌሎች ያውቁ ዘንድ ቻናላችንን ሼር በማድረግ ጓደኛዎን ይጋብዙ

ቻናላችንን ይቀላቀሉ
👇👇👇👇👇 👇👇👇👇👇
@ethiopianissm @ethiopianissm
@ethiopianissm @ethiopianissm
@ethiopianissm @ethiopianissm
#የማክሰኞ_ውዳሴ_ማርያም_ትርጓሜ

ለምስጋና ኹለተኛ፣ ለፍጥረት ሦስተኛ ቀን በሚኾን በዚህ ቀንም እመቤታችን ትመጣለች፤ የብርሃን ድባብ ይዘረጋል፤ የብርሃን ምንጻፍ ይነጸፋል፡፡ ከዚያ ላይ ኾናም፡- “ሰላም ለከ ኦ ፍቁርየ ኤፍሬም” ትለዋለች፡፡ እርሱም ታጥቆ እጅ ነሥቶ ይቆማል፡፡ ክርክር በዕለተ ሰኑይ አልቋልና “ባርክኒ” ብሎ ተባርኮ “አክሊለ ምክሕነ” ብሎ ምስጋናውን ይጀምራል፡፡

፩. ዳዊት ምንም ንጉሠ ነገሥት ቢባል የመመኪያችንን ዘውድ ማምጣት አልተቻለውም /፩ኛሳሙ.፲፮፥፲፫/፡፡ ኢያሱ ምንም የስሙ ትርጓሜ መድኃኒት ቢኾንም የደኅንነታችን መጀመሪያ መኾን አልተቻለውም፡፡ ኤልያስም ምንም ንጹሕ፣ ድንግል ቢኾንም የንጽሕናችን መሠረት መኾን አልተቻለውም፡፡ የመመኪያችን ዘውድ፣ የደኅንነታችን መጀመሪያ፣ የንጽሕናችን መሠረት ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው፡፡ የመመኪያችን ዘውድ “አክሊለ ሰማዕት” የሚባል ጌታችን ነው፡፡ የደኅንነታችን መጀመርያ “ጥንተ ሕይወት” የሚባል ጌታችን ነው፡፡ የንጽሕናችን መጀመርያም ኹሉ በእጁ የተጨበጠ፣ ዓለምንም በመዳፉ የያዘ፤ በጠፈር ላይ የሚቀመጥ ፣ ዳግመኛም መሠረቱን ከታች የሚሸከም “መሠረተ ዓለም” የሚባል ጌታችን ነው /ቅዳ.ማር. ቁ.፶፩/፡፡ እርሱም አካላዊ ቃልን በወለደችልን በድንግል ማርያም ተገኘልን፡፡ እኛን ስለማዳን ሰው ኾነ፤ ሰውም ከኾነ በኋላ ግን ፍጹም አምላክ ነው፡፡ ማኅተመ ድንግልናዋ ሳይለወጥ እንደ ወለደችው ኹሉ እርሱም አምላክነቱ ሳይለወጥ ሰው ኾነ፡፡ እርሷ “ድንግል ወእም (ድንግልም እናትም)” ስትባል እንደምትኖር ኹሉ እርሱም “አምላክ ወሰብእ (ፍጹም አምላክ ፍጹም ሰው)” ሲባል ይኖራል /ሃይ.አበ.፷፯፡፯/፡፡ ተፈትሖ ሳያገኛት (ማኅተመ ድንግልናዋ ሳይለወጥ) እንደምን እንደወለደችው ግን የማይመረመር አንድም ሊነገር የማይችል፣ ከኅሊናት ኹሉ የሚያልፍ ድንቅ ነው፡፡
*በማይመረመር ግብር ከወለድሽው ልጅሽ ጽንዕት በድንግልና እመቤታችን ጸጋውን ክብሩን እንዳይነሣን ለምኚልን፡፡

፪. “ቃል ሥጋ ኾነ” እንዲል በእርሱ ፈቃድ /ዮሐ.፩፡፲፬/፣ “ተቀዳሚ ተከታይ የሌለው ልጁን እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወዷልና” እንዲል በአባቱ ፈቃድ /ዮሐ.፫፡፲፮/፣ “በመንፈስ ቅዱስ በኀይልም እንደ ቀባው” እንዲልም /ሐዋ.፲፡፴፰/ በመንፈስ ቅዱስ ፈቃድ ሰው ኾኖ አዳነን፡፡ ሊቁ እንዲህ ማለቱ “ወልድ ያለ ፈቃዱ ሰው ኾነ” የሚሉ መናፍቃን ስላሉ ነው፡፡ ሌሎች ሊቃውንትም፡- “የእግዚአብሔር ልጅ ያለ ፈቃዱ ሰው እንደ ኾነ የሚያምን፤ የሚያስተምር፤ ወይም የአብ ፈቃድ ሌላ ነው፤ የወልድ ፈቃድ ሌላ ነው፤ የመንፈስ ቅዱስም ፈቃድ ሌላ ነው የሚል ቢኖር፤ ፈቃዳቸው አንድ፤ መንግሥታቸውም አንድ እንደኾነ የማያምን ሰው ቢኖር ውጉዝ ይኹን” ብለው አስተምረዋል /ሃይ.አበ.፻፳፫፡፪/፡፡

በድንጋሌ ሥጋ በድንጋሌ ነፍስ ፍጽምት የምትኾኚ እመቤታችን ሆይ! በድንግልና ጸንተሽ ብትገኚ ላንቺ የተሰጠሸ ጸጋ ፍጹም ነው፡፡ እግዚአብሔር ከሥጋሽ ሥጋ ከነፍስሽ ነፍስ ነሥቶ ካንቺ ጋራ አንድ ባሕርይ ቢኾን አንድም በጸጋ ቢያድርብሽ ባለሟልነትን አግኝተሸልና ለአንቺ የተሰጠ ክብር ፍጹም ነው፡፡ ይህ ከቃላት በላይ የሚያልፈው ባለሟልነቷ ቅዱስ ባስልዮስ ከሌሎች ቅዱሳን ጋር እያነጻጻረ ሲያብራራው፡- “የዚህ ዓለም ነገር ኹሉ አይመጥናትምና የሚመጥናትን ምን ዓይነት ምስጋና እናቅርብላት? ቅዱስ ጳውሎስ ስለ ቅዱሳን ሲናገር ዓለም አልተገባቸውም /ዕብ.፲፩፡፴፰/ ካላቸው ከከዋክብት በላይ ኾና እንደምታበራው ፀሐይ ለኾነችው ለአምላክ እናትማ ምን ልንል እንችል ይኾን?... ምን ምሥጢር እንደተከናወነ ተመልከት፤ ኅሊናን አእምሮን የሚያልፍ ነገር እንደኾነም አስተውል፡፡ ታድያ የአምላክ እናት ታላቅነት እንደምን ኹሉም ሰው አይናገር? ማንስ ነው ከቅዱሳን ኹሉ በላይ እንደኾነች ያላስተዋለ? እግዚአብሔር ለአገልጋዮቹ የሚልቅ ጸጋን ከሰጠና የሚነኩት ኹሉ ሰው ከበሽታው ከተፈወሰ፣ ጥላቸው ያረፈበት ተአምር ከተፈጸመለት፣ ጴጥሮስ በጥላው ካዳነ /ሐዋ.፭፡፲፭/፣ የጳውሎስ የልብሱ ዕራፊ መናፍስትን ካወጣ /ሐዋ.፲፱፡፲፩/ ለእናቱማ ምን ዐይነት ሥልጣንና ኀይል ተሰጥቷት ይኾን? በምን ዓይነትስ ሥጦታ አስጊጧት ይኾን? ጴጥሮስ፡- ክርስቶስ አንተ የእግዚአብሔር ልጅ ነህ ስላለው ብፁዕ ነህ ከተባለና የመንግሥተ ሰማያት ቁልፍ ከተሰጠው /ማቴ.፲፮፡፲፮-፲፱/ እርሷማ ከኹሉም ይልቅ እንዴት ብፅዕት አትኾን? /ሉቃ.፩፡፵፭/ ጳውሎስ ታላቅ ክብር ያለውን የክርስቶስን ስም በመሸከሙ ምርጥ ዕቃ ከተባለ /ሐዋ.፱፡፲፭/ የአምላክ እናትማ የምእመናን ምግብ የኾነ መናውን ሳይኾን የሕይወት ሰማያዊ እንጀራን ያስገኘች እርሷ ምን ዓይነት ልዩ ዕቃ ትኾን? … ነገር ግን ስለ እርሷ ብዙ እናገራለሁ ብዬ ስለ ክብሯ ጥቂት በመናገር ራሴን በኀፍረት ውስጥ እንዳልጨምር እፈራለኁ፡፡ ስለዚህ ከአሁን ወዲህ የንግግሬን መልሕቅ ስቤ በዝምታ ወደቤ ላይ ማረፍን መርጫለሁ” ይላል /መጋቤ ሐዲስ ሮዳስ ታደሰ፣ ነገረ ማርያም በሐዲስ ኪዳን፣ ገጽ ፺-፺፩ ይመልከቱ/፡፡

ከምድር እስከ ሰማይ ደርሳ፣ በላይዋ ዙፋን ተነጽፎባት በዚያ ላይ ንጉሥ ተቀምጦባት፣ መላእክት ሲወጡባት ሲወርዱባት ያዕቆብ በፍኖተ ሎዛ ያያት የወርቅ መሰላል አንቺ ነሽ /ዘፍ.፳፰፡፲፰-፲፱/፡፡ መተርጕማኑ ይህ ምን ማለት እንደኾነ ሲያብራሩ፡- “ከምድር እስከ ሰማይ መድረሷ የልዕልናዋ፣ በላይዋ ላይ ዙፋን ተነጽፎባት ንጉሥም ተቀምጦባት ማየቱ ፱ ወር ከ፭ ቀን በማኅፀኗ ለመሸከሟ፣ መላእክት ሲወጡባት ሲወርዱባት ማየቱ ደግሞ ጌታችን ከእመቤታችን ሰው ከመኾኑ አስቀድሞ ሰው የጸለየውን ጸሎት ያቀረበውን መሥዋዕት ለማሳረግ አይወጡም አይወርዱም ነበር፤ ጌታችን ከእመቤታችን ሰው ከኾነ በኋላ ግን ለተልእኮ የሚወጡ የሚወርዱ ኾነዋልና ሲል ነው” ይላሉ /ሉቃ.፪፡፲፬፣ ሐዋ.፲፡፫-፬፣ የኦሪት ዘልደትን ትርጓሜ ይመልከቱ/፡፡

*ያዕቆብ በፍኖተ ሎዛ በአምሳለ ንጉሥ ካየው ልጅሽ ጽንዕት በድንግልና እመቤታችን ጸጋውን ክብሩን እንዳይነሣን ለምኚልን፡፡
✤✞✤
ማርያምስ ዕጣን ናት።
✤✞✤
"ዕጣን ይእቲ ማርያም፤ ማርያምስ ዕጣን ናት" ከመጽሐፈ ቅዳሴ የተወሰደ ቃል
ነው (ሥርዓተ ቅዳሴ)።
እጣን የክህነትን ሥራ ይጠይቃልና፤ ከእጣኑ በፊት እግዚአብሔር ለሙሴ
የምስክሩን ድንኳን ያገለግሉ ዘንድ ለአሮን እና ለልጆቹ ክህነት ሰጣቸው። ዘጸ.
28:41
ከዚያም ለእግዚአብሔር የሚያስፈልገውን መስዋዕት ምን እንደ ሆነ ሲዘረዝር
ዕጣን እንዲያጥኑለት አዘዘ። 1.ዜና 6:49 ካህናቱ ምን እንዲለብሱም ሥርዓት
ሰራላቸው። ዘጸ. ም 30 በማእጠንት ግዜም ልብሰ ተክህኖ ይለበሳል።
ልብሰ ተክህኖ ለካሕናት ልዩ ልዩ አገልግሎት ዘርፍና ማዕረግ የሚያሳይ ነው።
ከሥር ቀሚስ፤ ከቀሚሱ ከላይ ትልቅ ቀይ ኤፉድ(እኛ የቅዳሴ ካባ የምንለው)
በሁለቱ ትከሻ የሚወርድ እንቁ ያለበት የአስራ ሁለቱ የእስራኤል ልጆች ስም
የተጻፈበት ኪስ አለው። በቤተ ክርስቲያንም ይህንንው ተከትለን በጥቂቲ ማሻሻያ
ሆኖ በሁሉም ማለትም በምዕራብም በምስራቁም ኦርቶዶክሶች ይህው ልብሰ
ተክህኖ ይለበሳል።
ሕዝቡ ወደ ካህናቱ የተለያየ መስዋዕት ያመጡ ነበር። ይህውም እንደ
ኃጢአታቸውና እንደ ኑሮ ደረጀቸው ይለያያል። ርግብ የድኃ መስዋዕት መሆኑን
ልብ ይበሉ። በብሉይ ይቀርብ የነበረው መስዋዕት ለግል ኃጢአታቸው ሥርየት
ሲሆን አንድ ግዜ በዓመት የማስተሰርያ መስዋዕት ለሁሉም ኅጢአት ማስተሰረያ
በግ በሊቀ ካህናቱ እጅ በቤተ መቅደስ፤ በመሰዊያው ላይ ይሰዋል። እንግዲህ
ይህ ሁሉ መስዋዕቱም ሆነ ሥርዓቱ በሐዲስ ኪዳን አገልግሎትና መስዋዕት
ተተክቷል።
ዕጣን ከግንድ ላይ መንጭቶ በመድረቅ የሚገኝ በጎ መዓዛ ያለው ሲሆን
ለተለያየ አገልግሎት ይውላል። ለመድኅኒት፤ ለመዓዛ ….። በቤተ ክርስቲያን
በብሉይ ኪዳን አገልግሎት ይውል የነበረው እጣን፤ በሐዲስ ኪዳን እጣኑ ይዘቱን
ሳይቀየር የእጣኑ ሚስጢር አማናዊውን ትርጉም ይዞ ለሥርዓተ አምልኮ (ቅዳሴ)
እንጠቀምበታለን። በቤተ ክርስቲያን የአምልኮ ማዕከል the center of
worship የምንለው ሥጋውና ደሙን (ቅዳሴ)ነው።
"ዕጣን"
በሐዲስ ኪዳን የዕጣን ታሪክ የሚጀምረው ከጌታ ልደት ልደት ማግስት ሲሆን
ሶስቱ ጠቢባን ሰዎች ሰብአ ሰገል (ማንቱሲማር፤ በዲዳስፋ፤ ሜልኩ) ይባላሉ።
እጅግ የብዙ ብዙ ሰራዊትም አብረዋቸው እንደነበርም ስማቸውን የጠቀሰልን
የቅዱስ ማቴዎስ ትርጓሜያችን ይነግረናል። ለመባዕ ካመጡለት ሥጦታ አንዱ
ዕጣን ነው። ይህም ቀድሞ እናጥንላቸው እንሰግድልቸው የነበሩ አማልእክት
ጣኦታት ፍጡራን ኋላም ኅላፍያን ናቸው። አንተ ግን ቀድሞም ያልተፈጠርክ፡
በኋላም የማታልፍ ነህ። እጣን ምኡዝ (የሚሸ) ነው፤ አንተም ምኡዘ ባኅርይ ነህ
ማለታቸው ነው። በአንተም የሚያምኑ ምዕመናን በምግባር በሃይማኖት የታነጹ
የሚሸቱ ናቸው። እጣን ከሩቅ የሚሸት ነውና ምዕመናንም የመምጣትህን
መንግስተ ሰማያትን ተስፋ እያደረጉ መኖራቸውንም ጠቋሚ ምስጢር ነው።
እጣን የጸሎታችንም ማረግ እግዚአብሔር ጸሎታችንን በበጎ መዓዛ መቀበሉንም
ያሳየናል። እስራኤልን ደመና እንደ ከበባቸው የእጣኑ ጢስ የእግዚአብሔርም
ምሕረት ያሳየናል። ወደ ቤተክርስቲያን ገና ስንገባ ከውጭው ካለው ነባራዊ
ሁሌታ የሚለየው አንዱ የአየሩ መዓዛ ነው። የምንተነፍሰው አየር ተመሳሳይ
ኦክስጅን (O2) ቢሆንም የቤተ ክርስቲያን ውስጥ አየር ግን በእጣን መዓዛ
የታጀበ የታሸ ነው። ይህ ቤተ ክርስቲያን ከዓለም የተለየች መንፈሳዊት ዓለም
መሆኗን ያሳየናል።
እጣን ከምንናቀርበው መስዋዕት መካከል ከመሆኑም ባሻገር እንዳተራው ሳይሆን
ራሱን የቻለ የእጣን ጸሎት (ጸሎተ እጣን) አለው። በየእለቱም ሰፊ ጸሎት እለው።
ዕጣኑም የተመረጠ ነው። ግብስብሱ ሁሉ የሚቀርብ አይደለም። (በክፈለ ሀገር
በዲቁና እያለን ቅዳሴ ከመግባታችን በፊት በፍልሰታ ነጭ ነጩን ኮረት ለቅመን
እናዘጋጅ ነበር። ዛሬም ይህንንው እመክራለሁ ለዲያቆናቱ)
በቅዳሴም እንድንጠቀም የታዘዘው የእጣን መጠን አምስት ቆቆር ሲሆን
የምንጠቀምባቸው የቅዳሴ ቦታዎችም ተለይተዋል። ብዙም ስለማይጤሱ እነሱን
ከጨመርን በኋላ እንደ አጃቢ ጠቀም ያለ ቁጥር ያለው እጣን መጨመር
የተለመደ ነው።
ቅዳሴያችንን ስናይ እመቤታችንን እጣን ነሽ ይላታል። "ዕጣን ይእቲ ማርያም
እጣን ውእቱ እስመ ዘውስተ ከርሳ ዘይትሚዓዝ እምኩሉ ዕጣን ዘወለደቶ መጽአ
ወአድኅነነ። ማርያምስ ዕጣን ናት፤ ዕጣን እርሱ ነው በማሕጸንዋ ያደረው፤
ከእጣን ሁሉ የሚሸት ነውና የወለደችው መጥቶ አዳነን። ይላል።
እጣኑ መዓዛ አለው ዕጣኑና መዓዛው አይለያዩም። እርሷ ዕጣን ናት፤ ልጅዋ
የዕጣኑ መዓዛ ነው። የሰው ልጅ ክፉ ሽታ የራቀባት እጣን፡ ምክንያተ ድኂን
ድንግል ማርያም ናት። መርገመ ሥጋ መርገመ ነፍስ የራቀባት፤ የሰው ልጅ
ድኅነት የተዋጀባት እጣናችን እመቤታችን ናት። የዛሬ የማንነታችን መዓዛም
እርስዋ ናት።ይቀጥልና፦
ጌታችንን ዕጣን ይለዋል። " አንተ ውእቱ ዕጣን ኦ መድኅኒነ እስመ መጻእከ
ወአድኅንከነ ተሳሀለነ" መድኅኒታችን ሆይ ዕጣን አነተ ነህ መጥተህ
አድነህናልና፤ ይቅር በለን።
ያለ እርሱ የሰው ድኅነት አልሆነም። ኃጢአትን ይቅር የሚል እርሱ ብቻ ነው።
የሰውን ልጅ ከወደቀበት በሞቱ አነሳው። ከፍቅር የተነሳ ሞተለት። ለሕይወታችን
መልካም መዓዛ ሆነን።
በስተ መጨረሻም ጸሎታችንን በመልአኩ እጅ ቅዳሴያችን፡ሰአታቱ ካለቀ ኋላ
ከእጣን ጋር ያሳርገዋል። “ሌላም መልአክ መጣና የወርቅ ጥና ይዞ በመሰዊያው
አጠገብ ቆመ፤ በዙፋኑም ፊት ባለው በወርቅ መሰዊያ ላይ ለቅዱሳን ሁሉ ጸሎት
እንዲጨምረው ብዙ ዕጣን ተሰጠው” ራእ. 8:3::
መ/ር ንዋይ ካሳሁን

👉እርሶ ያወቁትን እውቀት ሌሎች ያውቁ ዘንድ ቻናላችንን ሼር በማድረግ ጓደኛዎን ይጋብዙ

ቻናላችንን ይቀላቀሉ
👇👇👇👇👇 👇👇👇👇👇
@ethiopianissm @ethiopianissm
@ethiopianissm @ethiopianissm
@ethiopianissm @ethiopianissm
ቤተ ክርስቲያን ታመሰግንሻለች!!!
"ያዘነች ስትሆን በልጅሽ በወዳጅሽ ትንሣኤ የተጽናናችው፡፡ የተዋረደች ስትሆን
በድንግልናሽ ቡቃያ መውጣት ከፍ ከፍ ያለችው ቅድስት ቤተ ክርስቲያን
ታመሰግንሻለች፡፡ በዕለተ ዓርብ ከልጅሽ ቀኝ በፈሰሰው ውሀ ተጠምቃ
የውግታቱን ደም ተቀብታ ቅድስት ቤተክርስቲያን ታመሰግንሻለች። የልዑል
እግዚአብሔር በግ የተባለ ልጅሽ ዐማኑኤልየተሞሸረባት መርዓዊ ሰማያዊ
የተባለባት ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ታመሰግንሻለች"
አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ
እንኳን ለእናታችን፣ ለእመቤታችን ለበዓለ ጽንሰቷ በሰላም አደረሰን!
ዲያቆን አቤል ካሳሁን

👉እርሶ ያወቁትን እውቀት ሌሎች ያውቁ ዘንድ ቻናላችንን ሼር በማድረግ ጓደኛዎን ይጋብዙ

ቻናላችንን ይቀላቀሉ
👇👇👇👇👇 👇👇👇👇👇
@ethiopianissm @ethiopianissm
@ethiopianissm @ethiopianissm
@ethiopianissm @ethiopianissm
++ ዛሬ ነገ ነው? ++

‘‘አባዬ ዛሬ ነገ ነው?’’ አለ አቡሽ አባቱን ከተኛበት እየቀሰቀሰ

አባት እየተበሳጨ ‘ምንድን ነው የምትለኝ?’ አለ፡፡
ልጅ ‘ዛሬ ነገ ነው ወይ?’
አባት እንቅልፉ ስላልቀቀው ‘ሂድና እናትህን ጠይቃት በቃ ልተኛበት’ አለና እየተበሳጨ ፊቱን ሸፈነ፡፡

ልጅ ወደ እናት ሔዶ ያንኑ ጥያቄ ደገመላት
‘’እማዬ ዛሬ ነገ ነው?’’ እናት ፈገግ አለች
‘ምን ማለት ነው ደግሞ ዛሬ ነገ ነው? ማለት?’’ አለች የልጅዋን የተጋለጠ ደረት እየሸፈነች
‘ትናንት አስተማሪያችን ‘ነገ ትምህርት የለም’ ብላን ነበር ፤ ዛሬ ነገ ነው?’’
እናት ‘እ እ አዎ ልክ ነህ ዛሬ ነገ ነው’ አለች እየሳቀች፡፡

ይህ ለሕጻኑ ጥያቄ የተሰጠ መልስ ለእኛም ሳያስፈልገን አይቀርም፡፡ ብዙዎቻችን የምንኖረው ለነገ ነው፡፡ ለነገ እንማራለን ፣ ለነገ እንሠራለን ፣ ለነገ እንገነባለን፡፡ የተፈጠርነው ለዘላለማዊነት ነውና እንደምንኖር አስበን ማቀዳችን ባልከፋ፡፡ ነገር ግን ላላየነው ነገ ስናስብ ያየናትን ዛሬ እንዘነጋታለን፡፡ ለነገ ደመና የዛሬን ፀሐይ እንገፋታለን፡፡ እንዳቀድን እንዳለምን ለመኖር ስንዘጋጅ እንሞታለን፡፡ መጽሐፍ ‘’ነገ ወደዚህ ከተማ እንሄዳለን በዚያም ዓመት እንኖራለን እንነግድማለን እናተርፍማለን የምትሉ እናንተ፥ ተመልከቱ፥ ነገ የሚሆነውን አታውቁምና’ ‘ነገ ለራሱ ያስባልና ለነገ አትጨነቁ! ይላል፡፡ /ያዕ 4፡15 ፤ ማቴ 6፡34/

ሰይጣን ከሚጠቀምበት ሰውን ማጥቂያ መሣሪያም አንዱ ‘ነገ’ በሚል ቃል ማዘናጋት ነው፡፡ ነገ እማራለሁ ፣ ነገ እሔዳለሁ ፣ ነገ የታመመ እጠይቃለሁ ፣ ነገ ንስሓ እገባለሁ ፣ ነገ ወደ እግዚአብሔር እመለሳለሁ ፣ ነገ ይሄንን መልካም ነገር እሠራለሁ ነገ ነገ ነገ
ፈርኦን የሚባለው ጨካኝ ንጉሥ በመቅሠፍት ጓጉንቸር ተወርሮ ነበር፡፡ በመጨረሻም እስራኤልን እለቃለሁ ሲል ሙሴ ፦ ጓጉንቸሮቹ ከቤትህ እንዲጠፉ መቼ ልጸልይልህ? አለው፡፡ ፈርኦንም ፦ ነገ አለ፡፡

እንግዲህ ዛሬን ከጓጉንቸሮች ጋር ማደር ፈልጓል ማለት ነው፡፡ ወዳጄ በሕይወትህ ውስጥ ጓጉንቸሮች ምንድን ናቸው? ምን ዓይነት ክፉ አመል አለብህ ፣ ምን ዕረፍት ያሳጣህ ፣ ሰላም የነሳህ ነገር አለ? አልላቀቅ ያለህ ሱስ ፣ አልስተካከል ያለህ ድክመት ፣ አልድን ያለህ ቁስል ምንድን ነው? እርሱን መቼ ትላቀቀዋለህ? መቼ መዳን ትሻለህ? ነገ ካልከኝ ፈርኦን መሆንህ ነው? ‘አቤቱ አሁን አድን’ ካልክ ደግሞ እንደ ዳዊት ትሰማለህ

ነገ ይህንን ሱስ እተዋለሁ ፣ ነገ ይህን ልማድ እላቀቃለሁ ፣ ነገ ይህን መልካም ነገር አደርጋለሁ የሚል ቀጠሮ ሠርቶ አያውቅም፡፡ ነገ እንላለን እንጂ የሚገርመው በማግሥቱም መልሳችን ነገ ነው፡፡ ‘ዱቤ ዛሬ የለም ነገ ነው’ እንደሚለው የብልጥ ባለሱቅ ማስታወቂያ ነገ ስንሔድ ነገ እየተባለ የምንፈልገውን ሳንሠራ የማንፈልገውን እየሠራን እንኖራለን፡፡ ወዳጄ ነገ የአንተ አይደለችም ‘የተወደደው ሰዓት አሁን ነው’ መኖርህን ሳታውቅ ቀጠሮ አትሥጥ፡፡ ኃይልህ በአሁን ላይ ብቻ ነው፡፡ ማንም ሊሠራባት የማይችላት ሌሊት ሳትመጣ አሁንን ተጠቀምባት፡፡

አሁኑኑ ተነሥ ያሰብከውን መልካም ነገር ለመሥራት ፣ ክፉውን ነገር ለመተው ነገ አደርገዋለሁ አትበል
ትናንት ኅሊናህ ሲጠይቅህ ‘ነገ አደርገዋለሁ’ ብለህ ነበር ፤ ዛሬም ‘ነገ’ አትበል ምክንያቱም ሕጻኑ እንዳለው ‘ዛሬ ነገ ነው’

ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ

👉እርሶ ያወቁትን እውቀት ሌሎች ያውቁ ዘንድ ቻናላችንን ሼር በማድረግ ጓደኛዎን ይጋብዙ

ቻናላችንን ይቀላቀሉ
👇👇👇👇👇 👇👇👇👇👇
@ethiopianissm @ethiopianissm
@ethiopianissm @ethiopianissm
@ethiopianissm @ethiopianissm
እምየ ኢትዮጵያ
ቅዠት ና ህልሜ
የጠላትሽ እድሜ
ይጠር እንደ ጳግሜ።

በላይ በቀለ ወያ

👇👇👇👇👇
@ethiopianissm
@ethiopianissm
@ethiopianissm
ሰላም ውድ የኢትዮጵ ቤተሰቦች እንዴት ናችሁ?
እንደምታውቁት የምንፅፋቸው ፅሁፎች ብዙ አንባብያን ጋ አይደርሱም። እኛም ከደከምን አይቀር ብዙ ሰወች አንብበው ስለ ሀገራችችን ጥንታዊ ስልጣኔ ያውቁ ዘንድ ይሄን ፅሁፍ 1ሰው ለ10 ሰወች forward ያድርግ ከዛም join ማረጋቸውን ያረጋግጥ ፤ ይህን ለማድረግ ሶሥት ደቂቃ በቂ ነው። እናም ይህን ዘመቻ በአንድ ቀን ውስጥ ማድረግ ከቻልን የአባሎቻችን ቁጥር መጨመር እንችላለን

ሁላችንም ይሄን ማረግ አያቅተንም። የአንባቢዎች መብዛት እኛንም ያበረታናል።

፨፨፨ መልካም ዘመቻ፨፨፨

👇👇👇👇👇
@ethiopianissm
@ethiopianissm
@ethiopianissm
@ethiopianissm
#የሰኞ_ውዳሴ_ማርያም_ትርጓሜ

ሊቁ ምስጋናውን ሲቀጥል “እምቅድመ ዓለም የነበረው፣ ዓለምን አሳልፎ የሚኖረው፣ ለኩነት ሥጋ የመጣው፣ ዳግመኛም ዓለሙን ለማሳለፍ የሚመጣው አካላዊ ቃል ኢየሱስ ክርሰቶስ ካንቺ ሳይለወጥ ፍጹም ሰው ኾነ” ይላል፡፡ ይኸውም በሌላ አንቀጽ “ባሕርዩን ከፍሎ አልተዋሐደም፤ ባሕርዩንም ሕፁፅ በማድረግ ኹለተኛ እንስሳ አልኾነም፡፡ አንድ አካል አንድ ባሕርይ በመኾን ምሉ ፍጹም ሰው ነው እንጂ፡፡ የአምላክነትን የሰውነትንም ሥራ ይሠራል፤ ይህስ ባይኾን አንዱ ተለይቶ በቀረ ነበር” ካለው ጋር ተመሳሳይ ነው /ዮሐ.፩፡፩-፲፬፣ ሃይ.አበ.ዘኤፍሬም ፵፯፡፴፪/፡፡
“ተቀዳሙ ተካታይ የሌለው ወልድ ዋሕድ በሥራው ኹሉ ከነሣው ሥጋ አልተለየም፡፡” ይህም በኹለት መልኩ ይተረጐማል፡-
፩ኛ፡- “አካላዊ ቃል አንድ ግብር፣ አንድ ባሕርይ፣ አንድ አካል ነው እንጂ” ማለት ሲኾን፤
፪ኛ፡- ደግሞ “ተቀዳሙ ተካታይ የሌለው ወልድ ዋሕድ ሰውም ቢኾን ከአብ ከባሕርይ አባቱ፣ ከመንፈስ ቅዱስ ከባሕርይ ሕይወቱ አልተለየም፡፡ አካላዊ ቃል አንድ ኅብረ መልክዕ፣ አንድ ባሕርይ፣ አንድ አገዛዝ ነው እንጂ” ማለት ነው፡፡

ሰውም ቢኾን ከአብ ከባሕርይ አባቱ፣ ከመንፈስ ቅዱስ ከባሕርይ ሕይወቱ ካልተለየ ልጅሽ ጽንዕት በድንግልና እመቤታችን ጸጋውን ክብሩን እንዳነሣን ለምኝልን፡፡

ዳግማይ አዳም (ክርስቶስ) ካንቺ ባንቺ ባሕርይ ተወልዷልና የነቢያት ሀገረ ትንቢታቸው ቤተ ኀብስት እመቤታችን ሆይ! ደስ ይበልሽ፡፡ የቀደመ ሰው አዳምን ከሲዖል ወደ ገነት ከኀሣር ወደ ክብር ይመልሰው ዘንድ ካንቺ ባንቺ ባሕርይ ተወልዷልና የነቢያት ሀገረ ትንቢታቸው ቤተ ኀብስት እመቤታችን ሆይ! ደስ ይበልሽ፡፡ ከእናንተ መካከል፡- “ሊቁ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ዳግማይ አዳም ማለቱ ከቀዳማዊ አዳም ጋር የሚያመሳስለው ምን ስላለው ነው?” ብሎ የሚጠይቅ ሊኖር ይችላል፡፡ እኛም እንዲህ ብለን እንመልስለታለን፡- በቀዳማዊ አዳም ምክንያት የሰው ልጅ በሙሉ በርደተ መቃብር ላይ ርደተ ገሃነም ተፈርዶበት ነበር፤ በዳግማይ አዳም በክርስቶስ ግን የጽድቅ በር ለኹሉም ተከፍቷል፡፡ ከቀዳማዊ አዳም ጋር አብረው ዕፀ በለስን ያልበሉት ስንኳ ሞት ነግሦባቸው ይኖር ነበር፤ በዳግማይ አዳም በክርስቶስ ትሩፋት ግን የሰው ልጅ በሙሉ የድኅነት መንገድ ተሰጥቶታል፡፡ ስለዚህ ክርስቶስ ዳግማይ አዳም ሲባል በአዳም የመጣው በደል ክርስቶስ ከሰጠው ጸጋ ጋር ወይም ደግሞ በአዳም ምክንያት የመጣው ሞትና በክርስቶስ የተሰጠው ሕይወት ለማስተካከል ሳይኾን አዳም ለሚሞቱት ኹሉ አባት እንደኾነ ኹሉ ክርስቶስ ደግሞ ትንሣኤ ሕይወት ላላቸው ኹሉ አባታቸው መኾኑን ለመግለጥ ነው /St. John Chrysostom on Romans, Hom.10/፡፡ አንድም በጥንተ ተፈጥሮ ይመስሏልና፡፡
በዕፅ ምክንያት የወደቀ (ከገነት የወጣ፣ ከክብሩ የተዋረደ) አዳም ንስሐ ቢገባም፣ ጩኸቱን ሰምተው ነቢያት ካህናት ቢነሡም እንደ እርሱ ንጽሐ ጠባይዕ አድፎባቸዋልና በግዝረታቸው በመሥዋዕታቸው አዳምን ማዳን አልቻሉም /ኢሳ.፷፬፡፮/፡፡ ነገር ግን “አንሥእ ኃይለከ፤ ፈኑ እዴከ” /ኢሳ.፶፩፡፱/ ያሉትን ልመናቸውን ሰምቶ ካንቺ ባንቺ ባሕርይ ተወለደ (ሰው ኾነ)፡፡ የአዳምን ባሕርይ ባሕርይ አድርጐ “አዳም ጥንቱንም መሬት ነህ ወደ መሬትነትህ ተመለስ” ብሎ በአዳም የፈረደበትንም የሞት ፍርድ (መከራ) ተቀብሎ ያድነው ዘንድ ካንቺ ባንቺ ባሕርይ ተወልዷልና፣ የነቢያት ሀገረ ትንቢታቸው ቤተ ኀብስት እመቤታችን ሆይ! ደስ ይበልሽ፡፡ ብዙ ኃጢአት ካለች ዘንድ ጸጋ እግዚአብሔር ትበዛለች /ሮሜ.፭፡፳/፡፡ “በአንድ ሰው (አዳም) ምክንያት የገባች ኃጢአት ሕግ በተሰጣቸውና ባልተሰጣቸው ኹሉ እንዲህ ከነገሠች፣ በዳግማይ አዳም በአካላዊ ቃል በኢየሱስ ክርስቶስ የተሰጠች ጸጋማ እንዴት አብልጣ አትበዛ?” /St. John Chrysostom, Ibid/፡፡

ዳግማይ አዳም ከሚባል ልጅሽ ጽንዕት በድንግልና እመቤታችን ጸጋውን ክብሩን እንዳነሣን ለምኚልን፡፡
"ባልና ሚስት ከአንድ ወንዝ ይቀዳሉን እንጂ በተመሳሳይ ቀን ይወለዳሉንስ
አልሰማንም ነበር! ነገርግን ሚስት እና ባል በአራት ዓመታት ልዮነት በቅደም
ተከተል ነሐሴ 12 ቀን 1836 እና ነሐሴ 12 ቀን 1832 ዓ.ም ተወለዱ።
ምኒልክ የንጉሥ ሳህለ ሥላሴ ልጅ ከሆኑት ልዑል ኃይለ መለኮት እና ከወይዘሮ
እጅጋየሁ ለማ ከደብረ ብርሃን ደቡብ ምዕራብ አቅጣጫ አምስት ኪሎ ሜትር
ገደማ ርቃ
በምትገኘው የገጠር መንደር አንጎለላ ልዩ ስሟ እንቁላል ኮሶ መንደር ውስጥ
ነሐሴ 12 ቀን 1836 ዓ.ም ተወለዱ።
ብርሃን ዘ ኢትዮጵያ፤ ትልቁ ራስ ጉግሳ የጎንደሯን ባላባት ወይዘሮ ማሪቱን
አግብተው ወይዘሮ ሂሩትን፣ ወይዘሮ ተክሌንና ወይዘሮ አስቴርን ይወልዳሉ፡፡
ወይዘሮ ሂሩት ከራስ ገብሬ እና ከወይዘሮ ሳህሊቱ የሚወለዱትን ደጃዝማች ኃይለ
ማሪያምን አግብተው ደጃዝማች ብጡልን፣ ደጃዝማች መርሶንና ሌሎችንም
ልጆች ይወልዳሉ፡፡ ደጃዝማች ብጡል ደግሞ የጎጃም ደብረ መዊዕ ባላባት
የሆኑትን ወይዘሮ የውብዳርን አግብተው ነሐሴ 12 ቀን 1832 ዓ.ም ጎንደር ደብረ
ታቦር እቴጌ ጣይቱን ወለዱ፡፡
እቴጌ ጣይቱ የአባታቸው አያት በሆኑት በወይዘሮ ማሪቱ በኩል የዓፄ ፋሲል
ተወላጅ ከሆኑት ከዓፄ ተክለ ጊዮርጊስ (ፍፃሜ መንግሥት) የሚመዘዝ የዘር
ሐረግ አላቸው፡፡
ንጉሥ ምኒልክ ሚያዚያ 25 ቀን 1875 ዓ.ም በአንኮበር መድኃኒዓለም ቤተ
ክርስቲያን ከእቴጌ ጣይቱ ብጡል ጋር በቁርባን ጋብቻውን ፈፀሙ፡፡
አምስት ዓመታት ቆይቶም ጥቅምት 27 ቀን 1882 ዓ. ም ጣይቱ ብጡል
‹‹እቴጌ›› ተብለው ተሠየሙ፡፡ በዚህ ጊዜ ንጉሥ ምኒልክ ‹‹ንጉሠ ነገሥት ዘ
ኢትዮጵያ›› ከተባሉ ሦስተኛ ቀናቸው ነበር፡፡
ታኅሳስ 3 ቀን 1906 ዓ.ም አፄ ምኒልክ በተወለዱ በ69 ዓመታቸው በዕለተ
ዓርብ አረፉ፡፡
እቴጌ ጣይቱ ደግሞ የካቲት 4 ቀን 1910 ዓ.ም ሌሊት በተወለዱ በ78
ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ፡፡
እንኳን ተወለዱልን ንጉሡና ንግሥቲቱ!

👉እርሶ ያወቁትን እውቀት ሌሎች ያውቁ ዘንድ ቻናላችንን ሼር በማድረግ ጓደኛዎን ይጋብዙ

ቻናላችንን ይቀላቀሉ
👇👇👇👇👇 👇👇👇👇👇
@ethiopianissm @ethiopianissm
@ethiopianissm @ethiopianissm
@ethiopianissm @ethiopianissm
[ደብረ ታቦር]
ከመጋቤ ሐዲስ ዶክተር ሮዳስ ታደሰ
❖ ይኽ በዓል ከጌታችን 9ኙ ዐበይት በዓላት አንደኛው ሲኾን በዓሉ
በየዓመቱ ነሐሴ 13 ላይ በታላቅ ድምቀት ይከበራል፡፡ ታሪኩ በ3ቱ ወንጌላት ላይ
የተጻፈ ሲኾን ጌታችን አምላችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሌሎቹን ሐዋርያትን ከእግረ
ደብር (ከተራራው ሥር) ትቶ የምስጢር ደቀ መዛሙርት የሚባሉት ሦስቱን
(ጴጥሮን፣ ያዕቆብን፣ ዮሐንስን) ይዟቸው ወደ ታቦር ተራራ በመውጣት የሞተውን
ሙሴን ከ1644 ዓመታት በኋላ አስነሥቶ፤ የተሰወረውን ኤልያስንም ከብሔረ
ሕያዋን አምጥቶ የሕያዋን አምላክና የሙታን አሥነሺያቸው ርሱ መኾኑን
የገለጸበት ታላቅ ምስጢር የተከናወነበት ነው፡፡ (ማቴ 17፡1-9)።
❖ ጌታ 8ቱን ሐዋርያት ይዟቸው ያልወጣበት በይሁዳ ምክንያት ነው
ምክያቱም ከምሥጢረ መንግሥቱ ቢለየኝ ከሞቱ ገባኹበት ባለ ነበርና ነው፤
ነገር ግን በተራራው ላይ ለ3ቱ የተገለጸው ምስጢር ከተራራው ሥር ላሉት
ከይሁዳ በስተቀር ተገልጾላቸዋል፤ ለእኛም እንደ ሐዋርያት ምስጢሩን ጥበቡን
ይግለጽልን፡፡
❖ ብዙ ተራሮች ሳሉ የታቦር ተራራን የመረጠበት
1)አስቀድሞ የጌትነት ክብሩ በዚያ ተራራ ላይ እንደሚገልጽ ነቢዩ ዳዊት በመዝ
88፡12 ላይ “ታቦር ወአርሞንኤም በስመ ዚኣከ ይትፌሥሑ” (ታቦርና አርሞንኤም
በስምህ ይደሰታሉ) በማለት ጌታ በዚያ ተራራ ላይ ብርሃኑን ሲገልጽ የብርሃኑ
ነጸብራቅ እስከ አርሞንኤም ተራራ ድረስ እንደሚታይ የተናገረውን ትንቢት
ለመፈጸም ነው፡፡
❖ ሌላው ታቦር በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ 12 ጊዜያት ሲጠቀስ በተለይ በመሳ
4 እና 5 ላይ እንደተጻፈው አስቀድሞ በብሉይ ኪዳን የእስራኤል ጠላት የነበረው
ሲሳራን መስፍኑ ባርቅ በተራራው ላይ ድል ነሥቶበት ነቢይቱ ዲቦራም በተራራው
ላይ በደስታ አመስግናበታለች ዘምራበታለች፤ በተመሳሳይ መልኩ የእስራኤል
ዘነፍስ የክርስቲያኖችን ጠላት የኾነውን ዲያብሎስን የኹላችን ፈጣሪ ንጉሠ
ነገሥት ኢየሱስ ክርስቶስ አምላክነቱን ገልጦ ድል ስለነሣው ነቢያት ሐዋርያት
ምእመናን የሚያመሰግኑት ስለኾነ ለምሳሌነቱ ተስማሚነት ያለውን የታቦርን
ተራራን መርጦታል፡፡
❖ ለምን ሙሴንና ኤልያስን ከነቢያት መኻከል መረጠ? ቢሉ
ሀ) በማቴ 16፡13 ላይ ሐዋርያትን ስለማንነቱ እንደጠያቃቸው እንደመለሱለት
ኹሉ በእውነት ጌታችን የሙሴና የኤልያስ ፈጣሪ መኾኑን ሲገልጽላቸው ነው።
ለ) በዘፀ 33፡17-23 ላይ ሊቀ ነቢያት ሙሴ ከእግዚአብሔር ጋር ካለው ጥልቅ
ግንኙነት የተነሣ “እባክኽ ክብርኽን አሳየኝ” ብሎ ልመናን አቀረበ፤
እግዚአብሔርም "ወአነብረከ ውስተ ስቊረተ ኰኲሕ ወእከድን እዴየ በላዕሌከ
እስከ አኃልፍ" (በሰንጣቃው ዐለት አኖርሃለኍ፤ እስካልፍ ድረስ እጄን በላይኽ
እጋርዳለኍ፤ ካለፍኍ በኋላ እጄን አንሥቼልኽ ጀርባዬን ታያለኽ፤ ፊቴ ግን
አይታይም) ብሎታል (ዘፀ ፴፫፥፲፯-፳፫)፡፡
❖ ይኸውም ጀርባ በስተኋላ እንደሚገኝ ኹሉ በኋላ ዘመን አካላዊ ቃል
ከቅድስት ድንግል ማርያም ተወልዶ በታቦር ተራራ ላይ እንደሚገለጽለት
ሲያመለክተው ነው።
❖ ሊቁ ቅዱስ ያዕቆብም ስለ ታቦር በሚተነትነው መጽሐፉ ሙሴ በቃዴስ
ባለው በመሪባ ውሃ ከእስራኤል ጋር በበደለው በደል ምክንያት ምድረ ርስት
ኢየሩሳሌም እንዳይገባ አይቷት ብቻ በናባው ተራራ ላይ እንዲያርፍ ኾኗል (ዘፀ
፴፪፥፶፪፤ ዘፀ ፴፬፥፩-፰)፡፡
❖ ይኽ ለሙሴ አሳዛኝ ቢኾንም በኋላ ዘመን አካላዊ ቃል ክርስቶስ
ከቅድስት ድንግል ማርያም ተወልዶ ሙሴ በፊት በሩቁ ያያት ግን ያልገባባት
በምድረ ርስት በኢየሩሳሌም ያለች ታቦር ተራራ ላይ አምጥቶት በዘመነ ብሉይ
በአካለ ሥጋ ያልገባባትን ርስት እንዲገባባት አድርጎታል፤ ይኸውም አዳምና
ልጆቹ በአካለ ሥጋ ያጡትን ርስታቸው ገነትን በአካለ ነፍሳቸው ዳግመኛ
ሊያገባቸው እንደመጣ የሚያመለክት መኾኑን በስፋት አስተምሯል፡፡
❖ ጌታችን በብሉይ ኪዳን ከነበሩት ከነቢያት ሙሴንና ኤልያስን በሐዲስ
ኪዳን ከነበሩት ከሐዋርያት ሦስቱን በታቦር ተራራ ላይ ማውጣቱ፦
1) የታቦር ተራራ የቤተ ክርስቲያን ምሳሌ በመኾኗ ሲኾን በቤተ ክርስቲያናችን
ብሉይ ኪዳንና ሐዲስ ኪዳን እንደሚነገሩ ለማመልከት
2) በተራራ በተመሰለች በጉባኤ ቤት ብሉይና ሐዲስ እንደሚነገሩ ለመግለጽ፡፡
3) ሌላው የታቦር ተራራ የመንግሥተ ሰማያት ምሳሌ ስትኾን ይኸውም ጌታ
ነቢያትንና ሐዋርያትን በተራራዋ ላይ መሰብሰቡ መንግሥተ ሰማያትን ነቢያትም
ሐዋርያትም እንደሚወርሷን ለማመልከት
4) ሙሴ ያገባ ሲኾን ኤልያስ ድንግል ነውና መንግሥተ ሰማያትን ደናግልም
ያገቡም እንደሚወርሷት ለማጠየቅ ነው፡፡
5) እንደ ያዕቆብ ዘሥሩግ ትርጓሜ ሙሴ ኦሪት ዘፍጥረትን ሲጽፍ “በመጀመሪያ
እግዚአብሔር ሰማይንና ምድርን ፈጠረ” (ዘፍ 1፡1) እንዳለ፤ ዮሐንስም
“በመጀመሪያ ቃል ነበር” (ዮሐ 1፡1) ብሎ እንደ ሙሴ አምላክነቱን የሚመሰክር
ነውና ሙሴ አስቀድሞ የጻፈልኝ፤ አኹንም ዮሐንስ አምላክነቴን የሚጽፍልኝ እኔ
ነኝ ሲል ነው፡፡
6) ሙሴና ኤልያስ ይመሳሰላሉ፤ ይኸውም በሲና ተራራ 40 ቀንና ሌሊት
እንደጾመ ኤልያስም በደብረ ኮሬብ 40 ቀንና ሌሊት የጾመ ነውና፨
7) ሙሴ ንጉሡ ፈርዖንን የገሠፀ እንደነበር ኤልያስም ንጉሡ አክዐብን የገሠፀ
ነውና፨
8) ሙሴ ከንጉሡ ፈርዖን ፊት ሸሽቶ እንደሄደ ኤልያስም ከንግሥቲቱ ኤልዛቤል
ፊት ሸሽቶ ሄዶ ነበር።
9) ዳግመኛም ሰማይኑን ዝናብ እንዳያዘንም በተሰጠው ሥልጣን ባሰረውና ከ3
ዓመት ከ6ወር ቆይታ በኋላ እንዲዘንብ በፈታው ኤልያስን እንዳመጣ ኹሉ
የማሰር የመፍታት ሥልጣን ሥልጣነ ተሰጥቶት “እኔም እልሃለሁ፥ አንተ ጴጥሮስ
ነህ፥ በዚችም ዓለት ላይ ቤተ ክርስቲያኔን እሠራለሁ፥ የገሃነም ደጆችም
አይችሉአትም የመንግሥተ ሰማያትንም መክፈቻዎች እሰጥሃለሁ፤ በምድር
የምታስረው ሁሉ በሰማያት የታሰረ ይሆናል፥ በምድርም የምትፈታው ሁሉ
በሰማያት የተፈታ ይሆናል” (ማቴ 16፡18-19) ላለው ለጴጥሮስን ታላቅ ሰማያዊ
ሥልጣን መስጠቱን ለማመልከት አምጥቷቸዋል፡፡
❖ በቤተ ክርስቲያንና በሀገራችን ያለው መንፈሳዊ አከባበር ደማቅ ነው፤
ይኽ በዓል በቤተ ክርስቲያን በማሕሌት በቅዳሴ በትምህርት የሚከበር በዓል
ሲኾን በሀገርኛ የቡሄ በዓል ይባላል፤ ቡሔ ማለት ሊቁ ደስታ ተክለ ወልድ
በመዝገበ ቃላት ላይ ሲገልጹት ቧ ብሎ በደብረ ታቦር የተገለጠው የጌታችንን
የፊቱን ብርሃን ጸዳል የልብሱን እንደ በረዶ ነጭ መኾን ያስረዳል ስለዚኽ
የብርሃን፣ ብርሃናዊ ማለት ነው፡፡
❖ በዚህ በዓል በታቦር የታየው የብርሃኑ ምሳሌ የሚሆን ችቦ ይበራል፤
ሌላው በዚኽ በዓል ሰሞን በገጠር ከተራራ ላይ እረኞች ሕጻናት ዥራፍ እየገመዱ
ማስጮኻቸው ጌታ በተራራ ላይ ብርሃኑን በገለጸ ጊዜ አብ በደመና ኾኖ “እርሱ
ደስ የሚለኝ የምወደው ልጄ ይህ ነው፤ እርሱን ስሙት” ባለ ጊዜ ሐዋርያት
በድምፁ ደንግጸው መውደቃቸውን ለማመለክት ነው፡፡
❖ ሌላው ሙሉሙሉ ዳቦ መጋገሩ በትውፊት እንደምንረዳው ጌታ ብርሃኑን
ሲገልጽ ብርሃኑ እስከ አርሞንኤም ተራራ ድረስ ያበራ ስለነበር እረኞች ሌሊቱ ኹሉ
ቀን መስሏቸው እዛው ስለዋሉ ቤተሰቦቻቸው “ኅብስት” ይዘውላቸው ሄደዋልና
የዚያ ምሳሌ እንደኾነ ይነገራል፡፡
[በደብረ ታቦር ላይ ብርሃኑን የገለጠው አምላካችን ክርስቶስ ምስጋና ይግባው]፡፡
[መልካም በዓል]


👉እርሶ ያወቁትን እውቀት ሌሎች ያውቁ ዘንድ ቻናላችንን ሼር በማድረግ ጓደኛዎን ይጋብዙ

ቻናላችንን ይቀላቀሉ
👇👇👇👇👇 👇👇👇👇👇
@ethiopianissm @ethiopianissm
@ethiopianissm @ethiopianissm
ሰላም ውድ የኢትዮጵ ቤተሰቦች እንዴት ናችሁ?
እንደምታውቁት የምንፅፋቸው ፅሁፎች ብዙ አንባብያን ጋ አይደርሱም። እኛም ከደከምን አይቀር ብዙ ሰወች አንብበው ስለ ሀገራችችን ጥንታዊ ስልጣኔ ያውቁ ዘንድ ይሄን ፅሁፍ 1ሰው ለ10 ሰወች forward ያድርግ ከዛም join ማረጋቸውን ያረጋግጥ ፤ ይህን ለማድረግ ሶሥት ደቂቃ በቂ ነው። እናም ይህን ዘመቻ በአንድ ቀን ውስጥ ማድረግ ከቻልን የአባሎቻችን ቁጥር መጨመር እንችላለን

ሁላችንም ይሄን ማረግ አያቅተንም። የአንባቢዎች መብዛት እኛንም ያበረታናል።

፨፨፨ መልካም ዘመቻ፨፨፨

👇👇👇👇👇
@ethiopianissm
@ethiopianissm
@ethiopianissm
@ethiopianissm
HTML Embed Code:
2024/04/26 12:46:38
Back to Top