TG Telegram Group Link
Channel: ኢትዮጵ
Back to Bottom
በመጨረሻም… አቃጠሉት… አወደሙት

… መጀመሪያ ከግብርና ሥራቸው፣ ከሞቀ፣ ከደራ ከፈካ የገበሬ ቤታቸው፣ የገጠር መንደራቸው፣ አትክልቱን ከጓሮ እሸቱን ከማሳ ቀጥፈው ከሚበሉበት በጎተራ የሞላ እህላቸውን፣ በማሳ የተንዠረገገ ሰብላቸውን ተዘርፈው፣ ቤት ንብረታቸውን አቃጥለው፣ አባ ወራውን እማወራዋን ገድለው አስገድለው፣ ከብቱንም ሴት ሕፃናቱንም አርደው አሳርደው አወራርደው፣ በማህፀን ያለ ህጻን ሳይቀር የነፍሰጡር ሴት ሆድ ቀደው አርደው ፅንስ አውጥተው በልተው፣ አስከሬን ደፍረው፣ በጅምላ እስላም ክርስቲያኑን በአንድ ላይ ቀብረው የሞተው ሞቶ የተረፈው ከሞት አምልጦ ቻግኒ ገባ።

…በቻግኒ ህዝቡ አልቅሶ፣ ደግሶ፣ ተቀበላቸው። አስተናገዳቸው። መንግሥት ግን አዘነ፣ ብአዴን በሰጨው። በቻግኒ ሳሉ ስደተኞቹ ህክምና ተከለከሉ። ራቡም ፈጃቸው። ስቃይ በረታባቸው። በፖለቲከኞቹ ቁማር ንፁሃን አርሶ አደሮች ተበሉ። 

… ብአዴን ለርዳታ የመጣላቸውን እህል፣ ዘይት፣ ጨው፣ ፍራሽ እና ብስኩት ሳይቀር እያወጣ ለነጋዴ ሸጠው። ዘይቱን በ350 ብር ለመንግሥት ሠራተኞች አከፋፍሎ ጨረሰው። በመጪው ምርጫ ህዝቡ ይመርጡት ዘንድ ዘይት በርካሽ ሰጥቶ ቀሰቀሰበት፣ እጅ መንሻ መሆኑ ነው። ይሄም ብቻ አይደለም ብአዴን በስፍራው በበጎ ፈቃደኝነት ለስደተኞቹ አገልግሎት ይሰጡ የነበሩ ዜጎችን በሙሉ አባረረ። ገሚሶቹንም አሰረ።

… ዛሬ ደግሞ ይባስ ብሎ እስከዛሬ በመጋዘን ከዝኖ ያስቀመጠውን የስደተኞቹን መጋዘን ለብቻው ነጥሎ እሳት ለቀቀበት። እሳት በላው ተባለ። ህዝቡ እኮ ወገኑን መርዳቱን አላቆመም። ህዝቡ ለወገኖቹ ማዘን ማልቀሱን እኮ አላቆመም። መንግሥቱ ግን የሌለ ነው የጨከነው። እሺ አሁን ስደተኞቹ ምን ይዋጣቸው? ገበሬዎቹ፣ አዛውንቶቹ፣ ህጻናቱ ምን ይዋጣቸው? ራብ ክፉ ነው። ጊዜም አይሰጥ። 

… ወገኖቼ ፈጣሪ ይድረስላችሁ።
Forwarded from Gebreab Tamir
ረቡዕ ማታ ከ2:00-2:45 ድረስ በዚህ YouTube Channel የቀጥታ ሥርጭት ላይ አስገራሚ ስለሆነው ምስጢራዊው አንታርክቲካ ይዤላችሁ እቀርባለሁ። በበረዶዎቹ ውስጥ ስላሉት ለዓለም እንቆቅልሽ ስለሆኑ ምስጢራት፤ ከበረዶዎቹ ውስጥ ስለሚወጣው ደም መሳይ ፏፏቴ፤ ከበረዶው ውስጥ ስለሚሰማው የሐዘን ዜማና በዚህ ማስታወቂያ ስለማልነግራችሁ ዕጹብ ድንቅ የሆነ ጉዳይ ይዤላችሁ እቀርባለሁ።
መጋቤ ሐዲስ ዶክተር ሮዳስ ታደሰ
ቻናሉን ሰብስክራይብ አድርገው ዕውቀትን ከጥበብ ጋር አዋሕደው ይጓዙ
https://www.youtube.com/channel/UCFKnpmDyWe3LQ_9Gx3TMnAg
… በኦሮሚያ የዐማራ ዘር በዚህ መልኩ እየጠፋ ነው። ጄኖሳይድ እየተፈጸመ ነው።

ብአዴን ተባባሪ ነው። ኦህዴድ ፈጻሚ ነው። ሸኔ የዳቦ ስም ነው። በዘመነ ኦሮሞ ዐማራ በዚህ መልኩ ከምድሪቱ ላይ እየጸዳ ነው። የጊዜ ጉዳይ እንጂ ዐብይም ሆነ ሽመልስ ብልጽግና ነን ባዮች ሁሉ በምድርም በሰማይም ፍርዳቸውን ያገኛሉ።

… የሃይማኖት አባቶች ለዐቢይ አሕመድ ሦስተኛ ዓመት #በአለ_ሺሞት የድጋፍ ሰልፍ ለማድረግ በዝግጅት ላይ ናቸው።

ነፍስ ይማር ወገኖቼ !!
Forwarded from Minale One day .
"ይነጋል ባልነው ቀን ፣ ጨለማው ገነነ
አሻጋሪ ያልነው ፣ አሸባሪ ሆነ
እያለ ውስጥ ውስጡን ፣ ህዝብ ያጉረመርማል
ይሄ ምን ይገርማል?
"ህዝብ እየታረደ
የሰላም ሽልማት ፣ እሱ ይሸለማል"
እያለ አንዳንዱ ፣ በአሽሙር አንተን ያማል።
ይሄ ምን ይደንቃል?
እኔም አንድ ሰሞን ፣ በሚያሽኮረምም ቃል
እንዲህ ብዬ ነበር
በፍቅር ስብከትህ ፣ ልቤ እየራደ
"ከእባቦች እንቁላል ፣ እርግብ ተወለደ ።"
ብዬ ነበር ያኔ ፣ ምህረት ስትምገኝ
ተአምር መሥሎኝ ነበር
ከገዳዮች መሀል
"መግደል መሸነፍ ነው" ፣ ምትል አንተን ሳገኝ።
።።
ይሄ ምን ይገርማል?
"በግንቦት ሀያ ላይ ፣ ግንቦት ስላሴ ተቆጣ
ደርግ ጥሎን ሲሔድ ፣
ነፃ አውጪ ነኝ ብሎ ፣ሌላ ደርግ መጣ
ገዢ መንግስት ወርዶ ፣ ገዢ መንግስት ወጣ
ከተገዛች አይቀር
ድርሻዬ ይሰጠኝ ፣ ሀገሬ ተሽጣ"
ብዬ ነበር ያኔ
ዝም በል እያለ ፣ ሲገርፈኝ ወያኔ
ዝም አልልም ብዬ ፣ በሀገር ፍቅር ወኔ
የታገልኩት እኔ
ለቀብሬ አይደለም ፣ ቀን በቀን ለማልቀስ
ከሞት መች አዳነን
በታረድን ቁጥር ፣ ህወሐትንና ፣ ኦነግ ሸኔን መውቀስ
ማነው ከነትጥቁ
ወደሀገር ያስገባው ፣ ማነው ያስታጠቀስ?!
ፍትህ ስንጠይቅ
ሞት የሚፈርድብን ፣ የማን ሹም ነው ዳኛ
ማን ነው ስም ሚሰጠን
ስንሞት ኢትዮጵያዊ ፣ ስንኖር ነፍጠኛ
ብሎ የሚጠራን ፣ በጅምላ ስንረግፍ
ጭካኔ ሲበዛ ፣ በደል ሲያገፈግፍ
እጥፍ ድርብ ሲሆን ፣ ይቀራል ያልነው ግፍ
ትጠብቃለህ ወይ?
ህዝብ እየተገፋ ፣ አንተን እንዲደግፍ

።።
እና
ሬሳ ተለቅሞ ፣ ፍትህ ስትቀር ኦና
ሰርክ እየታረደ ፣ ሚሞት የለምና
ወይ ህዝብህን አስታጥቅ ፣ መይ መንግስት ሆነህ ና
ሀገር አይመራም!!!
"መግደል መሸነፍ ነው ፣ በሚል ፍልስፍና!
ሰው እየፈረሰ ፣ የለም ብልፅግና!
Forwarded from አርከለዲስ | Arkeledis Media (❇️ወደ ኋላ ፕሮሞሽን❇️)
🍀የሰው ነገር🍀

🍀 የሰው ነገር ሲነኳት የምትጠቀለለው አስገራሚ ዕፅ
🍀 የዕፅዋቷ ፈውስና ገቢር
🍀 ለማይግሬንና ለአጓጉት በሽታ መድኃኒት
🍀 ባህላዊ ህክምና

በታላቁ የዩቲዩብና የቴሌግራም ቻናል " ወደ ኋላ ጥንታዊ ጥበባት " ተዘጋጅቶ የቀረበ፥ ብሩህ አዕምሮ ላላቸው ለቀጣይ ሀገር ተረካቢዎች ምርምርን የሚከፍት መረጃ !
በYoutube ቻናላችን ላይ ይመልከቱ
👇👇👇

█►OPEN◄►OPEN█
█►OPEN◄►OPEN█
█►OPEN◄►OPEN█
█►OPEN◄►OPEN█

ቴሌግራም በጽሑፍ ለማንበብ 👇🏾
https://hottg.com/EthiopeTowoderos/4163
👆🏾👆🏾👆🏾
ሞት የማይገባው እርሱ ሞተ!
ሞትን ይሽረው ዘንድ ሞተ!
ሙታንን ያድን ዘንድ ሞተ!”
ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ

በርሱም ቍስል እኛ ተፈወስን።
ትንቢተ ኢሳያስ 53፥5

ተፈፀመ!

@EthioEthel @Ethio_Ethel
መቃብሩ ባዶ ነው !
  ~🌹🌹🌹~
    

※"ሞት ድል በመነሣት ተዋጠ " 1ኛ  ቆሮ 15፣54

… ከመጀመሪያው ሰው አዳም ጀምሮ እስከአሁን ድረስ የሞቱ፣ ወደፊትም የሞትን ጽዋ የሚቀምሱ ሁሉ በመቃብር ወስጥ አሉ። ይኖራሉም። ነብያት ቢሆኑ ሐዋርያት፣ ጻድቃንም ሰማዕታትም ቢሆኑ ነገሥታትና መኳንንት ሁላቸውም ሟቾች ናቸው። በየአንዳንዳቸው የመቃብር ሥፍራም ብንሄድ በዚያ የአጽማቸውን ቅሪት እናገኛለን።

… ይህንኑ ሲያረጋግጥ ሊቀ ሐዋርያት ቅዱስ ጴጥሮስ በበዓለ ኅምሳ ቀን በኢየሩሳሌም ለተሰበሰቡት እንዲህ አለ፤ " ወንድሞች ሆይ፥ ስለ አባቶች አለቃ ስለ ዳዊት እንደ ሞተም እንደ ተቀበረም ለእናንተ በግልጥ እናገር ዘንድ ፍቀዱልኝ፤ መቃብሩም እስከ ዛሬ በእኛ ዘንድ ነው።" የሐዋ 2፣29

… የጨካኞቹ ነገሥታት ከቀደሙቱ የነፈርኦን፣ ናቡከደነጾርና ዲዮቅልጥያኖስ፣ ከኋለኛው ዘመንም የእነሒትለርና ሞሶሎኒም ቢሆኑ የትም ይሁን የት በተቀበሩበት ሥፍራ አጽማቸውን እናገኘዋለን። ምስጥም አፈርም ቢበላቸው እንኳ ቅሪታቸው በዚህች ምድር ይኖራል።

… እውነት ነው፤ በየትኛውም የምድራችን ክፍል ላይ የሚገኙ የመቃብር ሥፍራዎችን ብንጎበኛቸው በሰዎች አጽም የተሞሉ ናቸው። ከሰው ወገን ሆነው እስከ አሁን ሞትን ያልቀመሱ አባቶቻችን እንደ ነቢዩ ኤልያስና ቅዱስ ያሬድ የመሳሰሉ ቅዱሳንም ቢሆኑ እንኳ እስከ ጊዜው ድረስ እንጂ የጊዜው ጊዜ ሲደርስ ሞት እንደሁ አይቀርላቸውም። ከዘመናት በኋላ ወደ ምድር መጥተው የሞትን ጽዋም ይቀምሳሉ።

※የኛ ጌታ መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የድንግል ማርያም ልጅ አማኑኤል ግን ሞቶ በዚያው አልቀረም። የሞት ኃይልም አላሸነፈውም። ሞትን በሞቱ ድል አድርጎ ተነሥቷል።" ሞት ሆይ፥ መውጊያህ የት አለ? ሲኦል ሆይ፥ ድል መንሣትህ የት አለ?" 1ኛ ቆሮ 15፣55 ተብሎ እንደተጻፈ ወደተቀበረበት ሥፍራ ወደ ቀራንዮም ብንሄድ በዚያ የለም። ምክንያቱም ሞት ድል በመነሣት ተውጦአልና መቃብሩም ባዶ ነው።

ይህንን እውነት ደግሞ ቅዱሳት መጻሕፍት ያረጋግጡልናል ።

👉" መጽሐፍ እንደሚል ክርስቶስ ስለ ኃጢአታችን ሞተ፥ ተቀበረም፥ መጽሐፍም እንደሚል በሦስተኛው ቀን ተነሣ" 1ኛ ቆሮ15 ፣ 3-4

👉" ሕያውን ከሙታን መካከል ስለ ምን ትፈልጋላችሁ? ተነሥቶአል እንጂ በዚህ የለም።" ሉቃ 24፣5

👉" እንደ ተናገረ ተነሥቶአልና በዚህ የለም፤ የተኛበትን ስፍራ ኑና እዩ።" ማቴ 28፣6

👉" አሁን ግን ክርስቶስ ላንቀላፉት በኩራት ሆኖ ከሙታን ተነሥቶአል።"1ኛ ቆሮ15፣20

እልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልል

ውድ ጓደኞቼ ፦እንኳን ለብርሃነ ትንሣኤው አደረሳችሁ ።

ዘመድኩን በቀለ ነኝ
ሚያዝያ 23/8/2008 ዓም
አዲስአበባ - ኢትዮጵያ ሆኜ የጻፍኩትን ዘንድሮ
ሚያዝያ 24/2013 ዓም
በድጋሚ ከራየን ወንዝ ማዶ ለጠፍኩላችሁ።
Forwarded from Gebreab Tamir
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

የአስጨናቂዎችሽም ልጆች አንገታቸውን ደፍተዉ ወደ አንቺ ይመጣሉ ፤ የናቁሽ ሁሉ ወደ እግርሽ ጫማ ይሰግዳሉ ፤
ትን.ኢሳ 60፥14
💚💛💚💛💚💛💚💛
"የብርሃናት ንጉሥ ብርሃን ኢየሱስ ክርስቶስን ለመውለድ ዛሬ የብርሃን እናት ቅድስት ድንግል ማርያም በእውነት ተወለደች።

በሔዋን ምክንያት የተዘጋው የሕይወት መንገድ ይከፈትልን ዘንድ የሕይወት እናት ዛሬ ተወለደች፡፡ የዓለም ብርሃን ኢየሱስ ክርስቶስን ከእርሷ ይወለድ ዘንድ እመብርሃን ዛሬ ተወለደች።

እውነተኛው ፀሐይ ኢየሱስ ክርስቶስ ከእርሷ ይወለድ ዘንድ እመ ፀሐይ (የፀሐይ እናት) ቅድስት ድንግል ዛሬ ተወለደች፤ ብርሃንን ለማስገኘት መወለድ መታደል ነው፤ ከሰው ልጆችም መካከል መመረጥ ዕፁብ ድንቅ ነው፤ የመድኃኔዓለም እናት ለመሆን መወለድ ሰማያዊ ፀጋ ነው።

የአለሙን ሁሉ መድኃኒት ለወለደች ለብርሃናት ጌታ እናት በቀራንዮ በመስቀሉ ስር እናት ትሆነን ዘንድ ለተሠጠችን ለመመኪያችን ዘውድ ለተወዳጇ ለቅድስተ ቅዱሳን እናታችን ልደት በዓል እንኳን አደረሰን አደረሳችሁ።"

✟ገብርዬ💚💛🙏

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
የሳጥናኤል ጎል ኢትዮጵያ ቁጥር 4 መጻህፍ ላይ "የአንዳምንን ስልጣኔ ማውደም!" የሚል ተልዕኮ ተሰጥቶዋቸው እሱኑ ሊያስፈጽሙ የመጡ 180 ዜጎች (ማለትም 90 ሴቶችና 90 ወንዶች) ምልምል ኢትዮጵያውያን ባለስልጣናት እንዳሉ ተገልጾዋል::
እነዚህ ኢትዮጵያውያን በተለያዩ መንግስታዊ ሴክተሮች በስልጣን ላይ እና በስራ ላይ የነበሩ ሲሆኑ (ወደፊት ከሚደረገው) ከመንግስት ለውጥ በሁዋላ (ኦልሬዲ ለውጡ ተደርጎዋል) ዋና ዋናውን የመንግስትነት ስልጣን ይዘው እንዲቀጥሉ የታጩ ናቸው::
እነዚህም ቀደም ብለው ተመልምለው ለትምህርት ለስልጠና ለወዘተ... በሚል ወደ ውጭ አገር የሄዱና በሲ.አይ.ኤ.እና በመሰል ዓለም አቀፍ ተቁዋማት አማካኝነት በልዩ ሁኔታ የሰለጠኑና በ2014 እ.ኤ.አ ልዩ እና ረቂቅ የተባለውን ስልጠናቸውን አጠናቀው ተመርቀው የተላኩ ናቸው::
እነርሱም ከለውጡ በሁዋላ በየዘርፉ ተሰማርተው ዓላማቸውን የሚከውኑ; የማይተዋወቁ መስለው ነገር ግን ተናብበው የሚሰሩና የተሰጣቸውን ተልዕኮ በየዘርፉ ተሰማርተው ሊፈጽሙ በእንግሊዙዋ ንግስትና በG20 አገራት መሪዎች ፊት የደም ቃል ኪዳን የፈጸሙ እንደሆኑ በመጽሃፉ ተገልጾዋል::
ከተልዕኮዋቸው ውስጥም አንዱና ዋናው "የአንዳምንን ስልጣኔ ማውደም!" የሚል ነው::
"የአንዳምንን ስልጣኔና አራማጆቹን ማፍረክረክ! ማሽመድመድና ማውደም! የሚለው......... ከተልዕኮዋቸው ውስጥ አንዱና ዋናው ነው::
ይህም በዋናነት ሐይማኖተኛውንና ሴሜቲኩን ህዝብ የሚመለከት ሲሆን; በዋናነት "ነጻ ህዝብ" ብለው የሚጠሩትን የአምሐራ እና ትግራይን ብሄር መንግስታዊ በሆኑና ባልሆኑ ልዩ ልዩና ሁሉን አቀፍ በሆኑ ዘርፈ ብዙ ዘመቻዎች ማፍረክረክ, ማሽመድመድና ከጥቅም ውጭ ማድረግ...!" የሚለው ይገኝበታል::
ይህ ከመሆኑ በፊት ግን በፖለቲካ ሰበብ የትግራዩን ሴሜቲክ ህዝብ ቀድሞ ማፍረክረክ እንደሚያስፈልግ, ሁለቱን ህዝብም እስከመጨረሻው ማቆራረጥ ግዴታ እንደሆነና ይህም በቅርቡ እንደሚደረግ, በስልጣን ያለውን መንግስትም (ህወሃትን) ማፍረስ ግድ እንደሆነና ያንንም እንደሚያደርጉ; ከዚሁ ጋርም አገሪቱን የኢኮኖሚ ቅኝ ተገዥ ያደረጋትን የገዥውን ፓርቲ ኤፈርት የተባለ ድርጅት ማፍረስ እንደሚያስፈልግ ከ ቁጥር 4 ቱ መጻህፍ በፊት በተጻፈው በቁጥር 3 ቱ መጻህፍ ተገልጾ ነበር::
ኢትዮጵያን በሚመለከት ጉባዔተኞቹ እ.ኤ.አ በ2014 ዓ.ም በአሜሪካ ኒዮርክ, በአውስትራሊያ ሜልቦርን እና በቤልጀም ብራሰልስ አዳራሾች በዝግ ጉባዔያቸው በዶለቱት መሰረትም ብዙዎቹን እቅዶቻቸውን ወደ ተግባር መለወጥ ጀምረዋል::
ኢትዮጵያን በሚመለከት አጠቃላይ እቅዳቸውን በኛ አቆጣጠር በ2007 ዓ.ም ለህትመት ከበቃው "የሳጥናኤል ጎል ኢትዮጵያ" ከሚለው ከመጀመሪያው መጻህፍ እና የዚያ መጻህፍ ተከታይ ክፍሎች ሆነው ተከታትለው ከወጡት "የሳጥናኤል ጎል ኢትዮጵያ ቁጥር 1, "የሳጥናኤል ጎል ኢትዮጵያ ቁጥር 2," "የሳጥናኤል ጎል ኢትዮጵያ ቁጥር 3" እና "የሳጥናኤል ጎል ኢትዮጵያ ቁጥር 4" በተሰኙት መጻህፍት አጠቃላይ እቅዳቸው በሙሉ በሰፊውና በዝርዝር እንዲሁም ቃል በቃል ተገልጾዋል::
በበኩሌ እነዚህን አራት መጻህፍት ገዝታችሁ እንድታነቡዋቸው ብቻ ሳይሆን በየሸልፋችሁ እንዲገኙ ከመምከር አልፌ ማሳሰብ እፈልጋለሁ!
ይህን የምለውም በምክንያት ነው እውነታው ያለው በእነዚህ መጻህፍት ውስጥ ስለሆነ ነው!በዚህም እርግጠኛ ስለሆንኩ ነው!
ኢትዮጵያን በሚመለከት በኅያላን አገራት መንግስታት በኩል ወደፊት የታቀደው ወይም የተደገሰው ምን እንደሆነ ለመረዳት ብቸኛ ምርጫችሁ እነዚህ መጻህፍት እንደሆኑ እርግጠኛ ሆኘ እነግራችሁዋለሁ!
"ለምን ኢትዮጵያን? እንዴት ኢትዮጵያን? ይቺን ተራ እና ምስኪን አገር በዚህ ደረጃ ማጥመድ ለምን አስፈለገ? ከኢትዮጵያ ምን ፈልገው?" ወዘተ... የሚሉ ጥያቄዎችን መረዳትም ሆነ ትክክለኛ ምላሻቸውን ማግኘት የሚቻለው በርግጥ በእነዚህ መጻህፍት ነው!
ማመን ያለማመን የእናንተ መብት ነው! ነገር ግን መጻህፍቱን እዩዋቸው አንብቡዋቸው!
የተጻፉትን አንዳንድ ነገሮች ዛሬ ላይ ላታምኑ ትችላላችሁ:: ነገር ግን የተጻፉት ነገሮች ወደ ተግባር ሲለወጡ ስታዩ ማመናችሁ ስለማይቀር ማንበብ ባትፈልጉ እንኩዋን መጻህፍቱን ይዛችሁዋቸው ቆዩ ብዬ በልበ ሙሉነት እመክራለሁ!
ሁሉም መጻህፍት ደግሞ እጅግ ቅናሽ በሆነ ዋጋ ገበያ ላይ የሚገኙ ናቸውና ፈጥናችሁ እዩዋቸው እላለሁ::
በቅርቡ ቁጥር 1, ቁጥር 2, ቁጥር 3, በተራኪ አፕ ተዘጋጅተው ሊቀርቡ እንደሆነ መረጃው አለኝ::
እስከዚያው ግን ቁጥር 4 ላይ አንዳንድ መረጃዎችን እየያዛችሁ ትቆዩ ዘንድ ያለ በቂ ዝግጅትም ቢሆን ወቅታዊ ክንውኖች ላይ በማተኮር አንዳንድ ሃሳቦች በወፍ በረር የሚተረኩበትን ይህን ቻናል ጆይን አድርጋችሁ እንዳንድ አሳቦችን እንድታደምጡ ተጋብዛችሁዋል::
ለምሳሌ "የአንዳምንን ስልጣኔ ማውደም!" ሲሉ ምን ማለታቸው ነው? "አንዳምን" የሚሉት ምኑን ነው? የሚለውን ነገር የቫቲካኑ ጳጳስ እንዲህ ሲሉ ገልጸውታል::
በመጽሃፉ ውስጥ ያለው "የአንዳምንን ስልጣኔ ማውደም" የሚል ገለጻቸው ያለ በቂ ዝግጅት በአጭሩ እንዲህ ተተርኮዋልና አድምጡት::
ወጣቱ ድምጻዊ ሮፍናን “ሦስት” በሚል ርዕስ አዲስ በለቀቀው ሙዚቃ “ሰከላ ዓባይን ወለደች እናቴም እኔን…” በማለት የሰከላን ወላዲተ ዓባይነት ተቀኝቶበታል፡፡

ለመሆኑ ሰከላ ማን ነች? ሰከላ ከባሕር ዳር 165 ኪ.ሜ፣ ከፍኖተ ሰላም 73 ኪ.ሜ፣ ከዋናው መንገድ ላይ ከምትገኘዋ የቲሊሊ ከተማ 30 ኪ.ሜ ርቀት ላይ የምትገኝ ወረዳ ናት። ሰከላ የግዮን (የአባይ ወንዝ) መነሻ ምንጭ'ም ናት።

"አባይ" ሰከላ ከሚገኘው "ግሽ" ከተባለው በደን የተሸፈነ ረግረጋማ ቦታ ላይ ይመነጫል። ከግሸን ተራራ ስር፣ ከሰቀላ ወረዳ ፈልቆ በግሸን ሜዳ ላይ ግልገል አባይን ሆኖ ይፈሳል። ግልገል አባይ፣ በግሸን ሜዳ ላይ ሮጦ ከጣና ሐይቅ ሲስርግ በጣና ተውጦ አይቀርም። በጣና ላይ ተንሳፎ፣ ወደ አባይ ሸጥ ይንደረደራል።

በመጨረሻም በደጀን በኩል ወደ ሱዳን ካርቱም፤ ግብጽና ወደ ሜዲትራንያን ባሕር ወርዶ ይቀላቀላል፡፡ በ3000 ዓ.ዓ. በሲና ምድረበዳ "ዘፍጥረትን" የጻፈው ሙሴ "ግዮን" ኢትዮጵያ፥ጎጃም፥ሰከላ ውስጥ ግሽ ተራራ ስር ፈልቆ የኢትዮጵያን ምድር ሁሉ እንደ ቀለበት ክብ ሠርቶ እንደሚፈስ ለመጀመሪያ ጊዜ ጽፏል።

ምድር በቁጥቋጦና በቡቃያ ሳትሸፈን ዝናብ መዝነብ ሳይጀምርና ተንቀሳቃሽ ሰው ሳይፈጠር አራቱ የውሐ ምንጮች በኤዶም በስተምሥራቅ የምትገኘውን ገነትን ያጠጡ እንደነበር ዘፍጥረት ላይ ሰፍሮ እናገኘዋለን። ከአራቱ የውሐ ምንጮች አንዱ "ግዮን" ወይንም "አባይ" ነው።

"ግዮን" ግዕዝ ሲሆን፣ "አባይ" በአማርኛ ከወንዞች ሁሉ ታላቅ ማለት ነው። የግዮን ጽንሰትና ቀዳማዊ ልደት ሰከላ ነው። ግዮን ምንጭ ላይ የአቡነ ዘርዓ ብሩክ ገዳም ይገኛል። "ዓባይ" እና "ግሽ ዓባይ" የሚሉ ስሞች ያወጡት እርሳቸው ናቸው።

ባጠቃላይ ወጣቱ ድምጻዊ ሮፍናን ጠንካራ መልእክት ነው ያስተላለፈው።
"ጦቢያው ለይቅርታ ቅደም
ቀድመህ እንዳትተወዉ ድገም
ደግሞ ቢስቀይምህ ሰልስ
ያባትክን አደራ መልስ
ያኔ በላይ ይዘልቃል
ያንጊዜም ቴወድሮስ ይደግማል
ያንጊዜም አሉላ ራስ ነው
ምኒሊክ ዛሬም ንጉስ ነው

ታደለ ጥበቡ

@ethiopianissm
@ethiopianissm
@ethiopianissm
የቴሌ ኮም ዘርፍ ሽያጭና ሰሞነኛው ዛቻ::
የዓለም አቀፍ ተቁዋማት አመራሮችና የኅያል አገራት መንግስታት በጋራ የቀረጹትን ፖሊሲ ያለ አንዳች ጉርምርምታና ተቃውሞ ወደ ተግባር ለመለወጥ ይረዳቸው ዘንድ ልዩ ጥንቃቄ ያደርጋሉ:: ዕቅዳቸውም በጥንቃቄ የተጠናና የግድ መፈጸም የሚኖርበት ዕቅድ ነውና ለተፈጻሚነቱ ሲሉ ማናቸውንም አይነት መስዋዕትነት ይከፍላሉ:: ከተራ ትችት ጀምሮ በዓለም አቀፍ ሚዲያዎች በብሄራዊ ደረጃ እስከ መብጠልጠል ድረስ ያለውን ውርጅብኝ በደስታ ያስተናግዳሉ::
የማይግባቡ መስለው ነገር ግን ተናብበው የሚሰሩ ናቸውና በመካከላቸው አንዳችም ጸብ ሳይኖር ውጊያ ቀረሽ ግብግብ ውስጥ የገቡ መስለው ይታያሉ::በዓለም አቀፍ ሚዲያዎች በቃላት ከመወራረፍ ያለፈ ሃሰተኛ የሚሳኤል ውጊያም ሊያደርጉ ይችላሉ:: ዕቅዳቸው ዳር ይድረስ እንጂ የዓለምን ህዝብ ጫጫታና ሃሜት እንዲሁም ትንተና ከመጤፍ አይቆጥሩትም!
በዚህ አይነት ሁኔታ "መስለው" ሳይሆን "ሆነው!" ስለሚተውኑ ለብዙዎች እንዲህ ያለውን እውነት ማስረዳት አይቻልም:: ማስረዳት ቢቻልም አስረድቶ ማሳመን አይቻልም::
እንዲህ ያለውን የረቀቀ አካሄዳቸውን ደግሞ በተቀደደለት የሰበር ዜና ቦይ በሚፈሰው በብዙሃኑ ህዝብ የፕሮፖጋንዳ ጫጫታ ያጅቡታል ሂደቱንም ከህዝብ ዕይታ ይጋርዱታል::የህዝቡን ትኩረት ሌላ ላይ እንዲሆን አድርገው ያቀዱትን ስራም ይሁን ሴራ በመንግስታዊ ህግ ያለ አንዳች ውይይትና ጉርምርምታ በምክር ቤት ደረጃ በሙሉ ድምጽ ያስጸድቁታል::መሻታቸውን በህጋዊ መንገድ በቁጥጥር ስር ያውሉታል::
በዚህ መሰሉ አካሄዳቸው ምክንያትም የነጠሩ ሴራ አዘል እውነቶቻቸው በጩኸት ብዛትና በተደጋጋሚ ሃሰተኛ የሰበር ዜና ርግብግቦሾች ይዳፈኑላቸዋል...::
**********
አብይ አህመድ ስልጣን በያዘ ማግስት ከአንደበቱ የወጣው የመጀመሪያው ቃል "ፕራይቬታይዜሽን..." የሚለው ቃል ነው:: ለዚህም የኖቤል ቀብዱን ወስዶዋል:: ህወሃት (ለራሱና ለቢዝነስ ኢምፓየሩ ሲልም ቢሆን) በአብዮታዊ ዲሞክራሲና በልማታዊ መንግስት ስም ዘግቶ ይዞት የነበረውን ርዕዮት ማስለወጥና ፕራይቬታይዜሽንን ተግባራዊ ማስደረግ ይፈልጉ ነበር::ነገር ግን ኢህአዴግ "ይህ የሚሆነው በኢህአዴግ መቃብር ላይ ነው!" የሚል ቁርጥ ያለ አቁዋም ይዞ በድርቅናው ቀጥሎ ነበር የቆየው::
አሜሪካና እንግሊዝ ደግሞ ይህን ጉዳይ የግድ ተግባራዊ ማድረግ ነበረባቸውና ህወሃት መራሹን ኢህአዴግንና የፕራይቬታይዜሽንን ጉዳይ ዘግቶ የያዘባቸውን የቢዝነስ ኢምፓየር ኤፈርትን ጥለው በኢህአዴግ መቃብር ላይ ብልጽግናን ተክተዋል::
በብልጽግና አማካኝነትም የቴሌኮሙን ዘርፍ የመቆጣጠር የረጅም ጊዜ ፍላጎትና ህልማቸውን በትላንትናው ዕለት አሳክተዋል::(የቴሌ ኮም ዘርፍ ሲባል የስልክና የኢንተርኔት ዘርፍ ብቻ ማለት ለሚመስላቸው የዋህ ዜጎች እንደዚያ ማለት እንዳልሆነ ወደፊት በስፋት ለማስረዳት ይሞከራል) እናም ያ የአሜሪካና የእንግሊዝ የቀደመ ህልማቸው ዛሬ ተሳክቶ የቴሌኮሙን ዘርፍ እንግሊዝና አሜሪካ በቁጥጥር ስር አውለውታል ወይም ገዝተውታል::
ወይም የመጠቅለል ጅምራቸውን በፓርላማ አስጸድቀው ዘርፉን በበላይነት ይዘውታል::
ሁኔታው ከኢትዮጵያ ጋር የተያያዘ እንዲመስልና ዘርፉ ከኢትዮጵያ መንግስት እጅ እየወጣ እንደሆነ እንዳናስብም ከ24 ሰዓት በፊት በሰየሙት አዲስ ስያሜ "Global partnership for ethiopia" ከሚለው አዲስ ስያሜ ጋር አገናኝተው የዘርፉን ሽያጭ ጨረታ ያሸነፉትን አካላት ይፋ አድርገዋል::”አሜሪካና እንግሊዝ የኢትዮጵያን የቴሌኮም ዘርፍ ገዙት” ከማለት ይልቅም በዚህ መንገድ አጨናብሮ መግለጹ የተሻለ እንደሚሆን ያውቃሉና ዜናውን በዚያ መንገድ ነው ይፋ ያደረጉት::
ዞሮ ዞሮ ግን Vodafone, Vodacom safari com, sumitomo corporation,and CDC group ሄድ ካርተራቸውን የተለያዩ አገራት ያድርጉ እንጂ የሁሉም ተቁዋማት መስራችና ዋና ባለቤት እንግሊዝና አሜሪካ ናቸው::የቴሌኮሙ ዘርፍ የተሰጠውም ለእነርሱ ነው::
ይህ በመሆኑም አሜሪካና እንግሊዝ ደስታቸው ወደር የለሽ ሆኖዋል:: የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚ/ርም ከእነሱ በላይ በደስታ ጮቤ መርገጡን ገልጾዋል:: ለ1.5 ሚሊዮን ዜጎች የስራ ዕድል ይፈጥራል, 8 ቢሊዮን ዶላር ኢንቨስት ማድረግ ይችላል, 850 ሚሊዮን ዶላር ጨረታውን አሸንፎዋል,ወዘተ የሚለውን ዜናም ለ "መጡልን" ባዮች አብስረዋል::ለ"መጡብን" ባዮች አርድተዋል::
ህዝቤ ደግሞ "አሜሪካ በኢትዮጵያ ባለስልጣናት ላይ የጉዞ እቀባ ልታደርግ ነው"
"አሜሪካ በኢትዮጵያ ላይ የኢኮኖሚ ማዕቀብ ልትጥል ነው"
"በፍርሃት ኢምባሲዎቻቸውን ዘግተው ዋሉ...
"አሜሪካ ተላላኪዋ ህወሃት ስለወደቀባት ተበሳጭታ የኢትዮጵያን መንግስት ጠምዳ ይዛዋለች...የቀድሞ ወዳጁዋ የህወህት መውደቅ አበሳጭቶዋት... የመንግስት ህግ የማስከበር ዘመቻ ከንክኖዋት ጥምድ አድርጋ ይዛናለች... ይቺን መሰሪ ሰልፍ እንወጣባታለን... ባንዲራዋንም በአደባባይ እናቃጥልባታለን..." ምናምን የሚል ሌላ ጫዋታ ውስጥ ነው::
ብዙሃኑ ኢትዮጵያዊ ይህን አይነቱን ሰበር ዜና በመሰባበር ላይ ነው!
በትናንትናው ዕለት በተወካዮቹ አማካኝነት" ተስማምቻለሁ ይሁን" ብሎ ስለፈረመበት ጉዳይ ግን ምንም የገባው ነገር የለም!
ህዝቡ እንዲህ ይነሆልል ዘንድም እነርሱ ብቻ ሳይሆኑ አፈቀላጤው መሪ ተብየ መድረክ እያመቻቸ "ማንም እንደፈለገ የማያዘን አገራችንን ቁርስ ይህን ብይ እራት ምን በላሽ ይሄን ቀሚስ ልበሽ...የሚሉን ሉዓላዊነታችን ያልገባቸው የአባቶቻችን ልጆች መሆናችንን ያልተረዱ..." እያለ የሃሰት ዛቻውን እያንበለበለ በመፎተት የግርዶሹን ቀዳዳ ይደፋፍን ነበር::
በተቀደደለት ቦይ መፍሰስ...የሚለው ጉዳይ በዚህ መንገድም ይገለጻል ለማለት ነው...::
ዲጂታል ሲስተም ውስጥ ከመግባት ጋር ተያይዘው የሚነሱ ዘርፈ ብዙ ነገሮችን ወደፊት በስፋት የምናያቸው ይሆናል::
እስከዚያ ድረስ ሊንኮቹን ተጭናችሁ እነዚህን 4 ትረካዎች እያደመጣችሁ ቆዩ::
https://youtu.be/SwvgH5TjbSA

https://youtu.be/2aeHXa32gBE

https://youtu.be/Zie4wh8550Y

https://youtu.be/Tnz0kEWE1Ig
በዚህ የፌስቡክ ገጽ ከሚቀርቡ ጽሁፎች ጋር ተያያዥነት ያላቸው ሃሳቦች የሚተረኩበት ቻናል ነውና የዚህ ገጽ ተከታዮች ቻናሉን ሰብስክራይብ ብታደርጉለት መልካም መሆኑን እጠቁማለሁ::መልዕክቱንም አስተላልፌያለሁ::
https://www.youtube.com/channel/UCpNPc78FhPGSXhAVVh_jQuA
በነገራችን ላይ ለሀገራቸው ሉዓላዊነት ታቦት አስከትለው የተጋደሉን አባቶቻችን
እነርሱን በጨቋኝነት ፈርጆ፣ ሰንደቃቸውን አግዶ፣ መንግሥታቸውን በዘረኝነት
ፈረካክሶ፣ ልጆቻቸውን (ሕዝብን) ሀገር አልባ በማድረግ በማንነታቸው እያሳደደ
የሚጨፈጭፈ አገዛዝ ፋሺስቶችን ለታገሉ አርበኞች አያቶቻችን ባንዳ ማለት እርሱ
ነው። በባንዳ ዓይን ደግሞ ጀግና ከባንዳ ይቆጠራል። ስለዚኽም ከአርበኞች
አያቶቻችን የወገነ በባንዳዎች ዘንድ እንደ ባንዳ መታየቱ አይቀሬ ነው። እኔ ግን
እግዚአብሔርን ያባቶቼን ሉዓላዊ ማንነት ከነታሪካቸው በልቤ ስላነገሠው
አመሰግነዋለሁ።


ተድላ መላኩ

@ethiopianissm
@ethiopianissm
@ethiopianissm
በየዕለቱ ስንሰማ ቆይተናል::አሁንም እየሰማን ነው ወደፊትም እንሰማለን::
ታዲያ ምንም አይነት የመደደር ፍንጭ በቤለበት "መደመር" የሚሉን ምኑን ነው?
የመደመርን መንግስታዊ ፍቺ እና ትክክለኛ ትርጉም በየት በኩል እናግኘው?ይህን መንግስታዊ ቃል በየትኛው ገጽታው ምን ብለን እንፍታው?
አገሪቱና ህዝቡ ከመደመር ጋር ጨርሶ ግንኙነት በሌላቸው ይልቁንም ተቃራኒ በሆኑ አስከፊ መንገዶች እየሄዱና እየፈረሱ ባሉበት ሁኔታ ውስጥ እንዳለን እየታወቀ እንዴት ነው በመንግስት ደረጃ በየዕለቱ ስለ መደመር ያለሃፍረት የሚቀነቀነው? ሰውየው በርግጥ መደመር ሲል ምን ማለቱ ነው? እያልን ማለቂያ የለሽ ጥያቄዎችን ብንጠይቅ ከበቀቀኖች በኩል በቂ አሳማኝና ትክክለኛ ምላሹን ማግኘት አንችልም::
በጥቅሉ ሰውየው ስላለው ብቻ እንዲሁ መደመር... መደመር... መደመር.... ተባለ እንጂ ትክክለኛ ትርጉሙ ወይም ዕቅድና አፈጻጸሙ ለማንም ግልጽ አይደለም!
ከለውጡ ጋር አብሮ መንግስታዊ ሆኖ የመጣው ይህ "መደመር" የሚል ቃል እንደ አንድ የፖለቲካ ፍልስፍና ተቆጥሮ በመንግስት ደረጃ ገና ከጅምሩ ነው መቀንቀን የጀመረው::እንዴት ሊቀነቀን ቻለ? መደመር የሚለው ቃልም በሉት ፖለቲካዊ ፍልስፍና በሁሉም ዜጎች ዘንድ እንዲሰርጽና እንዲቀነቀን የተፈለገው ለምንድነው?
የዚህን ጥያቄ ምላሽ ውስን የብልጽግና ባለስልጣናት ብቻ ያውቁታል::ወይም እንዲያውቁት ተደርጎዋል:: ሌሎቹ ግን በግምታዊ ጥሬ ትርጉሙ እንጂ ዋና ትርጉሙን አያውቁትም:: ብዙዎቻችም በተመሳሳይ ግምት ውስጥ ያለን ነን::
የብዙዎቻችን ግምትም ከላይ እንደተባለው "መደመር" ማለት ከፍቅርና ከመስማማት ጋር የተያያዘ ዜጎች በጋራ ሆነው በሰላም እንዲኖሩ ያለመ, በጥቅሉ ከአንድነትና ከህብረት ጋር የተያያዘ ለአገሪቱና ለዜጎች ጠቃሚ መሆኑ ታምኖነትና ታስቦበት የተመረጠ ቃል እንደሆነ ብቻ ነው::ከዚህ ግምታዊ ትጉም ውጪ በሌላ ገጽታው ተተርጉሞ የምናገኘው በሳጥናኤል ጎል መጽሃፍ ነው::
"መደመር" ሌላ ተራ የመሰለ ነገር ግን ተራ ያልሆነ ድብቅና ረቂቅ ዓለም አቀፍ ትርጉም እንዳለው ቃሉ መንግስታዊ ቃል ሆኖ ከመምጣቱ በፊት ምን ማለት እንደሆነ በ2007 ዓ.ም በወጣው በሳጥናኤል ጎል ኢትዮጵያ ቁጥር 1 ላይ የተገለጸ ሲሆን; ቃሉ መንግስትዊ ሆኖ ከመጣ በሁዋላ ደግሞ በቁጥር 4 ቱ መጽሃፍ ውስጥ የመደመር ትርጉም በሰፊው ተብራርቶ እናገኛለን::
በዚህ መጽሃፍ ውስጥ የመደመር ፍልስፍና እና አጠቃላይ የፍልስፍናው ጥግ ከእነመዳረሻው በብዙ ገጾች ተብራርቶዋል::
በአገርና በመንግስት ደረጃ ፖሊሲ ቀርጸው የሚንቀሳቀሱት "የርጉሙ ስልጣኔ አራማጆች" ይህን ቃል ለምን እንደሚጠቀሙበትና ለምን ሲጠቀሙበት እንደኖሩ: እንዲሁም "ትክክለኛ ትርጉም" ብለው ያስቀመጡት ፍቺ አለ:: ብልጽግና እየተጉዋዘበት ያለው ወይም በተግባር እየተረጎመው ያለውም በዚህ መጽሃፍ ከተገለጸው ትርጉም ጋር የሚጣጣም ነው::ስለዚህ ብልጽግና የራሱን ትርጉም በተግባር አሳይቶ የመደመርን ፍልስፍና ትክክለኛ ትርጉም እስኪያሳውቀን ወይም እስኪያሳየን ድረስ ይህንኑ ትርጉም ይዘን ከመቆየት ውጪ ሌላ ምርጫ ያለን አይመስልም..::
ወይም አሳማኝ የሆነ የተብራራ ምላሽ ማግኘት አንችልም::
በእነርሱ ስያሜና ቀመር ወይም የቃል ፍቺ ስንሄድ "የብልጽግና ጸር" ብለው ለይተው ያስቀመጡትን ሐይማኖትን እና "ሁዋላ ቀር" ብለው የሰየሙትን ሐይማኖተኛውን ህዝብ ወደ ክፉው መንፈስ አለቃቸው መደመር, ድፍን የአገሪቱን ህዝብ ወደ እርሱ መጨመር, የሐይማኖት ተቁዋማትንና ሐይማኖተኛውን ህዝብ ጠቅልሎ ለእርሱ ማስረከብ...አገሪቱንና ህዝቡን በዲጂታሉም በምኑም ተጠቅሞ ወደ እርሱ ክብ ማስገባትና ወደ እርሱ መጨመር...በእርሱ ዓላማ ክብ ውስጥ እንዲሆኑ ማድረግ, ጠቅልሎ ለእርሱ ማስረከብ, ለእርሱ ማስገዛት... ወደ እርሱ መደመር... የሚል ጥልቅና ሰፊ ትርጉም ያለው የግሎባሊዝም መደምደምደሚያ የሆነ መሰሪ ቀመርን እና እኩይ ዕቅዶችን በውስጡ የያዘ ቃል እንደሆነ ነው የምንረዳው::
ይህንን ነው "በመረጡትና ይሻለናል, ይመጥናል, በህዝቡ ዘንድ ጥያቄ አያስነሳም ብለው የሚያስቡትን ያሻቸውን አቻ የአማርኛ ትርጉም ፈልገው በአገሪቱ ህዝብ ዘንድ ያስርጹት.... በቃል ብቻም ሳይሆን በተግባር በአገሪቱ ላይ በመንግስት ደረጃ ያራምዱት...,የእኛ ጥንታዊ መነሻ ርዕዮት ግን ይህ ነው! መድረሻውም ይህ ነው! calculator!” (666)
ተብሎ የተሰጣቸውን የተልዕኮ ርዕዮት ነው "መደመር" ብለው ተርጉመው የተነሱት! ተነስተውም "መደመር" እያሉ እያደነቆሩን የሚገኙት!
ስለዚህ "መደመር" 7ኛው ንጉስ እንደሚለው በሻሻ እያለ በአእምሮው ይመላለስበት የነበረ ቃል ሳይሆን ሌላ ሚስጥር ያለው ነው::መደመር አገር በቀል ቃል አይደለም:: በሻሻ ላይ የተብሰለሰለ ጽንሰአሳብ አይደለም::የአገር ውስጥ ፖለቲከኞቻችን አስበውበትና ፈልገውት ለአገሪቱና ለህዝቦቹዋ የተሻለ ነገር ለማምጣት ብለው የመረጡት ቃል አይደለም::የአገር ውስጥ ፖለቲከኞቻችን የግል ፍልስፍናና ፍላጎትም አይደለም!
በዚህ መጽሃፍ እንደተገለጸው ከሆነ የ"መደመር" ፍልስፍና ለአዲሱ ፓርቲ ባለስልጣናት በኅያላኑ የተሰጣቸው የተልዕኮ ስያሜ ነው::
ፍልስፍናውም በውስጡ በርካታና ዘርፈ ብዙ የሆኑ እኩይ ዓላማዎችን የሰነቀ ነው::መንግስታዊ አፈጻጸሙም በተንኮል በሴራና በፖለቲካዊ ሸፍጥ ብቻ የታጀለ ረቂቅ አካሄድን የሚጠይቅ ነው:: መስለው ሳይሆን ሆነው እየተወኑ የሚተገብሩት ነው! ለአገርና ለህዝብ በማይጠቅሙ በውስጡ በያዛቸው ውስብስብና ኢ-ተገቢ በሆኑ ፖለቲካዊ አጀንዳዎች አማካኝነትም ወደፊት በመደመር መርህ መነሻነት ብዙ እኩይ ተግባራት በአገሪቱ ውስጥ በመንግስት ደረጃ ሲፈጸሙ እናያለን:: ወይም ልናይ እንችላለን::
ስለዚህ እንደዚያ ላሉት ነገሮች ስነልቦናችንን ከማዘጋጀት ጎን ለጎን ቃሉን በዚህ ትክክለኛ ምናልባትም ብቸኛ ትርጉሙ በኩል አውቀነው ብንቆይ የተሻለ ነውና ቢጠቅማችሁም ባይጠቅማችሁም ትክክለኛ ትርጉም ብለው ያስቀመጡን ያዙት እወቁት ለማለት ነው::
አብዛኞቻችሁ የዚህ ገጽ ተከታዮች ከ Calculator እስከ Vaccination (ሁለቱም 666 ማለት ነው)ብዙ ተብላችሁዋልና ሁኔታው በቀላሉ ግልጽ እንደሚሆንላችሁ ተስፋ አለኝ:: ቃሉ የኢትዮጵያ የፖለቲካ ርዕዮት ሆኖ መቀንቀን ከመጀመሩ ከዓመታት በፊት "መደመር" የሚለው የቃሉ ትርጉምና የቀመሩ መዳረሻ ከሌሎች ዝርዝር የቃል ቀመሮች ጋር ቀድሞ ይፋ ስለተደረገላችሁ ማለቴ ነው::
ቢሆንም ግን የመደመርን ትክክለኛ ትርጉም ከራሳቸው ገለጻ መረዳትና አዳዲሶቹ ኢ/ዊ ባለስልጣናት ሊያምኑት በሚከብድ መንገድ የደም ቃል ኪዳን ፈጽመው የመጡበት ርዕዮት እንደሆነ ደግሞ ደጋግሞ ማስታወስ ያስፈልጋልና ሙሉ ትንታኔያቸውን በትኩረት አንብቡት:: ከፊል ትረካውንም በትኩረት አድምጡት::
https://youtu.be/2aeHXa32gBE
ብዙዎች ዜናውን ብቻ ሰምተው ምንም ሳይመስላቸው በዝምታ አልፈውታል:: ለነገሩ ዝም አንልም ብንልም ምንም ስለማናመጣ ዝም ከማለት ውጭ ምንም ምርጫ የለምና ዝምታው አይገርምም::
አሜሪካና የእንግሊዝ የረጅም ዘመን ህልማቸው እውን ሆኖላቸዋል! በብቸኝነት ቀርታ የነበረችውን ኢትዮጵያ ሙሉ በሙሉ በቁጥጥር ስር አድርገዋል! በነገራችን ላይ 850 ሚሊዮን ዶላሩ ፈቃዱን ያገኙበት ገንዘብ ነው::የውል ወረቀቱን ለመያዝ ብቻ የከፈሉት ዶላር ነው:: ይህ ትንሽ ገንዘብ የፈቃድ ወረቀቱን በፓርላማ ያስጸደቁበት ገንዘብ ብቻ እንጂ ሌላ አይደለም:: በሌላ አገላለጽ አሜሪካና እንግሊዝ በወኪሎቻቸው አማካኝነት ለመጫረት ያስያዙት 1% ሲፒኦ እንደ ማለት ነው:: እናም ጨረታውን አሸንፈዋል ህጋዊ ፈቃዱን ይዘዋል:: ስለዚህ የቴሌኮሙ ዘርፍ ባለቤት ሆነዋል::
ወደ ዋናው ስራቸው ሲገቡ በመጀመሪያው ዙር ብቻ በመቶ ቢሊዮን ዶላር ደረጃ የሚከናውን ስራ ነው የሚጠብቃቸው:: ኢትዮ ቴሌ ኮም ደግሞ ከእነሱ ጋር በምንም መንገድ ተወዳዳሪ መሆን ስለማይችል ስራ በጀመሩ ማግስት ቀረ የሚባል የ % ድርሻ ካለው ሳይወድ በግዱ ፈጥኖ ያስረከባል ሙሉ በሙሉ ዘርፉን ይጠቀልሉታል::
***
ብዙሃኑ ኢትዮጵያዊ የቴሌኮም ዘርፍ ሲባል ስልክንና ኢንተርኔትን ብቻ የሚመለከት ጉዳይ ሊመስለው ይችላል::ነገር ግን እንደዚያ ማለት ብቻ አይደለም::
የቴሌኮም ዘርፍ ፋይናንሱንም ደህንነቱንም ባህሉንም ሐይማኖቱንም ልማድና የአኑዋዋር ዘይቤውን አጠቃላይ አገራዊ እሴትን ጨምሮ ሁሉንም ዘርፎች መጠቅለል የሚችልና አገሪቱንና ህዝቡን በቁጥጥሩ ስር አድርጎ የሚቀጥል ነው:: በእንግሊዝና በአሜሪካ የተፈረመው ይህ ውል ከድሮው ከውጫሌ ውል የከፋ ነው::ቀጥተኛ ቅኝ ግዛት ነው::
ምናልባት ርካሽና ነጻ ዳታ ስለሚሰጡ ሽልማት ወዘተ...ስለሚኖረው በጣም ደስ የሚለው ዜጋ ይበዛ ይሆናል::በውድ ገንዘብ ዳታ ገዝቶ የብልግና ፊልም ለሚያውርድ ዜጋ ነጻ ሲሆንለት እንዴት እንደሚደሰት ማሰብ ነው:: ብቻ ግን ጉዳዩ ከምንለውና ከምናስበው በላይ አደገኛ ነው! አደገኛ ስለሆነ እናስቁመው ለማለት አይደለም::ቢያንስ ግን ምን እየተከናወነ እንዳለ ተረዱ ለማለት ነው:: አሜሪካና እንግሊዝ ክኢትዮጵያ ጋር የተጣሉ መስለው ስለ ማዕቀብ ስለ ወዘተ... አውቀው ሲያወሩና ሲያስወሩ የነበረው ይች ጉዳይ ዳር እስክትደርስ ድረስ ብቻ ነበር ብል ያጋገንኩ እንዳይምስላችሁ! እነ አብይ አህመድና መሰሎቹ ከአሜሪካ ጋር የተጣሉ መስለው አንበረከክም ሉዓላዊነታችን አሳልፈን አንሰጥም... ወዘተ...በሚል አሜሪካን እየሰደቡ ነገር ግን በጎን በቴሌኮም ዘርፍ ስም ቀለል አድርገው ሁሉንም ዘርፍ ለአሜሪካ እንደሸጡ በርግጥ መታወቅ አለበት! በዚህም ትልቁን ተልዕኮዋቸውን ፈጽመዋል! አገሪቱን በዲጂታል ስም ቅኝ ለሚገዙት አካላት አስረክበዋል::ከዚህ በሁዋላ ያለው ነገር ቀላል ነው!ምክንያቱም ሁሉም ነገር በቴሌኮም ዘርፍ ይከናወናልና....
ዛሬ ላይ ሆናችሁ ስታነቡት የተጋነነና ምንም የማይገናኝ ገለጻ ሊመስላችሁ ይችላል:: ነገር ግን ወደፊት ራሳችሁን ቴሌኮም ዘርፉ ላይ ስታገኙት ታምናላችሁ:: ሐይማኖት ባህል ወግ ልማድ ሃብት ንብረት አጠቃላይ ነገራችሁን ቴሌኮም ዘርፍ ውስጥ ስታገኙት ምናልባት በዚህ ገለጻ ልትስማሙ ትችላላችሁ:: እኛ ምን እንደሸጥን እነሱ ምን እንደገዙ ትረዳላችሁ::
ለማንኛውም ለምልምሎች ከተሰጡ ተልዕኮዎች ውስጥ አንዱ ይህ ነበርና ተፈጻሚ ሆኖዋል::
ይህ በእንዲህ እንዳለም የቴሌኮሙ ዘርፍ ስለመሸጡም ሆና ከተሸጠ በሁዋላ አሜሪካና እንግሊዝ በዚህ ዘርፍ ብቻ የኢትዮጵያውያንን ባህል ሀይማኖት ወግ ልማድ ስርዓት እንዴት እንደሚሸረሽሩበት እንዴት ዓላማቸውን እንደሚያሰርጹበት ወዘተ... በጥቅሉ በዚህ ዘርፍ ብቻ ምን ምን አይነት ወሳኝ ተግባር መፈጸም እንደሚችሉ የተገለጸባቸውን የሳጥናኤል ጎል ኢትዮጵያ ቁጥር 3 እና ቁጥር 4 መጽሃፍት ገልጣችሁ ማየት ትችላላችሁ!
የውስጥ ጦርነቱም ሆነ ሌላው ሌላው ነገር እንዲሁም የኢትዮጵያ ጉዳይ በቀጥታ የG 20 እና የ G የ 7 አገራት አጀንዳ መሆን የጀመረበትን አጠቃላይ ምክንያትም በቁጥር 1 እና በቁጥር 2 መጻህፍ መገንዘብ ትችላላችሁ!
እነዚህን የሳጥናኤል ጎል ኢትዮጵያ የሚሉትን ተከታታይ መጽህፍት እንድታነቡዋቸው ደጋግሜ ለመጠቆም የሞከርኩትም ይህን የመሳሰለውን ጉዳይ በደንብ እንድትረዱት በመፈለግ ብቻ ነው::እንዳውም እየተሳቀቅሁና የመጽሃፍ ማስታወቂያ መስራት ማለት እየመሰለኝ ደጋግሜ አንብቡዋቸው አንብቡዋቸው እያልኩ አልጎተጎትኩም:: አሁን ግን እኔ ከምሞነጫጭረው ይልቅ እነዚህ መጽሃፍት ሁሉንም ነገር ይገልጻሉና አንብቡዋቸው! የሚል ጉትጎታየን መቀጠሌ ነው! ስለዚህ አንብቡዋቸው...!
ደግሞም አስታውሱ...ይህ ሁሉ የየዘርፉ ከበባም ሆነ ሌላው ሌላው ነገር በኢትዮጵያ ምድር ከመከናወኑና ከመሆኑ በፊት እንዲህ እንደሚሆን ቀድመው የነገሩን መጻህፍት ናቸው::ስለዚህ አንብቡዋቸው! ቢያሳምኑዋችሁም ባያሳምኑዋችሁም አንብቡዋቸው!ባይጠቅሙዋችሁም አይጎዱዋችሁምና አንብቡዋቸው እላለሁ::
በተረፈ አዳዲሶቹ ባለስልጣናት አውቀው ሲያብሉ እንጂ ከአሜሪካ ጋር አልተጣሉም!ስድባቸውም ሆነ የአንበረከክም ዛቻቸው የውሸት ነው! አብይም ሆነ ሽመልስ አዳነችም ሆነች ሌላው ባለስልጣን አሜሪካን ጠንከር ባለ ንግግር ደፍረው መሳፈጣቸው አይደለም! በራሳቸው በኩል "በሉ" የተባሉትን ማለታቸው ነው! ምክንያቱም የተጋጩና የማይግባቡ መስለው ዋና ዋና ስራቸውን በፍጥነት መስራት የተልዕኮዋቸው አንድ አካል ስለሆነ ነው! ይህን ጉዳይ በሚመለከት ማለትም የምልምል ባለስልጣናቱን ተልዕኮ የሚመለከተውንና የተጋጩና የማይግባቡ መስለው ነገር ግን እንዴት ተናብበው እንደሚሰሩ የተገለጸበትን የቁጥር 3 እና የቁጥር 4 መጽሃፍ ክፍል ገልጣችሁ ማየትና ከተግባራቸው ጋር አገናዝባችሁ ማረጋገጥ ትችላላችሁ::
መጽሃፍቱን በሃርድ ኮፒ ማግኘት ያልቻላችሁ ኢትዮጵያውያንም በትረካ መልክ እንድታገኙዋቸው እየተሞከረ ነውና ወደፊት ከታች በተቀመጠው አዲስ ቻናል የሚለቀቅላችሁ ይሆናል::
https://youtube.com/channel/UCpNPc78FhPGSXhAVVh_jQuA
ለጊዜው ግን መስለው ሳይሆን ሆነው የሚተውኑትን ኢ/ዊ ባለስልጣናቱን በሚመለከት የተልዕኮዋቸው ሙሉ ይዘትና ባለስልጣናቱ የገቡት ቃል በቁጥር 4ቱ በሰፊው ተገልጾዋልና በትረካ መልክ የቀረበውን ከፊል ገለጻ በዚሁ ሊንክ ገብታችሁ ለማድመጥ ሞክሩ::
https://youtube.com/channel/UCpNPc78FhPGSXhAVVh_jQuA
ሰበር ዜና !!

… የሰብዓዊ መብት ተሟጋቹ፣ የባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ሊቀመንበር እና የአዲስ አበባ ምክርቤት ዕጩ ተወዳዳሪው ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ህይወቱ አደጋ ላይ መውደቋን የደረሰኝ መረጃ አመልክቷል።

… የፍርድ ቤቱ የእስክንድርን በምርጫው መሳተፍ ውሳኔና በእስክንድር የተጻፈውን " ድል ለዲሞክራሲ" መጽሐፍ መታተም ተከትሎ በዶር ዐቢይ አሕመድ ጓደኛ በዐቃቤ ሕግ ሹሙ በዶር ጢሞቴዎስ ቀጥተኛ ትዕዛዝ እስክንድር ቀድሞ ከታሰረበት ዞን አሁን ወደሚገኝበትና ለህይወቱም ለጤንነቱም አስጊ ወደሆነው ዞን በግዳጅ እንዲቀየር መደረጉ ነው የተሰማው።

… ከውስጥ ከፖሊሶች የደረሰኝን መረጃ ሌሎች ሰዎች ራሱ እስክንድርን አነጋግረው እንዲያረጋግጡልኝ ያደረግኩ ሲሆን እስክንድርም እውነታውን እንዳረጋገጠላቸው በአካል የጠየቁት ወገኖች አረጋግጠውልኛል። እናንተም የምትችሉ በነገው ዕለት በመሄድ ማረጋገጥ ትችላላችሁ።

… እስክንድር ተቀይሮ በታሰረበት ዞን " የድብደባ ሙከራ" ተደርጎበት እንደነበር እና በታራሚዎች ርብርብ ድብደባው ለጊዜው መክሸፉ ተረጋግጧል። "ህወሓት በህዝብ እንድትጠላ ካደረጉት ሰዎች መካከል ቀንደኛው ሰው አንተ ነህ" የሚሉ የህወሓት አባል እስረኞች ናቸው አሉ የግድያና የድብደባ ሙከራ አድራጊዎቹ።

… እስከዛሬ ሲታሰር እና ሲፈታ የኖረው እስክንድር አሁን እነ ዶር ዐቢይ ከነበረበት ዞን ቀይረው ካስመጡት በኋላ የጤንነቱ ሁኔታም አሳሳቢ እንደሆነና በተለይ ዛሬ የጠየቁት ሰዎች " ብርድ ሳይመታው" እንዳልቀረም ተናግረዋል።

… ዝርዝር መረጃውን የምመለስበት ቢሆንም ለጊዜው ዶር ዐቢይ አሕመድ… ዶር ጢሞቴዎስ ጌዲዮን ምክንትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች እና የእስክንድር ለምርጫ ይወዳደር ዘንድ በፍርድበት ውሳኔ ከተሰማ በኋላ ወዶገቦቹ የጠቅላዩ አማካሪ የኢዜማ መሪዎች ሁላችሁም ቆም ብላችሁ ደጋግማችሁ ብታስቡ መልካም ነው። እስክንድርን አሁን ከከተታችሁት ቅርቃር በጤናና በህይወቱም ላይ ችግር ከሚያስከትል የአደጋ ዞን በአስቸኳይ ብታወጡትም ይመከራል።

… ሰምታችኋል  !! 
"መኳንንት ከግብፅ ይመጣሉ፤
ኢትዮጵያ እጆችዋን ወደ እግዚአብሔር ትዘረጋለች።"
https://youtu.be/Qa3TU_47ZO8
ንስር አሞራ እስከ ሰባ ዓመት በሕይወት የመኖር ጸጋ ተሠጥቶታል፡፡ ነገር ግን ይህን 70 ዓመት የዕድሜ ፀጋን አጣጥሞ ለመኖር አርባኛ ዓመቱ ላይ በሕይወቱ ወሳኝ የሚባል ውሳኔን ማሳለፍ ይጠበቅበታል፡፡

ይኸውም ንስሩ 40ኛ ዓመት ዕድሜው ላይ እነዚያ እንደልብ የሚተጣጠፉት ጥፍሮቹ እንደ እንጨት ይደርቃሉ፡፡ ስል የነበረው መንቆሩም ወደ አንገቱ ይታጠፍና ምግቡን አድኖ እንዳይይዝ ያግደዋል፡፡ የገረጀፉት ላባዎቹም ከደረቱ ላይ ተጣብቀው የመብረር ሥራውን አስቸጋሪ ያደርጉበታል፡፡

በዚህ ወቅት ንስሩ ሁለት ወሳኝ አማራጮች ይጠብቁታል፡፡ አንድም ሞትን አሜን ብሎ መቀበል ወይም ደግሞ አንድ መቶ ሃምሳ ቀናት የሚፈጅን ፈታኝ የለውጥ ሂደት ማካሄድ፡፡ በለውጡ ሂደት ለማለፍ ከወሰነ ቀጣዮቹን ተግባራት መፈጸም ይጀምራል፡፡ በመጀመሪያ ንስሩ ከፍ ካለ አለታማ ተራራ ላይ ይወጣና የታጠፈውን መንቆሩንና ጥፍሮቹን ከአለቱ ጋር ደጋግሞ በመምታት ወልቀው እንዲወድቁ ያደርጋል፡፡

የገረረውና የታጠፈውን መንቆር እንዲሁም ጥፍሮቹን አውልቆ ከጣለ በኋላ ከስር የወጣው ሙሽራ መንቆርና ጥፍር እስኪጠነክር ድረስ ለቀናት ይታገሰዋል፡፡ መንቆሩና ጥፍሮቹ ከጠነከሩ በኋላ ቀጣይ የሚጠብቀው ተግባር የደረቁትና ከደረቱ ጋር ተጣብቀው ከመብረር ያገዱትን ላባዎች እየነጨ በማራገፍ በአዲስ እንዲተኩ ማድረግ ነው፡፡

ይህን እልህ አስጨራሽና አንድ መቶ ሃምሳ ቀናት ወይም አምስት ወራት የፈጀውን የለውጥ ጉዞ ካካሄደ በኋላ ዳግም ውልደቱን የሚያበስር ቀጣይ ሰላሳዎቹን ዓመታትም በትኩስ ኃይል ለመኖር የሚያስችል ለውጥ አደረገ ማለት ነው፡፡ በዚህ ሁኔታም የዳግም ውልደቱን በረራ ወደ ሰማይ በመምጠቅ ይጀምራል፡፡
👇
በሕይወት አሸናፊ ለመሆን እልህ አስጨራሹን ውጣ ውረድና የለውጥ ሂደት መታገስና ማለፍ ይጠይቃል❗️
📖 📖


@Gebre2323
እንቅልፍ አጥተን የምንጽፈው አክቲቪስት ሆነን "ለመደደብ" አይደለም!እንቅልፍ አጥተን የምንጽፈው ነብይ ለመባል አይደለም!በዚህ ዘመን "ነብይ" ተብሎ ከመወደስ "አብይ" ተብሎ መሰደብ ይሻላል! ነገር ግን ዕውነት አለ!ሰሚ ያጣ ዕውነት....!
ያን ዕውነት ለማስረዳት ነው ደፋ ቀና የምንለው!
ድሮ ድሮ "ጠማማ ትውልድ ምልክት ይሻል" ነበር የሚባለው!
ይህ ትውልድ ግን ምልክት እያየ እንኩዋን አያምንም! ታዲያ ምን እናድርግ?!
በመሰረቱ.....ይሳካላቸዋል አይሳካላቸውም የሚለውን እኛ አናውቅም::እነርሱ ግን አቅደዋል::እቅዳቸውንም ከሞላ ጎደል በተግባር እየሄዱበት ነው:: ባይሆን....ተማምነው የላኩዋቸው ገልቱዎች የቁራ መልዕክተኛ እየሆኑባቸው ተቸገሩ እንጂ እነ ሄርማን ኮኸን ያቀዱትን ከመፈጸም አልቦዘኑም::
እና የዘንድሮው ጦርነትም የዕቅዳቸው አንድ አካል ነበርና ባቀዱት መሰረት ጀምረውታል::ሲጀምሩትም በጀመሩበት ዕለት ለምን እንዳስጀመሩት ገልጸናል:: ለምን እንዳስጀመሩት ብቻ አይደለም:: መቸ እና እንዴት እንደሚያስቆሙትም በወቅቱ ነግረናል! አሁን እሱን ለመድገምና ያለፈ ነገርን እያስታወሱ እኝኝኝኝኝ..... ለማለት አይደለም::ከዚህ በሁዋላ ምን እንደሚቀጥል ከወዲሁ ለመንገር ጭምር ነው! ስለዚህ የተለጠፈበትን ቀን አይቶ መፍረድና ቀጣዩን የ ሲ አይ ኤ እና የዊንድሶውር ቤተመንግስት ምዕራፍም ከወዲሁ መገንዘብ ይቻላልና ስሙት!
በተለይ ሁለቱ ህዝቦች ስሙትና ተዘጋጁበት! ስሙት! እርም በልታችሁ ከምትቀሩ ስሙት...እኔ እንደሰማሁት.....!!

https://youtu.be/dIaAJtFJ51k

https://youtu.be/VI0NNMP15hI
አይቴ ብሔራ ለገነት

ኤደን ገነት ሀገሯ ወዴት ነው.. "?

ማሳሰቢያ፦
ብዙ ጊዜ እንዲህ አይነት ጥያቄወች ሲፈጠሩ አሳማኝ ዶክሜንቶች የሌላቸው የምሁራኑ ትንታኔ እንደ በቂ ማስረጃ ሆኖ ሙሉ በሙሉ ሊታመኑ አይገባም። ነገር ግን ይህ እውነትነቱ ያጋደለ ቢሆንም አንድ ማስረጃ እውነተኝነቱ የሚረጋገጠው የራሱ የሆኑ መንገዶችን ተከትሎ ነው።

ነገር ግን ከዚህ ቀደም በውስጥ መስመር የጠየቃችሁኝ በእንደ ዚህ አይነት እና መሰል ጉዳይ ላይ የምትሰሩ ፤ጥናትና መርምር የምታደርጉ፥ ለጥናታዊ ጽሁፍ የምትፈልጉ፥ በፊልም ሆነ በመጻህፍ ድርስት ሙያ ላይ ያላችሁ ቤተሰቦቸ የማቀርብላችሁ ጽሁፍ እንደ እርሾ ወይም እንደ መሰረት አድርጋችሁ በበለጠ ሰፋ አድርጋችሁ መመርመሩ እና ለስራወቻችሁ መጠቀሙ ተገቢ ነው የሚል ሀሳቤን ከወዲሁ ለግሻለሁ..... ።

| ታላቁ የሥነ ፍጥረት መጽሐፍ የሆነው መጽሐፈ አክሲማሮስ አዳም እና ሔዋት ተፈጥረው ሲኖሩበት የነበውን የኤደን ገነት ስፍራ የምድር አካል እንደሆነ ይጠቅሳል፤ ሌሎች የሥነ ፍጥረት አንድምታ መጽሐፍትም በዚሁ ይስማማሉ፤ ታዲያ እቺ የመሬት አካል የሆነች ኤደን ገነት የት ትገኛለች? ብለን መጠየቃችን አይቀሬ ነው፣ እናም ለዚህ ምላሽ አለን ብለው በተለያዩ አመታት የተነሱ ሊቃውንት መደምደሚያቸውን ወደ ሃገራችን ኢትዮጵያ አድርገው እንመለከታለን፤ ለአብነት እንኳ የአክሱም ጽዮኑ ንቡረ ዕድ ኤርሚያስ ወልደ እየሱስ፣ የሊቃውንት ጉባኤ ሰብሳቢ የነበሩት አለቃ አያሌው፣ መሪራስ አማን በላይ እና አባ ተስፋ ሥላሴ ሞገስን ማንሳት እንችላለን። እነዚህ ታላላቅ የሃገራችን ሊቃውንት ከመጽሐፍ ቅዱሱ ግዮን ኤደንን አጠጪ ከሆነው ወንዝ በመነሳት ኤደን ገነት ኢትዮጵያ ላይ ትገኛለች ይላሉ፤ እንደማጣቀሻ ያደረጉትም ግዮን ተብሎ በመጽሐፍ ቅዱስ የተጠቀሰው ወንዝ አባይ እንደሆነ በማመልከት ነው። የአክሱም ጽዮኑ ነቡረ ዕድ ኤርሚያስ አዳምና ሔዋን በኢትዮጵያ በሚል መጽሐፋቸው የመጀመሪያዎቹ የሰው ልጆች አዳምና ሔዋን በኢትዮጵያ ምድር ተፈጥረው በኢትዮጵያ ምድር ኖረው አረፈዋል ብለው በልበ ሙሉነት ይናገራሉ፤ አለቃ አያሌውም ተመሳሳይ ሃሳብን የኢትዮጵያ እምነት በሦስት ሕግጋት በተሰኘው መጽሐፋቸው አንጸባርቀውታል፤ አባ ተስፋ ሥላሴም ከBBC ጋር ባደረጉት ቆይታ " ማዕከለ ምድር ኢየሩሳሌም ነው ማለት ፍጹም ስህተት ነው፤ ማዕከለ ምድር የመሬት ወገብ ሲሆን የመሬት ወገብም የሚያቋርጠው ኢትዮጵያን ነው እንጂ ኢየሩሳሌምን አይደለም። እራሱ ሕያው አምላካችን በኦሪት ዘፍጥረት 2፥ 10 ላይ ከአራቱ ወንዞች አንዱ ግዮን ወይ ዓባይ የኢትዮጵያን ምድር ከቦ ያጠጣል በማለት ኤደን ገነት መሆኗን አረጋግጧል " በማለት ምላሻቸውን አቅርበዋል። በጣና ደስያት ላይ የሚገኙ አበው መነኮሳትም በዚህ ዙሪያ እንደሚናገሩት እቺው ኤደን ገነት የጣናን ሐይቅ ከብባ በከፍታ ላይ በብርሃን ተሞልታ በስውር ትታያለች ይላሉ፤ በየሳምንቱ እሁድ ከሰዓት በኋላም ከእርሷ የሚመጣ ከባድ ነፋስ በዳጋ እስጢፋኖስ ላይ ይነፍስበታል ይባላል። በቅርቡ ብቅ ማለት የጀመሩ ተመራማሪዎችም ሆኑ መንፈሳዊ ሰዎችም ታዲያ ስለዚህች ስፍራ ሳይናገሩ አላለፉም ለአብነትም በ2007 ታትሞ ለንባብ የበቃው የተክለ ኪዳን " የኢትዮጵያና የዓለም የመጨረሻ ፍርድ አፈጻጸም ውሳኔ " የሚለውን መጽሐፍ መጥቀስ ሲቻል ተክለ ኪዳን የሲኦልን፣ የገነትን፣ የማረፍያ ቦታን ስፍራዎች በሥዕላዊ መግለጫው ላይ ገነትን ከምድር ጋር አነካክቶ አስቀምጦታል፤ ሌላው በደራሲ ጤንነት ሰጠኝ ተጽፎ በ2004 ለንባብ የበቃው " ምስጢረ ሰማያት ምስጢረ ኢትዮጵያ ፍልስፍና " ደግሞ ገነት እራሷን ችላ ከመሬት የራቀች መሆኗን ይነግረናል።

እኔ በደሰኩት አሰሳና የታሪክ እይታ የማያሻማ እና በልበ ሙሉትን መናገር የምችልበት ተጨባጭ መረጃወቸን እንደ ሚከተለው አቀርባለሁ።

ኦሪት ዘ ፍትረት ምዕ3 ላይ አዳም ከ ገነት ከወጣ በኋላ ያለውን ሲያስረዳ
''ወአዘዞሙ ለሱራፌል ዘ ውስተ እዳዊሆሙ በውስተ ሰይፍ እሳት እንተ ትትመየጥ ከመ ይቀቡ ፍናወ እጸ ሕይወት ከመ ይባእ አዳም አቢሎ ውስተ ገነት''።
''አዳም ተደፋፍሮ ወደ ገነት እንዳይገባ እጸ ሕይወትንም እንዳይበላ እግዚአብሔር የገነትን ደጂ ይጠብቁ ዘንድ የምትገለባበጥ የእሳት ሰይፍ የያዙ ሱራፌልን በገነት ደጂ አስቀመጣቸው '' ይላል።
ይህ ማለት አዳም እና ሔዋን ምድር ላይ ሁነው ወደ ገነት ይገቡ ዘንድ በተደጋጋሚ ይመኙ እና ወደ በሯም ይቀርቡ ነበር ማለት ነው ስለዚህ ገነት ከምድር ላይ ሁኖ በእግር መግባት የምታስችል ቦታ ናት ማለት አይቻልምን?

ኦሪት ዘፍጥረት 2 : 10
ወንዝም ገነትን ያጠጣ ዘንድ ከዔድን ይወጣ ነበር፤ ከዚያም ለአራት ክፍል ይከፈል ነበር።
ይልና ገነትን ከሚያጠጧት አንዱን የእኛው አባይ ግዮን እንደሆን እዚሁ ምዕራፍ ላይ ቅዱሱ መጻህፍ ያስረዳል።
ታድያ ከምድር የመነጨው አባይ ገነትን ያጠጣል ካለ መጽሕፍ ቅዱስ ኤደን ገነት ምድር ላይ አይደለችምን?

ከጥንት የብራና መዛግብት አንዱ የሆነው ገድለ አዳም ዘ ሚያዚያ ላይ እንዲህ ይላል።

አዳም ከገነት ከተባረረ በኋላ ዳግመኛም አዳም በገነት በር ነበር.. የሚያብለጨልጭ የእሳት ሰይፍ በእጁ የያዘ ኪሩብን ተመለከተ የአዳምን ከገነት በር ላይ መቆም ተመልክቶ ኪሩብም ተቆጣ ፊቱንም ቋጠረበት አዳምና ሔዋንም ከእርሱ የተነሳ ፈሩ ይላል።

ገድለ አዳም ዘ ግንቦትም
አዳምና ሔዋን ገነትን ይፈለጉ ዘንድ ሄዱ በማለት ምድር ላይ ሁነው ገነትን ይፈልጉ እንደነበር ያስረዳል።

ታድያ መሬት ላይ ያለው አዳም ገነትን በእግሩ ተጉዞ ያገኛት ነበር ለማለት አያስችልም?

ሌላው ገድለ አዳም ዘ ሐምሌ'' ኪሩብም ከምዕራብ በር ቁሞ አዳምና ሔዋን ወደ ገነት እንዳይገቡ የገነት በር ይጠብቅ ነበር ሊገቡ ፈልገው በበር ላይ ቁመው ሳለ ያን ኪሩብም የሳት ሰይፍ ይዞ ሊገድላቸው መጣ፤ አዳምና ሔዋንም ወደቁ እንደ ሞተ ሰው ሆኑ ሌሎች የኪሩብ ሰራዊቶችም ገነትን ወደ ሚጠብቀዉ ኪሩብ ወደ መሬት ወረዱ ''ይላል።
መጨረሻ ላይ ያለችው ቃል ገነትን ወደ ሚጠብቀው ኪሩብ ወደ መሬት ወረዱ ማለቱ ገነት መሬት ላይ መሆኗን ያስረዳል።

አዳምና ሔዋን እንዳይገቡ ከበሩ ላይ ጠባቂ ካቆመ በእግራቸው ተጉዘው ገነት ይገባሉ ማለት ነው። ከመሬት ወደ ገነት በእግር መምጣት ካልተቻላቸው ስለምን ጠባቂ አስፈለገ?
በተደጋጋሚ እንገባለን እያሉ መላእክት ሊቀስፏቸው ስለሆነ እግዚአብሔር መንገዲቱን ሰውራት እንጂ ይገባ ነበር ይላሉ መተርጉማኑ።
ቅዱሱ ሊቁ አባ ጊዮርጊስ ሲተረጉምም ገነት ሰው ሂዶ በእግሩ የሚገባባት ሀገር ናት ይላሉ::

ታድያ ኤደን ገነት ምድር ላይ ከሆነች ገነትን የሚያጠጣው ወንዝ አባይ ወይም ግዮን እንደሆን ቅዱሱ መጻሕፍ ከነገርን እንደ ቅዱሱ ቃል ገነት ከየትኛው አህጉር ከየትኛውስ ሀገር ናት ?
አይቴ ብሔራ ለገነት?


ይህ ፈለገ ጥበባት ነው ያላችሁ ሃሳብ አስተያየት @Nabuti21 ላይ አድረሱኝ።
4/ 11/7513
HTML Embed Code:
2024/04/29 11:30:36
Back to Top