TG Telegram Group & Channel
ኢትዮጵ | United States America (US)
Create: Update:

የበረኸኞቹን የትንቢት ቃል
ለመስማት እንዘጋጅ።
*~★★~*

• እፎይ የእረፍት ጊዜዬን በሰላም ፈጸምኩ። እንደ ንስርም ታድሼ እንደ አንበሳ እያገሳሁ፣ እንደፈረደብኝ ደግሞ ልንጫጫብህ፣ ልሟገትህ፣ ነጭ ነጯንም ልግትህ ልመጣ ነኝ። ጠብቀኝ። ሰምተሃል።

#ETHIOPIA | ~ ዘንድሮ በ2013 እና በቀጣዩ በ2014 ዓም በዋናነት በኢትዮጵያችን የሚጠበቁ ዋና ዋና ክስተቶች ዓለሙ ሁሉ ይሰማው ዘንድ በበረኸኞቹ ተዘጋጁ ተብላችኋል። ለመስማት እንዘጋጅ። ሲጨንቅ።

•••
አስቀድሞ እንደተነገረ ቀጣዮቹ ሁለት ዓመታት “ለኢትዮጵያ የከባድ ምጥ ዓመታት” እንደሆኑ ተነገሯል። ከአንድ ዓመት በፊት ጀምሮ መጪዎቹ ሦስት ዓመታት ለኢትዮጵያ እጅግ አስጨናቂ ዓመታት ይሆናሉ ተብሎ በ2011 ዓም ማብቂያ ላይ በበረኸኞቹ የተነገረው ትንቢት ዓምና በ2012 ዓም ቃል በቃል መፈጸሙም ይታወሳል። በበረኸኞቹ ከተናገሩት የትንቢት ቃሎች አንዳችም የቀረ የለም። በሙሉ ተፈጽሟል።

•••
አምና ገና መስከረም ወር ላይ ዘንድሮ በ2012 ዓም ማለት ነው ምርጫ የሚባል ነገር በኢትዮጵያ የለም። አይደረግምም በማለት ለህዝቡ ሁሉ እነገር ዘንድ ያዘዙኝና የነገርኳችሁ የትንቢት ቃል በሙሉ ዓይናችን እያየ አንድ በአንድ መፈጸሙን ታስታውሳላችሁ። ይህንን የበረኸኞች ቃል በእኔ በኩል ላለመናገር የነበረብኝን ጭንቀትም መድኃኔዓለም ብቻ ነበር የሚያውቀው።

•••
መንግሥት የምርጫ ቀን ቆርጦና ወስኖ እያየሁ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች ክርክርና የምረጡኝ ቅስቀሳ ጀምረው እያየሁ፣ የአውሮጳ ኅብረትና የአማሪካ መንግሥት ለምርጫው ማስፈጸሚያ ገንዘብ ለግሰው ወደፊት ሲሉ እያየሁ፣ አገር ምድሩ ምርጫ ምርጫ እያለ ሲራወጥ እያየሁ እኔ ይህን የአባቶች ትንቢት በድፍረት “ ዘንድሮ ምርጫ የለም” ብሎ መናገሩን ፈርቼ ላለመናገር የተጨነቅኩትን ጭንቀት ፈጣሪዬ ብቻ ነበር የሚያውቀው። እነሱ ግን ዘመዴ ንገር ያልህን ንገር፣ አክሊለ ገብርኤል አትፍራ፣ መልእክቱ በአንተ በኩል ያልፍ ዘንድ የተፈቀደ ስለሆነ አትስጋ። ማን ያውቃል የኢትዮጵያን ትንሳኤ አብሳሪ ሆነህስ እንደሆን። ብቻ ራስህን እየመረመርክ ንገር። እኛ የምንልህን፣ የምንልክልህንም በራስህ የአገላለጽ ፀጋ ለህዝቡ ሁሉ ንገር ብለው ወጥረው ሰቅዘው ያዙኝ።

•••
ቀጠሉና የቻይናው የወፍ ጉንፋን የመሰለ ጉንፋን በኢትዮጵያም፣ በመላው ዓለምም ይከሰታል። የኢትዮጵያው ከአፋር በሚነሱ ወፎች አማካኝነት ነው የሚገባው። እሱንም ንገር አሉኝ። ነገርኳችሁ። ያው የሆነው ሁሉ ሆነ።

•••
በ2012 ዓም መንገዶች ሁሉ ይዘጋሉ። የዐቢይ ጾም ዘንድሮ አይጾምም። ዓለም ጭንቅ ትሆናለች በል አሉኝ። እሱንም ነገርኳችሁ። የሆነው ሁሉ ሆነ።

•••
በወርሃ መስከረም በትግራይ የመስቀለ ክርስቶስ ህንፃ ቤተ ክርስቲያን ተሠርቶ ፍጻሜውንም አግኝቶ ይመረቃል። የቤተ ክርስቲያኑ መሥራች የሆኑት አባ ዘወንጌል የተባሉ ደገኛ አባት ከቤተ ክርስቲያኑ ምርቃት ማግሥት እንደሚያርፉ፣ ከእረፍታቸው ማግስትም በኢትዮጵያ የኦርቶዶክሳውያን መከራ በከፋ ሁኔታ እንደሚጀምር፣ ብዙዎች በሰማዕትነት እንደሚያልፉ ንገር የተባልኩትንም የነገርኳችሁ። በ2011 ዓም በወርሃ ነሐሴና በወርሃ መስከረም በ2012 ዓም ነግረኳችሁ። የዚህ የበረኸኞቹ የትንቢት ቃልም በወርሃ ጥቅምት ከአባ ዘወንጌል ባረፉ በማግስቱ “ ዐቢይ አህመድ ወደ ራሺያ በሄደ ጊዜ፣ ጃዋር መሐመድ “ ተከበብኩ” የሚል ኮድ በመስጠቱ ምክንያት በኦሮሚያ ክልል ያሉ ንጹሐን ኦርቶዶክሳውያን የተዋሕዶ ልጆች እንደበግ ታረዱ፣ እንደ እባብም ተቀጠቀጡ። ይሄም ተፈጸመ።

•••
ዐቢይ ጾምም በቴሌቪዥን ተቀደሰ። ቤተ ክርስቲያን ተዘጋች። የዓለም ሀገራት የየብስም፣ የባህርም፣ የአየርም መንገዶችም ተዘጉ። ተጠረቀሙ። የኢትዮጵያ ምርጫም ከግንቦት 7 ወደ ነሐሴ 10 ተዘዋወረ። እኔ መደንገጥ ጀመርኩ። ቀጥሎ ወደ ነሐሴ 23 ተዘዋወረ። አሁንም ደነገጥኩ። የበረኸኞቹ ቃል ላይፈጸም ነውን ብዬም ሰጋሁ። በመጨረሻም ዐብይ አህመድና ብርቱካን ሚደቅሳ እግዚአብሔር ይስጣቸውና “ ዘንድሮ ምርጫ የለም።” ብለው ገላገሉኝ። እፎይ እንዴት እንደሚጨንቅ። የነቢየ እግዚአብሔር ዮናስ ጭንቀት የገባኝ ባለፈው ዓመት ነበር። መጻኢውን ዘመን ቁልጭ አድርገው አይተው የሚሆነውን፣ የሚፈጸመውን ሁሉ የሚነግሩን አባቶቻችን ግን ምንኛ የታደሉ ናቸው? ይደንቀኛል። ከምር ስለ እውነት ዝም ብሎ ይደንቀኛል። እንኳንም ኦርቶዶክስ ሆንኩኝ። እንኳንም የተዋሕዶ ልጅ ሆንኩኝ። እንኳንም ኢትዮጵያዊ ሆንኩኝ። ታድዬ።

•••
ዘንድሮም እንደተለመደው የበረኸኞቹ መልእክት መጥቷል። ለሁሉም እነግር ዘንድ መልእክቱ መጥቷል። የዘንድሮው ግን ጫን ያለ ነው። እንዴት አድርጌ እንደማቀርበው ሁላ ጨንቆኝ ብቻዬን መንበጫበጭ ከጀመርኩ 15 ቀናት አለፉኝ። አሁን ግን የግድ ነው። የትንቢቱ መፈጸሚያ ቀናት እየተቃረቡ ስለሆነ መንገሬ ግድ ነው። እናም ተዘጋጅታችሁ ጠብቁኝ። ለመስማት ራሳችሁን አዘጋጅታችሁ ጠብቁኝ።

•••
ምንአልባት ዛሬ ማታ ላይ በዩቲዩብ ቻናሌ ላይ ማድረግ ስላለብን ነገሮች አስቀድሜ ትዘጋጁ ዘንድ በመጠኑም ቢሆን የመግቢያ ቃል እነግራችኋለሁ። እናም እንደተለመደው፣ እንደወትሮው ሁሉ ልክ በተለመደው ሰዓታችን በዩቲዩብ ቻናሌ ላይ እንገናኝ።

•••
የሚነገረውን ቃል ሰምተህ የታዘዝከውን፣ የታዘዝሽውን የማትፈጽሚ የማትፈጽመውም ከሆነ መስማቱ ምንም አይጠቅማችሁም። የበረኸኞቹ ቃል የሚነገረው ሰምተው የትእዛዝ ቃሉን ለሚፈጽሙ ነው። የትንቢት ቃሉን ሰምተህ ስትጨነቅ፣ ስትጠበብ፣ ስታለቅስ ስታነባም የምትውል ቢሆን ምንም ዋጋ የለውም። አንዳንዶች ይሰማሉ፣ ያለቅሳሉ፣ ነገር ግን እንዲህች ብለው ንስሃ አይገቡም። እንደ ጠንቋይ ትንቢት ማድነቅ ብቻ ነው ሥራቸው።

•••
የሚሰሙ ብዙዎች ናቸው። የሠሙትን ተግብረው እንደቃሉ የሚኖሩ ግን ጥቂቶች ናቸው። ከካህናት ወገን፣ ከዲያቆናት ከመነኮሳት፣ ከመምህራን ከዘማርያን ወገን፣ ወንድም ሴትም ቢሆኑ አብዛኛው የኖህ ዘመን ስሜትና ጠባይ ነው ያለን። ፒፕሉ እንደሆን በሚሰማውም በሚያየውም ነገር ሁሉ ያሾፋል፣ ያላግጣል፣ ይቀልዳል፣ ብዙ ምስጢር የተከደነበት፣ የተዘጋበትም ነው። ኋላ ላይ ግን መርከቡ ከተዘጋ በኋላ፣ የንፍር ውኃው አንገቱ ጋር ሲደርስ ወደ መርከቧ ለመግባት፣ ይራወጣል፣ ይንፈራገጣልም። ጥቂቶች ግን ልባቸውን ከፍተው ይሰማሉ። ይወስናሉ። በመጨረሻም ይድናሉም። ይኸው ነው።

•••
“እንዲሁ ኋለኞች ፊተኞች፥ ፊተኞችም ኋለኞች ይሆናሉ፤ የተጠሩ ብዙዎች፥ የተመረጡ ግን ጥቂቶች ናቸውና።” ማቴ 20፥16

•••
ፌስቡክ ምክንያቱን ሳይነግረኝ በሰጠኝ ፔጅ ላይ እንዳልጽፍ ከልክሎኛል። ሙግት ላይም ነኝ። እኔን ብቻም አይደለም። ዲን አባይነህ ካሴንም በአንደኛው አካውንቱ እንዳይጽፍ አግዶታል። እናም ሁኔታውን፣ ድርጊቱን ስናጤነው ነገርየው ጤናማ አይመስልም። የሆነ በእኛ ላይ የተመደበ ፀረ ኦርቶዶክስ ሰውም በቦታው የተመደበ ይመስላል። ሆኖም ግን እኔ የምነግራችሁ ነገር ቢኖር ሰባክያኖችም የተለያዩ አማራጮቹን መጠቀሙን አትርሱ። በተለይ የቴሌግራም ቻናሌንና፣ የዩቲዩብ ቻናሌን ሰብስክራይብ አድርጉ አስደርጉ። በፌስቡክ መንደር ያለውንም ህዝብ ወደ እዚህ ማፍለስ ነው። የአድማጭ ተመልካች የአንባቢንም ቁጥር ከፍ እንዲል አድርጉ። አስደርጉም።

•••
👉 ዩቲዩብ ፡https://www.youtube.com/c/ZemedkunBekele

👉ቴሌግራም: http://hottg.com/ZemedkunBekeleZ

•••
የማታ ሰው ይበለን።
•••

ሻሎም !

>>Click here to continue<<

ኢትዮጵ

Share with your best friend
VIEW MORE

United States America Popular Telegram Group (US)