TG Telegram Group & Channel
ኢትዮጵ | United States America (US)
Create: Update:

ዝክረ ዘርአ ያዕቆብ.....#share

*ዐፄ ዘርዓ ያዕቆብ.በረራ (አዲስአበባን) የቆረቆሯት የቀዳማዊ ዳዊት አራተኛ ልጅ ነው።የተወለደው ፈጠጋር ውስጥ ጥልቅ ከሚባለው ሥፍራ ነው።ከአባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ ዘንድ ተምሯል።በግሼን ብሉይና ሐዲስን መጻሐፍት ትርጓሜ በመማር እንዲሁም ሲኖዶስን በማጥናት አሳልፏል።

*.በ1426 ዓ.ም ዐፄ አምደ እየሱስ ሲያርፍ በግዝት ከነበረበት ግሽ አምጥተው ተጉለት ውስጥ "ደጎ"ላይ "ዐፄ ቆስጠንጢኖስ ንጉሠ ነገሥት ዘኢትዮጵያ "ብለው አነገሡት።
ዐፄ ዘርዓያዕቆብ በነገሠ በሰባት ዓመቱ ከአምሐራ መጥቶ ተጉለት ውስጥ እጉባ በሚባል ቦታ ከተመ።ሰሜን ሸዋ ሰላ ድንጋይ የምትገኘውን ደብረ ምጥማቅ ያሰሯት በዚህን ጊዜ ነበር።የአሕመድ በድላይን አመጽ የሰማውም ታኅሣሥ 21 ቀን በደብረ ምጥማቅ የእመቤታችንን በዓል እያከበረ እያለ ነበረ።(Les chronuques da zar'a Yaeqob et de Ba'ede maryam,88፤ encyclopedia Aethiopica,vol.ll,34-35)

*በዐፄ ዘርአ ያዕቆብ 3 ሃይማኖታዊ ችግሮች ነበሩ።እነርሱም፦

ሀ~ኤዎሳጣቴዎሳውያን፦ ቅዳሜን እንደ እሁድ ካላከበርን የሚሉ፣

ሁ~ደቂቀ እስጢፋ፦ቀደም ብሎ በዐፄ ያግብዐ ጽዮን ዘመን የነበረውን ጭቅጭቅ እንደገና አንሥተው ለሰውና ለማላእክት፣ለሥዕል እና ለመስቀል አንሰግድም የሚሉ እና

ሂ~ዘሚካኤላውያን፦አምላክ መንፈስ እንጂ እንደፍጡር መልክ የለውም የሚሉ ናቸው።

*.ዐፄ ዘርያ ያዕቆብ መጽሐፍ አዋቂና ለሃይማኖቱ ቀናተኛ ከመሆኑ ባሻገር እነዚህ ሰዎች ሕዝቡን በተለይም መንግሥቱን የሚከፋፍሉት መስሎት ትልቅ ሥጋት አደረበት።ጉዳዩን ትኩረት በመስጠት ከኤዎስጣቴዎሳውያን ጋራ የቅዳሜን መከበር ፈቅዶ ሌሎቹን ግን በካህናት በጉባኤ እየሰበሰበ ስሕተታቸውንአሳያቸው፤አስፈረደባቸው፤አጠፋቸው።ተዓአምረ ማርያምን ወደ ግዕዝ አስተረጎመ።በዓመት 33 ቀኖች በቅድስት ማርያም ስም ዓመት በዓል ሆነው እንዲከበሩ ዐወጀ።እምነቱን የሚያንጸባርቁ ብዙ መጻሕፍትንም ደረሰ፤ዋና ዋናዎቹ መካከል፦

1.መጽሐፈ ብርሃን፣ 7.መጽሐፈ ሚላድ፣
2.መጽሐፈ ሥላሴ፣ 8.መጽሐፈ ባሕርይ፣
3.ተዓቅቦ ምሥጢር፣ 9.ጦማረ ትስብእት፣
4.ስብሐት ፍቁር፣ 10.መልክአ ፍልስታ
5.ተአምራተ ማርያም 11. ድርሳነ መላእክት....
6.እግዚአብሔር ነግሠ

*በእግዚአብሔር ነግሠ ግጥም ውስጥ ይኩኖ አምላክን፣ዐምደ ጽዮንን እና ቴዎድሮስን ያነሳል።
"የባህር ዕንቁ ለሆነው፤
ምርጡን ይኩኖ አምላክን ሰላም እላለሁ።
ኢትዮጵያን እንደ ፀሐይ አበራት።
ጌታ ሆይ ከአሸበረቀችው ሀገርህ፥
የበጉ ውበት ከሚያበራባት አስገበው።"

*በሰሜን እስከ ምፅዋ ደሴት በምሥራቅ እስከ ዘይላ ወደብ አመፀኞችን ዘምቶ ስላስገበረው ዐምደ ጽዮን እንዲህ ሲል ገጥሞለታል።
"የአመፀኞች ጎማጅ የሆነውን፥
ዐምደ ጽዮንን ሰላም እለዋለሁ።
በሁሉ ቦታ አብያተ ክርስቲያናት ሠራ፤
ንግሡን ለአምላክ በትክክል ባስገዛ ጊዜ፥
ከባሕር እስከ ባሕር ፈረሱን አስኬደ።"

7.ዐፄ ዘርአ ያዕቆብ ዋና ሥራ የኢትዮጵያን የቤተመንግስት የሹም ሽር አወቃቀር፥ የፍርድ ስርአቱን ማሻሻል እና ወታደራቸውን በዝርዝር መከፋፈል ነበር።በዝርዝር የተከፈሉ ወታደሮች ስማቸው፦

1.በፀር ዋጀት፣ 11.በድል ደመና፣
2..በድል ሾተል፣ 12.በፀር ሾተል፣
3.ድብ ምልዓት፣ 13.ዣን ምልዓት፣
4.በድል መብረቅ፣ 14.በድል መስቀል፣
5.በአዳል ዣን፣ 15.አቄት በአምባ፣
6.በአዳል ዋዠት፣ 16.ጸመና አምባ፣
7.በባሕር ዋገት፣ 17.በአዳል መብረቅ፣
8.ዣን አሞራ፣ 18.ዣን ጸገና፣
9.ዣን ገደብ 19.ዣን ቀንጠፋ...

*በዚህ በተደራጀ ፈረሰኛ እግረኛ ባለጦር፥ባለቀስት፥ ባለ ሰይፍ ጀሌ ዐፄ ዘርዓያቆብ የዓምደ ጽዮንን የአገር ግምባታ ፖሊስና ተግባር የበለጠ በማጠናከር አገሮችንና ክፍለ ሀገራትን በሙሉ በአንድ ማዕከላዊ መንግሥት ስር አደራጀ፥በዘመኑ የቀይ ባህር የዳህላክ ደሴት፣በአዴን ባህረሰላጤ የዜላ ወደብ ጨምሮ በአፍሪካ ቀንድ በአዴን ባህረሰላጤ ጠረፍና በሕንድ ውቅያኖስ ዳርቻ የበርበሮች ምድር ጨምሮ በማዕከላዊ መንግሥት ሥር አደረገ።የአዳሎችን በድላይ ተዋግቶ አሸነፋቸው።

*ዘርዓ ያዕቆብ የቤተክርስቲያን ሥርዓት አቋቁመዋል፣የሳታት ጸሎት አስጀምረዋል፣መካነ ጎልጎታ፤መካነ ማርያምን፤በሰሜን ሸዋ የሚገኘው ደብረ ብርሃን ሥላሴ፣በሰሜን ሸዋ ተጉለት ይገኝ የነበረው ደብረ ምጥማቅ፣በአምሐራ ዳሕያ በሚባል ቦታ የመሠረተው ደብረ ነጎድጓድ አሠርተዋል።

*በሰሜን ሸዋ ተጉለት ይገኝ የነበረው ደብረ ምጥማቅ የተሰራችው በዚህ ምክንያት ነበረ።ላይላይ ግብፅ ክርስቲያኖቹ ሰንደፋ ከሚባል ቦታ ደብረ ምጥማቅ(ዴር አል-መግጠስ) በምትባል ቦታ ላይ በሡልጣን በርስበይ (1422-1438) ትእዛዝ ቤተ ክርስቲያኗን አፈረሷት።የዘመኑ ሊቀ ጳጳሳት አባ ዮሐንስ (1422-1438) በክርስቲያኖቹ ላይ የደረሰባቸውን በደል ለዐፄ ዘርዓ ያዕቆብ ላኩበት።ዘርዓ ያዕቆብ ለሡልጣኑ "አዚህ ኢት ያሉትን እስላሞች ማንም አይነካቸውም።ሌላው ቀርቶ እንደ ሌላው ሕዝብ ግብር እንኳን አናስገብራቸውም እናንተ ግን የሃይማኖት ነፃነት ትገፍፋላችሁ"የሚሉ ቃላትና ሡልጣኑ የማይሰማ ከሆነም ለመበቀል እንደሚችል የሚያመላክት ጠንካራ ደብዳቤ ጻፈለት።ለግብጻዊያን ክርስቲያኖች ማጽናኛ ትሆን ዘንድም በፈረሰችው ቤተ ክርስቲያን ስም እዚህ ኢትዮጵያ እጉባ ላይ "ደብረ ምጥማቅ" የምትባል ቤተ ክርስቲያን ሠራ።በዚያ ላይ በዚያን ጊዜ የአደሉን ንጉሥ በድላይን ድባቅ መምታቱ በክርስቲያኑ ዓለም ስለተሰማ ሡልጣን ጀቅማቅ ተደናግጦ ከሊቀ ጳጳሳቱ ጋር ቶሎ ታረቀ።(ጌታቸው ኃይሌ,ደቂቀ እስጢፋኖስ፣52-53)

*ባጠቃላይ ዐፄ ዘርዓያዕቆብያ ስርዓትና ደንብ"፣የመንግስት አወቃቀር፣የጦር አደረጃጀት፣የሹማምንት አሿሿምና ተግባር፣የመንፈሳዊ ክብረ በአላትና የጸሎት አይነቶችን ጨምሮ፤በርካታ ነገሮች ከነበሩበት ጨምረውና አሻሽለው በ34 አመታቸው ልክ በዛሬዋ ቀን ጳጉሜ 3 ቀን 1460 ዓ.ም. አረፉ።በኋላ ላይ አስክሬናቸው በጣና ሐይቅ ደሴተ ዳጋ እንዲያርፍ ተደርጓል።

*ከታደለ ጥበቡ የተወሰደ

👉እርሶ ያወቁትን እውቀት ሌሎች ያውቁ ዘንድ ቻናላችንን ሼር በማድረግ ጓደኛዎን ይጋብዙ

ቻናላችንን ይቀላቀሉ
👇👇👇👇👇 👇👇👇👇👇
@ethiopianissm @ethiopianissm

>>Click here to continue<<

ኢትዮጵ

Share with your best friend
VIEW MORE

United States America Popular Telegram Group (US)