TG Telegram Group & Channel
ኢትዮጵ | United States America (US)
Create: Update:

ነሐሴ 24

ድካም በማብዛት እንደ ነቢያት፣ ወንጌልን በማስተማር እንደ ሐዋርያት፣ በመገረፍ እንደ ሰማዕታት፣ አጥንቱ ከስጋው ጋር እስኪጣበቅ ከሰውነቱ ማለቅ ብዛትና የሚያቃጥለውን ላብ እንደ ደም ዥረርታ በማፍሰስ፥ ከስግደቱ የተነሳ የሰውነቱ መለያ እስኪቆጠር ድረስ ተባህትዎን በመያዝ እንደ መነኮሳት ሆኖ መንፈሳዊ መገዛቱን ለመጨረስ ቆርጦ የተነሳ።

አይን እያለው እንደማያይ፣ ጆሮ እያለው እንደማይሰማ፣ ክረምትና በጋን ሳያያቸው 8 ጦር ዙሪያው ተክሎ የእግሩ አገዳ እስኪቆረጥ ድረስ ያለ ምግብ ያለ ውሃ ቅጠል እንኩአን ሳይቀምስ በፅኑ ተጋድሎ እንባውን እያፈሰሰ በብዙ የደከመ። ብጹዕ አባታችን በህመም በተያዘ ጊዜ በመንፈስ ልጆቹ የሆኑ ሁሉ ወንዶችም ሴቶችም ተሰብስበው ብዙ አለቀሱለት፡፡

አባታችንም ‹‹ልጆቼ አታልቅሱ ነገር ግን የሽማግሌውን ቃል ስሙ ከሁሉ አስቀድሞ እምነታችን በእግዚአብሔር ላይ ይሁን፡፡ ልጆቼ ሆይ ሰላም ለእናንተ ይሁን እንግዲህ ወዲ ግን ተሰናበትኳችሁ የእግዚአብሔር ፍቅሩ የክብሩም ባለቤትነት የረዳትነቱም ሀብት ዘወትር ከእኔና ከሁላችሁም ጋር ለዘላዓለሙ በእውነት ይኑር፡፡›› በማለት እንደዚህች ባለች እለት በምግባር ፍጹም የሆነ ተጋድሎው የበዛ ትሩፋቱ ያማረ፣ ሌሊትና ቀን በመቆም እግሩ የተሰበረ፣ በክረምትና በበጋ ውርጭ መልኩ የጠቆረ፣ በጌታችን ስም ደም ተቀብቶ ሰማዕት የሆነ፣ የዓለም ፀሐይ የትምህርት ብርሃን #ብጹዕ_አባታችን_አቡነ_ተክለሃይማኖት በተወለዱ በ 99 ዓመት ዐረፉ፡፡
የአባታችን ረድኤት በረከት አይለየን፡፡

>>Click here to continue<<

ኢትዮጵ

Share with your best friend
VIEW MORE

United States America Popular Telegram Group (US)