TG Telegram Group & Channel
ኢትዮጵ | United States America (US)
Create: Update:

የድንግል ማርያም አስደናቂው ስብዕና
[ በብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊ ]
በቤተ መቅደስ ውስጥ በንጽሕናና በቅድስና ኖረች ፤ ከቤተ መቅደሳችን ውጪልን
በማለት ሰዎች እርሷን የሚያስገድዱበት ጊዜ መጣ ግን እርሷ ይህንንም
አልተቃወመችም። ፈቃዷ ያለ ጋብቻ መኖር ነበር ፤ በሰው ልጅ ጥበቃ ትሆን ዘንድ
ግድ አሏት ፥ ይህንንም አልተቃወመችውም። ይህም እንደ ጊዜያቸው ሥርዓት
ይጓዙ ነበርና ለአረጋዊ ዮሴፍ እንድትታጭ ሆነ ፤ ይህንንም ሳትቃወም ከመቅደስ
ውጪ መኖርን እንዳልተቃወመች ሁሉ ይህንንም ሁኔታ ባለመቃወም ፈጸመችው ፤
የኖረችው ሕይወት የመታዘዝ ሕይወትን ነውና።
ያለመቃወም ፣ ያለማጉረምረም ፣ ያለማንገራገር ሕይወት ፤ ነገር ግን በእርጋታ
የሯሷን ፈቃድ አሳልፋ ለእግዚአብሔር ፍቃድ ሰጠች እንጂ። የድንግልና
ሕይወትን ለመምራት ቆረጠች ፣ እናት እሆናለሁ የሚል ሀሳብ በእርሷ ውስጥ
ፈጽሞ አልነበረም። እግዚአብሔር እናቱ ትሆን ዘንድ ፈቃዱ ሲሆን ግን
የሚከተለውን ነገር ተናገረች "እነሆኝ የጌታ ባሪያ እንደ ቃልህ ይደረግልኝ" አለች
(ሉቃ. ፩፥፴፰)። ለዚህም ትህትናዋ እግዚአብሔር አምላክ የእናትነት ዘለዓለማዊ
ትሕትናን አጎናጸፋት። ይህችም ጸጋ ለዘለዓለም በእርሷ ላይ ጸንታ ትኖራለች።
እናቱ ትሆን ዘንድ በድንግልና አጸናት ፤ ስለዚህ ምክንያት ቅድመ ፀኒስ ጊዜ ፀኒስ
ድኅረ ፀኒስ ፣ ቅድመ ወሊድ ጊዜ ወሊድ ድኅረ ወሊድ በድንግልና ሀብታት ከብራ
እንድትኖር አደረገ እናትም ሆነችው።
ፈጽማ እሆናለሁ ብላ ያላሰበችው ምሥጢር ነበር ፤ ነገር ግን በመታዘዝ የጌታ
እናት ሆነች። ወደ ግብጽ እንድትመጣ ታዘዘች ሄደች ፣ በዚያም ኖረች። እርሷ
በስብዕናዋ ምሳሌ የምትሆን እመቤት ናትና። ለዚህ ነው "ብርቱ የሆነ እርሱ
ታላቅ ነገርን አድርጎልኛልና" በማለት ያመሰገነችው። በዚህ ነው ትሑትነቷንም
የገለጠችው የባሪያውን ትሕትናና መታዘዘ በእርግጥም እግዚአብሔር
ከማደሪያው ተመለከተ በማለት ብጹዕነታቸው አቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊ የግብጽ
ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፻፲፯ተኛ ጳጳስ በብዕራቸው ከትበውላታል።
የአምላክ እናት እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም አማላጅነት ፣
የብጹዕነታቸው ጸሎት በረከት አይለየን!!!
ሰዓሊ ለነ አእምሮውን ልቡን ሳይብን አሳድሪብን ፥ ጸጋውን ክብሩን እንዳይነሣን
ለምኝልን!!!

>>Click here to continue<<

ኢትዮጵ

Share with your best friend
VIEW MORE

United States America Popular Telegram Group (US)