TG Telegram Group & Channel
ኢትዮጵ | United States America (US)
Create: Update:

#የሐሙስ_ውዳሴ_ማርያም

ዘር ምክንያት ሳይኾናት አምላክን የወለደች ድንግል፣ የማኅፀንዋ ሥራ ምን ይረቅ? ምን ይጠልቅ? አንድም ለድንግል ለማኅፀኗ ሥራ አንክሮ ይገባል፡፡ ለዮሴፍ የነገረው መልአክ ሳይለወጥ ሰው የኾነ አካላዊ ቃል ከርሷ የሚወለድ በግብረ መንፈስ ቅደስ እንደኾነ መስክሯልና /ማቴ.፩፡፳/፡፡ ማርያም የዚህ ደስታ ዕፅፍ ድርብ የሚኾን ጌታን ወለደችው፡፡ ሴቶች ልጅ ትወልዳላችሁ ሲባሉ ደስ ይላቸዋል፤ ይልቁንም ወንድ ትወልዳላችሁ ሲሏቸው ደስ ይላቸዋል፡፡ እመቤታችን ግን ከዚሁ ኹሉ ያለፈ አምላክን ወልዷለችና ደስታዋ ዕፅፍ ድርብ ኾነላት፡፡ መልአኩ፡- “ልጅ ትወልጃለሽ፤ ስሙም አማኑኤል ይባላል” አላት፡፡ አማኑኤልም ማለት እግዚአብሔር ከሥጋችን ሥጋ ከነፍሳችን ነፍስ ነሥቶ ከኛ ጋራ አንድ ባሕርይ ኾነ ማለት ነው፡፡ ዳግመኛም ወገኖቹን ከኃጢአታቸው ፍዳ የሚያድናቸው መድኃኒት ይባላል አላት /ማቴ.፩፡፳፩/፡፡ በመኾኑም በክሂሎቱ (በከሃሊነቱ) ያድነን ዘንድ፣ ኃጢአታችንን ያስተሠርይልን ዘንድ (እስከ ዕለተ ምፅአት ድረስ ክብር ይግባውና) ሰው የኾነ እርሱ አምላክ እንደኾነ በተረዳ ነገር አወቅነው፡፡ አምላክ ብቻ ቢኾን ባልታመመ ነበርና፤ ሰውም ብቻ ቢኾን ባላደነን ነበርና፡፡ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅም ከዚህ ጋር አያይዞ ፡- “ፍቁራን ሆይ! ምንም እንኳን ለዚህ ክብር የተገባን ኾነን ባንገኝም አባታችን በከኀሊነቱ እንዲሁ ከኀጢአታችን አድኖናልና ይህን ክብር፣ ይህን ጸጋ በፍጹም ልናክፋፋው (ልናቆሽሸው) አይገባንም፡፡ ልጅነት እንዲሁ ሳይሰጠን ለምረረ ገሃነም የተገባን የቁጣ ልጆች ከነበርን፤ ይህ ከኅሊናት በላይ የኾነ ጸጋ ከተቀበልን በኋላማ ፍዳችን እንደምን የበዛ አይኾን? ልጆቼ! ይህን የምለው እንዲሁ ለመናገር ያህል አይደለም፡፡ ዳግም ከአብራከ መንፈስ ቅዱስ ከማኅፀነ ዮርዳኖስ ከተወለዱ በኋላ ብዙ ክርስቲያኖች በኀጢአት፣ በስንፍና፣ ለምግባርና ለትሩፋት ሳይሽቀዳደሙ ታክተው ስለምመለከት ነው እንጂ” ሲል ይመክረናል /St. John Chrysostom, Homily on the Gospel of St. Matthew, Homily IV/፡፡

ወዮ! ንዕድ ክብርት ከምትኾን ከእመቤታችን ይህ የአምላክ መወለድ ምን ይረቅ? ምን ይጠልቅ? ቃልን ወሰነችው፡፡ ለልደቱም ዘርዕ ምክንያት አልኾነውም፡፡ በመወለዱም ማኅተመ ድንግልናዋን አልለወጠውም፡፡ ከአብ አካል ዘእምአካል ባሕርይ ዘእም ባሕርይ ድካም ሳይሰማው የተወለደ እርሱ ፭ ሺሕ ከአምስት መቶ ዘመን ሲፈጸምም ከድንግል ሕማም ሴቶች የሚሰማቸውን ሕማም ሳይሰማት እርሱን ሕፃናትን የሚሰማቸው ሕማም ሳይሰማው ተወለደ እንጂ፡፡
ሰብአ ሰገል ሰገዱለት፡፡
አምላክ ነውና አምላክ እንደኾነ ለማጠየቅ ዕጣን አመጡለት፡፡ ንጉሥ ነውና ንጉሥ እንደ ኾነ ለማጠየቅ ወርቅ አመጡለት፡፡ ማኀየዊ የሚኾን የሞቱ ምሳሌ ከርቤንም አመጡለት፡፡

#አንድም “ይኸን ወርቅ እንገብርላቸው የነበሩ ነገሥታት ቀድሞም ፍጡራን ኋላም ኀላፍያን ናቸው፤ አንተ ግን ቀድሞም ያልተፈጠርህ ኋላም የማታልፍ ነህ” ሲሉ ወርቅ አመጡለት፡፡ “ይኽን ዕጣን እናጥናቸው የነበሩ ጣዖታት ቀድሞም ፍጡራን ኋላም ኃላፊያን ናቸው፤ አንተ ግን ቀድሞም ያልተፈጠርህ ኋላም የማታልፍ ነህ” ሲሉ ዕጣን አመጡለት፡፡ “ምንም ቀድሞ ያልተፈጠርህ ኋላም የማታልፍ ብትኾን በሰውነትህ መራራ ሞትን ትቀምሳለህ” ሲሉ ከርቤ አመጡለት፡፡

#አንድም ወርቅ ጽሩይ ነውና “ጽሩየ ባሕርይ ነህ” ሲሉ ወርቅ አመጡለት፡፡ ዕጣን ምዑዝ ነውና “አንተም ምዑዘ ባሕርይ ነህ” ሲሉ ዕጣን አመጡለት፡፡ ዳግመኛም “ከርቤ የተሰበረውን ይጠግናል፤ የተለያየውን አንድ ደርጋል፡፡ አንተም ከማኀበረ መላእክት የተለየ አዳምን አንድ ታደርገዋለህ፤ ጽንዓ ነፍስ ሰጥተህ ታጸናዋለህ” ሲሉ ከርቤ አመጡለት፡፡

#አንድም ወርቅ ጽሩይ ነውና “ባንተ ያመኑ ምዕመናን ጽሩያነ ምግባር ወሃይማኖት ናቸው” ሲሉ ወርቅ አመጡለት፡፡ ዕጣን ምዑዝ ነውና “ባንተ ያመኑ ምእመናንም ምዑዛነ ምግባር ወሃይማኖት ናቸው” ሲሉ ዕጣን አመጡለት፡፡ ዳግመኛም በዕለተ ሞቱ ያቀምሱታልና ከርቤ አመጡለት፡፡ ቸርና ሰው ወዳጅ የኾነ አንድ እርሱ ብቻ ነው፡፡ ቸርና ሰው ወዳጅ ከኾነ ልጅሽ ጽንዕት በድንግልና ሥርጉት በቅድስና እመቤታችን ጸጋውን ክብሩን እንዳይነሣን ለምኚልን፡፡

>>Click here to continue<<

ኢትዮጵ

Share with your best friend
VIEW MORE

United States America Popular Telegram Group (US)