TG Telegram Group & Channel
Channel: Amazing facts
Back to Bottom
#14_የአፍሪካ_ሃገሮች_ለፈረንሳይ_ግብር_እንደሚከፍሉ_ያዉቃሉ??
----------------------------------------------------------------

በፈረንሳይ አስገዳጅነት #Colonization_tax የተባለ #ድሃ_አፍሪካ ሃገራት ከቀኝ ግዛት ከተላቀቁ በኃላ እንኳ ከሚዘረፉት አንጡራ የተፈጥሮ ሃብት በተጨማሪ ረብጣ ዶላርም ከ1960-አሁን 2021 ድረስ ግብር እየከፈሉ ይገኛሉ። ሃገራቶቹ የሚከተሉት ናቸዉ

1)ቤኒን
2)ቡርኪናፋሶ
3)ጋቦን
4)ጊኒ-ቢሳው
5)አይቮሪ-ኮስት
6)ኮንጎ-ብራዛቪል
7)ማሊ
8)ኒጀር
9)ሴኔጋል
10)ቶጎ
11)ማህከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ 12)ኢኳቶሪያል-ጊኒ
13ካሜሮን እና
14)ቻድ ናቸው።

ይህ በጥንቃቄና በዘዴ የተዋቀረ "Compulsory Solidarity" 14 የአፍሪካ ሃገሮችን ያካተተ ሲሆን ግዴታውም በቅኝ ግዛትና በባርነት ወቅት ፈረንሳይ ለገነባቻቸው መንገዶች መሰረተ ልማቶች ላወጣቻቸው ወጪዎች ካሳ ይሆናት ዘንድ ከነዚህ አፍሪካ ሃገሮች ከውጭ ምንዛሪና ተቀማጫቸው ላይ 65% ለፈረንሳይ ቀጥታ Treasury ድጎማ ያስገቡላታል (500billion$)... ይህ ብቻ ሳይሆን 20% financial Liability ይከፍላሉ ይህ ማለት ከጠቅላላ ገቢያቸው 15% ብቻ ነው ለራሳቸው ሚያውሉት ማለት ነው።
ገንዘብ ካስፈለጋቸውም ብድር ከፈረንሳይ መንግስት የራሳቸውን ብር መልሰው ይበደራሉ ይህ እንግዲህ ከ1960 G.C ጀምሮ እየተተገበረ ያለ ግፍ ነው።

#ለምን_አንከፍልም_አይሉም?
ቀላል የሚመስል ጥያቄ ነው። ሴራው ግን ውስብስብና በተንኮል የታጨቀ ግፍ ነው።
#ሴኩ_ቱሬ_የጊኒ_ፕሬዝደንት ሞከረ "አልከፍልም እንቢ!" አለ ከኮሎኒ ኢምፓየርም እራሱን አገለለ...
ፈረንሳይ ተቆጣች በጊኒ ያለው የፈረንሳይ ጦርና አስተዳደር ሁሉንም ነገር "በፈረንሳይ ኃብት የተገነባ" ያሉትን ሁሉ ማውደም ጀመሩ 3000 ፈረንሳውያን ሃገሪቷን ጥለው ሲሄዱ ተንቀሳቃሽ ንብረት አንድም አልቀራቸውም ማይንቀሳቀሱትን ት.ቤት፣ሆስፒታል፣መንገድ፣ህንፃዎችን #አወደሙ። መድኃኒት፣መኪኖችን፣ትራክተሮችን፣መፅሐፍትን #አቃጠሉ። እንስሳት በሬዎች ላሞች ፈረሰችን #ገደሉ። በመጋዘኖች ያሉትን እህሎች #ቀበሩ_መረዟቸው። ሃገሪቱን እንዳልነበረች አደረጓት።
ይህም የሆነው ማንም ሃገር ፈረንሳይ ላይ አምፃለሁ ቢል የጊኒ እጣ እንደሚደርሰው ማስጠንቀቂያ ነው።
የጊኒው ሴኮ ቱሬን "we prefer freedom in poverty to opulence in slavery" የሚለውን መፈክር ማንም ሃገር በፍርሃት ሊያስቀጥለው አልወደደም።

#በ 612$ #መፈንቅለ_መንግስት
የቶጎው ተመራጭ ፕሬዝደንት Olympion የራሱን መገበያያ ማተም ከጀመረ በሦስተኛው ቀን ፈረንሳይ ባሰማራቻቸው #የገዛ_ወታደሮቹ ተገደለ። ለገዳዮቹም ፈረንሳይ በኢምባሲዋ በኩል #612_ዶላር ጎሽ! ብላ ከፍላቸዋለች።
Olympion ህልሙ ነፃ፣ራሷን የቻለች አዳጊ ቶጎን መገንባት ነበር። ፈረንስይ ሃሳቡን አልወደደችለትም እንጂ...

#መፈንቅለ_መንግስት
ባለፉት ሃምሳ አመታት በ26 አፍሪካ ሃገራት ውስጥ ከተደረጉት 67 መፈንቅለ መንግስታት 16ቱ የፈረንሳይ የቀድሞ ቀኝ ግዛት ሃገሮች ውስጥ ነው። ይህ ማለት 67% መፈንቅለ መንግስታት የተደረጉት በፈረንሳይ ድጋፍ ነው ማለት ነው።

#የግፍ_ክፍያዎች
1. #Colonial_Deb~ ፈረንሳይ ለገነባቻቸው መሰረተ ልማቶች የሚከፈል።
2. #Automatic_Confiscation of national reserve~ ሃገራቱ ብሔራዊ መጠባበቂያ ገንዘባቸውን France Central Bank ማስቀመጥ።
3. #Right of First refusal (raw or Natural Resource)
ፈረንሳይ በሃገራቱ መሬት ላይ ያለን የትኛውንም የተፈጥሮ ኃብት ቀድማ የመግዛት መብት አላት "አልፈልገውም" ካለች ብቻ ነው ሌላ ገበያ ማፈላለግ ሚጀምሩት።
4. #Priority_to_France~ የፈረንሳይ ካምፓኒዎች የህዝብ መገልገያ የሆነን የትኛውም ህንፃ ቅድምያ የማግኘት መብት አላቸው።
5. #Military_Equipment & Trainings~ የትኛውም ወታደራዊ ስልጠናም ሆነ ቁሳቁስ በፈረንሳይ በኩል ብቻ ነው በክፍያ ማግኘት ሚችሉት። ፈረንሳይ ወታደሮቿን ማሰማራት ቤዝ ማግኘት ትችላለች። ፈረንሳይ ችግር ካጋጠማትም ከጎኗ የመቆም ግዴታ ተጥሎባቸዋል።
6. #Obligation of French Language~ አፀያፊ ባህልም ቢሆን።
7. #Report~ ለፈረንሳይ ዓመታዊ ሪፖርት የማቅረብ ግዴታም አለባቸው።
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
#እኛ_ኢትዮጵያዊያን_ከቅኝ_ግዛት_ነፃ_የሆንነዉ_በነፃ_አይደለም💪
የተሰወረው የBitcoin የፈጠራ ባለቤት ማንነዉ??
___________________________________

የBitcoin'ን ግኝት የፈጠረው የኢኮኖሚና የሒሳብ ሊቁ Satoshi Nakamoto ይባላል።

ከስሙ ውጪ ስለዚህ ሰው ማንነት በግልፅ የሚታወቅ ነገር የለም።

Bitcoin ለዓለም የተዋወቀው በ2009 እ.ኤአ ነው። ይህ ሰው ከመጀመሪያዎቹ ተጠቃሚዎች ጋር ግኑኘነት የፈጠረው በE-mail እንጂ በስልክና በአካል አልነበረም።

#Bitcoin_ምንድነው?

Deepweb እንደ ገንዘብ (Cryptocurrency) የሚጠቀምበት ዓለም ዓቀፍ Digital መገበያያ ነው።

Decentralized (አንድ ሰው ብቻ የማይቆጣጠረው) ሥርዓተ-ገንዘብ ነው።

ይኽውም ለምሣሌ:- Digital ባልሆነው ሥርዓት ገንዘብ ስንለዋወጥ ልውውጡ መሃል ባንክ ቤቶች የግድ አሉ።

በBitcoin ሥርዓት ግን ያለ ባንክም ሆነ ማንም ጣልቃ ገብነት (peer-to-peer) ገንዘን ልውውጥ ይደረጋል ማለት ነው።
አሁን ያለን ጠቅላላ የባንክ ሥርዓትም በፍፁም ይቀይረዋል ማለት ነው።
ይኽ ልውውጥ እንዴት #Vertify ይደረጋል?

በ Network Nodes አማካኝነት የ Crypto Graphics Technology በመጠቀም ተግባራዊ ይሆናል።
ልውውጡም public Distributed Ledger block chain ይመዘገባል።

ሲጀመር ዋጋው በሳንቲም 0.00025$ ደረጃ የነበረ ሲሆን አሁን ላይ 1 Bitcoin = 885,454.56 ብር በላይ ያወጣል።

ለምሣሌ:- ከ10 ዓመት በፊት 100$ የሚያወጣ Bitcoin ገዝታችሁ ከነበረ አሁን ላይ $29,018,250 ይሆን ነበር።

አሁን አሁን Bitcoin ይበልጥ እየታወቀና እየተስፋፋ ቢመጣም ፈጣሪው Satoshi ግን ማንም ይኽ ነው ያለው የለም።

ጭራሽ በ 2011 ይኽ ሰው ሥራው ቢገንም ማይታወቀው መልኩና ማንነቱ ግን ልክ በአየር እንደ ተነፋ አረፋ በሚድያው አየር ላይ ከፍ ከፍ አለና #ብን ብሎ ድንገት ጠፋ ጠፋ።

ብዙዎች "Satoshi እኔ ነኝ" እያሉ ይመጣሉ። እንዳልሆኑ ይደረስባቸዋል ይሄዳሉ።

በ2014 NewsWeek በጋዜጣው ፊት ገፁ ላይ "Satoshi'ን አገኘሁት" ብሎ ነበር። ከሎስአንጀልስ ከተማ ወጣ ባለ ሥፍራ ነዋሪ የሆነ ሥራ አጥ ኢንጂነርና ዕድሜውም በስልሳዎቹ ውስጥ ያለ እንደሆነ ያስረዳል።

ሌላኛው መላምት በአብዛኛው Bitcoin ተጠቃሚዎች ዘንድ የሚታመነው ደግሞ ፣ Satoshi በብቸኝነት የሚኖር ትውልደ ሃንጋሪ አሜሪካዊ ሰው ስሙም Nick Szabo ነው ይላሉ።

ይኽ Szabo የተባለው ሰው ግን በBitcoin ቢዝነስ ቁልፍ ቦታ ቢኖረውም ግን "እኔ Satoshi አይደለሁም" በማለት ክዷል።

Satoshi ከ2011 እ.ኤ.አ በኃላ Bitcoin ላይ ተሳትፎውን አቁሟል።

የሱ አለመኖርም በጠቅላላ ኹነቶችና ነገረ ሥራዎች ላይ ምንም ለውጥ አያመጣም ፣ ቢባልም ግን በሱ ማንነት ላይ የትንግርት አይነት ስሜት ያደረባቸው አሁንም ድረስ ማንነቱን ለማወቅ ምሥጢራቱን በመፍታት በመበርበር ላይ ይገኛሉ።

የሚገርመው Satoshi ማንም ይሁን ማን Bitcoin ከሱ ውጪም ሆነ በሱ ውስጥ ቢዝነሱ ይቀጥላል።

የዓለማችንን ወደፊት የመገበያያ ሥርዓት አሸንፎ ይወጣል ተብሎም ይታመናል።

ይህ Bitcoin የሚያገለግለው እስከ 2140 እ.ኤ.አ ሲሆን 21 million Bitcoin በቁጥር ይመረታል።ከዚኽም ውስጥ እስከ አሁን ከ17 million ተመርተው ሰዎች እጅ ላይ አሉ። በሚመጡት ጊዜያትም እስከ 4 Million እንደሚመረቱ ይጠበቃል። ይኽንንም ሳይንሳዊ ቀመር አስቀምጦና አስልቶ....

Satoshi ምክንያቱ ምን ይሁን ምን? ባይታወቅም ደብዛው ሲጠፋ በጊዜው 1 Million Bitcoin ነበረው። ይኽ ማለት በዛሬ ሲሰላ በቢልየን ዶላሮች ዋጋ ካለው ገንዘብ ጋር ተሰውሯል ማለት ነው።
#ቡድሂዝም_መስራቾቹ_ኢትዮጵየዊ_ጥቁሮች
_______________________________

#Buddha የሕንድ ቡድሂዝም መስራች ሰው ጥቁር አፍሪካዊ ለዛውም የኢትዮጵያ የዘር ሃረግ ያለው ሰው እንደነበር ብዙ ጥናቶች እየወጡ አጀብ እያስባሉ ነው።

በቡድሃ ቤተመቅደሶችና በተለያዩ ቦታዎች የሚገኙት ጥንታዊ ለአምልኮ ግልጋሎት የሚውሉ ሐውልቶቹ ለዛ ነው ፀጉሩ ቁጥርጥር እንደተሰራ አይነት፣ ሰፋፊ ደፍጣጣ አፍሪካዊ አፍንጫ፣ ከርዳዳ ፀጉር ፣ወፍራም ከንፈር ያለውና ጆሮው በሰፊው የተበሳ (የተቀደደ ልክ አሁን የደቡብ ጎሳዎች ሃመሮች ቡርጂዎች እንደሚያደርጉት ያለ ቅድ) በብዛት በጥቁር ወይም ወርቃማ ቀለም ተገንብተው የሚታዩት።

በየትኛውም የብድሃ ታሪክ ላይ Buddha እንደ ነጭ ማንነት ተገልፆ አይገኝም።

የመጀመሪያዎቹ ስለ ቡድሃ conceptualized በማድረግና ጥቁሩን ቡድሃ ማምለክ የጀመሩት ጥቁሮች ሲሆኑ ሃሳቡንም ወደ መካከለኛው ምሥራቅ በመውሰድ የመጀመሪያዎቹ የሓይማኖቱ መልዕክተኞችም ሆነዋል።

Buddha ከ Sakya ጎሳ ከNagra ነገድ የሆነ የበራለት ሰው ነው። አስተምሕሮቶቹ ማጠንጠኛም እኩልነት፣ ነፃነት፣ ወንድማማችነት የተባሉ ናቸው።

በአእምሮ ኃይል ንቃተ ህሊና በመጠቀም የአእምሮን ኃይል መጠቀምን ያስተምራል።

Golden Rule የተባለ መሰረት ሲኖረው ክርስትና ከመመስረቱ ከ 500 ዓመታት በፊት በ Middle East (Afrika) ትቋቁሟል።

በነገራችን ላይ Buddha ሥም አይደለም The Enlightened "የበራለት" Blessed One "የተባረከ" To Become Awake "የነቃ ማለት ነው።

በክፍለዘመናት ውስጥም Buddhas ለመሆን የበቁ እንደ Gautama, Sakayanumi, and Siddhartha የመሳስሉ አሉ።

ከነዚህም ውስጥ በሕንድ መፅሐፍ ውስጥ 10 ያኽል ጥቁር Buddhas እንዳሉ ተጠቅሰዋል።

ጥቁር Buddhist missionaries (መልዕክተኞች) ለ China, Japan እና ሌሎች ሃገሮች በተለይ Ashoka በተባለው ጥቁር ንጉሥ አገዛዝ በአውሮፓና በብሪታንያ አስተምዕሮቶቹን አስፋፍተዋል።

Buddhism ሩቅ ምሥራቅ ላይ ጃፓን ወይም ቻይና አልተጀመረም በሕንድ እንጂ። ቀስ በቀስ ወደ እስያ ተስፋፋ።

የቡድሂዝም መስራቾች ከ50,000 ዓመታት በፊት ከኢትዮጵያ የተሰደዱ ጥቁር አፍሪካውያን እና የ Indus Valley Civilization ማስራቾች ናቸው።

ሁለት አይነት የሰው ልጅ ሥልጣኔ መሥራቾችና በዓለም የተንሰራፉ ጥቁሮች አሉ።

1_Nubian ሰፋ ያለ ፊት፣ ከርዳዳ ፀጉር ያላቸው።

2_Dravidian ሉጫ ፀጉርና ቀጥ ያለ አፍንጫ ያላቸው ናቸው። ሁለቱም ግን መሰረታቸው አፍሪካ ናት።

ኢትዮጵያውያውያንም የመጀመሪያውን ከአፍሪካ ወደ አለም ፍልሰትንን አነሳስተዋል።
ሁለተኛው ፍልሰት በ Australian Aboriginal ተደርጓል።

ይኽውም በሁለቱ ቡድኖች የተደረገ ቅልቅል "the people of the Indus Valley" ን አስገኝቷል። በኃላም "the Mediterranean Black Mongoloid" ዘሮች ከነዚሁ ጋር ተቀላቅለው India (which means Black) አስገኝተዋል።

በ Buddha ጊዜ 2,500 ዓመታት በፊት (500 B.C.) አፍሪካውያን የዓለምን ኃያልነት ተቆጣጥረው ነበር። ከ 500 ዓመታት በፊት Aryans የተባሉት ነጮች ሰሜናዊት ሕንድን በመቆጣጠር ጥቁሮቹን ወደ ደቡባዊት ሕንድ አሸሿቸው። ኃያልነቱንም ተቆጣጠሩ።

#ሕንድን_የመሰረቱ_ጥቁር_ኢትዮጵያኖች_የሚደርስባቸው_አሰቃቂ_ግፍ

በወታደራዊ ሥልታቸው ጥንካሬ በቀላሉ Black Nagas ማሸነፍ ያልቻሉት ነጮች ያደረጉት የጥቁሮቹን ጥንታዊ ማንነት፣ እምነትና ፅሁፎቻቸው መበረዝና በራሳቸው ኑፋቄ መቀየርና ጥቁሮቹን አሳንሶ መግለፅ ነበር።

ይኽ #anti-Black እንቅስቃሴ #Brahmanism ተብሎ ይጠራል። በሌላ ስሙ #Hinduism "the greatest curse to the Blacks (Sutras) of India" ይሉታል።

ይኽ Aryan Hindu (ነጮች) ፈጠራ ሐይማኖት ለዘረኝነት እውቅና የሰጠና የቀደምት ሕንድ ጥቁሮችን አእምሮን፣ አካልን፣ መንፈስን በቁጥጥር ሥር ለማድረግ የተቋቋመ ሴራ ነው።

ይኽ #Brahmin አሁን ድረስ ሕንድ ውስጥ የሚታይ የጉልበት ብዝበዛን ያመጣና እራሳቸውን ከሕብረተሰቡ በላይ ነን “Untouchables” ብለው በሚያስቡና በተቃራኒው “the heavily exploited, degraded, humiliated, slave-like, impoverished so called who carry the weight of the entire population on their shoulders, are at the bottom rung of this social ladder” በሚባሉ አስከፊ ጭቆናን አሜን ብለው በተቀበሉ ማሕበረሰቦች ተሞላች።

ሕንድ በአራት አስገራሚ ማሕበረሰቦች ተዋቅራለች
1. Brahmins (priesthood)
2. Kshatriyas (the warrior class)
3. Vaishyas (the merchant class)
4. Sudras / Untouchables / Outcastes, (the hated ones who refused to compromise or surrender to Aryan dominance).

ከነዚህ ውስጥ አራተኞቹ "The outcasts" የተባሉት ደግሞ

የሞቱ እንስሳት እንዲመገቡ የሚገደዱ
በሠባራ ገል ብቻ መመገብ የሚፈቀድላቸው
በአንገታቸው ዙሪያ ኮዳ መሳይ ነገር የሚያንጠለጥሉ ይኽውም በካይ ነው ተብሎ ሚታመነው ምራቃቸውን ያጠራቅሙበት ዘንድ ነው።
ሲራመዱ የተውትን ዱካቸውን ሚጠርጉበት ይዘውም ይጓዛሉ ይኽ ደግሞ ማንም ሰው ዱካቸውን ማቋረጥ የተከለከለና በካይም ነው ተብሎ ስለሚታመን ነው።
ወደ ነጮች መኖሪያ መግባት የሚችሉትም በምሽት ብቻ ሲሆን ምክንያቱም ጥላቸው እርጉም ነው ስለሚባል ነው።
ጥቁሮቹ አይነምድር ያፀዳሉ የሟቾችንም ልብስ ይለብሳሉ።
ሴቶቻቸውም በሴትኛ አዳሪነት ይሰማራሉ።

ይኽም ሥርዓት በ Brahmin religion ፍቃድ ያለውና Hinduism የሚባለው ነው።

በጥቁር ሕንዳውያንና በነጭ ወራሪዎች ዘንድ በተደረገ ፍልሚያና በጦርነቱና በ #Brahminism መነሳት መካከል ጥቁሩ #Buddha እና #Buddhist አስተምህሮቾቹን ቀስበቀስ በማጥፋት ተሐድሶ #reformist በሚል #Hinduism የተባለውን ሴጣናዊ ፈጠረ።

ጥቁሩ ንጉሥ King Ashoka and Buddha የነጮችን Aryan ወረራ ተፋልመዋል የ Black Naga Indians back
ሥልጣኔ ወደነበረበት ለመመልሥም ጥረዋል።

በራሳቸው ባንዳ ጥቁሮች፣ በአንድነት ማጣት በነጮቹ መሰሪነት ከፋፋይነት የከሰሙ ህዝቦች ሆነዋል።
#ሼህ_ሆጀሌ

ሼህ ሆጀሌ ዛሬ ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ግዛት የነበራቸው ሙስሊም ባላባት ነበሩ። በኋላ ዓፄ ምኒልክ የዛሬውን ኢትዮጵያ የሀገረ መንግስታቸው አካል ለማድረግ ሲንቀሳቀሱ በሰላም ገብረው የዓፄ ምኒልክ ወዳጅ ሆነዋል - ዓፄ ምኒልክም ሼህ ሆጀሌን የራስነት ማዕረግ ሰጥተው በቤኒሻንጉል ላይ ሹመታቸውን አፀደቁላቸው።

ሼህ ሆጀሌም
"የራስነት ማዕረጉ ይቅርብኝ ፤ "ሼህ" ራሱ ማዕረግ ነውና በእሱ መጠራትን እመርጣለሁ።" በማለታቸው እስከ ሕይወታቸው ፍፃሜ በዚያው ስም ሲጠሩ፡ኖሩ ።
የሃይማኖት መሪ ብቻ አለመሆናቸውንና የጦር ሜዳ ጀግንነታቸውን ያረጋገጡበት አጋጣሚ ደግሞ የዓድዋ ጦርነት ነበር ። ሼህ ሆጄሌ በዓድዋ ጦርነት ላይ 5000 ወታደርና ፈረሰኛ በማሳተፍ ለድሉ ከፍተኛ አስተዋጽኦ አድርገዋል ።

እኛ ከዚህ የምንማረዉ የዓድዋ ድል የሁላችንም ኢትዮጵያዊ አባቶቻችን ለመላዉ የጥቁር አፍሪካዊያን ያጎናፀፉት ታላቅ ድል መሆኑን ብቻ ነዉ።

👉 በአንድነት ምክኒያት የመጣን ድል ተገነጣጥሎ ቃላት እየተወራወሩ ማክበር ያሳፍራል። ዉርደት ነዉ።

#የዛሬዉ ሃገር ተረካቢ ትዉልድም ካለፉ ታሪኮቻችን መልካም ነገሮችን በመቅሰም ሃገራዊ አንድነትን ሊያመጡ የሚችሉ ሃሳቦችን ከማመንጨት ጀምሮ ሃገርን የመገንባትና የመጠበቅ ታሪኮችን ብቻ በማስመዝገብ እንዲሁም በጥሩ ስነ ምግባር የታነፀ ትዉልድ ለማነፅ በትጋት በስራት የሁሉም ሀገራዊ ግዴታ ሊሆን ይገባል።
2021/03/02 19:10:45
Load New Feed
Back to Top