TG Telegram Group Link
Channel: ህብረ ቀለማት ግጥሞች
Back to Bottom
Tattoo ለመሰራት

ጠባሰን ለመሸፈን
ድድ ለመነቀስ
ቅንድብ ለመነቀስ
🔝
Tribal tattoo
3D tattoo
Drawings
Symbols
Texts

ለሁሉም በ
+251965928512
+251923880303
Inbox @lanchi_new11
"ለመላው የሀገራችን ህዝቦች ፤

ውድ ህይወት አጥተናል። የዚህ ድንቅና አንፀባራቂ ወጣት አርቲስት ሓጫሉ ሁንዴሳ ህይወት መቀጠፍ ከተሰማ ጀምሮ በከባድ ሀዘን ውስጥ ለምንገኝ ሁሉ መፅናናትን እመኛለሁ ። የዚህን ክፉ ድርጊት ሙሉ የፖሊስ ምርመራ ሪፖርት እየተጠባበቅን እንገኛለን ። የድርጊቱን መጠን በመረዳት በሀገራችን ውስጥ ስለሚከናወኑ እንቅስቃሴዎች ትኩረት ሰጥተን የምንከታተልበት ወቅት ላይ ነን። ሀዘናችንን ራሳችንን በመጠበቅ እና ተጨማሪ ወንጀልን በመከላከል እንግለፅ።"

ጠ/ሚ ዶ/ር አብይ አህመድ
@ethiopiagna
@ethiopiagna11
ሰላም አደራችሁ?

በትናንትናው እለት ማንነታቸው ባልታወቀ ግለሰቦች አንድ ትልቅ ህይወት ፣ ትልቅ ተስፋ የሰነቀ ወጣት ፣ ታዋቂ ድምፃዊ እና የዘፈን ግጥሞች ደራሲን ሀገራችን አጥታለች። እውነት ለመናገር እንደዚ ያሉ ድርጊቶች በሀገራችን ብሎም በአለም ላይ የሀገርን ሰላም ለመበጥበጥ ሲደረጉ በተደጋጋሚ አይተናል። ከ ኢ/ር ስመኘው ህልፈተ ሂወት በኃላ እንኳን ብዙ ሰምተናል። በዚ መልኩ የከረረ እንደሆነ ግን አስበንም አናቅም። ከፌደራል ፖሊስ የተስተካከለ ፣ እውነትን የያዘ መረጃ ሳይወጣ በፊት ማንም ኢትዮዺያዊ በሀሰተኛ የ social media መረጃዎች ተነሳስቶ ምንም ባያደርግ ይመከራል። አሁንም ቢሆን ባጣነው ውድ ነፍስ ለተጎዳቹ በሙሉ ፣ ሀዘን ውስጥ ለገባቹ በሙሉ ፣ ለሀጫሉ ሆንዴሳ ቤተሰቦችም ጭምር በቻናላችን ስም ትልቅ መፅናናትን እመኛለው። ነፍሱን በገነት ያኖራት ዘንድ ፀሎታችን ይሁን።
ሰላም ውድ የህብረ ቀለማት ቤተሰቦች

ለጥቂት ጊዜ በቴሌግራም ተራርቀናል በአካል ግን አሁንም እርቀታችንን እንጠብቅ።

ለየት ባለ አቀራረብ ወደናንተ በቅርቡ እንደርሳለን። እስከዛ በድሮ ፖስቶችም ከጓደኞቻችሁም ጋር በማውራት ናፍቆታችሁን ተወጡ።

መልካም ቀን ተመኘው
አጭር ፅሁፍ(የጊዜ ልጅ)

በህብረ ቀለማት ግጥሞች
ሰሞኑን ይጀመራል
@ethiopiagna
አጭር ተከታታይ ፅሁፍ(የጊዜ ልጅ)

በህብረ ቀለማት ግጥሞች
ዛሬ ማታ 1:00 ይጀመራል
@ethiopiagna
ትውውቅ 1⃣

ሳላውቃት ሳታውቀኝ ፣ ሳላቀው ሳታቀው ፤ ተፋቅረናል።

ገና መጀመሪያ እንዳየኃት የሚያምር ተክለ ሰውነቷ ሳይሆን ንግግሯ ነበረ ከሀሳቤ የቀረው። አውርተን እስክንጨርስ እኔን ብቻ ስሙኝ የሚያሰኝ ድምፇን ስኮመኩም ቆየው።

ገና እንዳየችኝ ምን እንደተሰማት ባላውቅም ፣ የወደፊት የህይወት አጋሯን እንደማልመስል ግን ከአስተያየቷ መረዳት ይቻላል። እንዲ ቢሆን ብላ ከኔ ላይ ያሉ ነገሮችን ስታስተካክል በአይኗ ላይ የተፈጠረው ምስል ፍፁም ከኔ ይለይ ነበር።

ውበቷ ላይ ትኩረት ሳልሰጠው መለያየታችን የደነቃት ብትመስልም ምንም የማይወጣላት ቆንጆ እንደሆነች ግን ታቅ ነበር።

ለባልነት የሚመጥን ፣ የትክክለኛ አባት ስብዕና ቢኖረኝም ከላይ አይታ ቢሆን ብላ ከምታስበው ሰው ጋር ማመሳሰሏ እየከነከነኝ ተለያየን።

አታቀኝ አላቃት

ሀሳብ ሁና አመሸችብኝ። በሷ በኩል ግን ትዝም እንዳላልኳት እርግጠኛ ነኝ።

በሁለተኛው ቀጠሯችን ግን ያለጥርጥር ሀሳብ ብቻ ሳይሆን ህልሟም ላይ ስተውን እንደነበር አልጠራጠርም።

በሁለተኛው ግንኙነታችን ትኩረት ልሰጠው የሞከርኩት ውበቷ ሰበባ ሰበቦችን ደርድሮ ተመሸገ። አማራጭ ስላልነበረኝ አሁንም በድምፇ ተገታው። ምንም ጥያቄ በማይፈጥር መልኩ ድጋሜ ሀሳብ ሁና አመሸችብኝ።

እያለ እያለ

መገናኘት ስናበዛ ፣ ሳታውቅ ሳላውቅ ተፋቀርን።

አሁን ድረስ የውበት መስፈሪያ ውብ መሆኗን ልመን እንጂ ለውበቷ ትኩረት አልሰጠውትም። ድምፇን ግን የብሄራዊ ፈተና ተፈታኝ ትምህርቱን ሊያጠና በሚችለው ልክ አጥንቼዋለው።

እሷ ከቁመና እስከ ውስጥ ማንነቴ አብጠርጥራ ባታቀኝም ፣ ከብዙ ወንዶች ጋር ተደርስሬ እኔን ጠቁሚ ቢሏት በጣቷ እንደምጠነቁለኝ አውቃለው። የባህሪኝ አይነት ዘርዝረው የሱን ባህሪ ምረጭ ብትባል እኔ የማላውቀውን ባህሪዬን ትመርጣላች።

ትውውቃችን ይሄ ነው።

ሳላውቃት ሳታውቀኝ ፣ ሳታቀው ሳላቀው
ልቤ ልቧን ፣ ልቧ ልቤን ድንገት ነው የሰረቀው

ማንነቷን አወደዋለው። ልዩ ሴት ናት።

ልዩነቴን መረዳት ጀምራ ቢሆን ብላ የምታስበውን ሰው ትታ እኔነቴን ብትቀበል እያልኩ ተመኘው።

ይህ ነው ትውውቃችን።

ይቀጥላል

አጭር ፅሁፍ በ ጊዜ ልጅ

@ethiopiagna
@ethiopiagna11
።፡የወዳጄ ወዳጅ🤷‍♂፡።

ከዕለታት በአንዱ ቀን
ከጓደኞቼ ጋር ተማሪ ቤት ሳለው
ቆመው ከነበሩት
ተማሪዎች መሀል አንዲት ጉብል አየው
ደብተር በደረትዋ
በአግድም አርጋ ይዛ
ከፊትዋ በቆመው የብረት ቀዳዳ ታይ ነበረ ተክዛ

ኤሎሄ ኤሎሄ
አልኩኝ እንዳየዋት
መስላኝ ጠቢብ ረቆ
በብራና የሳላት
በመገረም ስሜት በቀቢፀ ተስፋ
ታየኛለች ብዬ አየኖቼን ሳለፋ
እስዋ ግን በቆመው የብረት ቀዳዳ ስታይ ነበር ፈዛ

ደሞ አሰብኩና ከእጅ ያመለጠ እንዳይሆን ነገሩ
እንደ ሀገሬ ተረት
ላወራት ተነሳው ግራ ቀኝ አይቼ
ከተቀመጥኩበት
ወደ እስዋ ለመቅረብ
ከትቢያ ስጠጋ
ድንገት ሳለስበው የትካዜ መልክዋ
ወገግ ብሎ ጠፍቶ ፈገግታዋ መጣ

እኔም ያየችውን ለማየት ጓግቼ
የአይኖችዋን ጫፍ ይዤ ዞሬ ብመለከት
በበሩ ቀዳዳ
አንድ ወንድ ልጅ አየው ተደግፎ ግንቡን
ሰፋ ባለው ሜዳ

አይኔ ባየው ነገር ልቤ የሽቅብ መታ
ሆኖም ግን አልቻልኩም አይኖቼን ማሳረፍ
ከቀዳዳው ቦታ
ወዳጁን እንዳየ አተኩሬ ልጅን አየዋለው ባይኔ
ለካስ የኔው ጉድ ነው የእናት የአባቴ ልጅ
ግንቡን ተደግፎ የቆመው ወንድሜ

አቤቱ፥ እንደ ሸክላ ሩቢ ዳግም ላይጠገን ተሰበረ ልቤ
የወዳጄ ወዳጅ ሆና በመምጣትዋ ያውም የወንድሜ
ከእንዲህስ ወዲያ እኔ ሰው አልወድም
በበረደው ልቤ እሳት አላነድም

ብንጠቅስም ገልጠን ከመፃፎ
ለአንድ ሰው አንድ ይላል ምዕራፉ

አዶኒያስ(LikeTed)
20/11/2012
@ethiopiagna
@ethiopiagna11
ትውውቅ 2

ትውውቃችን በኛ ብቻ አልቆመም። የሷ ጓደኞች ፣ የኔ ቤተሰቦች ፣ የሰፈር ውስጥ ሰዎች ፣ ከአዋቂ እስከ ህፃን ድረስ ትውውቃችን በአዋጅ የተነገረ ይመስል ተዳረሰ። ሀገር ያወቀው ፀሀይ የሞቀው ትውውቅ መሰረትን።

የዛኔ ነው

ሀገራት ሲያውቁን ፣ የየአለሞች ፀሀያት ሲሞቁን ፤ የሀገራቶችን የወሬ ሽኩቻ የፀሀያቶቹን የሙቀት ቡጥጫ እኔም እሷም በየተራ ቀመስነው። ተፈተንበት። ትውውቃችን የማናቀውን ማንነታችንን በጥሩም በመጥፎም አሳየን። መኮራረች የማንችልበት ፈተና አጋጠመን።

ትውውቃችን ግን አሁንም አለ

ሰሞኑን ስለውበቷ ማሰብ ማሰላሰል ጀምሪያለው። ውብ እንደሆነች እያወቀች እነግራታለው። ሰሞኑን ልዩነቴ እየገባት ነው። ቢሆን ብላ ያሰበችኝን ሰው አልሁን እንጂ እምደዚው ተግባብተናል። ተቃምሰናል። የኑሮን ፈተናም ቀምሰናል።

በጋራ ልናልፈው የሚገባ ፈተናን ለየብቻ ጀመርነው። መኮራረች ባንችልም ፈታኞቹም ፣ ህግ አውጪዎቹም ፣ ተፈታኞቹም እኛው ስለነበርን በግልፅ መጠያየቅ ነበረብን። ግን

ሳይሆን ቀረ

ተፈታተንን

ቆማ አስፈተነችኝ ቆሜ አስፈተንኳት። ፈተናው ሳይከብደኝ አለፉኩ። እሷ ግን ግራ ተጋባች። ስፈተን ብወድቅስ በሚል ፍራቻ አለመፈተንን መረጠች። ያለፈታኝ ፈተናው የሚቀል ይመስል ያለኔ መፈተንም አማራት። እኔ ከሌለው ፈተናው እንደሌለ የገባት አትመስልም።

በንደዚ አይነት ውዝግብ ውስጥ በቆየች ቁጥር የትቀውውቃችን ግለት እንፋሎቱ የፈጃቸው ሁሉ ይዘባርቁ ጀመር። ድካሟን እያነሱ ጥርጣሬዋን ያሰፉት ቀጠል። አሉ አሉ ሞከሩ ደከሙ የፍቅር እንፋሎት ውስጣቸው ያለውን ጥላቻ እያጣላ ሲያተነው ግን መቋቋም አልቻሉም። በእኔ እሷ ትውውቅ ፣ ባልተሰጣቸው እና በማይገባቸው ስልጣን ራሳቸውን ሹመው ፈላጭ ቆራጭ ሆኑልን።

ከፍርዳቸው በጥቂቱ ሳይሆን በጥቅሉ ሳወሳ መለያየታችን የሚያነሳ ነበር። ሌላ እንድትፈልግ መከሯት ፣ አልቻሉም እንጂ ባል ቢያጩላት ደስታቸው ነበር። ዘላቂ የሆነ ትውውቅ መሆኑን በስጋት ጠየቋት ፣ አሁንም ቢችሉ እርሽው ተይው ባሏት። ከአንድ ወር በኃላ ስሟን አደለም እሷነቷን እንደምረሳው ነገሩኝ ፣ አልቻሉም እንጂ የተሳሰርንበትን አካል ቆርጠው እሷን ቢያስረሱኝ ተመኙ። በጥቅሉ መለያየታችንን ከትውውቃችን አግዝፈው ሊያሳዩን ሞከሩ። ግን አልቻሉም።

ሌላው አምስት ጣቱን በቀለበት አንቆ ሲጓዝ ትዝ ያላላቸው ፣ እሷ በአንድ ጣቷ ላይ ያረገቻት እንደ ሺ ታየቻቸው።

ስንቱ በሸራ ላይ በሀውልት መልክ የፍቅረኛውን ምስል ሲስል እና ሶቀርፅ ያልታያቸው ፣ እኔ በአንድ ወረቀት ያሰፈርኩት የሷ ምስል ከበዳቸው።

ዘባረቁ

ሰማናቸው

ፈተናዋን አከበዱት

ቃሏን ቃሌን አስረስተው እሷነቷን አጠፉት።

ያሰቡት ተሳካ ከሷ ማንነት ጋር የኔም እኔነት አብሮ ተነነ።

ይገርፋቸው የነበረ የፍቅር እንፋሎት ቀለል አለላቸው።

ስታገኘኝ ይሰማት የነበረው እና ሳገኛት ይሰማኝ የነበረው የእፎይታ ስሜት ማንነታችን ጋር ተጠራርጎ አለቀ።

እንደገና በአዲስ ፣ የውሸት ማንነት መተዋወቅ ግድ ሆነ።

አለም ያላወቀው ፀሀይ ያልሞቀው ፣ የመቀራረብ እንፋሎቱ እንኳን ጥላቻን ይቅርና በቅጡ አይን የሚያስጨፍን ሳይሆን የቀረ ፣ ስሜቶቻችን ረግጦ የያዘ ፣ መፋቀራችንን አርቆ የጣለ ፣ በዙሪያችን የሚዘባርቁት የኔ እና የሷን ቅርበት በሚፈልጉት ልክ ቀረፁት። እንደገና ተዋወቅን።

ሳላቀው ሳታቀው የተሰራረቀው ልባችን እያወቅነው አለም እና ፀሀይ ሰረቀው።

ያሁኑ ትውውቃችን በሰማይ ባለው ፈላጭ ቆራጭ እና ሁሉን ፈራጅ በሆነው በአንዱ ከፀና የተሰረቅነውን ፍቅራችንን ለማስመለስ በቂ ነው። ታድያ ግን መልሰን ስምፋቀር

የአለም ሹክሹታ
የፀሀይ ሙቀቷ

የዘባራቂ ወግ
የመለያየት ሳግ

ብቻ ሁሉም ነገር የማይበግረው ትልቅ ቤትን እንመሰርታለን።

ፍቅር ረቂቅነቱ ለጊዜው ነው። ከቀናት በኃላ አቅፈዋለው ፣ እስመዋለው ፣ እዳስሰዋለው

የኔ እና የሷን ትውውቅ የዘባራቂ ወግ ቢያጠነክረው እንጂ አይንደውም

አራት ነጥብ የማይፈልግ ትውውቃችን ይቀጥላል

አጭር ፅሁፍ በጊዜ ልጅ

@ethiopiagna
@ethiopiagna11
Forwarded from ግጥሞቼን እንካችሁ (🗿 mïçkéŷ) via @like
ጉድ ሆኜልሽ ነበር ትላንትና ማታ
ይድረስ ላፍቃሪዬ ፣ባለሽበት ቦታ
አንቺ እንዴት ነሽልኝ፣ የኔ ቸኮላታ
እኔ እንዳለው አለው ፣በአንድ አንቺው ትዝታ
እናፍቅሻለው ዘውትር፣ ጠዋት ማታ
ናፍቆትሽ በርትቶ፣ ያየለብኝ ለታ
የስልክ ወሬያችን፣ ቢለኩስ ትዝታ
ተክለፍልፌ መጣው፣ ምትኖሪበት ቦታ
ላገኝሽም ሳይሆን ፣ላይሽ ነበር ላፍታ
ተስፋም አልቆረትኩም፣ ጠበኩ እስከ ማታ
ቆይቼ ሳስታውስ ፣ትዝ አለኝ ኮሮና
መገናኘት አይሻም፣በፍቅር ለፀና
ድሮስ ምን ሊጠቅመኝ፣ በሩቁ ሰላምታ
ብዬ ልመለስ ስል ፣ወደ ገዛ ቤቴ
አስደንግጦኝ ሮጥኩኝ፣ የጎረምሳ ኮቴ
አባሮሽ ቀጠለ ፣ እስከ ሰፈር ቤቴ
ቤት እንደደረስኩኝ፣ ዞር ብዬ ሳየው በዛውም ለእረፍቴ
ለካስ ነበር ሯጩ ፣እስፖርተኛው ጓዴ በቄ ጎረቤቴ። በ ዡንታኦ 22-11-12 ዓ.ም
@Gtmochen_Enkachu
@GEcommentbot
@Gtmochgroup
Audio
@Gtmochen_Enkachu
ርዕስ📌 ጉድ ሆኜልሽ ነበር 📌
ገጣሚ ዡንታኦ
አንባቢ 🗣ተስፋዬ ንጉሴ🔈🔉🔊
💈@Tesfaye_Negussie💈
@ethiopiagna
ለተጨማሪ @Gtmochen_Enkachu
🇪🇹 እናመሠግናለን🇪🇹
ንግስት ሆይ👸

ንግስት ነሽ አሉኝ
የመሪዎች መሪ የሀገሩ አለቃ
ዝናና ጥበብሽ
እንኮን ተፅፎልሽ ታስቦ ማይበቃ
ከሊቅ እስከ ደቂቅ
ከሹም እስከ ሿሚ ከንጉስ እስከ አለቃ
እጅ ይነሱ ነበር በወርቅ እና ከርቤ ለክብርሽ መግለጫ

እኔም አጎብድጄ ከርቤ ተሸክሜ
መላሽን ፍለጋ መንግስትሽ ብመጣ
ብለው አባረሩኝ
በአካል አትገኝም ዳግም እንዳትመጣ
መላ ስላጣሆኝ አድራሽ ካገኘውኝ ይደርስሻል ብዬ
አዘጋጀው ላንቺ የግጥም ደብዳቤ
ነገሩ እንዲ ነበር
አንድ ልጅ ነበረች
ልቤን የማረከች ቆንጆ ገና ለጋ
ፍቅሬን ስገልፅላት
ፍቃድ እንኳን የላት ለመሆን ከኔጋ
ያልሞከርኩት የለም
በቅኔ መወድስ ፍቃድዋን ለማግኘት
አሁን ግን ንግስት ሆይ ቃሌን አስተጋቢ አንቺው ካለሽበት

ንግስት ሆይ ፍርድሽን እርጂኝ በጥበብሽ
ልቧን አንዳገኘው ነፍሷ ከእኔ ሳትሸሽ

እናማ ምግስት ሆይ
እኔ ፅፌያለውኝ የፋቅርሬን ደብዳቤ
እንዳይቀር ከክብርሽ ሸክፌ በከርቤ

ቃልሽ እውን ሆኖ
ቁራሹ ካደለኝ የዝክርሽ ቡራኬ
መልክቴን ያድርሰው የፍቅሩ አምላኬ🙏

አዶኒያስ(LikeTed)
19/10/2012

@ethiopiagna
@ethiopiagna11
ህብረ ቀለማት ግጥሞች
አጭር ተከታታይ ፅሁፍ(የጊዜ ልጅ) በህብረ ቀለማት ግጥሞች ዛሬ ማታ 1:00 ይጀመራል @ethiopiagna
በህብረ ቀለማት ግጥሞች አዲስ ስለተጀመረው ፅሁፍ ማንኛውንም አይነት አስተያየት @lanchi_new11 ላይ አድርሱን።
ትውውቅ 3

ፍቅር ረቂቅነቱን ሊያሳየኝ ቆርጦ የተነሳ መሰለኝ። በዘባራቂ ወግ ፍላጎት ልክ የተቀረፀው ትውውቃችን እያስጠላኝ መጣ። ትውውቃችን አራት ነጥብ የሚያስፈልገው መሰለኝ። ፍቅራችን ፍርስርሱ ሲወጣ ተሰማኝ። በሷ ውስጥ በድንገት የጠፋውን ማንነቷን ፍለጋ ስል እኔ ራሴን አጣውት። መሽቶ ሲነጋ እና ከእንቅልፌ ስነቃ ሰክሮ እንዳደረ ሰው ያንጎላጅጀኛል ፣ እሷን እያሰቡ ማደር እረፍት ነስቶኝ ኖሮ ጠዋት ከእንቅልፌ ሳይሆን ከሀሳቤ መንቃ ት ልምድ ሆነ።

ውስጤ ብዙ ጥያቄ ተፈጠረ።

የኛን መለያየት የፈለጉ ሁሉም የተሳካላቸው መሰለኝ። ከአንድ ወር በፊት " ከወር በላይ አዘልቁም " ብለው ያሉንን ሰዎች አሰብኳቸው። ምን ያህል በትንቢተኛነታቸው እንደሚደሰቱ ሳስብ እበግናለው። ከኔ የተሻለ እንደሚገባት የነገሯትን ሳስብ ፣ ዘላቂ መሆኑን እንድጠራጠር ያደረጓትን ሳስብ ፤ ውስጤ አንዳች የፈላ ነገር ሲፈስበት ይሰማኛል።

በአዲሱ ትውውቃችን እንደማንራራቅ የተነጋገርን ቢሆንም አለመራራቁን አልቻልም። ክፍተት ተፈጠረ። ስጋታችን ጨመረ። ልንለያይ ይሆን? አላቅም። ምናልባት ትውውቃችን እስከዚ ብቻ ይሆናል መጓዝ የተፈቀደለት። ግን ደሞ እኛ ከዚም በላይ መንገድ አዘጋጅተንለት ነበር ብዙ መጓዝ ይችል ነበር። ግን አልተጓዘም። ብዙ ልንሆን ፣ ብዙ ልናደርግ ፣ ብዙ ልንፈጥር ብዙ ብዙ ነገር ይገባን ነበር ግን ሳይሆን ቀረ።

የቀዘቀዘ አይነት ትቅውውቅ ጀመርን።

በቀን አራት ጊዜ ድምፇን ከመስማት ወደ ምንም ያህል ጊዜ ደምፇን አለመስማት

በሁለት በሶስት ቀን አንዴ ከመተያየት ጭራሽ ምንም ወዳለመተያየት

ከፍቅር ፣ ከጓደኝነት ሰላምታ ወደ አይን ሰላምታ (እሱም ካገኘዋት)

በቃ እንዲ እንዲ እያለ ትውውቃችን ቀዘቀዘ። በረዶ ሰራ

አገር አውቆት ፀሀይ ሞቆት የነበረ ትውውቅ ሰው ወደማያውቀው በረዷማ ትውውቅ አመራ

ትውውቃችን አራት ነጥብ የፈለገ መሰለኝ

ግን አላረግበትም

ፍቅር ረቂቅነቱን ሊያሳየኝ ይሞክር እንጂ ፅኑነቱን ግን አውቀዋለው

በትዕስት ፀንቼ ትውውቃችን አስቀጥለዋለው

አራት ነጥብ የማይሻ ሳይሆን አራት ነጥብ ቢሻም ስለማይገባው የማልሰጠው አይነት ትውውቃችን ይሄ ነው

አጭር ፅሁፍ "ትውውቅ"
ፀሀፊ "የጊዜ ልጅ"

@ethiopiagna
@ethiopiagna11
ህብረ ቀለማት ግጥሞች pinned «በህብረ ቀለማት ግጥሞች አዲስ ስለተጀመረው ፅሁፍ ማንኛውንም አይነት አስተያየት @lanchi_new11 ላይ አድርሱን።»
ትውውቅ 4

ግልፅነት

ይሄ ነገር በኛ ትውውቅ ውስጥ ትልቅ ድርሻ ነበረው። መተሳሰብ እና ፍቅር የተቀረውን ድርሻ ይወስዳሉ። አለመተማመን እና ጥርጣሬ በጣም ትንሽ ድርሻ ተሰቷቸዋል። ግን ስራቸውን የሚወስነው የድርሻቸው ስፋት አልነበረም።

በጣም ትልቅ የእርሻ መሬት ላይ ሁለት ሰዎችን አርሰው ፣ ዘርተው ፣ አርመው ፣ አጭደው ፣ ከምረው ፣ ወቅተው ፤ ሁሉን ለብቻቸው አድርገው እንዲያቀርቡ ተገደዱ።

በሌላ በኩል ደሞ

በጣም ትንሽዬ የእርሻ መሬት ላይ ብዙ አባወራዎች ፣ ብዙ እናቶች ፣ ብዙ ብዙ ወጣቶች ፤ በትልቁ መሬት ከተሰማሩት ጋር ተመሳሳይ ነገር እንዲያደርጉ ታዘዙ።

ሁለቱ ትልቁን እርስታቸውን አርሰው ሳይጨርሱ ብዙዎቹ ትንሿን አርሰው ፣ ዘርተውባታል።

ሁለቱ ሰዎች ትዕግስት አላቸው። አንዱ አንዱን ያበረታታል። አይደክሙም።

ብዙዎቹ ሰዎች ግን ትዕግስት የላቸውም። ግን ደሞ አንዱ ቶሎ ሲሰለች ሌላኛው ይቀበላል።

ታድያ ሁለቱ ሰዎች አርሰው የጨረሱ ግዜ መዝራት ሲጀምሩ ብዙዎቹን አስደነገጣቸው። ምክንያቱም ከተዘራ በኃላ ያለው ውጤት ወይም የክምሩ ብዛት የነሱን 10 እጥፍ ይሆን ስለነበር።

አወጡ አወረዱ

በመጨረሻም ከአንድ ሀሳብ ላይ ደረሱ

ብዙዎቹ ሰዎች ሁለቱ ሰዎች የሚለያዩበትን ሰዐትን እየጠበቁ በግዙፉ መሬት ላይ የዘሩትን ማጨድ ይጀምራሉ። ከዛም ያቃጥላሉ።

በዚህ አይነት ሂደት ለጥቂት ቀናት ቀጠሉ።

ሁለቱ ሰዎች ግን ሲገናኙ እርስታቸውን እንጂ የተዘራውን ዘር ከለት ለት መቀነስ አላስተዋሉም።

ሁለቱ ሰዎች አርሰው ለመዝራት የፈጀባቸውን ቀን ግማሽ ብቻ ፈጀባቸው የተዘራውን አጭዶ ለማቃጠል።

እንደተለመደው ከእርስታቸው ሲገናኙ የበቀለው አዝርት የለም።
መደናገጥም መናደድም ታየባቸው።

አንተ ነህ አንተ ነህ መባባል አበዙ

በመጨረሻም ከውዝግብ ብዛት ከሁለቱ አንዱ ሰው ህብረታቸውን ስላልወደደው እና በብዙዎቹ ተንኮል ውስጡ ስለተነካ ሌላ ጥሩ ህብረት ፍለጋ ጓዱን ትቶት ሄደ።

በጉዞውም ከብዙዎቹ ጋር የነበረን አንድ ታታሪ ሰው ያገኝ እና ከሱ ጋር ይጣመራል።

ልክ እንደበፊቱ አይነት ግዙፍ መሬት ለሁለቱ (ለበፊቱ አንድ ሰው እና ለ አዲሱ ተጣማሪው) ተሰጣቸው። ማረስ ጀመሩ።

ያርሳሉ

ያርሳሉ

ከዛኛው ጓዱ ጋር የነበረው አንዱ አንዱን የማበረታታት ነገር ግን አልነበረም። ግዙፉን መሬት ለሁለት ተካፍለው ማረስ ጀመሩ። አዲሱ ህብረት እንደታሰበው አልሄደም።

የበፊት ጓዱ ትዝ እያለው ተቸገረ

ይሄኛው በፊናው "ይሄኔ ከብዙዎቹ ጋር ብሆን እንዲ አልደክምም" እያለ ያስብ ጀመር።

በፀፀት የተሞላ ህብረት

ሰላም ሳይኖር ስራ

በቃ አዲሱ ህብረት ይህ ነበር

ከብዙዎቹ አንዱ የነበረው ሰው ብቻውን ከአንድ ሰው ጋር መስራት ፣ ማረስ አልቻለም።

ለምን?

ለለምን መልስ የለም!

ከጅምሩ ብናስተውል አሁን ለምን አንልም። ከመነሻው የብዙዎቹ አላማ ማጨድ እና ማቃጠል እንጂ በአናሳ ቁጥር ሰርቶ መብላት አልነበረም። የብዙዎቹ ታታሪነት የተገነባን ማፍረስ ላይ እንጂ መገንባት ላይ አልነበረም።

በአዲሱ ህብረት የተካተተው አዲሱ ሰዉም ከብዙዎቹ አንዱ እንጂ ከሌላ ወገን የመጣ አደለም።

እንዳልኳቹ በኛ ትውውቅ ውስጥ ለግልፅነት ትልቅ ቦታ ሰተናል። መተሳሰብ አለን። ፍቅርን እንሰራለን።

ትንሿ ቦታ የሰጠናት አለመተማመን እና ጥርጣሬ በብዙዎች ታታሪነት የዘረናውን ፍቅር አመድ አረገው።

ብቻዬን አንድ ግዙፍ መሬት ላይ ነኝ።

አንድ ሰው ብቻውን ግልፅነትን ፣ መተሳሰብን ፣ ፍቅርን ቢይዝ ምን ዋጋ አለው።

ግልፅ ከሆነ ፤ ግልፅ የሚሆንለት አጋር ይፈልጋል።
መተሳሰብን ከቻለ ፤ የሚያስበለት ጓድ ይሻል።
ፍቅር ካለው የሚፈቀር ግድ ይላል።

ህበረታችን ትውውቃችን ነው

ትውውቃችን አራት ነጥብ አይገባውም

አንተ ነህ አንተ ነህ የተባባሉት ሁለቱ ባለመሬቶች እናንተ ናቹ ብለው ወደ ብዙዎች መጠቆምን ሲማሩ አልያም ደሞ እኛ ነን ማለትን ሲችሉ ፤ ያኔ ትውውቃች ይፀናል።

ለፅሁፌ እንጂ ለኔ እና አንቺ ትውውቅ የማልሰጠው ነገር ቢኖር ። ይህች አራት ነጥብ ብቻ ናት ።

ብቻዬን ግዙፉን መሬት አርሳለው

ልቤ ውስጡ ትዕግስት አለው



አጭር ፅሁፍ "ትውውቅ" ክፍል 4
ፀሀፊ "የጊዜ ልጅ"

@ethiopiagna
@ethiopiagna11
HTML Embed Code:
2024/06/05 14:14:49
Back to Top