TG Telegram Group Link
Channel: ከስነ-ፅሁፍ ዓለም
Back to Bottom
ዳ ን ኤ ል ፐ ር ል
━━━━━━━
«ጋዜጠኝነት የቀጨው ጋዜጠኛ»
@ethiobooks
Audio
ዳንኤል ፐርል - 1
Audio
ዳንኤል ፐርል - 2 የመጨረሻው!
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
📔 መጽሐፈ ትዝታ ዘአለቃ ለማ

>>>
ሰውየው አረጀ። ቁጭ ብሎ ሳለ፣ ሰውነቱ እጁ እግሩ ይጠያየቁ ጀመረ።

'ዓይን እንደምንድነህ?' አሉት እጅና እግር።

'አሄሄ! ሌሊት በጨለማ ምንገዱን ለይቼ እሄድ የነበረ፤ ዛሬ ጠሐይ መለስ ሲል አልታየኝ አለ'

'እግር እንደምን ነህ?'

'አዬ! የኔ ነገር ቀርቷል። አቀበቱን ስወጣው ቁልቁለቱን ስወርደው ስብር ስብር እል የነበረ፤ ወንዙን ዘልየ ስሻገር እንደ ቆቅ እሽከረከር የነበረ፤ ዛሬ የቤቴን መድረኩን መሻገር ተሣነኝ - እወጣለሁ ስል ያሰናክለኛል' አለ እግር።

'እጅ እንደምን ነህ?'

'አዬ! ወንዙን አሻግሬ እመታ የነበረ፤ ወደፊት እወረውርሃለሁ ያልኩት ወደ ኋላዬ ይወድቅ ጀመረ' አለ።

'ጥርስ እንደምን ነህ?'

'አዬ! ባቄላውን አተሩን ጥሬ ቆሎውን ስበላው ሳደቃቅቀው አጥንቱን የነበረ፤ አሁን ፍትፍቱን ለመብላት ተሣነኝ።'

'ልብሣ እንደምን ሁነሃል?' አሉት።

'ኧኸኸ! ወትሮ ከነበርኩበት እድር ከፍ ብዬ ወደ አንገት ጠጋ ብዬ ተቀምጫለሁ' አለ።

'ሁሉም አባይ ነው' አለ ሰውየው

'እውነተኛ ልብ ብቻ ነው!' እማያረጅ፤ እማይደክም ልብ ብቻ ነው።
>>>

━━━━━━━━
መንግሥቱ ለማ እንደጻፈው
📄 205
🗓 ፪ሺህ፯ ዓ.ም.
አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ፕሬስ

📖 📖 📖 📖 📖
https://hottg.com/Ethiobooks
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ሽማግሌው አናፂ
━━ 🔨━━

ሽማግሌው አናፂ ለበርካታ ዓመታት ሰለቸኝ ደከመኝን ሳያውቁ ታትረዋል። የሚሠሩበት የኮንስትራክሽን ድርጅት ቀደምት ሠራተኛም ናቸው። ታታሪነታቸውን ማንም ይመሰክራል - የሥራቸው ጥራትስ ቢሆን። አሁን አሁን ግን ዕድሜም ተጫጫናቸው መሰል ደከመኝ ማለት አምጥተዋል።

እንዲያውም አሁን በስተመጨረሻ፣ ድርጅቱን በሥራ አስኪያጅነትም ጭምር የሚያስተዳድረው የድርጅቱ ባለቤት ቢሮ ገብተው፣ “ይብቃኝ፣ አረጀሁ፣ ደከመኝ” አሉት። ለ30 ዓመታት ከሠሩበት ድርጅት ሲለቁ ዳጎስ ያለ የጉልበት ድካማቸውን እንደሚያገኙ ግልጽ ነው። በዚህችው ጥሪት ቀሪ ሕይወትን መግፋት ነው እንጂ ብለዋል ሽማግሌው አናፂ።

መቼም 'ሸክላ ሠሪ በገል ይበላል' ሆኖ፣ ለድርጅቱ በርካታ ውብ ከእንጨት የሚሠሩ ኮሎኒያል በሚል ስም የሚታወቁ ቪላዎችን ሲያንጹ ኖረው እሳቸው ግን እንደነገሩ በሆነች ዛኒጋባ ውስጥ ቢኖሩም፣ አያማርሩም! የእርጅናን ዘመን የሰው እጅ ሳያዩ በቋጠሩት ጥሪት ማሳለፍንስ ቢሆን ማን አይቶባቸው። ይህንኑ ነው የሚሉት እሳቸውም ቢሆኑ።

ለመልቀቅ የመፈለጋቸውን መርዶ የሰማው ወጣቱ የድርጅቱ ባለቤት በትካዜ አቀረቀረ። እሳቸው ለእሱ የድርጅቱ ታታሪ ሠራተኛ ብቻ አይደሉም። ድርጅቱን ያወረሱት አባቱ በሕይወት በነበሩበት ጊዜ ጀምሮ ነው የሚያውቃቸው።

እኒህ ጠንካራና ታታሪ አናፂ፣ “አሁን በቃኝ ሥራዬን ልተው ነው…” ሲሉት በአንዳች ጥልቅ ስሜት እንደተዋጠ ቀረ። ስለ ጤናቸው ጠያየቃቸው። አስፈላጊ ነገሮች ሁሉ በአስቸኳይ ተፈጽመው የጉልበት ድካማቸውን ክፍያ ከሳምንት ባልበለጠ ጊዜ ውስጥ እንደሚዘጋጅላቸው ገልጾ ከማሰናበቱ በፊት ግን… እንዲሠሩለት የሚፈልገው አንድ የመጨረሻ ሥራ እንዳለ አስታወሰ።

አዎን... ሥራቸውን ከመልቀቃቸው በፊት፣ የካበተ ልምድ ያላቸው እኒህ ጎበዝ አናፂ፣ አንድ የመጨረሻ ቪላ እንዲሠሩለት ይፈልጋል። ሽማግሌው አናፂ ተከፉ። ግን መቼስ ምን ማድረግ ይችላሉ። መከፋታቸውን ሸሽገው፣ የተባሉትን ይሄን የመጨረሻ ቪላ ሊያንፁ ቢሮውን ጥለው ወጡ።

ከሁለት ወራት አድካሚ ሥራ በኋላ የመጨረሻው ቪላ ተሠርቶ አለቀ። እነሆ አሁን ሥራውን ሊያስረክቡ ወጣቱን የድርጅቱን ሥራ አስኪያጅ ጠርተውታል። እናም… ሁሉም በተሰበሰበበት፣ በስተመጨረሻ፣ አናፂው የሠሩትን የመጨረሻ ቪላ ለወጣቱ አሳይተው የቤቱን ቁልፍ አስረከቡት።

ወጣቱ የድርጅቱ ሥራ አስኪያጅ ግን በተመለከተው የሽማግሌው አናፂ የመጨረሻ ሥራ ክው ብሎ ቀረ። እንዴት ሊሆን ይችላል ሲል አሰበ። ሽማግሌውን ሲያውቃቸው በጥንቁቅ ባለሙያነታቸው ነው። አሁን ግን ሠርተው ያስረከቡት ቪላ፣ ፈፅሞ በእሳቸው የተሠራ የማይመስል፣ መናኛ ቪላ ነበር።

በጣም ነው ያዘነው ሥራ አስኪያጁ። በግብር ይውጣ፣ ልባቸው ሳይፈቅድ የሠሩት የዚህ መናኛ ቪላ ጉዳይ በጣሙን ያሳዘነው ግን በአንድ ምክንያት ነበር። አዎን… ይህን የመጨረሻ ቪላ እንዲሠሩለት የጠየቃቸው ቤት መግዛት ለሚፈልግ ደምበኛ አልነበረም። ይልቁንም፣ ለሽማግሌው አናፂ ለራሳቸው እንደ ከ'የሥራ-ዘመን' መሰናበቻ ስጦታነት አስቦ ነበር ይህን ቪላ ሥሩልኝ ያላቸው።

እናም፣ ቀድሞውኑም ያሰበው ለራሳቸው ለአዛውንቱ አናፂ ነበርና፣ እያዘነ፣ ያንኑ እንደነገሩ የተሠራውን የቪላ ቤት ቁልፍ፣ መልሶ አስረከባቸው።
━━━━━━━━
ግሩም ተበጀ
📔 ግሩም የዓለማችን ምርጥ ታሪኮች
📄 179 - 180
📖 📖 📖 📖 📖
https://hottg.com/Ethiobooks
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ፀ ጉ ር
👨‍🦱 👨‍🦱

👨‍🦱
ፀጉር እና ጥፍር የሚሠሩት ኬራቲን ከተባለ የፕሮቲን ዓይነት ነው።

👨‍🦱
አንድ ሰው በሕይወት ዘመኑ 593 ማይልስ ፀጉር ያበቅላል።

👨‍🦱
አንዲት የፀጉር ሰበዝ በወር 1.2 ሳ.ሜ. ታድጋለች።

👨‍🦱
በአንድ ሰው ራስ ላይ ያሉት 100,000 ያህል ፀጉሮች ደግሞ በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ በድምሩ 1.2 ኪ.ሜ. ያድጋሉ።

👨‍🦱
በጣም ፈጣን ዕድገት የሚያሳየው የፀጉር ክፍል ሪዝ ነው።

👨‍🦱
የአንዲት ፀጉር ውፍረት 0.05 ሳ.ሜ. ነው።

👨‍🦱
አንዲት ነጠላ ፀጉር 100 ግራም ክብደት ያለው እቃ ማንጠልጠል ትችላለች።

👨‍🦱
የአንድ ሙሉ ሰው ጉንጉን ፀጉር 12 ቶን ክብደት ማንጠልጠል ይችላል። 

👨‍🦱 
በየቀኑ 80 የፀጉር ሰበዞች ከራስ ቅላችን ላይ ይነቀላሉ።

👨‍🦱 
ፀጉራችን ከበጋ ይልቅ በክረምት ወር ፈጣን ዕድገት ያሳያል።

👨‍🦱
ወሲብ ለመፈፀም በዝግጅት ላይ ያለ ሰው ፀጉሩ በ0.001 ሳ.ሜ. ያድጋል።

👨‍🦱
በሕይወት ዘመን በአንድ ሰው አፍንጫ ውስጥ የሚበቅለው ፀጉር ቢቀጣጠል 6 ጫማ ርዝመት ይኖረዋል።

━━━━━━━━
📖 📖 📖 📖 📖
https://hottg.com/Ethiobooks
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
አ ት ረ ሳ ም
══✦══
ሜሮን ጌትነት
'
ረስቻታለሁ የለኝም ትዝታ
አላስታውሳትም ጠዋትና ማታ
ትለኛለህ አሉ
ላገኘኸው ሁሉ
ምንም ብንራራቅ ባንሆን እንደ ድሮ
ያሳለፍነው ጊዜ አይቀርም ተቀብሮ
አውቃለሁ አትረሳም መች አጣሁት እኔ
ለኒያ ጎረቤትህ ይስጥልኝ እንጂ ዕድሜ
ሞክሼ ልጃቸውን በማዕረግ ካልዳሩ
ወይ ቤት ካልቀየሩ
አትረሳኝም ከቶ
ጠዋትና ማታ ስሜን እየጠሩ።
═══════
📔 ዙ ረ ት
📖 📖 📖 📖 📖
https://hottg.com/Ethiobooks
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ሄ ን ሪ ኪ ሲ ን ጀ ር
━━━━━━━
«ዕድሜያማው ዲፕሎማት»
@ethiobooks
Audio
ሄንሪ ኪሲንጀር - 1
Audio
ሄንሪ ኪሲንጀር - 2 የመጨረሻው!
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ገዴ /ገድ ገድዬ/
══ 🐦‍⬛️ ══
ካሕሳይ ገ/እግዚአብሔር
'
ገዴ ልዩ ባህርይና አኗኗር ካላቸው የአሞራ ዓይነቶች አንዱ ነው። መልኩ ከሆዱ (ከደረቱ) በኩል በጣም ነጭ ሆኖ ጀርባው ጥቁር ነው። በመሆኑም ከሩቅ ሲያዩት ከስር ነጭ ኩታ ለብሶ ከላይ ጥቁር ካባ የደረበ ካህን (ቄስ) ይመስላል።

ገዴ በትግራይ፣ በዋግ ሕምራና በከፊል ሰሜን ጎንደር ገድ ገድዬ እየተባለ ይጠራል። ገዴ የደስታ፣ የምስራች፣ የመልካም ነገር ተምሳሌት ተደርጎ ስለሚታመንበት በትግራይ «ገዴ ገድየ ሐጎስ» ብለው የሚጠሩትም አሉ።

ሰዎች በመንገድ ሲሄዱ ገዴ ነጭ ደረቱን ወደ እነርሱ አቅጣጫ አዙሮ ቁጭ ብሎ ካጋጠማቸው ያሰብነው ሁሉ ይሳካል፣ መልካም ነገር ያጋጥመናል ብለው ያምናሉ፣ ‹ገድ አውለኝ› ብለውም ጉዞአቸውን በደስታ ይቀጥላሉ። በአንጻሩ ጀርባውን ወደ እነርሱ አዙሮ ካገኙት የፍርድ ቤት ቀጠሮም ቢኖርባቸው ይመለሳሉ እንጂ ቅጣትንና እስራትን ፈርተው አይሄዱም።

ገዴ ሲጮኽም ሆነ ሲበላ አይታይም። ይሁንና አንድ ታዋቂ ሰው የሚሞት ከሆነ ማታ በሟቹ ቤት አጠገብ ከበሩ በስተግራ አቅጣጫ ካለው ዛፍ ላይ ሆኖ የተለየ የመርዶ ድምፅ ያሰማል። ሰዎች ይህንን ስለሚያውቁም የታመመ ሰው ካለ ለቀብሩ የሚያስፈልገውን ቅድመ ዝግጅት ያደርጋሉ። የታመመ ሰው ከሌለም «ገዴ ጮኻለች ማን ይሞት ይሆን?» እያሉ ይጨነቃሉ።

ገዴ (ገድ ገድዬ) ሌላም አስገራሚ ባሕርያት አሉት። ሴት ገዴ እንቁላሏን የምትጥለው ሰው ከማይኖርበት ቦታ ራቅ ካለ ሥፍራና ከሰዋራ ቦታ ነው። በመሆኑም የገዴ እንቁላል ማግኘት ከባሕር ወለል ድረስ ዋኝቶ እንቊ የማውጣት ያህል ከባድ ነው። በአጋጣሚ ከተገኘ ግን ዋጋው እጅግ ውድ ነው። የጥንት አባቶች በገዴ እንቁላል የተለያዩ ተአምራዊ ተግባራትን ያከናውኑ እንደነበር ይነገራል። ...

ሌላው የገዴ አስገራሚ ባሕርይ በተፈለገውና በየጊዜው አለመታየቱ ነው። ከዚህም በላይ የፈለገው አነጣጣሪ ተኳሽ ከቅርብ ርቀትም ቢሆን በጥይት ተኩሶ መምታት አይቻለውም። ገዴ ባገኘው ዛፍ ላይም አይቀመጥም። ገዴ ከዓመት እስከ ዓመት ቅጠላቸው እንደለመለመ በሚቆዩ እንደ ወይራ፣ ዶቅማ፣ ማቅማ በመሳሰሉ ዛፎች ወይም ቋሚ አለት ላይ ነው የሚያርፈው።
━━━━━━━━
📔 ኅብረ - ብዕር አንደኛ መጽሐፍ
📄 152 - 154
📖 📖 📖 📖 📖
https://hottg.com/Ethiobooks
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
‹ገድ› እና 13 ቁጥር
━━━✦━━━

በተለምዶ 13 ቁጥር የገደቢስነት ምልክት ተደርጎ ይወሰዳል። ይህ እምነት የተጀመረው የዛሬ ሁለት ሺህ ዓመት ገደማ ሲሆን አስራ ሁለቱ ሐዋርያት እና ኢየሱስ ክርስቶስ የመጨረሻውን የጌታ ራት ለመብላት በማዕድ ዙሪያ ተቀምጠው ሳለ ቁጥራቸው 13 እንደነበር እና በነጋታው ኢየሱስን አሳልፎ የሰጠው ይሁዳ ራሱን እንዳጠፋ፣ ክርስቶስም ተይዞ ስቅላት እንደተፈረደበት ከሚገልፀው ታሪክ ጋር ተያይዞ የመጣ ነው። ይህ ስሜት የአስራ ሦስትን ገደቢስነት በሰዎች አዕምሮ ውስጥ አሰረጸ።

➥ 13 ቁጥርን አጥብቆ የመፍራት ስነ-ልቦናዊ አባዜ ‹ትሪስካ ዴካ ፎቢያ› ይባላል።

➥ በብዙ አገሮች ሆቴሎች ውስጥ 13 ቁጥር አልጋ የለም። በአያሌ አይሮፕላኖች ውስጥም 13 ቁጥር መቀመጫ የለም። በአንዳንድ ቦታዎች 13 ቁጥር በሎተሪ ቲኬት ውስጥ አይካተትም።

➥ በትላልቅ ሆስፒታሎችም እንደሚታየው 13 ቁጥር አልጋ እንዳይኖር ይደረጋል። በህሙማን ላይ ስነ-ልቦናዊ ጫና እንዳይፈጥር በመስጋት ብዙ የኦፕሬሽን ክፍሎች 13 የሚል መለያ ቁጥር እንዳይኖራቸው ተደርጓል።

➥ በአንዳንድ አገሮች 13 እና አርብ ሲገጥም አያድርስ ፍርሃት ያመጣል። በዚህም ምክንያት የወሩ አስራ ሦስተኛ ቀን አርብ ላይ ከዋለ በተለይ የግል ድርጅት ያላቸው ባለሀብቶች ወደ ሥራቸው አይገቡም። በዚህም በብዙ ሚልዮን ዶላር የሚቆጠር ኪሳራ ይደርሳል።

➥ በአስራ ስምንተኛው ክፍለ ዘመን ካፒቴን ጂም ፍሪይዴይ የተባለ መርከበኛ በዕለተ አርብ በወሩ አስራ ሦስተኛው ቀን ‹HMS Friday› የተባለች መርከብ ይዞ ጉዞውን ቀጠለ። አሳዛኙ ገጠመኝ ግን መርከቡም መርከበኛውም በዚያው እንደወጡ መቅረታቸው ነው። እስከ አሁን ድረስ የመርከቢቷ ደብዛ አልተገኘም።

➥ አሜሪካኖች ጨረቃ ላይ በመንኩራኩር ለመድረስ አስር ጊዜ ሙከራ አድርገው ሳይሳካላቸው ቀረና በአስራ አንደኛው ሙከራ አፖሎ 11 በተባለች መንኩራኩር የሰው ልጅ ጨረቃ ላይ ሊወጣ ችሏል። ቀጥሎ አፖሎ 12 ተላከች፤ አሁንም ተሳካ።

➥ በማስቀጠል አፖሎ 13 ተላከች ነገር ግን ሙከራው ሳይሳካ ቀረ። አፖሎ 14 የተባለች መንኩራኩር ስትላክ ሙከራው በሚገባ ግቡን መታ። እንደዚህ ዓይነት ከ13 ቁጥር ጋር የተያያዙ በርካታ ምሳሌዎችን ማቅረብ ይቻላል።

➥ ለአንዱ ‹ገደ-ቢስ› ቁጥር ለሌላው የእድል ቁጥር ሊሆን ይችላል። ጣልያን ውስጥ በአንዳንድ ስፍራዎች 13 ቁጥር ተወዳጅ ቁጥር ነው። እንዲሁም ለግራኞች ‹ገድ› አለው ተብሎ የሚታመንበት ቁጥር 13 ነው።
━━━━━━━━
📔 የዕውቀት ማኅደር
በዶክተር ኬ.ኬ.
📖 📖 📖 📖 📖
https://hottg.com/Ethiobooks
HTML Embed Code:
2024/05/21 09:33:43
Back to Top