TG Telegram Group Link
Channel: የኢትዮጵያ አድባራትና ገዳማት ታሪክ
Back to Bottom
«ወደ እግዚአብሔር የምንጸልየው፥ መረጃ ወይም መመሪያ ልንሰጠው ሳይሆን፥ ወደ እርሱ እንድንቀርብና ከእርሱ ጋር ኅብረት ያለን እንድንሆን ነው።»
ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ

https://hottg.com/ethioadbrat
+ የሚሮጥ ዲያቆን +

የዛሬ ሁለት ሺህ ዓመት ገደማ ነው:: አቧራማውን የጋዛ ምድረ በዳ በፈጣን ሩጫ እያቦነነ የሚከንፍ አንድ ወጣት ታየ:: ሩጫው የነፍስ አድን ሠራተኞች ዓይነት ፍጥነት ያለው ነበረ:: አንዲትን ነፍስ ሳታመልጠው ለማትረፍ እየከነፈ ነው:: የሚሮጠው ደግሞ በፍጥነት በሚጋልቡ ፈረሶች የሚጎተት የቤተ መንግሥት ሠረገላ ላይ ነው:: በሰው አቅም ፈረስ ላይ ሮጦ መድረስ ባይቻልም ይህ ወጣት ግን ፈረሶቹ የሚያስነሡትን የጋዛን አቧራ በአፉ እየቃመ በአፍንጫው እየታጠነ እንደምንም ደረሰ::
በሠረገላው ውስጥ አንድ ጸጉረ ልውጥ የሩቅ ሀገር ሰው ተቀምጦ በእርጋታ መጽሐፍ እያነበበ ነው::

እግሩን እንደ ክንፍ ያቀለለው ሯጩ ዲያቆን ፊልጶስ ይባል ነበር::  በዚያ ምድረ በዳ ብቻውን ሲሮጥ የሚያጨበጭብለት ሰው የሚሸልመው ደጋፊ አልነበረም:: እንዲያውም ልብ የሚሰብ ኀዘን ላይ ነበረ:: እስጢፋኖስ የሚባል አብሮት ዲቁና የተሾመ የቅርብ ጓደኛውን በድንጋይ ወግረው በአሰቃቂ ሁኔታ ከገደሉበት ገና አርባ ቀን አልሆነም:: "ቤተክርስቲያን ስደት ላይ ሆና ምን ስብከት ያስፈልጋል?" በሚል ቀቢጸ ተስፋ እጁን አጥፎ ያልተቀመጠው ፊልጶስ ግን የወንድሜን ኀዘን ልወጣ ሳይል የምሥራች ለማብሠር በበረሃ ሮጠ::

ቀርቦ ያናገረው ጃንደረባ ደግሞ  "የሚመራኝ ሳይኖር እንዴት ይቻለኛል?" የሚል ኦሪትን ይዞ ትርጓሜ ፍለጋ የሚቃትት ፣  ጥላው ይዞ አካሉን ፍለጋ የሚጨነቅ ትምህርት የተጠማ ኢትዮጵያዊ ነበረ:: ስለዚህ ይህ ዲያቆን መዳን የምትሻውን የጃንደረባውን ነፍስ በመዳን እውቀት አረስርሶ አሁኑኑ ካልተጠመቅሁ አሰኛት:: ብቻውን የሮጠውና አንድ ሰው ያስተማረው ዲያቆን ፊልጶስ ሮጦ ያዳነው አንድ ሰውን ብቻ አልነበረም:: በአፍሪቃ ቀንድ ለምትገኘው ሀገር ኢትዮጵያና ሕዝቦችዋ የመዳን ቀንድ የሆነ ክርስቶስን አሳያቸው::  አንድ ኢትዮጵያዊ አጥምዶ በእርሱ ብዙዎችን ከማጥመድ በላይ ምን ሙያ አለ?   ጴጥሮስን በጀልባው ላይ ከዓሣ አጥማጅነት ወደ ሰው አጥማጅነት የቀየረ አምላክ ገንዘብ ያዡን ባኮስ ነፍሳት ያዥ አድርጎ ሸኘው:: "የህንደኬ ሹም ባኮስ ሆይ ከአሁን ወዲህ በህንደኬ ገንዘብ ላይ ብቻ አትሠለጥንም ፤ የእግዚአብሔር ገንዘቦች የነፍሳት ግምጃ ቤት ላይ የሠለጠንህ የመንግሥተ ሰማያት በጅሮንድ አደርግሃለሁ" ብሎ ሾመው::

ይህ ከሆነ ሁለት ሺህ ዓመት አለፈ:: የጃንደረባው የልጅ ልጅ የኢትዮጵያ ሕዝብም ከሠረገላ አልፎ በፍጥነት በሚሔድ ብዙ ዓይነት መጓጓዣ ሊሳፈር ተሰለፈ:: ትዕግሥት አጥቶ በገንዘብ ላይ ከመሠልጠን ይልቅ ገንዘብ ሠልጥኖበት በፍጥነት ከነፈ:: አንዱ ፊልጶስ ብቻ ሮጦ የማይደርስበት እልፍ ሕዝብ ዛሬ ሠረገላውን አጨናንቆታል:: እንደ ጃንደረባው መጽሐፍ ቅዱስ ላይ ሳይሆን ስልኩ ላይ ያቀረቀረ ፣ ስለ ትንቢት ትርጉም ሳይሆን ስለ ኑሮ ብልሃት የተመራመረ ትውልድ ተነሥቶአል:: የኢሳይያስ ትንቢት ስለማን ቢነግር የማይገደው የሕይወት ውጣ ውረድ ፍቺ የሚሻ ትንቢት የሆነበት ፣ በመንፈስ ጭንቀት የታወከ ምስኪን ትውልድ ተነሥቶአል:: በእርግጥ ይህ ትውልድ ከዚህ ጭንቀት ለመውጣት የሚመራው ሳይኖር እንዴት ይቻለዋል? ለዚህ ሁሉ ሕዝብ የሚሆን ፊልጶስ ከወዴት ይምጣ?

ኸረ የዲያቆን ያለህ? ነፍስ አድን ፊልጶሳዊ ዲያቆን ሆይ ከወዴት ነህ? ነፍሳትን ለማዳን የሚያሳድድ እንጂ የሥጋ ምኞቱን የሚያሳድድ ዴማሳዊ ዲያቆን አልጠፋም:: እንደ እስጢፋኖስ በድንጋይ የሚወገር ዲያቆን እንጂ ድንጋይ አንሥቶ የሚማታ ዲያቆን አልጠፋም:: ሰረገላ ላይ ሆነው ግራ የተጋቡ ባኮሶች ብዙ ናቸው የፊልጶስ ግን እጥረት አለ:: ችግራቸውን ፈትቶ ጥያቄያቸውን መልሶ የሚሰወር ከሠረገላ አልወርድም ብሎ የማያስቸግር ፊልጶስ ግን እጥረት አለ:: ከእናንተ ቀድመን በተሾምን ዲያቆናት  አንገትዋን የደፋች ቤተ ክርስቲያን በእናንተ ቀና እንድትል እንመኛለን:: የሚሮጥ ዲያቆን ያድርጋችሁ:: ምእመናን እሱን ፍለጋ የሚሮጡለት ዲያቆን ሳይሆን ነፍሳትን ፈልጎ የሚሮጥ ዲያቆን ያድርጋችሁ:: ከመቅደሱ ጠፍቶ የሚፈለግ ሳይሆን ፈረስ የማያመልጠው ዲያቆን ያድርጋችሁ::

ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
ዲበ ሠረገላ ሰማይ
ለኢጃት ዲያቆናት ሲመት

https://hottg.com/ethioadbrat
ምን እንማር
አባ ሙሴ ጸሊም 
ግብጻዉያን የኦርቶዶክስ ሃይማኖት አማኞች ስሙን ጠርተዉ ከማይጠግቡት አባት መሀከል ነዉ ጻድቁ አባ ሙሴ ጸሊም (ጥቁሩ ሙሴ)። በሰኔ 24 ቀን ዓመታዊ በዓሉ ታስቦ የሚዉለዉ አባ ሙሴ ጸሊም ትውልዱ ኢትዮጵያ ሲሆን ኑሮዉ ግን በግብጽ ነዉ፡፡
ቀድሞ የነበረዉ ህይወቱ እንደመልኩ የጠቆረ ነበር።  በግብሩም ሀይለኛ፣ አብዝቶ የሚበላ፣ ነጣቂ፣ አመንዝራ፣ ሰዉ ገዳይ እንዲሁም በባዕድ አምልኮ(ፀሐይን ለሚያመልኩ) ላሉ አገልጋይ ነበር፡፡ ነገር  ግን በጥበበ እግዚአብሔር አባ ሙሴ ከእለታት በአንድ ቀን ‹‹ፀሐይ ሆይ አንተ አምላክ ከሆንክ አነጋግረኝ›› ብሎ እንደ ጻድቁ አብርሀም ፈጣሪን በስነ ፍጥረት መፈለግ ጀመረ፡፡ የሰዉ ልጅ ይድን ዘንድ እንጂ መሞቱን የማይፈቅድ አፍቃሬ ሰብዕ ቸሩ እግዚአብሔር ወደ አስቄጥስ ገዳም መራዉ፡፡ በዛም ከካህናቱ አንዱ የሆኑትን አባ ኤስድሮስን ‹‹ እዉነተኛዉን አምላክ ታሳዉቁኝና ታስረዱኝ ዘንድ ወደ እናንተ መጣሁ›› አላቸዉ፡፡ አባ ኤስድሮስም  ወደ አባ መቃርስ መሩት፡፡ አባ መቃርስም የክርስትናን ሃይማኖት አስተምረዉና አጥምቀዉ  አመነኮሱት፡፡ አባ ሙሴም ጥሙድ እንደ በሬ ቅኑት እንደ ገበሬ ሁኖ ግዙፍ ሰዉነቱን በገድል ቀጠቀጠዉ ከቁመቱ በስተቀር ምንም አልነበረዉም።
የአምላካችን ቸርነቱ ምን ያህል ነዉ? ይህንን እንደ አለማወቅስ ያለ ምን ጉዳት አለ፡፡ ተስፋ ያስቆረጠህ፣ እንደተራራ የከበደብህ ኀጢያት በእግዚአብሔር ምህረት ዐይን ሲታይ ምንም እንደሆነ ከአባ ሙሴ ጸሊም ህይወት መማር ይቻልሀል፡፡
ወንበዴ ነህ፣ ነፍሰ ገዳይ ነህ፣ ዘማዊ ነህ፣ በሱስ ተይዘሀል፣ ወይስ በባዕድ አምልኮ ነህ…ምንድነዉ ከእግዚአብሔር የለየህ እና ያስጨነቀህ? እግዚአብሔር እንዲህ ይልሀል ‹‹ ወደኔ ተመለሱ እኔም ወደ እናንተ እመለሳለሁ›› ዘካ 1፤3፡፡ ስለዚህ ምክንያትህን ተዉና ዝም ብለህ ወደ እግዚአብሔር ና ፈልገዉ ሲፈልግህ ታገኘዋለህ፡፡አባ ሙሴ በሚኖርበት ገዳም ዉስጥ የሚኖሩ 500 የሚሆኑ ወንድሞች መነኮሳትን በአበ ምኔትነት እያስተዳደረ እያለ በማህበረ መነኮሳቱ ለሚበልጥ አገልግሎት ለቅስና ማዕረግ ተመረጠ፡፡ ሊሾሙት ወደ ቤተ መቅደስ ባቀረቡት ጊዜ ሊቀ ጳጳስሳቱ የቅስና ማዕረግ ሊሰጡት አልወደዱም ነበርና ‹‹ ይህን ጠቋራ ለምን አመጣችሁት? ከዚህ አዉጡት›› ብለዉ በዘመኑ ቋንቋ የዘረኝነት ጥቃት አደረሱበት፡፡ አባ ሙሴ ይህን ቃል ሲሰሙ ‹‹ መልክህ የከፋ ጠቋራ ሆይ መልካም አደረጉብህ›› እያሉ እራሳቸዉን እየገሰጹ ከቤተ መቅደስ ወጡ እንጂ ለራሳቸዉ ጥብቅና አልቆሙም፡፡
ከዚሁ ጋ የሚመሳሰል አንድ የመነኮሳት ታሪክ እናንሳ፡፡ በአንድ ገዳም የሚኖሩ ምግባረ ሰናይ በሁሉ የሚወደዱ አባት ነበሩ በዚህ የቀና አንድ መነኮስ ወንድም በአንድ ቀን እሳቸዉን ለማሳጣት አስቦ በጉባኤ መካከል ይሰድባቸዉ ያንቋሽሻቸዉ ጀመር በዚህ ጊዜ እኚያ አባት ‹‹ወንድሜ ሆይ አንተ ልታዉቅ የምትችለዉ በኣፋ ያለዉን ነዉ ዉስጤን ብታየዉ ከዚህ ይከፋል›› ብለዉ በትህትና ድል ነሱት፡፡ እዉነተኛ ትህትና እኔ አልረባም ማለት ሳይሆን አትረባም ሲባል መታገስ ነዉ ብሏል አፈ አፈዉ ዮሐንስ፡፡ በአንዲት ዕለትም አባ ሙሴ ከአረጋዉያን ጋር ወደ አባ መቃርስ በሔዱ ጊዜ አባ መቃርስ በመንፈስ ቅዱስ ተገልጾላቸዉ ‹‹ ከእናንተ ዉስጥ የሰማእትነት ክብር ያለዉ አንድ ሰዉ አያለሁ በማለት ለአባ ሙሴ ስለተዘጋጀዉ የሰማእትነት ክብር አስቀድመዉ ትንቢት ተናገሩ፡፡ አባ ሙሴም ይህን ቃል ሲሰማ ‹‹ እኔ እሆናለሁ በሰይፍ የገደለ በሰይፍ ይሙት የሚል ጽሑፍ አለና›› ብለዉ መለሱ፡፡ ‹‹ኀጢያታአችንን እኛ ስናስታዉሰዉ እግዚአብሔር ይተዉልናል እኛ ስንረሳዉ እግዚአብሔር ያስብብናል›› ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ፡፡
ራሳችንን ብንመረምር ግን እግዚአብሔር ባልፈረደብንም ነበር 1ኛ ቀሮ 11፤31

https://hottg.com/ethioadbrat
እንኳን ለኢትዮጵያ ብርሃን ፣ ለቤተክርስትያን ምስጢር አስገኝ ፣ ለዓለም የዜማ ምንጭ ለቅዱስ ያሬድ ዓመታዊ በዓል በሠላም አደረሳችሁ፡፡

ኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስትያን በግንቦት 11 ቀን ቅዱስ ያሬድ የተሰወረበትን ቀን ታከብራለች፡፡ በሚያዚያ 505 ዓ/ም አክሱም ውስጥ የተወለደው ቅዱስ ያሬድ የቤተክርስትያን መሠረቶች የሆኑትን ግዕዝ ፣ ዕዝል እና አራራይ ዜማን ለቤተክርስትያን ያበረከተ ታላቅ አባት ነው፡፡ ቅዱስ ያሬድ አካሔዱን ከእግዚአብሔር ጋር ስላደረገ እንደ አባቶቹ ሔኖክ እና ኤልያስ ሥጋው በዚህ ምድር አልተገኘም፡፡ አክሱም እና ሰሜን ጎንደር እየተመላለሰ ሲያስተምር ከቆየ በኋላ በሰሜን ተራሮች አካባቢ ግንቦት 11 ቀን ተሰውሯል፡፡
የቅዱስ ያሬድ ጸጋው፣ምልጃውና በረከቱ በምናከብረው በእኛ
በኦርቶዶክሳውያን ሁሉ ላይ ጸንቶ ይኑር፡፡

https://hottg.com/ethioadbrat
https://hottg.com/ethioadbrat
#ጸሎት_ከበረሓውያን_አበው


ሁሉም ነገር ለፈቃድህ የሚገዛልህና የሚታዘዝልህ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ፣ ያደረግሁትን ነገር ሁሉ ይቅር በለኝ፣ ኃጢአተኛ
የሆንኩትን እኔን ከአሁን በኋላ እንዳልበድል አድርገኝ፡፡ ጌታ ሆይ፣ የማይገባኝ መሆኔን
ባውቅም ከኃጢአቴ ሁሉ ልታነጻኝ ትችላለህ። ጌታ ሆይ፣ ሰው ፊትን እንደሚያይ፣ አንተ ግን ልብን እንደምታይ አውቃለሁ፡፡ ቅዱስ መንፈስህን ወደ ውስጤ ጥልቅ ላክልኝ፣ ነፍሴንና ሥጋዬን ይኖርበትና ገንዘቡ ያደርገው ዘንድ፡፡ ያለ አንተ ልድን አልችልም፤ በምትጠብቀኝ በአንተ ግን ማዳንህን እናፍቃለሁ፡፡ እናም አሁን አንተን ማዳንህን እለምንሃለሁ፡፡ የአንተን ጥበብ እሻለሁ፣ የሚረዳኝንና የሚጠብቀኝን ታላቁን ደግነትህንና ቸርነትህን እማጸናለሁ፡፡ ሁሉን ቻይ ታላቅ አምላክ እግዚአብሔር ሆይ፣ በቀንና በሌሊት የአንተን መኖር አስታውስና አንተን ሁል ጊዜ በፊቴ አደርግህ ዘንድ ልቤን ምራልኝ፡፡

+ አሜን +


#ዲያቆን_ያረጋል_አበጋዝ

https://hottg.com/ethioadbrat
ከእርሱ ጋር ኀብረት ፍጠሩ!
እግዚአብሔርን ለማወቅ ለመውደድ ከእርሱ ጋር መተባበር አለባችሁ። ንባብ ብቻውን በቂ አይደለም። ንባብ የሚከፍትላችሁ መዝጊያውን ብቻ ነው። ከዚህ በኋላ እናንተ ትገቡና ከእግዚአብሔር ጋር ትኖራላችሁ ከዚያም ከእርሱ ጋር መኖር ጣፋጭ መሆኑን እናንተ ራሳችሁ ታውቃላችሁ።

ስለሆነም ከእግዚአብሔር ጋር የሚሆን ሕይወትን ትሞክሩታላችሁ እርሱ በሁሉም ነገር ውስጥ ተካፋይ እንዲሆንም ትፈቅዳላችሁ።

እንደ ባልጀራችሁ አድርጋችሁ ልትወዱት ሞክሩ አሳቦቻችሁንና ሚስጥሮቻችሁን ለእርሱ ንገሩት። ከዚህ በኋላ የሚሆነውን ጠብቁና እርሱ ምን ያህል ከእናንተና ለእናንተ እንደሚሰራ ታያላችሁ። ከዚህ በተጨማሪ በአሳቦቻችሁና በተሰጥኦዎቻችሁ ከመተማመን የበለጠ በእርሱ ላይ መተማመንን ታውቃላችሁ።

ከብጹዕ አቡነ ሽኖዳ መጽሐፍ የተወሰደው

https://hottg.com/ethioadbrat
ኪዳነምህረት" ማርያም ሆይ! በመድኃኒትሽ ቁስሌን እንድትፈውሽ በኪዳንሽ ቤዛነት ነፍሴን እንድታድኚ እማለድሻለሁ። አሜን። <
               +"+ <መልክአ ኪዳነምህረት"+"+

@ethioadbrat
"ወደ ጌታ እቅፍ ዘንበል ያለው ሐዋርያ"

ወደ ጌታ እቅፍ ዘንበል ያለው ሐዋርያ ዮሐንስ መሆኑን በመጽሐፉ የገለጸው አውሳብዮስ የተባለው የታሪክ ጸሐፊ ነው።
ወደ ጌታ እቅፍ ዘንበል ማለት ግን እንዴት ይሆን? የጌታ እቅፍ ሙቀቱ እንደ ምን ይሆን? ይህን ሊመልስ የሚችለው እቅፉን የሚያውቀው ሐዋርያውና እመቤታችን ይመስሉኛል።

ገነት፣ መንግሥተ ሰማያትን በአብርሃም እቅፍ እንመስላታለን - በሞተ ሥጋ የተለየንን "ነፍሱን በአብርሃም እቅፍ ያሳርፍልን" እንድንል። ዮሐንስ ግን ወደ ጌታ እቅፍ ዘንበል አለ። የአብርሃም እቅፍ ገነትን ከመሰለ፣ ዮሐንስ ያረፈበት የጌታ እቅፍ እንዴት ያለ ይሆን?

ሲከፋንና የሚጎረብጥ ስሜት ውስጥ ስንሆን እቅፋቸውን የምንመኘው ሰዎች አሉ። ሽጉጥ ብለንባቸው ብንደበቅ የምንመርጣቸው። በእቅፋቸው ውስጥ ሆነን ብናነባ የምንፈልጋቸው። ከፍቅራችን ጽናት የተነሣ ከእቅፋቸው መለየት የማንፈልግ ሰዎች ይኖሩናል።

ዮሐንስ ግን መጽናናትን ፈልጎ ይሆን? ወይስ ከፍቶት? የጌታው እቅፍ ውስጥ የሸጎጠው ምን ይሆን? በርግጥ ቁጹረ ገጽ ነውና ይህ ቢያስኬድም፣ ያኔ የጌታ መከራ ገና በመሆኑ: ወደ ጌታው እቅፍ ዘንበል ያደረገው ፍቁረ እግዚእነቱ ነው እንላለን። የፍቅሩ ጽናት ከእቅፉ ከተተው። ያ የጌታችን እቅፍ ግን ምን ያህል ያጽናና!? ምን ያህል ያስደስት!?

ሕፃን ልጅን እናትና አባቱ "ትወደኛለህ?" ቢሉት "አዎ" ይላቸዋል። "እንዴት አድርገህ?" ቢሉት የመውደዱን መጠን የሚገልጸው በቻለው ኃይሉ ሁሉ ዕቅፍ በማድረግ ነው። ያለ የሌለ ኃይሉን ተጠቅሞ በዕቅፉ ለማስጨነቅ ይሞክራል። እመቤታችን ጌታን በልጅነቱ ስታጫውተው መውደዱን እንዴት ገልጾላት ይሆን? እንዴትስ አቅፏት ይሆን? አምላክ እናቱን ሲያቅፍስ እንዴት ይሆን? እርሷስ ዕለት ዕለት አቅፋ ስታሳድገው አምላክን በእናትነት ማቀፍ እንደ ምን ይሆን?

ስምዖን አረጋዊ ጌታን ለቅጽበት ቢያቅፈው ከዚያ በኋላ መሞትን ተመኘ። ጌታን ማቀፍ ማዳኑን እንደ መቅመስ መሆኑን ነገረን። ከእናቱ እቅፍ ተቀብሎ አቀፈውና "...እግዚአብሔርንም እየባረከ እንዲህ አለ፦ 'ጌታ ሆይ፥ አሁን እንደ ቃልህ ባሪያህን በሰላም ታሰናብተዋለህ፤ ዓይኖቼ በሰዎች ሁሉ ፊት ያዘጋጀኸውን ማዳንህን አይተዋልና"። (ሉቃስ 2:28-31)። (ልጅን ከእናቱ እቅፍ ሲያወጡት እንዲያለቅስ፣ ስምዖን ከእናቱ እቅፍ ሲወስደው ሕፃኑ ጌታ አይኑን ወደ እናቱ እያንከራተተ አልቅሶ ይሆን?)

ስምዖን አንድ ጊዜ አቅፎትና አይቶት ከዚህ ምድር መለየትን ከለመነ፣ ዕለት ዕለት አቅፋ ዓይን ዓይኑን የምታየው እመቤታችን ገናናነቷ ምን ይረቅ!? ምን ይደንቅ!?

ኧረ በጌታ የታቀፈ የዚህ ሐዋርያ እቅፍ፣ ጌታ ሲያቅፋት ያደገች፣ እርሷም ስታቅፍ ያሳደገችው የድንግል እቅፍ ምን ይመስል ይሆን!?

ቅዱስ ያሬድን አብልጠው የሚወዱት አንድ ሊቅ "እኔ ስሞት እንዲያው ቢፈቅድልኝ በአብርሃም እቅፍ ሳይሆን በቅዱስ ያሬድ እቅፍ ብሆን" ብለው ተመኙ። አንባቢ ሆይ! ማድላት እንዳይመስልህ፤ ዘይቤ ነው።
እኔ ደግሞ ዛሬ ይህን ሳሰላስል የዮሐንስንና የድንግልን እቅፍ ተመኘሁ።

እንኳን ለውዱ ሐዋርያ በዓል አደረሰን!

ዲያቆን ሕሊና በለጠ ዘኆኅተብርሃን

https://hottg.com/ethioadbrat
#ክፉ_አሳብ

ልጆቼ! ከመጀመሪያውኑ ክፉ አሳብ ባታስቡ መልካም ነው፡፡ ካሰባችሁ ግን ቢያንስ አትናገሩት፡፡ በዚያው በሕሊናችሁ ውስጥ እያለ ዝም አሰኙት፤ ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላም ወዳለመኖር ይኼዳል፡፡

እኛ ሰዎች ነን፡፡ በመኾኑም ብዙውን ጊዜ ክፉ፣ ያልተገቡና ጸያፍ ነገሮችን እናስባለን፡፡ ነገር ግን ቢያንስ እነዚህን አሳቦች አንናገራቸው፤ ቢያንስ ወደ ቃል አንለውጣቸው፡፡ ወደ ውጭ እንዳይወጡ አምቀን እንያዛቸው፡፡ ከጥቂት ጊዜ በኋላ እየከሰሙና እየደከሙ እየጠፉም ይኼዳሉ፡፡ አንድን እንስሳ ወደ ጉድጓድ ብትጥሉትና ጉድጓዱንም በመክደኛ ብትከድኑት ያ ወደ ጕድጓድ የጣላችሁት እንስሳ የሚተነፍሰውን አየር አጥቶ ይሞታል፡፡ ምናልባት ጥቂት ቀዳዳ ካገኘ ግን በዚያች ቀዳዳ በምትገባው አየር በሕይወት መቆየት ይችላል፡፡ ሲጨንቀውም እናንተን ክፉኛ ለመጉዳት ይዝታል፤ ከወጣም በኋላ ይጎዳችኋል፡፡ ልክ እንደዚሁ እናንተም በልቡናችሁ የተመላለሰውን ኩላሊታችሁ ያጤሰውን ክፉ አሳብ መውጫ ቀዳዳ እንዳይኖረው አድርጋችሁ ብትከድኑት (ብታፍኑት) ይሞታል፤ ከመኖር ወዳለመኖር ይለወጣል፡፡ በአንደበታችሁ በመናገር ጥቂት ቀዳዳ ከከፈታችሁለትና እንደ እንስሳው እንዲተነፍስ ከፈቀዳችሁለት ግን ክፉው አሳብ ክፉ ግብርን ይወልዳል፡፡ ያቆጠቁጣል፡፡ በአሳብ ሳለ ከጎዳችሁ በላይም በገቢር ተወልዶና ተለውጦ ክፉኛ ይጎዳችኋል፡፡

(#የክርስቲያኖች_መከራ #በቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ ገጽ 7

https://hottg.com/ethioadbrat
ምክረ አበው

ከወድሞች አንዱ ወደ አረጋዊ መጣና " አባ ፣ ደካማ ነኝና ጸልዩልኝ " አለው፡፡ አረጋዊም እንዲህ አለው " በሸተኛን ይቀባ ዘንድ በእጁ ቅባት የሚይዝና ሌላውን የሚቀባ ሰው እርሱም ደኀና ሆኖ ይቀባል፡፡

እንዲሁም እኛም ለሌላው ስንጸልይ ለራሳችን መድኃኒትና ፍስሐ ይሆነናል፡፡

ስለዚህ ወንድሜ ሆይ ፣ አንዳችን ለሌላችን ልንጸልይና እርስ በርሳችን በጸሎት ልንተሳሰብ ይገባናል፤ ሐዋርያው " ትድኑ ዘንድ ለወንድሞቻችሁ ጸልዩ " ብሎ እንዳዘዘን፡፡

https://hottg.com/ethioadbrat
ተወዳጆች ሆይ! እግዚአብሔርን ከማሳዘን ውጪ ምንም ይኹን ምን [አንፍራ፡፡] ሠለስቱ ደቂቅ የሚንበለበል እሳት በፊታቸው ቢያዩም ናቁት፤ ኃጢአትንም ብቻ ፈሩ፡፡ በእሳቱ ቢቃጠሉ ምንም የሚያስፈራቸው ነገር እንደሌለ፣ ፈሪሐ እግዚአብሔር ባይገኝባቸው ግን እጅግ የከፋ ጉስቁልና እንደሚያገኛቸው ያውቃሉና፡፡ ምንም ሳንቀጣ ብንቀርም እንኳን እጅግ ትልቁ ቅጣት ግን ኃጢአት መሥራት ነው፤ በሌላ መልኩ ደግሞ ምንም ያህል ቅጣት ቢያገኘንም እጅግ ትልቁ ክብርና ጸጥታ ግን በተጋድሎና በምግባር ሕይወት መኖር ነው፡፡

እግዚአብሔር ራሱ፡- “በደላችሁ በእናንተና በእኔ መካከል አልለየችምን?” ብሎ እንደ ተናገረ ኃጢአት ከእግዚአብሔር ይለየናል (ኢሳ.59፡2)፡፡ ቅጣት ግን “እግዚኦ አምላክነ ሰላመ ሀበነ እስመ ኵሎ ወሀብከነ - አቤቱ አምላካችን ኹሉን ሰጥተኸናልና ሰላምን ስጠን” እንደ ተባለ ዳግመኛ ወደ እግዚአብሔር እንድንመለስ ያደርገናል (ኢሳ.26፡12)፡፡

እንበልና አንድ ሰው ቁስል ወጣበት፡፡ የሚያስፈራው የትኛው ነው - የሚሰፋው ቁስል ወይስ የቀዶ ጥገና ሐኪሙ ቢላ? ብረቱ ወይስ እጅግ እየባሰበት ያለው ቁስል? ኃጢአት የሚሰፋ ቁስል (Gangrene) ነው፤ ቅጣት ደግሞ የቀዶ ጥገናው ሐኪም ቢላ ነው፡፡ ያልፈረጠ የሚሰፋ ቁስል ያለው ሰው ሕመሙ እንዳለበትና ለወደፊቱም የማያፈርጠው ከኾነ ሥቃዩ እየባሰበት እንደሚኼድ ኹሉ፥ ቅጣት ያላገኘው ኃጢአተኛ ሰውም ከሰዎች ኹሉ ይልቅ ጎስቋላው ሰው እርሱ ነው፤ ለወደፊቱ ጭራሽ ቅጣትና መከራ የማያገኘው ከኾነ ደግሞ ከአሁኑ ይልቅ እጅግ ጎስቋላው ሰው እርሱ ነው፡፡ የጣፊያ ወይም የሆድ በሽታ ያለባቸው ሰዎች ብዙ መብል ቢበሉ፣ ቀዝቃዛ መጠጦችን ቢጠጡ፣ የተለያዩ ዓይነት ጣፋጭና ቅመማ ቅመም የበዛባቸው መብሎችንም ቢወስዱ ይህ ድሎት ሕመማቸው እንደሚጨምረውና እንደ ሕክምናው ሕግ ራሳቸውን ከመብሉም ከመጠጡም በመጠኑ ቢወስዱ ግን የመዳን ተስፋ ሊኖራቸው እንደሚችል ኹሉ፥ በክፋት ዓዘቅት የሚኖሩ ሰዎችም ቅጣት ካገኛቸው በጎ ተስፋ ሊኖራቸው ይችላል፤ ከክፋታቸው ጋር አብረው ዝንጋዔንና ድሎትን የሚጨምሩበት ከኾነ ግን ሆዳቸውን ከሚያማቸው ሰዎች በላይ እጅግ ጐስቋሎች ሰዎች ናቸው - ደዌ ዘነፍስ ከደዌ ዘሥጋ ይልቅ የከፋ ነውና፡፡ ተመሳሳይ ኃጢአት እያላቸው አንዳንዶቹ በማጣትና በብዙ ሕመም ሲሠቃዩ፣ ሌሎቹ ግን እስኪበቃቸው ድረስ እየጠጡና እየተስገበገቡ የሚበሉ እየተመቻቸውም በደስታ የሚኖሩ ሰዎችን ብትመለከት እነዚያ መከራ የሚቀበሉት የተሻሉ እንደ ኾኑ አስተውል፡፡ በእነዚህ መከራዎች የተወገደላቸው የፈንጠዝያ ሕይወት እሳት ብቻ ሳይኾን ሊመጣ ወዳለው ፍርድና አስፈሪ ዙፋን ሲኼዱም ከቀላል ዕረፍት ጋር አይደለምና፤ ስለኾነም እዚያ ሲኼዱ ከኃጢአታቸው የሚበዛውን በዚህ ዓለም ባገኛቸው ሥቃይ አስወግደው ነው፡፡

#ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ

https://hottg.com/ethioadbrat
እንኳን ለእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የመገለጥ በዓል (ደብረ ምጥማቅ) በሰላም አደረሳችኹ

ደብረ ምጥማቅ

የአርያም ንግሥት: የሰማይና የምድር እመቤት: የሰውነታችንም መመኪያ ቅድስት ድንግል ማርያም በዚኽች ዕለት በምድረ ግብፅ ለተከታታይ ቀናት ተገልጻለች::

🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼

"የምድር ባለጠጐች አሕዛብ በፊትሽ ይማለላሉ:: ለሐሴቦን ንጉሥ ልጅ ኹሉ ክብሯ ነው:: ልብሷ የወርቅ መጐናጸፊያ ነው:: በኹዋላዋ ደናግሉን ለንጉሥ ይወስዳሉ . . . በአባቶችሽ ፈንታ ልጆች ተወለዱልሽ:: በምድርም ኹሉ ላይ ገዥዎች አድርገሽ ትሾሚያቸዋለሽ:: ለልጅ ልጅ ኹሉ ስምሽን ያሳስባሉ::"
መዝ. ፵፬:፲፪-፲፯

https://hottg.com/ethioadbrat
https://hottg.com/ethioadbrat
ደብረ ምጥማቅ ጻድቃኔ ማርያም

#Ethiopia | በአማራ ክልል በሰሜን ሸዋ ዞን በሞጃና ወደራ ወረዳ የምትገኘው የጻድቃኔ ማርያም መካነ-ቅዱሳን ገዳም በሰላ ድንጋይ ከተማ አቅራቢያ የሚገኝ ሲሆን ከክልሉ ርዕሰ ከተማ ባህርዳር 767 ኪሎ ሜትር፤ ከአዲስ አበባ 202 ኪሎ ሜትር እና ከዞኑ ርዕሰ ከተማ ደብረ ብርሃን 72 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የሚገኝ ገዳም ነው።

በመጀመሪያ የእመቤታችን ፅላት ወደ ኢትዮጵያ ከመምጣቷ በፊት የነበረችው በግብጽ ሀገር ዘይቱን ቤተክርስቲያን ውስጥ እንደነበረችና አባ ሚካኤል እና አባ ገብርኤል የተባሉ አገልጋዮች እንደነበሯት ንጉሤ ገ/ሚካኤል "መንገዳችን ለጽድቅ ወይስ ለኩነኔ" በሚለው መጽሃፋቸው ገልጸውታል፡፡ በእርግጥም በአፄ ዘርዓ ያዕቆብ ዘመነ መንግሥት ቱርኮች ግብጽን ወረው ክርስቲያኑን ፈጅተው በዚያው የሚገኘውን አብያተ ክርስቲያናት ባቃጠሉና በፈጁት ጊዜ በወቅቱ ከተቃጠሉት አብያተ ክርስቲያናት መካከል አንዷ የሆነችው የደብረ ምጥማቅ ማርያም ቤተክርስቲያን ነበረች፡፡ ከወረራውና ከቃጠሎው በፊት አስቀድመው ቀሳውስቱ ጽላቷን አውጥተውና ሸሽገው አስቀምጠዋት ስለነበር በጊዜው የነበረው የክርስቲያኑ መሪ ፅላቷን ይዛችሁ በአስቸኳይ ኢትዮጵያ ወደምትባል የክርስቲያን አገር ሂዱ፡፡ንጉሡም ክርስቲያን ስለሆነ ለእርሱ አስረክቡ ተብለው የተገለፁት መነኮሳት በሱዳን በኩል አድርው ወደ ሀገራችን መጥተው ፅላቷን ለአፄ ዘርዓ ያዕቆብ እንዳስረከቡ ከገዳሙ አባቶች የተገኙት ምንጮች ያስረዳሉ፡፡

ጽላቷ ወደ ኢትዮጵያ ስትመጣ ንጉሠ ነገሥቱ የእመቤታችንን ጽላት በእልልታና በደስታ ተቀብለው በዘመኑ ለነበሩት ካህናትና ዲያቆናት አስረከቧቸው፡፡ ቀጥሎም አጼ ዘርዓ ያዕቆብ ጅባት ከተባለው ከተማ ወደ እንጦጦ አምጥተው ለብዙ ጊዜ አስቀምጠዋታል፡፡ እንደገናም ከእንጦጦ አንስተው ወደ ደብረ ብርሃን አመጧት። ከዚያም አሁን ወዳለችበት አካባቢ ወደ ሠላ ድንጋይ ሞሊያ በተባለው ከፍተኛ ቦታ ለብዙ አመታት ቆይታለች፡፡ በመጨረሻም ለንጉሡ ለአጼ ዘርዓ ያዕቆብ የእግዚአብሄር ፍቃድ በመሆኑ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በራዕይ ተገልጻላቸው ወደ ምስራቅ ያዘኝና ተነስተህ ሂድ አለቻቸው። ንጉሱም ከነበረችበት ቦታ አንስተው ታቦቱን አስይዘው መንገድ ጀመሩ። በጉዞ ላይ እንዳሉ አሁን ደብረ ምጥማቅ እተባለ በሚጠራው ቤተክርስቲያን ታቦቱን የተሸከመው ካህን መንቀሳቀስ አልቻለም፡፡ ንጉሡ ቀድመው በበቅሎ ወደፊት ይሄዱ ነበርና ከመኳንንቱ አንዱ ይትባረክ ውእቱ የተባለው በፍጥነት ሄዶ ንጉሥ ሆይ ታቦቷን የያዘው ቄስ ሊራመድ አልቻለም፤ ሲላቸው ንጉሡ ደንግጠው ከበቅሏቸው ወርደው ታቦቷን ወደ ተሸከመው ቄስ ሄደው አመመህ ወይስ ደከመህ? ብለው ጠየቋቸው። ቄሱም ደህና ነኝ አላመመኝም ይሏቸዋል፡፡ ከዚያም በኋላ በተጉለት/አጉባ/ ዛሬ ደብረ ምጥማቅ በሚባለው አካባቢ ንጉሡ አጼ ዘርዓ ያዕቆብ የታቦቷን ድንኳን ስሩ ስዓታትንም ቁሙ መስዋዕትም አዘጋጁ ብለው ትዕዛዝ ሰጥተው ስለነበረ ሁሉም ይፈጸማል፡፡ ከዚህ ስፍራ ለንጉሡ እመቤታችን ሌሊት ላይ በራዕይ ተገለጸችላቸው። ራዕዩም ይህች ቦታ የፃድቃን የሰማዕታት የቅዱሳንና የመላዕክት ቦታ ናት ፤ ማረፊያዬ በዚህ ነውና ቤተክርስቲያን ስራ አለቻቸው፡፡ ንጉሡም ይህንን መልስ ከእመቤታችን እንደሰሙ ምስጋናቸውን ወደ እግዚአብሄር አቀረቡ፡፡ እመቤቴ ቦታዋን መርጣ ነገረችኝ ደስታው ለኢትዮጵያ ሕዝብ ነው ብለው በደስታ እመቤታችንን አመሰገኑ፡፡ ራዕዩን መሰረት አድርገው አሁን ደብረ ምጥማቅ እየተባለ በሚጠራው ቦታ ልክ እንደ አክሱም ጽዮን አስመስለው ታላቅ ቤተክርስቲያን አሳነጹላት፡፡ ከእየሩሳሌም ከተቀደሰው ቦታ አፈር በበቅሎና በፈረስ አስመጥተው ንጉሡ እንዳሰሩት የገዳሙ አባቶች ያስረዳሉ፡፡ በሌላ በኩል አጼ ዘርዓ ያዕቆብ ቤተክርስቲያኑን እንዲሰሩ የተነገራቸው ቦታ ባህር ስለነበር ባህሩ ላይ እንዴት ቤት መስራት እችላለሁ በማለት ድንግል ማርያምን በጸሎት ተማፅነው ድንግል ማርያምም በራዕይ ተገልፃላቸው ከግብጽ ሀገር አፈር አስመጥተህ ባህሩ ላይ ጨምርበት ብላ ነግራቸው ስለነበር አፄ ዘርዓ ያዕቆብም በተባሉት መሰረት አፈሩን ከግብጽ ሀገር በማስመጣት ከባህሩ ጨመሩበት። ባህሩም ደርቆ መሬቱ ዐለት ሆኖ ቤተክርስቲያኑን ሰርተውታል የሚል አፈታሪክ እንዳለ የገዳሙ አንደንድ አባቶች ይናገራሉ፡፡ ያም ሆነ ይህ ቤተክርስቲያኑ ተሰርቶ የቅድሰት ማርያም ጽላት ወደ መንበሯ የገባች መሆኑን ማረጋገጥ ይቻላል፡፡

የቤተክርስቲያኗም ስም በዚያው ግብጽ ባለው ማስታወሻ ይሆን ዘንድ ደብረ ምጥማቅ ተብላለች፡፡ ለማስረጃም ያህል አሁንም በግብጽ ደብረ ምጥማቅ የምትባል የእመቤታችን ቤተክርስቲያን ትገኛለች፡፡ ፅላቷን ይዘው የመጡት አባ ሚካኤልና አባ ገብርኤልም እስከ ዘመን ፍፃሜያቸው ሲያገለግሉ ቆይተው በዚሁ በደብረ ምጥማቅ አርፈው ተቀብረዋል፡፡ መቃብራቸውም በዚያው ስፍራ ይገኛል፡፡

ቤተክርስቲያኗ ከታነፀች ከብዙ ዓመታት በኋላ የኢትዮጵያን አድባራትና ገዳማትን ንዋዬ ቅድሳትን አጠቃላይ የቤተክርስቲያንን ንብረት እያቃጠለ የሚመጣ ወራሪ ስላለ የቤተከርስቲያንን ቅርሰና ንብረት በሙሉ በየዋሻውና በየፍርጉታው እየቆፈርክ በመላው ሀገሪቱ ያለውን ንብረት ሁሉ ሰውረው ብላ እመቤታችን ለንጉሡ በራዕይ ትነግራቸዋለች፡፡ እሳቸውም በታዘዙት መሰረት ደብረ ምጥማቅ ያለውን ንብረት አሁን ወዳለበት ፃድቃኔ ማርያም ዋሻ እንደሰወሩት የገዳሙ ታሪክ ይናገራል፡፡ እንደተባለውም ከዘመናት በኋላ የግራኝ አህመድ ወረራ ትልቅ ችግር ሆኖ ተከሰተ፡፡ ግራኝ አህመድም የኢትዮጵያን አድባራትና ገዳማትን እያቃጠለ መጣ፡፡ ከዚያም ደብረ ምጥማቅ ደረሰ፡፡ ቤተክርስቲያኑን ለማቃጠል ሲቀርብ የቤተክርስቲያኑን አሰራር አይቶ እጅግ ተደነቀ፡፡ ለማቃጠልም ሞክሮ አስቸገረው፡፡ ሆኖም የእሱን አሽከሮችና ጠንቋዮች ሰብስቦ ይህ ቤተክርስቲያን ከመሬት እየተነሳ አልቃጠል አለኝ፤ ምን እናድርግ ትላላችሁ? ብሎ ቢጠይቃቸው ሰይጣን ግብሩ ክፉ ሃሳቡ ጠማማ ምግባሩ ርኩስ በመሆኑ ከአገሬው ነዋሪ የዶሮ ኩስ ይሰብሰብና ግራና ቀኝ ሆነን ስንረጭበት ይቃጠላል አሉት፡፡ እሱም በምክራቸው ተስማምቶ የተባለው የዶሮ ኩስ ተሰብስቦ በቤተክርስቲያኑ ግራናቀኝ ሆነው የዶሮዉን ኩስ ሲረጩበት ቤተክርስቲያኑ እንደተቃጠለ ንገሤ ገ/ሚካኤል ባዘጋጁት ጽሁፋቸው ላይ ተገልፆ እናገኘዋለን፡፡

በእርግጥም ሰይጣን የማይፈነቅለው ድንጋይና ለጥፋት የማይተኛ ሴራዉም ጥላቻውም እጅግ ከባድ ነው፡፡ ጌታችንን የገደሉትና የሰቀሉት እውር በማብራቱ ለምፃም በማንጻቱ ጎባጣ በማቅናቱ አይደለምን?

በወረራው የተቃጠለችው ቤተክርስቲያን ከዘመናት በኋላ በዚሁ ስፍራ እንደገና ተሰርቶ አገልግሎት ሲሰጥ ቆይቷል፡፡ ዘመን ተሻጋሪ የሆነችው ቤተክርስቲያን በዕድሜ እርጅና ምክንያት ፈርሶ ስለነበር ታላቁ ንጉሠ ነገሥት ግርማዊ ቀዳማዊ ዓፄ ኃይለ ሥላሴ አንድ ኢጣሊያዊ መሃንዲስ ልከው አሁን አገልግሎት እየሰጠ የሚገኘውን መቅደስ በዘመናዊ መልክ አሰሩት፡፡ ገዳሙ በጥንቱ ይዞታ ላይ ለምዕመናን ማረፊያና አዳራሽ በመስራት በተሻለ መልክ እያማረ መጥቷል፡፡
ወደዚህ ቅዱስ ስፍራ የሚመጡትን ሰዎችና አገልግሎት የሚሰጡትን ተሽከርካሪዎች አስመልክቶ በምን ደረጃ ላይ እንደነበሩ ንጉሤ ገ/ሚካኤል የሚባሉት ጸሐፊ ስለገዳሟ በጻፉት ጽሁፋቸው በዝርዝር አስቀምጠውት ይገኛል፡፡ ጽሁፉ እንደሚለው ከመዲናችን አዲስ አበባ ተነስቶ ወደ ሠላድንጋይ አንድ መለስተኛ አውቶቡስ ተመድቦ አገልግሎት በመስጠት ከ1990ዎቹ ጀምሮ መንገደኞችን በማመላለስ እንደጀመረ በጥር ወር 1991 ዓ/ም ወደ ገዳሙ የሚመጡት ሰዎች ብዛት በግምት ከ30 የማይበልጡ ሲሆን በነሐሴ 1993 ዓ/ም ከ1500 ያላነሰ ህዝብ ለሱባኤ አንደገባ መረጃው ይጠቁማል። በተመሳሳይ ሁኔታ በነሐሴ ወር 1994 ዓ/ም ደግሞ በግምት ከ6 ሺህ ያልበለጠ ሰው ለሱባኤ እንደመጣ ያስቀምጣል፡፡ በአሁኑ ሰዓት የህዝብ ፍሰቱ ከዕለት ወደ ዕለት እየጨመረ መሄዱን የገዳሟ ምንጮች ማረጋገጫች ናቸው፡፡ በተለይም በተለይም ከነሐሴ1-1 ባሉት የሱባኤ ሳምንታት ውስጥ ከ200 ሺህ በላይ ምዕመናን በጸሎት ላይ የነበሩ መሆኑን የገዳሟ የመረጃ መዝገብ ያስረዳል፡፡

የጻድቃኔ ማርያም መካነ ቅዱሳን ገዳም ዓመታዊ በዓላት መስከረም 21፣ ጥር 21፣ ግንቦት 21 እና ነሐሴ 16 ሲሆኑ በእነዚህ በዓላትና ጊዜ ቁጥሩ እጅግ ከፍተኛ የሆነ ምእመናን ወደ ስፍራው ይመጣል፡፡

ወደዚህ ቅዱስ ስፍራ የሚመጣው ሰው ቁጥር በትክክል ባይታወቅም በዓመቱ ውስጥ ከ800 ሺህ እስከ 1 ሚሊዮን ይደርሳል፡፡

ለ10 ዓመታት በግንባታ የቆየው በ231,500,000.00 ( በሁለት መቶ ሰላሣ አንድ ሚሊዮን አምስት መቶ ሺህ) ብር ወጪ የተገነባው የጻድቃኔ ደብረ ምጥማቅ ቅድስት ማርያም ገዳም ሕንጻ ቤተክርስቲያን ቅዳሴ ቤት ባለፈው ዓመት በድምቀት ተከብሯል።

https://hottg.com/ethioadbrat
#ሰው_ሆይ!

በእግዚአብሔር አርአያና ምሳሌ የተፈጠርህ መሆንህን አስታውስ። ስለዚህ ስለ ራስህ በተጠየቅህ ጊዜ በሙሉ እምነት "እኔ የእግዚአብሔር አምሳል ነኝ " በማለት ተናገር።
አንተ በምድር ላይና ውስጥ ካሉት ሁሉ በላይ ዕውቀትና አንደበት የተሰጠህ የመለኮት ፍጡር ነህ። ከዚህ በተጨማሪ እግዚአብሔርን የማወቅ የማምለክና ደስ የሚያሰኘውን ሁሉ የመረዳት ችሎታ ያለህ ፍጥረት ነህ።

እስኪ ከፍ ካለው ተራራ፣ ከታላቁ ባህር፣ ከምታበራው ጸሐይና ከምታንጸባርቀው ጨረቃ የምትበልጥ መሆንህን አስብ! አንተ እኮ ስፋት ካለው ምድረ በዳና ከተንጣለለው ሜዳ እንዲሁም በምድር ላይ ያለውን ኃይል ሁሉ ከሚያጠፋው አቶም ትበልጣለህ። መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚነግረን እነዚህ ሁሉ ያልፋሉ። "ሰማይና ምድር ያልፋሉ" (ማቴ 20፥35)። አንተ የእግዚአብሔር አምሳያ ግን አታልፍም። ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በማያልፈው ቃሉ የዘላለም ሕይወት እንዳለህ ቃል ገብቶልሃልና ለአንተ በእግዚአብሔር አምሳል ለተፈጠርከው ሰው። (ዮሐ 4፥4)

ሰው ሆይ! አሁንስ የነፍስህን ዋጋና በእግዚአብሔር ፊት ያላትን ታላቅነት ተመለከትህ? ምንም እንኳ እግዚአብሔር በርኩሳን መናፍስት ሁሉ ላይ ሥልጣን ቢሰጥህም ዲያብሎስ በዚህ ክብርህና ታላቅነትህ ላይ እንደወደደ እንዲቀልድ ትተወዋለህን?

(ከአቡነ ሽኖዳ የነፍስ አርነት መጽሐፍ)

https://hottg.com/ethioadbrat
📌 ትሑትና ትዕግሥተኛ ሁን

❖ በምድረ ገጽ ላይ ከነበሩት ሰዎች ሁሉ ይልቅ እጅግ ትሑት የነበረውን ነቢዩን ሙሴን ምሰል

✍️“ሙሴም በምድር ላይ ካሉት ሰዎች ሁሉ ይልቅ እጅግ ትሑት ሰው ነበረ”
📖ዘኁ 12፥3

❖ ሁል ጊዜ መሐሪ እና ይቅር ባይ ለመሆን ሞክር ሐዋርያው

✍️ “ለማንም ስለ ክፉ ፋንታ ክፉን አትመልሱ በሰው ሁሉ ፊት መልካም የሆነውን አስቡ... ተወዳጆች ሆይ ራሳችሁ አትበቀሉ ለቁጣ ፋንታ ስጡ እንጂ ...” ብሏልና።
📖 ሮሜ 12፥17-19

❖ እንዲሁም ቁጣን ጊዜያዊ ስሜትን እና ንዴትን እንድናስወግድ
✍️“ክፉውን በመልካም አሸንፍ እንጂ በክፉ አትሸነፍ” በማለት ይጠይቀናል።
📖ሮሜ 12፥21

❖ በእርግጥ መታገስ የሚችል ሰው ዕድለኛ ሲሆን ይህንን የማይችል ግን ደካማ ነው፤ ለዚህ ነው ሐዋርያውም
✍️“እኛም ኃይለኞች የሆንን የደካሞችን ድካም እንድንሸከም ራሳችንንም ደስ እንዳናሰኝ ይገባናል” ያለው።
📖ሮሜ 15፥1

❖ ሌሎች አንተ እንዳሰብካቸው ፍጹም የሚስማሙ እንዲሆኑ አትፈልግ ነገር ግን መሆን እንዳለባቸው ሳይሆን እንደሆኑት አድርገህ ተቀበላቸው ሁላችንም ተፈጥሮን እንደራሷ አድርገን ተቀብለናል፤ ወቅቶችን ዝናባማ፤ ማዕበላማም ይሁን ሞቃታማ ተፈጥሮ ራሱን እንዲለውጥ ሳንጠይቅ ተቀብለነዋል፤ ከሰዎችም ጋርም ልክ እንዲሁ እናድርግ።

❖ ሰዎች ሁሉ ጻድቅና መልካም አይደሉም፤ ብዙዎቹ ድክመቶች ወይም የተወሰኑት ባሕርያቸውን ተቆጣጣሪ የሆነ አመሎች አሉባቸው፤ ሰዎች የተለያዩ ዓይነቶች ናቸው፤ ከእነዚህ አንዳንዶች ሁከተኞች ናቸው፤ ስለዚህ በጠባያቸው ተጽዕኖ እንደማይደረግበት ተመልካች እንሁን፤ ባሕሪያቸውንም በጥበብ እንቀበላቸው።

📌 ምንጭ
✍️ ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ሺኖዳ ሳልሳዊ

https://hottg.com/ethioadbrat
እንደ ሁሉም Airdrop ኦች #Holdcoin በቴሌግራም የሚደገፍ እና በአጭር ግዜ verify ማግኘት የቻለ ቦት ነው ።

➔ Holdcoin ላይ ትኩረት አድርጋችሁ ብትሰሩ ይመከራል

በተጨማሪ USDT በየቀኑ reward አለው እንዳያመልጣቹ

➔ ለመጀመር 👇👇👇
https://hottg.com/theHoldCoinBot/app?startapp=ref_Jpfct2kK
እንደ ሁሉም Airdrop ኦች #Holdcoin በቴሌግራም የሚደገፍ እና በአጭር ግዜ verify ማግኘት የቻለ ቦት ነው ።

➔ Holdcoin ላይ ትኩረት አድርጋችሁ ብትሰሩ ይመከራል

በተጨማሪ USDT በየቀኑ reward አለው እንዳያመልጣቹ

➔ ለመጀመር 👇👇👇
https://hottg.com/theHoldCoinBot/app?startapp=ref_Jpfct2kK
Forwarded from 🟢ናታኒም ፖሮሞሽን🟢
🙋‍♂አንድጥያቄ

✞በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ ሰው ሰውን መግደል የጀመረው በማን ነበር ?✟

          👇👇👇
https://hottg.com/addlist/2TkBck2rFoxMjNk
https://hottg.com/addlist/2Tk_Bck2rFoxMjNk
HTML Embed Code:
2024/06/16 00:06:36
Back to Top