TG Telegram Group Link
Channel: ስለአገው ህዝብ ይመለከተኛል
Back to Bottom
Forwarded from DW Amharic (DW Amharic)
በአዲስ አበባና አካባቢዋ ለልማት ሲባል ከቦታቸዉ ለተነሱ አርሶ አደሮች 20/80 የጋራ መኖሪያ ቤቶች ምትክ እንዲያገኙ የተወሰነው ከወራት በፊት ነው፤ ውሳኔው አዲስ አይደልም ሲል የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ገለፀ።
የኮርፖሬሽኑ ዋና ዳይሬክተር ኢንጂኒየር ደሳለኝ ተረፈ ለዶቼ ቬለ (DW)እንደገለፁት በአዲስ አበባ ዳርቻዎች ይኖሩ የነበሩና ከቦታቸዉ የተነሱ አርሶ አደሮች በ20 / 80 የጋራ መኖሪያ ቤቶች መርሃ ግብር ተጠቃሚ እንዲሆኑ የተወሰነው ታህሳስ 24 ቀን፣ 2011 ዓ.ም ነው።
ዉሳኔዉ በከተማዉ ካቢኔ መሰሰጠቱን የገለፁት ኃላፊዉ «ይህ ውሳኔ ደግሞ ግንቦት 2011 ዓ.ም ተግባራዊ ተደርጓል። እንደ አዲስ የሚያወዛግብ ነገር አይደለም » ሲሉ ገልፀዋል። ይሁንና ይህ ውሳኔ የሚመለከታቸው ሰዎች ቁጥር ምን ያህል ነው? በሚል ከDW ለተነሳላቸዉ ጥያቄ ኃላፊው፤ «ማህበራዊ መገናኛዎች ላይ የተምታታ ቁጥር አለ፣ ትክክለኛ ቁጥር የለም ቁጥሩንም አልገልፅም » የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።
ውሳኔው መጀመርያውኑም እጣ ከመውጣቱ በፊት የተወሰነ ነው ያሉት ኃላፊው አሰራሩ የነበረ እና ምትክ 20 / 80 ቤቱ በሁሉም የቤት ግንባታዎች በሚከናወኑባቸው ቦታዎች የሚሰጥ መሆኑን አብራርተዋል።
የልማት ተነሽዎቹ በወቅቱ ካሳ አልተከፈላቸዉም ወይ? በሚል ለተነሳላቸዉ ጥያቄ፤ ምላሽ መስጠት ያለበት ሌላ አካል መሆኑን አመልክተዋል።
ተነሺ አርሶአደሮቹ በዚህ የቤት መርሃ ግብር ተጠቃሚ ሊሆኑ የቻሉት ግን መንግስት በግልጽ በወሰነው የቆየ አሠራር ነው ብለዋል።
ለ20 / 80 የጋራ መኖሪያ ቤት ለዓመታት ቆጥበው እጣ የወጣላቸው የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች፣ እስካሁን ወደ ቤታቸው ያልገቡ እድለኞች አሉ፤ ይህስ የት ደረሰ ብለን የጠየቅናቸው ኃላፊው፦ ጉዳዩ ኮሚቴ ተቋቁሙ እየታየ ነው ብለዋል። በተጨማሪም በሃገር ደረ
ጠ/ሚር አብይ አህመድ ለኖቤል ሰላም ሽልማት መገመታቸውን የፖለቲካ ሰዎቻችን እንዴት አዩት? ካናገርኳቸውን የሁለቱን ላጋራችሁ:

ፕ/ር መራራ ጉዲና: "ሌላው ሌላው ነገር ውስጥ ሳታስገባኝ አንድ ኢትዮጵያዊ ቢያገኝ ጥሩ ነው። እኔ ሽልማቱን ቢያገኙ ተቃውሞ የለኝም። ሀገራችን መንታ መንገድ ላይ ትገኛለች፣ እንደዛም ሆኖ ቢያገኙ ጥሩ መስሎ ይታየኛል።"

አቶ መልካሙ ሹምዬ ከአብን: "ሽልማቱ ይገባቸዋል ብዬ አላምንም። እርሳቸው ስልጣን ላይ ከመጡ ጀምሮ በርካታ ግጭቶች፣ የሰዎች መሞት፣ መቁሰል እና መፈናቀል ተከስቷል። እየተነሱ ያሉት ግጭቶች ደግሞ communal violence ብቻ ሳይሆኑ የፖለቲካ ግጭቶች ናቸው።"

ሙሉ ዜናውን አሶሼትድ ፕረስ ላይ ይጠብቁ!

አሥተያየቶችን እዲሁም መረጃወችን በዚህ አድርሡኝ ፡- @Love7682

@ethio27 @ethio27
የባልደራስ በርካታ አባላቱና የሰልፉ አስተባባሪዎች ታሰሩ❗️

⚡️የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን በነገው ዕለት በከተማይቱ በሚገኘው የመስቀል አደባባይ የሚካሄድ ሰላማዊ ሰልፍም ሆነ ስብሰባ #እንደሌለ አስታወቀ። ለነገ ሰላማዊ ሰልፍ ጠርቶ የነበረው የአዲስ አበባ ባለ አደራ ምክር ቤት (ባልደራስ) በበኩሉ በርካታ አባላቱ እና የሰልፉ አስተባባሪዎች ዛሬ መታሰራቸውን ገልጿል።

⚡️የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን በይፋዊ የፌስ ቡክ ገጹ ዛሬ ይፋ እንዳደረገው በነገው ዕለት በሚኖረው ሰልፍ ምክንያት የሚዘጉ መንገዶች እንደሚኖሩ ፖሊስ ኮሚሽኑ እንደገለጸ ተደርጎ የተላለፈው መረጃ ሀሰተኛ ነው ብሏል።

⚡️ የከተማይቱ ነዋሪ በነገው ዕለት በመስቀል አደባባይ ሰላማዊ ሰልፍም ሆነ ስብሰባ የሌለ እና ምንም የሚዘጋ መንገድ አለመኖሩን ተገንዝቦ መደበኛ እንቅስቃሴ ማድረግ እንደሚችል ፖሊስ ኮሚሽኑ አሳስቧል። 

⚡️የነገውን ሰላማዊ ሰልፍ የጠራው በጋዜጠኛ እና አክቲቪስት እስክንድር ነጋ የሚመራው የአዲስ አበባ ባለ አደራ ምክር ቤት (ባልደራስ) በዛሬው ዕለት በበርካታ አባላቱ እና ደጋፊዎቹ ላይ የእስር ዘመቻ መደረጉን አስታውቋል። እስካሁን ምን ያህል ሰዎች በትክክል እንደታሰሩ እንደማይታወቅም አቶ እስክንድር ለ DW ተናግረዋል።   

©Dw

🦁@ethio27


አባይ ሚዲያ (ጥቅምት 1፣2012) የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር /ኢህአዴግ/ “ህዝባዊ ወያኔ ሃርነት ትግራይ /ህወሃት/፣ የአማራ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ /አዴፓ/፣ የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ /ኦዴፓ/ እና የደቡብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ /ደኢህዴን/” አራት እህት ድርጅቶች የተፈጠረ ግንባር መሆኑ ይታወቃል። ግንባሩ የቤንሻንጉል ጉሙዝ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ /ቤጉህዴፓ/፣ የሐረሪ ብሄራዊ ሊግ /ሐብሊ/፣ የጋምቤላ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ /ጋህዴን/፣ የሶማሌ ህዝቦች ዴሞራሲያዊ ፓርቲ /ሶህዴፓ/ እና የአፋር ብሔራዊ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ /አብዴፓ/ የተባሉ አምስት ፓርቲዎች ደግሞ በአጋርነት ይዟል።
ሆኖም ይህንን በግንባርና አጋርነት የሚገኘውን ፓርቲ በመተው አንድ ውህድ ፓርቲ ለመመስረት ታስቧል።
ሀዋሳ ላይ በተካሄደው 11ኛው የኢህአዴግ ድርጅታዊ ጉባኤ ግንባሩን ወደ አንድ ውህድ ፓርቲ ለማምጣት የሚያስችሉ ተግባራት እያከናወነ መሆኑም ተገልጿል። ይህንን የፓርቲውን እንቅስቃሴ አስመልክቶ የታሪክ መምህሩ ታዬ ቦጋለ እንዳሉት ውህደቱ እውን ከሆነ በአገሪቱ እየተስተዋለ ያለውን አንዱን ብሔር ከሌላው አብልጦ የማየት እሳቤ የሚያስወግድ ይሆናል። በዜጎች አብሮ የመኖር እሴትና ኢትዮጵያዊነትን በማጠናከር በኩል አወንታዊ ሚና እንዳለውና ሁሉም ዜጋ በአገሪቱ ጉዳይ ላይ እኩል ተሳታፊና ተጠቃሚ እንዲሆንም ያግዛል ነው ያሉት።
የኢህአዴግ የድርጅቶች አወቃቀር ከስያሜው ጀምሮ እሀትማማች ፓርቲና አጋር ፓርቲ ብሎ መለየት በራሱ ከፋፋይ ነበር ብለዋል መምህር ታዬ። ፓርቲው አሁን ሊተገበር ያሰበው ውህደት የመንግስትን አብሮ የመኖር እሴት ለማጠናከር የያዘውን አቋም ያሳየም ነው ብለዋል። ላለፉት በርካታ ዓመታት ከአገር ይልቅ ብሔር ቀድሞ የታየበትና አንዱን ብሔር ከሌላው አብልጦ የማየት እሳቤ የተንሰራፋበት ነበርም ነው ያሉት። ይህ ደግሞ ማህበረሰብ ውስጥ የነበረውን አብሮ የመኖር እሴት የመከፋፋለና ቁርሾ የፈጠረ በአገራዊ አንድነት ላይም ጥላሸትን የቀባ ነበር ብለዋል።
ከአገው ብሔራዊ ሸንጎ የዋግ ኽምራ ዞን ስራ አስፈጻሚ አባላት የተሰጠ መግለጫ
የዋግ ኽምራ የሸንጎ ስራ አስፈጻሚ አባላት ትናንት ጥቅምት 5/2/2012 ዓ.ም ሰፊ ውይይት በማድረግ በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ የአቋም መግለጫ በማውጣት ተጠናቋል። በብዙ ጉዳዮች ውይይት ያደረገው የሸንጎው የዞኑ ስራ አስፈጻሚ አባላት ስብሰባ ሸንጎ አስካሁን የመጣበትን ሂደት ገምግሟል። በግምገማውም በበቂ ደረጃ አደረጃጀት በመፍጠር እና በየወረዳው መዋቅር በፍጠር እረገድ ክፍተት እንዳለበት አይቷል። እንደዚሁም አደረጃጀቱን ለማጠናከር መሰናክል የሆነውን የፋይናንስ ችግር ለመቅረፍ ወደፊት በምን አቅጣጫ ሊጓዝ አንደሚገባው አስቀምጧል። መፍትሔ ተብለው ከተቀመጡት ውስጥ ድርጅቱ ከምርጫ ቦርድ አስፈላጊው የድጋፍ ደብዳቤ ስለተጻፈለት በጽ/ቤት ደረጃ የሸንጎ የባንክ አካውንት ተከፍቶ ከአባላቶቹ እና ደጋፊዎቹ መዋጮ መስብሰብ መጀመር እንዲጀምር ማድረግ ይገኝበታል። ይህም በቅርብ ጊዚያት እንዲጠናቀቅ ስምምነት ላይ ተደርሷል። ሌሎች የድርጅቱ የውስጥ ጉዳይችን በተመለከተም ሰፊ ውይይት የተደረገ ሲሆን በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ የሚከተለውን የአቋም መግለጫ አውጥቷል።
.
1, የሰዎች ተንቀሳቅሶ የመስራት መብት አለመከበርን በተመለከተ
የአገው ብሔራዊ ሸንጎ የዋግ ኽምራ ዞን ስራ አስፈጻሚ አባላት በወቅታዊ የሀገራችን ፖለቲካ ሁኔታ ውይይት ባደረግንበት ወቅት በሀገሪቱ አንዱ ለዲሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታ እንቅፋት በመሆን እያስቸገረ የሚገኘው የመንጋ ፍርድ እንደሆነ ገምግሟል። በዚህም መሠረት በየቦታው በቡድን የተደራጁ ኃይሎች የፈለጉትን መንገድ እየዘጉ ህዝብን እንደሚያጉላሉ በተጨባጭ ስለታየ መንግስት ኃላፊነቱን እንዲወጣ እንጠይቃለን። ለአብነት በቅርቡ ከአማራ ክልል እና ከትግራይ ክልል ወደ አዲስ አበባ የሚያስገቡ መንገዶች በተደራጁ ኃይሎች ተዘግቶ መመልከታችን ለአብነት የሚበቃ ክስተት ነው። እንደዚህ አይነቱ መንገዶችን እየዘጉ ህዝብን ማንገላታት የትኛውም አይነት ፖለቲካ ተቦክቶ ቢጋገር ከጥፋተኝነት ሊያድን የማይችል የኋላ ቀሮች ተግባር ነው። በመሆኑም ኢትዮጵያን የሚወድ ዜጋ ሁሉ የኢትዮጵያዊያንን በፈለጉት ቦታ ተዘዋውሮ የመኖር ፣ የመስራት እና ንብረት የማፍራት መብት እንዲከበር ህገ ወጥ ተግባርን አጥብቆ ሊታገለው ይገባል። መንግስትም ህገ ወጦችን ስርዓት ሊያሲይዝ ይገባል እንላለን።
.

2, የአበርገሌ ወረዳን ወቅታዊ ሁኔታን በተመለከተ
የዞኑ ስራ አስፈጻሚ አባላት ሰሞኑን አበርገሌ ወረዳ ላይ የአመራሮች እስርን ተከትሎ በተፈጠረው አከባቢያዊ ፖለቲካ ሁኔታ ውይይት አድርጓል። በውይይቱ የአገው ህዝብ ተደራጅቶ ማየት የማይፈልጉ ጸረ አገዎች የአዴፖን የውስጥ ጉዳይ ወደ ሸንጎ በማላከክ ውስጥ ውስጡን ሸንጎ አበርገሌ ላይ ብጥብጥ ለመፍጠር እየሰራ ነው የሚል አሉባልታ እየነዙ ይገኛል። እራሱ አዴፖ ሾሟቸው እራሱ አዴፖ ያሰራቸው የአበርገሌ አመራሮችንም የሸንጎ ደጋፊና አባላት ናቸው ተብሎ ወሬ እንዲሰራጭ እየተደረገ እንደሆነ ደርሰንበታል። የአመራሮቹ እስር ምክኒያት ወደፊት ፍርድ ቤት ወይም ራሱ አዴፖ የሚነግረን ሆኖ ሸንጎ አበርገሌ ጉባኤ ለማድረግ ሲሰናዳ ከፍተኛ ጫና ካደረጉብን አመራሮች መካከል አሁን በእስር ላይ የሚገኙት የአበርገሌ አመራሮች ይገኙበታል። በመሆኑም አዴፖ በውስጡ የሚገኙ አገዎችን በሸንጎነት እየከሰሰ ለማሸማቀቅ እና ለማስወገድ ካልፈለገ በስተቀር በየመንደሩ ሸንጎ ናቸው ከህወሓት ጋር ግንኙነት አላቸው የሚል አሉባልታ ማስወራቱ አይጠቅመውም። ስለሆነም ህዝባችን የአገው ሸንጎ የዋግ ኽምራ ዞን ስራ አስፈጻሚ አባላት በሰላማዊ መንገድ በምርጫ ብቻ ለመወዳደር የሚታገል ስብስብ እንጅ የጭፍኖች እና የግጭት ናፋቂዎች ፍላጎት ማስፈጸሚያ አለመሆኑን እንዲረዳ እናስገነዝባለን። የአበርገሌ ህዝብ በአገውነቱ የማይደራደር መሆኑን ጠንቅቀን የምናውቀው የዞኑ ስራ አስፈጻሚዎች አበርገሌን ወደ ትግራይ የመውሰድ እንቅስቃሴ ቢፈጠር የሚታገለው ማንም ሳይሆን እራሱ ጀግናው የአገበርገሌ ህዝብ እንደሆነ ጠንቅቀን እናውቃለን። ሸንጎም የሚታገለው ከአበርገሌም አልፎ በትግራይ ስለሚገኙም አገዎች ጭምር ስለሆነ የአገው ህዝብን አንድነት የሚፈታተን ስራ ውስጥ ፈጽሞ ሊገኝ እንደማይችል ለህዝባችን ማረጋገጥ እንወዳለን። አጽኖት ሰጥተን ማሳሰብ የምንፈልገው ነገር ቢኖር አዴፖ በዋግ ኽምራ ዞን አመራሮች ላይ ብቻ እየወሰደ የሚገኘው የእስር እርምጃ የህግ የበላይነትና እና ፍትህን የሚያስከብር እንደማይሆን ነው። ጉዳዮ የሙስና አለያም ሌላ የፖለቲካ ችግር ካለ እንደ ክልል በሁሉም ዞኖች በተመሳሳይ ሊተገበር ይገባል እንጅ የዋግ ኽምራ ዞንን ብቻ ማእከል ያደረገ የእስር ዘመቻ ከቀጠለ ወደ አከባቢው የጸጥታ መደፍረስ ላለመምጣቱ ዋስትና አይኖርም። ከህወሓት ጋር ንክኪ አላችሁ በሚለው የቆየ ፕሮፖጋንዳ ስራ ምክኒያት ዋግ ላይ የሚደረገው እንቅስቃሴ በህዝባችን ላይ አላስፈላጊ ጦስ ይዞ እንዳይመጣ እንሰጋለን። ስለሆነም አዴፖ በራሱ ያልተጠና ችጉል እርምጃ ምክኒያት በአከባቢያችን የጸጥታ ችግር ቢፈጠር በሶስተኛ ወገን አላኮ ሊያልፈው የሚችል ስላልሆነ የህዝባችንን አንድነትና ደህንነት አክብሮ እንዲንቀሳቀስ እንጠይቃለን።
.

3, መፍተሔ የራቀው የቅማንት ህዝብ ጥያቄ በተመለከተ
የዋግ ኽምራ ሸንጎ ስራ አስፈጻሚ አባላት ለቅማንት ህዝብ ጎንደር ከሚኖረው አማራ ፡ ለአማራ ህዝብ ጎንደር ከሚኖረው ቅማንት የበለጠ የሚቀርበው እንደሌለ ይገነዘባል። ይህ ብቻም ሳይሆን ህዝቡ በተለያየ የማንነት መጠሪያ ይታወቅ እንጅ አንድ ህዝብ እንደሆነ ይረዳል። ሸንጎ ለቅማንት አገዎች መብትም የሚታገል ፖርቲ ነው በዚህም የቅማንት ህዝብ ዘላቂ ጥቅምና ሰላም የሚረጋገጠው የወገኑ የአማራ ጥቅምና ሰላም ሲረጋገጥ ነው ብሎ ያምናል። የቅማንትና አማራን ፍቅርና አንድነት ሸንጎ አጥብቆ ይፈልገዋል። ህጋዊ የህዝብን ጥያቄ ተገን አድርጎ ተለያይተው የማይለያዩ ህዝቦችን እርስ በእርስ የሚያጋጩ ኃይሎች ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ እንጠይቃለን። የፌደራሉ መንግስት እና የክልሉ መንግስት የህዝብን ድምጽ ሰምታችሁ መፍትሔ ልትሰጡበት ይገባል። የቅማንት የማንነት ጥያቄ ምክኒያት ተደርጎ የሚፈጸመው የግጭት ነጋሪት እንዲቆም እንጠይቃለን። የጎንደር ቅማንት እንዲሁም የጎንደር አማራ መሞት ሊቅም ይገባል። ቅማንትን ያላከበረች ጎንደር ብሎም አማራ ክልል አማራን ያላከበረች ጎንደር ብሎም አማራ ክልል ሰላም እንደማትሆን ተገንዘበን እንድንከባበር ጥሪያችንን እናቀርባለን። .
የአገው ብሔራዊ ሸንጎ የዋግ ኽምራ ዞን ማስተባበሪያ ጽ/ቤት
ቀን 6/2/2012 ዓ.ም
ሰቆጣ
የአገው ህዝቦች ህልዉና በልጆቹ አንድነትና ጥረት እዉን ይሆናል፡፡
"Less less politics more more economics "
~~~
የአዊ ብሔረሰብ አስተዳደር በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ውስጥ ራሳቸውን በራሳቸው እንዲያስተዳድሩ ከተደረጉት 3 የብሔረሰብ ዞኖች አንዱ ነው። ዞኑ ከክልሉ ዋና ከተማ ባህርዳር በደቡባዊ ምዕራብ አቅጣጫ በ122 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ይገኛል። የብሔረሰብ አስተዳደሩ መቀመጫ የሆነችው እንጅባራ ከተማ ደግሞ ከአዲስ አበባ ባህርዳር መንገድ በ435 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ መገኛዋ ነው።
የአዊ ብሔረሰብ አስተዳደር
#በምስራቅ- የምዕራብ ጐጃም ዞን፣
#በምዕራብ- የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል፣
#በሰሜን- የሰሜን ጎንደርና ምዕራብ ጐጃም ዞኖች፣
#በደቡብ- ምዕራብ ጐጃምና የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልል ያዋስኑታል።
የአዊ ብሔረሰብ አስተዳደር የበርካታ ታሪካዊና ተፈጥሮአዊ መስህብ ሀብቶች፣ የባህል እሴቶችና ማህበራዊ ኩነቶች ባለቤት ነው። የተለያዩ ውሃማ አካሎች በጥቅም ላይ ሊውሉ የሚችሉ ትልልቅና መለስተኛ ወንዞች፣ ምንጮች፣ እርጥበት አዘል ባህር ሸሸ መሬቶች፣ ፏፏቴዎችና ሐይቆች የተመልካችን ቀልብ ሊስቡ የሚችሉ ውብና ማራኪ የቱሪስት መስህብ ሀብቶች መገኛ ነው። ማን ለሕዝቡ ጥቅም የውል? (የአዊ ባህልና ቱሪዝም መምሪያ ግን በሕይወት አለ? ከናይጄሪያ ነው ከቡልጋሪያ መጥተው እስኪያለሙልህ ነው የምትጠብቀው?) ዋታ ኩ ዲቪ?
ረጅም ዕድሜ ያስቆጠሩ በርካታ ገዳማት፣ አድባራትና አብያተ ክርስቲያናት፣ መካነ-መቃብሮችና ዋሻዎች፣ የብራና መጽሐፍት እንዲሁም ጥቅጥቅ የተፈጥሮ ደኖች፣ በርካታ የዱር እንስሳትና አዕዋፍ ዝርያዎች መገኛ ነው። ለአብነት የዘንገናና የጥርባ ሃይቅ፣ የትስኪ፣ የዶንደር፣ የፋንግና የጋርቾ ፏፏቴ፣ የዳንጉላ ዋሻና የወለተ ጴጥሮስ ገዳምን በጥቂቱ መጥቀስ ይቻላል። ይህ ሀብት ታዲያ የትኛው ስትራቴጅክ አመራር ወደ ገቢ ምንጭነት የቀረው?
ብሔረሰቡ ተቀድቶ የማያልቅ ባህል፤ የራሱ ቋንቋና በኢትዮጵያ ታሪክ አስተዳደራዊ ድርሻ የነበረው ቀደምት ህዝብ ነው አገው፡፡

አዊ ዞን እንፊዲ፣አሰም፣ዚሪኺ፣ገምበሃ እና ቓዣ ከሚባሉ ተራሮችና ሰንሰለታማ ጋራዎች በስተቀር ሜዳማና ለም ነው።የአዊ-አገው ሕዝብ በሰሌን ጥላ፣ በፈረስ እርሻ፣ በአካባቢ ጥበቃና ልማት ይታወቃል። በአዊ አካባቢ በውሀ ሀብት በኩል ጥቅም ሊውሉ የሚችሉ በርካታ ወንዞችና ሀይቆችም ይገኛሉ።ለምሳሌ ፣አዩ፣ዱራ፣አጣም፣ዲም፣ግዛኒ፣አርዲ የተባሉና ሌሎች ወንዞች ትስኪ፣ፋንግ፣ጋርቾ የተሰኙ ፏፏቴዎች ዚምቢሪ፣ዘንገና እና ጥርባ የመሳሰሉ ሃይቆች ይገኙበታል።ማልማት ለሚችል ባለሀብት ምቹ አጋጣሚ አለ።
ሌላው በአዊ ዘንድ የሚታወቀው የ‹‹አዊት ድጋግ›› ወይም "የአገው ዣን ጥላ" ነው።አዊት ድጋግ የአገው መገለጫ ልዩ ማህተም ነው። ዘንገና እንደምታዩት በከፍታ የመልክአ-ምድር ወለል ላይ የሚገኝ አስደማሚ የተፈጥሮ ውበት ነው።ዘንገና ሐይቅ 16ዐ ሜትር ጥልቀት አለው።በሀይቁ አቅራቢያ በደን የተሸፈኑ ተራሮችና በርካታ ዋሻዎች ይገኛሉ፡፡ከፍተኛ የቱሪዝም ምንጭ የሚሆኑ የተፈጥሮ ሀብቶች መገኛ ነው አገው ምድር! ነገር ግን ይህን በተፈጥሮ ፀጋ የታደለ ምድር በማንና እንዴት ይልማ? ይህ ሊያሳሰበን ይገባል! ኖጂ እንፃኽስትናውላስ አይ ይንታምባይ?
እርግጥ እየተሰራ ያሉ ጥቂት ስራዎችን እውቅና ሳንነፍግ ማለት ነው! የብሔሰቡ አስተዳደር ከእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ መቋቋምና በተፋጠነ ሁኔታ ወደ ስራ መግባት ጋር ተያይዞ ተጨማሪ የመልማት ዕድልን ከመጎናፀፉ ባሻገር በተለይ የእንጅባራ ከተማ እድገት ላይ በጎ አስተዋፅኦ እያበረከተ ይገኛል። በስራ ዕድል ፈጠራንም እያገዘ ይገኛል። ይሁን እንጂ አዊ አሁንም ከፍተኛ ቁጥር ያለው የተማረ ስራ-ዓጥ የያዘ፣በቂ መሰረተ ልማት ያልተዘረጋለት አካባቢ ነው። በተፈጥሮና ከተቸረው ፀጋ አኳያ ግን አሁን ትልቅ የመልማት አቅም ያለው ነገር ግን በአግባቡ ያልለማ አካባቢም ነው። ይህ ቁጭትን ሊጭር ይገባል። ብዙ ግዜ በክልሉ ከሚመደበው በጀት ጋር ተያይዞ የሚነሳ ቅሬታ መኖሩን ባውቅም የብሔረሰብ አስተዳደሩ በተሰጠው ስልጣን በራሱ መስራት የሚችላቸውን በርካታ ተግባራት እንኳ በቸልተኝነት የሚመለከት ነው። በነገራችን ላይ በአማራ ክልል ሕገ-መንግስት መሠረት ለብሔሰብ ምክር ቤቱ የተሰጡ ስልጠንና ተግባራትን ብትመለከቱ ከክልሉ ምክርቤት ያልተናነሰ ሰፊ ስልጣን ያለው ነው።

ለምሳል ብሔረሰብ አስተዳደሩ በሚከተሉት ጉዳዮች የክልሉን መንግስት መውቀስ አይችልም!

ሀ) በብሔረሰብ አሰተዳደሩ ስር የሚገኙ የዞኑ፣የወረዳ፣የከተማ አስተዳደር የመንግስት የስራ አስፈፃሚዎችን ሹመት፣(ማን መክሮ ዘክሮ አፅድቆ እንደሚልክ የሚታወቅ ስለሆነ) የመሰለውን መርጦ መላክ ስልጣን ተሰጦታልና!
ለ)የብሔረሰብ ምክር ቤት አባላት ምርጫ፣ (በሕዝብ የተመረጡ ስለሆኑ) የሚጠቅምህን መምረጥ መብትህ ነውና!
ሐ) በብሔረሰብ አስተዳደሩ አቅም በሚሰሩ ጉዳዮች( በተሰጠው ውስን በጀትም ቢሆን መለስተኛ ልማቶች ማከናወን፣የመልካም አስተዳደር ችግሮችን መፍታት፣ አገውኛ ቋንቋን ማሳደግ፣ ማበልፀግ ፣ባህሉን፣ታሪኩን ማስተዋወቅ ማሳደግ ወዘተ) እና ሌሎች መሰልጉዳዮችን በተመለከተ ለምን የክልሉን መንግስት ትወቅሳለህ? ኢክስተርናላይዝ ሳናደርግ ወደ ውስጥ እንመልከት! አካባቢውን እናልማ! ድህነትን የሚጠላ ማህበረሰብ እየበዛ፣ ፖለቲከኛ ብቻ ሳይሆን አልሚ አዕምሮዎች መበራከት አለባቸው! ለአዊ ውድቀትም ስኬትም ከታች እስከ ላይ ከሚገኙ የአዊ አመራሮች የተሻለ ሀላፊነት የሚወስድ ማነው? ማንም! ዘመኑን የዋጀ ጠንካራና ስትራቴጅክ አመራሮች እንደ ክልልም እንደዞንም ያስፈልጉናል!ትልቅ አቅም ያላቸው ምሁራን ወጣቶች አሉን እነሱ ወደ ፊት ይምጡ፣ ከምንም በላይ ግን ልማት የሕልውና ጉዳያችን ነው፤ ኢኮኖሚህን በአስተማማኝ መሠረት ላይ ከገነባህ የትኛውም ማዕበል አያናውጥህም! ከፖለቲካው ይልቅ ኢኮኖሚያዊ መበልፀጉ ላይ የሞት ሽረት ትግል ያስፈልጋል! ሁላችንም የራሳች በጎ አሻራ እናሳርፍ! ኬሻቲውማ ይዛኺ? "
ጜዋና ሳሳርስኹሳ ዳንዴ እድ ዋና ቼቫላላ"ናኑ ሴን ዝኮ!

https://m.facebook.com/story.php?story_fbid=1158866740982672&id=999060470296634
የአገው አባቶች በባህላዊ ልብሳቸው ሲደምቁ አቤት ማማራቸው።
💝💝💝💝💝💝💝💝💝💝💝💝
ጎበዝ የአገው አባቶች ከፍተኛ ምስጋና ክብር ይገባቸዋል።ለምን የሚለኝ ሰው ካለ
☞ጨዋ እና ታላቅ አክባሪ
☞ባህሉንና ተውፊቱን አክባሪ
☞ በየትም ቦታ እና ከየተኛውም ብሔርና ህዝብ ጋር ተዋዶና ተፋቅሮ የሚኖር ትውልድ በትጋት ቀርፀው አውጠዋልና።

©አስቹ አዊ
@ethio27
አዋሳ ይሰማል?

እንኳን ደስ አለን እንኳን ደስ አላችሁ።
የዛሬው ቀን ለእናንተ ብቻ ሳይሆን ለእኛ ለአገዎችም የደስታ ቀን ነው።
ያን ሁሉ ውጣ ውረድ አልፋችሁ ድልን
የተጎናፀፋችሁበት ልዩ ቀን ነው ዛሬ።
ደግሜ እንኳን ደስ አለን እንኳን ደስ አላችሁ!!!

::::::::::::::::::::://///////::::::::::::

#አዋሳ_ቢልም
#ሲዳማ_ቢሊማ

የአገውስ መቼ ይሆን•••••••••?

©ቲኖ ይን አገው
@ethio27
የመማር ማስተማር ሂደቱን ለማስቀጠልና የዩኒቨርሲቲውን ሰላም ለማስጠበቅ ከተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች በመጡ ተማሪዎች መካከል ስምምነት ላይ ተደረሰ፡፡
እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ፣ ህዳር 11/ 2012 ዓ.ም.
በተለያዩ የአገራችን ዩኒቨርሲቲዎች የተከሰተውን አለመረጋጋት ተከትሎ በእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ተፈጥሮ የነበረውን ስጋት ለመቅረፍ ከሰኞ ማለትም ከቀን 08/02/12 ጀምሮ ምክክር ሲካሄድ ቆይቷል፡፡
በምክክሩ ላይ የአካባቢው የሀገር ሽማግሌዎች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ ከክልልና ከዞን የተወከሉ አመራሮች፣ የዩኒቨርሲቲው የአስተዳደር አካላት፣ መምህራንና የተማሪ ተወካዮች እንዲሁም ሁሉም ተማሪዎች ተሳታፊ ሆነዋል፡፡
በውይይት ሂደቱም በዋናነት በሌሎች ቦታዎች ላይ የሚከሰቱት አላስፈላጊ ግጭቶች በዩኒቨርሲቲው ውስጥ ሊንፀባረቁ እንደማይገባና ተማሪ ጥያቄ ካለው በሰለጠነ መንገድ ማቅረብ እንዳለበት ተገልጿል፡፡
ከሁሉም አካባቢ የመጡ ተማሪዎች ተቻችለውና ተከባብረው ለዩኒቨርሲቲውና ለሀገር ሰላም በጋራ መቆም እንዳለባቸውም ስምምነት ላይ ደርሰዋል፡፡
በመጨረሻ የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚደንት ፕ/ር ብርሃኑ በላይ እና የሀገር ሽማግሌዎች ለተማሪዎች ምክር ሰጥተው፤ ለተገኘው ሰላምና በጋራ የመቆም መንፈስ አስተዋጽኦ ላበረከቱ አካላት ምስጋና አቅርበዋል፡፡
ከነገ ማለትም ከ12/03/12 ዓ.ም. ጀምሮ መደበኛ የመማር ማስተማር ሂደት የሚቀጥል ሲሆን ሁሉም ተማሪ በክፍል እንዲገኝም ስምምነት ላይ ተደርሷል፡፡
©እንጅባራ ዩንቨርስቲ
@ethio27
Channel name was changed to «አገው ህዝቦች_Agew_People»
Channel name was changed to «ስለአገው ህዝብ ይመለከተኛል»
The account of the user that owns this channel has been inactive for the last 5 months. If it remains inactive in the next 29 days, that account will self-destruct and this channel may no longer have an owner.
The account of the user that owns this channel has been inactive for the last 5 months. If it remains inactive in the next 8 days, that account will self-destruct and this channel may no longer have an owner.
HTML Embed Code:
2024/04/26 19:39:14
Back to Top