TG Telegram Group Link
Channel: Esat Tv Official (áŠĸáˆŗá‰ĩ) đŸ‡Ē🇹ī¸ī¸
Back to Bottom
Channel name was changed to ÂĢEsat Tv OfficialÂģ
ከጤፍ ዱቄá‰ĩ ጋር የተለá‹Ģዩ á‰Ŗዕá‹ĩ ነገሮá‰Ŋ áŠĨና ሰጋቱáˆĢ በመቀላቀል ለህá‰Ĩረተሰቡ ሊá‹Ģከፋፍሉ የነበሩ ግለሰá‰Ļá‰Ŋ በቁáŒĨáŒĨር áˆĩር ዋሉâ€ŧī¸

ህገ-ወáŒĨ ተግá‰Ŗሊ ሲፈፀም የነበረው በኮልፌ ቀáˆĢንዮ ክፍለ ከተማ ወረá‹ŗ 1 በተለምá‹ļ አጠáˆĢሊ ቆáˆŧ á‹ĩልá‹ĩይ ተá‰Ĩሎ በሚጠáˆĢው አáŠĢá‰Ŗá‰ĸ በአንá‹ĩ መጋዘን ውáˆĩáŒĨ ነውáĸ 

በመጋዘኑ ውáˆĩáŒĨ 47 ኩንá‰ŗል ምንነá‰ŗቸው á‹Ģልá‰ŗወቀ áˆĩáˆĢ áˆĩርና የáŠĨንጨá‰ĩ ፍቅፋቂ ሰጋ ቱáˆĢ 167 ኩንá‰ŗል የጤፍ ዱቄá‰ĩ ተከማá‰Ŋá‰ļ የተገኘ ሲሆን á‰Ŗዕá‹ĩ ነገሩን ከዱቄቱ ጋር የሚደá‰Ŗልቅ መጋዘኑ ውáˆĩáŒĨ áŠĨንá‹ŗይወáŒŖ የተቆለፈበá‰ĩ ሠáˆĢተኛ በፍተáˆģ መገኘቱን ፖሊáˆĩ አáˆĩá‰ŗውቋል áĸ

ከአáŠĢá‰Ŗá‰ĸው ማህበረሰá‰Ĩ በደረሰው áŒĨቆማ መሰረá‰ĩ የጅማ በር አáŠĢá‰Ŗá‰ĸ ፖሊáˆĩ áŒŖá‰ĸá‹Ģ በህግ አግá‰Ŗá‰Ĩ  á‰Ŗደረገው á‹ĩንገተኛ ፍተáˆģ በáˆĩáˆĢ ላይ የነበረውን ተጠርáŒŖáˆĒ áŠĨጅ ከፍንጅ በቁáŒĨáŒĨር áˆĩር አውሎ  á‰Ŗደረግው ተጨማáˆĒ   ምርመáˆĢ የንá‰Ĩረቱን á‰Ŗለቤá‰ĩን አፈላልጎ በመá‹Ģዝ  ተገá‰ĸው  ምርመáˆĢ áŠĨየተáŒŖáˆĢá‰Ŗቸው áŠĨንደሚገኝ  የአዲáˆĩ አበá‰Ŗ ፖሊáˆĩ ገልáŒŋልáĸ

በአቋáˆĢጭ ለመበልፀግ የሚሞክሩá‰ĩን ህገ-ወáŒĨ ነጋዴዎá‰Ŋን ህá‰Ĩረተሰቡ ሲመለከá‰ĩ  ለፖሊáˆĩ አጋልáŒĻ በመáˆĩጠá‰ĩ áŠĨá‹Ģደረገ á‹Ģለውን á‹ĩጋፍ አጠናክሮ áŠĨንዲቀáŒĨል የአዲáˆĩ አበá‰Ŗ ፖሊáˆĩ  áŒĨáˆĒውን አቅርቧልáĸ

@esattv1
@esattv1
HTML Embed Code:
2024/03/29 11:53:26
Back to Top