TG Telegram Group & Channel
Channel: ESAT TV
Back to Bottom
በኢትዮጵያ ተላላፊ ባልሆኑ በሽታዎች የሚያዙና የሚሞቱ ሰዎች ቁጥር በየጊዜው እየጨመረ ነው‼️

ጤናማ ያልሆነ የአናኗር ዘይቤ በኢትዮጵያ ተላላፊ ባልሆኑ በሽታዎች የሚያዙና የሚሞቱ ሰዎች ቁጥር እንዲያሻቅብ ማድረጉ ተገለጸ። ከፍተኛ የደም ግፊት፣ የስኳር ሕመም፣ ስር የሰደደ የመተንፈሻ አካል ችግር፣ ካንሰር፣ የልብ ህመም፣ የደም ስር ችግሮችና የመሳሰሉት ተላላፊ ካልሆኑ በሽታዎች መካከል የሚጠቀሱ ናቸው፡፡

@ESATTv1
@ESATTv1
#ችሎት‼️

ባለፉት አራት ተከታታይ የችሎት ቀጠሮ ላይ ሳይቀርቡ የቀሩት እነ አቶ ጃዋር መሃመድ ዛሬ ፍርድ ቤት ቀረቡ

ከአርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳ ግድያ ማግስት በአዲስ አበባ እና በኦሮሚያ ክልል ሁከት በማነሳሳት ወንጀት ተጠርጥረው የተከሰሱት የኦሮሞ ፌዴራላዊ ኮንግረስ (ኦፌኮ)አመራሮች እና በፖለቲከኛ ጃዋር መሃመድ ስም በተከፈተው መዝገብ ስር የተጠቀሱት ተከሳሾች ዛሬ ፍርድ ቤት ቀረቡ፡፡

ባለፉት አራት ተከታታይ የችሎት ቀጠሮ ላይ ሳይቀርቡ የቀሩት አቶ ጃዋር መሃመድ እና አቶ በቀለ ገርባ እንዲሁም በሁለትና ሶስት ችሎቶች ላይ ያልቀረቡት አቶ ሃምዛ አዳኔ እና አቶ ሸምሰዲን ጠሃን ጨምሮ በፖሊስ ቁጥጥር ስር የሚገኙ ሁሉም ተከሳሾች ዛሬ በፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ችሎት ቀርበዋል፡፡

ከዚህ ቀደም ታህሳስ 08 ቀን 2013 በዋለው ችሎት የተከሳሾቹ "ልዩ ችሎት" በማረሚያ ቤት አቅራቢያ ይቋቋምልን ጥያቄን ውድቅ ያደረገው ፍርድ ቤቱ በእለቱ በተከሳሾች ጠበቆች አማካኝነት ባደረሳቸው ትዕዛዝ ለዛሬው ችሎት "በኃይልም" ቢሆን እንዲቀርቡ የሚል ነበር፡፡

ይህንኑን በማስመልከት በዛሬው የችሎት ውሎ ላይ በእለቱ ለተሰየሙት ዳኞች ማብራሪያ የሰጡት የኦፌኮ ተቀዳሚ ምክትል ሊቀመንበር አቶ በቀለ ገርባ "ባለፉት የችሎት ቀጠሮዎች አራታችን ያልቀረብነው አገሪቱ ቀውስ ውስጥ የነበረች በመሆኑ ለደህንነታችን በመስጋታችን እና አስቀድመንም ማመልከቻ አስገብተን ነው" ብለዋል፡፡

በጠበቆቻቸው በኩል የደረሳቸው ትዕዛዝ "በኃይልም" ቢሆን እንዲቀርቡ የሚያዝ መሆኑን ለችሎቱ ያስታወሱት አቶ በቀለ ገርባ በዚሁ ንግግራቸው ከችሎቱ ሲቀሩ የነበረበት አግባብ ከቃሊቲው ማረሚያ ቤት ወደ ልደታ ፍርድ ቤት የችሎቱ ስፍራ ሲመላለሱ በደህንነታቸው ላይ የሚጋረጥ አደጋ ቢፈጠር "አገርንም ሌላ ቀውስ ውስጥ የሚያስገባት መሆኑን አስቀድመን በመገንዘብ እንጂ የፍርድ ቤቱን ትዕዛዝ ባለማክበር አይደለም" ነው ያሉት፡፡

"አንዳንድ የካቢነ ካባን የደረቡ ዳኞች ያሉት ያህል ሙያውን አክብረው ለፍትህ የቆሙ ዳኞች ለመኖራቸው እምነት አለን" ሲሉ አስተያየታቸውን ያከሉት አቶ በቀለ ገርባ ወደ ፍርድ ቤቱ ሲመላለሱ በየቦታው መቆማቸው ለደህንነታቸው አስጊ መሆኑን በመጠቆም ይህ እንዲታሰብበት ብለዋል፡፡ "ችሎቱ እና መንግስት ምንም አይነት አደጋ ላይደርስብን ኃላፊነቱን ሊወስዱ ይገባል፤ ወስደዋልም ብለን በማመናችን ነው በዚህ ችሎት ላይ ዛሬ የቀረብነው" ብለዋል፡፡

የኦፌኮ አመራር አቶ ጃዋር መሃመድ በበኩላቸው "እኛ ለህግ መከበር የታገልን በመሆኑ ህግ እናከብራለን፤ በወቅቱ በሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት ተከፍቶ አገሪቱ ቀውስ ውስጥ የገባችበት ወቅት መሆኑና እኛም የተከሰስንበት አንድ ብሔር ላይ ያነጣጠረ ጥቃት የሚል ክስ ስለሚገኝበት ሃገራችን ባለችበት ተጨባጭ ሁኔታ ለደህንነታችን ስጋት ገብቶን በችሎት ላይ ሳንታደም ቀርተናል" ብለዋል፡፡

ፖለቲከኛ ጃዋር መሃመድ አክለው ለችሎቱ
ባቀረቡት ሃሳብ "ወደፊትም ጥቃት ቢፈጸምብን በሸነ አሊያም ሌላ ቡድን ነው በሚል ማሳበብ እንደ ማይገባና ጥቃት ቢፈፀምብን መንግስት እና ይህ ችሎት ተጠያቂነቱን እንደሚወስዱ ህዝብና ችሎቱ ላይ የታደሙ የመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎች እንዲገነዘቡልን እንፈልጋለን" በማለትም ሃሳባቸውን ቋጭተዋል፡፡ የተከሳሾችን የቃል ማመልከቻ የሰሙት በእለቱ ችሎት የተሰየሙ ዳኛ የቀረበውን አቤቱታ ፍርድ ቤቱ ይረደዋል ብለዋል፡፡

"የተከሰሱ ማንም ሰው የፍርድ ቤቱን ትዕዛዝ አያከብሩም ብለን አናምንም፤ ትዕዛዙንም ስንሰጥ በዚሁ በመተማመን ነው" ብለዋል፡፡ ተከሳሾች ተገደውም ቢሆን ለዛሬው ችሎት ይቅረቡ የሚል ትዕዛዝ የተላለፈም ጉዳዩ እንዳይጓተት በማሰብ የቀረበ አማራጭ ሃሳብ ነው ያሉት የእለቱ ዋና ዳኛ ተከሳሾች ያቀረቡትን አቤቱታ በመንተራስ የችሎት ቁጥጥር እና ክትትል እንዲመቻች እናደርጋለን ብለዋል፡፡

"በችሎቱ እምነት እስካሁን የሚጎድል የለም" ያሉት ዳኛው በችሎቱ አመራሮችና በተከሳሾች በኩል ክፍተቶች ካሉም እያረምን እንሄዳለን በማለት ለጥያቄዎቹ ምላሽ ሰጥተዋል፡፡

በዛሬው ችሎት የተነበበው ብይን የጉዳዩ በፌዴራል ፍርድ ቤት መታየት አግባብነትን በህገመንግስቱ እና ሌሎችም አዋጆች በማጣቀስ ያስረዳ ሲሆን አቃቤህግ ባቀረበው ክስላይ ውድቅ የተደረጉ እና ተቀባይነት ያገኙ የተከሳሾች ጠበቃ የመቃወሚያ ሃሳቦችም
በዝርዝር ቀርበዋል፡፡

ግልጽነት የሚጎድላቸው እና ማብራሪያ የሚያሻቸው የዐቃቤህግ የክስ ሃረጎችም በተብራራ መልኩ እና በማያሻሙ ቃላት ተደግፈው እንደገና ተስተካክለው
እንዲቀርቡለት ችሎቱ ለአቃቤህግ ጥያቄ አቅርቧል፡፡

የጠቅላይ ዐቃቤህግ ተወካይም እንዲሻሻሉ የተባሉትን የክስ አንቀፆች አስተካክለው እንደሚያቀርቡ በመግለጽ፤ ነገር ግን ክሱን ያዘጋጁ የተቋሙ ባለሙያዎች የመስክ ስምሪት ላይ በመሆናቸው የአንድ ወር የጊዜ ቀጠሮ እንዲሰጣቸው ለችሎቱ ጥያቄ አቅርበው ነበር፡፡

የተከሳሾች ጠበቆች በፊናቸው ከቀረቡት የክስ መቃወሚያዎች ጥቂት ብቻ ተቀባይነት ማግኘቱ እንዳስከፋቸው አመልክተው፤ በዐቃቤህግ የተጠየቀው የአንድ ወር የቀጠሮ ጊዜ የሚረዝም፤ ፍትህን የሚያጓትት፣ የህግ የበላይነቱን ጥያቄ ውስጥ የሚያስገባ በመሆኑ፤በተቋም የሚዘጋጅ ክስ ባለሙያዎች መስክ ናቸው በሚል ሊሳበብ እንደማይገባ አንስተው ተከራክረዋል፡፡

የክስ ሂደቱ በተራዘመ ቁጥር ደንበኞቻቸው እንደሚጉላሉ ያነሱት የተከሳሾች ጠበቆች እስራቱም አስተዳደራዊ እስራት እንዳይመስል የአንድ ሳምንት ጊዜ ብቻ ክሱን አስተካክለው ለማምጣት በቂ ነው ሲሉም ሞግተዋል፡፡

ከተከሳሾች በክሱ ላይ የቃል ክርክር ያሰሙት አቶ ሃምዛ አዳነ "መንግስት እኛን ያሰረው ወንጀል ሰርተን ሳይሆን ከምርጫ ጫወታ ሊያገለን ነው" ብለዋል፡፡ "እስራታችን የፖለቲካ" ነው ያሉት አቶ ሃምዛ የፍርድ ሂደቱ ተቀላጥፎላቸው ወደ ቀጣዩ ምርጫ መሄድ እንዲቻል ፍርድ ቤቱ ጉልህ ሚናውን ሊጫወት ይገባል በማለት ለችሎቱ ጥያቄ አቅርበዋል፡፡

የፍርድ ቤት እና የፖሊስ ተቋማት ገለልተኝነት ለዴሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታ አበርክቶው የጎላ መሆኑን ለችሎቱ ያስረዱት ሌላኛው ተከሳሽ የኦፌኮ ስራ አስፈጻሚ አባል አቶ ደጀኔ ጣፋ በበኩላቸው ቀጣዩ ምርጫ ለኢትዮጵያ ሰላምና ለዜጎቿ ወንድማማችነት ያለው ወሳኝነት ከፍተኛ በመሆኑ የፍርድ ሂደቱ እንዲቀላጠፍላቸው ችሎቱን ጠይቀዋል፡፡

አቶ ደጀነ ችሎቱ መገናኛ ብዙሃን ከወገንተኝነት ፀድተው ትክክለኛ ዘገባ እንዲያቀርቡም ያሳስብልን
ባሉት መሰረት መገናኛ ብዙሃን የችሎቱን ውሎ ብቻ ነው መዘገብ ያለባቸው ብሏል፡፡ የግራ ቀኝ ክርክሩን ያደመጠው የእለቱ ችሎትም የፍርድ ሂደቱን ለማቀላጠፍ ሲባል በአስር ቀናት ውስጥ ዐቃቤህግ የክስ ማስተካከያውን አጠኖቆ ይቅረብ በማለት ለጥር 14 ቀን 2013 ዓ.ም. ተለዋጭ ቀጠሮ መስጠቱን ።

@ESATTv1
@ESATTv1
የትግራይ ግጭት የ2021 የቀጠናው ሀገራት ስጋት ነው ተባለ
ዓለም አቀፉ የስትራቴጂክ ጥናቶች ማዕከል ከሳሃራ በታች የሚገኙ ሀገራት በ2021 ሊያጋጥማቸው የሚችለውን ችግር በተመለከተ ትናንት ባወጣው ትንበያ አመቱ ለቀጠናው ሀገራት አስቸጋሪ መሆኑን አመልክቷል።በአካባቢው የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ከሚያሳድረው ኢኮኖሚያዊ ጫና በተጨማሪ በኢትዮጵያ በሞዛንቢክና በሳህል የሚታዩ ግጭቶች ከፍተኛ ተግዳሮቶች መሆናቸውን አመልክቷል።በተለይም ባለፈው ጥቅምት በኢትዮጵያ በፌደራል መንግስቱና በህዝባዊ ወያነ ሀርነት ትግራይ መካከል የተጀመረው ግጭት ቀጠናውን ሊያናጋው ይችላል ሲል ማዕከሉ አመልክቷል።ግጭቱ በቀጠናው መፈናቀልና አለመረጋጋትን ያባብሳልም ተብሏል። በኢትዮጵያ በሰላማዊ ሰዎች ላይ የሚፈፀመው ግድያ ፣ የኢትዮጵያ መንግስት ከሶማሊያ የሰላም አስከባሪ ወታደሮችን ማስወጣቱ፣ በኢትዮጵያና በሱዳን መካከል የተቀሰቀሰው የድንበር ውጥረት ም ለቀጠናው ሌላ ተጨማሪ ችግሮች መሆናቸውን የማዕከሉ ዘገባ ያሳያል።
ከዚህ በተጨማሪ በናይጄሪያና በታንዛኒያ የሚታዩ የተቃውሞ እንቅስቃሴዎች፣ በተለያዩ የቀጠናው ሀገራት የሚካሄዱ ምርጫዎች ሌላው የችግር ምንጭ ሊሆን እንደሚችሉም ተመልክቷል።

@ESATTv1
@ESATTv1
#FireAlert

በጦራ ከተማ በተለምዶ "ኑርቴ ነዳጅ" አከባቢ ከፍተኛ የሆነ የእሳት አደጋ መነሳቱን የከተማዋ ኮምኒኬሽን ጽ/ቤት አስታውቋል።

በጦራ ከተማ ከንግድ ባንክ በስተደቡብ ኑርቴ ነዳጅ ቤት አካባቢ የተነሳው ከፍተኛ የእሳት አደጋ ሙሉ በሙሉ ለመቆጣጠር ርብርብ እየተደረገ ይገኛል።

የእሳት አደጋው መንሰኤ ምን እንደሆነ ለግዜው አልታወቀም።

@ESATTv1
@ESATTv1
በመተከል ዞን የሟቾች ቁጥር ከ80 በላይ ሰዎች መገደላቸውን ኢሰመጉ አስታወቀ‼️

ከጥር 2 - 3 ቀን 2013 ዓ.ም በመተከል ዞን
በቡለን እና ጉባ ወረዳዎች፣ ኦሜድላ እና አይነሸምስ በተባሉ ቀበሌዎች ላይ ታጣቂዎች በፈጸሙት ጥቃት ከ50 በላይ ሰዎች መገደላቸውን እና መኖሪያ ቤቶችም መቃጠላቸውን ኢሰመጉ መረጃዎች ደርሰውታል፡፡

ታህሳስ 25 ቀን 2013 ዓ.ም ከቻግኒ ወደ ግልገል በለስ የሚሄድ መኪና ውስጥ የነበሩ ተጓዦች ማንዱራ ከተማ ላይ በታጣቂዎች እንዲወርዱ ተደርጎ አንድ ሰው መገደሉን እና ሁለት ሰዎች ደግሞ መቁሰላቸውን ለማወቅ ተችሏል፡፡

በሌላ በኩል፤ ‹‹በድባጤ ወረዳ፣ ቆርቃ ቀበሌ፣ ዳሌቲ በተባለች መንደር ትላንት ጥር 4 ቀን 2013 ዓ.ም ከሌሊቱ 11፡30 ጀምሮ የኦነግ ሸኔ እና የቤኒን ታጣቂዎች በፈጸሙት ጥቃት ሰዎች መገደላቸውን፣ እስከአሁን ድረስ እኔ ራሴ ባለሁበት የ82 ሰዎች አስከሬን በፍለጋ መገኘቱን እና የቀብር ቦታዎች እየተዘጋጁ መሆኑን አይቻለሁ›› ሲሉ አንድ የዓይን እማኝ ለኢሰመጉ ተናግረዋል፡፡

ኢሰመጉ፤ በትላንትናው ጥቃት ሰለባ የሆኑ ሰዎች ቁጥር ከ100 ሊበለጥ እንደሚችል፣ በአብዛኛው ሴቶችና ህጻናት መሆናቸውን እና ከ24 በላይ የሚሆኑ ሰዎች ቆስለው በጋሊሳ ጤና ጣቢያ እና ቡለን ሆስፒታል ውስጥ ህክምና እየተደረገላቸው መሆኑን ከአካባቢው ካሰባሰባቸው መረጃዎች ለማወቅ ችሏል፡፡

@ESATTv1
@ESATTv1
መከላከያ ሰራዊት አቶ ስዩም መስፍንን ጨምሮ ሌሎች የህወሓት አመራሮች መደምሰሳቸውን አሳወቀ።

የተደመሰሱት አመራሮች ፦

1. አቶ ስዩም መስፍን፣ የቀድሞው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የነበሩ እንዲሁም ውጊያውን የመሩና ሰራዊቱ ከቦታ ቦታ እንዳይንቀሳቀስ ያዘዙ፣ በመጨረሻም በሰራዊቱ ላይ ውጊያ እንዲከፈት ትዕዛዝ የሰጡ፣

2. አቶ አስመላሽ ወልደስላሴ፣ የህወሓት ከፍተኛ የፖለቲካ አመራር የነበሩ

3. አቶ አባይ ፀሃዬ፣ የህወሓት ከፍተኛ የፖለቲካ አመራር የነበሩ

4. ኮሎኔል ኪሮስ ሀጎስ ከመከላከያ የከዱ ከነጥበቃዎቻቸው ተደምስሰዋል።

በሌላ በኩል በቁጥጥር ስር የዋሉ ወታደራዊና የክልል አመራሮች ፦

1. ኮሎኔል ገብረመስቀል ገብረ ኪዳን፣ ከመከላከያ የከዱ
2. ኮሎኔል ፍስሃ ብርሃኔ፣ ከመከላከያ የከዳ፣
3. ኮሎኔል ዘረአብሩክ ታደሰ፣ ከመከላከያ የከዳ፣
4. ኮማንደር ገብረኪዳን አስገዶም የልዩ ሀይል ክፍለ ጦር አዛዥ የነበረ
5. አቶ መብራህቶም ክንዴ ሀይሉ፣ የክልሉ ውሃ ስራዎች ድርጅት ፋይናንስ ሀላፊ የነበረ በቁጥጥር ስር ውለዋል።

የሀገር መከላከያ ሰራዊት ኃይል ስምሪት መምሪያ ሀላፊ ብርጋዴር ጀነራል ተስፋዬ አያሌው፣ አሁንም የተደበቁ የህወሓት ቡድን አባላት በሰላማዊ መንገድ እጅ እንዲሰጡ ጥሪ አቅርበዋል።
@ESATTv1
@ESATTv1
📍አቶ ስብሃት “አሁን የቀብር ሥነ-ስርዓታችንን ነው በማስፈጸም ላይ ያላችሁት” ማለታቸውን ሌ/ጄኔራል ባጫ ገለጹ‼️

✒️አቶ ስብሃት በመከላከያ ሰራዊትና በፌዴራል ፖሊስ በቁጥጥር ስር ከዋሉ በኋላ በተለቀቀው ተንቀሳቃሽ ምስልና ፎቶ ሲስቁ ታይተዋል፡፡በርካቶችም አቶ ስብሃት ምን አሉ በሚል ሲነጋገሩ ነበር፡፡ሌፍተናንት ጄኔራል ባጫ ደበሌ እንደገለጹት አቶ ስብሃት ከተያዙ በኋላ አስተያየት ሰጥተዋል፡፡አቶ ስብሃት በተያዙበት ሰዓት ለከፍተኛ የመከላከያ መኮንኖች ፣ “እኛ እኮ ከሞትን ቆይተናል“ የሚል አስተያየት እንደሰጡ ሌ/ጄኔራል ባጫ ደበሌ ለጋዜጠኞች ተናግረዋል፡፡

✒️አቶ ስብሃት ከመያዛቸው አስቀድሞ “ቢያዙ ምን ይሉ ይሆን“ ብለው ጄነራሎቹ ይወያዩ እንደነበር የገለጹት ሌፍተናንት ጄነራል ባጫ “ግለሰቡ ቢያዙ ሕገ መንግስቱ ጥሩ ነው ፤ ሕገ መንግስቱ እንደዚህ ነው… ብለው ነው የሚያወሩት“ የሚል ግምት በጄኔራሎቹ ሀሳብ እንደነበር ተናግረዋል፡፡አቶ ስብሃት ከተያዙ በኋላም እንደተገመተው፣ አንደኛው ጄኔራል ሲያናግሯቸው “ሕገ መንግስቱ ጥሩ ነው፤ ተወያዩበት“ እያሉ ሲያወሩ እንደነበር የምዕራብ ዕዝ አዛዥ እንደገለጹላቸው ሌፍተናንት ጄነራል ባጫ ገልጸዋል፡፡

✒️ሌ/ጄኔራል ባጫ ተጫዋች ያሉት የምዕራብ ዕዝ ሌላ ጄኔራል አቶ ስብሃትን “ስለ ሕገ መንግስቱ ተወውና አንተ እስኪ ምን ይሰማሃል“ ብሎ እንደጠየቋቸው ተናግረዋል፡፡ አቶ ስብሃት ሲመልሱ “እኔ የሚሰማኝ እኛ ከሞትን እኮ ቆይተናል“ የሚል ነው፡፡

✒️“መቸ ነው የሞታችሁት“ የሚል ጥያቄ እንደተነሳላቸው ያስታወቁት ሌ/ጄነራል ባጫ “እኛ የሞትነውማ ኢህአዴግ የሚባለው የጠፋ ጊዜ ነው ፤ አሁን የምታደርጉት ምን እንደሆነ ልንገርህ? አሁን እያደረጋችሁ ያላችሁት የቀብር ሥነ ስነስርዓታችን እየፈጸማችሁ ነው“ ሲሉ መመለሳቸውን አንስተዋል፡፡

@ESATTv1
@ESATTv1
ሚስተር ባምቢስ አረፉ!

"ልቤን ብትከፍቱት ኢትዮጵያዊ ነኝ” -

በአገሪቱ የመጀመሪያው ሱፐር ማርኬት እ.ኤ.አ. በ1931 የተከፈተው በአዲስ አበባ ፍትሕ ሚኒስቴር አካባቢ የተተከለው ሱፐር ማርኬት ነው፡፡

የዚህ ሱፐር ማርኬት መከፈት ለአካባቢው ባምቢስ የሚለውን መጠሪያም አጋብቶበታል ።

ባምቢስ የሱፐርማርኬቱ ይዞታም ቻራ ላምቦስ ሲማስ በተባሉ ግሪካዊ ባለሀብት ሥር ነበር፡፡
ግሪካዊው ሚስተር ባምቢስ ቺማስ ከአገራቸው ወደ ኢትዮጵያ የመጡት በ1944 ዓ.ም ነው። ወደ ኢትዮጵያ ሲመጡ ገና የ21 ዓመት አፍላ ወጣት ነበሩ ፡፡ ባምቢስ ሱፐር ማርኬትን ከከፈቱበት ጊዜ ጀምሮ አካባቢው በስማቸው መጠራቱ ደስታ እንደሚሰጣቸውና እሳቸው ካለፉም በኋላ፣ ስማቸው ለዘላለም ኢትዮጵያ ውስጥ መቀጠሉን ሲያስቡት ኩራት እንደሚሰማቸው ተናግረው ነበር፡፡

ሚስተር ባምቢስ፤ ከሱፐር ማርኬት ስራቸው ጎን ለጎን ኢትዮጵዊያንን ለማገዝ በርካታ የበጎ አድራጎት ስራዎችን ሰርተዋለወ። ‹‹ሞት በኩላሊት ይብቃ››ለተሰኘው የኩላሊት ህሙማን ማህበር የ1 ሚሊዮን ብር ‹በሮተሪ ክለብ በኩል ለግሰዋል፡፡

ሰበታ ውስጥ ለአይነ ስውራን ህክምና የሚያገለግል በ5 ሚሊዮን 120 አልጋዎች ያሉትና ባለ ሶስት ፎቅ ሆስፒታል አሰርተዋል፡፡ 3 ትላልቅ አምቡላንሶችን ለሆስፒታል ለግሰዋል። ሁለቱን ለፖሊስ ሆስፒታል፣ አንዱን ደግሞ ለየካቲት ሆስፒታል አስረክበዋል፡፡

የኢትዮጵያው ወዳጅ ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩት በትናንትናው ዕለት ነው።

ነፍስ ይማር ሚስተር ባምቢስ!

@ESATTv1
@ESATTv1
📍በሻሸመኔ ከተማ ራሱን ሬንጀርስ ቡድን ብሎ የሚጠራ 38 አባላት ያሉት የማፊያ ቡድን በቁጥጥር ስር ዋለ‼️

✒️የሻሸመኔ ከተማ ሰላምና ጸጥታ ቢሮ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንዳስታወቀው በሞተር የታገዘ ከባድ ዝርፊያን ሲፈጽሙ የነበሩና ራሳቸወንን ሬንጀርስ ሲሉ የሚጠሩ የማፊያ ቡድን አባላትን በቁጥጥር ስር ውለዋል።

✒️የፅ/ቤቱ ሀላፊ አቶ ስንታየሁ ጥላሁን ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንዳሉት ይህ የማፊያ ድድን ከከተማዋ ወጣ ብሎ ባሉ የጨረቃ ቤቶች ይኖሩ የነበሩ ናቸው፡፡

✒️አሁን ደግሞ ራሳቸውን የበለጠ በማደራጀት በጦር መሳሪያ በመታገዝ ተመሳሳይ ቁልፎችን በማስቀረጽ የግለሰብ ቤቶችን ሲበርብሩ ፤ባለሶስት እና ባለ ሁለት እግር ሞተር ሳይክሎችን በመስረቅ በአጎራባች ክልሉች ጨምሮ እስከ ጠረፍ በመውሰድ ሲሽጡ እንደነበር ነው የተናገሩት፡፡

✒️የከተማዋ ፖሊስ ከህብረተሰቡ ጋር በመምከርም ባደረገው እልህ አስጨራሽ ጥረት ከ38 የቡድኑ አባላት ውስጥም 33ቱ በህግ ቁጥጥር ስር ውለዋል ብለዋል።

✒️በከተማዋ ውስጥ ከቅርብ ጊዜያት ጀምሮ ከባድ የንጥቂያና የዝርፊያ ወንጀሎች መበራከታቸውን ተናግረው በስርቆት ያገኙትንም ባጃጆችና ሞተር ሳይክሎች ወደ አጎራባች ክልሎች እስከ ጠረፍ ድረስ በመውሰድ ሲሸጡ እንደነበር ሃላፊው ተናግረዋል።

✒️ይህንን ተግባር ሲፈፅሙ የተገኙት ከከተማዋ ወጣ ካሉ የገጠር ከተሞች የመጡ እንጂ የከተማዋ ወጣቶች እንዳልሆኑ የሚናገሩት አቶ ስንታየሁ አሁን ጉዳያቸው በህግ እየታየ ነው ብለዋል፡፡

✒️የከተማዋ ነዋሪዎች በተደጋጋሚ በሰላም የመንቀሳቀስ ችግር እንዳለባቸው ሲናገሩ እንደነበር አስታውሰው አሁን ግን ከፖሊስ መዋቅሩ ጋር በተደረገው የተቀናጀ ጥረት 33ቱን ይዘናል ብለዋል አቶ ስንታዩ፡፡

Via Ethio FM

@ESATTv1
@ESATTv1
📍ስብሓት ነጋን ጨምሮ 20 የሕወሓት ቡድን ከፍተኛ አመራሮች ፍርድ ቤት ቀረቡ

✒️ስብሓት ነጋ እና ወ/ሮ ኬሪያ ኢብራሂምን ጨምሮ ሕገ መንግሥታዊ ሥርዓቱን በኃይል በመናድ ወንጀል የተጠረጠሩ 20 የሕወሓት ቡድን ከፍተኛ አመራሮች ዛሬ ፍርድ ቤት ቀርበዋል።

✒️የፌዴራሉ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በተጠርጣሪዎች እና በፖሊስ የቀረበውን የግራ ቀኝ ክርክር መርምሮ ፖሊስ የጠየቀውን የ14 ቀን የምርመራ ጊዜ ፈቅዷል።

@ESATTv1
@ESATTv1
አቶ ስብሃት ነጋ እና አቶ አባይ ወልዱን ጨምሮ በወንጀል የተጠረጠሩ 20 የህወሃት ቡድን አመራሮች ዛሬ ፍርድ ቤት ቀርቡ።‼️

የፌዴራል መካከለኛ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ችሎት በዛሬው እለት የቀረቡት የህወሃት ቁልፍ አመራሮች ከነበሩት መካከል አቶ ስብሃት ነጋ፣ አቶ አባይ ወልዱ፣ ዶክተር አብርሃም ተከስተ፣ ወይዘሮ ቅዱሳን ነጋ ይገኙበታል።

ተጠርጣሪዎቹ በሰሜን እዝ የአገር መከላከያ ሰራዊት ላይ በደረሰው ጥቃት እንዲሁም ሌሎች ተደራራቢ የወንጀል ተግባራት የሚፈለጉ መሆኑን መርማሪ ፖሊስ ገልጿል።

መርማሪ ፖሊስ ዛሬ ለመጀመሪያ ጊዜ ፍርድ ቤት የቀረቡት 20 ተጠርጣሪዎች ላይ የ14 ቀናት የምርመራ ጊዜ መጠየቁን ኢዜአ ዘግቧል። ፖሊስ በጠየቀው መሰረትም ፍርድ ቤቱ 14 ቀን የምርመራ ጊዜ ፈቅዷል።

@ESATTv1
@ESATTv1
አስቸኳይ ክፍት የስራ ማስታወቂያ
#CHOOICE AGENCY#
#08/05/2013#
⬇️⬇️⬇️⬇️⬇️⬇️⬇️⬇️⬇️⬇️
🔘የስራ መደብ:lab technician,Ho par time
#ት/ት ደረጃ:degree/diploma
#ልምድ:0
#ደሞዝ:4000-5000
🔘የስራ መደብ:ቢዝነስ ማኔጅምንት
#ት/ት ደረጃ:ዲግሪ
#ልምድ:0
#ደሞዝ ግራሚ
🔘የስራ መደብ:graphics designer
#ት/ት ደረጃ:በዘርፉ በቂ እውቀት ያላቸው
#ልምድ: 0
#ደሞዝ:በስምምነት
🔘የስራ መደብ:መምህርነት(chemistry, English,sport,biology)
#ት/ት ደረጃ:ዲግሪ በት/ቱ ዘርፍ
#ልምድ:0
#ደሞዝ:ምርጥ
🔘የስራ መደብ:ሹፌር 3ኛ መንጃ ፍቃድ
#ት/ት ደረጃ:10+
#ልምድ:0-3አመት
ደሞዝ:ገራሚ
🔘የስራ መደብ:any engineering degree and accountant, economics,psychologist,It,cheff, ሹፌር ህ1,auto,ደ1,ደ2 for NGO
#ት/ት ደረጃ:degree/diploma
#ልምድ:0 -1-2....
#ብዛት:250
#ደሞዝ:10,000 - 25,000
🔘የስራ መደብ:በany degree ለ አዲስ ፋብሪካ
#ልምድ:0........
#ፆታ:አይለይም
#ብዛት:399
#ደሞዝ:ምርጥ እና ሙሉ ወጪ ተችሎ
🔘የስራ መደብ:የልብስ ስፌት operator
#ት/ት ደረጃ:በሞያው በቂ እውቀት ያላት
#ልምድ:0-3 አመት
#ደሞዝ:ምርጥ
🔘የስራ መደብ:Hotel superior,house keeping
#ት/ት ደረጃ:በዘርፉ በቂ እውቀት ያለው
#ልምድ:0-2 አመት
#ደሞዝ:ገራሚ
🔘የስራ መደብ:Accountant &HR manager ኦሮምኛ እሚችሉ
#ት/ት ደረጃ:degree/diploma
#ልምድ:0-3አመት
#ደሞዝ:ገራሚ
🔘የስራ መደብ:F&B control እና አስተናጋጅ (የቀንም የማታም)
#ት/ት ደረጃ: በዘርፉ በቂ እውቀት ያለው
#ፆታ:ወ/ሴ
#ልምድ:ያላቸው ቢሆን ይመረጣል
#ደሞዝ:3500-5500
🔘የስራ መደብ:ሴልስ የcomputer ችሎታ ያላቸው
#ት/ት ደረጃ:10+
#ልምድ:0
#ደሞዝ:ደሞዝ +0.5-2% ኮሚሽን
🔘የስራ መደብ:ሹፌር ህ1 ወይም የድሮ 3ኛ መንጃ ፍቃድ እና ሞተረኛ
#ት/ት ደረጃ:10+
#ልምድ:2 አመት እና ከዛ በላይ
#ደሞዝ:በስምምነት
🔘የስራ መደብ:# HO,druggist
#የት/ደረጃ:ዲግሪ/ዲፕሎማ
#ፆታ: ወንድ/ሴት
#የስራ ልምድ:1-3አመት
#ደሞዝ:3500-4500
🔘የስራ መደብ:Lab technician, nurse par time
#ት/ት ደረጃ:ዲግሪ/ዲፕሎም
#ልምድ:0
#ደሞዝ: በቀን እና duty ያለው
🔘የስራ መደብ :Accountant
#ት/ት ደረጃ:ዲግሪ/ዲፕሎማ
#ልምድ:2-3አመት
#ደሞዝ:4500+
🔘የስራ መደብ :ሹፌር ደረቅ 1
#ፆታ:ወ
#ት/ት ደረጃ:10+
#ልምድ:1-3አመት
#ደሞዝ:ምርጥ
🔘የስራ መደብ:Marketing
#ፆታ:ሴ/ወ
#ት/ት ደረጃ:ዲግሪ
#ልምድ:0
#ደሞዝ:ምርጥ
🔘የስራ መደብ:office manager and also Acting H.R
#ት/ት ደረጃ:ዲግሪ በ management
#ልምድ:1-3አመት
#ደሞዝ:በስምምነት
🔘የስራ መደብ:Reception
#ት/ት ደረጃ :12+
#ልምድ:1 እና ከዛ በላይ
#ደሞዝ: በስምምነት
🔘የስራ መደብ:waiter
#ት/ት ደረጃ:10+
#ልምድ:0
#ደሞዝ:2000 እና ሰርቪስ ቻርጅ ያለው
🔘የስራ መደብ:clinical nurse,ፋርማሲስት
#ት/ት ደረጃ:degree diploma
#ልምድ:0-2አመት
#ደሞዝ:ምርጥ
🔘የስራ መደብ:Mechanical,electrical,Auto electrician,Auto mechanic
#ት/ት ደረጃ:degree/diploma
#ልምድ:0-3 አመት
#ደሞዝ:በስምምነት
🔘የስራ መደብ:graphics designer
#ት/ት ደረጃ:በዘርፉ በቂ እውቀት ያለው
#ልምድ:0-3አመት
🔘የስራ መደብ:ፀሀፊ
#ት/ት ደረጃ:በዘርፉ የተመረቀች
#ልምድ:ያላት ቢሆን ይመረጣል
#ደሞዝ:በስምምነት
🔘የስራ መደብ:ሜንቴናንስ
#የት/ደረጃ:በ Level /ዲግሪ/ዲፕሎማ
#ፆታ: ወንድ
#የስራ ልምድ:0-1ዓመት
#ደሞዝ:አሪፍ
🔘የስራ መደብ:ካሸሪ
#የት/ደረጃ: በማንኛውም Level /ዲግሪ/ዲፕሎም
#ፆታ: ሴት
#የስራ ልምድ:1-2ዓመት ላውንጅ ላይ ሰርታ እምታቅ
#ደሞዝ:በስምምነት
🔘የስራ መደብ:lab technician
#የት/ደረጃ:ዲግሪ/ዲፕሎማ
#ፆታ: ወንድ
#የስራ ልምድ:0 አመት ልምድ
#ደሞዝ:3000-4000
🔘የስራ መደብ:# IT ባለሞያ
#የት/ደረጃ:ዲግሪ/ዲፕሎም
#ፆታ: ሴት/ወንድ
#የስራ ልምድ: 0-1ዓመት ል
#ደሞዝ:በስምምነት
🔘የስራ መደብ:ሹፌር ደረቅ 1,የድሮ 3ኛ
#የት/ደረጃ:10ኛ+
#ፆታ: ወንድ
#የስራ ልምድ: 2 ዓመት+
🔘የስራ መደብ:phone operator,መረጃ ምዝገባ ክፍል
#የት/ደረጃ:ዲግሪ /ዲፕሎማ/#ፆታ:ሴ/ወ
#የስራ ልምድ: የሙያ ፈቃድ ያለው/ያላት
#የስራ ልምድ: 0 አመት
🔘የስራ መደብ::#ሴልስ
#የት/ደረጃ: 10ኛ
#ፆታ: ሴት/ወንድ
#የስራ ልምድ: 0 ዓመት
#ደሞዝ:ማራኪ
🔘የስራ መደብ:መምህር በተለያዩ
#የት/ደረጃ: any degree
#ፆታ: ሴ/ወ
#የስራ ልምድ: 0 ዓመት
#ደሞዝ:4000+
🔘የስራ መደብ:Reception par time
#የት/ደረጃ: ዲፕሎማ/ዲግሪ
#ፆታ: ሴት
#የስራ ልምድ: 1 ዓመት+
#ደሞዝ:በስምምነት
🔘የስራው መደብ:main cheff,ባር ቴንደር እና house keeping
#ት/ት ደረጃ:10+
#ልምድ:ልምድ ያላቸው ቢሆን
⬆️⬆️⬆️⬆️⬆️⬆️⬆️⬆️⬆️
##አድአድራሻ 22 ማዞርያ clinic አጠገብ New Day ህንፃ ላይ 2ኛ ፎቅ ላይ ለበለጠ መረጃ
☎️ስልክ:📱09 7410 27 37
📱09 7410 00 61
በስራ ሰአት ስለሚድውሉልን እናመሰግናለን::
🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏
በጅግጅጋ በ27.6 ሚልየን የተገነባ ትምህርት ቤት ተመረቀ!

ጥር 07፣ 2013 ዓ.ም

ቀዳማዊት እመቤት ወ/ሮ ዝናሽ ታያቸው እና የሶማሊ ክልል ምክትል ርዕሰ መሰተዳድር ሙሰጠፋ ሙሁመድ በተገኙብት የቀዳማዊት እመቤት ጽ/ቤት ያስገነባው የጅግጅጋ ኢለይስ 1 እና 2 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ዛሬ ተመረቀ፡፡

ትምህርት ቤቱ በፋፋን ዞን በ27።6 ሚሊዮን ብር ነውየተገነባዉ። በዉስጡም የአስተዳደር ህንጻ፣ የመማሪያ ክፍሎች፣ ላብራቶሪ፣ የቤተ መጽሀፍት ፣ የስብሰባ አዳራሽ እና የመጸዳጃ ህንጻዎችን ያካተተ ነው።

ዛሬ የተመረቀውን ጨምሮ ጽሕፈት ቤቱ እስካሁን ዘጠኝ ትምህርት ቤቶችን ያስገነባ ሲሆን በቅርብ ቀን በሁሉም ክልሎች ተጨማሪ ገንብቶ እንደሚያስመርቅ ታውቋል፡፡

ትምህርት ቤቱ አገልግሎት መስጠት ሲጀምር በአንድ ፈረቃ 1 ሺህ 80 ተማሪዎችን የመቀበል አቅም አለዉ፡፡

@ESATTv1
@ESATTv1
2021/01/15 20:19:53
Load New Feed
Back to Top