TG Telegram Group Link
Channel: መሰልጠን ወይስ መሠይጠን ( ምስል እና ፍልስፍና ቢጤ)
Back to Bottom
ውድ ኢትዮጵያውያን
እንኳን ለ125ኛው የአድዋ ድል በዓል በሰላም ና በጤና ጠብቆ አደረሳችሁ አደረሰን!!!

በዓሉን ጦርነቱን በማሰብ ብቻ ሳይሆን
የምናከብርበትን ምክንያትና ምንነት ልናውቅ ግድ ነው ።

እኛ ኢትዮጵያውያን የ7512 ዓመት ታሪክ አለ ምንል ብቻ አንሁን ታሪክን አውቆ ማንነችን በጥልቀት መርምሮ ለቀጣይ ትውልድ ያለምንም ግድፈት ልናስረክብና እኛም በዘመናችን ላይ ቆመን ታሪክ ለመስራት ከጥንታዊ ኢትዮጵያውያን አደራን ተቀብለናል።

አደራ በዪዎች እንዳንሆን ጊዜያችንን፣ እውቀታችን፣ ጉልበታችን፣ ሁሉ ነገሮቻችንን መስዋዕት አርግተን ልንሰራ ይገባል።

ምክንያቱም ደም የተከፈለልን ኩሩ እና አንገታችንን ቀና አድርገን በልበ ሙሉነት ምንጓዝ ድንቅ ሰዎች ብንኖር እኛ ኢትዮጵያውያን ብቻ ና ብቻ ነን!!

ስለዚህ ይህን ታሳቢ በማድረግ በዓሉ እናክብር።

መልካም የድል በዓል ውድ ኢትዮጵያውያን!!!

💚💛❤️
እንደምን አደራችሁ ውድ ኢትዮጵያውያን?
እግዚአብሔር ይመስገን እርሱ ወዶና ፈቅዶ ለዚች ቀን አድርሶናልና።

ሐምሌ ፳፬ ፳፻፲፪ የዛሬ አመት እ ምን ትዝ አላችሁ... ይህ ውዱ ጦማር የተከፈተበት ቀን ነበር። አረሳችሁትማ😉

እነሆ እንደ እግዚአብሔር መልካም ፍቃድ ለ፩ኛ አመቱ ተገኝተናልና እንኳን አደረሳችሁ አደረሰን!

ከዚህ በፊት ለተፈጠሩት የልጥፍ መቀዛቀዝ ከወዲሁ ይቅርታ እየጠየቅን፣እስከሁን በትዕግስት ለጠበቃችሁን ውድ አባላቶቻችን እግዚአብሔር ያክብርልን እያልን በአብሮነታችሁ የተሰማንን ጥልቅ ደስታ ለመግለፅ እንወዳለን።

እናም ዛሬ የውዱ ጦማራችን ልደት እንደ መሆኑ መጠን አንዴ ከመቀመጫችን ብድግ በማለት እንኳን ተወለድክ...ብቻ ፩ኛ አመቱን በማስመልከት የሆነ ነገር እንለዋለን😁
ይህ የሆነው ደሞ በአምላከ እግዚአብሔር ፍቃድ በ፩ ሰው ምክንያት ነው።

ይህም ሰው @yotor_ab (ዣ-ኤል) ሲሆን ይህን የመሰለ ጦማር ስለከፈትክልን ደስታችን ላቅ ያለ ስለሆነ እግዚአብሔር ያክብርልን!

ለማንኛውም ውድ አባሎቻችን ሆይ፦በአዲስ መልኩ ለመጀመር ተነስተናልና ምን ይጨመር ፣እንዲሁም ምን አይነት ነገሮች ይካተቱበት ሀሳብ አስተያየታችሁን
@yotor_ab እንዲሁም
@Eden_Heaven16 ላይ አድርሱን

ሁሉን ያደረገው እርሱ እግዚአብሔር ፣
አትለይምና እናቱ እናታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ጋር የተመሰገነ ይሁን።
አሜን፫
ይህችን ደብረ ሰላምን በመጀመሪያ አቤቶ እያሱ/አልጋ ወራሽ ልጅ እያሱ(ክፍለ ያዕቆብ)
በሐምሌ፳፮ ቀን:፲፱፻፫ ዓ.ም መሰረታት።

ሐምሌ፳፯ የልጅ እያሱ (ክፍለ ያዕቆብ)
ደብር የሆነው የቀጨኔ መድኃኔዓለም ቅዳሴ ቤቱ መታሰቢያ መሆኑ አንዳይዘነጋ!

ቀጨኔ ደብረሰላም መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን የ116 ዓመታት እድሜ ያለው ጥንታዊ የኢያሱ ደብረ።

''በወርቅ ወበዕንቁ ሥርጉት ደብረ ሰላም ወ ነገሥት ይትቀንዩ ለኪ''ሣረራ ኢያሱ ቀዲሙ ለዛቲ ቤት ፤ወፈጸመታ ንግሥት ዘውዲቱ።(ይህችን ደብረ ሰላምን በመጀመሪያ ልጅ እያሱ በሐምሌ ፳፮ቀን ፲፱፻፫ ዓም መሠረታት ነግሥት ዘውዲቱ አሁን ያለውን ሕንፃ ቤተክርስቲያን ጥቅምት፳፯ ቀን ፲፱፻፲፫ዓም አስፈፀመች።)

የሰላም አምላክ የፍቅር ጌታ ያደረባት ደብረ ሰላም ካሏት ከብዙ በጥቂቱ፦የብዙ ሊቀውንት መፍለቂያ፣የላይ ቤት አቋቋም፣የተክሌ ዝማሜና የሸዋና የራሱ የደብሩ ቀለም እንደ ወንዝ የሚፈስባት፣ታሪካዊ ቅርሶችን የያዘ ቤተ መዘክር ናቤተ መጽሀፍት የሚገኙበት፣ደብሩን አገልግለው ወደ ሌላ ደብር የሚዘዋወሩ ካህናት ሁሌም በዓይናቸው የደብሩ ፍቅር ውልብ የሚልባቸው ፣ምዕመናኑ በአጸዱና በግርማ ሞገሱ ሁሌም የሚደነቁበት ፣ስዕለት ሰሚ ታቦታት ያሉበት፣ወደ ፬ የሚጠጉ ፈዋሽ ጠበሎች የሚገኙበት፣ፅእዶች ሳይቀሩ በ፸፪ አርድዕት ቅዱሳን አምሳያ የተተከሉበት፣በቀደመው ዘመን መኀዛ ቅዳሴየተሰኘወሸ የአባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ ቅዳሴ በወርኃጽጌ የሚቀደስበት፣፫ጳጳሳትን ያፈራ ደብር ነው።

ለደብረ ሰላም ይደልዋ ስብሐት፤እስመ በውስቴታ ኀደረ መድኃኔዓለም (በደብረ ሰላም በውስጧ መድኃኔዓለም ስላደረ ምስጋና ይገባታል።

ሁላችሁም እንኳን አደረሳችሁ!
በተለይ ደሞ የዚህ አካል የሆናችሁ ወ አገልጋዮች እጅጉን ዕደለኞች ናችሁ
እግዚአብሔር አምላክ በብቱ ጠብቆ ያፅናችሁ።
ሰላም እንዴ ናችሁ ላለፉት 6 ወራት ጠፍቼ ነበር በጣም ይቅርታ እየጠየኩ ከዚ በኋላ ግን ላለመጥፋት ቃል እየገባሁ እንድሰራላችሁ ስለምትፈልጉት ነገር ፣ ጥያቄ እና አስተያታችሁን አድርሱን @yotor_ab
የመጀመርያ መመለሻዬን ስለ ቤቲንግ ፅሁፍ እያዘጋጀሁላችሁ ነው ጠብቁኝ 💚💛❤️
መሰልጠን ወይስ መሠይጠን ( ምስል እና ፍልስፍና ቢጤ) pinned «ሰላም እንዴ ናችሁ ላለፉት 6 ወራት ጠፍቼ ነበር በጣም ይቅርታ እየጠየኩ ከዚ በኋላ ግን ላለመጥፋት ቃል እየገባሁ እንድሰራላችሁ ስለምትፈልጉት ነገር ፣ ጥያቄ እና አስተያታችሁን አድርሱን @yotor_ab የመጀመርያ መመለሻዬን ስለ ቤቲንግ ፅሁፍ እያዘጋጀሁላችሁ ነው ጠብቁኝ 💚💛❤️»
አንድሮሜዳ 🇪🇹🇪🇹
ስለ ዩኒቨርሳችን መረጃ ያገኛሉ
በተጨማራም የምትፋልጉትን ጥያቄ comment
ላይ ፃፉልኝ የyoutube ቻናላችንን በመቀላቀል በቂ እውቀት ያግኙ 👇👇👇
YouTube channel https://youtube.com/channel/UCu7s3bTjiltwrnHvAZ6UK5w

Creator @tDoki
https://hottg.com/universeone123
ነገ ማታ ስለ ቤቲንግ ያዘጋጀሁላችሁን እለጥፍላችኋለሁ ጠብቁኝ
HTML Embed Code:
2024/04/30 00:56:31
Back to Top