TG Telegram Group Link
Channel: ድረ መፅሄት ስፖርት
Back to Bottom
ትውልደ ኢትዮጵያዊው ተጨዋች በጀርመን ሊግ ግብ አስቆጠረ!

በጀርመን ሁለተኛ ሊግ ለካይሰርላውተር የሚጫወተው ትውልደ ኢትዮጵያዊው ተጨዋች ኬኒ ሮዴንዶ ዛሬ ክለቡ ከ ፋርዝ ጋር ባደረገው ጨዋታ ግብ ማስቆጠር ችሏል።

@Dresport @Zamanuel_Mesfin
አሊ ሂላል የወዳጅነት ጨዋታ ሊያደርግ ነው!!

ቅዱስ ጊዮርጊስን በመጀመሪያ ዙር የአፍሪካ ቻምፒየንስ ሊግ ማጣሪያ ጨዋታ የሚገጥመው የሱዳኑ ሀያል ክለብ አል ሂላል ኦሙድርማን በአህጉሩ ውስጥ ካሉ 3 ሀያል ቡድኖች ጋር የወዳጅነት ጨዋታ ሊያደርግ ነው።

አል ሂላል የጋናውን አሳንቴ ኮንቶኮን ፣ የታንዛኒያውን ሀያል ክለብ ሲምባንን እና ዩጋንዳ ውስጥ የሚገኘውን ቫይፐርስን የሚገጥም ይሆናል።

@Dresport @Zamanuel_Mesfin
ወላይታ ዲቻ ጋናዊውን አጥቂ የግሉ አድረገ!

የወላይታ ዲቻ ስፖርት ክለብ በአጥቂ ስፍራ ያለበትን ችግር ለመቅረፍ ጋናዊውን አጥቂ ሚካኤል ሳርፖንግን በአንድ ዓመት ውል ወደ ክለቡ ቀላቅለዋል።

ሚካኤል ሳርፖንግ:

የሚጫወትበት ቦታ- አጥቂ
ከዚህ በፊት የተጫወተባቸው ክለቦች
1. ሊበርት ፕሮፌሽናልስ 2015
2. ድሪም ማዳን 2016-2018
3. ራያን ኒያንዛ 2018-2020
4. ያንጋ አፍሪካ 2020-2021
5. አልናሂዳ 2021-2022
6. ኤኤስ ክጋሊ 2022

@Dresport @Zamanuel_Mesfin
ዑመድ ኡክሪ በኦማን ሊግ ግብ እስቆጠረ!

በ2014 የቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሜር ሊግ በሀዲያ ሆሳዕና ቡድን ውስጥ ያልተሳካ ጊዜ አሳልፎ በያዝነው የውድድር ዓመት ኦማን ሊግ ውስጥ ለሚገኘው አል ሱዋቂ የፈረመው ኦመድ ዑክሪ ዛሬ ቡድኑ ከአል ኢትሀድ ጋር ባደረገው ጨዋታ ላይ የመጀመሪያ ግቡን ማስቆጠር ችሏል።

@Dresport @Zamanuel_Mesfin
አቡበከር ናስር ዛሬም ግብ አስቆጠረ😍

ማማሎዲ ሰንዳውንስ ከሱፐር ስፖርት እያደረጉት በሚገኘው ጨዋታ ላይ አቡበከር ናስር ተቀይሮ ወደ ሜዳ በመግባት ግብ ማስቆጠር ችሏል።
"ኤል ጉና" የሽመልስ በቀለ ቡድን ከግብፅ ሊግ ወረደ!!

በ2021/22 የውድድር ዓመት ደካማ እንቅስቃሴ ሲያደርግ የነበረው ኤል ጉና ከግብፅ ዋናው ሊግ ወደ ሁለተኛው ዲቪዚዮን ወርዷል። ኤል ጉና የውድድር ዓመቱ ሊጠናቀቅ ሲል የግብፁን ሀያል ክለብ ፔራሚድስን እና ፋቸርን ማሸነፍ ቢችልም ጋዛ ኤል ማሀላ ከ አል ኢትሀድ ጋር ያደረጉት ጨዋታ በአቻ ውጤት በመጠናቀቁ ኤል ጉና ከግብፅ ሊግ ሊወርድ ችሏል።

ሽመልስ በቀለ በውድድር ዓመቱ በቡድኑ ውስጥ ተፅዕኖ ማሳደር ሳይችል ቀርቷል።

@Dresport @Nati_pol
በእስራኤል ሊግ የሚጫወተው ትወልደ ኢትዮጵያዊው ተጨዋች አስደናቂ ግብ አስቆጠረ!

በእስራኤል ሊግ ለአሽዶድ ክለብ የሚጫወተው ትውልደ ኢትዮጵያዊው ተጨዋች ያቆብ በሪሁን ዛሬ ክለቡ ከ ቢር ሼቫ ጋር ባደረጉት ጨዋታ ላይ ተቀይሮ ወደ ሜዳ በመግባት በ85ተኛው ደቂቃ ላይ አስደናቂ ግብ በማስቆጠር ቡድኑ ሶስት ነጥብ ይዞ ከሜዳ እንዲወጣ ማድረግ ችሏል።

@Dresport @Zamanuel_Mesfin
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
በእስራኤል ሊግ ለአሽዶድ የሚጫወተው ትውልደ ኢትዮጵያዊው ተጨዋች ያቆብ በሪሁን ዛሬ ለቡድኑ ባለቀ ሰዓት ያስቆጠረው አስገራሚ ግብ::🇪🇹🕺💫

@Dresport @Zamanuel_Mesfin
የ2015 ዓ.ም ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሜር ሊግ መስከረም 20 ይጀምራል!

የቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሜር ሊግ መስከረም 20/2015 ዓ.ም በባህር ዳር አለም አቀፍ ስታዲየም የሚጀምር ሲሆን ውድድሩ ለአምስት ሳምንታት በባህር ዳር ቆይታ ካደረገ በኋላ በድሬደዋ ስታዲየም ከ6ኛ እሰክ 10ኛ ሳምንት እንዲሁም በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም ከ11ኛ እስከ 15ኛ ሳምንት ይካሄዳል።

@Dresport @Zamanuel_Mesfin
ኢትዮ ኤሌክትሪክ ተሸነፈ!

ዛሬ በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲ ስታዲየም በኢትዮ ኤሌክትሪክ እና በሱዳኑ አል መሪክ ክለብ መካከል በተደረገ የወዳጅነት ጨዋታ ኢትዮ ኤሌክትሪክ 1 ለ0 በሆነ ውጤት ተሸንፏል።

@Dresport @Zamanuel_Mesfin
አቡኪ ዛሬም ግብ አስቆጠረ

አቡበከር ናስር ዛሬ ማማሎዲ ሰንዳውንስ ከሱፐር ስፖርት ዩናይትድ ጋር ባደረጉት ጨዋታ ላይ ግብ አስቆጥሯል። በዛሬው ጨዋታ ማማሎዲ ሰንዳውንስ 2 ለ1 በሆነ ውጤት ተሸንፏል።

@Dresport @Zamanuel_Mesfin
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
አቡበከር ናስር ዛሬ ለማማሎዲ ሰንዳውንስ ባለቀ ደቂቃ ያስቆጠረው የግንባር ኳስ።🇪🇹💫🕺

@Dresport @Zamanuel_Mesfin
የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ዛሬ ወሳኝ ጨዋታ ያደርጋል!

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ዛሬ 10:00 ቻን ውድድር ላይ
ለመሳተፍ የሩዋንዳ አቻውን ይገጥማል።በመጀመሪያው ዙር ግንኙነታቸው ጨዋታው 0 ለ0 የተጠናቀቀ ሲሆን የዛሬውን ጨዋታ ያሸነፈው ቡድን ውድድሩን በቀጥታ ይቀላቀላል።

ድል ለብሄራዊ ቡድናችን🇪🇹

@Dresport @Zamanuel_Mesfin
የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ለቻን የአፍሪካ ዋንጫን አለፈ!

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ዛሬ የሩዋንዳ ብሄራዊ ቡድንን በዳዋ ሆጤሳ ብቸኛ ግብ 1 ለ0 በማሸነፍ አልጄሪያ ለሚደረገው የቻን ውድድር ማለፍ ችሏል።

እንኳን ደስ አላችሁ🇪🇹

@Dresport @Zamanuel_Mesfin
የኢትዮጵያ ፕሬሜር ሊግ ቡድኖች አደጋ ላይ ወደቁ!

ካፍ አዲስ ባወጣው የክለቦች ላይሰንሲንግ መቆጣጠሪያ ህግ የተነሳ በርካታ የአፍሪካ ቡድኖች ወደታችኛው የሊግ እርከን እየወረዱ ይገኛሉ። ለምሳሌ የዩጋንዳው ክለብ ኬይቱሜ በቡድኑ ውስጥ 18 ተጨዋቾች መመዝገብ ባለመቻሉ ከዩጋንዳ ዋናው ሊግ ወደ ሶስተኛው የሊግ እርከን እንዲወርድ ተደርጓል። በተጨማሪም አራት (4) የቦትስዋና ቡድኖች በዚህ ወር መጨረሻ ከሀገሪቱ ዋናው ሊግ ይወርዳሉ ተብሎ ይጠበቃል።

ወደ ሀገራችን ጉዳይ ስንመጣ ቅዱስ ጊዮርጊስ እና ፋሲል ከነማ የ2022/23 የካፍ ክለብ ላይሰንስ ያገኙ ብቸኛ የሀገራችን ቡድኖች ናቸው።

የካፍ ላይሰንስ ለማግኘት ከሀገራችን ቡድኖች ምን ይጠበቃል?

-የተረጋገጠ የታዳጊ ተጨዋቾች ማበልፀጊያ ዕቅድ

-ከ13፣ከ15 እና ከ18 በታች ቡድኖችን መያዝ

-ስታዲየም ሊኖራቸው ይገባል ከሌላቸው የሚጠቀሙበትን ስታዲየም ማሳወቅ አለባቸው

-ልምምድ የሚሰሩበትን ስታዲየም ማሳወቅ አለባቸው (ለሚሰሩበት ቦታ የተፈራረሙትን የሊዝ ስምምንት ማቅረብ አለባቸው)

-የሚገኙበት ፅህፈት ቤት (ቢሮ) ያስፈልጋቸዋል

- አሰልጣኝ ፣ የቡድን መሪ ፣ ምክትል አሰልጣኝ ፣ የበረኛ አሰልጣኝ ፣ የታዳጊ ቡድን አሰልጣኞች ያስፈልጋቸዋል

-የፋይናንስ እና የጥበቃ ሀላፊ ያስፈልጋቸዋል

-የፊፋን ፣ ካፍ እና ካስ መመሪያ መጠበቅ አለባቸው

-ቡድኖቹ ባለቤት ያስፈልጋቸዋል( ጥምር ባለቤትንት የተከላከለ ነው)

-ቡድኖቹ ኦዲት የተደረገ የሂሳብ ወረቀት ማቅረብ አለባቸው

-በፋይናንሳቸው ጥሩ ቁመና ላይ መገኘት አለባቸው።

ካፍ ክለቦች የላይሰንስ ምዝገባ ቀን የሚጠናቀቀው ጁን 30 ሲሆን የሀገራችን ቡድኖች ጊዜው እስኪደርስ ድረስ የሚጠብቃብችሁን ካልሰራችሁ ሊግ መፍረሱ አይቀሬ ነው።

@Dresport @Zamanuel_Mesfin
vdrftghjklø
Click Me Load More⚽️
ዛሬ ምሽት 5:30 🕠

ኢትዮጵያ ከ ጊኒ

በ ሞሮኮ የሚደረግ ተጠባቂ ጨዋታ

@Nati_QQQ

@Dresport
Live stream finished (19 seconds)
HTML Embed Code:
2024/05/18 23:30:54
Back to Top