TG Telegram Group Link
Channel: Commercial Bank of Ethiopia - Official
Back to Bottom
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለኢንዱስትሪ ዘርፉ ከፍተኛ የፋይናንስ ድጋፍ እያደረገ መሆኑ ተገለፀ።
**
ይህ የተገለፀው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሬዚዳንት አቶ አቤ ሳኖ በኢትዮጵያ ታምርት ኤክስፖ "የግል ኢንቨስትመንት እና ማኑፋክቸሪንግ አስቻይ ሁኔታዎች" በሚል ርዕስ እየተካሄደ በሚገኘው የፖናል ውይይት ላይ የኢትዮጵያ የፋይናንስ ተቋማት ለአምራች ኢንዱስትሪው የሚያበረክቱትን አስተዋፅኦ አስመልክተው በተናገሩበት ወቅት ነው፡፡

አቶ አቤ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፍ ዕድገት ከፍተኛ ድጋፍ እያደረገ እንደሆነ ገልፀው፣ ከ550 ቢልዮን ብር በላይ የብድር አቅርቦት ማድረጉን ተናግረዋል፡፡

ባንኩ በሚያደርገው የፋይናንስ አቅርቦት ከኃይል ምንጭ ስራዎች ቀጥሎ አምራች ኢንዱስትሪው ተጠቃሚ መሆኑን አቶ አቤ ጨምረው ገልፀዋል።

በቀጣይነትም የአምራች ኢንዱስትሪውን ለማገዝ ትኩረት ተሰጥቶት እየተሠራ መሆኑን ያስረዱት አቶ አቤ፣ ባንኩ ከብድር በተጨማሪ የውጭ ምንዛሬ በማቅረብም ዘርፉን በግንባር ቀደምትነት እየደገፈ መሆኑን ተናግረዋል።

በኢንዱስትሪ ሚኒስቴር አዘጋጅነት ከግንቦት 1 እስከ 5 ቀን 2016 ዓ.ም በሚሊኒየም አዳራሽ የሚካሄደው የኢትዮጵያ ታምርት ኤክስፖ 210 አምራች ኩባንያዎች ምርቶቻቸውን ያቀረቡበት ሲሆን፣ የፓናል ውይይቶች የኤክስፖው አካል ሆነው በመካሄድ ላይ ናቸው፡፡
የባንካችን ፕሬዚደንት አቶ አቤ ሳኖ ለ “ጽዱ ጎዳና-ኑሮ በጤና” ለሶስተኛ ጊዜ ዛሬ የዲጂታል ቴሌቶኑን ተቀላቅለዋል። #CBE #Ethiopia #abie_sano #media #PMO
ልዩ የዲጂታል ቴሌቶን ቀን ለ “ጽዱ ጎዳና-ኑሮ በጤና”
******************************************
ዛሬ ለ “ጽዱ ኢትዮጵያ” በአንድ ጀንበር 50 ሚሊዮን ብር የሚሰበሰብበት ልዩ ቀን ነው። የሕዝብ መፀዳጃ ቤቶችን በመገንባት ክብርን ጠብቆ የመፀዳዳት ባህልን ለማዳበር “ጽዱ ጎዳና-ኑሮ በጤና” በሚል የተጀመረው መርሃ ግብር ጽዱ ኢትዮጵያን ለመገንባት ለሚደረገው ጥረት ሁሉም የድርሻውን በማበርከት የተሻለች ሀገርን ለመገንባት በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተከፈተው ሒሳብ ቁጥር 1000623230248 በሁሉም የገንዘብ መላኪያ አማራጮች በመጠቀም አስተዋጽዎ በማድረግ የዜግነት ግዴታችንን እንወጣ።
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለ#ጽዱኢትዮጵያ ንቅናቄ በእያንዳንዷ 3 ብር መዋጮ ላይ 1 ብር እንደሚያዋጣ አስታወቀ።
****
በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ይፋ የተደረገው የ“ጽዱ ጎዳና - ኑሮ በጤና” ንቅናቄ በርካቶች በመቀላቀል ድጋፍ እያደረጉ ይገኛሉ።

#ጽዱኢትዮጵያ 50 ሚሊየን ብር በአንድ ጀምበር ለማሰባሰብ ሁሉም ዜጋ የሚሳተፍበት የዲጂታል ቴሌቶን በመካሄድ ላይ ይገኛል።

በዚህም የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለ#ጽዱኢትዮጵያ ንቅናቄ በእያንዳንዷ 3 ብር መዋጮ ላይ 1 ብር እንደሚያዋጣ የባንኩ ፕሬዝዳንት አቶ አቤ ሳኖ አስታውቀዋል፡፡

ባንኩ ዛሬ ለሚካሄደው የዲጂታል ቴሌቶን ሁሉንም የዲጂታል ግብይት መፈጸሚያ አማራጮች በአስተማማኝ ሁኔታ አገልግሎት እንዲሰጡ የበኩሉን አስተዋፅኦ እንዲደሚያደርግ አቶ አቤ ሳኖ በሰጡት ማብራሪያ ገልፀዋል፡፡

አቶ አቤ ለ#ጽዱኢትዮጵያ ንቅናቄ ከዚህ በፊት ካደረጓቸው ድጋፎች በተጨማሪ ለሶስተኛ ጊዜ የ50 ሺህ ብር ድጋፍ አድርገዋል፡፡
በዛሬው ዕለት ብቻ ለ “ጽዱ ጎዳና-ኑሮ በጤና” ልዩ የዲጂታል ቴሌቶን የተሰበሰበው ገንዘብ ከእቅዱ በላይ ሆነ
**********************************
#ጽዱኢትዮጵያ 50 ሚሊየን ብር በአንድ ጀምበር ለማሰባሰብ ታቅዶ ዛሬ የተጀመረው የገንዘብ ማሰባሰብ መርሃ ግብር እስከ አሁን 12፡30 ሰዓት ድረስ ከ 67.5 ሚሊዮን በላይ የተሰበሰበ ሲሆን ለዚህም በእያንዳንዷ 3 ብር መዋጮ ላይ 1 ብር እንደሚያዋጣ ባንካችን ቃል በገባው መሰረት ከ 23 ሚሊዮን ብር በላይ በመጨመር ከ 90 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ እንደሆነ ተረጋግጧል።
GetRooms
ከየትኛውም ቦታ ኢትዮጵያ ውስጥ የሆቴል ክፍል መያዝ እና ክፍያ መፈፀም ይችላሉ!
**********
በGetRooms ሆቴል ያስመዝግቡ፤
ክፍያዎን በሲቢኢ ብር፣ በሲቢኢ ሞባይል ባንኪንግ ወይም አቅራቢያዎ በሚገኝ ቅርንጫፍ ይፈፅሙ፡፡

ለዓለም አቀፍ ክፍያ ቪዛ፣ ማስተር ካርድ ወይም ዩኒየንፔይን መጠቀም ይችላሉ፡፡

አገልግሎቱን፡
www.getroomsonline.com ድረ-ገፅ፣
በ GetRooms የሞባይል መተግበሪያ፣ አሊያም
ወደ 9801 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡
*********
መተግበሪያውን ከ Play Store ወይም APP Store ያውርዱ!

Android: https://play.google.com/store/apps/details?id=com.getrooms

IOS: https://apps.apple.com/ke/app/getrooms/id1596445830

#CBE #GetRooms #CBEBirr #mobilebanking #VISA #MasterCard #UnionPay
ቆይታ ከአርቲስት ጥላሁን ጉግሳ ጋር
***********
አንጋፋው እና ታዋቂው አርቲስት ጥላሁን ጉግሳ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የ2016 ዓ.ም የትንሣኤ በዓል ልዩ ዝግጅት ላይ እንግዳ ሆኖ ቀርቦ ነበር፡፡

አርቲስት ጥላሁን የቁጠባን አስፈላጊነት ያጎላባቸው የጥበብ ሥራዎች አሉት፡፡ በዚህ እና በሌሎች ጉዳዮች ዙሪያ ያደረገውን አዝናኝ እና አስተማሪ ቆይታ ጋብዘናል፡፡
https://youtu.be/SSdvd8mY6vI
እንዴት የሞባይል ባንኪንግ ‘QR’ አገልግሎት ተጠቅመው ገንዘብ መቀበል/ክፍያ መፈፀም ይችላሉ?
====

1. ገንዘብ ላኪውና ተቀባዩ አንድ ላይ የማይገኙ ሲሆን

• ገንዘብ ተቀባዩ በሞባይል ባንኪንግ መተግበሪያው ላይ የሚገኘውን የ ‘QR’ ኮድ ምልክት ይጫኑ፤
• ‘ገንዘብ ለመቀበል’ ‘Receive Money’ የሚለውን ይምረጡ፤
• ‘የገንዘብ መጠን እና ምክንያት’ ‘Amount and Reason’ የሚለውን ይምረጡ፤
• የገንዘብ መጠን እና ምክንያቱን አስገብተው ‘ቀጥል’ ‘Continue’ የሚለውን ይጫኑ
• ‘ያጋሩ’ ‘Share’ የሚለውን ይጫኑ፣
• ‘በማስፈንጠሪያ መልክ ያጋሩ’ ‘Share as a link’ የሚለውን ተጭነው ‘እሺ’ ‘Ok’ የሚለውን ይምረጡ፣
• በSMS፣ በቴሌግራም እና በሌሎችም መንገዶች ተጠቅመው ማስፈንጠሪያውን ለገንዘብ ላኪው ይላኩ፣
• ገንዘብ ላኪው በመልእክት የደረሰውን ማስፈንጠሪያ (Link) በመክፈት የገንዘብ መጠን እና ምክንያት አረጋግጦ ገንዘብ ማስተላለፍ ይችላል፡፡

2. ገንዘብ ላኪውና ተቀባዩ በተመሳሳይ ቦታ የሚገኙ ከሆነ

• ገንዘብ ተቀባዩ በሞባይል ባንኪንግ መተግበሪያው ላይ የሚገኘውን የ ‘QR’ ኮድ ምልክት ይጫኑ፤
• ‘ገንዘብ ለመቀበል’ ‘Receive Money’ የሚለውን ይምረጡ፤
• የሚቀበሉትን ገንዘብ መጠን እና ምክንያቱን አስገብተው ‘ቀጥል’ ‘Continue’ የሚለውን ይጫኑ፤
• የሚመጣሎትን የQR ኮድ ወይም ምስል አዘጋጅተው ይጠብቁ፤
• ገንዘብ ላኪው በሞባይል ባንኪንግ መተግበሪያው ላይ የሚገኘውን የ ‘QR’ ኮድ ምልክት ይጫኑ፤
• ‘ስካን ኪው አር’ ‘Scan QR’ የሚለውን ይምረጡ፤
• ገንዘብ የሚልኩልት ሰው ስልክ ላይ ያለውን QR ኮድ ስካን ያድርጉ፤
• የሚላከውን የገንዘብ መጠን እና ምክንያት በማረጋገጥ ገንዘብ በቀላሉ መላክ ይቻላል፡፡
ይቆጥቡ፤ ይጓዙ!
ሲቢኢ ጉዞ የቁጠባ ሂሳብ
==============
ደንበኞች በሀገር ውስጥም ሆነ በውጭ ሀገራት ለሚያደርጉት ጉዞ ወጪ መሸፈኛ ገንዘብ አስቀድመው መቆጠብ እንዲችሉ የተዘጋጀ የቁጠባ ሂሳብ ነው፡፡

ሲቢኢ ጉዞ የቁጠባ ሂሳብ ከብር 1,000 ጀምሮ ይከፈታል፡፡

የቁጠባ ሂሳቡ የተለያዩ ጥቅሞች ያስገኛል፡፡

• ቆጣቢዎች በሀገር ወስጥ ጉዟቸው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክን ዲጂታል የክፍያ አማራጮች ተጠቅመው ለአየር ትኬት፣ ለቱሪስት መዳረሻዎች መግቢያ፣ ለሆቴል አገልግሎት እና ለመሳሰሉት ክፍያ በሚፈፅሙበት ወቅት ተመላሽ ያገኛሉ፤
• ዳያስፖራ ወይም የውጭ ሀገር ዜጎች የሲቢኢ ቱሪስት ካርድን ሲጠቀሙ እስከ 7 በመቶ የሚደርስ ተመላሽ ያገኛሉ ፤
• ለሀይማኖታዊ ጉዳይ ወደ ውጭ ሀገራት የሚጓዙ ደንበኞች ከአየር ትኬት ክፍያቸው እስከ 3 በመቶ የሚደርስ ተመላሽ ያገኛሉ፤
• ሌሎች ተጨማሪ ጥቅሞችንም ያስገኛል፡፡

ሂሳቡን በአቅራቢያዎ በሚገኝ ቅርንጫፍ ይክፈቱ፤ ለበለጠ መረጃ ወደ 951 ይደውሉ!
በዓቢይ ቅርንጫፍ ይገልገሉ!
********
በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አዲሱ ዋና መሥሪያ ቤት ህንፃ ሥር የሚገኘው ዓቢይ ቅርንጫፍ

እጅግ ዘመናዊ፣ ቀልጣፋና ምቹ አገልግሎት ለመስጠት በልዩነት የተደራጀ ነው፡፡

ሁሉም የባንካችን ደንበኛ የአገልግሎቱ ተጠቃሚ መሆን ይችላል!

#CBE #main #branch

https://youtu.be/DOJUFfj24oI
ይመልሱ፤ ይሸለሙ!
*************

ዛሬ ግንቦት 6 ቀን 2016 ዓ.ም ከምሽቱ 2፡30

• በፌስቡክ፦ https://www.facebook.com/combanketh
• በቴሌግራም ፦ https://hottg.com/combankethofficial
• በኦሮምኛ የፌስቡክ ገፅ፡- https://www.facebook.com/BaankiiDaldalaItiyoophiyaa
• በትግርኛ የፌስቡክ ገፅ:- https://www.facebook.com/profile.php?id=100063784606106
• በቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@combankethiopia

የጥያቄና መልስ ውድድር ይኖረናል፡፡ ትክክለኛ ገፃችንን በመቀላቀል ይሳተፉ፤ ይሸለሙ!

ማሳሰቢያ፡
*********
• የተስተካከሉ መልሶች ተቀባይነት የላቸውም፤
• ቀድመው የመለሱ አምስት ተሳታፊዎች በደረጃቸው ይሸለማሉ፤
• አንድ ተሳታፊ ከሁለት ጊዜ በላይ አይሸለምም፤
• ሽልማት የሚሰጠው በሲቢኢ ብር ሰለሆነ ደንበኛ ካልሆኑ በአቅራቢያዎ ወደሚገኝ የባንኩ ቅርንጫፍ ወይም የሲቢኢ ብር ወኪል ዘንድ በመሄድ ደንበኛ ይሁኑ፡፡

መልካም እድል!
HTML Embed Code:
2024/05/14 09:16:51
Back to Top