TG Telegram Group Link
Channel: በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ
Back to Bottom
ስም አውጡላት

ለእሷም ከኔ ፥ ለኔም ከሷ
ማንም የለን፥ እኔ እና እሷ
እናት ሆና ፥ እንደ አባትም
እንደ እህት ፥ እንደ ወንድም
ብዙ ሆነች ፥ ብቶን አንድም
ስም አውጡላት ፥ ሚሆን አቻ
አይገልፃትም ፥..እናት ብቻ

አቤል ታደለ

📱ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!📱
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
🎉 Hello, 10 million strong community! 🎉 Are you ready to exchange your hard-earned Shares for Taps? Save the date: Taps Pool is launching on May 30th! Get ready for a whole new level of earning potential! 💰💪

ያልጀመራችሁ ደግሞ
👇
https://hottg.com/tapswap_mirror_bot?start=r_323009513
"ለእሱ"

እስኪ ሁላችሁም መልካም ዕለት በሉ
አንድም "ለእሱ" ልደት አንድም ለበዓሉ

ወዳጅ ገጽ ቢኖረው ያንተኑ ይወርሳል
ወንድም ልክ ቢፈልግ ከመልክህ ይዋሳል

ጉልበት እንዳለው ሰው እኔ ቃል ላራቅቅ?
ደሞ እንደምችለው በእኔ አቅም ልመርቅ?
ይሁና...

ርቅ ነህ እንደሰው ግሩም እንደወንድም
ቅ ያሳድርህ ክፉህን አንወድም
ብር ያደላድልህ በቤቱ ኑርበት
ንድ አመት አይደለም ዘመን ገብርበት
ጹህ ልብ ያድልህ የሚወደድ ወድዶ
ምን ሚል ጠያቂ ማይደክም አሳዶ
ሻልን የሚያቀርብ ይብስ ወዲያ ሰድዶ
ብዘህ በጊዜህ ቤቶችህ ሳቅህን ከፊትህ ያግኙት
መትና ክብር ደጅህን ይጎብኙት።🙏

አሜን🙏

    በአቤኒ የተጻፈ✒️✒️
   ለሚያዚያ 27
(እንኳን አደረሰህ🙏)


📱ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!📱
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
.....
እሱ እኮ.. እያሉ ባሞገሱህ ቁጥር፤
አንተን እያነሱ ባወደሱህ ቁጥር፤

ልብህን አይሙቀዉ ፍፁም ደስ አይበልህ፤
ቀን የከፋ ለታ.........
ቁልቁል ይጥሉሃል....... እላይ የሰቀሉህ።
......................................
በዔደን ታደሰ

📱ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!📱
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
ረዘምዘሜ
--------------

ይወድሻል ቢሉሽ

ጸሀይ ትገባለች
ቢሉሽ በስተምስራቅ፣
ውሸት ነው በያቸው፣
ከነሱ በመራቅ፡፡

ምድር ጠፍጣፋ ነች፣
ቢሉሽም መልሰው፣
ሀሰት ነው በያቸው፣
ሳትቆጥሪያቸው ከሰው፡፡

አውራ ዶሮ እንቁላል
ይጥላል በማለት አጉል ቢሞግቱሽ፣
ቅጥፈት ነው በያቸው፣
የማይሆን ቢግቱሽ፡፡

ጽጌረዳ አበባን፣
ቢሉሽ ይች አደይ ናት፤
ሀቅ አይደል በያቸው፣
ትጊና በጽናት፡፡

ይሆናልም ቢሉሽ
ሰው እያደር እሸት፣
ብለሽ አጋልጫቸው---
‹‹አቤት! አቤት ውሸት! ››

ከኤሊና ጥንቸል፣
ቢሉሽ ኤሊ ፈጣን፣
ቀላማጅ! በያቸው፣
ተሞልተሸ በሥልጣን፡፡

ይህ ሰው አስር ሺ ዐመት፣
የሚኖር ነው ቢሉሽ ያለቅንጣት እፍረት፣
ይህ እውነት አይደለም፣
በያቸው በድፍረት፡፡

በዙ ውሸት ዋሽተው፣ ግን ቢሉሽ አንችዬ፣
‹‹ፍቅሬ ይወድሻል ከነፍሱ አስበልጦ!››
አንዳች ሳታመነች ‹‹እውነት ነው!›› በያቸው፣
ድምጽሽን ከፍ አርገሽ ፣ ሰምተሸ በተመስጦ፡፡

4/30/2017

By fikre tolosa

📱ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!📱
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
የማትጠልቂ ፀሐይ


ያለኝ የሌለኝን ሁሉን ስመዘበር፣
ሲከረቸምብኝ ተከፍቶ ያስገባኝ በር፤
ሲያነቅፈኝ ደልዳላው ሲጠልፈኝ የቀናው፤
ሲያባንነኝ ቅዠት ሲያባትተኝ ወናው፣
ምን ጉልበት ችሮት ነው?
ልብሽ እንዲህ የፀናው።

✍️©እስራኤል

@isrik

📱ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!📱
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Hey there, TapSwap crew! 👋

How's everyone's tapping going? Let's keep those fingers moving and those rewards coming in! Remember, every tap counts toward your crypto wallet! 💼💰

So keep up the great work, and happy tapping!

Click Here to start
ደብሮኝ ነበር ። ትንሽ አእምሮ እክል የገጠመው ሁለት ብር ስጠኝ እያለ የሚለምን ። ሲያየኝ ደስ የሚለው ሶስት ቀን ካለየኝ ምነው ጠፋ ብሎ ተገርሞ የሚጠይቀኝ ።

ኮስተር ብሎ በዘጠናዎቹ.... ኔሽን ጋዜጣ ላይ እነ አሌክሳንድሮቪች ፣ጤርጥዮስ-ከቫቲካን የፃፉትን ሙግቶች ​። ስነምግባር እና የእግዛብሄር ሃሳብ (Moral value and the idea of God) ያብራራልኛል ።1913- 1960 ድረስ ስለኖረው አልበርት ካሙ ስለ ሃሳብ ነፃነት ገደብ ሊጣልበት እንደማይገባ የተከራከረውን ። ቦንቦሊኖ እንዴት እንደተወደደ ...ጋዴ የሚሉት ጫማ ስለመጥፋቱ

ስለማይወደው Nihilist ቱ ኒቼ ..... ለራሱ mental breakdown የገጠመው ሰውዬ እግዜር የለም አለ እያለ.... ሂሂሂሂ እያለ እየሳቀ ያጣጥልልኛል።

ገሬ ቺክ ይፈራል ። አንድ ቀን "ሴክስ አድርገህ ታቃለህ እንዴ?" አልኩት እንዴት እንደተሽኮረመመ እንደ አስራ ሶስት አመት ልጅ አይነት መሽኮርምም ፊቱ ላይ ረበበ ።

ስለ Sex እና Art ግንኙነት ስለሚዘበዝበው Eroticism and Aesthetics እያብራራ ....ወሲብ አድርገህ ታውቃለህ ስለው በዚህ መጠን መሽኮረመሙ ይገርመኛል

የሆነ ሰሞን ድብርት ክፉኛ እየተላፋኝ ነበር ። ከማንም ጋ የማውራት አምሮት አልነበረኝም። የማውቀው ሰው ሲመጣ ችላ አለኝ እንዳይለኝ መንገድ የምቀይርበት ሰሞን ነበር ።

የሆነ ቀን ማኪያቶ የምንጠጣበት ጥግ ጠርዝ ላይ ተቀምጬ መጣ ። ደና ነህ ገሬ አልኩት እጁን ላከልኝ ሲጨብጥ እጁን ላላ አደርጎ ነው " ጠፋህ እኮ? "አለኝ ።

"አለው" ብዬው የሆነ ቀን እንደድሮ ሳንቀራረብ እሰጠው እንደነበረው አስር ብር ሰጠሁት ።

አየኝ ብሩን አየው ተቀበለኝ ። ሄደ ።

በነጋታው እመንገድ በጠዋት አገኘሁት ። ሲያየኝ ፈገግ ፈገግ አላለም ።

ቀጥታ መጥቶ .....

"ራከኝ እኮ አስቀየምኩ እንዴ ማታ ሳስብ.. ሳስብ .. ሳስብ ... ሳስብ ነበር ። ሌላ እኮ እንዳንተ የሚያዳምጠኝ ማንም የለም ። ጓደኛዬ እኮ አንተ ብቻ ነህ" አለኝ ።

አወራሩ ....ታረቀኝ ። እንደድሮ ጆሮ ስጠኝ ...ብር ሰጥተ አታባረኝ ....ነው
እምለው ሳጣ" እ... አሞኝ ነበር" አልኩት
ጓደኛ አመመኝ ተብሎ ይዘጋል ??

ይቅርታ ገሬ ....

አየህ ገረመው እንደሆነ ስሜ አንተ ነህ የምታስታውሰኝ እኮ" ።
.....ድንግጥ ብሎ "አሁን ተሻለ ግን ? "

በኛ መሳቅ ውስጥ የሚስቁ ሲጎልብን የሚጎልባቸው ሰዎች ካሉን ብቻውን ቀላል አይደለም መሰለኝ!!
© Adhanom Mitiku

📱ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!📱
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
🔥Finally... NotCoin Listing Date ታወቀ👏

May 16

Bybit Link
👇

https://www.bybit.com/invite?ref=LRQ97O1

OKX Link
👇
https://www.okx.com/join/71626412
እሱና እሷ

እሱና እሷ ከአንድ ቀን እይታ፣
ወዳጅነት ፈጥረው ፍቅር ተገንብታ፣
ተፈቃቅረው ከርመው ዓመታትን ቆጥረው፣
ጎጆ ለመቀለስ በአንድ ለመጠቅለል ሽማግሌ ልከው፣
ህይወት በአዲስ መልኩ ተጀመረ ይኸው።

የአንድ ቀን እይታ ዛሬ ፍሬ አፍርቶ፣
ሙሽሪት ፀንሳ ቤተሰብ መስርቶ፣
ሁለትነት ቀርቶ በዝተው ተበራክተው፣
ዘር የሚያስቀጥል አዲስ ትውልድ ፈጥረው፣
ባል አክብሮ ሚስቱን ሚስት ለባል ተገዝታ፣
ፍቅርና መቻቻል በእነሱ ላይ ታይታ፣
ለማየት በቅተናል ፍቅራቸው አፍርታ።

በሳምሪ የዝኑ ልጅ

📱ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!📱
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
ያንድ ምሽት ሀሳብ
(በእውቀቱ ስዩም)

ከባዶ ሶፋ ጋር ቤቴን ተዳብየ
ውጩ ምንም ቢዋብ፥ ውርጩን አመልጥ ብየ
በከዋክብት ላይ መጋረጃ ጣልኩኝ ፥ መስኮቴንም ዘጋሁ
ያደረግሽብኝን ለመርሳት ስታገል፤ ያደረግሽልኝን አብሬ ዘነጋሁ::

📱ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!📱
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
ማያልፍ የመሰለኝ ዳምኖ ህይዎቴ
ባዘነብኩት እንባ ታጥቦ ማንነቴ
ግርዶሹ በርትቶ ነገየን ጋርዶብኝ
ፍፁም አንዳልጓጓ ህመም በርትቶብኝ
ዛሬ ነገ እያልኩኝ ሞቴን ሲጠባበቅ
ህመሜን ሳዳምጥ ስሜቶቼን ሳረቅ
.
.
.
         መኖር ማለት ስቃይ
         መኖር ምለት ህመም
         መኖር ማለት ጭንቀት
         መኖር ማለት ድካም....

ወደ ተስፋ መንደር እልፍ ጊዜ ባመራ
የ እድሌን ልሻማ ከ እኩዮቼ ጋራ
ብፈልግ... ብጠብቅ ድርሻ የለኝ ሁኖ
ጠብታ እንኳን ሳይቀር ከ እኔነቴ ተኖ
ፀሐይ የለኝ ሁና ሕይዎቴ ዳምኖ
.
.
.
       ትላንት በመኖሬ ተስፋ እንኳን ሳይኖረኝ
       ምንም ያህል ባዝን የሚያልፍ ባይመስለኝ
       ቀን እየቆጠረ ቀን እየጨመረ
       የደመናው ጥቁረት መጠኑ ቀንሶ
       የስቃይ ዉርጅብኝ ከነበረው አንሶ
       ከ ሕይወቴ ጠፋ ቀስ በቀስ ጨርሶ...
.
.
.
የ ፀሐይ ዉበቷ
የፀሐይ ድምቀቷ
የዉበት ፍካቷ
ዛሬ ላይ ብሸፈን
ደመናው ሲገፈፍ ወደጎን ሲበተን....
.
.
.
       ህመም ብርድ ሁኖ ያገረጣው ትናንት
       ተንፏቆ እየዳሀ ዛሬን በመጠጋት
       አንድ ቀን ልጨምር ብዬ በመኖሬ
       ተስፋ ፀሐይ ሁኖ ከች አለልኝ ዛሬ!!
           
           📆ሚያዚያ 25 - 2016
                ዘይድ ሁሴን

📱ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!📱
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
አባቴ ጥቁር ነበር ፊቱ አይፈታም። ወታደር ነበር መቶ አለቃም ነበር ። ፀጉር ጥቅጥቅ ያለ ነበር ። አናፂ ነበር ። ብዙ አያወራም ነበር ።

ይወደኝ ነበር ። ያለውን ብር አውጥቶ ሱሪ ጥልፍልፍ ጫማ አቡወለድ ይገዛልኛል ። አታጨማልቀው ይሉት ነበር ። መቶኝ አያውቅም ።

ከጁ ሲጋራ ከእጁ እኔ አልጠፋም ነበር ። ሲጋራ ሽታው አባቴን ስለሚያስታውሰኝ ሲጋራ እወዳለሁ ። ሲጋራ አጤሳለሁ ።

አባቴ ኮስተር እንዳለ ነበር ውለታ የሚውለው ። አኮሰታተሩ አዲስ ሰው አያቀርብም ። የቀረበው ሁሉ ግን ይወደዋል ። ዝናብ ይወድ ነበር ። ፀሃይ ከረረ ብሎ አይነጫነጭም ብርድ ነው ሙቀት ነው እያለ ስለ አየር ሁኔታው አያብራራም ። ከተፈጥሮ ጋ ሲጨቃጨቅ ሰምቼው አላቅም ።

አባቴን እወደዋለሁ ። አይኑ ላይ የማየው ቸርነት እና ፍቅር የትም ስፍራ የትም ፊት ላይ አይቼው አላውቅም ። ምንም ነገር ለኔ ከሆነ ሲሳሳ አይቼ አላውቅም ። አለም ላይ ብቸኛ እንድበልጠው የሚፈልገው አባቴ ነው ።

አባቴ ሲናፍቀኝ ፎቶውን አያለሁ ኮቱን እለብሳለሁ ። ያለኝን አስታውሳለሁ ። ሳላማርር እናፍቀዋለሁ ። ከተፈጥሮ ጋር ሳልጨቃጨቅ ያወረሰኝን መልካምነት እኖረዋለሁ ።

መልኬን እምወደው ስለማምር አይደለም እሱን ስለምመስል ነው። አምሳያዬ ሶስት ቀን ብሎኝ ያውቃል ። እሱ እወዳቸዋለሁ ያለኝን ሰዎች ሁሉ እወዳቸዋለሁ ። እ......ማግኘት የሌለበት ናፍቆት ደስ አይልም መሰለኝ ።

© Adhanom Mitiku

📱ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!📱
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
አባቶች እናቶች
በፍቅር ተጋግዘው ፣ ያቆሙልን እውነት
በዘመን ጠልሽቶ...
ለእኛ ለልጆች ፣ ይመስለናል ተረት፡፡
።።።።።።
የኛ ትልቅ ችግር ፣ የኛ ትልቅ ህመም
"ተረት ተረት"ሲባል
መሰረት ሳንይዝ
"የመሰረት" ብሎ ፣" እሺ" እያሉ ማዝገም፡፡
።።።።።።፣
ተረት ተረት
"የመሰረት"
አንድ ሀገር ነበረች
"እሺ"
እምነትን ከፍቅር ፣ ገምዳ ያስተማረች፡፡
"እሺ"
አናም በዚች ሀገር...
ሙስሊሞች በእምነት ፣ መስጅድ ሲገነቡ
ክርስቲያኖች በፍቅር...
ይታዩ ነበረ ፣ ምሶሶ ሲያቀርቡ፡፡
"እሺ"
፡፡፡፡፡፡፡፡፡
እናም በዚች ሀገር...
ክርስቲያኖች በምነት ፣ ቤተስኪያን ሲያንፁ
ሙስሊሞች በፍቅር...
ይታዩ ነበረ ፣ ጉልላት ሲቀርፁ፡፡
"እሺ"
እናም በዚ መልኩ ፣ ሲኖሩ ሰኖሩ
እንደተዋደዱ እንደተፋቀሩ
እንደተጋገዙ እንደተባበሩ
መሰረት እንድናይ...
አንዋር ከራጉኤል ፣ ተጎራብተው ቀሩ
"እሺ"
"እሺ" ማለት ጥሩ
መሰረት ሳይዙ ...
የመሰረት ብሎ ፣ መኖር ነው ችግሩ!!!
።።።።።

By Belay Bekele Weya

📱ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!📱
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
አይ ሰው መሆን ከንቱ !!

(✍️እስራኤል )

ዘመኑ ሊፈጠም ጥቂት ምዕት ቀረው
እገሌን ሸለመው እገሌን ቀበረው
የሚል ሰበር ዜና፣
በጤና ይስጥልኝ የሚዘርፍ ጤና፣
ሺህ ሰው ተሰረዘ ከህይወት መዝገብ ላይ፣
የእግዜር እንባ መጣ ተመስሎ በማይ፣
ታጠበ ጎዳናው የማይጠራ እድፉን፣
ሰው ዘበት አያጥፈው መች ይተዋል ግፉን፣
ድንኳኑ ብስክስክ አያስጥልም ዶፉን።
እንደ ሽማግሌ ሲመክረን ተፈጥሮ፣
ሰማይ ማይ ይሸናል አመት ተወጥሮ።
አውሎው አኮርባጅ ነው የማይራራ በትር
ረሀቡ ጅራፍ ነው የሚገርፍ ዘወትር።

በሰቆቃም መሐል፥ በችግርም መሐል
ሰው ጥፋትን አይተው፣
ሰንካላ ሀሳቡ መልካም የተባለን
አያስመለክተው።

አይ ሰው መሆን ከንቱ!!

📱ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!📱
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
አባቴ ጥቁር ነበር ፊቱ አይፈታም። ወታደር ነበር መቶ አለቃም ነበር ። ፀጉር ጥቅጥቅ ያለ ነበር ። አናፂ ነበር ። ብዙ አያወራም ነበር ።

ይወደኝ ነበር ። ያለውን ብር አውጥቶ ሱሪ ጥልፍልፍ ጫማ አቡወለድ ይገዛልኛል ። አታጨማልቀው ይሉት ነበር ። መቶኝ አያውቅም ።

ከጁ ሲጋራ ከእጁ እኔ አልጠፋም ነበር ። ሲጋራ ሽታው አባቴን ስለሚያስታውሰኝ ሲጋራ እወዳለሁ ። ሲጋራ አጤሳለሁ ።

አባቴ ኮስተር እንዳለ ነበር ውለታ የሚውለው ። አኮሰታተሩ አዲስ ሰው አያቀርብም ። የቀረበው ሁሉ ግን ይወደዋል ። ዝናብ ይወድ ነበር ። ፀሃይ ከረረ ብሎ አይነጫነጭም ብርድ ነው ሙቀት ነው እያለ ስለ አየር ሁኔታው አያብራራም ። ከተፈጥሮ ጋ ሲጨቃጨቅ ሰምቼው አላቅም ።

አባቴን እወደዋለሁ ። አይኑ ላይ የማየው ቸርነት እና ፍቅር የትም ስፍራ የትም ፊት ላይ አይቼው አላውቅም ። ምንም ነገር ለኔ ከሆነ ሲሳሳ አይቼ አላውቅም ። አለም ላይ ብቸኛ እንድበልጠው የሚፈልገው አባቴ ነው ።

አባቴ ሲናፍቀኝ ፎቶውን አያለሁ ኮቱን እለብሳለሁ ። ያለኝን አስታውሳለሁ ። ሳላማርር እናፍቀዋለሁ ። ከተፈጥሮ ጋር ሳልጨቃጨቅ ያወረሰኝን መልካምነት እኖረዋለሁ ።

መልኬን እምወደው ስለማምር አይደለም እሱን ስለምመስል ነው። አምሳያዬ ሶስት ቀን ብሎኝ ያውቃል ። እሱ እወዳቸዋለሁ ያለኝን ሰዎች ሁሉ እወዳቸዋለሁ ። እ......ማግኘት የሌለበት ናፍቆት ደስ አይልም መሰለኝ ።

© Adhanom Mitiku

📱ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!📱
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
የሞተ ፍቅር

ፍቅር ሲፈርስ
ከኮዳው ሲፈስ
ከጆንያ ሲበተን
ከገንዳው ላይ ሲተን
ፍቅርን አዬሁት
እንዳልተ መኘሁት


ውሀ እንዳጣ ተክል  መንምኖ
እንደ ሀምሌ ሰማይ  ዳምኖ
እንደ ወራጂ ውሀ ድፍርስ ብሎ
እንዳልመጣ ሁሉ  ተንበልብሎ
ጠራርጎ ሲያልፍ እሱም ያልቃል
ከታተመበት  ልብ ላይ ይፋቃል

ነፍስ የዘራው ነፍስ ሲያጣ
እያወዛ  ያደመቀው  ሲገረጣ
እርቆ ሊሄድ  ለሞት ዳና ያቃጥራል
ስንገድለው  ለነፍስ ውጭ ያጣጥራል
እንደዘበት ትዝታ ሆኖ ይቀራል

By kerim

📱ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!📱
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
----
የሚያዋጣው ይህንን ግጥም መደጋገም ነው።
እንዲህ፦
😂

---❶--
ነድፋኛለች ብዬ - በውበቷ ምትሃት፣
በይፋ ከስሼ- ፍርድ እንዳላቀርባት
ለካስ እሷ ራሷ - መፅሐፍ ገላጭ ናት
😁
--- ❷ ---
ከፊት እሷን መሳይ - የጠይም ወላላ፣
በድንቡሽ ብርጭቆ - ወይን እየተሞላ፣
እሱን እየጠጡ -
ለሰስ ባለ ዜማ - እየተመሰጡ
ደግሞ በመሃሉ - እየተቃበጡ
ፍቅር ፍቅር ብቻ - እየመሰጠሩ፣
ዓለምን ረስተው - ምናለ ቢኖሩ፣
------ ❸ -----
ጨለምለም ባለ የብርሃን ድባብ ውስጥ፤
እልም ብሎ መጥፋት - ጭልጥ ብሎ ቅልጥ፤
በልቤ ትርታ - በነፍስ ቋንቋዬ፣
እየደባበስኳት - ምነ ባዜምኩላት - አንቺ ሆዬ ብዬ፤
----
--- ❹ -----
ዝ.....ም!!!
ከዚህ ኋላ ያለው - በቃ አይነገርም! 😁

📱ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!📱
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
HTML Embed Code:
2024/05/14 06:20:26
Back to Top