TG Telegram Group Link
Channel: የሕይወት መንገድ
Back to Bottom
ማራኪ አንቀፅ
የሕይወት አዙሪት!

ሕይወት አዙሪት ናት፡፡ ረጅም ርቀት የተጓዝክ ቢመስልህም ነገር ግን የምትጨርሰው ከጀመ
ርክበት ነው፡፡ ልብ በል!
.
• ራቁትክን ትወለዳለህ፤ እርቃንህን ወደ መቃብር ትወርዳለህ፡፡

• በጥርስ አልባው ድድህ እየጋጥክ ትጀምራለህ፤ ጥርሱን ባረገፈው ድድህ እያልጎጠጎጥክ ትጨርሳለህ።
• የሕይወትን ትግል እየዳህ ትጀምራለህ፤ አጎንብሰህ ትጨርሳለህ፡፡
.......
ዘመንም ተምኔታዊ ነው፡፡
መስከረም ጥቅምት ብሎ ያስጀምርህና መስከረም ብሎ ይመጣብሃል፤ ሠኞ ማክሠኞ ብለህ ተጉዘህ፤ እንደገና ሠኞ ትላለህ፡፡ እናም ሕይወት አዙሪት ናት!
.
መጀመሪያህ መጨረሻህ ነው፡፡ የጀመርክበትን አትርሳ፤ መጨረሻህ ነውና፡፡ የጀመርክበትን አትናቀው፤ ትጨርስበታለህና፡፡ ተራ ሠው ሆነህ ትጀምራለህ፤ ተምረህ ዕውቀት ብትጨምርም፤ ነግደህ ሃብት ብታገኝ፤ ተሹመህ በሕዝብ ላይ ብትሠለጥን፤ ክቡረ ክቡራን ሆነህ የወርቅ ካባ ብትለብስ፤ የምትጨርሠው እንደተራ ሠው አፈር ለብሠህ ነው፡፡
.
ልብ በል! ባለማወቅ ትጀምራለህ፤ በመዘንጋት ትጨርሳህ፡፡ ዕውቀት አላመጣህምና ዕውቀትም ይዘህ አትሄድም፡፡በለቅሶ ትጀምራለህ፤ በጭንቅ ትጨርሳለህ፡፡ በሠው እቅፍ ትጀምራለህ፤ በሠው ሸክም ትጨርሳለህ፡፡ ልደትህ ከሞትህ በምን ይለያል? ሞትህስ ከልደትህ በምን ይከፋል? ሕይወት መጀመሪያዋና መጨረሻዋ አንድ ነው፡፡ በዚህ የተነሣ ጠቢቡ እንዳለው ሁሉም የከንቱ ከንቱ ነው፡፡ ከፀሐይ በታች አዲስ ነገር የለም፡፡ ልብ በል! የዓለም #ከንቱነት ግን ውበትዋ ነው፡፡ ዓለም አዲስ ነገር ቢኖራት እኛን እንዴት በፀፀተን፤ ሞት የእውነት መጨረሻ ቢሆን እንዴት በቆጨን!! ‹‹ርቀህ የሄድክ ቢመስልህም፤ ትልቅ ክብ ሰርተህ ተመልሰህ እዚህ ትመጣለህ፡፡ ዋናውን ተግባርክን ግን እስካሁን አልጀመርከውም፡፡››

ዶክተር ዓለማየሁ ዋሴ
አንድ ተማሪ በፈተና አዳራሽ ገብቶ ሁለት ጥያቄዎችን እንዲሠራ ተሰጠው። ጥያቄዎቹ እነዚህ ናቸው።

1. ስለ እግዚአብሔር ጻፍ
2. ስለ ሰይጣን ጻፍ የሚሉ ነበሩ።

ጥያቄዎቹን ካነበበ በኋላ ስለእግዚአብሔር ጻፍ የሚለውን ይጽፍ ጀመረ። ነገር ግን የተሰጠው ጊዜ አንድ ሰዓት ብቻ ስለነበር ሙሉውን ሰዓት ስለ እግዚአብሔር ሲጽፍ ቆይቶ ሰዐቱን ጨረሰ።

የፈተናውን ወረቀት የሚሰበስበት ጊዜ ደርሶ ደውል ተደወለ ብልሁም ተማሪ ሁለተኛውን ጥያቄ አለመሥራቱን ተረድቶ "ለሰይጣን ጊዜ የለኝም" ብሎ በአንድ መስመር መልስ ሰጠ።

ሰው ሆይ ለሰይጣን ጊዜ አይኑርህ።
@And_Haymanot
@And_Haymanot_bot
ተኩላ ውሻና አንበሳ አንዲት ላም ያገኛሉ። አንበሳው ላሟን ይሰብርና ከመሬት ጥሎ የጤና በማይመስል ቸርነት ውሻን ለ 3 አካፍለን ይለዋል .....ውሻውምያልለፋበት ግዳይ ላይ የማካፈሉ ድርሻ ሲሰጠው የሥጋውን ዓይነት በመልክ በመልክ እያደረገ እኩል በእኩል ለ3 መደብ ከፈለና እኩል የሆኑትን ፫ (3)መደቦችለአንበሳው እያሳየሽ "አያ አንበስ መርጠው ይውሰዱ" አለ ...የሚመረጥሳይኖር መርጠው ይውሰዱ የተባለው አንበሳ እኩል የመካፈሉ ነገር አበሳጭቶት ውሻውን በክርኑ አድቅቆት ዘነጣጥሎ ከላሚቱ ሥጋ ጋር ከቀላቀለው በኋላ ተኩላን "በል አንተ ደግሞ "ለሁለት አካፍል" አለው። ተኩላውም የጤና ስላልመለሰው በጥንቃቄ ጉዳዩን መርምሮ ሲያበቃ ሥጋ ሥጋውን በአንድ ቦታ ፤ አጥንት አጥንቱን በአንድ ቦታ ከምሮ ሲያበቃ "አያ አንበሶ መርጠው ይውሰዱ" አለው ፤ አያ አንበስም በሁኔታው ተደስቶ
"አያ ተኩላ!እንዲህ ዐይነቱን የማካፈል ጥበብ ከየት ተማርከው እባክህ?"ቢለው አያ ተኩላም ተኩራርቶና ዘና ብሎ "ከውሻው ሞት ነዋ!ጌታው" አለው ይባላል።
@@@@@🙏🙏🙏🙏@@@@@

ሰው ከክፉም ሆነ ከበጎው ይማራል። ሰካራሙ ለባለ እእምሮው ጥሩ መምህር ነው።
ስለዚህ ከቃለ እግዚአብሔር በተጨማሪ ዙርያችንን በመቃኘት መማር አለብን።።
@qedusan
#የጣፈጠ #ህይወትን ይፈልጋሉ?

አንተ ልዩ ሆነህ የተፈጠርከው በእግዚአብሔር  ፈቃድ ነውና ምንም ሳታማርር ህይወትህን ኑራት።
#ባለህ_እየታመንኽ ህይወትህን አጣፍጣት። #ሰዎችን_ለመምሰልና_የነሱ_ግልባጭ_ለመሆን_አትጣር
 የአንተ ንጹህና እጹብ ድንቅ ያልታየ ማንነት የሚወጣው በራስህ
#መተማመን፣መኩራትና እራስህን ማክበር ስትጀምር ነውና። በዙሪያህ ምንም አይነት ዝነኞች ትልቅና ልዩ ተሰጦ ያላቸው ሰዎች ቢኖሩም በአንተ ውስጥ ያለው ልዩ ስጦታ ግን ከሁሉም ይለያል! ይልቃል! ይበልጣል! እነዚህ ልዩ ያልካቸው ሰዎች በአፈጣጠራቸው የተለዩ ሆነው ሳይሆን ይህንን ምስጢር ስላወቁትና ስለተገበሩት ብቻ ነው ከሌሎች ተለይተው አሁን ያሉበት የደረሱት። አንተም እንደነሱ የደረሱበት እንደውም ከነሱበላይ መስጠት መስራትና ማበርከት ከፈለክ ወደ እኔ ጠጋ በልና ጆሮህን ስጠኝ እኔም ሚስጢሩን ሹክ ልበልህ።

 ተጠጋኸኝ ልጀምር? "

#እራስህን_ሁን! #እራስህን_አክብር! #እራስህን_ውደድ!" #እራስህን_እንደማትወደው_እንደማታከብረውና_እንደማትሆነው_ስታስብ_ከማይመረመረው_ከእግዚአብሔር _እውቀትጋር_እየተደራደርክ_ነውና_ሁለቴ አስብ። ሰዎች ከሚሉህ በላይም እግዚአብሔር ሲፈጥርህም ምክንያት አለውና የሌለህን ትተህ ያለህን ዋጋ ስጥ። በሌለህ ነገር ስለምታገኘው ሳይሆን ባለህ ነገር ስለምትለውጠው ተመራመር። በሌለህና ባልተጨበጠው ነገር ትልቅ ነገር ለመስጠት ከማሰብ ይልቅ ባለህ ነገር ትንሽ ነገር ለመስጠት ሞክር። ያኔ አንተ ውስጥ የተደበቀው ከሌሎች የተለየው ድንቅ ፍልቃቂ ማበብ ይጀምራል። ብርሃንህ በዓለም ሁሉ ይሰፋል። ስምህም በሰዎች ልብ ውስጥ ይነግሣል። በምድር ላይ በኖርክበት ዘመን ሁሉ ዘመንህ የጣፈጠ ይሆንልሀል።

#መልካም ቀን

#ባለ ማዕተቦችን ወደዚህ
ግሩፕ ይጋብዙ

ለመቀላቀል 👉
@ortodoxtewahedo

🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏
"ምድሪቱን ይበላ ዘንድ አንበጣን ባዝዘው፥ ወይም በሕዝብ ላይ ቸነፈር ብሰድድ፥ በስሜ የተጠሩት ሕዝቤ ሰውነታቸውን አዋርደው ቢጸልዩ፥ ፊቴንም ቢልፈጉ፥ ከክፉ መንገዳቸውም ቢመለሱ፥ በሰማይ ሆኜ እሰማለሁ፥ ኃጢአታቸውንም ይቅር እላለሁ፥ ምድራቸውንም እፈውሳለሁ"
2ኛ ዜና 7:13

አቤቱ እንደ ቸርነትህ እንጂ እንደ በደላችን አይሁን!

👉👉ይህንን እንዳነበባችሁ በያላችሁበት አባታችን ሆይ በሉና ለምኑ:: ምሕላ ይታዘዝ እንዲህ ይደረግ ከምንል ከራሳችን እንጀምር:: ይህንን ፖስት ለማንበብ ጊዜ ካለን በፊቱ ለመውደቅ ጊዜ አለን:: እባካችሁ ስልካችንን አስቀምጠን ለዐሥር ደቂቃ ማረን እንበል!

ዲን ሄኖክ ሀይሌ
Forwarded from Deleted Account
​​መናፍቃን ማንኛውንም ጥያቄ ሲጠይቅወት መልሱ ይኸው ሼር አድርጉት መረጃው ለሁሉም ይድረስ
፨፨፨ለመናፍቃን የማያዳግም መልስ፨፨፨
የመጽሐፍ ቅዱስ ማስረጃ

1: ሥለ ሥላሴ

የእግዚአብሔር አንድነትና ሶስትነት:-
✞ዘፍ 1:26 ዘፍ 3:22
✞ዘፍ 11:18 ዘፍ 18:1-2
✞ኢሳ 48:26 ማቴ 3:16-17
✞ማቴ 28:19 ሉቃ 1:35
✞ዮሐ 7:28-29 ዮሐ 14:25-26
✞የሐ.ስራ 3:14 1ኛ ቆሮ 12:4-7
✞2ኛ ቆሮ 13:14 ኤፌ 4:4-7

2: የእመቤታችን ቅድስናዋ ፣ ክብሯ ፣ ድንግልናዋንና
አማላጅነቷ:-

✞መዝ 9:11 መዝ 13:10
✞መዝ 44:9 መዝ 86:5
✞መዝ 131:13 መዝ 44:2
✞መኃ 4:12 ኢሳ 7:14
✞ኢሳ 49:23 ኢሳ 60:14
✞ማቴ 1:23 ሉቃ 1:28
✞ሉቃ 1:42 ዮሐ 2:1-11
✞ዮሐ 19:16 ሮሜ 11:26-27
✞2ኛ ቆሮ 11:2 ራዕ 12:16

3: ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ፈራጅ እንጅ አማላጅ
አይደለም፡-

✞ዘፍ 3:22 1ኛ ሳሙ 16:1
✞ኢሳ 9:6 ዳን 7:14
✞ሆሴ 13:4 ዘካ 9:9-10
✞ሚክ 5:2 ሉቃ 1:32-33
✞ዮሐ 10:30 ሉቃ 2:12
✞ዮሐ 14:7 ሮሜ 9:5
✞ቆላ 2:9-10 ቲቶ 2:11-13
✞ዕብ 1:3-4 ዕብ 1:10-11
✞1ኛ ጴጥ 3:23 1ኛ ዮሐ 2:23
✞ራእ 3:22 ራእ 22:12-13

4: ስለታቦት እና ፅላት

✞ዘፃ 24:12 ዘፃ 25:10
✞ዘፃ 25:21 ዘፃ 26:34
✞ዘፃ 31:18 ዘፃ 32:15
✞ዘፃ 34:1 ዘፃ 34:28
✞ዘፃ 37:1 ዘፃ 40:20
✞መኃ 7:89 ኢያ 3:3
ኢያ 7:6 2ኛ ቆሮ 6:16

5: ሥለ ፆም የመጽሐፍ ቅዱስ ማሥረጃ:-

✞ዘፃ 34:28 ዘፃ 9:9
✞ሳሙ 20:26 1ሳሙ 7:6
✞1ሳሙ 31:13 2ኛ ሳሙ 1:12
✞2ኛ ሳሙ12:16 ዕዝ 8:21
✞ዕዝ 68:10 ዕዝ 108:24
✞ኢሳ 48:3 ኤር 36:9
✞ዳን 9:3 ዳን 20:2-3
✞ኢዩኤ 2:14 ኢዩኤ 2:12
✞ዩና 3:5 ማቴ 4:2
✞ማቴ 6:16:18 ማቴ 9:14-15
✞ማቴ 17:21 ማር 2:18
✞ማር 9:29 ሉቃ 2:37
✞ሉቃ 18:12 የሐ.ስራ 13:3 ✞የሐ.ስራ 14:23 2ኛ ቆሮ
11:17

6: መስቀል በመጽሐፍ ቅዲስ:-

✞ማቴ 10:38 ማቴ 16:20
✞ማር 8:34 የሐ.ስራ 5:30
✞1ኛ ቆሮ 1:18 ገላ 3:13
✞ገላ 6:13 ፊል 2:8
✞ፊል 3:18

7: ጥምቀትን በተመለከተ:-

✞ሕዝ 36:25 ማቴ 3:5-6
✞ማቴ 26:19-20 ማር 1:4-5
✞ማር 16:16 ሉቃ 3:21
✞ዮሐ 3:5 ዮሐ 3:22
✞ኤፌ 4:5 ገላ 3:26-27
✞የሐዋ 19:4 የሐዋ 18:8
✞የሐዋ 13:24 የሐዋ 10:47
✞የሐዋ 9:18 1ኛ ቆሮ 1:16
✞1ኛ ቆሮ 10 :2 1ኛ ቆሮ 12:13

8:ስዕለትን በተመለከተ:-

✞ዘኁ 28:20 ዘኁ 21:2
✞ዘፃ 23:21 መሳ 11:30
✞መዝ 49:14 መዝ 75:11
✞1ኛ ሳሙ 1:11 መክ 5:4-5
✞ዮና 2:10 ናሆ 1:15
✞የሐዋ 18:18

9: ፃድቃን ሠማዕታት ያማልዳሉ:-

✞ዘፍ 18:17-18 ዘፍ 18:23:24
✞ዘፍ 20:7 ዘፍ 33:3
✞ዘፍ 42:6 1ኛ ሳሙ 28 :14
✞2ኛ ሳሙ 1:2 2ኛ ነገ 1:13
✞2ኛ ነገ 2:15 2ኛ ነገ 4:9
✞2ኛ ነገ 4:32-35 መዝ 88:34
✞ማቴ 18:18 ዮሐ 20:23
✞የሐዋ 10:25 የሐዋ 16 :29
✞1ቆሮ 6:1-2 ፊሊ 4:6
✞1ኛጢሞ 5:17 ያዕ 5:14
✞ራዕ 14:13

10: መላዕክት ዘወትር በእግዚአብሔር ፊት ይቆማሉ:-

✞መዝ 148:2 ኢሳ 6:3
✞ማቴ 4:12 ማቴ 18:10
✞ማቴ 25:31 ማር 8:38
✞ራእ 1:11 ሉቃ 1:19

11: መላዕክት ፀሎታችን ወደ እግዚአብሔር ያደርሳሉ:-

✞ጦቢ 12:15 ሉቃ 15:10
✞የሐዋ 10:4 እዩብ 25:3
✞ኤር 33:22 ዳን 7:10
✞ሄኖ 10:1 ራዕ 5:11

12:ለመላዕክት የአክብሮት ስግደት ይገባል:-

✞ዘፍ 19:1 ማኅ 22:31
✞ኢያ 5:14 ዳን 8:16-17
13:መላዕክት አብሣሪያን ናቸው:-
✞ዘፍ 16:11 ሉቃ 1:13
✞ሉቃ 1:19 ሉቃ 1:30-31
✞ሉቃ 2:10-11

14:መላዕክት በአደጋ ጊዜ ፈጥነው ይደረሣሉ:-

✞ዘፍ 22:11-12 መዝ 90:11-12
✞ዳን 6:22 ዳን 10:13
✞ማቴ 2:13 የሐዋ 5:19-20
✞የሐዋ 12:7

15: ፀበል መርጨት ያስፈልጋል:-
✞ዘኁ 19:20

በተጨማሪም ሁላችንም እያንዳንዱን የመፅሐፍ ቅዱስ ክፍል ደጋግመን እናንብበው እግዚአብሔር አምላክ ማስተዋልና ጥበቡን ይስጠን አሜን፡፡

#ሼር
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️
የተሠጠህን ቁጠር

ሔዋን ከዕባብ ጋር እየተነጋገረች ነው:: የመጀመሪያ ጥፋትዋ ካለደረጃዋ ወርዳ ከዕባብ ጋር ወዳጅነት መጀመርዋ ሳይሆን አይቀርም:: ዕባብ ደግሞ የስይጣን አንደበት ነበረ::
ሰይጣን እንዲህ አላት :- በውኑ እግዚአብሔር ከገነት ዛፍ ሁሉ እንዳትበሉ አዝዞአልን? አላት።
ልብ አድርጉ እግዚአብሔር "ከገነት ዛፍ ሁሉ እንዳትበሉ" አላለም:: የከለከለው አንዲት ዛፍ ነው:: ሰይጣን ግን ሁሉን ተከልክላችሁዋል? ብሎ እንዳላዋቂ ጠየቀ:: ሰይጣን በመጽሐፍ ቅዱስ ንግግሩን የከፈተው በውሸት ነበረ::

ዓላማው ከሔዋን መረጃ ለማግኘት አልነበረም:: ሔዋን እስከዛሬ ያላሰበችውን ማሳሰብ ነበር:: ብሉ ተብሎ ከተሠጣቸው ብዙ ሺህ ዛፍ ይልቅ የተከለከሉትን አንዲት ዛፍ አሳይቶአት ሔደ:: ከዚያች ደቂቃ ጀምሮ ስላልተሠጣት ማሰብ ጀምራ ደስታዋን አጣች:: የተከለከለችውን በልታ የተሠጣትን ብዙ ሥጦታ ከነሠጪው አጣች::

ወዳጄ የቀደመው እባብ ዛሬም መርዙን ይረጫል

በሕይወታችን ከተሠጠን ብዙ ነገር ይልቅ ያልተሠጠንን ጥቂት ነገር እናስባለን:: ገንዘብ እንደሌለህ እያሰብክ ጤና እንዳለህ ትረሳለህ:: ጫማ እንደሌለህ እያሰብክ እግር እንዳለህ ትረሳለህ:: አልጋ እንደሌለህ እያሰብክ እንቅልፍ እንዳለህ ትረሳለህ::
ስለዚህ ውስጥህ ያለውን የዕባቡን ድምፅ አትስማ ከሌለህ ይልቅ ያለህ ይበልጣልና የተሠጠህን ቁጠር::

ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
ከእለታት 1 ቀን እሳትና ውሃ ስምምነት ለመፍጠር አንድ በሬ ገዙ አሉ፣ ያንን በፍቅር በስምምነት የሚንከባከቡት በሬያቸውን ሌባ ሰርቆ አረደባቸው ፡፡
ፈለጉ አሰሱ ደከሙ በዚህ ጊዜ አቶ እሳት ጌታዬ አቶ ውኃ ካንተ በቀር እኔ ሁሉን አሸንፋለሁ የሚችለኝ የለም ገንዘቡ እንደሆነ የሁለታችንንም ነው፡፡ ስለዚህ ተነስቼ ሰው ሁሉ ባዶ እንዲሆን ደኑንም ሣሩንም ቤቱንም አቃጥዬ የበሬአችንን ሌባ ልፈልገው፣ አለው ፡፡ ውኃውም ወንድሜ አቶ እሳት ምነው እንደዚህ ማለትህ የሰረቀውንም ደኅነኛውንም አንድ ላይ አድርጎ ማቃጠል የሚገባ ነውን? ሌባችንን ለመያዝ እንደሆነ የሚቸግረን ነገር የለም አሁን በእጃችን ይወድቃል እናገኘዋለን፡፡ አንተ ደግሞ ይዞ አይመጣ የት እናገኘዋለን ? ሲለው ቀላል ነው ይመጣል እንዴት አትለኝም፦
#ጊዜው_ኮሮናም_አይደል_ስለዚህ_ጥሬ_አትብሉ_ተብለዋል
#እጠብስ_ያለ_ካንተ_አጥብ_ያለ_ደግሞ_ከእኔ_የሚቀር_አለን??? እስኪ መልስልኝ በዚህ ጊዜ ልንይዘው ይቻለናል ሲል መለሰለት፡፡ ወዲያው ይኽንን ተነጋግረው ጥቂት ሳይቆዩ አንዱ ቅልጥም ይዞ ወደ እሳት ሲመጣ ሌላው ደግሞ ጨጓራ ሊያጥብ ከውኃ ዘንድ ሄደ፡፡ በዚህ ጊዜ ሌቦቹ ተያዙና እድሜ ልካቸው ውኃ እና እሳት እንዳያገኙ ተስረው ተከለከሉ አሉ፡፡

እናም ወዳጆቼ፦ #መተባበርን_ገንዘብ_ያደረገ_ጠላቱን_ያሸንፋል_እንዲባል_እኛም_ከምን_ጊዜም_በላይ_በጸሎት_በመጠንቀቅ_በመተባበር_ይህንን_ጊዜ_እንለፈው! ፡፡
....የእግዜር በግ....

አቤል በግ አወጣ
ቃየን ስንዴ አመጣ
ፈጣሪም መረጠ ~ ፈጣሪም ወደደ
የቃየንን ትቶ ~ የአቤልን ወሰደ
ቀናቶች ~ ከነፉ
ዘመናት ~ አለፉ
ሌላ ትውልድ መጣ ~ አብርሃም ተገኘ
ልጁን ለመሰዋት ~ ከልቡ ተመኘ
• • •
ጨለማን ከብርሀን ~ ሁን ብሎ የለየ
በአብርሀም እምነት ውስጥ ~ ይስሀቅን ስላየ
ታዛዡን ሊታደግ ~ አዳኝ እጁን ሰድዶ
ለወደደው ሰጠ ~ ከወደደው ወስዶ

✍️ከሙሉቀን ሰ•
☞ታዲያ ህይወት ለሰጣቸውና ለሞተላቸው ምግበ ነፍስ ምግበ ስጋ ለሰጣቸው ለክርስቶስ ያልሆነ ሰው ላንተ ይሆናል ብለህ ታስባለህ ።በፍፁም አይሆንም !!

✿ሰው ሸንበቆ ነው ከተደገፍከው ይሰበራል ።
:
✿ተሰብሮም አይቀርም ይወጋሀል ።

☞ወንድሜ ያንተም ነገር ይሄ ነው !!

★ወዳጆችህ ቀን አይተው ቢከዱህ ፣
:
★ዘመዶችህ ማጣትህን አይተው ገሸሽ
ቢያረጉህ ፣
:
★ብቻህን ከራስህ ጋር ብትቆም አትደነቅ።

☞ ግን በዚህ መካከል አንድ ነገር አስተዉል:-
:
✔️ጊዜን አይቶ የማይከዳ ፣

✔️በሁኔታዎች የማይለዋወጥ ፣
:
✔️ሁል ጊዜ ሰው ለሌላቸው ቀድሞ የሚደርስ ፣
:
✔️የጭንቅ ቀን ባለ ውለታ፣
:
✔️የቁርጥ ቀን ወዳጅ እግዚአብሔር ካንተ ጋር ነው።

☞ እርሱ ካንተ ጋር መሆኑን ካመንክ ሰው የለኝም እያልክ የምታንጎራጉረው መዝሙር ግጥሙም ዜማውም ይቀየራል !!!
ሰው ክቡር ነው

ድንግል ማርያም ክርስቶስን ይዛ ግብፅ በተሰደደችበት ጊዜ ውሃ ይጠማትና አንድ ቤት አንኳኩታ የሚጠጣ ውሃ ትለምናለች ። ሴትዮዋም ድንግልን አይታ መልክሽ የንግስት ይመስላል ልጅሽም የንጉስ ልጅ ይመስላል ይሄን የመሰለ መልክ ይዘሽ ባልሽ ያባረረሽ ፀባይሽ ቢከፉ ነው አለቻት ። አረጋዊዉ ዮሴፍም ለሚለምን ሰው ወይ ይሰጡታል ወይ ደሞ ከሌለ ካለበት ቦታ ያድርስህ ብለው ይመርቁታል እንጂ እንዴት እንዲ ይናገሩታል አላት ። ሴትዮዋም ጭራሽ ድንግል በጥፊ መታ ክርስቶስን ደሞ ከእቅፏ ተቀብላ ትወረውረዋለች ። ድንግልም ልጄን ብላ ልታነሳው ስትል ዮሴፍም እጇን ይዞ ተይው ተዓምሩን ያሳያቸው አላት ። ወዲያውኑ ሴትዮዋ ከነ አሽከሯ ወደ ጦጣነት ተቀይራ የራሷ ውሾች እያባረሯት ጫካ ገባች ። የኛ የአሁን ጊዜ አስተሳሰባችን እና ድርጊታችንም ፈጣሪ መአቱን እንዲያመጣብን ተአምሩን እንዲያሳየን እያስጨከነው ይመስላል ። ሰው በፈጣሪ አምሳል የተፈጠረ ክርስቶስ የሞተለት እነሆም በደጁ ቆሞ ደጁን የሚያንኳኳለት ለሚከፍትለትም ገብቶ ከሱ ጋር እራቱን የሚበላለት ፍጡር ነው ። ተራራውን እየው አያምርም ? የጨረቃ ድምቀት የከዋክብቱ ፍካት የፀሀዩዋ ውበት የአእዋፏቱ ዝማሬ ድንቅ ነው
አበቦች ፍካታቸው ፏፏቴዎች ፏጨታቸው ደስ አይልም ? በጣም ይላል

ግን 1 ነገር ልንገርህ እነዚህ ሁሉ ያልፉሉ ሰው ግን ለዘለዓለም የሚኖር የማያልፍ ፍጡር ነው ።[ ሞት እንኳ ቦታ መቀየሪያ እንጂ የህይወት ማብቂያ አይደለም ። የሰው ህይወት ትቀጥላለች። ሰው እኮ የባህር አሶችን የሰማይ ወፎችን የምድር አራዊትን ግዛ ተብሎ የፀጋ አምላክነት የተሰጠው ፍጡር ነው ። ሰው እኮ አምላኩ ስጋዬን ብላ ደሜንም ጠጣ ያለው ፍጡር ነው ። ይህ እኮ ለመላዕክትም አልተሰጠም ። ሴጣን እኮ በኛ ቢቀና የተሰጠንን ፀጋ ስለሚያውቅ ነው እኛስ በፈጣሪ አይን እኩል ሆነን አንዳችን አንዳችንን ለማጥፉት መነሳታችን ለምን ይሆን ? አዳም የእግዚአብሔር ምሳሌ ነው

በኛ ቤተክርስቲያን ቤተክርስቲያን ሲገነባ ጉልላት ሲደረግለት ያ ህንፃ ቤተክርስቲያን አለቀ ይባላል ። እግዚአብሔርም ስነ ፍጥረትን ሁሉ ከፈጠረ ቡሃላ አዳምን ፈጠረ ከዛ ሄዋንን የስነ ፍጥረት ጉልላት አርጎ ፈጥሮ አስቀመጣት ። ሴትነት ክቡር ነው ። ክርስቶስ ወደዚህ አለም ሲመጣ እናት እንጂ አባት አላስፈለገውም ። የሀገር መሪዎች ጀግና የጦር ሜዳ ወታደሮች ጳጳሶች ... ሁሉም ከሴት የተወለዱ ናቸው ። ወንድም ሁን ሴት ሁኚ ሰውነት ክቡር ነው ። ከሰውነት ወጥተን እንደ እንስሳ ባናስብ መልካም ነው ። በፍቅር በይቅርታ በመቻቻል ልዩነታችን ውበታችን አርገን ኢትዮጵያን ወደ ልዕልናዋ እንመልሳት

የነ ላሊበራ ከጣራው ተጀምሮ በመሰረቱ ያለቀ ውብ ፍልፍል መቅደስ ከአንድ ድንጋይ የተቀረፀ ውብ የአክሱም ሀወልት በውሀ ላይ የተገነባ የነ ይምርሀነ ክርስቶስ ቤተ መቅደስ ጣራው ክፍት ሆኖ ውሀ ማያስገባው የነ አቡነ አሮን መቅደስ እኮ የኛ ናቸው ። ቀደምት አባቶቻችን እኮ በዘር በሀይማኖት ተከፉፍለው አይደለም እኚን ሁሉ የገነቡት ። እንደ ሰው እናስብ እንደ ሰው እንኑር ። ሰውነት ክቡር ነውና ። አሁን እየሆኑ ያሉት ነገሮች የኛ የኢትዮጵያውያን ባህል አይደለም ። ከየት ይሆን ያመጣነው ? ከአልሸባብ ? ከIsis ? ከልባችን አመነጨነው ? ከአክቲቪስቶቻችን ወሰድነው ? ወይስ ከሌላ ? ብቻ አይበጀንምና ወደ ቀድሞ ባህላችን ፍቅራችን መቻቻላችን እስላም ክርስቲያኑ አስደናቂ የጋራ ኑሯችን እንመለስ


ለኦርቶዶክስ ተዋህዶ ልጆች #share እናድርግ !
#join_share
@qedusan
H/yohans(abeni)

እንኳን ለቅዱስ ዮሐንስ አደረሳችሁ
+++የኢትዮጵያ የዓመቱ ወራት ሥፍረ ሰዓት በቤተክርስቲያናችን+++
@afrohabeshaa
1. መስከረም .. የቀኑ ርዝመት ...12:00 ... የሌሊቱ ርዝመት ....12:00
2. ጥቅምት .... የቀኑ ርዝመት ...11:00 ... የሌሊቱ ርዝመት ....13:00
3. ህዳር ........ የቀኑ ርዝመት ...10:00 ... የሌሊቱ ርዝመት ....14:00
4. ታህሣሥ ... የቀኑ ርዝመት ... 09:00 ... የሌሊቱ ርዝመት ....15:00
5. ጥር ......... የቀኑ ርዝመት ...10:00 .... የሌሊቱ ርዝመት ....14:00
6. የካቲት ....... የቀኑ ርዝመት ...11:00 ... የሌሊቱ ርዝመት ....13:00
@afrohabeshaa
7. መጋቢት....... የቀኑ ርዝመት...12:00 ... የሌሊቱ ርዝመት ....12:00
8. ሚያዝያ....... የቀኑ ርዝመት...13:00 ... የሌሊቱ ርዝመት ....11:00
9. ግንቦት ...... የቀኑ ርዝመት ...14:00 ... የሌሊቱ ርዝመት ....10:00
10. ሰኔ ........ የቀኑ ርዝመት ...15:00 ... የሌሊቱ ርዝመት ....09:00
11. ሐምሌ .... የቀኑ ርዝመት ...14:00 ... የሌሊቱ ርዝመት ....10:00
12. ነሐሴ ...... የቀኑ ርዝመት ...13:00 ... የሌሊቱ ርዝመት ....11:00
@afrohabeshaa
(ምንጭ: መዝሙረ ማኅሌት ወቅዳሴ: በመምህር አፈወርቅ ተክሌ የቅኔ መምህር መጽሐፍ ላይ ከገጽ 36 ላይ የተወሰደ)

ጳጉሜን ፭/፳፻፲፪ ዓ᎐ም
አቤኔዘር ዘተዋሕዶ ገፅ
(በላይ በቀለ ወያ)
.
.
ክፉም ንጉስ መጣ
ደግም ንጉስ መጣ
ብቻ ግን ያልፋሉ ፣ ሁሉም እንደመልኩ
ይብላኝ ከህዝብ ጋር
ለሚጣሉ ህዝቦች ፣ መሪ እያመለኩ !!!

➡️ ክብር ለኢትዮጵያ ክብር ለሀገሬው!!!
"ትዳር ከንብ ጋር መኖር ነው። #የማትናደፍ_ንብ ከፈለክ #ከዝንብ ጋር ተጋባ"
ትዳር ከንብ ጋር መኖር ነው። ለማሩ ስንል ንድፊያውን መታገሥ፡፡ ቆይተህ ደግሞ ንድፊያውን መልመድ፡፡ገበሬ ቀፎ ሰቅሎ ንብ ሲያንብ፣ ንብ እንደምትናደፍ ሳያውቅ ቀርቶ አይደለም፡፡ የማትናደፍ ንብ ከፈለገ በየደጁ ቆሻሻ ፍለጋ የምትጓዘው ዝንብ ነበረችለት፡፡ ዝንብ ምን ጠባይዋ ሸጋ
ቢሆን፤ ጠብ የሚላት ግን ሌላ ነገር ነው፡፡ይህን ያውቃል ገበሬው፡፡ እያወቀም ንብ ያንባል፡፡ ማነብ ብቻ ሳይሆን ከንብ ጋር እንዴት መኖር እንደሚቻልም ያውቃል፡፡ንብ ትናደፋለች፤ ግን እንዳትናደፍ ማድረግም ይችላል፡፡ የምትወደውና የማትወደው ሽታ አለ፡፡ ስትቀርብህ ምን ማድረግ እና ምን አለማድረግ እንዳለብህ ገበሬው ያውቃል፡፡

በሀገራችን ንብ አትገደልም፤ ነውር ነው፡፡ብትነድፍም አትገደልም፡፡ የንቧን ማር ለመውሰድም ንቧን ገድሎ፣ አጥፍቶ፣ ጎድቶ ወይም አሰቃይቶ ሳይሆን በጭስ ራሱን እየተከላከለ፣ ፊቱን በጨርቅ ሸፍኖ፣ ወደ ንቧ ቀፎ ገብቶ ነው ማሩን የሚቆርጠው፡፡ ንቧም ሳትጎዳ፣ ማሩም ሳይጠፋ፣ እርሷም ሳትናደፍ፡፡

ትዳርም እንዲህ ነው፡፡ አኗኗሩን ነው ማወቅ፤ የንቧን ንድፊያ የመቀነሻውን መንገድ ነው ማወቅ፣ የማሩን አቆራረጥ መንገድ ነው ማወቅ፡፡ ደግሞም‘ኮ አስገራሚው ገበሬው የሚከባከበው ይህቺኑ የምትናደፈውን ንብ መሆኑ ነው፡፡

የምትቀስመው አበባ ትፈልጋለች፣ ንጹሕ አካባቢ ትፈልጋለች፣ ከጉንዳንና ከአውሬ ነጻ የሆነ ቀፎ ትፈልጋለች፡፡ ግን ትናደፋለች፡፡ ደግሞም ማር ትሰጣለች፡፡ትዳር አስደሳች ነገር ብቻ ሳይሆን አስመራሪ፣ አስጠሊታ፣ ጨጓራ አንዳጅ፣ ልብ አቃጣይም ክፍል አለው፤ ይናደፋል፡፡ግን ደግሞ ክብካቤም ይፈልጋል፡፡ ንጹሕ ልብ፣ ታማኝ ኅሊና፣ ቻይ አንጀት፣ ታጋሽ ሆድ፣ ጠቢብ አእምሮ፣ አሳላፊ
ልቡና ይፈልጋል፡፡ ለምን ቢሉ?
ማር ይሰጣልና
💜 ዳንኤል ክብረት
፨ምነው እመብርሃን፨

አዬ ምነው እመብርሀን
ኢትዮጵያን ጨከንሽባት
ምነው ቀኝሽን እረሳሻት
እስከመቼ ድረስ እንዲህ መቀነትሽን ታጠብቂባት
ልቦናሽን ታዞሪባት
ፈተናዋን ሰቀቀኗን ጣሯን ይበቃል ሳትያት
አላንቺ እኮ ማንም የላት
አውሮፓ እደሁ ትናጋዋን በፋሺስታዊ ነቀርሳ
ታርሳ ተምሳ በስብሳ
ምድራዊ እባጭ ጫንቃዋን እንደ ኮረብታ ተጭኗት
ቀና ብላ እውነት እንዳታይ አንገቷን ቁልቁል ጠምዝዟት
ነፍሷን ድጦ ያስበረከካት ስልጡን ብኩን መፃጉዕ ናት
እና ፈርቼ እንዳልባክን ሲርቀኝ የሀይልሽ ውጋጋን
አንቺ ካጠገቤ አትራቂ በርታ በይኝ እመብርሀን
ቃልኪዳኔን እንዳልረሳት እንዳልዘነጋት ኢትዮጵያን
አዎን ብቻዬን ነኝ ፈራሁ
እሸሸግበት ጥግ አጣሁ
እምፀናበት ልብ አጣሁ
እማማ ኢትዮጵያን መንፈሴ ተፈትቶ እንዳይክዳት ሰጋሁ
አዋጅ የምስራች ብዬ የትብት ምግቤን ገድፌ
ከእናቴ ማህፀን አልፌ በኢትዮጵያ ማህፀን አርፌ
ካፈሯ አጥንቴን ቀፍፌ ደሜን ከደሟ አጠንፍፌ
ከወዟወዟን ቀፍፌ
በህፃን እግሬ ድኬባት በህልም አክናፌ ከንፌ
እረኝነቴን በሰብሏ በምድሯ ላብ አሳልፌ
ከጫጩት እና ከጥጃ ከግልገል ጋር ተቃቅፌ
በጋው የረኛ አደባባይ ክረምት እንደ ወዙ ፍሳሽ
በገጠር የደመና ዳስ በገደል የሸለቆ አዳራሽ
ከቆቅና ከሚዳቋ ከጅግራ ጠረን ስተሻሽ
በወንዝ አፋፍ ሐረግ ዝላይ መወርወር መንጠልጠል ጢሎሽ
ከፍልፈል ጋር እሩጫ ስገጥም ከቀበሮ ድብብቆሽ
ከራዳ ጫፍ ሳር ለግት ላሜ ትንሽ ግጦሽ
ለጥጃዬ የሌት ግርዶሽ
ለጥማድ በሬዎቼ እራት ለማታቸው ጥቂት ድርቆሽ
ለግልገሌ ከአውሬ ከለል እማሳው ስር ጎጆ መትከል
ለፀሐይ የሾላ ጠለል ለዝናብ የገሳ ጠለል
ውሎ የንብ ቀፎ ማሰስ ያበባ እምቡጥ ሲፈነዳ
የግጦሽ ሳር ሲለመልም ሲሰማሩ ሰደድ ሜዳ
አዝመራው ጣል ከምበል ሲል ከብቱ ለሆራ ሲነዳ
ፈረስ ግልቢያ ስሸመጥጥ ከወፎች ዜማ ስቀዳ
ልቤ በንፋስ ተንሳፎ በዋሽንት ዋይታ ሲከዳ
ያቺን ነው ኢትዮጵያ የምላት
እመብርሀን ምነው እረሳሻት
ያቺን የልጅነት ምስራች የህፃንነት ብስራት
የሳቅ የፍንደቃ ዘመን የምኞት የተስፋ ብፅዓት
ያቺን የልጅነት እናት
አዛኝቱ እንዴት ብለሽ ጥርሶችሽን ትነክሺባት
ስሜን በስምሽ ሰይሜ ባገልግሎትሽ ስዋትት
ከዜማ ቤት ቅኔ ቤት ከድጓ ቤት መጻህፍት
ካንቺ ተቆራኝታ እድሌ ካንቺ ተቆራኝታ ነፍሴ
ከቀፈፋ ደጀ ሰላም ከቤተልሄም ቅዳሴ
አኮ... ቀዶ.. ቀፍፎ .... ዳባ ለብሶ
ቅኔ ዘርፎ .....ግስ ገሶ
መቅደስ አጥኖ ማሕሌት ቆሞ
በልብሰ ተክሕኖ አጊጦ በብር አክሊል ተሸልሞ
እመብርሀን ያንቺ ፅላት ነፍሴ ላይ በሳት ታትሞ
የመናኒው የአባ ተድላ ርድ ሆኜ አብሮኝ ታድሞ
ሕይወቴ እምነትሽን ፀንሶ
ስጋ ፈቃዴ ተድሶ
ለሕንፃሽ መዲና ቆሞ ለክብርሽ ድባብ ምሰሶ
ስሜን በስምሽ ሰይሜ ሆነሽኝ የእምነቴ ፋኖስ
ለዋዜማሽ ግሸን ማርያም ለክብርሽ ደብረ ሊባኖስ
ስሮጥ በወንበሩ አኖርሽኝ በአንበሳው በቅዱስ ማርቆስ
ታዲያን ዛሬ ኢትየጵያ ስትወድቅ ከምትሰጪኝ ለፍርሃት ጦስ
ምነው በእረኝነት እድሜ አይኔን በጓጎጣት የሎስ
የጋኔል ጥምብ አንሳ ከንፎ ወርዶ በጨለማ በርኖስ
እባክሽ እመብርሀን ይብቃሽ እባክሽ ስለ ፍቅሩ ወልዳ
ፅናት ስጪኝ እንድካፈል የእናቴን የኢትዮጵያን ፍዳ
ከነከሳት መርዝ እንድቀምስ ከነደደችበት እቶን
የእሷን ሞት እኔ እንድሞታት ገላዋ ገላዬ እንዲሆን
አዎን ብቻዬን ነኝ ፈራሁ
እምፀናበት ልብ አጣሁ
እሸሸግበት ጥግ አጣሁ
ህፃን ሆኜ የርግብ ጫጩት
አንዳንዴ ራብ ሲያዳክማት
ችጋር ከጎጆዋ ገፍቶ እዛፉ ግርጌ ሲጥላት
እናቷ በርራ ደርሳላት
በአክናፏ ሙቀት ታቅፋት
እፍ እያለች ግንባሯ ላይ ሕይወት ስተነፍስባት
ወዲያው ነፍስ ትዘራለች
ችር.... ብር.... ትር.... እያለች
እባክሽ
የአንድ የታወቀ ዩኒቨርሲቲ መምህር የሆነ ፕሮፌሰር የሚከተለውን ድንቅ ጥናት እንዳገኘ በቅርቡ ይፋ አድርጓል !! ጥናቱም የእንግሊዘኛ ፊደሎችን ከመጀመሪያው አስከመጨረሻው በቅደም ተከተል አስቀመጠ A b c d e f g h i j k l m n o p q r s t u v w x y z ። የነዚህን ፊደላት አሃዳዊ ቅደም ተከተል ኣስቀመጠ 1 2 3 4 5 6 7 8 9 10 11 12 13 14 15 16 17 18 19 20 21 22 23 24 25 26 በጥናቱም ለያንዳንዱ ፊደላት በቁጥር ቅደም ተከተል ሚዛን ሰጠ ለ"A"=1 ፣ ለ"B"=2 ......... እያለ አስከ "Z" =26ን ሰጠ ። በመጨረሻም የቃላት ደረጃን መመዘን ያዘ ።

1.
#የሥራ_ትጋት

(H+a+r+d+w+o+r+k)
(8+1+18+4++23+15++18+11)=98%

2.
#እውቀት

(K+n+o+w+l+e+d+g+e)
(11+14+15+23+12+5+4+7+5)=96%

3.
#ፍቅር

(L+o+v+e)
(12+15+22+5)=54%

4.
#እድል (L+u+c+k) = 47%
በዚህ መሰረት ከላይ የጠቀስናቸው ቃላት አንዳቸውም መቶ ፐርሰንት (100%)
ለውጥ ሊሰጡ አንደማይችሉ አስቀመጠ ።
ታዲያ (100%) ሊሰጠን ሚችለው ጉዳይ ምንድን ነው? ገንዘብ ይሆን እንዴ??

5.
#ገንዘብ_ነዋይ (M+o+n+e+y)

(13+15+14+5+25)=72%
አይደለም ምን አልባት አመራር ይሁን?

6.
#አመራር

(L+e+a+d+e+r+s+h+i+p)
(12+5+1+4+5+18+19+8+9+16)=97% አሁንም አይደለም! ለሁሉም ነገራት መፍትሄ አለው። አስተሳሰብ ፣ አካሄድ አኳኋናችንን ስንቀይር ይቀየራል ። ስለዚህ አስተሳሰብ ሁኔታን ሞከረ

7.
#አስተሳሰብ

(A+t+t+i+t+u+d+e)
(1+20+20+9+20+21+4+5)=100%
እናም ወዳጄ ውጤትና የ100% ለውጥ ሊያመጣልን የሚችለው #የአስተሳሰብ ለውጥ መሆኑን አረጋገጠ::

#አስተሳሰብ_አመለካከት=100%
HTML Embed Code:
2024/05/11 15:54:14
Back to Top