TG Telegram Group Link
Channel: አሐዱ፡ባንክ / Ahadu Bank S.C.
Back to Bottom
አሐዱ:ባንክ የኢንሹራንስ ክፍያን በተመለከተ የሦስትዮሽ ስምምነት በማድረግ አገልግሎቱን ይበልጥ እያሰፋ ነው!

አሐዱ:ባንክ በተነሣበት ከብዙዎች ለብዙዎች መርሕ ለብዙዎች ለመድረስ አጠናክሮ በመቀጠል ከብሔራዊ የኢትዮጵያ ኢንሹራንስ ኩባንያ (ናይስ) አ.ማ እና ከኤኮስ ኮሚሽን ኤጀንት ኃ/የተ/የግ/ማ ጋር በዋናው መሥሪያ ቤት ሐመር አዳራሽ ግንቦት 28/2017 ዓ.ም ስምምነት አደረገ::

የኢንሹራንስ ደንበኞች ለመኪናቸው የሚከፍሉትን ዓመታዊ የአረቦን ክፍያ 22% ብቻ በአሐዱ፡ባንክ በኩል ከቆጠቡ ባንኩ ፋይናንስ በማድረግ ዓመታዊ የኢንሹራንስ ክፍያቸውን እንደሚከፍልላቸው እና በ9 ወራት ጊዜ ውስጥ መክፈል የሚችሉበት ዕድል መመቻቸቱን የአሐዱ:ባንክ ተ/ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ሲሳይ ገብሩ በአፅንኦት ተናግረዋል::

የኤኮስ ኮሚሽን ኤጀንት ኃ/የተ/የግ/ማ ዋና ሥራ አስፈጻሚ የሆኑት አቶ ዐቢይ ዓለሙ፤ ብሔራዊ የኢትዮጵያ ኢንሹራንስ ኩባንያ (ናይስ) አ.ማ በርካታ ሥራዎችን የሠራ አንጋፋ እና ውጤታማ ኩባንያ በመሆኑ፤ ከአሐዱ ባንክ ጋር በአጋርነት ለመሥራት ስምምነት ማድረጉ ለባንኩ ውጤታማነትም አስተዋፅኦ እንደሚያበረክት ባለሙሉ ተስፋ ነኝ በማለት ገልጸዋል::

ብሔራዊ የኢትዮጵያ ኢንሹራንስ ኩባንያ(ናይስ) አ.ማ ተ/ዋና ሥራ አስፈጻሚ ወ/ሮ ዓለም ፀሐይ ደጋጋ በበኩላቸው፤ ኩባንያችን የአሐዱ ባንክን አክሲዮን ቀድሞ በመግዛት ባለቤትም በመሆኑ አብረን ስንሠራ ቆይተናል፤ የላቀ ውጤት ለማስመዝገብም ከዚህ በበለጠ የአጋርነት ሥራችንን አጠናክረን እንቀጥላለን በማለት ገልጸዋል::

አሐዱ፡ባንክ
ከብዙዎች ለብዙዎች

የአሐዱ፡ባንክ ማኅበራዊ ትስስር ገጾችን ይቀላቀሉ!
Website|Facebook|Instagram|LinkedIn|YouTube
🕌ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች በሙሉ፤ እንኳን ለአረፋ በዓል አደረሳችሁ።


አሐዱ፡ባንክ
ከብዙዎች ለብዙዎች
!
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
🕌ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች በሙሉ፤ እንኳን ለአረፋ በዓል አደረሳችሁ።


አሐዱ፡ባንክ
ከብዙዎች ለብዙዎች!
💼 We are Hiring

👉Place of work: Addis Ababa (Head Office)
👉Salary: As per the Bank’s Scale
Required Quantity for each position: (One) 1
👉Interested and qualified applicants shall apply via the following link only
https://forms.gle/n5dSvGesT6pugAyk7

Only Shortlisted Candidates will be communicated.
If you need more information, please call us on
📞+251-11-5-260-795
Application Deadline Date
June, 12 2025

Ahadu Bank
Inclusive Intermediation
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
🚺 አሐቲ የቁጠባ ሒሳብ፤ ዕድሜያቸው ከ 18 ዓመት በላይ ለሆኑ እኅቶች እንዲሁም እናቶች የተዘጋጀ!

🎯 ጠቀም ያለ ወለድ የሚያገኙበት
🎯 ኤቲኤም ካርድ በነፃ ታትሞ የሚበረከትበት የቁጠባ ሒሳብ ነው::

አሐዱ፡ባንክ
ከብዙዎች ለብዙዎች

የአሐዱ፡ባንክ ማኅበራዊ ትስስር ገጾችን ይቀላቀሉ!

Website|Facebook|Instagram|LinkedIn|YouTube

#አሐዱባንክ #AhaduBank #AHATI
🚘አሐዱ:ባንክ የኢንሹራንስ ክፍያን በተመለከተ እያከናወነ ያለውን የሦስትዮሽ ስምምነት አጠናክሮ ቀጥሏል!

አሐዱ:ባንክ በተነሣበት ከብዙዎች ለብዙዎች መርሕ ለብዙዎች ለመድረስ አጠናክሮ በመቀጠል ከቡና ኢንሹራንስ አ.ማ እና ከኤኮስ ኮሚሽን ኤጀንት ኃ/የተ/የግ/ማ ጋር በዋናው መሥሪያ ቤት ሐመር አዳራሽ ሰኔ 05/2017 ዓ.ም ስምምነት አደረገ::

“የኢንሹራንስ ደንበኞች ለመኪናቸው የሚከፍሉትን ዓመታዊ የአረቦን ክፍያ 22% ብቻ በአሐዱ፡ባንክ በኩል ከቆጠቡ ባንኩ ፋይናንስ በማድረግ ዓመታዊ የኢንሹራንስ ክፍያቸውን እንደሚከፍልላቸው እና በ9 ወራት ጊዜ ውስጥ መክፈል የሚችሉበት ዕድል መመቻቸቱን” የአሐዱ:ባንክ የዋና ሥራ አስፈጻሚ ኤክስክዩቲቭ አሲስታንት አቶ ዳንኤል ተስፋዬ ገልጸዋል፡፡

የቡና ኢንሹራንስ አ.ማ ም/ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ዮናስ ደበበ በበኩላቸው፤ “የጋራ ደንበኞቻችን በጋራ ለማገልገል አሐዱ ባንክ ይሔን የፕሪሚየም ፋይናንሲንግ አገልግሎት ይዞልን በመምጣቱ በኩባንያው ስም ደስታዬን እየገለጽኩ፤ ከዚህም የበለጠ ስትራቴጂክ አጋርነት በመፍጠር ሥራችንን አጠናክረን እንቀጥላለን” ብለዋል፡፡

የኤኮስ ኮሚሽን ኤጀንት ኃ/የተ/የግ/ማ መሥራች እና ዋና ሥራ አስፈጻሚ የሆኑት አቶ ዐቢይ ዓለሙ በበኩላቸው፤ “ከመፈራረም ባሻገር ከዚህ በላይ ተደራሽ ሆነን ውጤታማ ሥራ መሥራት ይጠበቅብናል÷ በጋራ እንድንሠራ ዕድሉን ላመቻቸው አሐዱ ባንክ ምስጋናዬ ላቅ ያለ ነው” በማለት ገልጸዋል፡፡

አሐዱ፡ባንክ
ከብዙዎች ለብዙዎች

የአሐዱ፡ባንክ ማኅበራዊ ትስስር ገጾችን ይቀላቀሉ!

Website|Facebook|Instagram|LinkedIn|YouTube

#አሐዱባንክ #AhaduBank #Buna_Insurance
👉 ከብዙዎች ለብዙዎች በሚል ልዩ መርሕ ብዙዎችን ለመድረስ ዓልሞ የመጣው ባንክ ባለቤት ይሁኑ!

✔️አሁኑኑ በአቅራቢያዎ ወደሚገኝ የአሐዱ ባንክ ቅርንጫፍ በመሔድ ባለቤት የሚያደርግዎትን አክሲዮን የራስዎ ያድርጉ!
✔️በተጨማሪም የባንኩ ድረ-ገጽ ላይ 
https://www.ahadubank.com/sharesale/ በመግባት የሚያገኙትን ቅፅ  ሞልተው በዚህ ኢሜል አድራሻ  መላክ ይችላሉ! ([email protected])

አሐዱ፡ባንክ
ከብዙዎች ለብዙዎች

የአሐዱ፡ባንክ ማኅበራዊ ትስስር ገጾችን ይቀላቀሉ!

Website|Facebook|Instagram|LinkedIn|YouTube

#አሐዱባንክ #AhaduBank #Share_Sales
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
📖 በየሦስት ወራቱ የምትወጣው አሐዱ፡ሰሌዳ ዲጂታል መጽሔት ቅጽ 4 ለንባብ ትበቃለች!

📖 ይጠብቁን!

አሐዱ፡ባንክ
ከብዙዎች ለብዙዎች

የአሐዱ፡ባንክ ማኅበራዊ ትስስር ገጾችን ይቀላቀሉ!

Website|Facebook|Instagram|LinkedIn|YouTube

#አሐዱባንክ #AhaduBank #AHADU_SELEDA
ዛሬ የዓለም የጥቃቅን ፣ አነስተኛ እና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች (MSMEs) ቀን ነው!
ይህንን ያውቃሉ?

👉90% - የሚሆነውን ቢዝነስ በጥቃቅን ፣ አነስተኛ እና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች (MSMEs) የተሸፈነ ነው!
👉ከ60-70% - የሚሆነው የውጤታማ ሠራተኞች መገኛ ብቻም ሳይሆን የብዙዎቹ እንጀራ ይህ ዘርፍ ነው!
👉50% - የሚሆነው የዓለም GDP የ(MSMEs)ውጤት ነው !
አሐዱ፡ ባንክ በዚህ ዘርፍ ትርጉም ያለው ሥራ እየሰራ ይገኛል::
በርካቶች ሕይወታቸው ተቀይሯል፤ ከራሳቸው አልፈው ለብዙዎች መትረፍ ችለዋል!
ይምጡና ተግባራዊ መልሱን እኛ ዘንድ ያግኙ!

አሐዱ፡ባንክ
ከብዙዎች ለብዙዎች!


የአሐዱ፡ባንክ ማኅበራዊ ትስስር ገጾችን ይቀላቀሉ!
Website|Facebook|Instagram|LinkedIn|YouTube

#አሐዱባንክ #AhaduBank #MSME
✍️ሀገር አቀፉ የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና ዛሬ መሰጠት ተጀምሯል፡፡

✍️በባንካችን "ደቀ መዝሙር የቁጠባ ሒሳብ" የተሻለ ለቆጠቡ ተማሪዎች ጠቀም ያለ ወለድ ይጠብቃቸዋል!

✍️ለተፈታኝ ተማሪዎች በሙሉ መልካም ፈተና ይሁንላችሁ!


አሐዱ ባንክ
ከብዙዎች ለብዙዎች!

የአሐዱ፡ባንክ ማኅበራዊ ትስስር ገጾችን ይቀላቀሉ!
Website|Facebook|Instagram|LinkedIn|YouTube
#AhaduBank #አሐዱ_ባንክ #National_Exam
📱የአሐዱ፡ባንክ ዲጂታል ባንኪንግ አገልግሎቶች ተጠቃሚ ይሁኑ!

ባሉበት ሆነው ራስዎን ይመዝግቡ!
For Android: https://play.google.com/store/apps/details?id=com.ahadubank.retail
For Apple iOS: https://apps.apple.com/us/app/ahadu-mobile-banking/id6463130433
For USSD: *611#

Beyond Convenience!
ከምቾት በላይ!


አሐዱ ባንክ
ከብዙዎች ለብዙዎች!

የአሐዱ፡ባንክ ማኅበራዊ ትስስር ገጾችን ይቀላቀሉ!
Website|Facebook|Instagram|LinkedIn|YouTube
#AhaduBank #አሐዱ_ባንክ #DigitalBanking
አሐዱ ባንክ የታክስ ክፍያን በኤሌክትሮኒክስ ዘዴ ለማሰባሰብ የሚያስችል ስምምነት ከገቢዎች ሚኒስቴር እና ከኢንፎርሜሽን መረብ ደኅንነት አስተዳደር ጋር የሦስትዮሽ ስምምነት ተፈራረመ!
ይኽ ስምምነት ሰኔ 25/2017 ዓ.ም በገቢዎች ሚኒስቴር አዳራሽ ከገቢዎች ሚኒስቴር እና ከኢንፎርሜሽን መረብ ደኅንነት አስተዳደር ጋር የተካሄደ ሲሆን፤ ስምምነቱ የታክስን ክፍያን በኤሌክትሮኒክስ ዘዴ ለማሰባሰብ የሚያስችል የሦስትዮሽ ስምምነት ነው፡፡
የገቢዎች ሚኒስቴር ሚኒስትር ክብርት ዓይናለም ንጉሤ እንደገለጹት፤ “የታክስ ክፍያ ሥርዓታችንን በማዘመናችን የኢንፎርሜሽን መረብ ደኅንነት አስተዳደር ባዘጋጀው ፕላትፎርም 153 ቢሊዮን ብር መሰብሰብ መቻላችን መልካም ቢሆንም፤ ሁሉም ባንኮች ቶሎ ወደ ተግባር በመግባት በሀገር እድገት ላይ የበኩላቸውን አሻራ ማሳረፍ ይጠበቅባቸዋል” ብለዋል፡፡
የኢንፎርሜሽን መረብ ደኅንነት አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር ክብርት ትዕግስት ሀሚድ በበኩላቸው፤ “በዲጂታል ሥርዓት 'ደራሽ' በተሰኘ የክፍያ ፕላትፎርም የታክስ ክፍያን በቀላሉ መሰብሰብ የሚቻልበትን የኤሌክትሮኒክስ ዘዴ ተግባራዊ በማድረጋችን ደስተኞች ነን፤ አሐዱ ባንክም በሀገር ደረጃ ለሚሰበሰበው የግብር ሥርዓት የድርሻውን የሚወጣበት እንደሚሆን” ገልጸዋል፡፡
አሐዱ፡ባንክ ከብዙዎች ለብዙዎች በሚለው መርሑ ለብዙዎች እየደረሰ ያለ፣ ከ 1 ሚሊዮን በላይ ደንበኞች ያሉት እና በዲጂታል ባንኪንግ ዘርፉም በርካታ ተግባራትን እየከወነ የሚገኝ ባንክ መሆኑን የአሐዱ ባንክ ተ/ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ሲሳይ ገብሩ አብራርተዋል፡፡ “አሐዱ ባንክ የዲጂታል ሥርዓቱን በመጠቀም፤ የታክስ አሰባሰብ ዘዴውን ዘመናዊ በማድረግ፤ ለከፋዮች ምቹ ሁኔታ ለመፍጠርና ቀልጣፋ አገልግሎት ለደንበኞች ለመስጠት ዝግጁ መሆኑን” አቶ ሲሳይ ጨምረው ገልጸዋል፡፡
HTML Embed Code:
2025/07/04 22:43:32
Back to Top