TG Telegram Group Link
Channel: አዲስ ጥበብ/ Addis Tibeb
Back to Bottom
#ኦ_አዳም'
አዳምን ልነካው ስለ ደፈርኩ ይቅርታ እጠይቃለው፡፡ ይቅርታ ጠይቄ ግን እፅፋለው፡፡ ((የማፈንገጥ አንድ ገፅ የአዳምም መልክ ነው፡፡))
https://www.facebook.com/habtu.girma

ግራጫ ፀጉር አለው፡፡ ትከሻው ሰፊ ነው፡፡ አይኖቹ መነፀር ይለብሳሉ፡፡ እጆቹ ለስላሳ ናቸው፡፡ ጣቶቹ ሲጋራ ይይዛሉ፡፡ እሱን ሳይ ሲጋራ አጢስ ብሎኝ ያውቃል፡፡

ብሄራዊ ሰፈር የምከርም ስለሆንኩኝ አዳምን በአመት ውስጥ አንዴ ሳላገኘው ቀርቼ አላውቅም፡፡ አዳም እንዴት ነህ ብዬ ብዙ ጊዜ ከትኩረቱ አናጥቤዋለው፡፡ ጥርሱን ትንሽ ፈገግ አድርጎ ሰላም ይለኛል፡፡ መዐዛ ቡና ከስኒዎቹ ቡና ሲጠጣ፣ ራስ ሆቴል ደጃፍ ሲራመድ አታጡትም፡፡ ካሳንችስም እግር እንደሚያበዛ ሰምቼአለው፡፡ ((አለማየሁ ገላጋይ ቤት ዙሪያ፡፡ ወዳጅ ናቸው፡፡ እኩያ ወዳጆች፡፡))

አዳም ረታን ሳስበው ይደክመኛል፡፡ አካሌን ያዝለዋል፣ ነብሴን ያደክመዋል፡፡ ልሸከመው አልችልም፣ ቆሜ ስለ እርሱ መናገር ያስፈራኛል፡፡ በርከክ ብዬ ባወራ እመርጣለው፡፡ እንደ ሰማይ የራቀ፣ ከአድማስም ባሻገር የደረሰ ነውና፡፡ (ከአድማስ ባሻገር መድረሻ አለው እንዴ?))

ለኢትዮጵያ ስነፅሁፍ ንጉሰ ነገስት ነው ተብሎ ለሚታመነው አዳም ረታ "ብዙዎች እልልታ" ሲያበዙ ይሰማኛል፡፡ ይኽ እልልታ ከማወቅ፣ እሱን ከመረዳት፣ ፅሁፎቹን አገናዝቦ ከመረዳት የመጣ ነው ወይንስ አዳምን አላነብም፣ አላደንቅም ማለት ወፈፌ ያስብል ይሆን ወይ ብዬ እፈራለው!?

እንጀራ፣ ሕፅናዊነትን፣ ሰአሊ ደራሲነቱን ((ጥልቅ ገለፃውን በማሰብ ነው ሰአሊ ማለቴ፡፡)) በቃላት የሚስል ፀሀፊነቱን ለማስታወስ፣ በድህረ ዘመናዊነት ውስጥ የሚንፈላሰሰውን ስብእናውን፣ ጥልቅ ንባቡን (የህዳግ ማጣቀሻዎቹን ማየት በቂ ነው)፣ የምናብ አድማሱን ስፋት፣ የበይነ ዲስፕሊን ሀልዬትን በተግባር ስለሚገልፅ አዳምን መንካት ያስፈራኛል፡፡

አዳም በአማርኛ መምህሩ አንደበት
አዳም በምናብ፣ በስሜቱ አንዴ ልጅ፣ ሌላም ጊዜ ወጣት፣ ሲያሻውም ቢሸመግልም የ60 አመት ጎልማሳ ነው፡፡ ((1950 ነው የተወለደው))፡፡ የረታ ልጅ በልጅነት ራዲዮ አድምጥ፣ ጋዜጣ አንብብ የተባለ ነው፡፡ እሱ ግን እግር ካስ የሚወድ እግረኛ ነበር፡፡ በትምህርት ቤት በራዲዮ የሰማውን፣ ከጋዜጣ ያነበበውን ለክፍል ተማሪዎች ያቀርብ ነበር፡፡ ይኽ ድግግሞሽ የቤት ስራ ግን ያሰለቸው ነበር፡፡ bored provokes new spirits.

እናም አዳም የጋዜጦቹን እና የራዲዮኑን ጭማቂ ወሬዎች አሽቀንጥሮ ጥሎ በመንገድ ያየውን "ዶሮዎች ከቅርጫት አምልጠው ዶሮ ነጋዴዎቹ ነፃነቴን ያሉትን ዶሮዎች ለመያዝ የሚያደርጉትን ርኩቻ ፅፎ አነበበ፡፡" መምህሩም ከታዘዘው ይልቅ ያልታዘዘውን ለፃፈው ልጅ ምስክር ሆኑ፡፡ ((አፈንጋጭነት አንድ)) አዳም ደራሲ ይሆናል ብለው በእኩዬቹ ፊት ተናገሩ፡፡ እሱ አልበረደው፤ አልሞቀውም፡፡ ((አሁንም እኮ ምንም ብትለው አይሞቀውም፡፡))

አርአያ የለውም
ግጥም እንደ ነብስ ቢወድም፡፡ በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ፣ በወመዘክር የመፅሀፍ መደርደሪያዎች ላይ ያሉትን ቢሰለቅጥም፡፡ የባህር ማዶ ፀሀፊዎችን እይታ በተለይም ደግሞ ተረት፣ ሳይንስ ፊክሽን እና ፋንታሲ ፅሁፎችን ቢያነብም "እከሌ፣ እንቶኔ" የተባለ ፀሀፊ ለፀኀፊነት እንድነሸጥ አድርጎኛል አይልም፡፡ ተረት፣ ሳይንስ ፊክሽን እና ፋንታሲ የሆኑት የፅሁፍ አይነቶች የወደደበት ምክንያት በድግግሞሽ አድካሚ ከሆነው ኑሮ ስለሚያፋቱት ይመስለኛል፡፡ ከአለም ነጥቀው ሩቅ ይወስዱታላ፡፡ ((አፈንጋጭነትን ሁለት))

የስነ መልክአ ምድር ትምህርት እና ስራ
በካርታዎች ስራ ድርጀት ለ8/ 9 አመታት የቢሮ ሰራተኛ ነበር፡፡ በነዚህ የሲቪል ቅጥረኝነቱ ብዙ ማንበቢያ ጊዜ አግኝታል፡፡ እጅጉን ጥልቅ አንባቢነቱም እጁን እንዲያነሳ ((እጅ ማንሳት ለብዕር እንደሆነ ይሰመርልኝ፡፡)) ብዕሩንም እንዲሲል፣ እንዲፅፍ ከልጅነት ጊዜ ተረቶች ወደ አዋቂነት ፅሁፎች/ ፀሀፊነት ገፍተውታል፡፡

የጂኦግራፊ ተማሪነቱ እና ሰራተኝነቱ አንድ መልካም ነገር እንዳዋሱት ይሰማኛል፡፡ የስነ መልክአ ምድር ትምህርት ሀሳቦች/ ሀልዮቶች/ ሀቲቶች) ከሂሳብ፣ ከፊዚክስ የጥናት ዘሮች ይዋሳል፡፡ ስነ መልክአ ምድር ሆደ ሰፊ የሆነ የሙያ ዘርፍ መሆኑን ሌሎችን መስኮች በመቀበል ያሳያል፡፡ አዳምም ከዚህ የጥናት ዘርፍ እና ባለሙያነት "የበይነ ዲሲፕሊን" አስተምህሮን እንደቀሰመ ይሰማኛል፡፡ ማንም ብቻውን ይቆም ዘንድ ልክ አይደለም፡፡ ደጋፊ፣ ረዳት፣ አጋዥ እንደሚያስፈልገው በእውኑ አወቀ፡፡ ((በቀደመው ዘመን የድህረ ዘመናዊነት ሀሳብን ቢረዳም፡፡))

የአዳም እንጀራ
ከማህሌት ጀምሮ እስከ አፍ ድረስ አዳም ብዙ ነገሮችን ሞክራል፡፡ በሀሳብ፣ በታሪክ ግንባታ፣ በምናብ አፅናፍ (ወደፊትም፤ ወደኃላም ዘመን) በስነፅሁፍ ዘርፎች በአጭር ታሪኮች፣ በኖቬላዎች፣ በረጅም ልብወለድ (ለእኔ የአዳም ረጅም ልብ ወለድን አባይ ልብ ወለድ ነው የምለው፡፡] ወንድሜ፣ እህቴ ለአንድ ሺ ገፅ የተማረከ ነው፡፡ የስንብት ቀለማትን ብዙ አመት ነው የፃፈው፡፡ ስለዚህ መፀሀፍ ከአስር አመት በፊት ጀምሮ ሲናገርበት ነበርና!]

ለኢትዮጵያዊው ስርወ ሀገር ውስጥ እንጀራ እኩያ ነው፡፡ ይኽን ውብ የሐገር "ሰንደቅ" ስንቱ ሲያናንቀው፣ ሲያጣጥለው እሱ ግን ለፅሁፉ ውክልና አደረገው፡፡ የጤፍ ዘር ደቃቅነትን አልናቀም፡፡ ያ ደቃቃ ዘር ተዘርቶ በመልካሙ መስክ ሲዘራ እልፍ ይሆናል፡፡ ተፈጭቶም፣ ተጋግሮም አይን ያለው ይሆናል፡፡ በክብነት ውስጥ ባለ ብዙ አይን ያለው እንጀራም ይፈጠራል፡፡ Semiotic representation. የእንጀራ መነሻውና መድረሻው በክብነት ውስጥ አያስታውቅም፡፡ ይኸንን ውክልና ለታሪክ ግንባታው፣ ለአዳም የስነፅሁፍ ዛር ውቃቢው ሆነ፡፡

ምናብና አዳም
በ 34 አመት የፀሀፊነት የአደባባይ ህይወት ውስጥ፡፡ ከማህሌት እስከ አፍ ድረስ ያሉትን ታሪኮች "በፍፁም" ህሊናህ ካልሆንክ በምን መስመር፣ በምን ሀሳብ፣ በምን መቼት እንዳገናኛቸው ግራ ሊገባህ ይችላል፡፡ አንዳንዴም ምንድን ነው የሚፅፈው አይገባም ልትል ትችላለህ፡፡ ((ይኽን ነገር ኩራዝ አሳታሚ ውስጥ የነበሩ ሰዎችም ይሉት ነበር፡፡ ባለ መቀሶች ሳንሱራሞች]

ምናብ ለአዳም የበኩር ልጁ ነው፡፡ በምናብ አማካኝነት ወደ ኋላ ተጉዘህ፣ ወደ ፊት ቀድመህ ተራምዶ ታሪክን፣ ሀልዩትን፣ ሂስን እና ሌሎች የሰውነት እና የአለምን ስራ ማስተሳሰር ይችልበታል፡፡ ይህን ንስር አይናማነቱ፣ ልሂቅነቱን ማሳያ መልክ ነው፡፡ አዳምም ፅሁፍ አላቂ አይደለም፡፡ አላቂነት የፀሀፊው ምናብ ነው፡፡ ትልቅ ምናብ ያለው ፀሀፊ አለቀ የተባለን ታሪክ አንስቶ ነብስ ዘርቶ ይቀሰቅሰውና ህያው ያደርገዋል ይላል፡፡

የአዳም ረታ የምናብ ከሀሊነትን በዚህ ታላቅ እሳቦቱ ውስጥ ገብተን መቅመስ አለብን
አዳም የምናብ ሀያልነቱን በሁሉት ነገር ማስተዋል እንችላለን፡፡ አንደኛው በሕፅናዊነት ስራው ውስጥ በአንዱ መፅሀፍ ውስጥ ልጅ ሁና ጭቃ ስታቦካ የነበረችው ልጅን፣ በሌላኛው መፅሀፉ ከሞት ብኌላ በሰማይ መንገድ ላይ ነብሳን ሊያናግራት ይችላል፡፡ አሳድጎ፣ አበልፅጎ ያሳያሀል፡፡ እንደ ሰው ልጅ መወለድ፣ ማደግ፣ መሞት በሚለው ግቢ ሳይወሰን፡፡ ከአድማሱ ወዲያ ይወስደዋል፡፡ የአዳም ምናብ፣ የራሱን አለም ሰርቶ ሁለተኛ ፈጣሪነቱን ያሳያሀል፡፡
አስካልን ማሳያ ነው፡፡ አንባቢው አንድን ጉዳይ እንደ ሽንኩርቱ ድርብርብ ገላ እየገሸለጠ ያሳይሀል፡፡ ተገርመህ ታነበዋለህ፡፡

የምናብ አስተምህሮው ይቀጥላል፡፡ የሚያልቅ ታሪክ የለም ለሚለው አዳም ረታ፡፡ በመፅሀፎቹ ውስጥ አንዳንዴ ታሪኮች በእንጥልጥል ይቀራሉ፡፡ እነዚህ በእንጥልጥል የቀሩ ታሪኮችን አንባቢው በምናቡ መሙላት ይችላል ይላል፡፡ ግድ ፀሀፊው ሁሉን መንገድ ይዞ መጋዝ የለበትም ባይ ነው፡፡ አንባቢው ባለው መረዳት (እውቀት እና ምናብ) ታሪኩን መቋጨት ይችላል፡፡ the golden thought of open ended rules.

ሕፅናዊነት እና በይነ ዲስፒሊን
አንድ ታሪክ ከሌላው ታሪክ፣ አንድን ሙያ ከሌላው ሙያ ጋር፣ አንድን መፅሀፍ ከሌላው መፅሀፍ ጋር ማስተሳሰር ይቻላል፡፡ ብቻውን የቆመ ሀልዮት የለም፡፡ አዳምም ይኽንን Interdisciplinary and Multiplicity ምግባር በስራዎቹ ማወቅ ያስፈልጋል፡፡ ሀሳቡን፣ የአፃፃፍ ቅርፁን፣ ሙዚቃዎቹን፣ ካርታዎቹን፣ በመፅሀፋ ውስጥ ያለውን ቀለሞች በአንድ አገናኝተህ ተንትነህ ካላነበብክ አዳምን እፍታውን ብቻ ነው የምታውቀው፡፡

ከተለምዶዋዊ የአተራረክ መንገድ አፈንግጦ፣ በደህረ ዘመናዊነት ዙፋኑን ለወረሰው አዳም በነጠላ እውቀቶች መረዳት አዳጋች ነው፡፡ በድርብ፣ ድርብርብ የእውቀት ጋቢዎች ውስጥ መመዘን ይገባል፡

የመጨረሻ መጀመሪያ
አዳም በወሰደው ባመጣው መንገድ፣ እቴ ሜቴ ሎሚ ሽታን ዘምረናል፡፡ ከሰማይ የወረደው ፍርፍር መረቅ በዝቶበት፣ ምስር ፈልገን በአለንጋ አስገርፎናል፡፡ በግራጫ ቃጭሎች ተደመን ማህሌት አቅርበናል፡፡ ለፍቅሩ ህማማት በገና ደርድረናል፡፡ ኦ አዳም ብለንም ለስንብት ቀለማት ተንበርክከናል፡፡

እናም:-
ፐ እና ኦ የተባሉት ቃላት አይዘይሩትም፡፡ አዳም የሚለው ሀያል ስም ራሱ የበይነ ዲሲፕሊን ደረጃ ነው፡፡
የሸዋሉል መንግሥቱ እና የጥላሁን ገሠሠ “አከም ነጉማ”
የሸዋሉል መንግሥቱ እና የጥላሁን ገሠሠ “አከም ነጉማ”
ጸሐፊ፡ አፈንዲ ሙተቂ

በአንድ ዘመን በኢትዮጵያ ደራሲያን ሲጻፉ የነበሩት ዘፈኖች “ዘፈን” ተብለው ብቻ የሚታለፉ አይደለም፡፡ አንዳንዶቹ በመልዕክታቸው ሀያልነት፤ ከፊሎቹ ደግሞ በዜማና ግጥማቸው ህብርነትና የረቀቀ መስተጋብር ዘመን አይሽሬ የሚባሉ ዓይነት ናቸው፡፡ በዚህ ጽሑፍ በሁለተኛው ዘርፍ ከሚመደቡት ዘመን አይሽሬ ዘፈኖች መካከል አንዱን አስቃኛችኋለሁ፡፡

ዘፈኑ “አከም ነጉማ” ይሰኛል፡፡ ታዲያ ይህንን ዘፈን “ዘፈን” በመሆኑ ብቻ ልዳስሰው የተነሳሁ እንዳይመስላችሁ፡፡ ከጀርባው ያለውን አስገራሚ ታሪክ ላካፍላችሁ በመሻቴ ነው ለቅኝቴ የመረጥኩት (እንጂ እኔ በበኩሌ በአሁኑ ጊዜ ለዘፈን ብዙም “ሀጃ” የለኝም)፡፡
***** ***** *****

የዘፈኑ መጠሪያ አከም ነጉማ (“Akkam Nagumaa”) ነው- በርዕሱ ላይ እንደጠቆምኩት፡፡ በኦሮምኛ “እንዴት ነሽ ሰላም ነሽ” እንደማለት ነው፡፡ ዘፋኙ አንጋፋው ኮከብ ጥላሁን ገሠሠ ነው፡፡ በኔ የዕድሜ ክልል ውስጥ ያላችሁ ሰዎች (ከ30 ዓመት በላይ የሆናችሁ) ዘፈኑን በደንብ እንደምታስታውሱት ይታወቀኛል፡፡ ከኔ የምታንሱትም ብትሆኑ ጥላሁን በ1987 በለቀቀው አልበም ውስጥ በድጋሚ በዘፈነው ጊዜ እንደ አዲስ አጣጥማችሁታል (ለዘፈን ባይተዋር ካልሆናችሁ በቀር)፡፡

“አከም ነጉማ” የፍቅር ዘፈን ነው፡፡ ጥላሁን ከአጠገቡ የተለየችውን አፍቃሪውን ነው “እንዴት ነሽ? ነሽ አማን ነሽ?” እያለ የሩቅ ሰላምታ የሚያቀርብላት፡፡ በዘፈኑ ውስጥ በናፍቆት ብስልስል ብሎ እንደተቃጠለላት ያወሳል፡፡ “እንቅልፍ አጥቻለሁ ቶሎ ነይልኝ” እያለም ይለማምናታል፡፡ እስቲ የዘፈኑን ግጥም ከአማርኛ ትርጓሜው ጋር ልጋብዛችሁ (ቃል በቃል ለመፍታት ቢከብድም እንደሚሆን አድርጌ ጽፌዋለሁ)፡፡

------
አዝማቹ
Akkam nagumaa fayyumaa (እንዴት? ነሽ አማን ነሽ? ደህና ነሽልኝ?)
Hiriyaa hinqabuu kophumaa (ሌላ ጓደኛ የለኝም እኔ ብቻዬን ነኝ)
Dhuftee na laaltus gaarumaa (እጅግ መልካም ነበር መጥተሸ ብታይኝ)
Akkam nagumaa fayyumaa (እንዴት? ነሽ አማን ነሽ? ደህና ነሽልኝ?)
----------


Eessattin si arga garamin harkisaa (የት ነው የማገኝሽ ወዴትስ ልጓዘው?)
Mee nama naaf dhaami bakki jirtu eessa (እስቲ ሰው ላኪብኝ ቦታሽን ልወቀው)
Yaa damme yaa dammee yaa dammee bulbulaa (የኔ ማር የኔ ማር የኔ ወለላ ማር )
Ani hirriiba dhabe suman yaadaa bulaa (እንቅልፍ አጥቻለሁ ካንቺ ሓሳብ በቀር የለኝም አዳር)
---------

Namni na ilaalee karaa na ceesisaa (ሰዎች ያዩኝና መንገድ ያሻግሩኛል)
Gidiraan jaalalaa sihi na feesisaa (የፍቅር ውቃቢው አንቺን ያሰኘኛል)
Garaan nurakinnaan sabbataan hidhannee (ሆድ ቢያስቸግር እንኳ በመቀነት ያስሩታል)
Ijaa ammo akkam goona tan ilaaltee hin obsine (አይታ የማትታገሰውን ዐይን በምን ያባብሏታል?)
--------

Bakka ati jirtu qalbiin koo na yaaddee (ያለሽበትን ቦታ በልቤ እያሰብኩት)
Numan ciisa malee hirriibni na dide (ተጋደምኩት እንጂ ምኑን ነው የተኛሁት)
Nagaatti, nagaatti nagaatti jiraadhu (በሰላም በአማን በደህና ኑሪልኝ)
Guyyaa tokko dhufee hamman sidhungadhuu (አንድ ቀን መጥቼ ስሜሽ እስኪወጣልኝ)
------
ዘፈኑን ከነዜማው መስማት የሚፈልግ ካለ ይህንን የዩቲዩብ ሊንክ ይከተል፡፡
http://www.youtube.com/watch?v=QNfu_1TEQXk
------

ይህ “አከም ነጉማ” የተሰኘው ዘፈን “የጠላሽ ይጠላ ብድሩ ይድረሰው” በሚለው የጥላሁን አልበም ላይ ነው የሚገኘው፡፡ በካሴት የታተመበት ጊዜ በ1973/1974 ይመስለኛል፡፡ ዘፈኑ በተለቀቀበት ጊዜ በሙዚቃ ያጀበው ባንድ የማህሙድ አህመድን “እንቺ ልቤ እኮ ነው-ስንቅሽ ይሁን ያዥው” ያጀበው ባንድ እንደሆነ በትክክል ያስታውቃል፡፡ በመሆኑም ባንዱ በዘመኑ ገናና የነበረው አይቤክስ ባንድ ነው ማለት ነው፡፡ ዘፈኑ በ1973/74 ቢለቀቅም እስከ ሰማኒያዎቹ መግቢያ ድረስ ይሰማ ነበር፡፡ እኔም እርሱን በደንብ ለመስማት የታደልኩት በዚሁ ምክንያት ነው፡፡

“አከም ነጉማ”ን በፊት ሳውቀው እንደ ማንም ተራ ዘፈን ነበር የምመለከተው፡፡ ክቡር ዶ/ር ጥላሁን ገሠሠ ባረፈበት ዕለት የአሜሪካ ድምፅ ሬድዮ የኦሮምኛ ፕሮግራም ለቃለ-ምልልስ የጋበዘው አርቲስት ዶ/ር ዓሊ ቢራ “ከጥላሁን ዜማዎች መካከል የትኛውን ታስበልጣለህ?” የሚል ጥያቄ ቀርቦለት “አከም ነጉማ” የሚል ምላሽ ከሰጠ በኋላ ግን በስስት ዐይን አየው ጀመር፡፡ ይሁንና ዘፈኑን ጠለቅ ብዬ የመመርመርና እንደ ቅርስ የማየት አባዜ የመጣብኝ ባለፈው የመስከረም ወር ነው፡፡

በወቅቱ (መስከረም/2005) ዩቲዩብ በሚባለው ዝነኛ የኢንተርኔት ቻናል ቆየት ያሉ ቪዲዮዎችን እበረብር ነበር፡፡ በተለይ በዚያ ወር የኮሎኔል መንግሥቱን መጽሐፍ አንብቤ ስለነበረ የሳቸውን ንግግሮች የያዙ ቪዲዮዎችን ዳውንሎድ ለማድረግ ከፍተኛ ፍተሻ አደርግ ነበር፡፡ ታዲያ በመንጌ ቪዲዮዎች መካከል በተሸጎጠ አንድ ፋይል ላይ “Tilahun Gessesse’s Akkam Neguma” የሚል ርዕስ በማየቴ ተደነቅኩና ከፈትኩት፡፡ ዘፈኑን ከመስማቴ በፊት ግን ስለዘፈኑ በተጻፈ መጠነኛ ማብራሪያ ውስጥ “Written by Yeshewalul Mengistu” የሚል ሐረግ ታየኝና አድናቆቴ ይበልጥ ጨመረ፡፡ እስከዚያን ጊዜ ድረስ ይህንን መረጃ ባለማወቄም በእጅጉ አዘንኩ፡፡
***** ***** *****

ይገርማል! ታሪካችን ይገርማል! የታሪክ አጻጻፋችንም ይገርማል፡፡ የምንጠላውን ሰው የሰይጣን ቁራጭ እያደረግን የአጋንንት መልክና የጋንጩር ቁመና እንሰጠዋለን፡፡ የምንወደውንም ሰው የመንግሥተ ሰማያት ሙሽራ እናስመስለውና ከመላእክት ተርታ እናሰልፈዋለን፡፡ በዚህ መሀል መታወቅ የነበረበት ሐቅ ይደበቅና አድናቆትና ጥላቻ የታሪክ አጸቆች ሆነው ቁጭ ይላሉ፡፡ ይሁንና ዛሬ የተደበቀው ሐቅ ትክክለኛ ጊዜውን ጠብቆ አንገቱን ቀና ያደርጋል፡፡ ያኔ ተረትን በታሪክ ቦታ ያነገሡ የጥላቻ ደቀ-መዛሙርት አንገታቸውን ይደፋሉ፡፡ እውነት ኮራ ብላ መራመድ ትጀምራለች፡፡፡፡

“አከም ነጉማ”ን በውብ ብዕሩ ከሽኖ ለሀገር ቅርስነት ያበቃው ደራሲም የነዚህ የጥላቻ ደቀ-መዛሙርት የጥቃት ሰለባ ሆኖ ታሪኩ ሲበላሽበት ኖሯል፡፡ ሀገርና ትውልድ ሲያጠፋ እንጂ ለሀገር አንዳች ጠቃሚ ነገር ጠብ እንዳላደረገ ሲጻፍበት ሰንብቷል፡፡ ሆኖም በአንድ ወቅት የተነሳው የጥላቻ አቧራ ብንን ብሎ ሲጠፋለት ደራሲው እጅግ መልካም የሆኑ ቁምነገሮች እንደነበሩት ታሪክ ይመሰክርለት ይዟል፡፡ የዚያ ደራሲ ስም የሸዋሉል መንግሥቱ ይባላል፡፡ ደራሲውን በወንዴ ጾታ ስጠራው ግን ወንድ እንዳይመስላችሁ፡፡ “ሴት” ናት፡፡

“የሸዋሉል መንግሥቱ” የሚለውን ስም ለመጀመሪያ ጊዜ ያየሁት “አጥፍቶ መጥፋት” በሚለው የሙሉጌታ ሉሌ ድርሰት ውስጥ ይመስለኛል፡፡ በማስከተልም በባቢሌ ቶላ “የትውልድ እልቂት”፣ በክፍሉ ታደሰ “ያ ትውልድ” እና በሌሎችም ኢህአፓ-ቀመስ ድርሰቶች ውስጥ ስሙን አይቼዋለሁ፡፡ በዚህ
ስም የምትጠራው ሴት በየመጻሕፍቱ ውስጥ ጨካኝ፣ አረመኔ፣ ገዳይ፣ ገራፊ፣ ዘራፊ፣ ለወጣት የማትራራ ወዘተ… በሚሉ ቃላት ተገልጻለች፡፡ በተለይ አንደኛው መጽሐፍ “እንደ ወንድ የታጠቀ ስኳድ እየመራች ከየቤቱ ወጣቶችን እያደነች የምትገድልና የምትገርፍ የሴት አረመኔ” ብሎ እንደገለጻት እስከ አሁን ድረስ ይታወሰኛል (በዚያ ዘመን ካለርሷ በስተቀር እንዲያ አይነት ጭካኔ የፈጸመች ሴት አልነበረችም ለማለት ይመስላል)፡፡

የሸዋሉል የኖረችው በዘመነ ቀይ ሽብር ነው-ከአያያዜ እንደምትረዱት፡፡ ይህቺ ሴት በ1969/1970 በኢህአፓ ገዳይ ስኳዶች “ሰባራ ባቡር” በሚባለው ሰፈር ከነበረው ቤቷ በራፍ ላይ ተገድላለች፡፡ ኢህአፓዎች የግድያዋን ምክንያት ሲያስረዱ “በንጹሐን ደም እጇን ያጨቀየች ቀንደኛ የመኢሶን ገራፊ እና የገዳይ ጓድ መሪ ነበረች” ነው የሚሉት፡፡ ሴትዮዋ የኢትዮጵያ ሬድዮ ጋዜጠኛ እና የፕሮግራም መሪ ሆና ሳለ እንዲያ ዓይነት ወራዳ ተግባር ውስጥ የገባችበትን ምክንያት በትክክል መረዳት ቢከብደኝም በኢህአፓ አባላትና ደጋፊዎች የተጻፈውን ገለጻ የማስተባብልበት መንገድ ስላልነበረኝ “ታሪኩ እውነት ነው” በማለት ተቀብየው ኖሬአለሁ፡፡ ስለርሷ በጎውን የሚናገሩ ጽሁፎችንና ቃለ ምልልሶችን አልፎ አልፎ ባነብም ሙያዋንና ችሎታዋን በዝርዝር ያስረዳኝ ሰው ስላልነበር በጨካኝነቷና በገራፊነቷ መዝግቤአት ቆይቻለሁ፡፡ “የአከም ነጉማ” ደራሲ እርሷ መሆኗን ከተረዳሁበት ዕለት ጀምሮ ግን አቋሜን ሙሉ በሙሉ ለመቀየር ተገድጃለሁ፡፡

አዎን! የሸዋሉል ከዕድሜዋ በፊት የተቀጨች ባለ ልዩ ችሎታ እመቤት ነበረች፡፡ ከጥላሁን “አከም ነጉማ” ሌላ በርካታ የኦሮምኛ እና የአማርኛ ዘፈኖች ግጥምና ዜማ ደራሲ ናት፡፡ ለምሳሌም በቅርብ ጊዜ ካገኘሁት መረጃ እንደተረዳሁት “ወይ ዮቢ ዮቢ ሐደሶ ሊባነታ” የሚለውን የዓሊ ቢራ ዘፈን የደረሰችው እርሷ ናት፡፡ የሸዋሉል በጋዜጠኝነቱም ቢሆን ወደር አልነበራትም፡፡ አድናቂዋ እና የሙያ ባልደረባዋ የነበረው አንጋፋው ደራሲና ጋዜጠኛ አበራ ለማ ኢትኦጵ ከሚባል መጽሔት ጋር ባደረገው ቃለ-ምልልስ “ትንታግ” በሚል ቃል ገልጾአት እንደነበር ይታወሰኛል (በወቅቱ የርሱ ቃለ ምልልስ ዘርዘር ያለ ስላልነበር ስለርሷ በጎውን እንዳስብ ሊያነሳሳኝ አልቻለም እንጂ)፡፡ ነገር ግን የዚያ ዘመን የደም ትርኢት ይህችን የመሰለች ውብ የኪነት እመቤት ምንጭቅ አድርጎ በላት፡፡ ሚስኪን!

ስለሸዋሉል እውነተኛ ታሪክ ለመመርመር ጉዞ ጀምሬአለሁ፡፡ በተለይ በርሷ ስራዎች ዙሪያ አንድ መጣጥፍ የማጠናቀር ሃሳብ አለኝ፡፡ ሴትዮዋ ኢህአፓዎች እንደሚሉት ገራፊ እና ገዳይ ከሆነች እርሱንም ለወደፊቱ ላስነብባችሁ ቃል እገባለሁ፡፡ ይሁንና ይህ አስቀያሚ ታሪኳ (በእውነትም እንደዚያ አይነት ታሪክ ካላት) መልካም ታሪኳን በምንም መልኩ ሊያስቀረው እንደማይችል መታወቅ አለበት፡፡ ስለርሷ ገራፊነት ስትነግሩን የኖራችሁ ወገኖችም የሸዋሉል “አከም ነጉማ”ን የጻፈችበት ውብ ብዕርና ምትሃታዊውን ዜማ ያፈለቀችበት ውብ አዕምሮ እንደነበራት ልታወጉን ወኔው ይኑራችሁ፡፡ እንዲያ ካልሆነ እውነት ለመናገራችሁ አናምናችሁም፡፡

እኔ ጸሓፊው ከሁለቱም ወገን አይደለሁም፡፡ የኢህአፓም ሆነ የመኢሶን አድናቂ አይደለሁም፡፡ በመሆኑም የኢህአፓዋን ወይዘሮ ዳሮ ነጋሽን “ነፍሰጡሯ ሰማዕት” እያልኩ የማሞግስበትና የመኢሶኗን የሸዋሉል መንግሥቱን “ዮዲት ጉዲት ናት” ብዬ የምራገምበት ምክንያት የለም፡፡ ለኔ ቀይ ሽብርም ሆነ ነጭ ሽብር ውጉዝ የሆነ የታሪክ እዳ ነው፡፡ ያንን እዳ ማወራረድ ያለበት ግን ያኛው ትውልድ ራሱ እንጂ ይህኛው ትውልድ አይደለም፡፡ ከያኔው ጥላቻ ጋር የሰዎችን ስብዕና እያጎደፉ መበከል በዚህ ትውልድ መቀጠል የለበትም፡፡ ውቢቷ የብዕር ገበሬና ጠንካራ ጋዜጠኛ የነበረችው የሸዋሉል መንግሥቱም በታሪክ ተገቢ ስፋራዋ ሊሰጣት ይገባል፡፡
“አከም ነጉማ ፈዩማ
ሂሪያ ሂንቀቡ ኮጱማ
ዱፍቴ ነላልቱስ ጋሩማ
አከም ነጉማ ፈዩማ”
“Anyone whose goal is 'something higher' must expect someday to suffer vertigo. What is vertigo? Fear of falling? No, Vertigo is something other than fear of falling. It is the voice of the emptiness below us which tempts and lures us, it is the desire to fall, against which, terrified, we defend ourselves.”

—Milan Kundera
የሚላን ኩንድራ መፃህፍትን በሙሉ ያውርዱ
በአብዛኛው “The Unbearable Lightness of Being” በሚለው መፅሃፉ የሚታወቀው የቼክ ተወላጁ ሚላን ኩንድራ በአለም የስነፅሁፍ መድረክ እጅግ ገናና የሆነ ደራሲ ሲሆን እስካሁን ባሳተማቸው መፃህፍቱ ያሳያቸው ድንቅ የስነፅሁፍ ቴክኒኮች እንዲሁም ልዩ ፍልስፍናዊ እሳቤዎች ስሙን ከማይደረስበት የልቀት ከፍታ ላይ ሰቅሎታል።
የሚላን ኩንድራ ጠቅላላ ስራዎች በቀላሉ በ Epub እና PDF ፎርማቶች ከታች ዳውንሎድ ማድረግ ይችላሉ። ዳውንሎድ ካደረጉ በኋላ Unzip ሁሉንም ፋይሎች ያገኟቸዋል።
“Everybody has a superficial side and a deep side, but this culture doesn’t place much value on depth — we don’t have shamans or soothsayers, and depth isn’t encouraged or understood. Surrounded by this shallow, glossy society we develop a shallow side, too, and we become attracted to fluff.

—Joni Mitchell
What makes people despair is that they try to find a universal meaning to the whole of life, and then end up by saying it is absurd, illogical, and empty of meaning. There is not one big, cosmic meaning for all, there is only the meaning we each give to our life, an individual meaning, an individual plot, like an individual novel, a book for each person.

~Anaïs Nin
Men are so simple and so much inclined to obey immediate needs that a deceiver will never lack victims for his deceptions. ~Niccolò Machiavelli
Put your principles into practice – now. Stop the excuses and the procrastination. This is your life! You aren’t a child anymore. The sooner you set yourself to your spiritual program, the happier you will be. Separate yourself from the mob. Decide to be extraordinary and do what you need to do – now. ~Epictetus
I can bear any pain as long as it has meaning. ~Haruki Murakami
People become neurotic when they content themselves with inadequate or wrong answers to the questions of life. They seek position, marriage, reputation, outward success of money, and remain unhappy and neurotic even when they have attained what they were seeking. ~Carl Jung
“My thought is me: that's why I can't stop. I exist because I think . . . and I can't stop myself from thinking. At this very moment, it's frightful, if I exist, it is because I am horrified at existing. I am the one who pulls myself from the nothingness to which I aspire: the hatred, the disgust of existing, there are as many ways to make myself exist, to thrust myself into existence. Thoughts are born at the back of me, like sudden giddiness, I feel them being born behind my head... if I yield, they're going to come round in front of me, between my eyes, and I always yield, the thought grows and grows and there it is, immense, filling me completely and renewing my existence.” ~Jean Paul Satre
“Another way to be prepared is to think negatively. Yes, I'm a great optimist but, when trying to make a decision, I often think of the worst case scenario. I call it 'the eaten by wolves factor.' If I do something, what's the most terrible thing that could happen? Would I be eaten by wolves? One thing that makes it possible to be an optimist, is if you have a contingency plan for when all hell breaks loose. There are a lot of things I don't worry about, because I have a plan in place if they do.” ~Randy Pausch (Book: The Last Lecture
It is man's intelligence that makes him so often behave more stupidly than the beasts. ~Aldous Huxley
"I can try." then they were in the car, driving. some son of a bitch hit his throttle and tried to ram them as they made a left turn. "baby, why do people try to hit us with their cars?" "well, mama, it's because they are unhappy and unhappy people like to hurt things." "aren't there any happy people?" "there are many people who pretend that they are happy." "why?" "because they are ashamed and frightened and don't have the guts to admit it." "are you frightened?" "I only have the guts to admit it to you — I'm so god damned scared, mama, that I think I'm going to die any minute." "baby, do you want your bottle?" "yes, mama, but let's wait until we get home." they drove along, turned right on Normandie. it was harder for them to hit you when you were turning right."

~Charles Bukowski
"An artist is a sort of emotional or spiritual historian. His role is to make you realize the doom and glory of knowing who you are and what you are. He has to tell, because nobody else in the world can tell, what it is like to be alive. All I’ve ever wanted to do is tell that, I’m not trying to solve anybody’s problems, not even my own. I’m just trying to outline what the problems are.

I want to be stretched, shook up, to overreach myself, and to make you feel that way too.

In this country … if you’re an artist, you’re guilty of a crime: not that you’re aware, which is bad enough, but that you see things other people don’t admit are there."

-James Baldwin
"It is Art because it is alive. It proves that, if you and I are to create at all, we must create with today and let all the Art schools and Medicis in the universe go hang themselves with yesterday’s rope. It teaches us that we have made a profound error in trying to learn Art, since whatever Art stands for is whatever cannot be learned. Indeed, the Artist is no other than he who unlearns what he has learned, in order to know himself; and the agony of the Artist, far from being the result of the world’s failure to discover and appreciate him, arises from his own personal struggle to discover, to appreciate and finally to express himself.

The thing of course, is to make yourself alive. Most people remain all of their lives in a stupor. The point of being an artist is that you may live.”

-E E. Cummings
HTML Embed Code:
2024/06/15 16:04:09
Back to Top