TG Telegram Group Link
Channel: Abel Birhanu የወይኗ ልጅ
Back to Bottom
የአልቃይዳ መሪ አይማን አል ዛዋሂሪ አፍጋኒስታን ውስጥ በአሜሪካ ሰው አልባ አውሮፕላን ጥቃት መገደሉን ዩናይትድ ስቴትስ አስታወቀች።የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን የተሳካ ያሉት ይኽው ጥቃት የዩናይትድ ስቴትስ ጠላቶች ሁሉ ግልጽ መልዕክት ነው ሲሉ ዋሽንግተን ውስጥ ተናግረዋል ። የሀገራቸው የስለላ ድርጅት ሲአይ ኤ የኦሳማ ቢን ላደን ተተኪ የተባለውን አል ዛዋሂሪ በያዝነው በጎርጎሮሳዊው 2022 ካቡል አፍጋኒስታን ውስጥ እንዳለ እንደተደረሰበት እና ከሳምንት በፊት፣ በአል-ዛዋሂሪ ላይ "ርምጃ" እንዲወሰድ መፍቀዳቸውን የተናገሩት ባይደን ጥቃቱ መድረሱን ማረጋገጣቸውንም ገልጸዋል። « ከቤተሰቦቹ መካከል አንዳቸውም አልተጎዱም። በሰላማዊ ሰዎች ላይም ምንም ጉዳት አልደረሰም። አሁን ይህን ዜና ለአሜሪካ ህዝብ የማካፍለው የተልእኮውን ስኬት ከፈጸሙ የፀረ ሽብር ማህበረሰብ እና ከፍተኛ ጥረት ካደረጉ ቁልፍ አጋሮች ካረጋገጥኩ በኋላ ነው።»
ግብፅ ሀገር የተወለደው አል ዛዋሂሪ አይማን እጎአ መስከረም 11 ቀን 2001 ዓ ም ኒውዮርክ ዩናይትድ ስቴትስ ከተፈፀመው የሽብር ጥቃት ጀርባ እጁ እንዳለ ይታመናል። እንደ ዩናይትድ ስቴትስ ገልፃ ቢን ላደንን የተካው የአልቃይዳ መሪ የተገደለው እሁድ ጠዋትነው። 71 ዓመቱ ነበር። ዩናይትድ ስቴትስ በጥብቅ የምትፈልገውን ይህ ሰው ያለበትን ቦታ ለጠቆመ 25 ሚሊዮን ዶላር እንደምትሰጥ አስታውቃ ነበር።

# DW Amharic
የዩናይትድ ስቴትስ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ-ጉባዔ ናንሲ ፔሎሲ በእስያ ጉዟቸው ታይዋንን የሚጎበኙ ከሆነ ዩናይትድ ስቴትስ “ዋጋ ትከፍላለች” ስትል ቻይና ዛሬ አስጠንቅቃለች። ፔሎሲ በይፋ ወደ ታይዋን መጓዛቸውን ባያረጋግጡም የዩናይትድ ስቴትስ እና ታይዋን መገናኛ ብዙኃን ይህንን እየዘገቡ ይገኛሉ። የቻይና ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ሀው ቹንይንግ ቤጂንግ ላይ ዛሬ በሰጡት መደበኛ ጋዜጣዊ መግለጫ እንደተናገሩት “የቻይናን ሉዓላዊ የፀጥታ ጥቅሞች ለማዳከም አሜሪካ ለምትወስደው ርምጃ ኃላፊነቱን ትወስዳለች» ብለዋል። ፔሎሲ በርግጥ ታይዋንን የሚጎበኙ ከሆነ ከ 25 ዓመታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ የጎነኙ ከፍተኛ የአሜሪካ ባለስልጣን ይሆናሉ። ቻይና ታይዋንን የራሷ አንድ አካል አድርጋ የምታይ ሲሆን ታይዋን ግን ራሷን እንደ ነፃ እና ዲሞክራሲያዊት ሀገር አድርጋ ታያለች። የፔሎሲ የታይዋን ጉብኝትን በተመለከተ ዩናይትድ ስቴትስ ቤጂንግን ለማስቆጣት ሆን ብላ ያደረገችው ነው ስትል ሩሲያ ዛሬ ለቻይና ድጋፏን አሳይታለች። ፔሎሲ ዛሬ ማሌዢያ ኩዋላ ላምፑርን ጎብኝተው ከማሌዢያ ጠቅላይ ሚኒስትር ኢስማኢል ሳብሪ ጋር እንደተገናኙ የፈረንሳይ ዜና ምንጭ ዘግቧል። የታይዋን የዜና ምንጮች እንደዘገቡት ናንሲ ፔሎሲ ዛሬ ማምሻውን ታይዋን ይገባሉ።

# DW Amharic
የቤት ኪራይ ለቀጣይ ስድስት ወራት መጨመር አይቻልም ተባለ፡፡

የመኖርያ ቤት ኪራይ መጨመርም ይሁን ተከራይን ማስወጣት የሚከለክለው ደንብ ለቀጣይ ስድስት ወራት ተራዘመ፡፡

የመኖርያ ቤት ኪራይ መጨመርም ይሁን ተከራይን ማስወጣት የሚከለክለው ደንብ ለሚቀጥሉት ስድስት ወራት መራዘሙን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አስታዉቋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ዜጎች ላይ የሚደርሰውን የኑሮ ጫናን ለመቀነስ በመኖርያ ቤት ተከራዮች ላይ የኪራይ ዋጋ ጭማሪ እና ተከራይን ማስለቀቅን የሚከለክል ደንብ አውጥቶ ተግባራዊ ማድረጉ ይታወቃል፡፡

ይህም ደንብ በተለያየ ጊዜ እየተራዘመ ላለፈው አንድ አመት ተግባራዊ ተደርጎ ቆይቷል፡፡

ስለሆነም የከተማ አስተዳደሩ አሁን ያለውን አጠቃላይ ነባራዊ ሁኔታ እና የህብረተሰቡን የኑሮ ጫና ከግምት ባስገባ ወቅቱን በአብሮነትና በመተሳሰብ ለማለፍ ይረዳ ዘንድ ይህ ደንብ ለሚቀጥሉት ስድስት ወራት እንዲራዘም ወስኗል፡፡

በመሆኑም ይህንን ክለከላ በመተላለፍ ተከራዮችን የሚያስወጡ እና የኪራይ ዋጋን የሚጨምሩ አካላት ላይ ማህበረሰቡ በ 9977 አጭር ቁጥር  ጥቆማውን ለከተማ አስተዳደሩ ማድረስ እንደሚችል አስታዉቋል፡፡

#Ethio Fm
የኢትዮጵያ አየር መንገድ 'የአፍሪካ ተወዳጁ አየር መንገድ' ሽልማትን አሸነፈ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ የ2022  'የአፍሪካ ተወዳጁ አየር መንገድ' ሽልማትን ማሸነፉን አስታወቀ፡፡

ግሎባል ትራቭል ማጋዚን  'ትሬዚስ አዋርድ' በተሰኘው ውድድር ድምጽ የማሰባሰብ ሂደት አየር መንገዱ አሸናፊ የሚያደርገውን ድምጽ አግኝቷል፡፡

አየር መንገዱ ሽልማቱን ያሸነፈው በተከታታይ ለ3ኛ  ጊዜ መሆኑን የሽልማቱ አዘጋጅ አስታውቋል፡፡

የኢትዮጵያ አየር መንገድም  በደንበኞቻችን ዘንድ የአፍሪካ ተመራጩ አየር መንገድ እንድንሆን ድምጻቸውን ስለሰጡን እናመሰግናለን ፤ ኩራትም ይሰማናል ብሏል፡፡

አየር መንገዱ ሽልማቱን ያሸነፈው በተከታታይ ለ3ኛ  ጊዜ መሆኑን የሽልማቱ አዘጋጅ አስታውቋል፡፡

#EBC
የቀድሞዋ የሶቪየት ህብረት መሪ ሚሀይል ጎርባቾቭ በ91 አመታቸው አረፉ
የተለያዩ የዜና አውታሮች የሩሲያ የዜና ወኪሎችን ጠቅሰው እንደዘገቡት  የመጨረሻው የሶቪየት ህብረት መሪ ሚሀይል ጎርባቾቭ በሞስኮ ማዕከላዊ  ሆስፒታል ነው ያረፉት።
«ግላስኖስት» እና «ፔሬስትሮይካ» በመባል የሚታወቁትን የተሃድሶ እንቅስቃሴዎች በሶቭየት ህብረት የመሩት  ጎርባቾቭ በ91 አመታቸው ነው ከዚህ አለም በሞት የተለዩት።
የሆስፒታል ባለስልጣናትን ጠቅሰው የተለያዩ የዜና አውታሮች ትናንት ማምሻውን እንደዘገቡት ጎርባቾቭ “በአስቸጋሪ እና ለረዥም ጊዜ በቆየ ህመም” ነው ህይወታቸው ያለፈው።
ጎርቫቾቭ በ53 ዓመታቸው በጎርጎሪያኑ 1985 የኮሚኒስት ፓርቲ ዋና ፀሃፊ ሆነው የሰሩ ሲሆን፤  ፓርቲው እስኪፈርስ እስከ1991 ዓ/ም ቀጥለዋል።  ብዙም ሳይቆይ ደግሞ ሀገራቸው ሶቪየት ህብረት ፈራርሳለች።
የሶስተኛውን የአለም ጦርነት አስቀርተዋል በሚል የሚወደሱት ጎርቫቾቭ በጎርጎሪያኑ 1990  የሰላም የኖቤል ሽልማት አግንተዋል።
የጎርቫቾቭን ህልፈት ተከትሎ ተከትሎ የዩኤስ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን “አስደናቂ ራዕይ” ያላቸው ሰው በመሆናቸው እና ሀገራቸውን በተሃድሶ ጎዳና በመምራታቸው ትልቅ ክብር እንደነበራቸው ተናግረዋል።
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሃፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ በበኩላቸው ጎርባቾቭን ታላቅ ፣ቁርጠኛ እና ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ ለሰላም ጠበቃ የሆኑ መሪ ሲሉ ገልፀዋቸል።
ጎርባቾቭ በሞስኮ ኖቮዴቪቺ መቃብር  ስፍራ ከባለቤታቸው  አጠገብ ዘላለማዊ እረፍት እንደሚያደርጉም  ዘገባዎች ያሳያሉ ።

DW Amharic
የማይናማሯ የቀድሞ መሪ አዉንግ ሳንሱኪ በምርጫ ማጭበርበር የ 3 ዓመት ፍርድ ተፈረደባቸዉ፡፡

➯ይህ የ 3ዓመት ፍርድ ከዚህ በፊት በወታደራዊዉ የማይናማር መንግስት በተፈረደባቸዉ 17 ዓመት የእስር ጊዜ ላይ የሚጨመር ነዉ፡፡

➯ሳንሱኪ በምርጫ ማጭበርበር ወንጀል የ3 ዓመቱ ፍርድ ከከባድ የስራ ጫና ጋር የተፈረደባቸዉ ሲሆን፣ ከዚህ በፊት በተለያዩ ወንጀሎች ከተፈረደባቸዉ የ 17 ዓመት እስር ላይ የሚጨመር መሆኑም ነዉ የተገለጸዉ፡፡

➯ሳንሱኪ በ2020 ህዳር ወር ላይ በተደረገዉ ምርጫ ላይ ፓርቲያቸዉ በከፍተኛ የበላይነት አሸንፏል በማለት ምርጫ አጭበርብረዋል ነዉ የተባለዉ ፡፡

➯በዚህ ወንጀል የተነሳ በተፈረደባቸዉ ፍርድ ሳንሱኪ ለሚቀጥሉት 20 ዓመታት ከፖለቲካዉ ርቀዉ ይቆያሉ የተባለ ሲሆን፣ ወታደራዊዉ መንግስት በሳንሱኪ ዙሪያ ከዚህ በኋላ የሚከሰዉ እና ለፍርድ የሚያቀርባቸዉ ብዙ ወንጀሎች አሉት ነዉ የተባለዉ፡፡

➯የኖቤል ሽልማት ተሸላሚዋ እና የማይናማር ተቃዋሚ ፓርቲ ቀንደኛ መሪ አዉንግ ሳንሱኪ ባለፈዉ ዓመት በመፈንቅለ መንግስት ከስልጣን መዉረዳቸዉ የሚታወስ ነዉ፡፡

➯ወታደራዊ መንግስቱ ወደ ስልጣን ከመጣ ወዲህ በተፈጠሩ ግጭቶች ከ 2ሺህ 200 በላይ የሚሆኑ ዜጎች ህይወታቸዉን ያጡ ሲሆን ፣ ከ 15ሺህ በላይ የሚሆኑት ደግሞ ለእስር ተዳርገዋል ሲል የዘገበዉ አልጀዚራ ነዉ፡፡

#Ethio Fm
ሌባ ላመሉ ዳቦ ይልሳል አሉ😂

➯በአዲስ አበባ አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ መስከረም 11 አንድ ግለሰብ ከሚስቱ እጅ ሞባይል መንትፎ ሲሮጥ በቁጥጥር ስር ውሏል።

➯ጉዳዩ እንዲህ ነው የአካባቢያቸውን ጸጥታ ለመጠበቅ የተሰማሩ አካላት (ሮንድ ጠባቂዎች) በምሽት አንድ ግለሰብ ከተበዳይ እጅ ሞባይል መንትፎ ሲሮጥ ተመልክተው ግለሰቡን ተከታትለው በቁጥጥር ስር በማዋል ለፖሊስ ያስረክባሉ።

➯በዚህን ግዜ ታዲያ ጉድና ጅራት ከወደኋላ ነው እንዲሉ አበው ግለሰቡ በፖሊስ ቁጥጥር ስር ከዋለ በኋላ ሞባይሉን የዘረፈው ከራሱ ሚስት ላይ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል።
ተወዳጁ ድምጻዊ ማዲንጎ አፈወርቅ አረፈ።

ተወዳጁ ድምጻዊ ማዲንጎ አፈወርቅ ባደረበት ህመም ምክንያት ማረፉን የቅርብ ወዳጆቹ ገልጸዋል።

በድምጻዊው ህልፈት የተሰማውኝ ሐዘን እየገለጽኩ ለቤተሰቦቹ፡ ለአድናቂዎቹና ለወዳጅ ዘመዶቹ መጽናናትን ይመኛል።
የነዳጅ የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ላይ ማስተካከያ መደረጉን የንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

በዚህም በአዲስ አበባ ከተማ ፦

- ቤንዚን በሊትር 57 ብር ከ05 ሳንቲም፣

- ነጭ ናፍጣ በሊትር 59 ብር ከ90 ሳንቲም

- ኬሮሲን በሊትር 59 ብር ከ90 ሳንቲም መሆኑ ተገልጿል፡፡

ይህ ማስተከከያ ከመስከረም 18 ቀን 2015 ዓ.ም እኩለ ሌሊት 6:00 ሰዓት ጀምሮ ተግባራዊ ይሆናል ተብሏል።

ሌሎች የነዳጅ ውጤቶች ማለትም የአውሮፕላን ነዳጅ ፣ ቀላል ጥቁር ናፍጣና ከባድ ጥቁር ናፍጣ ባሉበት እንዲቀጥሉ መወሰኑን የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር ገልጿል።

በሌላ በኩል አነስተኛ ገቢ ያላቸውን ዜጎችን ተጠቃሚ ለማድረግ በተረዘጋው የታለመ ድጎማ አሠራር ታቅፈው ሕዝቡን እንዲያገለግሉ የተመረጡት የሕዝብ ትራንስፖርት ተሽክርካሪዎች በሚጠቀሙት ነዳጅ ላይ በ2ኛው ምዕራፍ ምንም ዓይነት የዋጋ ጭማሪ አልተደገረም።

ሚኒስቴሩ እነዚህ ተሽከርካሪዎች በሐምሌ ወር በተወሰነላቸው ዋጋ ፦
- ቤንዚን በብር 41.26 በሊትር
- ነጭ ናፍጣን በብር 40.86 በሊትር እየገዙ እንዲቀጥሉ ብቻ ሳይሆን ከእጥፍ በላይ ያደገ ድጎማ ከመንግሥት እንዲያገኙ የተደረገ ስለሆነ በሚቀጥለው ጊዜ ዋጋ እስኪሻሻል ድረስ በሕዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ላይ ምንም ዓይነት ጭማሪ አይደረግም ብሏል።

ምንጭ፦ የንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር / ኢብኮ
Abel Birhanu የወይኗ ልጅ
ተወዳጁ ድምጻዊ ማዲንጎ አፈወርቅ አረፈ። ተወዳጁ ድምጻዊ ማዲንጎ አፈወርቅ ባደረበት ህመም ምክንያት ማረፉን የቅርብ ወዳጆቹ ገልጸዋል። በድምጻዊው ህልፈት የተሰማውኝ ሐዘን እየገለጽኩ ለቤተሰቦቹ፡ ለአድናቂዎቹና ለወዳጅ ዘመዶቹ መጽናናትን ይመኛል።
የአርቲስት ማዲንጎ አፈወርቅ ስርዓተ ቀብር ተፈጸመ
*************************

የአርቲስት ማዲንጎ አፈወርቅ ስርዓተ ቀብር በመንበረ ጸባኦት ቅድስተ ሥላሴ ካቴድራል ተፈጽሟል።

በስርዓተ ቀብሩ ላይ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግስት ኃላፊዎች፣ የሙያ ባልደረቦቹ እንዲሁም አድናቂዎቹ ተገኝተዋል።

ዛሬ ጠዋት በአርቲስቱ መኖሪያ ቤት ቤተሰቦቹ፣ የሙያ ባልደረቦቹ፣ አድናቂዎቹ በተገኙበት በሃይማኖታዊ ሥርዓት ተከናውኖ የአስከሬኑ ሽኝት ተከናውኗል።
በመዲናዋ የኢሬቻ ሆራ ፊንፊኔ በዓል ተከብሮ እስኪጠናቀቅ የሚዘጉ መንገዶች ይፋ ተደረጉ

በአዲስ አበባ ከተማ የሚከበረው የኢሬቻ ሆራ ፊንፊኔ በዓል በሰላም እንዲከበር የፀጥታ አካላት ቅድመ ዝግጅታቸውን አጠናቀው ወደ ሥራ መግባታቸውን የፀጥታና ደህንነት የጋራ ግብረ ኃይል አስታውቋል።

የምስጋና፣ የፍቅር፣ የሰላምና የይቅርታ በዓል የሆነው እና በዓለም የትምህርት፣ ሳይንስና የባህል ድርጅት /ዩኔስኮ/ በማይዳሰሱ በዓለም ዓቀፍ ቅርስነት የተመዘገበው የገዳ ስርዓት አካል የሆነው የኢሬቻ በዓል በአገራችን በብሄራዊ ደረጃ በልዩ ልዩ ዝግጅቶች በመከበር ላይ ይገኛል።

በርካታ ህዝብ የሚታደምበት እና አባገዳዎች፣ አደ ስንቄዎች፣ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች የሚገኙበት የኢሬቻ ሆራ ፊንፊኔ በዓል መስከረም 21 ቀን 2015 በልዩ ድምቀት በአዲስ አበባ ይከበራል፡፡ በዓሉ በሰላም እንዲከበር መላው የፀጥታ አካላት ዝግጅታቸውን አጠናቀው ወደ ስራ መግባታቸውን የፀጥታና ደህንነት የጋራ ግብረ ኃይል አስታውቋል።

የአዲስ ዓመትና እና የመስቀል በዓል አከባበር የነበሩ ጠንካራና ያጋጠሙ ክፍተቶች ተለይተው ለኢሬቻ ሆራ ፊንፊኔ በዓል በሰላም መከበር ጠቃሚ ግብዓቶች መወሰዳቸውንም ግብረ ኃይሉ ጨምሮ ገልጿል።

ከዚህም በተጨማሪ ለወንጀል መከላከል ተግባር ልዩ ትኩረት በመስጠት አብዛኛውን የሰው ኃይል በወንጀል መከላል ሥራ ላይ መሰማራቱንና በዓሉ ወደ ሚከበርበት ስፍራ የሚመጡ ታዳሚዎች ለጋራ ደህንነት ሲባል ፍተሻ መኖሩን ተገንዘበው አስፈላጊውን ትብብር እንዲያደርጉ የፀጥታና ደህንነት የጋራ ግብረ ኃይሉ ጠይቋል።

በያዝነው ዓመት በርካታ ህዝብ የታደመባቸው ልዩ ልዩ ሃይማኖታዊና ብሄራዊ በዓላት በሰላም እንዲከበሩ ህብረተሰቡ ከፀጥታ አካላት ጋር በመተባበር ወሳኝ ሥራ ማከናወኑን ግብረ ኃይሉ አስታውሶ፤ የዘንድሮው የኢሬቻ ሆራ ፊንፊኔ በዓል በሰላም እንዲከበር የበዓሉ ታዳሚዎች እና የከተማው ነዋሪ የተለመደውን ትብብራቸውን እንዲያደርጉ በፀጥታ አካላት ሥም ጥሪውን አስተላልፏል።

በተመሳሳይ ዜና የኢሬቻ ሆራ ፊንፊኔ በዓል ተከብሮ እስከሚጠናቀቅ የትራፊክ መጨናነቅ እንዳይፈጠር እና አሽከርካሪዎች አማራጭ መንገድን እንዲጠቀሙ ዝግ የሚደረጉ መንገዶችን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል።

በዚህም መሰረት፡-
=> ከቦሌ አየር መንገድ በሚሊኒዬም አዳራሽ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ወሎ ሰፈር አደባባይ

=> ከመገናኛ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ 22 ማዞሪያ

=> ከ4ኪሎ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ኮንሰን መስቀለኛ ወይም ወዳጅነት ፓርክ

=> ከፒያሳ በቸርቸር ጎዳና ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ቴዎድሮስ አደባባይ

=> ከጦር ሃይሎች በለገሃር ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ልደታ ከፍተኛ ፍርድ ቤት

=> ከጀሞ በትንባሆ ሞኖፖል ወደ ሜክሲኮ የሚወስደው መንገድ አፍሪካ ህብረት አደባባይ

=> ከቄራ ወደ ሜክሲኮ አደባባይ የሚሄደው መንገድ ቡልጋርያ ማዞሪያ

=> በአዲሱ መንገድ ከቄራ በቂርቆስ ወደ ለገሃር የሚወስደው መንገድ ታቦት ማደሪያ

=> ከሳሪስ ፣ በጎተራ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ጎተራ ማሳለጫ

=> ከቦሌ ወደ ቅዱስ ዑራኤል ቤተ ክርስቲያን የሚወስደው መንገድ አትላስ ሆቴል አካባቢ

=> ከአዋሬ ወደ ካሳንቺዝ የሚወስደው መንገድ ሴቶች አደባባይ

=> ከልደታ በጌጃ ሰፈር ፣ ጤና ጥበቃ የሚወስደው መንገድ አብነት ፈረሰኛ ፖሊስ አካባቢ

=> ከመርካቶ በጎማ ተራ ወደ አምስተኛ የሚወስደው መንገድ በርበሬ በረንዳ

=> ከመርካቶ በራስ ቴአትር ወደ ጎማ ቁጠባ ተክለ ሃይማኖት አደባባይ

ከአርብ መስከረም 20 ቀን 2015 ከቀኑ 6፡00 ሰዓት ጀምሮ ፕሮግራሙ እስከሚጠናቀቅ ድረስ መንገዶቹ ለጊዜው ለተሽከርካሪ ዝግ ይሆናል።

በዓሉ በሚከበርበት ዙሪያ እና በአካባቢው በግራና በቀኝ ለረጅም ሆነ ለአጭር ጊዜ ተሽከርካሪ አቁሞ መሄድ ፍፁም የተከለከለ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ ገልጿል።

በመጨረሻም ህብረተሰቡ የፖሊስን አገልግሎት ለማግኘትም ሆነ አጠራጣሪ ነገሮች ሲያጋጥሙት መረጃ ለመስጠት በ991 ወይም 816 ነፃ የስልክ መስመሮችን እና 01-11-11-01 -11፣ 01-11-26-43-59፣ 01-11-01-02-97፣ መጠቀም እንደሚችል እና ለፀጥታው ሥራ ስኬታማነት ህብረተሰቡ እያደረገ ላለው ቀና ትብብር የአዲስ አበባ ፖሊስ በመላው የፀጥታ አካላት ስም ምስጋናውን እያቀረበ በዓሉ የሰላምና የደስታ እንዲሆን መልካም ምኞቱን ገልጿል።
(አዲስ ማለዳ)
በመዲናዋ የስነጥበብና የሳይንስ ሙዚየም በዛሬው ዕለት ይመረቃል

➯ማክሰኞ መስከረም 24 ቀን 2015 (አዲስ ማለዳ) በመዲናዋ አዲስ አበባ አስደናቂ የቀለበት ቅርጽ ያለው ህንጻ እና ማራኪ የጉልላት ቅርጽ ያለው ተደርጎ የተገነባው ማዕከል እንዲሁም በአይነቱ አዲስ የሆነው የስነጥበብና የሳይንስ ሙዚየም በዛሬው ዕለት ይመረቃል።

➯ሙዚየሙ በ7 ሄክታር መሬት ላይ ያረፈ ሲሆን፤ በኪነ-ህንጻ ንድፍ ውስጥ ያካተተው ክብ ቅርጽም በማያቋርጥ እድገት ውስጥ ያለን እድገትና የሰው ልጆችን ጥበብ የሚያመለክት ነው ተብሏል።

➯በተጓዳኝም ኢትዮጵያ በአስገራሚ ፍጥነት በማደግ ላይ ካለው ቴክኖሎጂ ጋር ለመጣመር ያላትን ቁርጠኝነት የሚያሳይም እንደሆነም ተነግሯል።

የስነ ጥበብና የሳይንስ ሙዚየሙን አስደናቂ የሚያደርገው ምንድነው?

➯ሙዚየሙ በጥንቃቄ የተዘጋጁ የመኪና ማቆሚያዎች በተጨማሪ በዙሪያው ካሉ የከተማችን ፓርኮች ጋር የሚያገናኘው ውብ የእግረኛ መንገዶች ያሉት ነው።

➯ ትልቁ ህንጻ ከ15 ሺሕ ሜትር ካሬ በሚበልጥ መሬት ላይ ያረፍ ሲሆን፤ አጠቃላይ ሥፋቱ 132 ሜትር ያህል ነው።

➯ ከተፈጥሮ ስርዓት ጋር ተስማሚ በሆነ መንገድ ሃይል ከሚያመነጩ የውሃ ግድቦቻችን እንዲሁም በጣሪያው ላይ ከተገጠሙ የጸሀይ ብርሃን ሰብሳቢ መሣሪያዎች የሚያስፈልገው የኤሌክትሪክ አቅርቦት የሚያገኘው ይህ ሙዚየም ተፈጥሮአዊ የሃይል ማስተላለፊያዎችንና ሃይል ቆጣቢ የተፈጥሮ ብርሃንን የሚጠቀም ነው።

➯ይህ የስነጥበብና የሳይንስ ሙዚየም ትላንታችንን፣ ዛሬያችንን እና ነገአችንን በአንድ ላይ አሰናስኖ ሳይንስን ጥበባዊ በሆነ መንገድ፤ ጥበብን ደግሞ ሳይንሳዊ በሆነ መንገድ የሚያስቃኝ በመሆኑ አስደማሚ ተሞክሮዎችና አዳዲስ እውቀቶች የሚቀሰሙበት እንደሚሆንም ኢብኮ ዘግቧል።

#አዲስ ማለዳ
HTML Embed Code:
2024/05/18 09:22:12
Back to Top