#ዙል_ጀላል
ሙሳ (አ.ሰ) አላህን እንዲህ ሲሉ ጠየቁ፦ "ጌታዬ ሆይ ደካሞች ከጠንካሮች እንዴት መብታቸውን ማስመለስ ይችላሉ?"
ኃያሉ አላህም "ከሰአት በሆላ እንደዚህ አይነት ቦታ በዚህ አይነት ቀን ሂድ... ደካሞች መብታቸውን ከጠንካሮች እንዴት እንደሚወስዱ ታያለህ!" አላቸው።
ሙሳም ወደ ስፍራው ሄዱ ከአንድ ተራራ ላይ ፏፏቴ ሲወርድ አዩ ሙሳም በአቅራቢያው ቁጭ ብለው መመልከት ጀመሩ፡ ከቆይታ ቡሀላ አንድ ፈረሰኛ ከፈረሱ ወርዶ ውሀ ፍለጋ ወደ ፏፏቴው አምርቷ ከጠጣና ከታጠበ ቡሀላ ይዞት የነበረውን ቦርሳ ረስቶ ሄደ...
ሙሳ ከቦታቸው አልተነቃነቁም ከቆይታ ቡሀላ አንድ ወጣት ባሪያ በአህያ ተጭኗ ወደ ፏፏቴው መጣ እስኪጠግብ ጠጣና ታጠበ ሁሉን ቻይ ለሆነው አላህም ምስጋና አቀረበ ሊመለስ ሲልም ከፏፏቴው አጠገብ አንድ ቦርሳ ተመለከተ ባሪያውም ቦርሳውን ከፍቷ ሲያይ ወርቅ ገንዘብና ውድ ጌጣጌጦች ይዟ ነበር ባሪያውም አላህን አመስግኗ ቦርሳውን ይዞ ሄደ።
ከትንሽ ቆይታ ቡሀላም አንድ ሽማግሌ ሊጠጣና ሊታጠብ መጣ እየታጠበም ሳለ ቦርሳውን የረሳው ፈረሰኛ እየሮጠ ወደርሱ መጣ ፈረሰኛው ለአዛውንቱ እንዲህ አላቸው፦ እዚህ የተውኩት ቦርሳ የት ነው ያለው? ሽማግሌውም እንዲህ ሲሉ መለሱ "እኔ አላውቅም ቦርሳ አላየሁም.." ፈረሰኛውም ምንም ሳይናገር በንዴት ወዲያው በሰይፍ አንገታቸውን ቀላው።
ሙሳ (አ.ሰ) ይህን ሁሉ ከተለመከቱ ቡሀላ "ጌታዬ ሆይ ፈረሰኛው ሽማግሌውን በድሏል አሉ?" አላህም እንዲህ አለ: "ሙሳ ሆይ ሽማግሌው ከረጅም ጊዜያት በፊት የፈረሰኛውን አባት ገድሎ ነበር : የባሪያው አባት ደግሜ ለፈረሰኛው አባት ለሀያ አመታት አገልግሎ ምንም ክፍያ አላገኘም። ስለዚህ *ፈረሰኛው የአባቱን ገዳይ ሽማግሌውን በመገደል ሀቁን አገኘ : ባሪያውም አባቱ ሃያ አመት የለፋበትን ከፈረሰኛው አገኘ!"
"*ሊበድልህ አይችልም፤ ፍላጎቱም የለውም፤ ስትበደልም አያስችለውም... በቃ ከምትገምተው በላይ ይወድሀል።"
@abduftsemier
@abduftsemier
>>Click here to continue<<