#የማሊክ_ኢብኑ_ዲናር_ንሰሃ 2⃣
ኢብኑ ቁዳማህ እንዲህ እያሉ የሰይዲ ማሊክን ቂሷ ያጫውቱናል፡ ማሊክ ኢብኑ ዲናር አላህ ይዘንላቸውና የተፀፀቱበትን ምክንያት ተጠይቀው እንዲህ አሉ፡- እኔ ባለስልጣን ነበርኩ አርብ ለሊት የሻእባን ወር ግማሽ (ኒስፉ ሻእባን) ለሊቱ በወይን ሰከርኩ እና የመጨረሻውን ምሽት ኢሻ ሶላት መስገድ ተስኖኝ ነበር እናም በቤቴ ገብቼ ተኛሁ ። ትንሳኤ እንደጀመረ፣ መለከት ሲነፋ፣ መቃብሮች እንደተገለበጡ፣ ፍጥረታትም እንደተሰበሰቡ በህልም አየሁ፣ እኔም በመካከላቸው ነበርኩ። ከኋላዬ ድምፅ ሰማሁ እና ዘወር አልኩ አንድ ታላቅ ዘንዶ አየሁ፣ከዚህ በላይ ጥቁር አላየሁም፣አፉ የተከፈተ ነበር እና ወደ እኔ እየሮጠ ነው። በድንጋጤና በፍርሀት መሸሽ ጀመርኩ፣ ከዚያም አንድ አዛውንት በመንገዴ አለፉ። ንፁህ ልብስ እና አስደናቂ መዓዛ ነበረው። ሰላምታ ከተለዋወጥን ቡሀላ። እኔም እንዲህ እለው ጀምር “አንተ ሽማግሌ! ከዚህ ዘንዶ ጠብቀኝ! በአላህ ይሁንብህ!” አዛውንቱ አለቀሱና “እኔ ደካማ ነኝ ይህ ዘንዶ ከእኔ ይበረታል” አሉኝ። በእርሱ ላይ ምንም ሥልጣን የለኝም፤ ነገር ግን ሩጥ፤ ምናልባት አላህ ከርሱ የሚያድንህን ይሰጥሃልና። ከዚያም፣ ወደ ሌላ አቅጣጫ መሸሽ ቀጠልኩ እና ወደ ትንሳኤው ገደል ላይ ወጣሁ በእሳት ጉድጓድ እስክድረስ ድረስ። ድንጋጤውን ተመለከትኩ ከእሳቱና ከዘንዶው ፍርሃት የተነሳ ልሞት ተቃረብኩኝ። “አንተ ከእሳት ህዝብ አንዱ አይደለህምና ተመለስ!” የሚል ድምፅ ጮኸ። በዚህ ድምጽ ዘንዶው እኔን ከማሳደድ ወደ ኋላ ተመለሰ እና ሽማግሌው እንደገና ወደ እኔ መጣ። እኔም “ሽማግሌ! ከዚህ ዘንዶ እንድትጠብቀኝ ጠየቅሁህ እና አልቻልክም። አዛውንቱ አለቀሱና “እኔ ደካማ ነኝ ነገር ግን ወደዚህ ተራራ አፈግፈግ እያመላከቱኝ፤ ምክንያቱም በውስጡ የሙስሊሞች መኖሪያ አለ። ለአንተ በውስጧ ማረፊያ አለችና ይረዳሀል አሉኝ። ተራራውን ተመለከትኩ በብር ተሸፍኖ ነበር ፣ በውስጡም የተከፈቱ ጉድጓዶች ፣ በየመንገዱ ላይ መጋረጃዎች የተንጠለጠሉበት ፣ እና በቀይ ወርቅ የተገጠሙ የሰማይ መብራቶች ፣ በቀይ ወርቅ የተለጠፉ ፣ የእያንዳንዱ ሰማይ ብርሃናት ህብረ ከዋክብት በንጹህ ሐር ተለብጠዋል። ተራራውን ስመለከት ወደ እሱ እየሸሸሁ ዞር ብዬ ስመለከት ዘንዶው ከኋላዬ እየተከተለኝ መሆኑን ተረዳሁ፣ ወደ እኔ በሚቀርብ ጊዜ የአንዳንድ መላእክት ድምፅ፣ “መጋረጃዎቹን ጎትት፣ መስኮቶቹን ከፍተህ ወደ ውስጥ ግባ!” እያለ ጮኸ። በመካከላችሁ ለዚህ አደጋ ሰውን ከጠላቱ ለመጠበቅ ማረፊያ ሊሆን ይችላል!” ስል በተማፅኖ ጠየቅኩ እነሆ፣ መጋረጃዎቹ ተነሱ፣ መስኮቶቹም ተከፈቱ፣ እና ልጆች እንደ ጨረቃ ፊታቸው የሚያበሩ ከቤቱ ወጡ። ዘንዶው ወደ እኔ ቀረበ እና በጉዳዬ ተስፋ ቆርጬ ነበር። አንዳንድ ልጆች “ወዮላችሁ! ጠላት ወደ እርሱ እየቀረበ ነውና ሁላችሁም ግቡ!" አሉ በቡድን እየተከፋፈሉ ሁሉም ወደ ውስጥ ገቡ እኔም የሞተችውን ህፃን ሴት ልጄን ያዝኩ። ከእነርሱ ጋር ገባች። ስታየኝ አለቀሰች እና በግራ እጇ ቀኝ እጄ ያዘችው ከዛም ቀኝ እጇን ወደ ዘንዶው ዘረጋች እርሱም ለመሸሽ ዞረ። ከዚያም መቀመጫ ሰጠችኝ እና ጭኔ ላይ ተቀመጠች። በቀኝ እጇ ፂሜን እየነካች
< أَلَمْ يَأْنِ لِلَّذِينَ آمَنُوا أَنْ تَخْشَعَ قُلُوبُهُمْ لِذِكْر اللَّهِ فبكيت>
"አባቴ ሆይ ለእነዚያ እምነት ያላቸው አላህን በማውሳት ልቦቻቸው የሚዋረዱበት ጊዜ አልደረሰም?" (57:16)
አለቀስኩና፡- “ልጄ ሆይ ሁላችሁም ቁርኣንን ታውቃላችሁ?” አልኳት። እሷም “አባቴ ሆይ ከአንተ የበለጠ እናውቃለን!” አለችኝ። “ሊያጠፋኝ ስለሚፈልገው ዘንዶ ንገሪኝ” አልኳት። እሷም “መጥፎ ስራዎችህ በጀሀነም እሳት ሊበሉህ ፈለጉ።" በአጠገቤ ስላለፉት አዛውንት ንገሪኝ አልኳት። እሷም "አባቴ ሆይ ይህ የአንተን መጥፎ ስራ ማሸነፍ እስኪያቅተው የተዳከመው ጥሩ (የፅድቅ) ስራህ ነው። እኔም "ልጄ ሆይ በዚህ ተራራ ምን ታደርጊያለሽ?" አልኳት። እሷም "እኛ ለአቅመ አዳም ሳንደርስ ወደዚህ አለም የተሸጋገርን የሙስሊም ልጆች ነን ሰአቲቱ እስክትቆም ድረስ በዚህ እንኖራለን።" ይህን አስፈሪ ክስተት በልቤ ያዝኩና ከነበርኩበት የወንጀል እንቅልፍ ነቃሁ እናም ወደ ሁሉን ቻይ ወደ ሆነው አላህ ንሰሀ ገባሁ። የንሰሃዬ ምክንያት ይህ ነው..
ይቀጥላል...
@abduftsemier
@abduftsemier
>>Click here to continue<<