TG Telegram Group Link
Channel: ዩዘርሲፍ
Back to Bottom
Channel created
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
╭─┅───══───┅─╮
ከሌላ ወንድ በዚና ያረገዘችውን ልጅ
ባሏ ቤት ይዛው የገባችዋ ሙሽራ
╰─┅───══───┅─╯

ባል ምንም በማያውቀው ሁኔታ ከቤቱ የመጣችዋ ሙሽራ ለመውለድ ጥቂት ቀን የቀራት እርጉዝ ነች። ልጅቷም እስከዛ ቀን ድረስ የደበቀችው ሚስጥር አሁን ከአሏህ ቀጥሎ በባል እጅ ወድቆባታል። ባል ምን አይነት እርምጃ ይወስድ ይሆን? ብለው መጠየቅዎ አልቀረም።

ባል ይሄንን ጉድ እንዳየ የልጅቷን ገበና ማንም እንዳያውቅባት ከሰው ነጥሎ አስቀመጣት። የመውለጃዋ ስአት ሲደርስም በሚስጥር ጎረቤት ዘመድ አዝማድ ጭምር ሳያውቁ እንድትወልድ ካደረገ በኋላ የተወለደውን ህፃን ልጅ ታቅፎ በድብቅ ወደ መስጂድ ያመራና ሁሉም ሰላት ላይ በቆሙበት ስአት ሰው ሳያየው ልጁን መስጂዱ ደጃፍ አስቀምጦት ወደ ውስጥ ገባ። ሰላቱ ተጠናቆ ሰው መውጣት ሲጀምር የተጣለ ህፃን ልጅ ከበረንዳው ተቀምጧል። ጀመአው በጣም አዝኖ ከበው ያዩታል ያኔ ባልየው ያስቀመጠውን ሀፃን እንደማያውቅ ሁኖ ከተቀመጠበት አንስቶ የመስጂዱን ጀመዓ እንዲያሳድጉት በየተራ ይጠይቃቸው ጀመር። እነሱም ምክንያታቸውን በመደርደር ፍቃደኛ እንዳልሆኑ ይገልፁለታል። እሱም በቃ ልጁን እኔ ወስጄ ማሳደግ እፈልጋለሁ ግን እንደምታውቁት ባለቤቴ ሙሽራ ስለሆነች ሂዳችሁ ፍቃዷን ጠይቁልኝ በማለት አንገቷን የሚያስደፋትን ገበና በመሸሸግ ጭራሽ ተለምና እባክሽ ይሄንን ልጅ ባልሽ ማሳደግ ይፈልጋልና እሽ በይው ብታሳድጉት አጅር ከአላህ ዘንድ ታገኙበታላችሁ ተብላ ተለምና ልጇን እንድትቀበል በማድረግ ከዱላ ብትር በላይ በሚያም በደሏን በመልካምነት ቀይሮ በወንጀሏ ተፀፅታ ወደ አሏህ እንድትመለስ ያደረገ ባል…

ሱብሀንአላህ ብዙ እህቶች ወደ አልባሌ ቦታ የሚገኙት ገበናቸውን የሚሸፍን ቤተሰብ ሲጠፋ በዛው ጉዞ ይጀመራል ሸሪአዊ ሁክሙን ለኡለሞች በመተው ምድር እንደነዚህ አይነትም ደጋግ ሰዎችን አቅፋ መያዟን ለናንተ ማካፈል ወደድኩ።
ስንቶቻችን ነን በየ ቤታችን በቀላሉ በጥበብ በፍቅርና በሆደ ሰፊነት ሊፈቱ የሚችሉትን ጉዳዮች በእሳት ላይ የባሰ ቤንዚን አርከፍክፈን ወደማያልቅ ጦርነት ውስጥ የገባነው?
አላህ የችግሮችን ሁሉ መፍቻ ትዕግስቱንና ጥበቡን ይወፍቀን!!
#Share

@yuzersef_1
Forwarded from LIJ MUAZ (ⓁⒾⒿ ⓊⒶⓏ) via @Qualitymovbot
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
ዩዘርሲፍ pinned Deleted message
Forwarded from LIJ MUAZ (ISLAM)
Forwarded from LIJ MUAZ (ISLAM)
አዲስ ቪድዮ ተለቋል ገባ ገባ በሉ
https://youtu.be/ZnDgtScbegQ
HTML Embed Code:
2024/06/09 11:42:33
Back to Top