TG Telegram Group Link
Channel: ውብ ታሪኮች ®
Back to Bottom
ራቢዓና እናቷ ከመሃል ኸው

ለትና ሲሃም ደግሞ ከኋላ ሆነው መንገድ እየጠቆማቸው ወደ ቤት ሲሄዱ ኢልያስ ስለ ሲሃም አባት ያስባል። ሁለ ነገራቸው ይገርመዋል። ሁልጊዜ ባገኙት ቁጥር አስተቃቀፋቸው እንደ አባት ነው። ተቀምጦ እስከሚነሱ ድረስ እንቅስቃሴውን ይከታተላሉ። ከሳቸው ጋር ያለው ቅርርብ ያን ያክል ቢሆንም እንክብካቤያቸው፣ የሚያሳዩት ትህትና፣ አቀራረባቸው፣ ፈገግታቸው ግን እንዳሳደጉትና ለረዥም ጊዜ እንደሚያውቁት ዓይነት ነው። የምግብ አጎራረሱን ጭምር ስለሚከታተሉት በተደጋጋሚ አይን ለአይን ሲጋጩ ባዶ ፈገግታ ለማሳየት ተገዷል።

" ከኔ የፈለጉት የሆነ ነገርማ አለ።" እያለ ሲያስብ አንድ ሰው ከፊት ለፊቱ ተመለከተ። ለመጓጓዣ የሚጠቀምባትን አህያውን ከመጠን በላይ ጭኗት ታቃስታለች። የጋለባት ፈረስም እንደደካማት ከአፏ የሚወጣው የበዛ ምራቅ ያስታውቃል። ኢልያስ የአህያዋንና የፈረሱን ድካም አይቶ ከልቡ አዘነ። እንዴት በእንስሣት ይጨክናሉ።

ለራሳቸው ተደላድለው እንዴት እንስሶቹን ይጎዳሉ በማለት ከራሱ ጋር ማውራት ጀመረ። ይህንኑ ለሰውዬው ለመንገር በማመንታት ላይ ሳለ ሰውዬው አልፈውት ሄዱ። ኢልያስ ሰውዬውን ባለመናገሩ ና በእንስሣቶቹ ላይ የደረሰውን በደል እያብሰለሰለ በራሱ መቆጨት ጨመረ። ቁጭቱ እያብከነከነው #ሁለተኛ በኸይር ሥራ ላይ ለደቂቃ ወደ ኋላ ላለማለት ለራሱ ቃል ገባ።

ሲሃም ኢልያስን በፍቅር እየተመለከተችው ነበር። ሲሃም አጅነቢ የሆነ ወንድን መመልከት ሐራም መሆኑን ብታውቅም ኢልያስ ጋር ስትሆን ግን ትረሳዋለች። አታስታውሰውም።
እሱ ሲሄድ ነው " አስተግፊሩላህ" የምትለው።
ጓዟቸውን ቀጥለው በመሀል " እንዴት አይነት ወንድም ነው ያለሽ?" አለቻት።
" እንዳየሽው አይነት" አለች ኸውለት እየሳቀች።
" እድለኛ ነሽ።" አለቻት በፈገግታ
" አይዞሽ አንቺም እድለኛ ነሽ ያንቺስ ወንድም አይደል እንዴ?" ስትላት ፈገግታዋ በቅፅበት ጠፍቶ መሬት መሬት እያየች ዝም አለች።

.
ወደ ቤት ሲገባ የሲሃም አባትና እናት ከትንንሽ ልጆቻቸው ጋር ቆመው እየጠበቋቸው ነበር። ሰላም ከተባባሉ በኋላ ወደ አዲሱ ቤት በዱዓ ገቡ፤ ገና ከበር ሲገቡ እጃቸውን እየታጠቡ ነበር የገቡት። ሴቶች ጓዳ፣ ወንዶቹ ሳሎን ሆነው ምግብ ተመገቡ። ሸህ ዐብዱ ከሚያውቁት ምግብ የማያውቁት ምግብ በዝቶባቸው ስለነበር በሲሃም አባት ገላፃ ነበር የሚጣፍጠውን ምግብ የበሉት።
" ኢልያስ እየበላህ።" ትለዋለችው ሲሃም በተደጋጋሚ በፍርሃት ድምፅ

" አብሽር እየበላሁ ነው።" ይላታል። ሲሃም ጓደኛዋ ኸውለት መሆኗን የረሳች እስኪመስልባት ድረስ የጎደለውን ነገር በላይ በላይ እየጨመረችለት አስተናገደችው።

ከምግብ በኋላ ቡና እየጠጡ ስለልጆች አስተዳደግ፣ ስለ ቁርዐን፣ ስለ ነብዩ [ሰ.ዐ.ወ] ስለተለያዩ የዓለም ሀገራት፣ ስለ ትምህርት፣ ስለ ትዳር፣ ስለ ዘካ፣ ስለ ብዙ ነገር እየተቀባበሉ ሲያወሩ አመሹ።

የሲሃም አባት ኢልያስን እንደተለመደው በአትኩሮት እየተከታተሉት ነው። በንግግር አደቡ፣ ለቤተሰቦቹ በሚያሳየው ትህትናና በፍቅሩ ስለሚገረሙ ለሱ አጸፋዊ የሀፍረት እይታ ሳይጨነቁ ያጤኑታል። ምግብ ሲበላ ከአቀማመጡ እስከ አነሳሱ ያዩታል። በተለይ በተለይ በጣም ያስደነቃቸው ሲሃም ሽር ጉድ እያለች ስታስተናግደው ቀና ብሎ እሷን ያለማየቱ ነው።
" የጨዋነትን ትርጉም ዛሬ ገና አየሁት።" አሉ በሃሳባቸው።
በሳቸው ተደጋጋሚ እይታ የተነሳ አንገቱን ለመድፋት ለተገደደው ኢልያስ
" አይዞህ ልጄ! ሁሉ ነገርህን ተደንቄበት ነው! ለጥሩ ነገርም እያሰብኩህ ስለሆነ ነው።" ይሉታል በሃሳባቸው።
ስለ አምስት የኢስላም ማዕዘናትና ስለስድስቱ የኢማን ማዕዘናት የነሱን ጥያቄ እየመለሱ ሸህ ዐብዱ በቂ ገለጻ አደረጉላቸው። ቀጥለው
" እናንተ በአላህ አምናችኋል፤ ሶላት እየሰገዳችሁ ነው፤ ትፆማላችሁ፤ ሁለት ነገር ግን ይቀራችኋል፤ ዘካ መስጠት እና ሀጅ ማድረግ።"

" እንደነገራችሁኝ ዘካ አውጥታችሁ አታውቁም፤ ቅድም በሰፊው እንደነገርኳችሁ ዘካ ገንዘብን ያበዛል። ይጠብቃል። ድሆች ለኛ ጥሩ ስሜት እንዲኖራቸው ያደርጋል፤ ብዙ እህት ወንድሞቻችንን ከጭንቀት ይገላግላል፤ ዘካ ገንዘብን ከማጥራቱ ጋር ለአላህ ርህራሄና ችሮታ ምክንያት ነው። በተጨማሪም ምፅዋት የሚሰጥ ሰው በትንሳኤ ቀን ከመልካም ጥላው ስር አላህ ያስጠልለዋል።"

" ዘካ የማይሰጥ ሰው ነገ የራሱ ገንዘብ እሳትና የሚናደፍ እባብ ሆኖበት አላህ ይቀጣዋል።" አላህ ይጠብቀንና አሉ ሸህ ዐብዱ።
የሲሃም እናትና አባት አንገታቸውን ደፍተው ያዳምጣሉ። በተለይ አባቷ ስሜታቸው ተለውጦ በትካዜ ነበር የሚያዳምጡት።

" ለማንኛውም ከዚህ በፊት ዘካ ሰጥታችሁ ባታውቁም በጥሩ ሁኔታ ዘካን አስልተው የሚያቀርቡ የሂሳብ ባላሙያዎች አሉ እነሱን አስተዋውቃችኋለሁ" አሏቸው። የሲሃም አባት ቀና ሳይሉ " ዱኒያን እንዲህ አሳምሬያት አኼራዬን አበላሽቻት ነበር። ይኼ ሁሉ ሀብት የራሴ ሁኖ በኋላ በራሴ ላይ ሊመሰክርብኝ?" አሉ በጣም በደከመ ድምፅ።
" አሁን ይኼን ሁሉ ወንጀል ይዤ ብሞትስ?"
ቀና ብለው " ያ አላህ ሞት አልፈራም ነበር፤ አሁን ግን ፈራሁ። ምክንያቱም ያስቀደምኩት ምንም ኸይር ሥራ የለምና ነው"
" አሁን እንዴት ነው ዘካ የምሰጠው? ማለት ከመቼ ጀምሮ?" አሉ። ሂሳቡ አስቸጋሪ መሆኑን እያሰቡ
" አንተ ቅድም በነገርኩህ መስፈርት መሰረት ግዴታ ይሆንብሻል ብለህ የምታስበውን ጊዜ አስታውስ" አሉት
" እረ ይከብዳል?" አሉ።
" ለሂሳቡ አትጨነቅ! ልጆቹ ከዚህ በላይ ውስብስብ የሆነ ሥራም ይሰራሉ ብቻ አንተ ዓመቱን አስታውስ"
" ኢንሻአላህ" አሉ።
ሲጨዋወቱ አምሽተው በስተመጨረሻ ሊሄዱ ሲሉ የሲሃም አባት " እኔ አንድ ሀሳብ አለኝ?" አሉ፤ ሁሉም ወደሳቸው ሲዞሩ
" እናንተ ሀጅ ዋጅብ ሁኖባችኋል ብላችሁናል። እኔ ደግሞ በመጭው ረመዳን ይሄው የሁለታችንንም ቤተሰብ ሀጅ ማስደረግ እፈልጋለሁ እላችኋለሁ።" አሉ።
ሁሉም ተገርመው አዩዋቸው!
" አላህ ሰዎችን የሚያገኛቸው ለበጎ ነው ብላችኋል። ስለዚህ ፍላጎቴን እንዳትቃረኑ። የኔንም የናንተንም ቤተሰብ በአንድ ጠቅልለን ወደ አላህ ቤት እንሄዳለን።" አሏቸው።

የኢልያስ ቤተሰቦች በደስታ " ኢንሻአላህ" ሲሉ ሲሃም ደስ አላት። ማትሪክ ያለፈች ነበር የመሰላት። ከኢልያስ አጠገብ ሁና ሀጅ ማድረግን ስታስብ ደስታ ወረራት። ብቻውን የምታገኝበት አጋጣሚ መሆኑን ስታስብ ደግሞ እዛው አግብታው የምትመለስ መሰላት። ደስታዋ ገደብ አልነበረውም። ኢልያስም ደስ አለው። ሁሉም ተነስተው በደስታ እርስ በርስ ተቃቀፉ። ሲሃም ሃውለትንም ራቢዓንም በደስታ ስማቸው ዘወር ስትል ኢልያስን አባቷ ግንባሩን ስመውት ወደሷ ሲዞር ተገጣጠሙ። ሲሃም ላቧ ግጥም አለ። ለማቀፍ ያነሳችውን እጇን ቀስ ብላ አወረድችው። ኢልያስም ፈገግታዋን ሲያይ የጠዋት ፀሀይ ፊት ለፊቱ የወጣች ነበር የመሰለው። ለምን እንደሆነ ሳያውቀው አንገቱን ሰበረ።

ሲሃም አገጩን ይዛ ቀና ማድረግ አማራት።
በዝምታ ኢልያስ መሬቱን ሲሃም እሱን እያዩ ቆሙ።
" ይሄ ነገርህ እኮ ነው የሚገለኝ። አንድ የፍቅር ቃል እንኳን ቢወጣህ ምን አለበት?" አለች በ

ምሬት ለራሷ። በቤተሰቦቹ መሀል እሷን ማናገር ያልፈለገው ኢልያስም " ሲሃምዬ ያለመደብኝን በሰው መሀል እንዴት ላናግርሽ?" እያለ ሲያስብ እናቱ መጥተው በደስታ ሲያቅፉት ሲሃም በንዴት ወደጓዳ ገባች። በአይኑ እየሸኛት
" ስሜትሽ ስሜቴ መሆ
ኑን ማን በነገረሽ።" እያለ በ

ሆዱ።
በመጨረሻ የኢሻን ሶላት ሰግደው ተሰነባበቱ።
የኢልያስ ስልክ ጠራ። አነሳው።
" ኢልያስዬ"
" አቤት"
" አወከኝ?"
" አዎ አውቄሻለሁ"
" ሃሳብህን አልቀየርክም?"
" ሀሳብ ያለው ሰው ነው ሀሳብ የሚቀይረው"
" ቆይ ሰው አያሳዝንህም?"
" ወደ መጥፎ ቦታ ሲሄድ፣ ሐራም ሲሠራ ያሳዝነኛል"
" ሰው ሲያለቅሥስ?"
" ጀሀነምን ፈርቶ ወንጀሉን አስቦ ሲያለቅስ ያሳዝነኛል። ያስለቅሰኛልም።"
ዝም አለች። " ያንተ ሲሪየስ መሆን ፍቅሬን የባስ እያናረው ነው። ትሰማኛለህ? ዛሬ ላገኝህ እፈልጋለሁ። ዛሬ ኮስፒ ሆቴል መጥተህ ካላገኘሁህ ራሴን አጠፋለሁ።" ኢልያስ ደነገጠ

" ራሴን ከማጥፋቴ በፊት ግን ደብዳቤ ፅፌ አንተ እንደገደልከኝ እናዘዛለሁ።" ብላው ስልኩን ዘጋችው።
ዘወር ዘወር ብሎ አየ። አጠገቡ ማንም የለም። በድንጋጤ አልጋው ላይ ዘፍ ብሎ በጭንቀት መብሰልሰል ያዘ........


ክፍል-42 ይቀጥላል #ሼር / እንወዳችኋለን❤️

ቻናላችንን ይቀላቀሉ፡ @WubTarikoch
ለሀሳብና አስተያየት፡ @WubTarikoch_bot
°° ካምባስና ፍቅር °°
ክፍል-42 / ልብ-ወለድ


..... በእድሜውም ሆነ በስፋቱ ትልቅ የሆነው የአንዋር መስጂድ ዙሪያውን ኢስላማዊ ቁሳቁሶች ይሸጡበታል። ከኮፊያ እስከ ጀለቢያ፣ ከሙሰቢሀ እስከ ሽቶ፣ ከመስገጃ እስከ ምንጣፍና አበያ በየአይነቱ አለ። አራት በሮች ያሉት አንዋር መስጂድ እጅግ ብዙ ሰዎችን ማስተናገድ የሚችል ሰፊ የመስጊድ ክፍል እንዲሁም ግቢ አለው።

ለሰጋጆች ሁሉ ነገር በተሟላበት በዚህ መስጂድ ውስጥ ሸህ ዐብዱና የሲሃም አባት በቀጠሯቸው ሰዓት ተገናኝተዋል። የአስርን ሶላት አብረው ከሰገዱ በኋላ ከመስጂዱ አንደኛው ጥግ ተቀመጡ። ዱኒያዊ ነገር እንደሚያወሩ የገመቱት ሸህ ዐብዱ በእሳቸው ገፋፊነት በመስጊዱ ዋና በር አካባቢ ወደሚገኘው የሳቸው ሱቅ ወሰዷቸው። ሱቃቸው ውስጥ ገብተው አንዳንድ ወሬዎችን ሲያወሩ ቆይተው
" አሁን ልሰማህ ዝግጁ ነኝ የፈለክብኝን ጉዳይ ልትነግረኝ ትችላለህ።" አሉ ሸህ ዐብዱ ወሬውን ለመጀመር ያላቸውን ጉጉት አይተው።

የሲሃም አባት ፈራ ተባ ይላሉ፤ የሸህ ዐብዱን አይን ማየት ፈሩ፤ እጃቸውን ያሻሻሉ፤ " ግዴለም ወንድሜ ንገረኝ። አትጨነቅ። አላህ ለሁሉም አለበት" አሏቸው ሸህ ዐብዱ ፍርሃታቸው ስለገባቸው።
" እውነትም አላህ አለበት!" አሉ በሆዳቸው።
" ምን መሰለህ"
" ማለቴ እናንተ ያላችሁን የዲን ፍቅር ተመልክቻለሁ። ከእናንተ አልፋችሁ ለኛም መስተካከል ሰበብ ሆናችኋል። አላህ ጀዛችሁን ይክፈላችሁ።"
" አሚን" አሉ ሸህ ዐብዱ ባልተቆጠበ አትኩሮት
" ይሄ ቅርርባችን የማያለያየን እንዲሆን ማለቴ እንዳንራራቅ እፈልጋለሁ"
አሏቸው።
ሸህ ዐብዱም " ኢንሻአላህ በአላህ ፈቃድ መቼም አንራራቅም። በየጊዜው እንተዋወሳለን" አሏቸው።

" ለማለት የፈለግኩት ግንኙነታችንን ቤተሰባዊ እናድርገው ማለቴ ነው" ብለው ጎንበስ አሉ።
" ማለት?" አሉ ሸህ ዐብዱ ነገሩ እንዳልገባቸው በሚያስመስል የፊት ገፅታ።
" ማለቴ ልጅህን ለልጄ...." ብለው ሳይጨርሱት ወደመሬት አቀረቀሩ። ጥቂት ዝምታ በመካከላቸው ሰፈነ።

የሲሃም አባት ከባህል ውጪ የወንድ ቤተሰብን የሴት ቤተሰብ ለትዳር መጠየቁ የሰሃባን ዘመን አስታወሳቸው። እንዳያፍሩ ስለሰጉ ፈጠን ብለው

" አይ ወንድሜ! ታዲያ አላህ የወደደውን ነገር ለመጠየቅ ምን አስፈራህ?" አሏቸው። ዝም አሉ የሲሃም አባት።

" ለማንኛውም ነገሩን እኔም ሳላስበው የቀረሁ ቢሆን ኖሮ በፈራህ ነበር" ሲሏቸው። ካጎነበሱበት በግርምት ቀና አሉ። ጭንቅላታቸውን ላይና ታች እያነቃነቁ

" እኔም አስቤው ነበር። ልነግርህ ጊዜ ስጠብቅ ነው አንተ የቀደምከኝ።" አሏቸው። የሲሃም አባት በደስታ ብዛት ሄደው ሲያቅፏቸው ከመደርደሪያው ጋር ተጋጩ። የተሰቀለው መስገጃ ሁሉ እነሱ ላይ ወረደባቸው።
ተነስተው መስገጃውን አስተካክለው በጋራ እየሰቀሉ ሳለ
" ያ አላህ ስንት ውለታ ነው የምትውልልኝ? ያለኝን ሀብት የሚያስንቅ ሌላ ሀብት ሰጠኸኝ? አልሀምዱሊላህ።" አሉ።
" አላህ ተመላሾችን ይወዳቸዋል" አሏቸው ሸህ ዐብዱ።
ከዚያ ስለ ብዙ ነገር እያወሩ ከእሳቸው ሀብት አንጻር እዚህ ግባ የማትባለዋን የሸህ ዐብዱን ሱቅ እየቃኙ

" በል በልጅህ በኩል ጨርስ! የኔ ልጅ ከትዕዛዜ ንቅንቅ አትልም" አሏቸው
" ወዴት ወዴት ነው? የማን ልጅ ታዛዥ አይደለም ለማለት ነው?" አሏቸውና ሳቁ።

" ለማንኛውም" አሉ ሸህ ዐብዱ

" ሁለቱም በራሳቸው ላይ የመወሰኛ እድሜ ላይ ስላሉ ውሳኔውን ለራሳቸው እንተዋለን። አላህ ግን ያሳካዋል ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ። ምክንያቱም እኛ መሰረት ያደረግነው ሀብት፣ ቁንጅና፣ ወይ ታዋቂነት ሳይሆን ዲን ነው። ይሄ ደግሞ አላህ የሚወደው ነገር ነው። እሱ የሚወደውን ነገር ስናደርግ ደግሞ እንደሚረዳን አልጠራጠርም።" አሏቸው።

" አላህ ይርዳን።" የሲሃም አባት ስልካቸው ጮኸ። ኪስ ውስጥ ያለ ትንሽ ቁርዐን የሚያክል ስልካቸውን አውጥተው በማይገባ ቋንቋ ማናገር ጀመሩ።
" የወደፊት አማቼ ደግሞ ምን አመጣህብኝ?" አሉት አናግረው ሲጨርሱ።

" ፈረንሰኛ ነው። የተበላሸች ፋብሪካ ስለነበረችኝ እሷን ለማሰራት ያመጣኋቸውን ባለሙያዎች እያናገርኩ ነበር።" አሉት።
በመጨረሻ ለሌላ ጊዜ ቀጠሮ ይዘው በአደራ ተለያዩ።

ኢልያስ ጨንቆታል። የቀጠሯቸው ሰዓት ደርሷል። ከአያያዟ ራሷን ለማጥፋት እንደማትመለስ አስቧል። አደገኛ ፍቅር ውስጥም እንደገባች ተገንዝቧል።

" እንደፈለገች ትሁን እንጂ አልሄድም። ወንድና ሴት እንዲህ አይነት ቦታ ላይ ብቻቸውን መገናኘት የለባቸውም።"
ጥቂት አሰበና " ለምን ታዲያ ሁለት ሁነን አንሄድም?"
" ምን በወጣኝ ብዬ እሄዳለሁ"
" አሃ? ራሷን ብታጠፋስ? በዚያ ላይ የኔን ስም እገልጻለሁ ብላለች"
" እኔን ብትጽፍ ደግሞ ለጥቂት ጊዜም ቢሆን ከትምህርቴ ያስተጓጉለኛል። " እረ ያ አላህ ከዚህ ጉድ አውጣን"
" ቆይ አሁን ምን ላድርግ?"
" ከዚህ ሁሉ ጉድ ብሄድስ?" ብሎ ዘሎ ተነሳ።
ሸሚዙን ቀይሮ ጃኬት ለብሶ ከዶርም ወጣ። ብዙ ሃሳብ ያብሰለስላል።

" ለነገሩ ራስ ማጥፋት ሀራም መሆኑን አስረድትሃት፣ ደግሞ እንዲህ ማድረግ እንደሌለባት ነግረሃት ትመለሳለህ" ይለዋል ሸይጧን።
" ሁኔታዋ ግን በዚህ ብቻ የምትለቀኝ አያስመስልም። ቢቀርብኝ ይሻላል" ብሎ ቆመ።
" ልሂድ አልሂድ?"
" ቆይ ሽወዳ ቢሆንስ? እረ እያለቀሱ ሽወዳ የለም?"
ሲወዛገብ ቆይቶ የወንድና የሴት ዶርም መገንጠያ አጥር ጋር ሲደርስ...


ክፍል-43 ይቀጥላል #ሼር / እንወዳችኋለን❤️

ቻናላችንን ይቀላቀሉ፡ @WubTarikoch
ለሀሳብና አስተያየት፡ @WubTarikoch_bot
°° ካምባስና ፍቅር °°
ክፍል-43 / ልብ-ወለድ


............ " አላህ እያየኝ አይደለም እንዴ?" አለ በድንጋጤ። አላህ ያልወደደውን ነገር ለማድረግ መንቀሳቀሱ በሀፍረት አሸማቀቀው።

" አላህ ይታዘበኛል ይቅርብኝ።" ብሎ ወዲያውኑ በፍጥነት ተመለሰ። አላህ ከፈተና ስለጠበቀውም " አልሀምዱሊላህ" አለ።
ዶርም ሲገባ ስልኩ ጮኸ። አነሳው።
" ምነው ቀረህ እንዴ?"
" አንቺ ልጅ አላህን ፍሪ አልመጣም" አላት።
ልጅቱ " ሁኔታህን 4ኛ ፎቅ ዶርማችን ላይ ሁኜ ከሩቅ እያየሁ ነበር። እኔ ጋር ለመምጣት አስበህ ተዘጋጅተህ ኋላ ግን ተመለስክ። በጣም ጠንካራ ልጅ ነህ። አትጨነቅ። እየቀለድኩብህ ነበር። ፈተናዬን በማለፍ ጉብዝናህን አስመስክረሃል።"

" ኡፍፍፍፍፍፍፍፍፍፍ! " አለ
" ዶርም አንተን ቀጥሬ አገኝሀለሁ ብዬ ተወራርጄ ስለነበር ነው። አልተሳካልኝም። ወንድ ሲያሸንፈኝ ለመጀመሪያ ጊዜ! ለማንኛውም ባህሪህን በዚሁ ቀጥልበት።" አለቺው።
" ስልኩን ከመዝጋቴ በፊት ምን እንዳስመለሰህ ትነግረኛለህ?" አለቺው
" የሰማየ ሰማያት ፈጣሪ አላህ እንደሚያየኝ ትዝ ሲለኝ ተመለስኩ" አላት።
" ይገርማል። በዚህ ወቅት እንዳንተ አይነት ወንድ ማግኘት ይከብዳል። ባህሪህ ይገርማል።
ኢልያስ አንድ ነገር የመጨረሻ?" አለችው
" ምንድን ነው?"
" ምን መሰለህ። እውነቱን ለመናገር ብዙ ጊዜ አንገትህን ደፍተህ ነው የማይህ። ሁሉም ሰው በጸባይህ የሚማረክብህ ቢሆንም አንተ ግን የምትፈልጋቸውን ብዙ ነገሮች በሰው ይሉኝታ ብቻ ላታፈርጋቸው ትችላለህ። ወንድ ነህ። ስሜት አለህ። ብዙ ነገት ትመኛለህ። ካምፓስም ስለጨረስን የፈለከው ቦታ ሁነህ አንድ ቀን ደውልልኝ አስደስትሃለሁ።" ብላ ስልኩን ዘጋችው።

" አስተግፊሩላህ" " አስተግፊሩላህ" " አስተግፊሩላህ" አለ ኢልያስ።
ስልኩን አጠፋና አልጋው ላይ ደገፍ አለ። ስለ መመረቂያ ጽሑፍ ለማሰብ ቢፈልግም አልሆነለትም። ስለ ምርቃት ላስብ ቢል በየት ብሎ! ሸይጧን በጣም ይወሰውሰው ገባ።

" እውነቷን ነው። አንተም ስሜት አለህ። አንድ ጊዜ ብትሳሳትም ትቶብታለህ ምን ችግር አለው። አላህ እድሜ ልኳን ዚና ስትሰራ የኖረች ሴትን በጫማዋ ከጉድጓድ ውሃ አውጥታ ውሻ በማጠጣቷ ምሯት የለም እንዴ እንኳን አንተን የመሰለ አላህን ፈሪ! ስለዚህ ኢልያስ ደውልላት።" ይለዋል ሸይጧን

" አስተግፊሩላህ" " አስተግፊሩላህ" ኢልያስ አልጋው ላይ ከግራና ከቀኝ እየተዟዟረ ይህን ዚክር ይደጋግማል።

" ተው ኢልያስ ይህ እድል አያምልጥህ። ቤትህ ድረስ የመጣ ሲሳይህን ገፍተህ አታባረው። በዚያ ላይ ማንም አያይህም። ከግቢ ራቅ ያለ አካባቢ ቅጠራት። በዚያውም ወደፊት ሲሃምን ስለምታገባ እሷ ፊት እንዳታፍር ከአሁኑ ብትለማመድ የተሻለ ነው።" ሸይጧን ጉትጎታውን አላቋረጠም።

" አኡዙ ቢላሂ ሚነሸይጧኒሮጂም" " አኡዙ ቢላሂ ሚነሸይጧኒሮጂም" ይላል ኢልያስ ሀሳቡን ወደ ሌላ ማድረግ የፈለገ ቢሆንም ፍጹም ዳገት ነው የሆነበት። ሸይጧን አለቀቀውም።

" ተው ኢልያስ እፍረት አይያዝህ ትፈልጋለህ እኮ? ግቢ ካለቀ በኋላ ለአንድ ጊዜም ለመጨረሻ ጊዜም ስለማታያት ሴት ምን አስጨነቀህ? እርግዝናም ሊያስጨነቅህ አይገባም ብዙ መከላከያ ትጠቀማለህ? በዚያ ላይ ልምድን የመሰለ ትምህርት በዚህ ምድር ላይ የለም።"

ኢልያስ ከተኛበት አልጋ ላይ ተነሳ። " የት ልሂድ? አዎ ውዱእ ላድርግ።" ብሎ ከዶርም ወጣ። ውዱእ አድርጎ ሲመለስ አንዋር ስልክ ሲያወራ አገኘው።

" ሴቶች ጋር ከጋብቻ በፊት ነገር የጀመረና ያልጀመረ ትዳርን እኩል አያጣጥሙትም። ትዳር ግማሽ ኢማንን የሚሞላ ሲሆን ከትዳር በፊት ያለ ግንኙነት ግን ሙሉ ኢማንን የሚያጠፋ ነው። አላህ ይጠብቀንና ደግሞ ስርቆትና ዚና ሱስ ይሆናል ሲባል ሰምቻለሁ። ስለዚህ ራሳችንን በማንኛውም ዋጋ ከሸይጧንና ከነፍስ ጉትጎታ መጠበቅ አለብን።" ይላል በስልክ ከሚያወራው ጓደኛው ጋር።

ኢልያስን ወደ አዕምሮው የተመለሱት አረፍተ ነገሮች ነበሩ። " አልሀምዱሊላህ ሳታውቅ መከርከኝ አላህ ይስጥህ" ብሎ መረቀው በልቡ።

መስገጃ ከአልጋው ላይ እያነሳ " እውነትም ሙስሊም የሚጠነክረው በወንድሙ ነው። ሸይጧን ሀሳቤን ሲሸራርፍብኝ ከአቋሜ ሲያዛንፈኝ ይታወቀኝ ነበር። አላህ ከሴት ፈተና እኔንም እናንተንም ይጠብቀን" እያለ ሱነተል ውዱዕ ሊሰግድ መስገጃውን አነጠፈ።
ከመጀመሩ በፊት ስልኩን አወጣና የተደወለበትን ቁጥር ሊያጠፋ ሲል

" ተወው ኢልያስ ለምን ታጠፋዋለህ? ባትደውልላትም ይቀመጥ ምክንያቱም ልጅቱ ሀራም ነገር ላይ ልትወድቅ ስለምትችል ትመክራታለህ። በዚህም የተነሳ አጅርም ታገኛለህ።" ይለዋል ሸይጧን

ኢልያስ ለራሱ " ሸይጧን እውነትም በሰው ልጆች ደም ውስጥ ነው የሚዘዋወረው" ያሉት ረሱል [ሰ.ዐ.ወ] ሀቅ ነው። ሱብሃን አላህ። አንተ ለቀላል ሰው አትመለሰም። አሁን ግን የአላህን ባሪያ ለማሳሳት አልተቻለህም።" ብሎ ስልኳን ከስልኩ ላይ አጠፋ። ደግማ የሱ ስልክ ላይ እንዳትደውልም ሞባይሉ ላይ ወደእሱ ስልክ መደወል ከማይፈቅርድላቸው ስልኮች ተርታ እሷንም ጻፋት። አላሁ አክበር.... የውዱዕ ሱና ጀመረ።

የሲሃም አባት ካለወትሯቸው ቤት በጊዜ መጥተዋል። ያሰቡትን ሃሳብ ለባለቤታቸው ለመናገር። ባለቤታቸውን አስጠርተው ከተቀመጡ በኋላ ሀሳባቸውን ነገሯቸው። ባለቤታቸው በደስታ ስሜት እሳቸውም ማሰባቸውን ነገር ግን ለመናገር አለመድፈራቸውን ገለጹላቸው፤ የሲሃም አባት ተደሰቱ። ነገሩ ሁሉ አልጋ ባልጋ የሆነላቸው መሰላቸው። ቀጥለው
" ለሲሃሜ እንዴት ልንገራት?" አሉ።
" እርሷ ላንተ ታዛዥ ናት። የጠየቅካትን በፍጥነት ስለምታደርግ ይሄን ሀሳብ የምትቃወም አይመስለኝም" አሉ እናትዬዋ
" ለኔ ታዛዥ እንደሆነች ባውቅም ይሄ እስከዛሬ ከጠየኳት ወይም ካዘዝኳት የተለየ ነው። ህይወቷን የሚመለከት እና የኔ ግፊት እሷ ካላመነችበት በስተቀር የማይሰራበት ነው። እስኪ አላህ ይርዳኝ"
" ቤት አለች እንዴ?" አሉ
" አዎ አለች"
" እስኪ ዱዓ አድርጊልኝ!" ብለው ወደ ሲሃም ክፍል ሲቆርቁሮ ዲያሪዋን አስቀምጣ ተነስታ ከፈተችላቸው.......


ክፍል-44 ይቀጥላል #ሼር / እንወዳችኋለን❤️

ቻናላችንን ይቀላቀሉ፡ @WubTarikoch
ለሀሳብና አስተያየት፡ @WubTarikoch_bot
°° ካምባስና ፍቅር °°
ክፍል-44 / ልብ-ወለድ


... ስመዋት ከተቀመጡ በኋላ ስለ ፈተናዋ፣ ስለ መጽሀፍቶቿ፣ ስለሶላቷ፣ ስለብዙ ነገር እያወሯት ቆዩ።

" አባዬ ክላስ እየመጣህ የምታይብኝ ጊዜ እኮ አሁን ነው የጨመረው ጭራሽ ትተኸኝ ነበር። ኢስላምን ማወቅ ስትጀምር፣ እዚህ እየመጣህ የምነግርህ ሀዲሶች ሲጥሙህ ግን አልሃምዱሊላህ በየቀኑ መምጣት ጀመርክ።" አለቻቸው

ሲሃም አንድ ነገር ገብቷታል። አባቷ ያልተለመደ ባህሪ ያሳያሉ ያነሱትን መጽሀፍ ገልብጠው ይዘው ውጭ ውጪውን ይመለከታሉ። ፈራ ያሉም ይመስላሉ።

" አባየ? ልትነግረኝ የፈለግከው ነገር ካለ ንገረኝ? የምታዘኝ ነገር ካለም ንገረኝ? ትምህርት ስለጨረስኩ አትጨነቅ። ፋብሪካዎቹንም እንድጎበኝ ከሆነ ሁሉንም አይቻቸው እመለሳለሁ" አለቻቸው።
" ነገሩ እንደሱ አይደለም የኔ ልጅ።"
" ታዲያ ምንድን ነው?" አለች ተነስታ አልጋዋ ላይ እየተቀመጠች።

ለመናገር እየፈለጉ ይመስላሉ። ምክንያቱ ደግሞ በጣም ይወዷታል። ያከብሯታል። ምንም ነገር ጠይቀዋት እምቢ አትልም። በእሽታ ትታዘዛቸዋለች። በተለይ በዚህ ዓመት አይናቸውን እንኳን ቀና ብላ ሳታይ ነው የምትታዘዛቸው። " ትቀየመኝ ይሆን?" ብለው ፈርተው ነው። ፊታቸውን ወደ በሩ አዙረው
" የኔ ልጅ ታውቂያለሽ እኔ ዙሪያ ጥምጥም ማለት አላውቅበትም!"
" እኔ በነሸህ ዐብዱ በኩል ያለንን ግንኙነት ባንቺ ማጠናከር እፈልጋለሁ" አሏት።
ፊቷን ጭፍግግ አደረገችውና እንዳልገባት ለማሳየት።

" ማለቴ አንቺ የኢልያስ ሚስት እንድትሆኚ እፈልጋለሁ።" አሏት ወደሷ ዘወር ሳይሉ ግድግዳው ላይ ያለውን የማያውቁትን ቁርዐን ሊያነቡ እየሞከሩ።

በህልሟ ይሁን በዕውኗ አልታወቃትም፤ የሰማችው ነገር ቀልድ ይሁን! የሷ ፍላጎት በአባቷ ተመስሎ የሚናገራት ይሁን አልገባትም። ተደናገጠች፤ የምትይዘው የምትጨብጠውን አጣች፤ በሌላ በኩል ደግሞ ፊቷ በራ፤ በፍጥነት ከአልጋዋ ወርዳ የአባቷን ጉልበት ሳመች።
" አባዬ? አለች። አይኗ እምባ ሞልቷል።

" አስቀየምኩሽ እንዴ የኔ ልጅ? ግዴለሽም ላማክርሽ ብዬ ነው እንጂ አላስገድድሽም" አሏት የሀሳባቸው ተቀባይነት ያለማግኘት እያንገበገባቸው። ያለቀሰችው ሀሳባቸውን ባለመቀበል መሆኑ ስለተሰማቸው።
" አባዬ!" አለች በድጋሜ የሳቸው እቅፍ ውስጥ ገብታ
" የሴት ወጉ ይዞኝ ነው እንጂ እኔም ልነግርህ ሳወጣ ሳወርድ ነበር" አለቻቸው። አባቷ በጣም ተደሰቱ፤ ሳሟት፤ ጥብቅ አድርገውም አቀፏት።
" ምንም ነገር እንዳትለኝ?" አለች ከእቅፋቸው ወጥታ እንባዋን እየጠረገች።
የአባቷ ፊት በደስታ በርቷል።

" ያልከኝን ሁሉ ተግብረው፤ ለሀሳብህ ተገዥ ነኝ" አለቻቸው። አባቷም እሷ ስታለቅስ እሳቸውም አላስችል ብሏቸው አይናቸው እንባ ሞልቶ
" እውነትም አላህን ወደሽ ወደሱ ለመቅረብ እየሞከርሽ ነው። በዚህ ሁኔታ ደግሞ አላህ አይገፋሽም። ሀሳቤን አጠነክራለሁ ለአባቱም ነግሬያቸዋለሁ።" አሏት።
ሲሃም በጥፊ እንደተመታ ሰው ክው ብላ ደነገጠች።
ምን ሊሉ እንደሚችሉ እያሰበች ምን አሉ? አለቻቸው። ምላሷ እየተያየዘባት "እኔም አስቤው ነበር አሉ" ሲሏት ዘላ ጥምጥም አለችባቸው።" አባዬ እድሜ ልኬን ባሪያህ እሆናለሁ" " አይ! አንቺ የኔ ልጅ ነሽ። ለልጂ የምችለውን ከማድረግ ደግሞ አልቆጥብም" አሏት። ከዛ ተንስተው " በይ ዱዓ አድርጊ ይቺን ለመናገር ነው ስራ ትቼ የመጣሁት። ማታ በሰፊው እናወራለን።" ብለው ግንባሯን ስመው ሄዱ።
በጉጉት ሲጠብቁ የነበሩት እናቷ ምን አለችህ? አሏቸው። " ልክ በልጅነቷ አሻንጉሊት ሲገዛላት እንደምታቅፈኝ ይሄንንም ስሠማ መጥታ አቀፈቺኝ። አሏቸው።

" አልሃምዱሊላህ" አሉ እናቷ ወደ ሰማይ ቀና ብለው።
እየሳቁም ይለቀሳል እንዴ? ሲሃም እየሳቀች ታለቅሳለች።
" አላህ ሆይ! ሳልጠይቅህ እኔን ወደ ቀናው ጎዳና መለስከኝ። ይሄንን ያንተን ባሪያ ደግሞ ጠይቄህ አትከልክለኝ። አንተን የሚወድ ቤት ልመስርት። አላህዬ አደራህን ይሄንን ሃሳብ አሳይተህ እንዳነሳኝ። በለቅሶ አላህን ትለምናለች።
ቤታቸው የሚገኘው የግድግዳ ሰዓት አዛን ሲል አቆመች። አዛኑን ሲጨርስ " በአዛን እና በኢቃም መሃል የሚደረግን ዱዓ አላህ ይቀበላል።" የሚለውን የነብዩ [ሰ.ዐ.ወ] ሃዲስ ትዝ አላት። ወደ ቂብላ ዞራ ተንበርክካ አላህን የለመነችውን ደገመችው። " አላህ ሆይ! እንቢ እንዳታስብለኝ። አደራህን የሚወደድ፣ የሚናፈቅ ትዳር የምመሰርተው በኢልያስዬ ጋር ብቻ ነው" ሁልጊዜ ስለ ዲን የሚያወራኝ እሱ ብቻ ነው" በህይወቴም ፍቅር የያዘኝ" ከሱ ብቻ ነው" ፍላጎቴን የሚረዳልኝ" የሚያከብረኝ፣ የሚንከባከበኝ ኢልያስዬ ብቻ ነው። አንተን የሚፈራና በዲን የተሞላ ቤት የሚኖረኝ ከሱ ጋር ብቻ ነው፤ ያረቢ ይህን ልጅ የሰጠኸኝ እንደሆነ ወር ሙሉ እጾማለሁ።" ብላ ተስላ እንባዋን ጠርጋ ለውዱዕ ተንስታ ወጣች።

" በጀነት ይህን አዋጅ የሚናገር ተናጋሪ አለ። ለናንተ ጤንነት እንጂ ህመም የሚባል ነገር ፈጽሞ አይነካችሁም። ሁል ጊዜ ነዋሪዎች ስትሆኑ ሞት የሚባል ነገርም አያገኛችሁም። ሁልጊዜ ወጣቶች ሁናችሁ እንጂ እርጅና አይገጥማችሁም። ከሁሉም በላይ እናንተ ሁልጊዜ በሃብትና ጸጋ ላይ እንጂ በጉስቁልና አትኖሩም ብለዋል ነብዩ [ሰ.ዐ.ወ] ።

ጀነት የገባ ሰው ምቾት ያለውና ሃሳብ የሌለበት የደስታ ኑሮ ይኖራል። ሃዘን የማይነካቸው ሲሆን ልብሶቹ አያልቁበትም። ወጣትነቱም አይፈጁም።

ራህማ " ጀነትና ጀሃነምን " መፅሀፍ እያነበበች ሲሃምና ኸውለት ቤቷ ሲመጡ ጪኽ ብላ እያነበበችላቸው ነበር።
" እኛ! " አለች ቀጥላ
" እኛ ዘላለማዊ ደስታ ያለበትን ጥለን ለጊዜያዊ ደስታ ስንሮጥ እንኖራለን። ፀፁቱ በኋላ ነው። ዱኒያ ፈተና ናት። የሥራ ሀገር ናት። አኼራ ደግሞ የሂሳብ ሀገር ናት። ስለዚህ መዘጋጀት አለብን።" ሁለቱም በግርምት ያዳምቷት ነበር። ማሻአላህ ሞት በደንብ ነው የመከራት።

ሶላቷን ትሰግዳለች። ቤተሰቧቿን ትታዘዛለች። ስልክ ቀይራለች። ቤት መዋል፣ መፅሀፍትን ማንበብ አብዝታለች። ለማይሰግደውና ለማይሰማት ወንድሟ ዳዕዋ ታደርግለታለች። ድሮ የቀራችውን ቁርዐንና ሀዲስ አሁን እየከለሰች ነው። ብቻ ተለውጣለች። የኸውለት ስልክ አቃጨለ።
አናግራ ስትጨርስ " ቤት ነይ እየተባልኩ ነው።" አለቻቸው።
" ቆይ ልብስ ልቀይርና እንሸኝሻለን" አለቻት ራህማ የምታነበውን መፅሀፍ ዝቅ አድርጋ።
" እሽ ቶሎ በይ" አለቻት።
ጓዳ ገብታ ማሻአላህ የሆነ ልብስ ለብሳ ተያይዘው ወጡ።

ራህማ እያጫወተቻቸው እያሳቀቻቸው ሲሄዱ ሲሃም ግን አትስቅም፣ አታወራም፣ አልፎ አልፎ በሃሳብ ጭልጥ ብላ ትሄዳለች፤ ኸውለት ስታወራ ደግሞ ቀና ብላ አታያትም።
" ሲሃምዬ የሆንሽው ነገር አለ እንዴ?" አለቻት ራህማ ድንገት ወደ እሷ ዙራ። ዝም አለቻት
" ሲሃም?" አለቻት ራህማ ጮክ ብላ " አቤት?" አለች ደንገጥ ብላ
" የጠየኩሽን መልሽልኝ?"
" ምን ጠየቅሽኝ?" አለቻት።
" ጎሽ! ጭራሽ አልሰማሽኝም? ሀሳብሽን የወሰደውማ ሰው በርግጠኝነት አለ! "
" ወሬኛ" አለቻት ለመሳቅ እየሞከረች። " የዛሬ ሁኔታሽ ግን ግራ ያጋባል።
ምንም እኮ አላወራሽም?" አለቻት።
በሲሃም ዝምታ እየቀለዱ፣ ስለፈተና እያወሩ ታክሲ ቦታ ደረሱ።
" ለማንናውም ጓደኞቼ እኔ እዚህ ታክሲ ልያዝ፤ እናንተ ተመለሱ

። ሲሃምዬ ደግሞ እደውልልሻለሁ" አለቻት ኸውለት።
በመጨረሻ በእሽታ ተሳስመው ተለያዩ።

ሸህ ዐብዱ ከጓዳ ሲወጡ ኸውለት ገባች።
" ውይ ኸውልዬ ስጠብቅሽ ነው የመጣሽው።"
" በሰላም ነው አባዬ?"
" የኔ ልጅ ቁጭ በይ
እስኪ!" አሏት
ኸውለት ከ

ተቀመጠች በኋላ
" በል አባዬ ንገረኝ?" አለች ራቢዓ። ኸውለት ካልመጣች በስተቀር አልነግርሽም ተብላ ስለነበር። ሸህ ዐብዱ ባለቤታቸው አጠገብ ከተቀመጠ በኋላ ጥቂት ዝም አሉ።
" ምን መሰላችሁ?"
" ኢልያሴ ምን አይነት ባህሪ እንዳለው ታውቃላችሁ፤ አላህ ጥሩ ልጅ አድርጎታል። ለሰው አሳቢ፣ ታዛዥ፣ ሰው የማያስቀይም ልጅ ነው። ሁላችንም እንወደዋለን። ነገር ግን የተፈጥሮ ህግ ሆኖ ከኛ ጋር ለዘላለም አይኖርም።" ብለው ዝም አሉ። እናታቸው ቀበል ብለው
" ከኛ ጋር እንዲኖር ብንፈልግም የምታኗኑረውን መዳራችን ግን ግዴታ ነው" አሉ።
ኸውለትና ራቢዓ እርስ በርስ ተያዩ።

" ለናንተ አስቀድመን የነገርናችሁ የቤቱ ሰው ሁሉም ማወቅ ስላለበት፣ በሁኔታው ላይ ምክንያታዊ አስተያየት መስጠት ስለሚኖርበት ነው ምክንያቱም ወንድማችሁ ስለሆነ።"
" ቆይ ግን ልጅቷ ማን ናት?" አሉ ሁለቱም በአንድነት። የሁለቱም ቀልብ ላይ ያለችው ግን አንድ ሴት ናት...ቁርዐን ሀፊዟ
" ሁለታችሁም የምታውቋት ጥሩ ልጅ ናት። ከሁሉም በላይ ግን ኸውሊ ስለምታውቃት አብራትም ስለምትማር መረጃ ከሷ እንፈልጋለን።" አሉ ወደ እሷ ዞረው።

ኸውለት ሲሃም እንደሆነች ወዲያው ገባት። ለማሰብ ቸል ብላው እንጂ የነገሮች መገጣጠም ሁለቱም መተሳሰባቸውን ያሳይ ነበር። የኢልያስን ስልክ ከየት እንዳመጣችው ሳይታወቅ ስልኳ ላይ በኮድ ተፅፎ ማየቷ፣ ስለሚወዳቸውና ስለሚጠላቸው ነገሮች በተደጋጋሚ መጠየቋ፣ እሱን ለማግኘት የሚታይባት ከልክ ያለፈ ጉጉት፣ ሲገናኝ የሚታይባቸው መፈራራት ሁሉ ፍንትው ብሎ ታያት። ኢልያስም ቢሆን ከሴት ጋር ሲሄድ አይታው የማታውቀውን ባለፈው ረዥም መንገድ ከሷ ጋር መሄዱ ታወሳት።

" አስገራሚ ነው፡! አሻንጉሊት አደረጉኝ!" አለች በሆዷ ለሷ ሳይነግሯት በሚስጥር መጨረሳቸውን አስባ።
ጥቂት ዝምታ ሰፈነ።

" ቆይ ይሄን ጉዳይ ከናንተ በፊት ማወቅ የነበረብኝ እኔ ነበርኩ። ያስተዋወኳቸው እኔ ሆኘ እንዴት እኔን ይደብቁኛል?" አለች በንዴት።
ሸህ ዐብዱ ፈገግ ብለው
" ስለዚህ ጉዳይ ከኔና ካባቷ ውጭ ምንም አያውቅም። ለናታችሁም ገና አሁን ነው የነገርኳት" አሉ። ኸውለት ውስጧ ተረጋጋ። " እፎይ!" አለች። ያሰበችው መጥፎ ነገር ደግሞ አሳፈራት። ሸይጧን ሲቀልድባት መቆየቱን አስባ
" አኡዙ ቢላሂ ሚነሸይጧኒሯጅም" አለች። ቢሆንም ግን ዱብዳ ስለሆነ ጉዳይ ማሰቧን አላቆመችም።
በመሀል ሌላ ዝምታ ሰፈነ።
" ኸውሊዬ አንቺን ነው የምንጠይቀው" አሏት እናቷ ከቆይታ በኋላ።
" ነገሩ ለኔ ግርምት ነው የሆነብኝ እማየ። ወንድሜን የገዛ ጓደኛዬ ታገባለች ብዬ አስቤም አልሜም አላውቅም ነበር።" አለች ከፍተኛ የሀሳብ መደበላለቅ ስሜት እየታየባት።
ቆየት ብላ አነስ ባላ ድምፅ
" በኔ በኩል!" አለች ቃላቶቹን ያዝ እያደረገች።

" በኔ በኩል ወደ ዲን እሷም ቤተሰቧቿም መቅረባቸው፣ ለዲን ያላት ፍላጎት፣ ነገሮችን የምታይበት መንገድ፣ በተለይ በቅርብ ጊዜ ያመጣችው ኢስላማዊ ስነምግባሯ በጣም ጥሩ ነው። ከኢልያስ ጋር ይመጣጠናሉ ባልልም አሁን ባላት ለውጥ ላይ እሱ ቢጨመርበት ግን የምትገርም ሴት እንደምትሆን አልጠራጠርም። አዕምሮዋ ሁልጊዜ ለለውጥ ዝግጁ በመሆኑ የኢልያስ ንግግሮችን በሚገባ አዳምጣ አላህን በጣም ፈሪ እንደምትሆን ይሰማኛል። ስለዚህ ሚስቱ ብትሆን በኔ በኩል ቅራኔ የለኝም።" አለች ፈገግታ በሌለው ንግግር።
ሸህ ዐብዱ ወደ ራቢዓ ዞሩ።

" ልክ እንደሱ ከልጅነቷ የቀራች እንዲያውም ቁርዐን የሀፈዘች፣ ዲኗን ከድሮ ጀምራ የምትወድ፣ ባህሪዋን ሰፈር የመሰከረላት ልጅ ነበር የምመኝለት። ነገር ግን ተውበት ያደረገችም ቢሆንም አልጠላም።" አለች።

" እኔም እንዳንቺ ነበር የማስበው ራቢዓዬ። ነገር ግን እኛ ሰዎች የምናስበው ሁልጊዜ አይሆንም። አላህ የቀደረው ነው የሚሆነው። ይሄን ነገር እኔና እናታችሁ ከብዙ ጫፎች አንፃር አይተነው ነበር። የሚሆን መስሎ ታይቶናል። በዚያ ላይ አላህ ተመላሾችን ይወዳል። የሷ የድሮ አለመስተካከልም ቢሆን የመጣው ከቤተሰብ ነው። አሁን አልሃምዱሊላህ ቤተሰብ ተስተካክሏል። ለዚያውም በሷ የተነሳ ስለዚህ አሁን ባላት ጅምር ላይ ኢልያስ ቢጨመር ጥሩ ትዳር ይወጣላቸዋል ብለን ነው ያሰብነው።" አሉ ሸህ ዐብዱ
" ግን ኢልያስ ተጠይቋል?" አለች ራቢዓ።
" አልተጠየቀም!"

" እሱ ምን መወሰን እንዳለበት ያውቃል። በህሊናው ይዳኛል። ለራሱ እንተውለታለን። እናንተን አስቀድመን የጠየቅናችሁ ይሄን መጀመሪያ ነግሬው ቢያስብበት ' እናንተስ ምን አላችሁ? ' ማለቱ ስለማይቀር ይሄንን ለማስቀረት ብለን ነው።" አለ።
" ኳ" " ኳ" " ኳ" በሩ ተቆረቆረ። ሂጃብ ያወለቀችው ኸውለት ሩጣ ጓዳ ገባች።

" ይግቡ!" አለ ሸህ ዐብዱ። በሩ ተከፈተ፤ ሁሉም አፋቸውን ከፍተው ቀሩ፤ የሚያዩትን ማመን አቃታቸው፤ እጆቹ ይንቀሳቀሳሉ፤ ሰውነቱ መለስ ብሏል፤ በስርዓት ይራመዳል፤ እየተራመደ ወደ ቤት ገባ። ሸህ ዐብዱ ተነስተው ደባበሱት አቀፉት፤ ሳሙት።
" በጤና ተመለስክ? አልሃምዱሊላህ!"

ወ/ሮ ሀሊመት ማልቀስ ጀመሩ። ራቢዓ በግርምት ከላይ እስከ ታች ታየው ነበር። ኸውለት ከጓዳ እየወጣች
" ሙክታር?"
" ተረፍክ?"
" እንዴት? በምን ተዓምር?"
" አላህ አተረፈኝ"
" እሱኑ አምኜ ሄጄ ሳያሳፍር መለሰኝ" አላቸውና አረፍ አለ።
" ምን ተዓምር ተገኝቶ ነው? አንተ የምትቆየው ከአሁን በኋላ ሁለት ወር ቢሆን ነው ሲሉ አልነበረም እንዴ ዶክተሮቹ?"
" ዶክተሮቹ እንጂ አላህ አላለም።"

" ወደ መካ የሄድኩት ያንን ' የዘምዘም ውሃ የጠጣ ሰው ላሰበበት ነገር መፍትሄ ይሆነዋል። ' የሚለውን የነብዩን [ሰ.ዐ.ወ] ንግግር አምኜ ነው። ዑምራ ካደረኩ በኋላ ውሀውን አገኘሁት። እንባዬ መጣ። አብሮኝ የነበረው ሰው

' አይዞህ ነብያችን [ሰ.ዐ.ወ] ሁልጊዜ ትክክል ናቸው። ከልብህ ምንም ሳታጓድል ነይተህ ጠጣው።' አለኝ። ከበሽታዬ ልድን፣ አላህን ፈሪ ልሆን ብዬና ሌላ አንድ ኒያ ጨምሬ ጠጣሁት። ከቀናት በኋላ የሚያስቸግረኝ እግሬ መስተካከል ጀመረ። የማይንቀሳቀሰው እጄ መንቀሳቀስ ጀመረ። በጣም አለቀስኩ። አላህን አመሰገንኩ። ቁሜ መስገድ ናፍቆኝ ስለነበር የዛን ቀን ለይል እየሰገድኩ ነጋ። የነብያችን ቃል ሀቅ ነው። ለዚህ እኔ ምስክር ነኝ።" አለ። ረዥሙ አረቢያን መጅሊስ ላይ ከተቀመጠ በኋላ

" ወደዚህ ሳልመጣ በፊት ከአውሮፕላን እንደወረድኩ ቀጥታ የሄድኩት ዶክተሩ ጋር ነበር። በጣም ተገርሞ ተደንቆ አይቶኝ አልበቃ ብሎት ነበር። በመጨረሻ መፅሐፍት ካሉህ ስጠኝ ብሎኝ የሀይማኖት ንፅፅር መጽሐፍትን ሰጥቸው መጣሁ።" አላቸው።

" ድጋሜ እናይሀለን ብለን አልጠበቅንም ነበር። እንኳን አላህ አተረፈህ" አሉት በረዥሙ እየተነፈሱ።

" እናቴ እግር ስር ሆኜ እሷን ማገልገል፣ መታዘዝ፣ የሷን እግር ማጠብ ናፍቆኛል። የሰለቸኝን ሕይወት ከርቸሌ ነው ትቸው የመጣሁት።" አላቸው።

በሙክታር መምጣት የተደሰተችው ኸውለት ጓዳ ገብታ ስቅስቅ ብላ አለቀሰች። " አይ! እስኪ ሂድና አባብላት" አሉት ሙክታርን።

ሙክታር ክፍሏ ሄዶ ያባብላት ጀመር።
" ሀውሉ ተይ እንጅ! በመሳቅ ፋንታ ለምን ታለቅሻለሽ?"
" ደስ ብሎኝ እኮ ነው።" አለችው አሁንም ከነእምባዋ ከላይ እስከታች እያየችው።

ከልጅነቷ የሚያስቸግሯትን የሚመታላት፣ ስትበሳጭ ብሶቷን ከነእምባዋ የምትዘረግፍለት፣ ከሱ ጋር ስትሆን ሁልጊዜ ጥርሷን የሚያስከድናት ሰው ሞተ ተብሎ ሲመጣ አዛኝ ሆዷ አልቻለም ነበ
ር።
" ታዲያ እኔን ይከፋኛላ

?" አላት።
ሳቅ አለችና " ሂድ በቃ መጣሁ" አለችው። ተነስቶ እየወጣ
" ይችን የቻይና አይንሽን በዚያው ልታጠፊያት ነው እንዴ?" ሲላት እየሳቀች እምባዋን መጥረግ ጀመረች።
ሸህ ዐብዱ ሙክታር ሲወጣ ተመልክተው
" በሉ የሚበላ አምጡልንና ከልጄ ጋር እንብላ።" አሏቸው።
ወደ ሙክታር ዞረው
" በል አንተም ናና ስለ ዑምራ እየነገርከን እኛም የወንድምህን ሚስት ታሪክ እያጫወትንህ ማሳችንን እንበላለን።" አሉት
" የማን የኤላ?"
" ማን ነች ይቺ እድለኛ?" አለ በደስታ ስሜት
" በመጀመሪያ ታጠብና ተቀመጥ" አሉት።

የሲሃም ባህሪ ከወትሮው ተለይቷል። ሁሉም ሰው ማወቁን ተረድታለች። ቀን ማታ ዱዓ ታደርጋለች፣ ትሰግዳለች፣ ትፆማለች፣ ቁርዐን ትቀራለች። ከሰሞኑ በተለየ መልኩ ወደ አላህ ቀርባለች። የቤቱ ሰው ሁሉ የሷ እነሱን መዘንጋት ገርሟቸዋል። ለትንንሽ ወንድሞቿ እንኳ ማታ ማታ በግድ አስነስታ የምታነብላቸውን የነብያት ታሪክ ማስቀረቷ አስገርሟቸውም አስከፍቷቸውም ነበር። ስልክ በተደወለ ቁጥር ትደነግጣለች።
" ግን ሲጠየቅ ምን ይል ይሆን?" "እምቢ?" "እሺ?"
" እሷን ላገባ? ሥራም አላጣሁ? እንደዚህ አይልም መቼም።"
" ቆይ ላስብበት ገና ተማሪ ነኝ ሊል ይችላል።"
" መስፈርቱ ምን ይሆን? ሀውሊን ጠይቄያት ቢሆን ኖሮ? ለነገሩ ምን ያደርግልኛል አላህ አለኝ።"
" ከሱ ጋር አብሬ ባልና ሚስት እሆን ይሆን? እሱ ነገ ወደቤት ይመለሳል። እኔ በጭንቀት ሞትኩኝ።"
ከራሱ ጋር ብቻዋን በር ዘግታ ታወራለች።

" በህይወቴ ብዙ ነገር ፈልጌያለሁ። ሁሉንም አግኝቻለሁ። እንደዚህ አጥብቄ የፈለኩትም በቀላሉ የማይገኝ ነገርም ግን አጋጥሞኝ አያውቅም! ከሱቅ ሄዶ አይገዛ ነገር! ለነገሩ ገንዘቤ ዱዓዬ ነው።"

" አላህ ሆይ ይሄን አዛኝ ልጅ የኔ አድርገው። አፋ ላይ እሽ የሚል ቃል እንጅ ሌላ እንዳይወጣው አድርግልኝ አደራህን!" ሱጁድ አደረገች።

በአላህ ፍቃድ ጤንነቱን መልሶ ያገኘው ሙክታር ወደ ቀድሞው የማረሚያ ቤት ጓደኞቹ እየሄደ ነው። በመሃል የእናቱ ሁኔታ ድቅን አለበት።

ልክ እንዳዩት ተንደርድረው ሲጠመጠሙበት፣ ሁሉ ነገሩን ሲስሙት፣ እጁን ፊቱን ሲደባብሱት፣ ምግብ አቅርበው ሲያጎርሱት፣ እንባቸው እየሳቁ ሲወርድ፣ የሚይዙት የሚጨብጡት
ሲያጡ፣ እግሩን ሲያጥቡት፣ ተደብቀው መስገጃቸው ላይ ሄደው ልብሳቸው እስኪርስ ሲያለቅሱ፣ ፍቅራቸው እንክብካቤያቸው ሁሉ ታየው።

" አይ እናት! አላህ ቢያልቅሽ፣ ክብር ቢሰጥሽ፣ ከወንድ የበለጠ የጉድኝት መብት ቢያጎናፅፍሽ፣ ያንቺ መስተካከል የህብረተሰብ መስተካከል ነው ቢልሽ፣ ዘጠኝ ወር ተጨንቀሽ ጀነት አንቺ እግር ስር ናት ቢልሽ አይገርምም። ምክንያቱም ያንቺ ደረጃ እውነትም ላቅ ያለ ስለሆነ ነው።" ይላል ሙክታር በሃሳቡ የናቱ ነገር እየመጣበት።

" ከአሁን በኋላ እናቴን ማክበር፣ ከወንጀል ውጭ ባሉ ነገሮች መታዘዝ፣ እሷን ለማስደሰት መጣር፣ በሁሉም ጉዳዬች ፈቃዷን መጠየቅ፣ ለርሷ መተናነስ፣ በጠቅላላው ከርሷ ጋር ከድሮው የተሻለ ግንኙነት መፍጠር አለብኝ።" እያለ ማረቢያ ቤት ደርሶ ሁሉንም አገኛቸው።

" እስካሁን አዲስ ሰው አልተመደበም። አትመለስም እንዴ?" አለው አቡበከር በቅድሚያ ሰላምታ ከተለዋወጡ በኋላ። ተሳሳቁ።
" አሁን እንዴት ነህ?"
" አልሃምዱሊላህ አሁን ደህና ነኝ" አለው።
" እኔም ያው የእስር ጊዜየ እየሄደ ነው። የስከዛሬው ኑሯችን በጣም ይፀፅተኛል። ተመልሼ ወጥቼ ዲኔንም የሰፈሬንም ሰው የማገለግልበት ጊዜ ናፍቆኛል። ቤተሰቦቼም ገና ትናንት ነበር ሀገር ውስጥ የገቡት። ትናንትናውኑ መጥተው ጠይቀውኝ ሄደዋል። በል እንግዲህ አንተም ጥሩ ሰው ሁን። በዚሁ ቀጥል።
እነዚያን የሰረቅናቸውን ሰዎች አፉ በሉን በላቸው። አላህ ወንጀሎችን ሁሉ የሚምር ቢሆንም በሰዎች መካከል ግን አይገባም" አለው።
" ሂጄ ነበር።"
" ምን አሉህ?" አለው።
" አይናቸውን ማየት በጣም ፈርቼ ነበር። እንደምንም ይቅርታ ለኔም ላንተም ጠይቄያቸው ተቀብለውናል።" አለው።

የተለያዩ የጋራ ጉዳዮቻቸውንና በእስር ቤት ጓደኞቻቸው ዙሪያ ሲያወሩ ቆይተው ሙክታር
" በል እየተመላለስኩ እጠይቃሃለሁ" ብሎት አቡበከር ሲሄድ ጋዜጠኛው መጣ። ሰላምታ ተቀያይረው ስለገጠመኙ በሙሉ ነገረው።
" የነገርከኝ ሀዲስ ትክክል ነበር። እዚያው ተፈውሼ መጣሁ።"
" ለሱ አልጠራጠርም። ነብያችን [ሰ.ዐ.ወ] ከዚህ የበለጡ ብዙ ነገሮችን ተናግረዋል። የቁርዐን አስተማሪህም ሰላም ብለውሃል" አለው።
"መጥቼ እጠይቅሃለሁ አላህ ያሽርሁ በልልኝ" አለው

" በል በዲንህ ጠንክር፣ ኸይር ሥራ ብቻ ሥራ፣ እናትህን ተንከባከብ፣ ደግሞ ለሰፈርህ ሰው ሰላይ በንቃት ተንቀሳቀስ። አስተሳሰብህም እርምጃህም እንደድሮው ሼኮች ይሁን። አስተሳሰብህ ዜሮ እግርህ ደግሞ ሁለት እንዳይሆን ተጠንቀቅ! ጋዜጣም፣ መፅሄትም፣ የዲን መፅሀፍትንም አንብብ። ሁሉም የዕውቀት መሰረቶች ናቸው። የማያነብ ሰው ልክ እንደ ባዶ ቤት ነው። ትምህርትህንም ጨርስ። የተለያዩ ሀገራትን ዜናዎች ተከታተል። እንዲያ ከሆነ ጥሩ ተቆርቋሪ ሰው ይወጣሃል።" " እሽ " አለ ሙክታር
" በል አትርሳን ጠይቀን ደህና ሁን" ብሎ ሰላም ብሎት ተለያዩ።
ወንድማገኝ መጣ። ከሰላምታ በኋላ
" አንተ ደግሜ የማይህ አልመሰለኝም ነበር።" አለው
" እመን አይተኸኛል" ብሎ ሁኔታውን አስረዳው። በመጨረሻ
" አንተ? እኔም ሂጄ ቢሊኒየር ልሁን ብየ ብጠጣስ ሃሳቤ ይሞላልኛል?" አለው።
ሙክታር እየሳቀ " መጀመሪያ የልብህ ነገር መስተካከል አለበት" አለው።

" ለማንኛውም ስለ ነብያችሁ ብዙ ማወቅ እፈልጋለሁ ለጠቅላላ ዕውቀትም ቢሆን" አለው። ሌላ ጊዜ ሲመለስ መፅሀፍት እንደሚያመጣለት ቃል ገብቶለት ቻው ሲለው

" ቆይ? ባለፈው ስለ ሰፈርህ በነገርከኝ መሰረት ኢንተርኔት ቤት ብትከፍት ካለው ተጠቃሚ አንፃር ያዋጣሃል። ስለዚህ በርታና ሥራ፤ ሀብታም ሁን፤ ከዚያ ሥራህን ሀይማኖትህ አድርገው።" ብሎት ተሰበባበቱ።

ሙክታር " ሀይማኖቴማ ሥራዬ ሊሆን አይችልም" ብሎ ተሰናበተው ሁሉንም በእስታ አሰናበታቸው። ይገርማል የሰው ነገር። ሶስት የተለያዩ ሰዎች በአንድ አለም ውስጥ። አንዱ ተቀየር፣ አንዱ አንብብ፣ አንዱ ቢዝነስ ሥራ፤ የአላህ ሥራ ይገርማል። ጫጫታ የነገሰበትን የማረቢያ ቤቱን ግቢ ጨርሶ ሲገባ ያስረከበውን እቃ ተቀብሎ ለቆ ሄደ።

" ኸውለት ሃልጋዋን እያነጠፈች ሲሃም ጋር በስልክ እያወራች ነው። ሲሃም ለረዢም ጊዜ ከወቀሰቻትና ድብቅነቷን ከኮነነቻት በኋላ በረድ ብላ

" ለነገሩ መጀመሪያ ባለመስማቴ ተናድጄ ነው እንጂ አንቺ ምንም አላጠፋሽም።" አለቻት የአልጋዋን ትራስ እያስተካከለች።

" ኸውሉ ከቤተሰቦችሽ ቀድመሽ ከኔ መስማት እንደነበረብሽኮ ሳላውቅ ቀርቼ አይደለም። ነገር ግን ያልነገርኩሽ ስለፈራሁሽ፣ ስላፈርኩሽ ነው። በዚያ ላይ እንደዚህ ይፈጥናል ብዬም ስላላሰብኩ ነው! አፉ በይኝ?" አለቻት።

" ችግር የለም። ግን ወንድሜን አንዲት ብታስከፊው አለቀልሽ!" ስትላት ሁለቱን ሳቁ።
ኸውለት ወደቁም ነገር ተመልሳ
" ሲሃምዬ በመጀመሪያ እንኳን ደስ ያለሽ ልበልሽ።" አለቻት አንጥፋ የጨረሰችው አልጋዋ ላይ እየተቀመጠች
" ለምኑ?"
" እድለኛ ነሻ ጥሩ ባል አላህ ሰጥቶሻል። ጥሩ ሚስት ሁነሽ አስደስችው። በጣም ደስተኛ

የሆነ፣ የሚናፈቅ፣ ባንቺም በሱም ቤተሰቦች መልካም ፈቃድ የተፈፀመ በመሆኑ እድለኛ ያደርግሻል።" አለቻት
" ቆይ ኸውሉ ሚስት ባል የሚትይው ገና ኢልያስ መቼ ተጠየቀ?"
" ወን
ድሜን አውቀዋለሁ ባክሽ! ምርጫው

ንም አውቃለሁ። ከብዙው በጥቂቱ ታሟያለሽ። ስለዚህ ሃሳብ አይግባሽ። ዱዓ ግን አድርጊበት።"

" ሲሃም ደስ አላት።"
" ኸውለት ፈጠን ብላ"
" ኢልያስ መጣ?" አለቻት በመስኮት አሻግራ ወደ ግቢ ገብቶ የሱን አትክልት የሚንከባከቡትን አባቱን ሲያቅፋቸው ተመልክታ።
" ወላሂ በይ?"
" አልልም " አለቻት እየሳቀች።
" ኸውልዬ በጣም ፈርቻለሁ። በአላህ ቶሎ ቶሎ ደውይልኝ እሽ?"
" እኔማ ትንስ ሳላሰቃይሽ አልደውልም!"..................


ክፍል-45 ይቀጥላል #ሼር / እንወዳችኋለን❤️

ቻናላችንን ይቀላቀሉ፡ @WubTarikoch
ለሀሳብና አስተያየት፡ @WubTarikoch_bot
°° ካምባስና ፍቅር °°
ክፍል-45 / ልብ-ወለድ


.... " በአላህ ኸውሉ በማይቀለድ ነገር አትቀልጂ" ስትላት
" እሽ ውዷ ጓደኛዬ እደውልልሻለሁ" ብላት ስልኩን ዘጋችው።
ኢልያስ የናፍቆቱን ሁሉንም ሳማቸው። አባቱ
" ኢልያሴ ሻወር ውሰድ፣ ምሳ ብላ፣ ከዚያ እኔ ክፍል ናቶሎ" አሉት። በቤተሰቡ ላይ የሆነ የተለየ ነገር አንብቧል። ግን አባቱ ይነግሩኛል ብሎ ስላሰበ መጠየቁን ተወው።
ሻወር ወሰደ፣ ምሳ በልቶ አረፍ ካለ በኋላ ወደ አባቱ ክላስ ሂዶ ቆረቆረ።
" ግባ? " አሉት።
" የምረቃ ዝግጅት እንዴት ነው ኤልያሴ?" አሉት ገብቶ ከተቀመጠ በኋላ
" አልሃምዱሊላህ በጣም ጥሩ ነው።" አላቸው። አባቱ ጥቂት ዝም አሉ።
" አባ ግቢ ፕሮግራም ስላለን እንዳላረፍድ የፈለክብኝን ጉዳይ ቶሎ ንገረኝና ልሂድ።" አላቸው።
" ኤልያሴ!" አሉት እያመነቱ
" ምንም ሳልንደረደር ወደ ጉዳዩ ልግባልህና ከኸውለት ጓደኛ ቤተሰቦች ጋር ያለንን ግንኙነት ያው ታውቀዋለህ፤ ጥሩ ሰዎች ናቸው፣ አላህን አውቀዋል፤ ተዋደናል፤ አንተ ደግሞ በጣም የምኮራብህ ልጄ ነህ፤ አላህ አንተን ስለሰጠኝ አመሰግናለሁ። አሉና ቀና ብለው አዩት። አሁንም እንዳጎነበሰ ነው።

" ያሰብኩት ኤልያሴ። ከነሱ ጋር ያለንን ግንኙነት ባንተ በኩል ለማጥበቅ ነው፡" አሉት
" አልገባኝም አባዬ?" አላቸው።
" ያንተን ፍሬ ከኸውለት ጓደኛ ለማየት አላህ ይወፍቀን ዘንድ ፍቃድህን እየጠየቅኩ ነው።" አሉት።

ኢልያስ ፊቱን አጨማደደ፤ አባቱን አፍጦ ተመለከታቸው። " ምንድን ነው የምሰማው?" አለ ለራሱ። አንድ ጊዜ መሬቱን አንድ ጊዜ አባቱን ይመለከታል። ደስታ፣ ድንጋጤ፣ ሽብር፣ በሰውነቱ ተሰራጩ። ብርክ ብርክ ያለው መሰለው፤ ከንፈሩ ደረቀ፤ ውሃም የጠማው መሰለው። ሰውነቱ ውስጥ ያሉት ሴሎች ሁሉ ለአዕምሮው የሚያስተላልፉት አለቀብኝ፤ ጨምርልኝ፤ አምጣልኝ ብቻ ሆነ።....ልቡን ጨምሮ

" አባዬ በምን ተአምር አሰበው? የት ያውቃታል? ምንስ ልበለው? ከሷ የያዘኝ መውደድ እውነተኛ ነው ወይስ ስሜታዊው ነው የሚለውን ገና መቸ ለየሁት? ሰው አንድ ነገር ሲፈልግና በሃሳቡ ማግኘት እንደሚችል ሲያስብ ደስታው ሌላ ነው። በተግባር ሲሆን ግን ሽሽት? ያስገርማል!"

" ለነገሩ ልጅቱ ደስ ትለኛለች። ማግባት ፊት ለፊቴ ሲመጣ ፍርሀት ለምን ይይዘኛል?" " ግን እኔ ላገባ?"
" እኮ እኔ ላገባ?"
" ከቤተሰብ ልለያይ?"
" ከሴት ጋር መኖር ልጀምር?" እያለ በጉርብጥና ሲያብሰለስል የተለየ ስሜት ያነበቡበት አባቱ
" ትምህርት፣ ለትዳር ዝግጅት፣ ቤት፣ ኑሮ፣ ለሚስትነት ቅድመ ሁኔታ፣ ብዙ ነገር እንዳለ አውቃለሁ። ሁሉንም ነገር አስብበት። አሁን አላስቸግርህም። አንተም አስበህበት ኸውሉንም አማክረሃት ውሳኔህን ትነግረኛለህ።" አሉት።
በተደበላለቀና ግራ በተጋባ ስሜት ውስጥ ሁኖ ትንሽ ቆየ።
ትንሽ ከተረጋጋ በኋላ
" እሷን እንዴት መረጣችኋት?" አላቸው አትኩሮ እያያቸው።
" በቀላሉ የማልነግርህ ብዙ ነገሮችን ተመልክተን ነው የመረጥናት።" አሉት
" ሁላችሁም በዚህ ጉዳይ....." ብሎ ሳይጨርስ
" ሁላችንም ተነጋግረንበታል። ስለ ባህሪዋም አጥንተናል። በኛ በኩል ሁላችንም ፈቃደኞች ነን።"
" በሌለሁበት ድራችሁ ነዋ የጠበቃችሁኝ?" አላቸው ፈገግ ብሎ። አባቱ ደስ አላቸው። አንድ እርምጃ መሰላቸው።
" የኔ ልጅ ረጋ ብለህ አስብበት። ገና ነኝ የሚል ስሜት እንዳይሰማህ። ቀጥሎ ለሚመጡት ነገሮች አላህ አለባቸው" አሉት በለሰለሰ ድምፅ
" ኢንሻአላህ! አስቤበት እነግርሀለሁ" ብሏቸው እጃቸውን ስሞ ተነሳ። ለሁለተኛ ጊዜ ደስ አላቸው።

" አይ አባዬ! ሃሳቤን ይዘህ መጥተህ ፍቃድ ትጠይቀኛለህ?" አላቸው ለራሱ ከጥርስ ተነስቶ ውስጥ ለውስጥ ሄዶ ለእግር በሚሰማ ድምፅ እየሳቀ።
ኢልያስ ከቤት ወጥቶ መንገድ ላይ እየሄደ ያስባል።
" ቆይ አላህንና ረሱልን ትወዳለች?" " በመነጋገርስ ታምናለች ይሆን?"
" ለነገሮች ያላት አመለካከትስ?"
" የአዕምሮ ብስለቷስ?" " ጸባይዋስ?" " ስነምግባሯስ?"
" እኔን ለዲን ታበረታታኝ ይሆን?"
" ቤተሰቦቼንስ ትወድልኝ ይሆን?"
" ልጆቼንስ በጥሩ ተርቢያ ታሳድግልኛለች?"
" ሳያትስ የምትማርከኝ የምናፍቀኝ ነች?" ፈገግ አለ። ለራሱ የጥያቄ መዓት እያዥጎደጎደ ይሄዳል። ለነዚህ ጥያቄዎች በቂ መልስ ኸውለት ጋር ይገኛል ብሎ ስላሰበ ደወለ። ታክሲ መያዣ እስኪደርስ ድረስ ለረዥም ጊዜ አወራት።
ከኸውለት የተረዳው ብዙ ጥሩ ጎኖች እንዳላት ነው። በከፍተኛ ደረጃ ላይ ሳይሆን በመካከለኛ ደረጃ ላይ ነው ያለችው።
" ፍጹም ሰው መጠበቅ የለብኝም የባህሪ ለውጥ አሳይታለች። አዕምሮዋ ለለውጥ ዝግጁ መሆኑ ከምንም በላይ አስደሳች ነው" አለ ለራሱ።

" ከመስፈርቶቼ የማታሟላው አለ ይሆን?" ብሎ አሰበ።
" ኢማኗ አልሃምዱሊላህ ነው፤ መልኳ ደግሞ ከሶስቱም መስፈርቶቼ በሙሉ ነጥብ እንዲያውም ከዚያ በላይ የምታሟላው ነው፤ ቢክራ መሆኗን ግን አላውቅም!" ብሎ ለኸውለት ደግሞ ደወለላት። የሰጠችው መልስ በፈገግታው የተነሳ ብዙዎቹን ጥርሶቹን ያሳየ ነበር።

" ቢክራ ነች! አትጠራጠር!"
" እረ ቆይ! ስለሷ አስባለሁ እኔስ? እሷን ተንከባክቤ በደስታ ማኖር እችላለሁ?" ብሎ ራሱን ጠየቀ።
" ማስተዳደር አሁን አልችልም። ግን ደግሞ ኢንሻአላህ ሥራ ለማግኘት ብዙ ጊዜ አይፈጅብኝም። በዚያ ላይ ሪዝቅ ከአላህ ነው። ስለዚህ ይሄ ሊያስጨንቀኝ አይገባም። በአዕምሮ፣ በአካል እንዲሁም በመንፈስ ዝግጁ ነኝ?"

" አዎ ዝግጁ ነኝ" ለራሱ።
" በንግግር አምናለሁ?"
" አዎ! ሚዛናዊ የሆነ አመለካከት ሊኖረኝ ይገባል በተለይ ካገባሁ።"
" ጥሩ አባት ይወጣኛል? ጥሩ ባልስ?" ሳቅ አለ።
" በአላህ ፈቃፍ ይወጣኛል።"
" ስለዚህ ምን አስጨነቀኝ? ከጋብቻ በኋላም ከልጅ በኋላም በጥሩ ሁኔታ ለማኖር አላህ ይረዳኛል። ኸይር ነገር ላይ የአላህ እርዳታ ሁል ጊዜ አብሮን አለ!"
" ስለዚህ ኢልያስ ማግባት ትችላለህ ማለት ነው?" አለ ለራሱ። ሳቅ አለ።
" አላህ ያግራልኝ። ለጓደኞቼም አላህ ይስጣቸው።"

ኢልያስ በሀሳብ ውስጥ ሆኖ ሁለት ታክሲ ካቀያየረ በኋላ ግቢ ደረሰ። በጣም ሰርፕራይዝ ነበር የሆነው። የግቢው ሙስሊም ተማሪዎች ለተመራቂዎቹ የሽኝት ፕሮግራም አዘጋጅተውላቸው ነበር።

በፕሮግራሙ ላይ ታዋቂ የሀገራችንን ዳዒ አስጠርተው ስለነበር ሙሀደራ አቀረበ። የተለያዩ አዝናኝ ነሽዳዎች፣ ግጥሞች፣ የተለያዩ ሀዲሶች፣ የእንኳን ደስ ያላችሁ የምኞት መግለጫዎች፣ ከምረቃ በኋላ ሊኖራቸው ስለሚገቡ ባህሪያት ንግግር ተደረገ። በመጨረሻ የሽልማት ስነ-ስርዐት ነበር።

የጀመዓው የቁርዐን አሚር፣ የመፅሀፍት አሚር፣ የገንዘብ አሚር፣ የዳዕዋ አሚር፣ የትምህርት አሚር ሁሉም በየተራ ተሸለሙ። አህመድ ቁርዐንን ግቢ ጀምሮ እዚያው በማክተሙ በልዩ ተሸላሚነት ሲሸለም ኢልያስም በጠቅላላ የግቢ አሚርነትና በጎበዝ ተማሪነት ተሸለመ።

መድረክ መሪው

" በመቀጠል ከአንድ እህታችን የተላለፈ መልዕክት ስላለ ወደሱ እናልፋለን" አለ የታሸገውን ነገር እያነሳ።

" በስነ ምግባሩ ምሉዕ በመሆኑ፣ በውጤቱም ሰቃይ በመሆኑ፣ ለኢስላም ጥሩ መመኪያ ይሆናል ብዬም ስላሰብኩና በሕይወቴ የሱን አይነት ተማሪ ባለማየቴ ዛሬ በሁላችንም ፊት በልዩ ተሸላሚነት ይህንን ሽልማት አበርክቱልኝ።" ብላ አንድ እህታችን መልዕክት ልካለች።

" ሽልማቱ ደግሞ የተበረከተው ለኢልያስ ነው። እባክህ መጥተህ ሽልማቱን እንድትወስድ በአ
ላህ ስም እጠይቃለሁ።" አለው

ተማሪዎቹ በተክቢራ አጅበውት ወደ መድረክ ወጥቶ ሽልማቱን ከተቀበለ በኋላ
" አንድ ነገር ተናገር?" ተባለ።
" አላህ በዚህ መድረክ እንደሰበሰበን በጀነትም ድጋሜ ይሰብስበን።" ብሎ ወደ መቀመጫው ተመለሰ። መድረክ መሪው

" በል በድጋሜ ወደ መድረክ ና ብዬ አላስቸግርህም። ባለህበት ሽልማቱን ገልጠህ አሳየን አለው።
በፈገግታ ተነስቶ ገለጠው።
አንድ የሚያምር፣ በቆምኩበት ቅራኝ ቅራኝ የሚል ቁርዐን ነው። ሌላው ደግሞ " አታንገራግር" የሚል መፅሀፍ ነበር።
አንዋር ቀጠለና
" ያው እንደተመለከታችሁት ስጦታው የአላህ ቃል ቁርዐንና ' አታንገራግር ' የሚለውን ሰዎች ሚስት ለማግባት ምክንያት እያበዙ እንዳይሸሹ የሚከለክል መፅሀፍ ነው" አለ ኢልያስ በጣም ገርሞት ' አታንገራግር ' የሚለውን ቃሉን ብቻ ስምንት ጊዜ አነበበው።

ፕሮግራሙ ካበቃ በኋላ ሽልማቱን ማን እንደላከው ሲጠይቅ ስለልጅቷ ነገሩት። አንድ ወቅት መረብ ኳስ ጨዋታ መመልከቻ ደረጃ ላይ ቁርዐን አስቀምጣ የነበረችው ልጅ መሆኗን አስታወሰ። " አላህ ዱኒያ አኼራሽን ያሳምርልሽ።" እያለ እየመረቃት ወደ ዶርም ሲሄድ ስልኩ ጠራ። አነሳው። የኢትዮጵያ ሙስሊሞች የበላይ ጠባቂ የህዝብ ግንኙነቱ ነበሩ። ያቀረበውን ጥናታዊ ፅሁፍ ለብዙ ባለሙያዎች ተባዝቶ ተሰጥቶ እንደወደዱት፣ ዑለሞችም ፋይዳው ብዙ መሆኑን ስላመኑበት፣ ኮሚቴው ለሙስሊሙ ማህበረሰብም ሆነ ለጠቅላላ ሀገራችን ፋይዳው ብዙ ሆኖ በማግኘቱ በተጨማሪም ሀሳቡ ከዚህ በፊት ተነስቶ በነካ ነካ የተተወና እንደዚህ በጥናታዊ ጽሁፍ መልክ ያለመቅረቡ እስከዛሬ ላለመከፈቱ እንቅፋት መሆኑን ገልፀው በቀጣዩ ሐምሌ 3 ማህበሩ እውን እንደሚሆን በደስታ አበሰሩት።

በማህበሩ ምስረታ ላይ ይገኝ ዘንድም በአክብሮት ጠይቀውት ፈቃደኝነቱን እሱም ገልጾላቸው ተሰነባበቱ። " የኢትዮጲያ ዘካ ሰብሳቢዎች ማህበር ሊመሰረት? አልሀምዱሊላህ!" አለ ወደ ሰማይ ቀና ብሎ። ከልቡ ነበር የተደሰተው።

ሸህ ዐብዱ፣ ባለቤታቸው፣ ሲሃምና ኸውለት ቤት ሁነው እያወሩ ኢልያስ መጣ። ሰላምታ አቅርቦላቸው ተቀመጠ።
ከሲሃም ጋር ቀና ብለው አልተያዩም።

ሸህ ዐብዱ አንዳንድ ቀልዶችንና ታሪኮችን እያነሱ ያስቋቸው ነበር። ወደ ባለቤታቸው ዘወር ብለው

" እኔ እናታችሁን ለመጀመሪያ ጊዜ ለጋብቻ ሳስጠይቃት አፍራ ጓዳ ገባች አሉ። ከዚያ በኋላ በዚያ ቢባል በዚህ ቢባል እንዴት ትውጣ?" ሲሉ ሁሉም ሳቁ።
" ከዚያስ?" አለች ኸውለት።
" ነብዩ [ሰ.ዐ.ወ] ' የሴት ልጅ ፈቃደኝነቷ ዝምታዋ ነው። ' ስላሉ ሀሳቧ ሞልቶላት አገባችኝ።" አሉ። የዚህን ግዜ ባለቤታቸው ዞረው አዩዋቸውና
" እንዲያውም ትንሽ ማልፋት ነበረብኝ" አሏቸው የውሸት ቁጭት እያሳዩ።
" እረ ጉድ ማልፋት? ሲጀመር መቼ አስችሎሽ? እኔ ቤት ለመምጣት ችኮላሽ ችኮላ ነበር እንዴ?" ሲሏቸው ሁሉም ሳቁ። በጨዋታቸው መሀል

ሸህ ዐብዱ " መጣሁ ተጫወቱ " ብለው ወጡ። ሚስታቸውም የስኒ ማስቀመጫውን ይዘው ጓዳ ገቡ። ኸውለት ደግሞ ስልክ የምታናግር አስመስላ " ሄሎ!" " ሄሎ!" እያለች ወጣች።

ሁለቱም ነገሩ ገብቷቸው ነበር፤ ቢሆንም በዝምታ ቆዩ። ዝምታውን መስበር የፈለገችው ሲሃም

" እናትና አባትህ ደስ ይላሉ። በጣም ነው የሚያስቀኑት።" አለችው።

" አዎ አላት። ፍራት ፍራት እያለው ነው። ቤቱ ስላወራት ይሁን ወደ ተግባር እየገባ በመሆኑ ይሁን ግን አላወቀም።

" ረቢ ሸረህሊ ሰድሪ ወየስርሊ አምሪ ወህሉል ኡቅደተ ሚሊሳኒ የፍቀሁ ቀውሊ" አለ በሆዱ።
" ምን ታስቢያለሽ?" አላት ከአፋ አምልጦት......


ክፍል-46 ይቀጥላል #ሼር / እንወዳችኋለን❤️

ቻናላችንን ይቀላቀሉ፡ @WubTarikoch
ለሀሳብና አስተያየት፡ @WubTarikoch_bot
°° ካምፓስና ፍቅር °°
ክፍል-46 / ልብ-ወለድ


... " እንዳንተ አባትና እናት አይነት ሂወት መኖር።" አለችው ጠንከር ብላ።
" ትዳር ላንቺ ምንድን ነው?" አላት። ወደ ርዕሱ ዘሎ መግባቱ ለራሱ እየደነቀው።
" ሁለት ልብ አንድ ጭንቅላት" አለቺው እሷም ዱብዳ ሁኖባት። ኢልያስ ፍርሃቱ እየገፈፈለት መጣ።
" እንደማያውቃት ሰው ምን ያስፈራኛል?" ይላል በሆዱ።
" እኔን ለባልነት ብቁ የሚያደርጉኝ ነገሮች አሉ ብለሽ ታስቢያለሽ?" አላት። አቀርቅራ ትንሽ ዝም አለች።
" የአላህ ፍራቻህና ስነምግባርህ ከምንም በላይ ብቁ ያደርጉሃል!" አለቺው።
" ትዳር ሌላ የህይወት ምዕራፍ ነው። ለዚህ ምን ዝግጅት አድርገሻል?" አላት

እንዳጎነበሰች ቀና ሳትል
" ከትዳር በኋላ ስለሚያጋጥሙ ችግሮችና ስለመፍትሄዎቻቸው እንዲሁም ጥሩ ሚስት እንዴት እንደሚኮን የሚጠቅሙ መፅሀፍቶችን እያነበብኩ ነበር።

ቤተሰቦቼም ብዙ ነገር መክረውኛል። አለችው።
" ምን አልባት አላህ ቢለው ምን አይነት ትዳር የሚኖረን ይመስልሻል?"
" በጣም የሚያምር፣ በጣም የሚናፈቅ፣ አላህን ሁልጊዜ የሚያስታውስ፣ በጠቅላላው ሩህሩህ የሆነ ባልና ታዣዥ የሆነች ሚስት ሊኖራቸው የሚችለው ትዳር የሚኖረን ይመስለኛል።" አለችው ፍርሀት በሚነበብበት ድምፅ።

" እናንተ ሀብታሞች ናችሁ። እኔ ደግሞ ገና ተማሪ ነኝ። ቤት የለመድሽውን ነገር እኔ ጋር መጥተሽ ማግኘት አትችይም። እና አይከብድሽም?" አላት።

" ሀብት የሚባለው ፍቅር እንጅ ቁስ አይደለም። ምንም አይኑርህ።..... እኔ ግን ሁልጊዜም ከጎንህ ብሆን ደስ ይለኛል። ስትደሰት ደስ እንዲለኝ፣ ሲከፋህ እንዲከፋኝ፣ ችግር ሲያጋጥምህ አብሬ መፍትሄ ባፈላልግልህ ደስተኛ እሆናለሁ።" አለችው።

" አንቺ እኔን አገባሽ ማለት" ሲል አላስጨረሰችውም።
" ዱኒያ አኼራየ ተስተካከለ ማለት ነው።" አለችው።
" አላማሽ ምንድን ነው?" አላት ዝም ብሎ ከቆየ በኋላ እጇን እያሻሸች ቀና ለማለት ብላ ተወችው። በረጋና በለሰለሰ ድምፅ

" በፀሀይ ለብቻዬ ከምሄድ በጨለማ ካንተ ጋር መሄድ፣ ስለዲን ካንተ ጋር ብዙ ማውራት፣ ሷሊህ የሆኑ ልጆችን መውለድ፣ ሁልጊዜ ከፈገግታህና ከስኬትህ ጀርባ መሆን፣ የምትወደውንና የምትጠላውን ነገር ካወቅኩ በኋላ አንተን ሁልጊዜ ማስደሰት፣ በኋላም ጀነት ገብቼ ድጋሜ ያንተ ሚስት መሆን።" አለችው

በመልሷ በጣም ተደሰተ፤ ዘወር ብሎ አያት፤ ቀና አላለችም። ውስጥ እጁ ላይ ያሉ መስመሮችን የምትቆርጥ ትመስላለች።

" ፀጉርሽን ታሳይኛለሽ?" አላት። በቅፅበት
" አንድ ወንድ የሚያገባትን ሴት የሚያስበውን አካል አስቀድሞ መመልከት ይችላል።" የሚለውን የነብዩን [ሰ.ዐ.ወ] ንግግር ትዝ አላት።
ግራ እጇን አንስታ ቀስ ብላ ሂጃቧን ዝቅ አደረገችው።
ኢልያስ ምናልባትም ለመጀመሪያ ጊዜ ሴትን እንደዚህ ሲመለከት
" ሱብሀነላ.........ህ " አለ።
አይኑን መለሰና
" ምንም የምትጠይቂኝ ጥያቄ የለሽም?" አላት እሱ በተራው አቀርቅሮ።
ትንሽ ዝም አለችና
" በቃ እ.....ኔ.....ና ... አንተ ...." ራቢዓ ቆርቁራ ገባች። ኢልያስ ራቢዓ ስትገባ ደንገጥ አለ። " ኢልያስዬ ሙክታር እየፈለገህ ነው?" አለችው እየሳመችው። ሲሃምን ስትስማት ኢልያስ ወደ ውጭ ወጥቶ ሄደ። ሲሃም በአይኗ ሸኘችው።
" ሂጃቧን እየሸፈነችላት ምነው?" አለቻት።
ራቢዓ ሂጃቡን ያወለቀችበት ምክንያት ወዲያውኑ ስለገባት አይኗን አፍጥጣ
" እኔ እኮ አላምንም?" አለች።
ሲሃም እየሳቀች አየቻትና
" ምናለ አንድ ደቂቃ ቢትዘገይ?" አለቻት።
" ወይኔ...?"
" በጣም ይቅርታ....?"
" ኢልያስ?" " ኢልያስ?" እያለች ልትወጣ ስትል ሳብ አድርጋ እቅፍ አደረገቻት።

" ሀምሌ 15 ቀን፣ ከሀምሌ 1-15 ሲካሄድ የነበረው የጧኢፍ ኤክስፓ የመዝጊያ ስነ-ስርዓት። ለኢልያስ ልዩ ቀን ነበር።
ታላላቅ ዳኢዎች፣ የእስልምና ጉዳዮች ፅ/ቤት የበላይ ጠባቂ ሃላፊዎች፣ የዩንቨርሲቲ ሙስሊም ተማሪዎና ምምህራን፣ አህለል ኸይሮች፣ የሚመለከታቸው የመንግስት ሀላፊዎች እንዲሁም ዘመድ ጓደኞቹ በተገኙበት " የኢትዮጲያ የዘካ ሰብሳቢዎች" ማህበር ተመረቀ።

በበላይ ጠባቂው ግቢ ውስጥን ቢሮ ተሸጋሸገለት። ለመጀመሪያ ጊዜ ለተመረቀው ለዚህ ድርጅትም የማህበሩ ሀላፊ ተደርጎ ኢልያስ ተመረጠ።

ብቃቱና ልምዱ ባላቸው የውጭ ሀገር ምሁራን በቂ ትምህርትና ስልጠና እንዲወስድ ሁኔታዎች ተመቻቹለት። ተበታትነው ይሰሩ የነበሩ የዘካ ሰሪዎችም በአንድ ሁነው በማህበሩ ስር እንዲሰሩ ተወሰነ።

" እሽ እንዴት ነሽ?" አላት ሙክታር ኸውለትን እነሱ ቤት ከመጣ በኋላ። ቤት ማንም ስላልነበረና ለረዥም ጊዜ ሳይገናኙ ቆይተው ስለነበረ ኸውለት ደውላለት ነው የመጣው።

" እንደምታየኝ" አለችው ፊት ለፊቱ እየተቀመጠች።
" ፈተናውስ ደግዬ ነበር?" ሲላት እየሳቀች።
" ደግየ ነበር" አለችው።
" የወንድማችንስ ሚስት?" አላት።
" እሷም ደግየ ነች።" ስትለው እሱም በተራው ሳቀ። ያፈላችውን ሻይ አምጥታ ቀድታለት ወደ ቦታዋ እየተመለሰች
" እሽ ምን አዲስ ነገር አለ!" አለቺው ወደ ቦታዋ እየተመለሰች
" ለኔ ሁሉም ነገር አዲስ እኮ ነው" አላት።
" በነገራችን ላይ" አለች ኸውለት ሙክታርን ከእግር እስከራሱ እያየችው።

" ለውጥን ሳውቀው ቀስ በቀስ ነበር። ይሄ ግን አንተ ላይ አይሰራም። በአንድ ጊዜ እንደዚህ

" ፂምህ፣ ሱሪህ፣ ትህትናህ ሁሉ ነገር ይቀየራል? ፊትህ ለራሱ ኑር በሩር ሆኗል፤ ያለመደብህንም አደበኛ ሁነሃል።" አለችው በአድናቆት።
" አፈር እንዳላመጣ!" ሲላት ሳቀች። የሚያደንቃቸውን ሰው አፈር እርጩበት የሚለውን ሀዲስ ሁለቱም አስታውሰውት ነበር። ወደ ሳዑዲ የሄደበትን አጋጣሚ በጨረፍታ አስታውሳ
" ወይ ጉድ!" አለች የተቀመጠችበትን መጅሊስ እየመታች

" እኔ ቁጭ ብየ አይኔ እያየ ዑምራ አርገህ ትመጣ?" አለቺው መስጂድ ለመሄድ ሺህ ምክንያት ሲደረድር እንዳልነበር ዑምራ ገርቶለት መሄዱ ከአዕምሮዋ አልጠፋ ብሎ።
" አላህ የሻውን ይመርጣል ምን ታደርዋለሽ የቀና ይጎብጣል"
በቀልድ እየሳቀች " ግን ምን ተሰማህ ሙክታር? ሀገሩ፣ አየሩ፣ ኢባዳው፣ መስጂዶቹ ያን ሁሉ ስታይ ግን ምን አልክ?"

" ምን እላለሁ ኸውሊ! ተሰምቶኝ የማያውቅ አዲስ ስሜት፣ ሊፈራና ሊለመን የሚገባው ፈጣሪ መኖሩን የሚያሳይ የተለየ ስሜት፣ ሁሉም ነገር እንደሚቻል ያመንኩበትና ያረጋገጥኩበት ወርቃማ አጋጣሚ፣ ሰው ለሰው እንደሚያስፈልገው የተረዳሁበትና ያስተነተንኩበት ታሪካዊ አጋጣሚ እንዲሁም ዱኒያ ዜሮ መሆኗን ለራሴ አሳምኜ የመጣሁበት አይረሴ አጋጣሚ ነበር።" አላት።

" ወይ ጉድ! ደግሞ ከመቼ ወዲህ ነው ተናጋሪ የወጣህ እባክህ!" አለችው እጇን አገጯ ላይ አድርጋ በንግግሯ ተገርማ

" ውሎና አዳሬ ጋዜጤኛ ጋር እንደነበረ ባይረሱት መልካም ነው የኔ እመቤት!" አላት።
" ከፊት ለፊታቸው አፍሪካ ቲቪ ጥያቄና መልስ ፕሮግራም ላይ ነበር። " ከተቀመጡበት ቦታ ሲነሱ የሚባለው አዝካር ምንድን ነው?" ተብሎ ሲጠየቅ
" ታውቂዋለሽ?" አላት።
" አንተ ታውቀዋለህ?" አለችው የምትደነቅበት ነገር በዝቶ
" አልሃምዱሊላህ አውቀዋለሁ" አላት።
አፍጣ አየችው " ለመሆኑ ሌላ ምን ዚክር ታውቃለህ?" አለችው።
" መጓጓዣ ላይ ሲወጣ፣ ከቤት ሲወጣ ሲገባ፣ ሽንት ቤት ሲገባ ሲወጣ፣ ልብስ ሲለበስ ሲወለቅ፣ ምግብ ሲበላ ሲጠጣና ሌሎችም" አላት።
" ቀኑን ሙሉ በዚክር ነዋ የምትውለው።" አለችው። አቀረቀረ። ኸ
ውለት የታዘበችው ሌላ ነገር ደግሞ ፈጣጣነቱ ፈፅሞ ከሱ ጋር አብሮ አለመኖሩን ነው። አልፎ አልፎ አይን መስበሩና ማፈሩም አስደስቷታል።
" ኸውለት አንድ ነገር ልነግርሽ እፈልጋለሁ" አላት ካቀረቀረበት ቀና ሳይል።
" ምንድን ነው?" አለች በምላሹ በጥያቄ እይታ እያየቺው
ዛሬ ከሱ የምትሰማው ሁሉ አዲስ ስለሆነባት ለመስማት ጓጓች።
" ሌት ከቀን ብዬ ቁርዐኔን ከርሬ ልጨርስና ከረመዷን በኋላ ቁርዐን ሂፍዝ መግባት እፈልጋለሁ። ጋዜጠኛው የመያዝ ችሎታህ ከማንም በላይ ስለሆነ ብትችል ቁርዐን ሀፍዝበት ብሎኝ ነበር። ፈተናውን ካለፍኩኝ መርከዝ ለመግባት አሁን ወስኛለሁ።"

" ኸውለት ስሜቷን መለየት አቃታት። ግርምት፣ ደስታ፣ ሀዘን፣ እንዴት?" በምን ተዐምር? የሚሉት ሆዷን አደበላለቁት። ከሙኽታር መስማቷን እየተጠራጠረች ከእግር እስከ ራሱ ታየዋለች ራሱ ነው። የድሮው ሙክታር ነው።

ዝም አለች፤ ምንስ ትበል? አፍ የሚያዘጋ፤ ጭጭ የሚያስብል አጋጣሚ ሁነባት! ሙክታር ሴት ለካፊው የሰባቱን ሰማይ ጌታ ቃል ሊሀፍዝ? ጫት ቀለሙን የቀየረው ጥርስና ምላሱ የሰባቱን ምድር ጌታ ቃል ሊያነበንብ? ወሬና ወንጀል ያደረቀው ቀልቡ በፉርቃን መስታወት ሊሆን? ምን አይነት ተዐምር ነው የምሰማው? ከጎዳና ወደ መርከዝ ያለ ሽግግር የክብደቱን ያክል ለሙክታር እንዴት እንደገራለት ገረማት።

" ወላሂ አላህ የሻውን ይመራል ጥርጥር የለውም" አለች በሆዷ። ለሱ ያላት ሀዘኔታ ከልክ ያለፈ ቢሆንም ሁኔታው ግን ስሜቷን ቀየረው። ጭንቅላቷን አነቃነቀው። ወደራሷ ተመለሰችና ጭንቅላቷን የከነከናትን ጥያቄ ለመጠየቅ አሰበች። ለመተውም ለመጠየቅም እያለች

" ማሻአላህ ነው። ቀጥልበት ይሄ እኮ ሰው ማማከር አያስፈልግም። አላህ እንደው በላይ በላይ ይጨምርልህ። ተውበትህን አብዝቶ ይቀበልህ። " አለችው።
" አሚን" አለ እየሳቀ።ጥቂት ዝም ካለች በኋላ
" ሙክታር አንድ ጥያቄ ልጠይቅህ?" አለችው ቀና ብላ ሳታየው
" በደስታ" አላት።
" በቀደም ' የዘምዘምን ውሃ ለ #ሶስት ነገሮች ነይቼ ጠጣሁት። ከበሽታየ ልድን፣ አላህን ፈሪ ልሆንና ሌላ አንድ ኒያ ጨምሬ" ብለህ ነበር።"

" #ሶስተኛው ኒያህ ምን ነበር?" አለችው የሚነይተው ነገር የበሰለ እንደሚሆን በማሰብ።
ሙክታር " ጉድ ፈላ!" አለ። አፉ ተያያዘበት። እሱ በወቅቱ መናገሩንም የማያስታውሰውን ነገር እሷ ግን ይዛው ነበር። ውስጡ ተረበሸ። ምን እንደሚላት ግራ ገባው። ሶስተኛ ኒያው ከሷ ጋር የተገናኘ መሆኑን ያውቀዋል።"
" ይለፈኝ ኸውሊ።" አላት አፍሮ አንገቱን እየደፋ
በሁኔታው ተገርማ " ችግር የለም ንገረኝ! እኔና አንተ ከልጅነታችን ጀምሮ ሚስጥር ተደባብቀን እናውቃለን? ባልና ሚስት ሁነን እቃቃ የተጫወትን ልጆች በግዜ ብዛት ሚስጥር ስንደባበቅ አይደብርም?" ስትለው
" እሽ አትቀየሚኝም?" አላት።
" ለምኑ?"
" በምነግርሽ ነገር?"
" ማለት?"
" ካንቺ ጋር የተገናኘ ነው ኒያየ።"
ለመስማት ጓጓች። ከመቀመጫዋ ተስተካከለችና
" ንገረኝ?" አለችው።

" ኸውሊ እኔ ካንቺ ጋር ተደባብሬ መኖር አልችልም። የምነግርሽም መርከዝ ስለምገባ ብታኮርፊኝም አንገናኝም ብየ ነው እንጂ እዚሁ ብሆን ኩርፊያሽ ብቻውን ወደ ዱሮው ሂይወቴ ስለሚመልሰኝ አልነግርሽም ነበር።" አላት።
" ምንም ላልልህ ቃል እገባለሁ።" አለችው ልቧ በሀይል እየመታ።
የውጩ በር ተቆረቆረ።
ኸውለት ለበሩ መቆርቆር ደንታ ሳይኖራት
" ንገረኝ እንጂ?" አለችው።
" መጀመሪያ በሩን ክፈችው" አላት።
" ተዋቸው ባክህ!" አለችው የልብ ትርታዋ እየጨመረ
" እኔ እከፍተዋለሁ" ብሎ ሲነሳ በጓዳ በር ወጥታ የከፈተችው ሰራተኛቸው
" ኸውለት የሲሃም አባት ይፈልጉሻል" አለቻት" ቤት መጥታ
" ለምን?" አለቻት ጥያቄዋ ለራሷም ቆይቶ እየገረማት
" እኔንጃ ግን ከብዙ ፖሊሶች ጋር ነው የመጡት" ስትላት ከሙክታር ጋር ተያዩ። በድንጋጤ ፈጠን ብለው ወጡ።

ብዛት ያላቸው የፖሊስ መኪኖች ተከታትለው እየሄዱ ነው። ኸውለትና ሙክታር ፊተኛው መኪና ላይ ናቸው። የሲሃም አባት አላህን እየተማፀኑ ከኋላ ይከተሏቸዋል። የፖሊሶቹ መኪና ባቡር የሆነባት ኸውለት ሲተጣጠፉ ልቧ ለሁለት ክፍል እየለ በጭንቀት ትጓዛለች።

በር ላይ ጠርተው ያወሯት ትዝ አላት።

" ሲሃም ሙሉ ቀን እንደጠፋች ነው። አዲስ አበባ ከተማ ላይ ያልተደወለለት ዘመዷ የለም ግን ማናቸውም ጋር የለችም።" አላት ፖሊሱ በሚያስፈራራ እይታ እየተመለከታት

" አንች ጋር የመጣነው ከሷ ጋር የተጣላ ወይ የሚያስቸግራት ሰው ካለ እንድትነግሪን ነው" አላት። ግራ በተጋባችበት ሁኔታ ጭንቅላቷ ላይ አንድ ሰው ብቻ ነበር የመጣው...የራህማ ወንድም።

ይሄንኑ ስትነግራቸው ቤቱን እንድታሳያቸው ፈልገው ግዴታ በሚመስል ሁኔታ የፖሊሱ መኪና ውስጥ አስገቧት። ፍራት ፍራት አላት። ሊንቀሳቀሱ ሲሉ ሙክታር ኸውለት በጣም መፍራቷን ሲመለከት ለብቻዋ ሊተዋት አልፈለገም ነበር።

ፈጠን ብሎ አጠገቧ ያለውን ፖሊስ

" አብሬያችሁ ልሂድ! ቤቱ ከሌለ የሚኖረው ጓደኛው ጋር ነው። የጓደኛውን ቤት ደግሞ እኔ አውቀዋለሁ።" ሲለው በምልክት እንዲገባ ፈቀደለት።
" ኸውለት መኪናውን እንዲያፈጥነው በተደጋጋሚ ትነግራዋለች። ፖሊሱ በቻለው ፍጥነት በኸውለት መንገድ ጠቋሚነት እያበረረው ነው።

" ልጁ ሸይጧን ነው! በዚያ ላይ ለመድፈር አይመለስም! ከተደፈረች ደግሞ ኤች አይ ቪ መያዟ ነው።" አለች በሆዷ። መናገር ፈልጋ የነበረ ቢሆንም አይቡን እንዳታወጣበትና ራህማ " ለማንም እንዳትናገሪ" ብላ ያስጠነቀቀቻትን አስታውሳ ተወችው።

ሙክታርም መኪናውን እንዲያፈጥነው ይወተውተዋል። ጭቅጭቁ የበዛበት ፖሊሱ
" ጤና የላችሁም እንዴ?" አላቸው ከዚህ በላይ ምን ላድርገው በሚል ሁኔታ

" ልጁ ኤች አይ ቪ (ፖዘቲብ) ነው! በዚያ ላይ ለመድፈር ቅንጣት ታክል እርህራሄ የለውም።" ሲለው የመኪና አስፋልቱና ጎማው እሳት ፈጠሩ።
" ደግሞ ላንተ ማን ነገረህ?" የሚል መልዕክት ባለው እይታ ሙክታርን አየችው። " የኢልያስ ትዳር ይሰናከልበት ይሆን?" በማለት ጭንቀቱ አጥንቱን ሰርስሮ የገባው ሙክታር መንገድ መንገዱን እያየ ለኸውለት እይታ ትኩረት አልሰጠም ነበር።

ከጥቂት ጉዞ በኋላ አላፊ አግዳምው ምን ተፈጠረ እያለ እያያቸው እየተከታተሉ በቦታው ደረሱ። አይ ሀብታም! አጃቢው መብዛቱ፣ ተንከባካቢው፣ ጠብ እርግፍ ባዩ፣ ምን ላድርግልህ ባዩ መብዛቱ፣ ችግር ያጋጠማቸው እለት ደግሞ የስራ ሰዐት ቢሆን ባይሆን፣ ቦታው ቅርብ ሆነ አልሆነ፣ ሌላ ስራ ያዙ አልያዙ፣ ሲጣሩ በረው ይመጡላቸዋል...የፈለጓቸው ሰዎች።

ከሩቅ ፖሊሶች እየተመለከቷት ኸውለት እነ ራህማ ቤት ቆርቁራ ገባች።

ራህማን ሰላም ብላት ወንድሟን ስትጠይቃት እዚህ ያለማደሩንና ጓደኛው ጋር መሆኑን ትነግራታለች።
" እደውልልሻለሁ" ብላት በፍጥነት ተመለሰች። ራህማ ግራ ተጋባች። " ምን ሁና ነው?" ምን ችግር አጋጥሟት ነው? እሱንስ ለምን ፈለገችው? እያለች ብትጠራትም ዞራ አላየቻትም። ጥሪዋ ሲደጋገምባት በእጇ የእደውልልሻለሁ ምልክት ሰጥታት መንገዷን ቀጠለች። ራህማ ለወንድሟ ለመደወል በፍጥነት ወደ ቤት ገባች።

የመግሪብ ሶላት ተሰግዶ አልቋል። የመግሪብ ሶላት ወቅቱ አጭር ቢሆንም እነኸውለት ሳይሰግዱ ወደ ጓደኛው ቤት የመኪኖቹ ጩኸት ሰፈሩን እያቀለጠው በፍጥነት ነጎዱ።
" የት ነው የምታውቀው?" አለው ፖሊሱ ሲቃረቡ።
"ድሮ ጫት ቤት" አለው።

ብዙም በማይርቀው የጓደኛው ቤት ሲደርሱ ፖሊሶች ከየመኪናቸው
ወረዱ። በየራሳቸው ኮድ እየተነጋገሩ ቀስ በቀስ ቤቱን ከበቡት።

ቤቱን የመቆርቆር ተራው የሙክታር ነበር።
ሙሉ ቀን መብራት ስላልነበረ ፀሀይ ስራዋን ስታገባድድ የሚቀበላት ባለመኖሩ ጨለማ ሆኗል። ከሌሎች ቤቶች ነጠል ብሎ ወደሚገኘውና ግቢ ወደሌለው በር አመራ።
ቆረቆረ መልስ የለም።
ደግሞ ቆረቆረ መልስ የለም።በተደጋጋሚ ቢቆረቁርም መልስ አላገኘም።

ሁኔታውን የሚከታተሉት ፖሊሶች ወደ ቤቱ አመሩ። እርስ በርስ ከተነጋገሩ በኋላ በሩን ገነጠሉት። ብቅ ያለ ሰው የለም፤ የሚጮህ ሰው የለም፤ ጸጥ ያለ ነው። ሙክታር ዘወር ሲል ኸውለት መኪናው አጠገብ እየሰገደች ተመለከተ። እሱም በፍጥነት ሄደ።

የመጀመሪያው ፖሊስ ጥይቱን ደግኖ በጥንቃቄ ገባ። ቤቱን ሲቃኝ በአንደኛው ጥግ ሻማ በርቷል። ካጠገቡ ሲሃም ወንበር ላይ ተጠፍራ ታስራለች። ቀሚሷ እስከ ባቷ ተገልጦ አየ። ሲጠጋት በአይኗ ምልክት ሰጠችው። ሲዞር በመስኮቱ ዘለው ማምለጣቸውን አወቀ።

ፖሊሱ በሲሃም አለባበስ ምራቁን ውጦ እራሱን ለመቀጣጠር እየሞከረ በቅድሚያ እጇን ሲፈታት ቶሎ ብላ ቀሚሷን ዝቅ አደረችው። ፕላስተሩን ከአፏ ላይ አላቃ ቤቱን ለቅሶ በለቅሶ ስታደርገው አባቷ ተንደርድረው ገቡ።

አባቷ እቅፍ አድርገዋት አለቀሱ። እጇን፣ ፊቷን እየደባበሳት ተያይዘው አነቡ።
" አንድ የምመካባትን ልጄን ጉድ ሰሩኝ" እያሉ እንደ ህፃን አለቀሱ። ለቅሷቸው አላልቅ ያላቸው ፖሊሶች ዝም ካስባሏቸው በኋላ አረጋጓቸው።

" ምን አደረጉሽ ልጄ?" አሏት የጆቿን መቆሳሰል ተመልክተው እያሻሹላት።
" ምንም አላደረጉኝም" አለች በደከመ ድምፅ ለቅሶው መልሶ እየጀመራት።

" ኤች አይ ቪ ማለት ምን እንደሆነ ዛሬ በተግባር ታይዋለሽ። ቁርኝታችሁን ትጀምራላችሁ። መብራት ይምጣና ስልካችንን ቻርጅ አድርገን ለአባትሽ በቅድሚያ ደውለን ብር ታስመጪዋለሽ እምቢ ካሉ ቫይረሱ በደማቸው ካሉ እህት ወንድሞችሽ ጋር አደባልቀን እንልክሻለን። " ያሏት ትዝ አላት።

" አላህ ወዶኝ መብራት ያለመኖሩ ነው እንጂ አባዬ ዛሬ ጉድ ሁኜ ነበር!" ብላ ተንሰቅስቃ አለቀሰች። ከአባቷ ብር ቢቀበሉም እንደማይለቋት አስታውሳ።

በሴትነቷ የቀለዱባት፣ ያሰቃዩዋትና የደበደቧት፣ ስሜቱ እየተሰማት ሲመጣ መናገር ደከማት። ሰውነቷ ዛለ። አባቷ ክንድ ላይ እንዳለች በሰመመን ተኛች።

ሙክታርም ኸውለትም መግሪብ ሶላትን ጨርሰው መጥተው ሲያፅናኖአትም አልተሰማትም።

በዚህ መሀል ኸውለት የደወለችለት ኢልያስ በኩንትራት ታክሲ መጣ። ሲገባ ሲሃም የአባቷ ክንድ ላይ ገደፍ ብላ ተመለከተ።
" ደህና ነች?" አለው ሙክታርን ድንጋጤው ሳይለቀው
" አልሃምዱሊላህ ጥቂት ድካም እንጂ ደህና ናት።"
" አይዞህ ተረጋጋ!" አለው እያቀፈው።
" እሽ ሙክታርዬ።" አለው በልቡ አላህን እያመሰገነ።
" ምንድን ነው የተፈጠረው?"
" ኸውለት የነገረችህ ነው አዲስ ነገር የለም"
" ግን ምንም አላደረጓትም?"
" ምንም አላደረጓትም። አላህ ደርሶላታል።"
" ሂጄ ልጠይቃት?" አለው ትንሽ ቆየት ብሎ
" ባትሄድ ጥሩ ነው።"
" ለምን?"
" ትንስ ስለደከማት አታወራህም። እኛንም በደንብ አላወራችንም።" አለው።

የአባቷ እቅፍ ውስጥ ያለችው ሲሃም ወደ በሩ ስትዞር ኢልያስን አየችው። የተሳሰረው ፊቷ ለቀቅ አደረጋት፣ የዛለው ሰውነቷ በረታ፣ እንባ መንታ መንታ ሆኖ በአይኗ ይወርድ ጀመር።

አይኗ ተስለመለመ፣ ከንፈሯ ተንቀጠቀጠ፣ እንባዋ ፊቷን እያሞቀው መውረዱን ቀጠለ። ውስጧ ተንተከተከ።

" ኢልያስዬ ዛሬ አጥቼህ ነበር። ሁለት ሞት ሙቼ ነበር።" እያለች በሆዷ እንደገና ተንሰቅስቃ ማልቀስ ጀመረች።
" በስሜት ለውጧ ውስጡ የተነካው ኢልያስም የእምባዋ መውረድ ሩህሩህ ልቡን ከድንጋጤ ወደ ሀዘን ለወጠው። አይኑ እምባ ሞላ። ዘወር ብሎ የአይኑን ጫፎች ሲጠርግ ሲሃም አየችው። ለቅሶውን ስታይ ስላላስቻላት ውስጧን እምቅ አድርጋ አለቀሰች። የሱ እምባ በመቶ ተባዝቶ በሷ ይወጣ ይመስል እየፈነቀላት ይወርድ ጀመር።

አባቷ ትንሽ ካረጓጓት በኋላ" ቶሎ ሆስፒታል ሂደን ካልተሻላት በአፋጣኝ ወደ ታይላንድ እንሄዳለን።" እያሏት በገመዱ እስራት የተነሳ መራመድ ባለመቻሏ በእጃቸው ተሸክመዋት ወጡ።

" አላህ ያሽርሽ" አላት ኢልያስ በአጠገቡ ስታልፍ።
ውስጥን ሰርስሮ በሚገባ እይታ ውጭ ምንም አላላቸውም።

ሲሃም በአባቷ መኪና፣ ነገ የሚመረቀው ኢልያስ ከኸውለትና ከሙክታር ጋር በላዳው ታክሲ፣ የራህማ ወንድምና ጓደኛው ደግሞ በፖሊሶቹ መኪና ወደየተለያየ አቅጣጫ ሄዱ።

ኸውለት ተኝታ እያሰላሰለች ነው። ታወጣለች፤ ታወርዳለች፤ ትጥላለች፤ ታነሳለች፤ ከአንድ ጉኗ ወደ ሌላ ጉኗ ትዘዋወራለች።
ቅድም ሙክታር ያላት ትዝ አላት።
ከላዳው ታክሲ ወርደው ወደየ ቤታቸው ሊገቡ ሲሉ
" ሙክታር የቅድሙን አትነግረኝም?" አለችው።
ያለምንም መንደርደሪያና ማቅማማት " ዘምዘም ውሃ የጠጣሁት #ሶስተኛ ኒያየ አንቺን ሊድረኝ ብየ ነው። ደህና እደሪ።" ብሏት በሩን ዘጋው።

ባለችበት ደርቃ ቀርታ ነበር፤ ወደምትራመድበት ጠፋት፤ የሲሃም ሀስብ ከላይዋ ላይ ጠፍቶ በራሷ ሀሳብ ተተካ፤ ድብልቅልቅ ያለ ለመለየት የሚከብድ ውዥንብር ተፈጠረባት። እሽ አይባል ነገር እምቢ አይባል ነገር።

በተኛበት የሲሃም እገታን ከቁብ ሳትቆጥር መብሰልሰሏን ቀጠለች። ተሰምቷት የማያውቀው እንቅልፍ የማጣት ስሜት ጀመራት።
ስለ ሙክታር ስታወጣ ስታወርድ ቆየች።

" እንዴት ደፍሮ አሰበኝ? ሺ ጊዜ ቢለወጥ እንዴት የሱ አይነት ሰው ለኔ ባል ይሆናል? በዚህ ህይወት ላይ ያለፈ ሰው መከታ፤ የልጅ አባት፤ የጀነት መንደርደሪያ እንዴት ይሆናል? ባል ቀላል ነገር ነው እንዴ?"

" አኡዙቢላሂ ሚነሸይጧኒ ረጂም! ምን ነካኝ? ሸይጧን ነው እንዲህ መጥፎ መጥፎውን የሚያሳስበኝ።" ወዳልተኛችበት ጎኗ ዞረች።
" ለነገሩ ሰው እንደሆነ ያጠፋል። ምን አዲ ነገር አለው? አይደለም እሱ ከሱ በላይ ናቸው የሚባሉትም ያጠፋሉ። ምርጡ ግን ከጥፋቱ ተመላሹ ነው። እሱ ደግሞ መመለስ ብቻ ሳይሆን ጠንካራ መመለስ ላይ ነው ያለው።ሱናን በራሱ ላይ አምጥቷል።"
መዟዟሯን ቀጥላለች።

" ከጨዋታው አንፃር እድሜ ልኬን ተደስቼ እንደምኖር ባውቅም ዋናው ግን ዲን ነው። በዲን በኩል ደግሞ ሞት አፋፍ ላይ ሆኖ ሆስፒታል ከመሄድ ይልቅ ዑምራን ከመመኘት በላይ ዲነኝነት የለም።"

" አኽላቁ፣ አክብሮቱና ክድሚያው ሁሉ ተስተካክሏል። አይኑም መሰበር ጀምሯል። ከምንም በላይ ደግሞ ቁርዐን ሀፍዞ አላህ ትልቅ ደረጃ ከሚሰጣቸው ሰዎች ሊሆን ነው። እኔንም ሊያሳፍዘኝ ይችላል። ይሄ ደግሞ በህልሜም በእውኔም አስቤው የማላውቀው እድል ነው።"

" በዚያም አለ በዚህ እሱን እንቢ ለማለት ሸርጥ የለኝም። እሽታም ግን አስቸጋሪ ነው። የሰፈር ሰው ግን ምን ይለኛል?"

" ምን አባቴ ላድርግ?"

በሃሳብ ባህር እየቀዘፈች መቆም በሌለባት እየቆመች መሄድ በሌለባት እየሄደች የወደፊት ህይወቷን አጋር መዳረሻዋ ላይ መረጠችው። ከአድካሚ ጉዞ፣ እልህ አስጨራሽ ትግልና ለውሳኔ አስቸጋሪ ከሆነ እንቅልፍ ማጣት በኋላ ለእምቢታዋና እሽታዋ ተቀራራቢ ነጥብ የሰጠቻቸው ቢሆንም 51 ለ 49 ሁነውባት ሀሳቧ ያዘነበለበትን መረጠች።

በመጨረሻም #አዳበ ነውም አድርጋ ተኛች....

ክፍል-47 ይቀጥላል #ሼር / እንወዳችኋለን❤️

ቻናላችንን ይቀላቀሉ፡ @WubTarikoch
ለሀሳብና አስተያየት፡ @WubTarikoch_bot
°° ካምፓስና ፍቅር °°
ክፍል-47 / ልብ-ወለድ


................... " ጢርርርርርርርርር"
" ስልኳ ጠራ።"
" በዳበሳ ፈልጋ አነሳችው።
" ሄሎ"
" ኸውሉ አሰላሙአለይኩም"
" ወአለይኩመሰላም ሙክታር"
" ደግ አድረሻል!" ሲላት ፈገግ ብላ " ደግ አድሪያለሁ" አለችው።
" ተኝተሽ ነው እንዴ?"
" አዎ ስንት ሰዐት ሆነ?"
" ሀለት ተኩል?"
" ምን? ሱብሂ እኮ አልሰገድኩም?" አለች በድንጋጤ
" ኢናሊላሂ በይ ቶሎ ተነሽ" አላት።
" እሽ " ብላ ቶሎ ተነሳች።
" ሰግደሽ ስትጨርሽ ምን የመሰለ ቁርስ ስርቻለሁ መጥተሽ እማየ ጋር በጋራ እንበላለን" አላት።
" ኢንሻአላህ" አለች በፈገግታ እየወጣች።

ሱብሂ ሶላት ሰግዳ እንደጨረሰች ዱዓ ካደረገች በኋላ ጎረቤት እንደምትሄድ የረሳች ይመስል አለባበሷን አሳምራ ወጣች። ቤታቸው ስትደርስ ሙክታር አጎንብሶ ከሰል ሲያራግብ ፂሙ አመድ ሁኖ ተመለከተችው። ሙክታር ቀና አለ። ያየው ነገር ግን ሌላ ነገር ስላሳሰበው ቶሎ ብሎ አጎነበሰ። በሆዱ ግን ጥያቄው አወንታዊ ምላሽ እያገኘ መሆኑ ስለተሰማው ልቡ ጮቤ ረግጧል። ሰላምታ ቅድሚያ ለናቱ ሰጥታ ወደሱ ሳትዞር " አሰላሙአለይኩም" አለችው።
አጸፋውን መልሶላት
አጠገቧ ምንም መቀመጫ እንዴለለ እያወቀ " ተቀመጭ!" አላት።
" ደረቅ!" ብላው እየሳቀች እናቱ አጠገብ ሂዳ ተቀመጠች።
የሰራውን ፍርፍር በትሪ እያቀረበ " ኸውሊ እጅ አስታጥቢ" አላት።
" አንተ ኸውሊን ታዛለህ?" አሉት እናቱ።
" ላሁን ካልሆነች ለመቸ ታገለግለኛለች እማየ?" ሲላቸው
" ችግር የለውም ማዘር " ብላ ውሃ አንስታ አስታጠበቻቸው። ማስታጠቢያውን ልታስቀምት ስትል
" እኔንስ?" አላት።
" ፈገግ እያለች እሱንም ማስታጠብ ጀመረች።
" እንግዲህ ማትሪክን አላህ ያሳልፍሽ!" " አሚን!"
" ያንቺን ፋይል አላህ ከላይ ያድርግልሽ!" " አሚን!" ሳቀች።
" እናት አባትሽን አገልጋይ አላህ ያድርግሽ!" "አሚን!"

" አስር ልጅ አላህ ይስጠን" ሲል ቀና ብላ አየችው። ሳያስበው በመናገሩ እሱም ደንግጦ አይቷት በንግግሩ አፍሮ ዝም አለ።
እናትየዋ ሁኔታቸውን በጥሞና ይከታተላሉ። አስቀድሞ ኸውለትን መጠየቁን ነግሯቸው ደስ ብሏቸው ነበር። ኸውለትን ቁርስ ጥራት ያሉትም ሁለቱን ይበልጥ ለማቃረብ ስለፈለጉ ነው። አለባበሷ፤ ስታየው ማፈር መጀመሯ፤ ከፍላጎት የመነጨ መሆኑን ከልምዳቸው ስለሚያውቁት ደስታቸውን ባይገልጹትም ውስጣቸው ተደስቷል።
" ምን አነሰ?" አላት ፍርፍሩን አቅርቦ መብላት ሲጀምሩ
" ሁሉም አለ" አለችው።
" ሙያ እንዴት ነኝ? አላት።
"በርበሬ የሌለው ፍርፍር ሰርተህ ደግሞ ትጎርራለህንዴ?" አለችው ለናቱ እያጎረሰቻቸው።
" ቆይ በርበሬ ላምጣ!" ብሎ ሲነሳ
" እረ ተቀመጥ?" አለችው እየሳቀች።

እናቱ ለሷም ለሱም እያጎረሷቸው በሰፊው ሲያወሩ ቆዩ። ሙክታር ጋር ሲተያዩ ልቧ እየዘለለባት፤ በቀልዱ እየሳቀች፤ በቁም ነገሩ እየተደነቀች ቆየች። እናቱ ከወትሮው በተለየ ዝም ማለታቸው ሲገርማት
" ሙክታር አጉርሳት እንጂ!" ሲሉት ከሳቸው ያልጠበቀችው በመሆኑ ሳቋ ጠፋ። ምራቋ በዛ። ሙክታር ምንም ሳይመስለው እሱ የሚጎርሰውን ያህል ጠቅልሎ ሊያጎርሳት ሲል
" ለማን ነው?" አሉት እየሳቁ።
" ለኸውለት ነዋ! ጉርሻና ፍቅር ሲያጨናንቅ ነው እንጂ ያዢ!" አላት ወደ አፏ እያስጠጋ።
" ልትገለኝ ነው እንዴ?" አለችው ጉርሻውን እያየች።
" የገባ ይጠቅማል እንጂ አይገልም።" አላት ወደ አፏ በጣም እያስጠጋ

" እረ ሙክታር አላህን ፍራ ቀንሰው! ገና አስር ሳንወልድ ገለህ ልታሳርፈኝ...." ሳትጨርሰው አፏ ላይ ያዘችው
ምን ዋጋ አለው መልዕክቱ ተላልፏል። ሃሳቧ መውጣት ከማትፈልገው ቦታ ሊገባበት የማትፈልገው ጆሮ ገብቷል። የአፍ ወለምታ በቅቤ አይታሽ ነገር! የተናገሩትን ከሰው ጆሮ መልሶ አያስወጡት ነገር። ብትሞት የተሻለ እስኪመስላት ድረስ ደርቃ ቀረች። ወደ አፏ የቀረበው ፍርፍር ላይ አፍጣ ቆየች...


#መጨረሻው ክፍል ይቀጥላል #ሼር / እንወዳችኋለን❤️

ቻናላችንን ይቀላቀሉ፡ @WubTarikoch
ለሀሳብና አስተያየት፡ @WubTarikoch_bot
°° ካምፓስና ፍቅር °°
#መጨረሻ ክፍል.

..በንግግሯ አፍራ ማናቸውንም ለማየት አልደፈረችም። የሙክታር ሳያንሳት የናቱ ማወቅ ይባስኑ አበሳጫት። እናትየዋ ምንም እንዳልተፈጠረ እና ነገሩ እንዳልገባቸው ሲሆኑ " አልሃምዱሊላህ እሳቸው አልገባቸውም!" ብላ ትንሽ ተረጋጋች። ወደ አፏ የቀረበውን ፍርፍር በእጇ ቆርሳ አነሳችው። የተረፈውን ሙክታር በላው።
የስሜት ለውጧን የተረዱትና በጣም የተደሰቱት እናቱ

" አንቺ ደግሞ በተራሽ ዳቦቆሎ አሳክለሽ አጉርሽው" አሏት።

ልብም ብላ ቤቱ ሲቆረቆር ድንጋጤዋ ለምን እንደሆነ ሳይገባት ልቧ ውጥት ያለ እስኪመስላት ድረስ ደነገጠች።

" ኸውለት የኢልያስ የምርቃን ዝግጅት ጀመረ" አለቻት። ሰራተኛዋ ነበረች። ኸውለት ወደዚህ ከመምጣቷ በፊት " ፕሮግራሙ በቴሌቪዥን መተላለፍ ሲጀምር ጥሪኝ" ብላት ስለነበር። ለመውጣት ሰበብ ስትፈልግ የነበረችው ኸውለት በቅጽበት ተነስታ
" አላህ ይስጥልኝ ደህና እደሩ።" አለቻቸው።

ሙክታር እየሳቀ

" ደህና አርፍጂ!" አላት። ከጊቢው ሲወጡ ሰራተኛዋ

" ኢልያስ ደግሞ በቤት ስልክ ደውሎ ሲሃምን ሰላም በይልኝ ብሎሻል" አለቻት። ቅድም የተፈጠረውን ነገር በሀሳብ እያብሰለሰለችው የምትሄደው ኸውለት

" በስልኬ አይደውልም ነበር?" አለቻት።
" ስልክሽን እቤት ትተሽው ሂደሽ ነበር እኮ" አለቻት።
ኸውለት ወደ አዕምሮዋ ተመልሳ ለሲሃም እስካሁን ያለመደወሏ እያሳፈራት ቤት ስትደርስ ስልኳን አንስታ ደወለችላት።

" ጥሪ አይቀበለም"

ወ/ሮ ሀሊመት ከኸውለትና ከሰራተኛቸው ጋር ተቀምጠው ፕሮግራሙን በቀጥታ ሲከታተሉ ሙክታር ከእናቱ ጋር መጣ። ከኸውለት ጋር ቀጥ ብለው ሳይተያዩ ቦታ አመቻችተው ካስቀመጧቸው በኋላ ኢልያስን በቴሌቪዥኑ መስኮት ላይ ይፈልጉት ጀመር።

ሲሃምም ቲቪው ላይ ተተክላ ኢልያስን እየፈለገችው ነው። ከህመሟ ትንሽ አገግማለች። ቀስ በቀስ እየተራመደች መጥታ ነው ከወንድሞቿ ጋር ሳሎን የተሰየመችው።

" ግን ለምን አልደወለም?" አለች ስለሱ ማሰብ ስትጀምር። መልሱን ግን ታውቀዋለች።

ስልኳን ተሰርቃለች። የቤት ስልክ ደግሞ የላቸውም። አባቷም ቢሆኑ ደህንነቷን አረጋግጠው በጠዋት ነው ለአስቸኳይ ሥራ የወጡት።

ሁሉም አሰፍስፈው የሚጠብቁት ፕሮግራም ከሚሊኒየም አዳራሽ በቀጥታ ተጀመረ።

" የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት፣ የተመራቂ ተማሪዎች ቤተሰቦች፣ ጋዜጠኞች፣ እንዲሁም የእለቱ የክቡር እንግዳ ክቡር ሚኒስተር በዚህ ልዩ የተማሪዎች የምርቃን በዓል ላይ ስለተገኛችሁ እጅግ አድርገን እናመሰግናለን።" አለ የፕሮግራሙ መሪው።

ሲሃም በሽታዋን እረስታ እየተቁነጠነጠች መከታተል ጀመረች። በተለይ ውጤቱ ከፍተኛ መሆኑን ኸውለት የነገረቻት ትዝ ሲላት ሲሸለም ለማየት ቋመጠች።

" ፕሮግራሙን የሚከፍቱልን የዩንቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ይሆናሉ። በጭብጨባ እንቀበላቸው።" አለ። ተማሪው በሚያስተጋባ በጭብጨባ ተቀበሏቸው።

የዩንቨርሲቲው ፕሬዝዳንት የመግቢያ ንግግር ካደረጉ በኋላ በልጆቹ የተቀናበረ ሙዚቃን ጨምሮ የተለያዩ ፕሮግራሞች ቀረቡ።

ሚሊኒየም አዳራሽ የተገኙት የኢልያስ አባት ዚክር እያደረጉ ኢልያስን ከርቀት ይመለከቱታል።

በየፋካሊቲው ከፍተኛ ውጤት ያመጡ ተማሪዎች ተሸለሙ። ኢልያስም በፋካሊቲው በእጅግ በጣም ከፍተኛ ማዕረግ ሰቃይ ሁኖ ተሸለመ። ሁሉም ተሸልመው ሲያበቁ።

" በመቀጠል" አለ መድረክ መሪው ዙሪያውን እየተመለከተ ሞቅ ባለ ድምፅ።

" በመቀጠል የአዲስ አበባ ዩንቨርሲቲ የዚህን ባች ሰቃይ ተማሪ እንሸልማለን!።"

" ተማሪ.......ኢልያስ .....ዐብዱ...አለ" በጩኸት።

" የኢፍ ቢ ኢ ተማሪዎች ሁሉም ከመቀመጫቸው ተነስተው በፊሽካ እያጀቡ አጨበጨቡለት። ግማሾቹ " ይገባዋል" " ይገባዋል" ይሉም ነበር። የነሱን መነሳት ያዩ ሌሎች ተማሪዎችም ተነስተው አጨበጨቡ። በተማሪዎች ጭብጨባ እየታጀበ ወደ መድረኩ ሲወጣ ተጋባዡ ሚኒስተር የወርቅ ኒሻን አጠለቁለት። አቅፈው ሳሙት። ኢልያስ ሽልማቱን ከተቀበለ በኋላ

" በነገራችን ላይ ይህ ቆማችሁ የምታጨበጭቡለት ተማሪ ከጋወኑ ስር የሸፈነው ሱፍ ከውስጥ አዋቂዎች እንደሰማሁት የመመረቂያም የመሞሸሪያም ነው።" ሲል ተማሪዎቹ በጩኸት አዳራሹን አቀለጡት። ጭብጨባ በጭብጨባ ሆነ። በዚህ ሁኔታ ለትንሽ ጊዜ ቆየ። አላቆም ሲል መድረክ መሪው ቢቸግረው።

" እናመስግናለን።" " እናመስግናለን።"
" ተቀመጡ" ብሎ አስቆማቸው።
በቲቪ የሚመለከቱት እናቱ አለቀሱ። " አልሀምዱሊላህ።" ልጄ እንዲህ እንደሚሆን በአላህ ፈቃድ አውቅ ነበር።" አሉ።

" ምናልባት ይሄን ልጅ ለማታውቁት ግቢ ውስጥ በስነ-ምግባሩ ምስጉን የሆነ ተማሪ ነው። አንድ ቃል እንዲናገር እድል ብትሰጠው..... የሚል ነገር መጥቷል። እስኪ አንድ ቃል ይነገር" ብሎ ማይኩን አቀበለው።

ኢልያስ ጥቂት ዝም አለ። አዳራሹ ውስጥ ያለ ሰው፣ በየቤቱ የሚከታተሉት ሁሉ ንግግሩን በጉጉት እየተጠባበቁት ነው። ሲሃም በተለይ ቲቪው ውስጥ ልትገባ ምንም አልቀራትም ነበር። " ገዋኑ እንዴት አምሮበታል?" እያለች ስታስብ ንግግሩን ጀመረ።

" አልሃምዱሊላህ። ለዚህ ሁሉ ተግባር ቅድሚያ የሚወስደው አላህ ነው። በመቀጠልም ቤተሰቦቼ ለኔ መስተካከል ተጨንቃችኋል። ሁልጊዜ የኔን ጥሩ አስባችኋል።" እንባ አይኑን ሞላው።

" በጣም እወዳችኋልሁ። ውለታችሁን አላህ ይክፈልልኝ።" ቤተሰቦቹ ሁሉም ያለቅሱ ነበር ሲሃምም እንባውን ስታይ አለቀሰች።

" ኤፍ ቢ ኢ የነበራችሁ ጓደኞቼ እስከዛሬ በጣም ተዋደን ነበር የኖርነው። እናንተ ጓደኞቼ ስለነበራችሁ በጣም ደስተኛ ነበርኩ። እዚህ አዳራሽ ውስጥ የምትገኙ ተመራቂዎች እንዲሁም የተመራቂ ቤተሰቦች እንኳን ደስ አላችሁ" አለ። ተጨበጨበ። ሁሉም ቤተሰቦቹ በቲቪ እንደሚከታተሉት የሚያውቀው ኢልያስ አንገቱን አቀረቀረ።

" አላህ ሆይ ልመናዬን ተቀብለህ የምወደው፣ የማፈቅረው፣ የምሳሳለት፣ ሊንከባከበኝ ዘንድ የሚችል ባል ሰጠኸኝ። አልሃምዱሊላህ። ታለቅሳለች። ፍሬያችንን አንተን የሚያውቅ አደርገዋለሁ። ያረቢ ባሌን በሄደበት ጠብቅልኝ።" ለቅሶዋ ማባሪያ አልነበረውም።

ስልኳ ጠራ፤ ኸውለት ነበረች፤ " ኸውሊዬ!" አለች እያለቀሰች
" ሲሀምዬ ትዝ አለሽ አላህ ወደሱ ተመላሾችን ይወዳቸዋል የሚለው የቁርዐን አንቀፅ!"
አዎ አለች ጠንከር ብላ።
" አላህ በርግጥ ተመላሾችን ይወዳቸዋል!"

ስልኩን ዘጋችው። ስጁድ አደረገች ወደ ሰማይ ቀና ብላ
" አልሀምዱሊላህ!" "አልሀምዱሊላህ!" " አልሀምዱሊላህ!" ሱመ አልሀምዱሊላህ! ምን ይሳንሀል? ምንም።
" ኢንሻአላህ ነገ ፆሜን እጀመራለሁ" ብላ ወደ ወንድሞቿ ተመለሰች
" ሲሃምም ምኞቷን አላህ አሳካው"
" ኸውለትም ተሳክቶላት ሙክታርን......
ሂወት ይቀጥላል ካምባስና ፍቅር

እዚጋ #አበቃ በሌላ ታሪክ እስክንገናኝ ድረስ ማ ሰላም!


ቻናላችንን ይቀላቀሉ፡ @WubTarikoch
ለሀሳብና አስተያየት፡ @WubTarikoch_bot
ለሰው ደስታ..!

ሁለት ሰዎች በአንድ ሆስፒታል ክፍል ውስጥ አልጋ ይዘው ተኝተዋል! ... ሁለቱም በጠና ታመው በአምላክ እጅ ተይዘዋል። አንደኛው ሳንባው የቋጠረውን ውሀ ለማድረቅ ሲባል ለሰአታት ያህል አልጋው ላይ ቁጭ እንዲል ይደረጋል። አልጋው የሚገኘው በክፍሉ ብቸኛ ከሆነው መስኮት አጠገብ ነው። ሌላኛው ህመምተኛ ደግሞ በተቃራኒው ለሰአታት በጀርባው እንዲተኛ ይደረጋል።

እነዚህ ህሙማን በቆይታቸው ብዙ ተጨዋውተዋል። ስለ ቤተሰቦቻቸው፣ ስለ ኑሯቸው፣ በወታደር ቤት ስለሰጡት አገልግሎት፣ የእረፍት ጊዜያቸውን የት እንደሚያሳልፉ... ወዘተ አውርተዋል። ከመስኮት አጠገብ ያለው ህመምተኛ ቁጭ በሚልበት ሰአት ወደ ውጭ እየተመለከተ ሁሉን ነገር በጀርባ ለተኛው ሰው ይገልጽለታል። "...በሚያማምሩ ዛፎች የተከበበ ሀይቅ ይታየኛል ... በሀይቁ ላይ ዳኪዬዎች ይዋኛሉ... ህጻናት ደግሞ ከወረቀት የሰሩትን መርከቦች በሀይቁ ዳርቻ በማስቀመጥ ይጫወታሉ... ፍቅረኛሞች በአንድ እጆቻቸው አበባ በሌላው ደግሞ ተቃቅፈው ሀይቁን ይዞራሉ .. ከሀይቁ ባሻገር ውብ የሆነ ከተማ ይታየኛል .... ህፃናቶችም በደስታ ይቦርቃሉ " በማለት ዘወትር የሚያየውን ሁሉ በሚያምር አገላለፅ ይተርክለታል! ...

በዚህ አይነት ሁኔታ ሳምንታት አለፉ። አንድ ማለዳ ነርስዋ ገላቸውን ልታጥብ ውሀ ይዛ መጣች። ከመስኮት አጠገብ ያለው በሽተኛ ግን በህይወት አልነበረም። በጣም ደነገጠች። ጓደኛውም እንዲሁ አዘነ። ነርስዋ አስከሬኑን በቶሎ እንዲያነሱ ሰዎች ሌሎች ነርሶችን ጠርታ አዘዘቻቸቸው! ... ያ ብቻውን የቀረው በሽተኛ አልጋውን ከመስኮቱ አጠገብ ሊወስዱለት ይችሉ እንደሆነ ጠየቀ። ወሰዱለት። በመስኮት ለማየት በጣም ቸኩሏል። ቀና ብሎ ወደ ውጭ ተመለከተ። ከመስኮቱ ባሻገር ያለው ጥቁር ቀለም የተቀባ ግድግዳ ብቻ ነው። ደነገጠ!!!

"ምን ሆንክ?" አለቸው ነርሰዋ። "ሰዉዬው ብዙ አስደሳች ነገሮችን በዚህ መስኮት አሻግሮ ይመለከት ነበር" አላት። "ኧረ ሰዉዬው ማየት የማይችል አይነስውር ነበር አለችው።" ልብ የሚነካ ነገር.... ስቅስቅ ብሎ አለቀሰ። ለካስ እሱን ለማስደሰትና የመኖር ተስፋ ለመስጠት ነበር ያን ሁሉ ነገር ፈጥሮ የሚያወራው።

@WubTarikoch
ፖሊስ: ተበተኑ!

እኛ: ኧረ ታክሲ እየጠበቅን ነው

ፖሊስ: እኮ አንድ ሰው ይበቃል ሌሎቻቹ ተበተኑ

@WubTarikoch
ልጅቷ ለአባቷ እንዲህ ብላ ጠየቅችው ፣ በሶስት ወንዶች ታጭቻለው የመጀመሪያ ሀብታም ነው ። ፣  ሁለተኛው ቆንጆ ነው  ፣ ሶስተኛው ድሃ ነው የሱ ድህነት በጣም ዝቅተኛና የባሰ ነው ?!

አባትም አለ ልጄ ሆይ ሀብታም ብታገቢ በጣም ሀብታም እና ከዛ በላይ ትሆኛለሽ ፣ ቆንጆ ብታገቢ ያንቺ ቁንጅና ተጨምሮ አሪፍ ይሆናል ፣ አደራ ድሃ ግን አታግቢ ያንቺ ድህነት ተጨምሮ ይብሳል

ልጅቷም አለች አይ አባቴ ወንድ ልጅ ምንም አታቅም ማለት ነው ፣ ሀብታም ባገባ ሶስት ይጨምርብኛል አራተኛ ሆናለው ፣ ቆንጆ ባገባ በአስር ሴቶች ይወደዳል ፣ ድሃውን ካገባው ግን ብዙ አመታቶችን ከዛም በላይ እንኖራለን። ብላ መለሰችለት !

ብልህ እና አስተዋይ እንሁን ለማለት ያክል ነው!
@WubTarikoch
ፈገግ..

ሹፌሩ የሚያሽከረክረው አውቶብስ ተገልብጦ 40 ሰዎች ይሞታሉ ፖሊስም ሹፌሩን በቁጥጥር ስር አውሎ ምርመራውን ያደርጋል.
.
ፖሊስ:-ለመሆኑ እንዴት አደጋውን ልታደርስ ቻልክ?.
.
ሹፌሩ:- በሰአት 120 ኪ.ሜ እየነዳሁ እያለ ሁለት ሰዎች መንገድ ሊያቋርጡ መሃል መንገድ ገቡብኝ። ፍሬን ለመያዝ ስሞክር እምቢ አለኝ። በሚገርም አጋጣሚ ሁለቱ ሰዎች መንገድ ሲያቋርጡ ከመንገዱ ዳር ሰርገኞች ነበሩ። ወደ ሰርገኞቹ ከምሄድ ብዬ ሁለቱ ሰዎች ላይ ፈረድኩባቸው።.
.
ፖሊሱ:- በርግጥ ወደ ሰርገኞቹ መሄድ መተውህ እና ሁለቱን ሰዎች ለመግጨት መወሰንህ የአደጋውን ጉዳት ይቀንሰዋል።.
.
ሹፌሩ:- ትክክል ብለዋል! እኔም ሁለቱ ሰዎች ላይ ፈርጄ አንዱን ገጨሁት ሌላኛው ግን ወደ ሰርገኞቹ ስለሸሸ


እሱን ለመግጨት ስከተል ነው አደጋው የከፋው!!

#ሼር @WubTarikoch
የአንድ ትምህርት ቤት ርዕሰ መምህር ከፈተና በፊት ለተማሪዎች ወላጆች የላከው ደብዳቤ 👏

''ወድ ቤተሰቦች፣ የልጆቻችሁ ፈተና በቅርቡ ይጀምራል፡፡ የልጆችዎ ፈተና ጉዳይ እንዳስጨነቅዎ ይገባናል፡፡ ነገር ግን፣ እባክዎን ይህን ያስታውሱ፡፡ ለፈተና ከሚቀመጡት ተማሪዎች መካከል በሂሳብ መራቀቅ የማይጠበቅት አርቲስት ይኖራል፡፡ ስለታሪክ እና ሥነፅሁፍ ግድ የማይሰጠው የነፃ ሥራ ፈጣሪም አለ። የኬሚስትሪ ውጤቱ ከፍ አለ፣ ዝቅ አለ በሕይወቱ ላይ ለውጥ የማያመጣበት ሙዚቀኛም ከተማሪዎች መካከል አለ፡፡ ከፊዚክስ ይልቅ የአካል ብቃቱ ጉዳይ ወሳኝ የሆነበት አትሌትም ይኖራል፡፡ ስለዚህም ልጆዎ በፈተና ከፍተኛ ውጤት ካመጣ ጥሩ ! ዝቅተኛ ውጤት ካመጣ ግን እባከዎን በራስ መተማመኑን እና ከብሩን አይንጠቁት፡፡ ምንም ማለት አይደለም በሏቸው ይልቅ !

ከትምህርት ቤት ፈተና ለላቀ ታላቅ ጉዳይ ወደዚህ ዓለም እንደመጡ ንገሯቸው፡፡ የትኛውንም ውጤት ቢያመጡ እንደምትወዷቸው፤ ዝቅተኛ ውጤት አመጡ ብላችሁ እንደማትፈርዱባቸው ንገሯቸው:: አዎን ... እባክዎን ይህን ያድርጉ ... አንድ ፈተና ወይም አነስተኛ ውጤት ህልምና ክህሎታቸውን አታድርጉ፡፡ እንዲነጥቃቸው፤ በራስ መተማመናቸውን እንዲያሳጣቸው እናም እባከዎን ልጆችዎ ገና ለገና ዶክተር እና ኢንጂነር ካለሆኑ ደስተኛ አይሆኑም ብላችሁ አታስቡ::
ከሞቀ ሰላምታ ጋር!!

#ሼር | @WubTarikoch
HTML Embed Code:
2024/05/20 00:42:56
Back to Top