TG Telegram Group & Channel
ወሒድ የዕቅበተ ኢሥላም መጣጥፍት"Wahid Articles of Islamic Apologetics" | United States America (US)
Create: Update:

በጌትነቱ ላይ ባርነት ያለበት ኢየሱስ የባሕርይ ጌታ አለመሆኑን ይህ ጥቅስ በቂ አስረጅ ነበር። ማርያም እና ዮሴፍ ኢየሱስ በጌታው ፊት ሊያቆሙት ወደ ኢየሩሳሌም ወሰዱት፦
ሉቃስ 2፥24 "በጌታ ፊት ሊያቆሙት"፥ በጌታም ሕግ፦ “ሁለት ዋሊያ ወይም ሁለት የርግብ ጫጩቶች፡” እንደ ተባለ፥ መሥዋዕት ሊያቀርቡ ወደ ኢየሩሳሌም ወሰዱት።

"በጌታ ፊት ሊያቆሙት" የሚለው ይሰመርበት! የተወሰደው ኢየሱስ እና ጌታው በማንነት ሆነ በምንነት ሁለት ለየቅል የሆኑ ሃልዎት ናቸው፥ "የባሕርይ ጌታ" ማለት ጌትነቱ በራሱ የተብቃቃ እና ጌትነቱ የራሱ ገንዘቡ የሆነ ማለት ነው። ይህ የኢየሱስ ጌታ እና አምላክ አንዱ ጌታ አምላክ ነው፦
ዘዳግም 6፥4 እስራኤል ሆይ ስማ! አምላካችን ያህዌህ አንድ ያህዌህ ነው። שְׁמַע, יִשְׂרָאֵל: יְהוָה אֱלֹהֵינוּ, יְהוָה אֶחָד.
ማርቆስ 12፥29 ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አለው፦ “ከትእዛዛቱ ሁሉ ፊተኛይቱ፦ "እስራኤል ሆይ ስማ!  ጌታ አምላካችን አንድ ጌታ ነው"። ἀπεκρίθη ὁ Ἰησοῦς ὅτι Πρώτη ἐστίν Ἄκουε, Ἰσραήλ, Κύριος ὁ Θεὸς ἡμῶν Κύριος εἷς ἐστιν,

እዚህ አንቀጽ ሆነ ዘዳግም 6፥4 ግሪክ ሰፕቱአጀት ላይ "አንድ" ለሚል የገባው ቃል "ሄይስ" εἷς ሲሆን ለአንድ ማንነት የሚል አንስታይ መደብ ነው። ከ 130 እስከ 202 ድኅረ ልደት ይኖር የነበረው ኢራንዮስ ዘልዮን"Irenaeus of Lyon" የፖሊካርፐስ ዘሰርምኔስ ተማሪ ሲሆን "እስራኤል ሆይ ስማ! ጌታ አምላካችን አንድ አምላክ ነው" የተባለው የኢየሱስ አባት እንደሆነ በግልጽ አስቀምጧል፦
"ኦሪት ያወጀው፣ ነቢያት ያስተማሩት፣ እንዲሁ ክርስቶስ አባቱ እንደሆነ የመሰከረለት፦ "እስራኤል ሆይ ስማ! ጌታ አምላካችን አንድ አምላክ ነው" የሚል አይደለምን?" ዘዳግም 6፥4 ።
Against Heresies (St. Irenaeus) Book V(5) Chapter 11 Number 1

የአይሁድ ሕግ ዐዋቂ ኢየሱስን "አንድ ነው ከእርሱም በቀር ሌላ የለም" ብለህ መልካም ተናገር በማለት የኢየሱስ ተልእኮ ከጥንት ነቢያት የተለየ እንዳልሆነ አረጋግጦአል፦
ማርቆስ 12፥32 ጻፊውም፦ “መልካም ነው፥ መምህር ሆይ! "አንድ ነው ከእርሱም በቀር ሌላ የለም" ብለህ በእውነት ተናገርህ።

አሁንም እዚህ አንቀጽ "አንድ" ለሚል የገባው ቃል "ሄይስ" εἷς ሲሆን ይህ አንዱ ጌታ አምላክ ለኢየሱስ የአባቱን የዳዊትን ዙፋን የሚሰጥ ነው፦
ሉቃስ 1፥32 ጌታ አምላክም የአባቱን የዳዊትን ዙፋን ይሰጠዋል።

ሰጪ አንዱ ጌታ አምላክ ባለቤት ሲሆን ተሰጪ ማርያም የፀነሰችው ወንድ ልጅ ተሳቢ ነው፥ "ይሰጠዋል" የሚል ተሻጋሪ ግሥ"Transitive Verb" በባለቤት እና በተሳቢ መካከል መኖሩ ጌታ አምላክን ከወንድ ልጅ በምንነት ሆነ በማንነት ይለየዋል፦
ራእይ 21፥22 ሁሉንም የሚገዛ ጌታ አምላክ እና በጉ መቅደስዋ ናቸው።

ሁሉንም የሚገዛ ጌታ አምላክ አብ እና በጉ መሢሑ "እና" በሚል መስተጻምር መለየታቸው እና "ናቸው" በሚል የብዜት አያያዥ ግሥ መቀመጣቸው የኢየሱስ ጌታ እና አምላክ ከኢየሱስ በሰዋስው ተለይቶ ተቀምጧል፦
ማቴዎስ 4፥10 ለጌታህ ለአምላክህ ስገድ እርሱንም ብቻ አምልክ።

ኢየሱስ ጠቅሶ እና አጣቅሶ "እርሱንም ብቻ አምልክ" ብሎ ካስተማረ "እርሱ" ተብሎ በነጠላ ተውላጠ ስም የተቀመጠውን ጌታ አምላክ ማምለክ ከጀሀነም ዘውታሪነት ነጻ ያወጣል። እንግዲህ ኢየሱስ ጌታ ካለው፣ ለጌታው ባሪያ ከሆነ፣ ጌትነቱ በመደረግ ላይ የተመሠረተ መነሻ እና ጅማሮ ካለው እንግዲያውስ በጌትነቱ ባርነት የሌለበትን የባሕርይ ጌታ የሆነውን አሏህን በብቸኝነት አምልኩ! እንደ ኢየሱስ ለጌታችን ባሪያ መሆን ምንኛ መታደል ነው? ስለዚህ የኢየሱስን ጌታ እንድታመልኩ ጥሪያችን ነው። ጌታችን አሏህ ሂዳያህ ይስጣችሁ! ለእኛም ጽናቱን ይስጠን! አሚን።

ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ
https://hottg.com/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም

>>Click here to continue<<

ወሒድ የዕቅበተ ኢሥላም መጣጥፍት"Wahid Articles of Islamic Apologetics"

Share with your best friend
VIEW MORE

United States America Popular Telegram Group (US)