TG Telegram Group Link
Channel: የድንግል ማርያም ልጆች!♥ጥያቄና መልስ ቻናል!
Back to Bottom
ለስም አጠራሩ ክብር ምስጋና ይድረሰውና ጌታችን ምድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለሰማዕቷ ለትውልድ የሚተላለፍ የዘላለም ቃል ኪዳን ገብቶላታል፡፡ መታሰብያዋን ያደረገ ስሟን የጠራ በስሟ ቤተ ክርስትያን የሠራ፣የተራበውን በስሟ ያበላ፣የተጠማውን በስሟ ያጠጣ፣የገድሏን መጽሐፍ የጻፈውን፣ያጻፈውን፣ያነበበውን፣የተረጎመውን፣ሰምቶም በልቡ ያኖረውን፣የልቡን መሻት እንደሚፈጽምለት እና በመንግስተ ሰማያት እንደ እርሷ የክብር አክሊል እንደሚያቀዳጀው፤ሥዕሏን አሥሎ በክብር በቤቱ አስቀምጦ ሽቶ እየረጨ ቢጸልይበት ጸሎቱ እንደሚሰማና ልብን የሚመስጥ ጣፋጭ የሆነ መዓዛ እንደሚያሸተው፣ወንድ ልጁንና ሴት ልጁን በስሟ የሰየመ በመንግስተ ሰማያት የበለጠና የከበረ ስም እንደሚሰጣቸው፣ዕጣን፣ስንዴና መብራትን፣ልብሰ ተክህኖ፣መጋረጃ ቢሰጥ በሞቱ ቀን የብርሃን ልብስ እንደሚለብስ፣ያለ ወቀሳ ያለከሳ ባህረ ሲኦልን ተሻግሮ መንግስቱን እንደሚወርስ ቃል ኪዳን ገብቶላታል፡፡

ሰማዕቷን ከሌሎች ቅዱሳን ልዩ የሚያደርጋት ታሪክ

በግብጽ አገር አርባ ዓመታት የነገሠ ባለ 12 ክንፉ ብጹአዊ አቡነ ሙሴ የሚባሉ ታላቅ ጻድቅ አሉ፡፡ እኝህ ጻድቅ ከንግስና ወደ ምንኩስና የተሸጋገሩ መንፈሳዊ አርበኛ ናቸው፡፡

ታድያ እኝህ ጻድቅ የቅዱሳን፣የሰማዕታትን ዓጽም እሰበሰቡ ደግላቸውን እያጻፉ፣ቤተ ክርስትያን በመስራት፣ታቦታቸውን በማክበር፣በበዓላቸውም ቀን ይቀድሱ ነበር፡፡

ከእለታት አንድ ቀን ታቦት ለማሰናዳት፣ሜሮን ለመቀባት ወደ ቤተ መቅደስ በገቡ ጊዜ በወርቅ የተለበጠ እና በላዩ በሮማይስጥና በጽርዕ ቋንቋ የብጽዕት ቅድስት አርሴማ ስም የተጻፈበት አንድ ጽላት ያገኛሉ፡፡ ያን ጊዜ የቅዱሳንን ስማቸውን አሰቡ፡፡ የገድላቸውንም ዜና መረመሩ፡፡ ግን የቅድስት አርሴማን ግድልና የሞቷን ዜና አላገኙም፡፡ ስለዚህም ነገር በምን ዘመን ሰማዕት እንደሆነች እና የሰማዕትነቷን ሥራ ያስረዳቸው ዘንድ ወደ እግዚአብሔር በጸሎት አመለከቱ፡፡

ያን ጊዜ የእግዚአብሔር መልአክ ለአቡነ ሙሴ ተገልጦ ‹‹ብጽአዊ ሙሴ ሆይ የብጽእት አርሴማን ሥራ እነግርህ ዘንድ ስማ፡፡ ይህቺ ሰማዕት ገና አልተጸነሰችም፣አልተወለደችም፤በወርቅ ዓምድ በሕይወት መጽሐፍ ስሟ ተጽፏል እንጂ፡፡ ነብዩ በመጽሐፍ ውስጥ ሁሉ ይጻፋል እንዳለ እርሷም በኋለኛው ዘመን ሰማዕት ትሆናለች፤በዓለም ዳርቻ ሁሉ የገድሏ ዜና ይታወቃል፡፡

ተአምሯ የሚነገረው በኢትዮጲያ ነው፡፡ ስለዚህ ከዚህ ጊዜ ጀምሮ የብጽዕት ቅድስት አርሴማን የስም መታሰብያ መጥራት አትተው፡፡ ጽላትዋም ከአንተ ጋር ይኑር፡፡ የመቅደስዋም ህንጻ በህንጻህ ቦታ ጎን ይኑር፡፡ ስምህ በተጠራበትም የስሟ መታሰብያ ይጠራል›› ብሎ መልአኩ ወደ ላከው እግዚአብሔር ተመለሰ፡፡

አቡነ ሙሴም የእግዚአብሔር መልአክ እንዳዘዛቸው አደረጉ፡፡ ሰማዕቷም ገና ሳትወለድ በፊት እንደ እመቤታችን በእግዚአብሔር ህሌና ታስባ ትኖር ነበር፡፡ እኛም እንደ እንደ ጻድቁ አቡነ ሙሴ በሰማዕቷ ጸሎት እና ቃል ኪዳን ልንጠቀምባት ይገባል፡፡
ተወዳጆች ሆይ ቅዱስ ጳውሎስ ‹‹እንግዲህ ምን እላለሁ? ስለ ጌዴዮንና ስለ ባርቅ ስለ ሶምሶም ስለ ዮፍታሔ ስለ ዳዊትና ስለ ሳሙኤልም ስለ ነብያትም እንዳልተርክ ጊዜ ያጥርብኛልና›› ነው ያለው፡፡ /ዕብ 11÷32/ እኔም ስለ እዚች ድንቅ ብርቅ እና ከወርቅ በላይ የከበረች ከአልማዝም በላይ የተወደደች ስለ ሰማዕቷ ለመተረክ ጊዜ ስለማይበቃን እዚህ ላይ ይብቃን፡፡

የሰማዕቷ የቅድስት አርሴማ ጸሎት፣በረከት ከሁላችን ጋር ይሁን፡፡

በድጋሚ የተለጠፈ

መስከረም 29/1/15 ዓ.ም
አዲስ አበባ
💚 ወደእኔብረሪ💚
በርግብ ክንፎችሽ ከአውሬው ስትሸሽ፣
በጸዳል እግሮችሽ ስትንከራተቺ
በበረሃዉ ጉያ ስትመላለሽ
ከአህያይቱ ጀርባ ጫማ ተሸክሜ
ምነው በነበርኩኝ እኔ እንደ ሰሎሜ።
ከሄሮድስ ዱላ ከሳለው ጋሻ ጦር
ፈጥነሽ እንደበረርሽ ልጅሽን ለመሰወር
እኔም እንድሰደድ ከኃጢአቴ መንደር
ለጽድቅ እንድፋጠን በሰማይ እንድበር
ደግፊኝ እመ አምላክ ክንፌ እንዳይ ሰበር።
የቀላያት ጌታ ውኃ እንደተጠማ
በነፋስ የሚበርርበ ደመናው ማማ
ውኃ ስትለምኚ ጫማ እንደተቀማ
እኔን ድርቅ ያርገኝ ከኃጢአት ልጠማ
ደረቄን እንዳልቀር ከፍሬው አውድማ።
ምድርንም ያጸና ሰማይን የታታ
ግሩም እምግሩማን ያኀያላንጌታ
ለሰው ፍቅር ብሎ ብዙ ሲንገላታ
በዉኃ እንዳጠብሽው ኃይሉ እንዲበረታ
በእንባሽ እጠቢችኝ ኃጢአቴ በርትቶ የተረታሁ ለታ።
ጸሐይንያዘልሽው ደመና መፍጠኒት
የወርቅ ሐመልማል ርግብየ ኅሪት
አክናፍኪ መስቀል የሕይወት መሠረት
ሄሮድስ ሳይውጠኝ ሳልቀሰፍ በሞት፤ወደ እኔ ብረሪ አዝለሽልኝ ምሕረት።
የግብጽን በረሃ የጎበኘሻቸው
አድባረ አግአዚትን ዞረሽ ያየሻቸው
የሕይወትን ውኃ ያዘነብሽላቸው
ሐሩሩ ሕይወቴን ፍጹሙን በረሀ
ታስትይዮ ስቴ እሴፎ አሜሃ።
ነውር የሌለብሽ መልካም ጸጌረዳ
በመንከራተትሽ ውስተ ምድረበዳ
ሸክም ቀለለልን ከፈልሽልን እዳ
በምጽአቱ ጌዜ ፍቁርሽ እንግዳ
ቅርጫፍሽ ልሁን አይብላኝ አንጋዳ።

👉መጋቤ ብሉይ ወ ሐዲስ አባ ገብረ ኪዳን ግርማ
#ፍቅረ #ቢጽ// #ባልንጀራን #መውደድ
ተግሣጽ 1 ምስጋና ይግባውና ፈጣሪ አንደበትን እንድንሳደብበት ሐሰት እንድንናገርበት እና እርስ በእርስ እንድንከራከርበት አልሰጠንም።እርሱን እግዚአብሔርን አመስግነን እንድንጠቀምበት ነው እንጂ።ለሚሰሙን ሰዎችም በንግግር ደስ እናሰኛቸው ዘንድ ነው፡ወደመልካምም እንስባቸው ዘንድ ነው።እስኪ አንተ ሰው ንግረኝ እገሌ ክፉ ነው ብትል የምታገኘው ጥቅም ምንድን ነው? ተግሣጽ 3 በንግግርህ መልካም ሁን።ተግሣጽ 25 አንተ ሰው ከከፍታህ ወርደህ ወደ ስድብ ጉድጓድ አትውደቅ። ተግሣጽ 1 ባልጀራውን የሚያከብር እግዚአብሔርን ያከብራል።ተግሣጽ 3 እግዚአብ ሔራዊት የሆነች ፍቅር ሁሉን እንደ ወንድም አድርጎ መውደድ ነው።ተግሣጽ 19 ፍቅር በባልንጀራ ላይ ክፉ አታሳስብም ክፉም አታሰራም።ለራሳችን ክፉ እንደማናስብ ሁሉ ለሌላውም ክፉን ማሰብ የለብንም።ሁሉን እንደራስህ ውደድ ተብለን ተነግረናልና።ክፉ በሰራ ጊዜ በራሱ የሚቀየም በራሱ የሚቆጣ አለን?!።ራሱን ይቅር ይል የለምን።እንዲህ ከሆነ አንተም በሌላው አትቆጣ አትቀየም።ይቅር በል እንጂ።ምጽዋት የፍቅረ ቢጽ መገለጫ ነው።ምጽዋት የተሠራ ለሀብታሞች ብቻ አይደለም።ጸሪቀ መበለት ካላት በመመጽወቷ በፈጣሪ ዘንድ ተመስግናለችና።

"እስመ ፈጣሪ ሎቱ ስብሀት ኢወሀበነ ልሣነ ከመ ንጽርፍ ቦቱ።ወንንብብ ሐሰተ ወንትገዐዝ በበይናቲነ።አላ ከመ ንሰብሖ ቦቱ። ለእግዚአብሔር ልዑል ወናስተፍሥሖሙ በንባብ ለእለ ይሰምዑነ ከመ ይኩኖሙ በቁኤተ ወንስሐቦሙ ኀበ ሠናይ።ንግረኒ እስኩ ኦ ብእሲ ምንት ብከ በቁኤት ለእመ ትቤ እገሌ እኩይ ውእቱ። ተግሣጽ 3 ኩን ሠናየ በቃልከ።ተግሣጽ 25 ኢትደቅ እምልእልናከ ውስተ ግበ ጽርፈት። ተግሣጽ 1 ዘያከብር ቢጾ ያከብሮ ለእግዚአብሔር።ተግሣጽ 3 ወፍቅርሰ ዘበእንተ እግዚአብሔር ዛቲ ይእቲ አፍቅር ኩሎ ከመ አኃዊከ።ተግሣጽ 19 ፍቅርሰ ኢታገብር እኩየ ወኢታሔሊ እኩየ ወኢታሔሊ ኅሡመ በላእለ ቢጽ። መኑ እምሰብእ ዘይትቄየማ ለነፍሱ ወይትመዓዕ ላእሌሃ አኮኑ ይሣሀላ።

የንጉሥን አዋጅ ማፍረስ ንጉሡን ማዋረድ እንደሆነ፤ አንድም ሕንጻውን መንቀፍ ሐናጺውን መንቀፍ እንደሆነ፤ ፍጡርን መንቀፍ ፈጣሪውን መንቀፍ ነው።ስለዚህ ሰውን አትጥላ።

ረድኤተ እግዚአብሔር አይለየን።
Audio
💠"መንግሥተ ሰማያት ቀርባለችና ንስሐ ግቡ::"💠    /ማቴ ፫:፫/

❀እንኳን አደረሳችሁ!
"" ቅዱስ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ ""

"ማደሪያየ ለራቀ ለኔ ወዮልኝ!" (መዝ. ፻፲፱:፭)

(ጥቅምት 3 - 2015)

በመምህር ዲ/ዮርዳኖስ አበበ

ዝክረ ቅዱሳን ማኅበረ ቅዱስ ዳዊት ጉባኤ ዘጎንደር።

" ፍቅር ያጌብረኒ ከመ እንግር ዜናሆሙ ለቅዱሳን"::/የቅዱሳንን ዜና(ታሪክ) እንድመሰክር ፍቅር ያስገድደኛል::  አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ /መጽሐፈ ምሥጢር/
1 ልጄ ለእግዚአብሔር ትገዛ ዘንድ ብትሄድ ሰውነትህን ለመከራ አዘጋጅ

2 ልብህን በምግባር አቅና መከራውንም ታገሥ አትጠራጠር በመከራውም ብትጨነቅ አትጠራጠር

3 ነገር ግን እግዚአብሔርን ተከተለው ኋላ በፍጻሜ ዘመንህም ክብርህ ትበዛ ዘንድ አትተወው።

4 የደረሰብህን መከራ ሁሉ በትዕግሥት ተቀበል ወርቅን በእሳት እንዲፈትኑት ጻድቅንም ሰው ችግርን በሚያመጣ መከራ ይፈትኑታልና

5 ገንዘብ በተቸገርክበት ወራት መከራውን ታገሥ።

6 እግዚአብሔርን እመነው ይረዳሃል ሥራህን አቀና በሱም እመን።

7 እግዚአብሔርን የምትፈሩት ሰዎች ቸርነቱን ደጅ ጥኗት ለመከራ እንዳትወድቁ ከሱ አትራቁ

8 እግዚአብሔርን የምትፈሩት ሰዎች እመኑት ዋጋችሁንም እንዳታጡ ሁኑ።

9 እግዚአብሔርን የምትፈሩ ሰዎች በጎ ረድኤቱን ተስፋ አድርጓት ዘለዓለም ጸንቶ የሚኖር ደስ የሚያሰኝ ቸርነቱን ተስፋ አድርጉ።

10 በዘመን የቀደሙ ሰዎችን አስተውሉ በእግዚአብሔር አምኖ ያፈረ ማነው? እወቁ እሱን በመፍራት መከራውን የታገሠ በመከራ እንደ ጣለው የቀረ ማነው? ለምኖትስ ቸል ያለው ማነው?

11 እግዚአብሔር ይቅር ባይ ነውና ርኅሩኅ ነውና ኃጢአትን ይቅር ይላል፥ ከመከራም ቀን ያድናል።

(መጽሐፈ ሲራክ 1-11)
ሞትን ስታስብ ምን ይሰማሀል?
ልክ ስትሞት በዚህ ምድር አለኝ የምትለው ነገር ሁሉ የአንተ ወዳለመሆን ይሸጋገራል።የለፋህበት የተጣላህበት ነገር ሁሉ ከንቱ ይቀራል። በዚህ ምድር ያሉት ሀብት ሥልጣን ክብር ጉልበት ዕውቀት እና የመሳሰሉት በዚህ ምድር እስካለህ ድረስ ብቻ የሚያገለግሉህ ናቸው።ስትሞት እነዚህ ሁሉ ምንም ናቸው።በእርግጥ እኒህን ነገሮች ከሞት በኋላ ለሚመጣው ሕይወት ካዋልካቸው ለነፍስህ ጥቅምን ይሰጣሉ።

ብዙ ቅዱሳን የዚችን ዓለም አጭርነት ተረድተው ንቀዋት በምናኔ በየጫካው በየፍርክታው በጾም በጸሎት ተወስነው ያሳልፏታል።ሞት አንዱ የሕይወታችን አካል ነው።ቀድሞ የነበሩ ሰዎች አሁን በሥጋ የሉም።ዓለምን አንቀጥቅጠው የገዙ ዝናቸው በዓለም የታወቀ ሰዎች አሁን የሉም ሞተዋል።

መጀመሪያውንም ካለመኖር ያመጣን እግዚአብሔር በሥጋ ወደ አለመኖር ይወስደናል።ሞት ሲታሰብ ይጨንቃል ምክንያቱም ሞተን ስላላየነው አናውቀውም።ሞት በዚህች ምድር ሳሉ ሥልጣናቸውን ጉልበታቸውን እውቀታቸውን ሀብታቸውን በአግባቡ ለመልካምነት ለተጠቀሙት ሰዎች ዕረፍት ነው። በተቃራኒው ሀብታቸውን ሥልጣናቸውን እውቀታቸውን ሌላውን ለመጉዳት ለተጠቀሙት ሰዎች ሁለት ሞት ነው።

ስለዚህ ሞትን ላለመፍራት ከፈለግህ በዚህች ምድር እስካለህ ድረስ ሕገ እግዚአብሔርን ጠብቅ።3 ነገሮች ያስፈሩኛል ብሏል አንድ ሊቅ።እኒህም አለ፦
1ኛ ነፍሴ ከሥጋየ ስትለይ
2ኛ ለፍርድ በእግዚአብሔር ፊት ስትቆም
3ኛ ሲፈረድባት
ሁላችንም ካለመኖር እንድንኖር ያደረገን እግዚአብሔር ፊት እንቆማለን።ስለዚህ የእርሱን ረድኤት ጋሻ አድርገን በእርሱ ፊት ለመቆም የሚያበቃንን ስራ እንስራ።

እግዚአብሔር በቸርነቱ ይቅር ይበለን።
http://thevoicechanger.com
Voice changer with effects (http://thevoicechanger.com)
፩. መልክዐ ሥላሴን የደረሰ አባት ማነው?
፪. ሰይፈ ሥላሴን የደረሰ አባት ማነው?
፫. መልክዐ እየሱስን የደረሰ አባት ማነው?
፬. መልክዐ ሚካኣልን የደረሰ አባት ማነው?
፭. መልክዐ ማርያምን የደረሰ አባት ማነው?
፮. ከ12ቱ ሐዋርያት ለየት የሚለው ሐዋርያ ማነው?
፯. አረብ ሃገር በሙስሊም ቤት ነው የምንሰራው። ሙስሊም ነን ብለን ስለገባን አሁን ክርስቲያን ነን ማለት አንችልም። ስለዚህ እንዴት ነው ንስሃ የምንገባው? ክህደት አይሆንም ወይ?
፰. በግዝት በዓላት ለቅድስት ሥላሴ የምንሰግደው ስግደት ምን አይነት ነው?
፱. የግዝት በዓላት ባልሆነ ጊዜ ለእመቤታችን የምንሰግደው ስግደት ምን አይነት ነው?
፲. የንስሃ ስግደት እና የተጋድሎ ስግደት የምንሰግደው ምን አይነት ነው?
፲፩. በእመቤታችን ምስል ላይ በግራ እና በቀኝ ያሉት ቅዱሳን አባቶች ማን እና ማን ናቸው?
፲፪. ለምን በቀኝ እጃችን እናማትባለን?
፲፫. አንድ ዲያቆን ሚስቱን ቢፈታ ቅስናው ይፈርሳል ለሚለው ማስረጃ ከመፅሐፍ ቅዱስ ብትሰጡኝ?
፲፬. መፅሐፍ ቅዱስ ላይ ጳውሎስ ነገርን ባስረዘመ ጊዜ ይላል። ምን ማለት ነው?
፲፭. ሰማይና ምድር ያልፋል ቃሌ ግን አያልፍም ሲል ምን ማለቱ ነው?

*ከምዕመናን ለመጡ ጥያቄዎች መልስ*
በእኅት ምህረት ፍቅርተ ክርስቶስ
ለእኅታችን ቃለ ሕይወት ያሰማልን
*ማኅበረ ተዋሕዶ ዘኦርቶዶክስ*
ደቂቃው *//23:54//*
*Ke Me'emenan Lemetu Tyakewoch Mels*
Be Eht Mehret Fikrte Kristos
Le Ehtachn Kale Hiywet Yasemaln
*MAHBERE TEWAHDO ZE ORTHODOX*
👆🏽👂🏽👂🏽👈🏽
💒#ሰላም_ለኪ_ቅድስት_ቤተክርስቲያን💒

ቤተክርስቲያን ማለት ቤተ ፀሎት ናት (ማቴዎስ 21÷13)
ቤተክርስቲያን ማለት የተቀደሰ ቸረ ሰፍሪያ ናት (መዝ 28÷2)
ቤተክርስቲያን ማለት ሐመረኖህ ናት (ኦርት ዘፍጥረት 6÷1)
ቤተክርስቲያን ማለት የሰማይ ደጅ ናት( ኦሪት ዘፍ 28÷10)
ቤተክርስቲያን ማለት ቤተልሔም ናት (የሉቃስ ወንጌል 2÷15)
ቤተክርሲቲያን ማለት ኢየሩሳሌም ናት( ማቴዎስ 12÷42)
ቤተክርሲቲያነረ ማለት ቀራኒዮ ናት (የማቴዎስ ወንጌል 16÷14)
ቤተክርሲቲያን ማለት ደብርሲና ናት( ዘፀ 3÷2,)
ቤተክርስቲያን ማለት ናዝሬት ናት( ሉቃስ 1÷26)
ቤተክርሲቲያን ማለት ደብር ታቦር ናት (ማቴዎስ 17÷18)
ቤተክርሲቲያን ማለት ደብር ዘይት ናት (ሉቃስ 21÷37)
ቤተክርስቲያን ማለት ደብር ጺዮን ናት( መዝ 19÷2)

❤️ብሩህ ሰንበት🌹
🌼🌹 (ነጭም ቀይም አበባ የተባለ ልጅሽን ታቅፈሽ” 🌼🌹
የ (እንዘ ተሐቅፊዮ..) አስደሳች ትርጒም

በመጋቤ ሐዲስ ዶክተር ሮዳስ ታደሰ

❖ በማሕሌተ ጽጌ ላይ አባ ጽጌ ድንግል የደረሰው በወርኀ ጽጌ በቅድስት ቤተ ክርስቲያን በእሑዱ ማሕሌት የሚደርሰው በሊቃውንቱና በምእመናን ዘንድ የሚወደደው ምስጋና “እንዘ ተሐቅፊዮ” ነው፤ በዚኽ ምስጋና ላይ እመቤታችን ልጇን ታቅፋ (ምስለ ፍቁር ወልዳ) ያለው ሥዕል ወጥቶ በማዕጠንት እየታጠነ ምእመናን ኹሉ ጧፍ እያበሩ፤ ሊቃውንት እያሸበሸቡ፤ በአንዳንድ አድባራት ደግሞ እጅግ የሚያስደስቱ የጽጌ ረዳ አበባዎች ተይዘው ምስጋናዋ ሲቀርብ ነፍስን ወደ ሰማየ ሰማያት ይነጥቃል፤ ታዲያ ይኽቺ ልዩ ምስጋና ያላትን ምስጢር ማሳወቅ ስለሚገባ ከዚኽ በታች አቅርቤያታለኊ፡፡

🌼🌹 “እንዘ ተሐቅፊዮ ለሕፃንኪ ጽጌ ጸዐዳ ወቀይሕ
አመ ቤተ መቅደስ ቦእኪ በዕለተ ተአምር ወንጽሕ
ንዒ ርግብየ ትናዝዝኒ እምላሕ
ወንዒ ሠናይትየ ምስለ ገብርኤል ፍሡሕ
ወሚካኤል ከማኪ ርኅሩኅ”

🌼🌹 (ነጭም ቀይም አበባ የተባለ ልጅሽን እያቀፍሽው በተአምርና በንጽሕና ቀን ወደ ቤተ መቅደስ በገባሽ ጊዜ ርግቤ ድንግል ማርያም ሆይ ከልቅሶ ከሐዘን ታረጋጊኝ ዘንድ ነዪ፤ መልካማዬ ከደስተኛው ገብርኤልና እንዳንቺ ርኅሩኅ ከኾነው ከሚካኤል ጋር ነዪ) ይላል፡፡

❖ የማሕሌተ ጽጌ ደራሲ አባ ጽጌ ብርሃን በቅዱሳት መጻሕፍት ምስጢር እየተራቀቀ የአምላክን እናት ያወድሳል፤ ይኸውም ልጇ ኢየሱስ ክርስቶስን አስቀድሞ በነጭና በቀይ አበባ ይመስለዋል፤ ስለምን ቢሉ ሰሎሞን በመሓልይ ላይ "ወልድ እኁየ ፀዐዳ ወቀይሕ" (ወልድ ወንድሜ ነጭም ቀይም ነው) ብሎ ተናግሯል፨

❖ ሊቁም “ወልድ እኁየ ፀዐዳ በመለኮቱ ወቀይሕ በትስብእቱ” (ወንድሜ ወልድ በመለኮቱ በነጭ፤ ሥጋን በመዋሐዱ ቀይ ነው (በቀይ ይመሰላል)) ብሎ ሊቁ የሰሎሞንን መሓልይ እንደተረጐመው ሥጋን የተዋሐደ ንጹሐ ባሕርይ አካላዊ ቃል ክርስቶስን ንጽሕት ድንግል ማርያም በኅቱም ድንግልና በወለደችው በአርባ ቀኗ ጌታን ወደ ቤተ መቅደስ ይዛው በገባች ዕለት ታላቅ ተአምር ተፈጽሟልና “ዕለተ ተአምር” አላት፨

❖ ይኸውም ተአምር ከአልጋ ተጣብቆ የነበረው አረጋዊዉ ስምዖን ታድሶ ልክ እንደ 30 ዘመን ጐልማሳ ኾኗል፤ ይኸውም ከ285-246 ቅድመ ልደተ ክርስቶስ ጽርእን ይገዛ የነበረው በጥሊሞስ የብሉይ ኪዳን መጻሕፍት ወደ ጽርዕ ቋንቋ እንዲተረጎም ባዘዘው መሠረት መጽሐፈ ኢሳይያስን እንዲተረጕም ለስምዖን ደረሰው ሲጽፍ “ናሁ ድንግል ትፀንስ ወትወልድ ወልደ” ከሚለው አንቀጽ ደረሰ፤ ርሱም ድንግል በድንግልና ትፀንሳለች ብዬ ብጽፍ ስንኳን የአሕዛብ ንጉሥ የእስራኤልስ ንጉሥ ቢኾን ይቀበለኛል? ብሎ “ወለት ትፀንስ” ብሎ ጻፈ እንቅልፍ መጥቶበት ተኝቶ ቢነቃ ወለትን ፍቆ ድንግልን ጽፎ አገኘ፤ ስምዖንም ድንግልን ፍቆ ወለት ብሎ ጽፎ እንቅልፍ መጥቶበት ተኝቶ ቢነቃ በድጋሚ ወለትን ፍቆ ድንግልን ጽፎ አገኘ፤ ሦስተኛም እንቅልፍ መጥቶበት ተኝቶ ቢነቃ ወለትን ፍቆ ድንግልን ጽፎ አገኘው እፍቃለኊ ሲል “ኢትመውት ዘእንበለ ትርአይ መሲሖ ለእግዚአብሔር” ብሎ መሲሑን ሳያይ እንደማይሞት ነገረው፡፡

✝️ በኢሳይያስ የተነገረው ተፈጽሞ ጊዜው ደርሶ ቅድስት ድንግል ማርያም በኅቱም ድንግልና መሲሑ ጌታን ፀንሳ በድንግልና ከወለደችው በኋላ በ፵ ቀኑ ጌታን ወደ ቤተ መቅደስ በወሰደችው ጊዜ “ወወሰዶ መንፈስ ምኲራበ” ይላል ካልጋ ተጣብቆ ሲኖር መንፈስ ቅዱስ አነሣሥቶ አጽናንቶ ወደ ምኲራብ ወሰደው፤ ጌታንም በቤተ መቅደስ ባየ ጊዜ ፍጹም እንደ ፴ ዓመት ወጣት ታድሷል፤ ወዲያው ጌታን በደረቱ ታቅፎ እያመሰገነው “ይእዜ ትሥዕሮ ለገብርከ በሰላም እግዚኦ በሰላም አዘዝከ”

✝️ (ጌታ ሆይ አኹን እንደ ቃልኽ ባሪያኽን በሰላም ታሰናብተዋለኽ ዐይኖቼ በሰዎች ኹሉ ፊት ያዘጋጀኸውን ማዳንኽን አይተዋልና) በማለት የኢሳይያስ ትንቢት ተፈጽሞ መሲሑ የባሕርይ አምላክ የዓለም መድኀኒትን ርሱን በዐይኑ በማየቱ ደስ ተሰኝቶ በሰላም በሞት እንዲያሰናብተው መሲሕ ጌታን ከለመነ በኋላ እመቤታችንንም “በአንቺም ደግሞ በነፍስሽ ሰይፍ ያልፋል” በማለት እንደ ጦር ለልቡና የምትሰማ የጌታን የዕለተ ዐርብ መከራውን ነግሯታልና (ሉቃ ፪፥፳፭-፴፭)፡፡
አባ ጽጌ ድንግል በመቀጠል “ርግቤ ከልቅሶ ታረጋጊኝ ዘንድ ነዪ” በማለት በኖኅ ርግብ፣ በዳዊት ርግብ፣ በሰሎሞን ርግብ የተመሰለች ቅድስት ድንግል ማርያም ከሐዘን ትሰዉረው ዘንድ ይማጸናታል፡፡

ይኸውም ይኸውም እናታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የጥፋት ውሃ የመጒደሉን ነገር ባፏ የዘይት ቅርንጫፍ ይዛ የምሥራቹን ለኖኅ ባሳወቀችው ርግብ መመሰሏን ሲያይ ነው (ዘፍ ፰፥፲፩)፤ ያቺ ርግብ የጥፋት ውሃ የማብቃቱን ነገር “ሐጸ ማየ አይኅ ነትገ ማየ አይኅ” (የጥፋት ውሃ ጐደለ፤ የጥፋት ውሃ ተገታ) ስትል የምሥራቹን የዘይት ቅጠል ይዛ እንደታየች ኹሉ ቅድስት ድንግል ማርያምም “ሐጸ ማየ ኀጢአት ነትገ ማየ መርገም” (የኀጢአት ውሃ ጐደለ፤ የመርገም ውሃ ተገታ) ስትል ዓመተ ፍዳ ዓመተ ኩነኔን አሳልፎ ዓመተ ምሕረትን የተካ፤ ለዓለሙ ኹሉ ታላቅ የምሥራች የኾነ፤ የዓለም መድኀኒት ክርስቶስን ወልዳልናለችና በኖኅ ርግብ ተመስላለች፡፡

🕊️ አንድም ርግበ ዳዊት አላት፤ ሰባት ሀብታት የተሰጡት ነቢየ እግዚአብሔር ዳዊት በምድረ ርስት በኢየሩሳሌም ላይ የተገኘች በየዋህነቷ በርግብ የምትመሰል ቅድስት ድንግልን ክንፎቿ በብር በተሠሩ ጐኖቿም በወርቅ በተሸለሙ በርግብ አምሳል በመንፈሰ እግዚአብሔር ተመልክቶ በመዝ ፰፯፥፲፫ ላይ “እመኒ ቤትክሙ ማዕከለ መዋርስት” (በርስቶች መኻከል ብታድሩ) በማለት ቀድሞ ኖኅ ለልጁ ለሴም ባወረሰው ኋላም ለአብርሃም ወደ ተሰጠው ወደ ሴም ዕፃ ብትደርሱ
🕊️ “ክነፈ ርግብ በብሩር ዘግቡር” (ከብር እንደተሠሩ እንደ ርግብ ክንፎች) በማለት በዚያች የሴም ርስት ውስጥ በየዋህነቷ በርግብ የተመሰለችው ቅድስት ድንግል ማርያምን ክንፎቿ በብር በተሠሩ ርግብ አምሳል ማለት የሥጋዋን የነፍሷንና የሕሊናዋ ንጽሕናን በብር በተሠሩ ክንፎች አምሳል ማየቱን ከገለጸ በኋላ “ወገበዋቲሃኒ በሐመልማለ ወርቅ” (ወገቦቿም በወርቅ ቅጠል የተሠሩ) በማለት በወርቅ የተመሰለ ወገበ ልቡናዋ “እንደ ቃልኽ ይኹንልኝ” በሚል የቅዱስ ገብርኤልን ብሥራት በማመን የጸና መኾኑን በምስጢር ገልጧልና፡፡

🕊️ አንድም ርግበ ሰሎሞንም ተብላለች ሰሎሞንም በመንፈሰ እግዚአብሔር በመቃኘት በየዋህነቷ በርግብ የተመሰለች ቅድስት ድንግል ማርያምን ስፍር ቊጥር ከሌላቸው ከሌሎች ሴቶች ተለይታ ለአምላክ እናትነት ብቸኛ ተመራጪ መኾኗን በማሕ ፮፥፰‐፲ ላይ “አዋልድ እለ አልቦን ኊልቊ” (ቊጥር የሌላቸው ቆነዣዥት አሉ) በማለት ስፍር ቊጥር የሌላቸው እጅግ የበዙ ሴቶች መኖራቸውን ከተናገረ በኋላ “አሐቲ ይእቲ እምኔሆን ርግብየ ፍጽምትየ” (ርግቤ መደምደሚያዬ አንዲት ናት) ብሎ ከነዚያ ኹሉ ተለይታ በየዋህነቷ በርግብ የተመሰለችው ቅድስት ድንግል ብቸኛ እናት ትኾነው ዘንድ በአምላክ የመመረጧን ነገር ተናግሯልና፡፡
✝️ በመጨረሻም ሊቁ፤ ሙሴን ከፈርዖን፣ ኢያሱን ከአማሌቅ፣ ሕዝቅያስን ከሰናክሬም፣ ዳዊትን ከጎልያድ እጅ በተራዳኢነቱ የጠበቀ በርኅራኄው የታወቀውን ቅዱስ ሚካኤልንና፤ ፍሡሐ ገጽ (ፊቱ በደስታ እያበራ) “ተፈሥሒ ፍሥሕት ኦ ምልዕተ ጸጋ” (ጸጋን የተመላሽ ደስተኛዪቱ ሆይ ደስ ይበልሽ) ብሎ የደስታ ብሥራትን ያበሠራትን፤ በኋላም ጌታን በወለደችው ጊዜ ለዕረኞች “እነሆ፥ ለሕዝቡ ሁሉ የሚሆን ታላቅ ደስታ የምሥራች እነግራችኋለሁና አትፍሩ፤ ዛሬ በዳዊት ከተማ መድኃኒት እርሱም ክርስቶስ ጌታ የሆነ ተወልዶላችኋልና” በማለት አስደሳች ብሥራትን ከተናገረው ከቅዱስ ገብርኤል ጋር ወደ ርሱ እንድትመጣ በተመስጦ ሆኖ ይማፀናታል፡፡
🌼🌹 ️ የአምላክ እናት ሆይ ዛሬም ከርኅሩኁ ከቅዱስ ሚካኤልና ከደስተኛው ከቅዱስ ገብርኤል ጋር በመምጣት ትባርኪንና፤ በነጭ በቀይ አበባ ከተመሰለ ልጅሽ ትለምኝልኝ ዘንድ እንማፀንሻለን፡፡
* በመጋቤ ሐዲስ ዶክተር ሮዳስ ታደሰ
ሰላም ለእናንተ ይሁን እንደምን ሰነበታችሁ እነሆ 5️⃣ኛ ዙር


1️⃣ አባታችን ያዕቆብ ከእግዚአብሔር ጋር ሲታገል ያደረበት ስፍራ

ሀ/ከነአን
ለ/ኡር
ሐ/ጵንኤል (ዘፍ32-30
መ/ ዮርዳኖስ

2️⃣ በመፅሀፍ ቅዱስ የመጀመያው የብሉይ ኪዳን ሰአሊ ማነው ?

ሀ/ አዳም
ለ/ሙሴ
ሐ/አሮን
መ/ ኢያሱ

3️⃣ በፀሎቱ ለሶስት አመት ተኩል ሰማይ ዝናብ እንዳያዘንብ የዘጋው የእግዚአብሔር ነብይ ማነው?

ሀ/ ኤልሳ
ለ/ ኤልያስ
ሐ/ ዳንኤል
መ/ ኤርሚያስ

4️⃣ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሲሰቀል ሰማይ ለስንት ሰአት ጨለመ ??

ሀ/ ከ3--9 ሰአት
ለ/ ከ6--12 ሰአት
ሐ/ ከ6--9 (ማቴ  27-45
መ/ ከ3--6 ሰአት


5️⃣ ነብዩ ከሰፒራ የወለደው የመጀመርያ ወንድ ልጅ ስሙ ምን ይባላል ??

ሀ/ ቢንያም
ለ/ ጌርሳህ ዘፀ 2-22
ሐ/ ሮቤል
መ/ ባኮስ

6️⃣ ሰባቱ ሊቃነ መላዕክት የሚባሉት ዘርዝሪ?

ቅዱስ ሚካኤል
ቅዱስ ገብርኤል
ቅዱስ ሩፋኤል
ቅዱስ ዑራኤል
ቅዱስ ራጉኤል
ቅዱስ ፋኑኤል
ቅዱስ ሳቁኤል

7️⃣ በእለተ ረቡዕ የተፈጠሩ ፍጥረታት  ስንት ናቸው ስማቸውስ ??

# ሶስት ናቸ
-- ፀሀይ
--ጨረቃ
-- ከዋክብት

8️⃣በቅዳሴ ጊዜ አምስት መስዋዕቶች አሉ ምን ምን ??

ቁርባን መስዋዕት
የመብራት መስዋዕት
የከንፈር መስዋት
የእጣን መስዋዕት
የሰውነት መስዋዕት

9️⃣ አምስቱ ፍኖተ ጽድቅ የሚባሉትን ዘርዝሪ?

ፍቅር ትህትና ፆም ጸሎት ምፅዋት

🔟 ቤተክርስቲያን ሶስት መቅደሶች አሏት ምን ምን ይባላሉ ??

ቤተ መቅደስ
ቤተ ቅድስት
ቤተሌሔም

1️⃣1️⃣ በገዛ ወንድሟ የተደፈረችው የዳዊት ልጅ ስሟ ደሊላ ይባላል ?

2ሳሙ 13÷1 ሀሰት

1️⃣2️⃣ በሀገራችን ኢትዮጵያ የመጀመሪያው ሊቀጳጰጳስ አቡነ ተክለሀይማኖት ይባላሉ??

ሀሰት  ፍሬምናጦስ (አባሰላማ

1️⃣3️⃣ ቅዳሴ ማርያምን የደረሰው አባት  ቅዱስ ዮሃንስ አፈወርቅ ነው??

ሀሰት አባ ህርያቆስ ነው

1️⃣4️⃣ ከሴቶች ከተወለዱት መካከል ከእርሱ የሚበልጥ የለም ብሎ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተናገረለት ለማነው??

ሀ/ ለቅዱስ ዳዊት
ለ/ለመጥምቁ ዮሃንስ (ሉቃ 7-28)
ሐ/ ለነብዩ ዳንኤል
መ/ለነብዩ ሙሴ

1️⃣5️⃣ የኢያሪኮን መራራ ውሃ ያጣፈጠው ነብይ ማን ይባላል

ሀ/ነብዩ ኤልያስ
ለ/ነብዩ  ሙሴ
ሐ/ ነብዩ ኤልሳዕ
መ/ነብዩ ዳንኤል


1️⃣6️⃣ በማንም ላይ ክፋትን አትስሩ አትፍረዱ ይህንን ከጠበቃችሁ እርስቲቱን ትወርሳላችሁ ያለው አባት ማነው ??

ሀ/ አቡነ ሺኖዳ
ለ/ ዮሃ አፈወርቅ
ሐ/ አባ መቃርስ
መ/ አባ ይስሀቅ

1️⃣7️⃣ሰባቱ ሰማያት የሚባሉትን ዘርዝሩ?

ሰማየ ሰማያ
መንበረ መንግስት
ሰማይ ውዱድ
ኢየሩሳሌም  ሰማያዊት
ኢዮር
ራማ
ኤረር


1️⃣8️⃣የነብዩ ሙሴ ሚስት የነበረችው ኢትዮጵያዊቷ ሴት ማን ትባላለች ?

ሀ/ ቤርሳቤህ
ለ/ ሩት
ሐ/ሰፒራ (ዘፀ 2-21)
መ/ማርያም

1️⃣9️⃣ አንቀፀ ብርሀን የተኘውን የእመቤታችን የምስጋና ፀሎት የደረሰው ኢትዮጵያዊው ቅዱስ ያሬው ነው ??

እውነት

2️⃣0️⃣ በአዲስ ኪዳን የመጀመሪያዎቹ ሰባቱ ዲያቆናት የሚባሉትን ዘርዝሪ ??

   ሐዋ. ሥራ 6
5፤ ይህም ቃል ሕዝብን ሁሉ ደስ አሰኛቸው፤ እምነትና መንፈስ ቅዱስም የሞላበትን ሰው *_እስጢፋኖስን ፊልጶስንም ጵሮኮሮስንም ኒቃሮናንም ጢሞናንም ጳርሜናንም ወደ ይሁዲነት ገብቶ የነበረውን የአንጾኪያውን ኒቆላዎስንም መረጡ።_*
6፤ በሐዋርያትም ፊት አቆሙአቸው፥ ከጸለዩም በኋላ እጃቸውን ጫኑባቸው።


ወስበሀት ለእግዚአብሔር
🕊

   †       †       †
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬

            †
-------------------------------------------------

† እንኳን ለጌታችንና አምላካችን መድኃኔ ዓለም ኢየሱስ ክርስቶስ ዓመታዊ የስቅለት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ፤ አደረሰን። †


🕊   †    መድኃኔ ዓለም   †     🕊



      [  በቀሲስ ኅብረት የሺጥላ   ]

------------------------------------------------

" እርሱም በእውነት ክርስቶስ የዓለም መድኃኒት እንደ ሆነ እናውቃለን " [ ዮሐ.፬፥፵፪ ]

▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
          ድንቅ የሆነ ትምህርት !
                        👇


🕊                   💖                       🕊
🕊


† እንኳን ለጻድቁ አቡነ ይምዓታ እና ለአበው ቅዱሳን መርትያኖስ ወመርቆሬዎስ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ፤ አደረሰን። †

† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †


🕊   †   አባ ይምዓታ ጻድቅ     †     🕊

† ጻድቁ ገድላቸውን የፈጸሙት በኢትዮዽያ ቢሆንም ሃገረ ሙላዳቸው የጥንቱ የሮም ግዛት የሆነችው ታናሽ እስያ ናት:: አባ ይምዓታ ከዘጠኙ [ተስዓቱ] ቅዱሳን አንዱ ናቸው:: ዘጠኙ ቅዱሳን ተወልደው ያደጉት ምንም በአንድ የሮም ግዛት ሥር ቢሆንም መነሻ ቦታቸው ግን የተለያየ ነው::

ሁሉንም አንድ ያደረጋቸው መንፈስ ቅዱስ በኪነ ጥበቡ ነው:: በምክንያት ደረጃ እንግለጸው ከተባለ ደግሞ የአንድነታቸው ምሥጢር :-

፩. የቀናች ሃይማኖታቸው ተዋሕዶ::
፪. ዓላማ [የእግዚአብሔር መንግስት] እና
፫. ገዳማዊ ሕይወት ነው::

አባ ይምዓታን ጨምሮ ሁሉም ቅዱሳን ዘራቸው ከቤተ መንግስት ነው:: እነርሱ ግን ምድራዊውን ክብር ንቀው ሰማያዊውን ክብር ገንዘብ ማድረግን መርጠዋል:: አስቀድመው ቅዱሳት መጻሕፍትን ያጠኑት አበው በተለያየ ጊዜ እየመነኑ ከሮም ግዛት ወደ ግብጽ በርሃዎች ወርደዋል::

በምናኔ ቅድሚያውን አባ ዸንጠሌዎንና አቡነ አረጋዊ ይይዛሉ:: ዘመኑ የተዋሕዶ አማኞች የሚሰደዱበት ፭ኛው መቶ ክ/ዘመን ነበርና እምነትን ላለመለወጥ ዘጠኙ ቅዱሳን ስደትን መረጡ::

በወቅቱ ደግሞ ለስደት መጠለያ የምትሆንና ከኢትዮዽያ የተሻለች ሃገር አልነበረችም:: ስለዚህም በ፬፻፸ዎቹ ዓ/ም አልዓሜዳ በኢትዮዽያ ነግሦ ሳለ ቅዱሳኑ በአረጋዊ መሪነት መጡ::

ንጉሡም ሲጀመር የእግዚአብሔር እንግዳ ስለሆኑ: ሲቀጥል ደግሞ ቅድስናቸውን ተመልክቶ መልካም አቀባበልን አደረገላቸው:: ማረፊያ ትሆናቸውም ዘንድ አክሱም ውስጥ አንዲት ቦታን ወስኖ ሰጣቸው:: ይህች ቦታ "ቤተ ቀጢን" ትባላለች::

አባ ይምዓታና ፰ቱ ቅዱሳን ወደ ሃገራችን እንደ ገቡ የመጀመሪያ ሥራቸው ቋንቋን መማር ነበር::

ልሳነ ግዕዝን በወጉ ተምረው እዛው አክሱም አካባቢ ሥራቸውን አንድ አሉ:: በወቅቱ በአቡነ ሰላማ: በአብርሃ ወአጽብሐና በአቡነ ሙሴ ቀዳማዊ የተቀጣጠለው ክርስትና በተወሰነ መንገድ ተቀዛቅዞ ነበርና እነ አባ ይምዓታ እንደ ገና አቀጣጠሉት::

ሕዝቡን በራሱ ልሳን ለክርስትና ይነቃቃ ዘንድ ሰበኩት:: የካደውን እየመለሱ: የቀዘቀዘውን እያሟሟቁ ለዓመታት ወንጌልን ሰበኩ:: ቀጣዩ ሥራቸው ደግሞ መጻሕፍትን መተርጐም ሆነ::

ከሃገራቸው ያመጧቸውን ቅዱሳት መጻሕፍት ተከፋፍለው ወደ ግዕዝ ልሳን ተረጐሟቸው:: በዚህም ለሃገራችን ትልቁን ውለታ ዋሉ:: ይህ ሁሉ ሲሆን እነ አባ ይምዓታ የሚመገቡትም ሆነ የሚጸልዩት በማሕበር ነበር:: በመካከላቸውም ፍጹም ፍቅር ነበር:: ጸጋ እግዚአብሔር አልተለያቸውም::

የነ አባ ይምዓታ ቀጣዩ ተግባራቸው ደግሞ ገዳማዊ ሕይወትን ማስፋፋት ሆነ:: ይህንን ለማድረግ ግን የግድ መለያየት አስፈለጋቸው:: እያንዳንዱም መንፈስ ቅዱስ ወደ መራው ቦታ ሔደ::

- ዸንጠሌዎን በጾማዕት::
- ገሪማ በመደራ::
- ሊቃኖስ በቆናጽል::
- አረጋዊ በዳሞ::
- ጽሕማ በጸድያ::
- ሌሎችም በሌላ ቦታ ገዳማትን መሠረቱ::
- አባ ይምዓታ ደግሞ በመንፈስ ቅዱስ መሪነት ምርጫቸው ገርዓልታ [እዛው ትግራይ] ሆነ::

ጻድቁ ወደ ቦታው ሲሔዱ ወንዝ [ባሕር] ተከፍሎላቸዋል:: ወደ ቦታው ደርሰውም ገዳም አንጸዋል:: በቦታውም ብዙ ተአምራትን ሠርተው በርካታ ደቀ መዛሙርትን አፍርተዋል:: የአቡነ ይምዓታ ገዳም ገርዓልታ [በፎቶው ላይ እንደምናየው] እጅግ ድንቅና ማራኪ ነው::

ነገር ግን እዛው ድረስ ሒዶ ለማየት ብርታትን ይጠይቃል:: በተራሮች መካከል ከመቀመጡ ባሻገር የአባቶቻችንን ጽናት የሚያሳይ ድንቅ ቦታ ነው:: ጻድቁ በዚሁ በፎቶው ላይ በምናየው ገዳም ለዘመናት ተጋድለው በዚህች ቀን ዐርፈዋል::


🕊    †    ቅዱሳን መርትያኖስና መርቆሬዎስ   †     🕊

† እነዚህ ቅዱሳን የቁስጥንጥንያ ሰዎች ሲሆኑ የወቅቱ ፓትርያርክ አባ ዻውሎስም ደቀ መዛሙርት ናቸው:: በ4ኛው መቶ ክ/ዘመን አጋማሽ አካባቢ በአርዮሳውያን ምክንያት ስደት በሆነ ጊዜ አባ ዻውሎስ: ቅዱስ አትናቴዎስ: ቅዱስ ኤዎስጣቴዎስና ቅዱስ ሊዋርዮስ ከመንበራቸው ተፈናቀሉ::

በስደቱ ቅዱስ ኤዎስጣቴዎስ ሲያርፍ ቅዱሳኑ አትናቴዎስና ሊዋርዮስ ተመለሱ:: አባ ዻውሎስን ግን በእሥር ቤት ውስጥ ሳለ በንጉሡ ትዕዛዝ አርዮሳውያን አንቀው ገደሉት:: ይህንን ያወቁት 2ቱ ደቀ መዛሙርቱ [መርቆሬዎስና መርትያኖስ] ቅዱስ አባታቸውን ቀብረው ንጉሡን ረገሙት::

አርዮሳዊው ታናሹ ቆስጠንጢኖስም ይህንን በሰማ ጊዜ ፪ቱንም አስመጥቶ በአደባባይ በሰይፍ አስመታቸው:: ይህ ከተከናወነ ከ፶ ዓመታት በሁዋላም ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ የቁስጥንጥንያ ፓትርያርክ ሆኖ በመምጣቱ ሥጋቸውን አፈለሠ:: ቤተ ክርስቲያንንም አንጾ ቀድሶላቸዋል::

† አምላከ አበው ቅዱሳን በምልጃቸው ይማረን:: ከበረከታቸውም ይክፈለን::

🕊

† ጥቅምት ፳፰ [28] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት

፩. አባ ይምዓታ ጻድቅ [ከተስዓቱ ቅዱሳን]
፪. ቅዱሳን መርትያኖስ ወመርቆሬዎስ [ሰማዕታት]
፫. አባታችን ያፌት [የኖኅ ልጅ]

† ወርኀዊ በዓላት

፩. አማኑኤል ቸር አምላካችን
፪. ቅዱሳን አበው [አብርሃም: ይስሐቅና ያዕቆብ]
፫. ቅዱስ እንድራኒቆስና ሚስቱ ቅድስት አትናስያ
፬. ቅድስት ዓመተ ክክርስቶስ
፭. ቅዱስ ቴዎድሮስ ሮማዊ [ሰማዕት]
፮. ቅዱስ አባዲርና ቅድስት ኢራኢ

† "በጐንም ለማድረግ ብትቀኑ የሚያስጨንቃችሁ ማን ነው? ነገር ግን ስለ ጽድቅ እንኩዋ መከራን ብትቀበሉ ብጹዓን ናችሁ:: ማስፈራራታቸውንም አትፍሩ: አትናወጡም:: ዳሩ ግን ጌታን እርሱም ክርስቶስን በልባችሁ ቀድሱት::" † [፩ዼጥ.፫፥፲፫]


†  ወስብሐት ለእግዚአብሔር  †


[ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ ]

▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬

💖                   🕊                    💖
HTML Embed Code:
2024/06/01 00:05:04
Back to Top