TG Telegram Group Link
Channel: S֮t֮r֮o֮n֮g֮ I֮m֮a֮n֮🇵🇸
Back to Bottom
ሰላት ግዴታ እንጂ  ውዴታ
     አይደለም ❗️❗️

እናንተ ደጋግ የአሏህ ባሪያዎች ሆይ ተነሱ በመስገጃችሁ ላይ ታገሱ ወደሱም ተማፀኑ 🌸

@STRONG_IMAN
😊<<አላህን(ሱዕ) ከሚያስረሳህ ድሎት ይልቅ
ወደእርሱ የሚያቃርብህ ድህነት ይሻልካል>>
     
  ኢብን ተይሚያ

          #ያማረ_ጁመአ🥰

@strong_iman
ናፈቁን ያ ረሱለላህ አዲስ ሊሪክስ ነሺ...
NidaTube.com
When neshida was a neshida🤌
Even ግጥሞቹ እራሱ ምነኛ ያማሩ ነበሩ...
@STRONG_IMAN
6645823265 (8)
<unknown>
🍁የዛሬው የቁርዓን ግብዣ🍁

@Strong_iman
ልጅ አግኝቶ ፍቅር ካጣ እና ፍቅር አግኝቶ ልጅ ካጣ ሰው የየትኛው ህመም ይገዝፋል?
Crafting Our Dreams 🎯-1

There is a saying that goes like ;

"Discipline is choosing between what you want now and what you want most"

☆ ልክ ጌታችን አላህ ( ሱብሀነሁ ወተዓላ) እንደነገረን; 
"ذَٰلِكَ مَتَٰعُ ٱلۡحَيَوٰةِ ٱلدُّنۡيَاۖ وَٱللَّهُ عِندَهُۥ حُسۡنُ ٱلۡمَـَٔابِ"

ወይ ጊዜያዊ ፍላጎትህን ታስቀድማለህ ወይ ያማረ መጨረሻን ትመርጣለህ!
ምርጫው ያንተ ነው!

Stay Focused, Stay Committed and Embrace the Reward 🤗

© @islamicpsychologycommunity
@strong_iman
አንዳንዴ ሂወታችሁን ሲዖል ሚያረጉት.... ቤተሰብ ሚባሉ ፍጥሮች ናቸው.....
በማያገባቸው ሚገቡ፣ አጉል ፈራጅ የሚሆኑ ቤተሰቦች.....

Just leave us alone 😑
ደሞ የተናደድኩበት ነገር እዚ ሳልጮህ😭......

ምን ያህል ግን አሽቃባጭ ነን በአላህ....
ልክ አለፍን
ምን የሚሉት ነው አንድ ተጫዋች ሞተና እሄ ሁሉ ስለሱ ወሬ.....
Who cares......😑

ኸረ ቢያንስ አርዕስ አርገን ምናወራውን ነገር እንለይ.....
it's not only about በየቀኑ በአሰቃቂ ሁኔታ ስለሚገደሉና ስለሚጨፈጨፉ ህፃናት ችላ ብለን ሰለሱ ማውራታችን....እሱ ብቻ አይደለም.....

nigaa Ethiopia ላይ ነህ በቁምህ ሞተሀል እኮ.... እሱ እድሜ ልክህን በእውንህ ማታየውን መኪና እየነዳ ነው የሞተው አንተ ግን እዚ በቅጥቅጥ መኪና ለመሄድ ተሰልፈህ ሞተ ብለህ እምቧ ከረዩ ትላልህ😑 ቲሽሽ
እኔ ብቻ ነኝ ግን ማታ ማታ እንቅልፍ እምቢ ሲለኝ......

አንድ ምወደውን ሰው እመርጥና ወይ ከባድ ህምም ታሞ ሊሞት አጭር ጊዜ ቀርቶት ወይ ደሞ ሞቶ ብይ እያዘንኩ እራሴን እዛ ሁኔታ ውስጥ እንዴት እንደምሆን እያሰብኩ እንቅለፍ እንዲወስደኝ ማረገው🥲
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
#ንጹሁ_ፈጅር

የፈጅር አየር እንዴት በዚህ ልክ ንጹህ ኾነ ብለው ለጥበበኛው ቢጠይቋቸው « ከመናፍቃን ትንፋሽ የተጠበቀ በመኾኑ» ሲሉ መለሱ። የዚህን ውድ ሰዓት አየር ለመሳብ የታደለ ሰው፣ የአዕዋፋቱን አዝካር ማዳመጥ የቻለ የሰአቱን ዝምታ አላህን በማወደስ ያሳመረ ሰው በእርግጥም ብዙ ጸጋዎች ተሰጥተውታል።

አላህ ደጋግሞ ይረዝቀና
©best kerim
:
@strong_iman
🥹...¡
🍁የዛሬው የቁርዓን ግብዣ🍁

تِلَاوَةٌ طَيِّبَةٌ لِسُوْرَةِ ٱلْقِيَامَةِ | ٱلشَّيْخُ : مُحَمَّدٌ ٱلْلُّحَيْدَانُ.
@STRONG_IMAN
🦋ቀልብ በቸልተኝነት ትቢያ ውስጥ የተዘፈቀች የጨለማ ጌጥ ናት ፣መያዣዋ ፊክር ፣ብርሃኗም አሏህን ማውሳት ፣ሳጥኗም ሶብር ነው።

ሰይዲ አህመድ አል-ሪፋዒይ
S֮t֮r֮o֮n֮g֮ I֮m֮a֮n֮🇵🇸
#ከታሪክ_ቅምሻ [ብላቴናው ጀግና] ታዳጊ ነው ግና አፈር ፈጭቶ ጭቃ አቡክቶ አላደገም። ስለ ኢስላም በልጅነቱ ተምሮ ዲኑን ለመርዳት እያለመ፣ በአላህ መንገድ ነፍሱን ለመሰዋት እያሰበ ያደገ ብላቴና ነው። አረፋ ብልጭልጭ ይሉታል አብረውት ያደጉ ልጆች። ጉላም አል ፊቃኢም ሲሉ ይጠሩታል በጀግንነቱ የተደመሙበት የፈረንሳይ የመስቀል ጦረኞች። እንዴት አይገረሙበት ገና በልጅነቱ የአላህ ጠላቶች ኢስላምን ሲያዳክሙ…
#ከታሪክ_ቅምሻ
[ከአሚርነት ወደ አናፂነት]

ዐሊ ኢብን መእሙን አል-ዐባሲ በአንድ ወቅት የሙስሊሞች አሚር /አስተዳዳሪ/ ነበር፡፡ እጅግ የናጠጠ ሀብታምና ከኹለፋኦች ዝርያ የሆነው ይህ ሰው

ኑሮዉንም ያደረገው በእጅጉ ዉድ በሆኑ ጌጣጌጦች ባሸበረቀዉና ቅንጦት ከሞላበት ቤተ-መንግስቱ ነው። ከዚያው ግቢው ዉስጥ ልቡ ያሰበው፣ ዉስጡ የተመኘዉና የጎመዠው የዱኒያ ጥቅምና ሥጋዊ ፍላጎት ሁሉ አለለት። እንዲህ ሁሉ ነገር የተሟላለት ቢሆንም ቅሉ ዉስጡ ሠላም አልነበረዉም፡፡ ግራ ቀኙን በዱኒያ ፀጋዎች የተከበበ፤ በድሎቷ መሓል የሰጠመ ቢሆንም የሆነ ነገር እንደጎደለው ይታወቀዋል፡፡ ሙሉ እርካታን ለመታደል አልበቃም፡፡ ከዱኒያ መስፋት ጋር ዉስጣዊና እዉነተኛ የሆነ እርጋታና እርካታ ርቆታል።

ይኸው ሰው አንድ ቀን ከዉብ ቤተ-መንግስቱ ሰገነት አሻግሮ ሲመለከት እሱ ከሚኖርበት ዉጭ የሆነ በሌላ የሰው የዓለም ክፍል የሚኖር አንድ የጉልበት ሰራተኛ ያያል፡፡ ይህ ሰራተኛ በየቀኑ ዉሎው ከዚያ ነው፡፡ ቀኑን ሙሉ ላቡን ጠብ አድርጎ እስኪደክመው ይሰራል፡፡ በማለዳ ሥራ ገብቶ ሲሰራ ከቆየ በኋላ ፀሐይ ከምድር ከፍ ስትል ከዚያው ከሚሠራበት ከጤግሮስ ወንዝ ዳርቻ ወዱእ ያደርግና እርጋታ በተሞላበት ሁኔታ ሰላት ይሰግዳል - ሁለት ረከዓ- የዱሓ ሰላት። ፀሐይ ለመጥለቅ ስታዘቀዝቅ ደግሞ ወደቤቱ ይጣደፋል፡፡ ፆመኛ ነዉና ከፀሐይዋ ቀድሞ ገብቶ እቤቱ ለማፍጠር ይገሰግሳል።

ይህን ሰው አንድ ቀን አሚሩ ወደ ቤተ-መንግስቱ አስጠራዉና ስለኑሮው ሁኔታ ጠየቀው፡፡ ሰራተኛዉም ሰዉዬ ሌላ የገቢ ምንጭ እንደሌለዉና በዚሁ ሥራ በሚያገኘው ገቢ ሚስቱን፣ ሁለት እህቶቹን እና ወላጅ እናቱን እንደሚያስተዳድርነገረው፡፡ ልማዱ አድርጎ በየቀኑ ይፆማል፤ በሱና ሰላቶችም ላይ ይበረታል፡፡ እቤቱ ሲገባም ቤት ባፈራው ነገር ደስ እየተሠኘ ያፈጥራል።

አሚሩ ሰዉየዉን ሲያዳምጠው ከቆየ በኋላ 'በኑሮህ ያልተመቸህ የምትማረርበትና የምረዳህ ነገር ካለ' ሲል ጠየቀው፡፡ ሰራተኛው ሰዉዬ “ምስጋና የዓለማት ጌታ ለሆነዉ ለአላህ ሱብሓነሁ ወተዓላ ይሁን አልሐምዱሊላህ ምንም አልፈልግም ምንም ችግር የለብኝም አላህ ይስጥልኝ ብሎት _ በዚሁ ተሰነባበቱ፡፡

ከቀናት በኋላ አሚሩ ቤተ-መንግስቱንና አሚርነቱን ጠፋ፡፡ ከዓመት በኋላም ኹራሳን በሚባለው አገር በአንድ የእንጨት ዉጤቶች መሥሪያ ቦታ ዉስጥ ሙቶ


ተገኘ፡፡ አሚሩ ደስታን ፍለጋ አገር ለቀቀ፡፡ እርካታንም ያገኘው በቤተ መንግስት የቅንጦት ኑሮ ዉስጥ ሣይሆን በእጅ ሠርቶ ከሚያገኘው ገቢ ዉስጥ ነበር።

ደረቅ ዳቦ ከሠላም ጋር እየፈሩ እየተንቀጠቀጡ ከሚበሉት የማር ወለላ በላይ ይጣፍጣል፡፡ ፈተናዎች ከሚበዙበት የቤተ መንግሥት ቪላ ይልቅ ገመናን ብቻ ለመሸፈን የምታገለግል ጎጆ በቂ ናት፡፡ የበረንዳ ላይ ኑሮና የገንዳ ዉስጥ ምግብ ከኢማን ጋር ኩፍር ላይ ሆነዉ ከሚተኙበት የስፖንጅ ፍራሽ፣ ከሚጠጡት ቀዝቃዛ ጭማቂ በላይ ያረካል፡፡

ይሉናል – የ 'ላተሕዘን' መፅሐፍ አዘጋጅ ዶ/ር ዓኢድ አልቀርኒ
:
@STRONG_IMAN || LECTURER PAGE
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ዓለም ትኩረት የነፈጋት ምድር። ግፍ እየተቦካ የሚጋገርባት በተንኮል ጭስ የታፈነች መንደር። በደም አበላ የታጠበች በሰምዓታት አጥንቶች የተከበበች አምባ። አዋ እሄም የወንድሞቻቹ ቀን በቀን በግፍ የሚገደሉ ከ ወደ ጋዛ ነው።
ዛሬም መገደላቸው መራባቸው ቀጥሏል?
በእግር ኳስ ድል የምትጨፍሩ "የሸሂዶች ክምር" የተሰኘ ቡድን በጋዛ መኖሩን እወቁ። እዚያ ጎል የሚቆጠረው በደምና በስጋ ነው።
በዱዓ አንርሳቸው እጃችንን ከፍ አድርገን ያ አላህ እንበልላቸው

@STRONG_IMAN
@STRONG_IMAN
HTML Embed Code:
2025/07/08 04:24:14
Back to Top