TG Telegram Group Link
Channel: ABX
Back to Bottom
ይህን ቪዲዮ ልድገማችሁ ...☝️


ያኔ ገዛ በከፍተኛ ሁኔታ ስትወድም፣ ሰዎቿም ክፉኛ ሲረግፉ ...
ይህን በሞት ጥላ መካከል ሆኖ፣ በፍርስራሽ መሀል ተነስት በተበዳዮች ላይ ተስፋ ሊዘራ ቆሞ ሲሰብክ የነበረውን ሰው አስታወሳችሁ አይደል ?

"በጌታችሁ ላይ ያላችሁ ጥርጣሬ መልካም ይሁን። በአላህ ምድር ላይ ነገሮች ሁሉ ያሉት በአላህ እጅ እንጂ በአሜሪካ ወይም በአዝራኢል እጅ አይደለም ። ቀልባችሁ በአላህ ላይ ብቻ ይንጠልጠል።"

እሱ ለተናገረው ነገር ውጤቱን ባያይ እንኳ በእምነቱ ረግቶ፣ በየቂኑ ፀንቶ፣ መልዕክቱን አስተላልፎ ዱንያን ተሰናብቶ ሄደ ። አላህ ይዘንለት።

አላህም ገዛውያንን ለመርዳት እሩቅ አልሄደም። የሆነ ቀን ሱብሒ ሰዓት ላይ አዝራኢልን ወደ ኢራን ተኩሺ አላት። እሷም ተኮሰች። ምላሹ ደግሞ ይኸው መውጫ መንገድ አሳጣት።

አሁን ዐስር ላይ ሐይፋ፣ ቴልአቪቭና ቁድስ በኢራን ሚሳይሎች ክፉኛ እየተደበደቡ ነው።

ፈለስጢን ሆይ በአንድ ዓመት ከምናምን ጊዜ ውስጥ ብቻ ስንት ነገር አስተማርሽን። ሱብሓነላህ!!


https://hottg.com/MuhammedSeidAbx
ከጥቂት ቀናት በፊት አዝራኢል የኢራንን የአየር ክልል ሙሉ በሙሉ ተቆጣጥሬ እንደፈለግኩ እየወጣሁ እየገባሁ ነው ብላ ነበር፡፡ ሆኖምግን ከአገረ ፍልስጤም የነጠቀችውን ክልሏን ግን ከኢራን ሚሳኢሎች መቆጣጠር ባለመቻሏ እንደሻቸው እየፈነጩበት ነው፡፡ ብዙ የተወራላቸው የሚሳይል መቃሚያዎቿ አረር መብላት ቢያምራቸውም አየር ላይ እያዩት እንደቋመጡ ዝም ብለዋል፡፡ እነዚህ እጅግ ውድ የሆኑ መቃወሚያዎች ጉልበታቸው ያለቀው ኢራን በመጀመርያ አካባቢ በተኮሠቻቸው አሮጌ ሚሳይሎች ነው ተብሏል፡፡ አንድ ጊዜ ወደላይ የሚተኮሰው ብቻ 200 ሚሊዮን ዶላር ያወጣል መባሉን ልብ ይሏል፡፡

ክትናንት ወዲያ ጀምሮ ኢራን “ሲጂልን” የመሣሠሉ የአዲሱን ትውልድ ሚሳይል መጠቀም ስትጀምር የአየር መቃወሚያዎቹ በእጅጉ ግራ ተጋብተው ታይተዋል፡፡ ከፊሎቹ በመጀመርያዎቹ ቀናት ሥራ በዝቶባቸው ስለነበር ጥይት የጨረሱ ናቸው፡፡ አንዳንዶቹ እርስ በርስ ሲመታቱ፣ ሌሎቹ ደግሞ በደመነፍስ ከዒላማቸው ውጭ ሲሄዱ ታይተዋል፡፡ ትንሽ ከፍ ብለው ከሄዱ በኋላ መልሰው በራሣቸው ሕንፃ ላይ የወደቁም አሉ፡፡

አዳዲሦቹ የኢራን ሚሳይሎች እንኳን ለመቆጣጠር ለማየትም የሚያስፈሩ ናቸው ተብሏል፡፡ አንድ ነው ተብሎ የተተኮሰው ሚሳይል ዒላማው በታሰበበት ሰማይ ላይ ሲደርስ ባለብዙ ጭንቅላት ሆኖ ወደየኢላማው ስለሚከንፍ ለማክሽፍም አስቸጋሪ ሆኗል፡፡
ሌላው ዛሬ ጠዋት ቢእር ሰበእ ላይ ወድቆ ብዙ ጉዳት እንዳደረሰ የተነገረለት ሚሳይል ደግሞ ጭራሽ በየትና እንዴት እንደወደቀም አልታየም ነው የተባለው፡፡

 እስካሁን ባለው ጥቃት ኢራን የአዝራኢልን በርካታ የደህንነት፣ የወታደራዊና ሳይንሳዊ ተቋማትን አውድሜያለሁ ያለች ሲሆን አዝራኢልም የኢራንን የኒውክሌር ማብለያ ተቋማትና እጅግ በርካታ ኢላማዎች አንድም አላስተረፍኩም ብላለች፡፡
የሚገርመው በመቶዎች የሚቆጠሩ የጦር ጀቶች  ቀን ላይ ያለ የሌለ ኃይላቸውን ተጠቅመው የኢራንን የሚሳይል ማስወንጨፍያ ቦታዎችንና ምሽችን አውድመናል ብለው ቢመለሱ ምሽት ወይም ንጋት ላይ ግን ወደሙ የተባሉት ከሞት የተነሱ ያህል የአዝራኢልን ሰማይ ያጓሩበታል፡፡

በዚህ መልኩ የአየር ላይ ጨዋታው ሲቀጥል፤ መሬት ላይ ደግሞ የሚሳይል ሲስተሞችን ለመቆጣጠርና ለመነጣጠቅ የሳይበር ውጊያዎች ከአየር ባልተናነሰ መልኩ የቀጠሉ ሲሆን በዚህም ኢራኖች አልተቻሉም ነው የተባለው ፡፡

አሁን እንዲህ እንዲህ እያልን እዚህ ደርሰናል፡፡ ወደፊት የሚሆነውን ደግሞ  አላህ ያውቃል፡፡ ብዙ ነገር ላናውቅ እንችላለን አንድ ነገር ግን እርግጠኞች ነን፡፡ በተፈጥሯዊ ሕግ መሠረት ከፍ ያለ ነገር ሁሉ ተመልሶ መውደቁ አይቀርም፡፡ ባለፉት ሰባና ሰማኒያ ዓመታት ዓለምን የፈነጩበት እነዚህ ጽዮናውያን አሁን መውደቂያቸው የተቃረበ ይመስላል፡፡ አሁን ባይወድቁ እንኳ ነገ ተነገወዲያ መውደቃቸው አይቀርም፡፡ አላህ ጥፋትን ለዘላለሙ እንዲነግስ አይሻምና፡፡


ሰላም ለተበዳይ ፍልስጤማውያን፣
ሰላም ለዓለም ሕዝብ ሁሉ


  https://hottg.com/MuhammedSeidAbx
Forwarded from Nejashi Printing Press
ስለ ዕውቀት


ከ”የዕውቀት ኃይል በኢስላም” መጽሐፍ
አዘጋጅ ፡ ኡስታዝ ሙሐመድ ዑመር
****

1-     እንደ ቁራ በመማለድ
አቡ ሙጅሊዝ የተባሉት ሰው እንዲህ ይላሉ ‹‹ከሸዕቢይ የበለጠ እውቀት ያለው ሰው በዘመኔ አላጋጠመኝም፡፡ አንድ ቀን ይህንን ሁሉ እውቀት እንዴት ልታገኝ ቻልክ? ተብለው ተጠየቁና መልስ ሲሰጡ ‹‹ስለሌሎች ጉዳይ ያለኝን ሃሳብ አራግፌ በመጣል ትኩረቴን በሙሉ በእውቀት ላይ በማድረጌ፣ እንዲሁም ወደብዙ ሀገሮች ለትምህርት በመሄዴ፣ በተጨማሪም እንደ እርግበ ትዕግስተኛ ሰው በመሆኔና እንደ ቁራ በጠዋት ማልጄ በመነሳት ነው፡፡›› ያገኘሁት ብለው ሲመልሱ ሰምቻለሁ ብለዋል፡፡ (አክሰሩ ሚን አልፍ ቂሳ)
 
2-    ምግብን ባለማብዛት
ኢማሙ አሽ-ሻፍዒይ (ረ.ዐ) ‹‹ለአስራ ስድስት ዓመታት እስከምጠግብ ድረስ ተመግቤ አላውቅም ምክንያቱም ብዙ መብላት አካልን ያከብዳል፤ ልብን ያደነድናል፤ ብልህነትን ይጎዳል፤ እንቅልፍን ይጋብዛል፤ ከኢባዳ ያደክማል›› አሉ (ኑሩል አብሷር ፊመናቂብ አሀል አልበይት ገጽ 301)

3-    እወቀት የማይወድ ሰው
ኢማሙ አሽ-ሻፍዒይ (ረ.ዐ) ‹‹እውቀት የልብ ሐያት፣ የህሊና ብርሃን ነው፡፡ እናም እውቀትን የማይወድ ሰው ጥሩ ነገር ስለሌለው ከርሱ ጋር ትውውቅም ይሁን ጓደኝነት ሊኖርህ አይገባም››፡፡ (ኑሩል አብሷር ፊመናቂብ አሀል አልበይት ገጽ 301)

4-   ዕውቀት ማለት
ሙሳ ኢብን የሳር ‹‹ሰልማን ለአቡ ዳርዳእ የጻፉት ዳብዳቤ ደርሶኛል ካሉ በኋላ የደብዳቤው ይዘት ‹‹እውቀት ማለት ሰዎች ከዚያም ከዚህም እየመጡ እንደሚቀዱት የምንጭ ውሃ ነው፡፡ በርካታ ሰዎችን መጥቀም ይችላል፡፡ የማይናገሩት ጥበብና እውቀት ሕይወት ያልተዘራበት በድን አካል ነው፡፡ ለሌሎች የማያካፍሉት እውቀት ስግብግብ ሰው እንደያዘው ሃብት አስቀያሚ ነው፡፡ እውቀቱን ለሰዎች የሚያካፍል ሰው ምሳሌው በጨለማ መካከል ሆኖ ብርሃን በማብራቱ አላፊ አግዳሚው ዱዓ እንደሚያደርግለት ሰው ነው›› የሚል መሆኑን ተናግረዋል፡፡ (አድ-ዳሪሚ ቁጥር 568)

5-    ማመዛዘን
አንድ ወቅት ኢማሙ አሽ-ሻፍዒይ (ረ.ዐ) ጥያቄ ቀርቦላቸው መልስ ሳይሰጡ ዝም አሉ፡፡ ለምንድን ነው መልስ ከመስጠት የተቆጠቡት? ብለው ጠየቋቸው፡፡ እሳቸውም መልስ መስጠቴ ወይስ ዝም ማለቴ የትኛው ነው የተሻለ ውጤት ያለው የሚለውን እስከምለይ ድረስ ነው ዝም ያልኩት›› ሲሉ መለሱ (ኑሩል አብሷር ፊመናቂብ አሀል አልበይት ገጽ 301)

6-   ዕውቀትን አለማካፈል
ዶክተር ሙሳ ሻሂን እንዲህ ሲሉ መክረዋል ‹‹እውቀትን ለሌሎች አለማካፈል እንዲሞት ያደርገዋል፡፡ መስጠትና ማስፋፋቱ ግን በባለቤቱ ላይ በሕይወት እንዲኖር ያስችለዋል፡፡ ሽቶ በጠርሙስ ውስጥ ታሽጎ እስከተቀመጠ ድረስ ሊሰጥ የሚችለውን ዋጋ ያጣል፡፡ ወደልብስ ከተርከፈከፈ ግን ባለቤቱንም ሆነ በዙርያው የተገኙትን ሁሉ ይጠቅማል›› (ተርቢየቱ አል-አውላድ)

7-    የእለት ውሎውን መበደል
አንድ ወቅት ለዐሊይ ኢብን አቢ ጣሊብ (ረ.ዐ) “አንድ ሰው የቀን ውሎውን ሊበድል ይችላልን? የሚል ጥያቄ ቀረበላቸው ዐሊይም (ረ.ዐ) እንዲህ ሲሉ መለሱ፡- ‹‹በእለቱ የሚመለከተውን ሳይሰራ፤ ወይም ያለበትን ግዴታ ሳይዋጣ፤ ወይም ክብሩን የሚያሳድግለት ነገር ሳይከውን፤ ወይም የሚያስመሰግነውን ነገር ሳያደርግ፤ ወይም እውቀት ሳይቀስም፤ የእለት ውሎውን በከንቱ ያሳለፈ ሰው ቀኑን አስከፍቷል ነፍሱንም በድሏል›› ሲሉ መልሰዋል (አክሰሩ ሚን አልፍ ቂሳ- ሂሻም አዋድ)


https://hottg.com/NejashiPP
 
በሌላ ዜና ከእንቅልፋችን ብድግ ትንል አዲስ ወሬ ሰምተናል -
የአሜሪካ ነጩ ሰውዬ ሌሊቱን ጄቶቼ ፎርዶ የተባለውን እጅግ ጠንካራውን ጨምሮ የኢራንን ሶስት የኒውሌር ጣቢያዎች ሲደበድቡ አድረው በሰላም ወደማረፊያዎቻቸው ተመልሰዋል ብሏል፡፡

ሲመረጥ ዓለም ላይ ሰላምን ማስፈን ዋና ሥራዬ ነው ብሎ የነበረው ጥራምፕ፤ አሁን ዓለም ከምንጊዜውም በላይ ሰላም ትሆናለች ብሏል በጡሁፉ፡፡ ያው እኔና አዝራኢልን የሚቀናቀን አይኖርም አካባቢውን ብቻችንን በበላይነት እንቆጣጠራለን ማለቱ ነው ትርጉሙ፡፡
ሰውየው ዓለም ላይ የዚህ ዓይነቱን ከባድ ግዳጅ የሚፈጽም ጦር የም ያለ ሲሆን ኢራን ለሰላም እጅ የማትሰጥ (ለኛ የማትገብር) ከሆነ ጥቃቱ በዚህ ብቻ የሚቆም አይደለም ብሏል፡፡

ኢራን በበኩሏ ጥቃቱ እንደተፈፀመባት አምና አሁን ላይ በዚያ አካባቢ የሚገኝ ማንኛውም አሜሪካ ዜጋ፣ ጥቅምም ሆነ የጦር ሰፈር ዒላማዬ ነው ብላለች፡፡

ኢራንን ብቻውን አቅቶት ሲዳክር የነበረው ነተንያሁ፤ የትራምፕን የድፍረት ውሳኔ አድንቆ የዓለም ሰላም የሚገኘው በጉልበት ነው ብሏል፡፡ በርግጥ ሰዎቹ ሳይነጋገሩ ነው ጉዳዩ የተፈፀመው ማለት ይከብዳል ።
እንግዲህ ዓለም ወዴት እየሄደች ይሆን የምናየው ይሆናል።

ቸር ያሰማን፡፡
ሶባሐል ኸይር

https://hottg.com/MuhammedSeidAbx
በዱዓችሁ
***

መካከለኛውን ምሥራቅ አዲስ ገፅታ እናላብሳለን ብለው የተነሱ ሰዎች እየተረዳዱ ይቃወሙናል ብለው ያሰቡትን ይደቁሱ ይዘዋል። በቀናት ሂደት የአዝራኢል አቅም መዳከም የታያት አሜሪካ እሷ የጀመረችውን ተቀብላ ጨርሳላታለች። በኢራን ላይ የተደረገውን ጥቃት ምዕራባውያን ሲደግፉ ሙስሊሞች እና ዐረቦች ኮንነዋል ። ያልኮነኑት ቢያንስ ጉዳዩ አሳስቦናል ብለዋል።

በኢራን ጉዳይ በተሸፈነችውና በተረሣችው ገዛ ባለፉት አሥር ቀናት ውስጥ ብቻ በአማካይ በቀን ከ100 ሰው በላይ ሲገደል ነው የሰነበተው ። በዚህም የተገደሉ ሰዎች ቁጥር 56 ሺህ ደርሷል። ገዛውያን ጥሙ ረሀቡና ቦንቡ አሳር ሆኖባቸዋል። የጦርነቱና የከበባው ጉዳዩ በቅርብ ማብቂያ ያለው አይመስልም ።

ሙስሊሙ መንግሥታት ኅይል ቢኖራቸው እንኳ አንድነት የላቸውም ። ሁሉም በየራሣቸው ጉዳይ ተወጥረዋል። አንዳንድ ጊዜ ይህን ልብ ሰባሪ ግፍ ዝምብለው ከሚመለከቱ ምናለ በልመናና በተማጽኖ እንኳ ማስቆም በቻሉ ያሠኘኛል።

ቲስበሑ


https://hottg.com/MuhammedSeidAbx
- ለቡቲኮች
- ለኮስሞቲክስ
- ለሞባይል ቤቶች
- ለፋርማሲዎች
- ለኬክ ቤቶች እንዲሁም
ለተለያዩ ድርጅቶች፣
ለአከፋፋዮች መረከብ
ለሚፈልጉ በተመጣጣኝ ዋጋ
እናቀርባለን፡፡

በራሳቸው ሎጐ ድርጅታቸውን
ማስተዋወቅ ለሚፈልጉም
በድርጅታቸው ስም እናትማለን
0926688916
0936034545


https://hottg.com/MuhammedSeidAbx
ኢስላም - ወርቃማው የሳይንስ ማዕከል
በሙሐመድ ዐሊ (ቡርሃን አዲስ)
*

8ኛው ክፍለ ዘመን

1. ኻሊድ ኢብን ዘይድ ይባላል፡፡ በኬሚስትሪ ዘርፍ የተመራመረ ሙስሊም ሳይንቲስት ነው…
2. ጃቢር ኢብን ሐያን፡፡ የኬሚስትሪ ሊቅ ለዘመናዊ ኬሚስትሪ ጠንካራ መሰረት የጣለ ሳይንቲስት ነው፡፡ በርካታ መጽሐፍት የደረሰም ምሁር ነው፡፡ በተለይ የኢን-ኦርጋኒክ ኬሚስትሪ አባት ነው፡፡
3. አል-አስመዒ፡፡- በሶስት የባዮሎጂ ትምህርቶች የተመራመረ ሳይንቲስት ነው፡፡ የእንስሳት ሳይንስ /Zoology/፣ የእፅዋት ሳይንስ /Botany/ እና የእንስሳት እርባታ ሳይንስ /Animal production/፡፡
4. አል-ኸዋሪዝሚ ይባላል- የሂሳብ ፕሮፌሰር እና የአል-ጀብራ (የሒሳብ ስሌት) ጥናት አባት ነው፡፡ በተጨማሪም በአስትሮኖሚ፣ በትሪጎኖሜትሪና በጂኦሜትሪ ጥናቶች የመጠቀ ሙስሊም ጠቢብ ነው፡፡

9ኛው ክፍለ ዘመን

5. አል-ኪንዲ፡- የመጀመሪያው ተብሎ የሚገመተው ሙስሊም ፈላስፋ ነው፤ በአስትሮኖሚ (ኦፕቲክስ) ና በፊዚክስም ድንቅ ሳይንቲስት ነው፡፡
6. አል-ዲነዋሪ፡- በሂሳብ፣ በቋንቋና በባዮሎጂ ዘርፎች አስደናቂ ግኝቶች የነበሩት ሳይንቲስት ነው፡፡
7. ሣቢት ኢብን ቁራ፡- በአውሮፓውያን ዘንድ ቴቤዝ በሚለው ስሙ ይታወቃል፡፡ በአስትሮኖሚና በሂሳብ ጥናቶች አንቱታን ያተረፈ ሊቅ ነው፡፡
8. አጥ-ጦበሪ፡- በህክምና ሳይንስ፣ በህክምና ስነ-ምግባር፣ በህክምና ድርሳናትና በሂሳብ ትምህርቶች “ተዓምረኛ ነው” የተባለለት ሳይንቲስት ነው፡፡
9. አል-ፈርጋኒ፡- የሲቪል መሃንዲስ ነው፡፡ በኤሮዳይናሚክስ ሥራዎቹ ሰዎች ተደምመውበታል፡፡ ከዳቪንቼ ስድስት መቶ ዓመታት በፊት የበረራ ሳይንስን ፈጥሮ አሳይቷል፡፡
10. አል-ራዚ፡- በውስጥ ደዌ ህክምና ሳይንስ ለዘመናዊ ህክምና መሰረት የጣለ ዶክተር ነው፡፡ በ20 ቅፆች የተሞላ መጽሐፉ ለአውሮፓ የሰባት መቶ ዓመታት ማስተማሪያ ነበር፡፡

10ኛው ክፍለ ዘመን

11. አል-ዘህራዊ፡- የቀዶ ህክምናን ሳይንስ በአውሮፓ የጀመረ ሳይንቲስት ነው፡፡ ህክምናን በተመለከተ ሰላሳ ቅፅ መጽሐፍ አለው፡፡ ሲሪንጅን (የሕክምና መርፌ) የፈለሰፈ ሳይንቲስትም ነው፡፡
12. ሙሐመድ አል-ቡዝጃኒ፡- በአስትሮኖሚ፣ በአል-ጀብራና በጂኦሜትሪ ከዓይን ያውጣህ የተባለ ሊቅ ነው፡፡
13. ኢብን አል-ሐይሠም፡- ከኒውተን በፊት የኒውተንን ሕግ የቀመረ፤ ከአንስታይን በፊት የብርሃንን ቁሳዊ ባህሪ የተናገረ በሰባት ቅፆች የፊዚክስን ፅንሰ-ሀሳቦች የነደፈ ሳይንቲስት ነው፡፡
14. አል-ቤሩኒ፡- የሒሳብን ጥበብ የተረዳና በቀላሉ ማስረዳት የቻለ ፊት አውራሪ ጠቢብ ነው፡፡
15. ኢብን ሲና፡- በህክምና ዘርፍ የጻፈው ግዙፍ መጽሐፍ ከአንድ ሚሊዮን ያላነሱ ቃላት እንዳሉት ተመራማሪዎች ይናገራሉ፡፡ በህክምናና (መድሐኒት ቅመማ) የተባ ፈጠራ ያለው ሳይንቲስት ነው፡፡

11ኛው ክፍለ ዘመን

16. ኢማም አል-ገዛሊ፡- የሳይንስ ሚዛን የሆኑ ሁሉ አቀፍ ተመራማሪ፡፡
17. ኢብን ዙህር፡- በቀዶ ህክምና ሳይንቲስት ትልቅ ሥራ የሰራ ሳይንቲስት፡፡
18. ኢብን በይጧር፡- የፋርማኮሎጂ (የመድኃኒት ምርምር) ሳይንቲስት፡፡
19. አል-ኢድሪሲ፡- የጂኦግራፊ ሊቅ፡፡ የመጀመሪያውን ሉል (ግሎብ) የነደፈ ሰው ነው፡፡
20. ኢብን ባጃህ፡- የህክምና ሳይንቲስት
21. ኢብን ሪድዋን፡- የህክምና ሳይንቲስት
12ኛው ክፍለ ዘመን
22. ኢብን ጡፈይል፡- የህክምና ሳይንቲስት
23. ኢብን ዐሊ አልኪማዊ፡- የኬሚስትሪ ሊቅ
24. አል-ባግዳዲ፡- ኬሚስት፣ ሀኪምና የጂኦግራፊ ሳይንቲስት
25. አሱሪ፡- የእፅዋት ሳይንስ ተመራማሪ

13ኛው ክፍለ ዘመን

26. ነስረዲን አል-ቱሲ፡- የጂኦሜትሪ፣ የአልጀብራና የአስትሮኖሚ ሊቅ
27. ኢብኑ ነፊስ ፡- (የአናቶሚ አባት) ከዊሊያም ሀርቬ በፊት የደም ዝውውርን ያጠና ሳይንቲስት
28. ቁጥቡዲን አል-ሺራዚ፡- የአስትሮኖሚ፣ የጂኦግራፊና የሒሳብ ሊቅ
29. ኢብን አልበናህ፡- የህክምናና የሒሳብ ሊቅ
30. አቡል ፊዳ፡- የአስትሮኖሚና የሒሳብ ሊቅ
31. ኢብን ሩሽድ፡- የህክምና ሳይንቲስት
14ኛው ክፍለ ዘመን
32. ኢብን አሽ-ሻጢር፡- የአስትሮኖሚና የሒሳብ ሊቅ
33. አል-ፋሪሲ፡- የኬሚስትሪ ሊቅ
34. ኢብን አል-መጅዲ፡- የሒሳብና የአስትሮኖሚ ሊቅ

ድንቅ መጽሐፍ ነው፡፡ ያንብቡት ነጃሺ መፃሕፍት መደብር ያገኙታል፡፡
ነጃሺ የዕውቀት ማዕድ፡፡


https://hottg.com/MuhammedSeidAbx
ባለፈው ለታ እዚሁ ሰፈር የሆነ ቪዲዮ ተለቆ ነበር፡፡ የገዛ ታጋዮች ክላሽ ይዘው ታንክ ሲያባርሩ ላየ በሬ እንጂ ብረት ለበስ የሚያባርሩ አይመስልም ነበር፡፡ የዚህ ዓይነቱ ድፍረት በርግጥ ለኛ ዓይነቱ ሰው የጤና አይመስልም፡፡
ትናንት ደግሞ ሌላ ቪዲዮ ተመከለትኩ፡፡ ሰው በዚህ ልክ እንዴት ይዳፈራል አልኩ፡፡
በርግጥ ገዛ ምግብና ውሃ አጥታ ከተራበች ከተጠማች ከዓመት በላይ ሆናት፡፡ ከተማዋም ከፈራረሠች ወራት ተቆጠሩ፡፡ ባለፈው ሳምንት አንዱ የአዝራኢል ጦር አዛዥ ሰሞኑን ቀን በኻን ዩኑስ ክፍለ ከተማ ብቻ ከ10ሺ በላይ ሕንፃዎችን አውድመናል ሲል ሰምቼው ነበር፡፡ ሰዎቹ ሕንፃዎችን የሚያወድሙት ወደው አይደለም፡፡ አንዳንድ ጊዜ አንድ የሚፈልጉት ነጠላ ሰው በዚህ አካባቢ አለ ብለው ከገመቱ ያለ አንዳች ርሕራሄ በቅጽበት ሙሉውን ብሎክ ወደፍርስራሽነት ይለውጣሉ፡፡ ከተማዋ በዚህ መልኩ ብትፈርስም ነፍስ ይኖራል ተብሎ በማይታሰብበት አስፈራ ፍርስራሽ መካከል ከምግብና ዉሃ በላይ ነፃነት የጠማቸው ወጣቶች ይኖራሉ፡፡
ትናንት በተለቀቀው ቪዲዮም የታየው ይኸው ነበር፡፡ የተወሰኑ ታጋዮች አንዲትን እግሯ ብረት የሆነ እጅግ ዘመናዊ  የጦር ተሸርካሪ ለማደን ሲከታተሉ ከቆዩ በኋላ የሆነ ቦታ ላይ መቆሟን አስተዋሉ፡፡ በዚህን ጊዜ ከነርሱ መካከል አንዱ ወጣት ባዶ እግሩን የሚፈነዳ ነገር ይዞ ወደዚያ ይሮጣል፣ እዚያ እስኪደርስ ያለው ርቀት አጭር ቢመስልም ለተመልካች ጭምር ግን ልብን ቀጥ ያረጋል፡፡
ወጣቱ ልክ እንደደረሰ ተሸከርካሪው ላይ ወጥቶ በአናቱ በመግቢያው በኩል ወደ ውስጥ የሚፈነዳውን ነገር ወረወረው፡፡  ወዲያው ከውስጥ ጩኸት የተሰማ ሲሆን ተሸከርካረውም በፍንዳታ ነደደ፡፡ እውስጡ የነበሩ ሰባት ወታደሮች አንድ ኮሎኔልን ጨምሮ ለመውጣት ጊዜ አላገኙም፡፡ እያለከለከ የሚመለስው ወጣት ተረፍኩ እፎይ ከማለት ይልቅ ጌታዬ ሆይ ለዚህ ዓይነቱ ተልዕኮ ሁለት ሦስቴም አራቴም ምረጠኝ እያለ አምላኩን ሲማፀን ይሰማል፡፡ ወጣቱ በሰላም ወደተነሳበት ተመለሰ፡፡ ተልዕኮውን ራሱ ይቅረጽ ሌላ ሰው አብሮት ይኑር ማወቅ አልቻልኩም፡፡
ፍንዳታውን የሰሙ የወራሪ ወታደሮች ወዲያው በሄሊኮፍተር እቦታው ላይ ቢደርሱም ሰዎቹም ተሽከርካሪውም ነደው አልቀው የከሰለ ነገር ብቻ ነው ያገኙት ተብሏል፡፡
ይህ ወደ ሁለት ዓመት የተጠጋው የገዛ ወጣቶች ሕይወት ነው፡፡ ወደ ሁለት ሚሊዮን ከሚጠጋው አጠቃላይ ነዋሪ በርግጥ በ10 ሺዎች የሚቆጠሩ ወጣቶች አልቀዋል፡፡ እንዲያም ሆኖ ግን ያሉት አሁንም አሉ፡፡
 ይህ ጦርነት ገና ብዙም ሳይሄድ መቆም ይችል ነበር፡፡ ግና በፖለቲካዊ ምክንያቶች ሊቀጥል እንደቻለ ብዙዎች ይስማማሉ፡፡ ጦርነቱ ከቆመ የነተንያሁ መንግሥት ከሥልጣኑ ስለሚወገድ በዚሁ ፍራቻ የንፁሐን ሰቆቃ ቀጥሏል፡፡ ነተንያሁ ሙሉ ድል/total victory ብቻ ነው የምንፈልገው በእብሪት በተደጋጋሚ ቢያውጅም የገዛ ወጣቶች በቀላሉ እጅ የሚሠጡ አይመስሉም፡፡
ጫና የበዛበት የነተንያሁ መንግሥት የዚህ ቪዲዮ መለቀቅ ተጨማሪ ጫና ሆኖበታል፡፡ በገዛ አሸዋና ፍርስራሽ ወታደሮቻችን እየተቀበሩ ነው፣ ያለ ድርድርም በጦርነት ታጋቾቻችን የሚለቀቁበት ዕድል ዜሮ ነው በማለት ተማረዋል፡፡  ራሱ ጦርነት ፈጥሮ ራሱ ሰላም አመጣሁ የሚለው የአሜሪካው ነጩ ሰውዬ ሰሞኑን ጥረቶች አሉ ያለ ሲሆን የምር ይሁን እንደተለመደው የማዘናጊያ ንግግር የታወቀ ነገር የለም፡፡
ለዓለም ሕዝቦች ሁሉ፤ በተለይ ደግሞ ሰቆቃቸው ለረዘመው ፍልስጤማውያን ሰላምና ፍትህን እንመኛለን፡፡

ሶባሐል ኸይር

ቪዲዩውን ከታች 👇 ይመልከቱ።

https://hottg.com/MuhammedSeidAbx
Forwarded from Nejashi Printing Press
የሙሐረም ወር ታላቅነት
ኢስላማዊው አቆጣጠር አንድ ብሎ ከተጀመረ እነሆ 1447 ዓመት ሆነው፡፡ የሂጅሪያ ቆጣጠር ይሠኛል፡፡ የሂጅሪያውን አቆጣጠር ለሙስሊሞች የመቁጠሪያ ዓመት ሆኖ እንዲቀጥል ያስቀመጡት ከአላህ መልዕክተኛ ሰ.ዐ.ወ. ህልፈት በኋላ በመሪነት ከአቡበክር ቀጥሎ ሁለተኛው ሰው የሙስሊሞች ኸሊፋው ዑመር ኢብኑል ኸጧብ (ረ.ዐ.) ናቸው፡፡ ይህ መደረጉ የሂጅራን ታላቅነትን የታሪክን ማርሽ ቀያሪነት ያሳያል፡፡
ሂጅራ ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ.) ከመካ ወደ መዲና የተሠደዱበት የጉዞ ሂደት ነው፡፡ በጥቅሉ ስደት ማለት ሲሆን ሙስሊሞች በሃይማኖታቸው ምክንያት ከሚደርስባቸው ጭቆና ለመሸሽ ነበር ወደ መዲና የተሰደዱት፡፡
1447ኛው ዓመተ ሂጅራ ዛሬ ገባ፡፡ የኢስላማዊው አቆጣጠሩ የመጀመርያው ወር ሙሐረም ይሠኛል፡፡
-       በኢስላም ውስጥ አላህ ክብር ከሠጣቸው አራት ወራት ውስጥ አንዱ ነው፣
-       ለወሩ ክብር ሲባል በውስጡ ጦርነት የተከለከለ ነው፣
-       በውስጡ የሚሠሩ መልካም ነገራት ትልቅ ምንዳ እንዳላቸው ሁሉ በደሎችን ኃጢኣቶች ከባድ ቅጣት አላቸው፣
-       አላህ ያከበረውን ወር አለማክበር አላህን ካለማክበር ይታያልና፣
-       ሙሐረም የአላህ መልዕክተኛ ሰ.ዐ.ወ ሸህሩሏህ አል-ሙሐረም (የተከበረው የአላህ ወር) ብለውታል፤
-       የአላህ ወር ተብሎ መጠራቱ ወሩ ያለውን ክብር ያሳያል፣
-       ፆም በወሩ ውስጥ ከሚወደዱ ተግባራት መካከል አንዱ ነው፣
-       የአላህ መልዕክተኛ  ሰ.ዐ.ወ. ከረመዷን ቀጥሎ ምርጡ ፆም  የሙሐረም ወር ፆም ነው ብለዋል፣
-       በዚህ ወር ውስጥ ያለው አሥረኛው ቀን ደግሞ ዓሹራ ይሠኛል፣ 
-       ዓሹራ አላህ ሱ.ወ. ለነቢዩ ሙሳ ዐ.ሰ. በፊርዐውን ድል የሠጠበት ቀን ነው፣
-       ዓሹራ በአላህ ያመኑ ምእመናን ከአምባገነኑና ከሀዲው ፊርዐውን ጭቆና ነፃ የወጡበት የድል ቀን ነው፡፡
-       ዓሹራ የምስጋና ቀን ነው፣
-       የዓሹራን ቀን መፆም የነቢዩ ሙሳ ዐለይሂ ሰላም እና የነቢዩ ሙሐመድ ሰልለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም ፈለግ ነው፣
-       የዐሹራን ቀን መፆም ያለፈውን ኣመት ወንጀል ያስምራል፡፡
 
አላህ ዓመቱንም፣ ወሩንም ቀናቱንም ይባርክልን፣ መልካም ሥራዎችን ያግራልን፣ ከክፋትና ጥፋት ይጠብቀን፡፡

https://hottg.com/NejashiPP
ከዚህ ከታች ከቀረበው ገጽ ብቻ የሚከተሉትን ትምህርቶች እንወስዳለን።
1- የዓለማችን ወደር ያልገኘለት እጅግ ምርጡ አቀባበል ።
2- ጦለዐል በድሩ ዐለይና ዘመን አይሽሬው ዜማ።
3- ከባልደረባቸው መለየት እስኪያቅት ድረስ የታላቁ ነቢይ ትህትና።
4- መዲና የዓለማችን እጅግ ዕደለኛዋ ከተማ።
5- ሂጅራ በኢስላም ታሪክ ማርሽ ቀያሪ ክስተት።

ይህን መጽሐፍ የምታነቡ ወዳጆች ሁሉ የነቢያችንን ታሪካቸዉን ልክ እንደምናየው አድርገው ያስነበቡንን ለአዘጋጁ ዶ/ር ዐሊ ሶላቢ እና ለተርጓሚው አቡ ቢላል እንዲሁም ለአሳታሚው ነጃሺ ማተሚያ ቤት ባለቤቶች ዱዓ አድርጉ።

https://hottg.com/MuhammedSeidAbx
Forwarded from Nejashi Printing Press
መዲና ሲደርሱ / ዒሽቅ እና ትዝታ

****

የመዲና ሰዎች የአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) ከመካ መነሳታቸውን እንደሰሙ በየዕለቱ ማለዳ ላይ ከቤታቸው እየወጡ ‘አል-ሐርራህ’ በተሠኘ መዲናን ባካበበ ድንጋያማ (ዓለታማ) ሥፍራ ይጠባበቋቸው፡፡ ከእነዚያ ቀናት በአንዱ እንደልማዳቸው ሲጠባበቋቸው ካረፈዱ በኋላ ወደየቤታቸው ተበታተኑ፡፡

በዚህ መካከል አንድ አይሁዳዊ ሰው ከቤቱ ጣሪያ ላይ ወጥቶ የሆነ ነገር እያከናወነ እያለ ከሩቁ ነጫጭ አልባሳትን ለብሰው ወደ መዲና የሚመጡ ሰዎችን አስተዋለ፡፡ እየቆዩና እነርሱም እየቀረቡት ሲመጡ የአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) እና ጓደኞቻቸው መሆናቸውን በመገንዘቡ ራሱን መቆጣጠር አልቻለም፡፡
ስለሆነም “የመዲና ዐረቦች ሆይ! እነሆ የምትጠብቁት ሰው መጣ!” ሲል በጩኸት ለፈፈ፡፡ ይህን የሰሙት ሙስሊሞች መሣሪያዎቻቸውን እያነገቡ አል-ሐርራህ ወደተባለው ሥፍራ ተመሙ፡፡ ከዚያም የዐምር ኢብን ዐውፍ ጎሳ ይዞታ ወደሆነ አካባቢ እየመሩ ወሰዷቸው፡፡ ይህ የሆነው በወርሀ ረቢዕ አል-አወል ዕለተ ማክሰኞ ነበር፡፡ በዚያ ጊዜ አቡበክር (ረ.ዐ) ቆመው የነበረ ሲሆን ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) ግን ተቀምጠው ነበር፡፡ ይህን ያዩና በተለይም ደግሞ ነቢዩን (ሰ.ዐ.ወ) በአካል ተመልክተዋቸው የማያውቁ አንሷሮች ለአቡበክር (ረ.ዐ) ሰላምታ ማቅረብ ጀመሩ፡፡ በዚህ ጊዜ አቡበክር (ረ.ዐ) ጨርቅ ያዙና ከነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) አናት ላይ በማድረግ ከፀሐዩ ሀሩር ጋረዱላቸው፡፡ ሰዎችም ነቢዩን (ሰ.ዐ.ወ) በትክክል አወቁ፡፡

የአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) በበኑ ዐምር ኢብን ዐውፍ መንደር ከአሥራ ሦስት እስከ አሥራ ዘጠኝ ለሚቆጠሩ ቀናት ሰነበቱ፡፡ በዚያ ጊዜም በአላህ ፍራቻ (ተቅዋ) ላይ እንደተመሠረተ የሚነገርለትን የቁባ መስጊድ ገነቡ፡፡
ከዚህ ሁሉ ጊዜ በኋላ ነው እንግዲህ የአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) እና አቡበክር (ረ.ዐ) ወደ መዲና ያቀኑት፡፡ ከእናታቸው በኩል ከሚወለዷቸው በኑ ነጃር ጎሳ መካከል መሳሪያ የታጠቁ አጃቢዎች ተልከውላቸው እርሳቸውና አቡበክር (ረ.ዐ) በመጓጓዣ ግመል ላይ ሆነው ወደ መዲና ገቡ፡፡

በዚያ ዕለትም ‘ሠንየተል ወዳዕ’ በተሠኘው ሥፍራ በርካታ ሕዝብ ተሰብስቦ ምስጋናና ውዳሴ እያሰማ ተቀበላቸው፡፡ መዲና በታሪኳ እንደዚያ ቀን የደስታ እልልታ ገጥሟት አያውቅም፡፡ ዕለቱ በእርግጥም ኢስላም ጠባብ ከሆነው የመካ አስጨናቂ ሕይወት ወደ ሠፊውና አስደሳች ወደ ሆነው የመዲና ሕይወት ሽግግር ያደረገበት ታሪካዊ ቀን ነበር፡፡ የመዲና ሕዝቦች የአላህን ታላቅ በረከትና ጸጋ በደስታ ተቀብለው ምስጋናና ውዳሴ ያሰሙበት ድንቅ ዕለት፡፡ ለምን አመስጋኝ አይሆኑ! ምድራቸው ታሪካዊውን የኢስላም ብርሃን ለዓለም እንድታደርስ ተመርጣለች፡፡ የመጨረሻውንና የነብያት ሁሉ መደምደሚያ የሆኑትን ሙሐመድን (ሰ.ዐ.ወ) ተቀብላ ለማስተናገድ ከመታደል የበለጠ ምን ልቅና ትሻለች! ዕድለኛ ከተማ፡፡

በጊዜው ሁሉም “የአላህ መልዕክተኛ! የአላህ መልዕክተኛ! ሙሐመድ!” እያለ ደስታውን ሲገልጽ ይታይ ነበር፡፡
ሴቶችና ሕፃናት በበኩላቸው ታዋቂውንና ዝነኛውን ግጥም በዜማ እያወረዱ ደስታቸውን ገለጹ፡-

ጦለዐል በድሩ ዐለይና
ሚን ሠኒየቲል ወዳዕ
ወጀበ ሹክሩ ዐለይና
ማ ደዓ ሊላሂ ዳዕ
አዩሀል መብዑሡ ፊና
ጂእተ ቢልአምሪል ሙጧዕ
ጂእተ ሸረፍተል መዲና
መርሐበን ያ ኸይረ ዳዕ

ጨረቃው ወጣልን እሰየው
‘ሠንየተል ወዳዕ’ ከተሰኘው
ምስጋና ይገባው በያይነቱ
ቅኑን መንገድ ለእኛ በማመላከቱ
ከመሃላችን የተላክኸው አንተ የነቢያት ዓይነታ
መጥተሃልና በማይታበል ዕውነታ
የምንታዘዘው በሆነ ሃቅ ያለምንም ቅሬታ!

https://hottg.com/NejashiPP
አላህ የሰውን ልጅ ከሚጠገንባቸው መንገዶች መካከል አንዱ መርሳት ነው።
ሐቢቢ! አቤት ያ የማይረሳ የሚመስለው ነገር ሁሉ ተረሳ ከማለትህ ቀጥሎ ጌታዬ ሆይ ምስጋና ይገባህ በል።


https://hottg.com/MuhammedSeidAbx
ምስጋና፣ ትዕግስት፣ ተስፋ፣ ኢስቲግፋር ... የደስታ እና የፅናት ምንጮቻችን ናቸው፡፡ እናመሰግናለን፣ እንታገሳለን፣ ተስፋ እናደርጋለን፣ ስላጎደልነው ነገር ሁሉ ከአምላካችን ምህረትን እንለምናለን።
ሁኔታዎችን በየቅጽበቱ የምትለዋዉጥ አምላካችን ሆይ! ሁኔታችንን ሁሌም ይበልጥ ወደተሻለው ሁኔታ ለዉጥልን፡፡

ሰባሐል ኸይር!



https://hottg.com/MuhammedSeidAbx
HTML Embed Code:
2025/06/29 09:50:56
Back to Top