TG Telegram Group Link
Channel: MuhammedSirage M/Nur TextPosts
Back to Bottom
Forwarded from የሙሀመድ ሲራጅ የድምፅ ፋይል የሚሰራጭበት ቻናል (كوني زوجة صالحة تقية)
ከላይ የተለቀቁትን አጫጭር 90 የሚጠጉ ምክሮችን የያዘ የቴሌ ግራም ሊክ ሲሆን ሰዎች ጋር ይደርስ ዘንድ #ጆይና__ሸር በማረግ የበኩላችሁን አስተላልፉት አያስከፍልም መልካምነት ለራስ ነው በአንችና በአንተ ሸር ምክናየት ብዙ ሰዎችን ወደ ሱና ልናመጣ እንችላለን ባረከላሁ ፊኩም !
hottg.com/Muhammedsiragecom/463
hottg.com/Muhammedsiragecom/464

የቴሌ ግራም ቻናላችን
hottg.com/Muhammedsirage
hottg.com/Muhammedsiragecom
Forwarded from የኢብኑ ሙነወር የድምፅ ፋይል የሚሰራጭበት ቻናል (كوني زوجة صالحة تقية)
السلام  عليكم  ورحمة الله وبركاته
ተቀርቶ የተጠናቀቀ የኪታቡ ተዉሒድ ሙሉ  ደርስ ፦
🎙በኢብኑ ሙነወር (ሐፊዛሁሏህ)

የድምፅ ፋይል 1- 76👇      
hottg.com/IbnuMuneworcom/230

በቴሌግራም ቻናል:-👇
hottg.com/IbnuMunewor/3466
Audio
→እገሌን እገሊትን የመከተል ግዴታ የለብንም !!!

ሙሐመድ ሲራጅ ሙ ኑር

https://hottg.com/Muhammedsirage

https://hottg.com/MedrestuImamuAhmed
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
➧የወንድማችን አብዱሽኩር አቡ ፈዉዛን ቻናል

➷ይቀላቀሉ ይጠቀማሉ ኢንሻ አላህ!
➘➘➘➘➘➘➘➘➘➘➘➘➘
https://hottg.com/abu_fewzan_abdu_shikur
https://hottg.com/abu_fewzan_abdu_shikur
Forwarded from MuhammedSirage M.NOOR (MuhammedSirage MuhammedNoor)
እቃዎችን በመግዛት ላይ ተመስርቶ እጣ ለሚወጣላቸው ሰዎች የሚሰጡ “ ሽልማቶች”ን በተመለከተ ….


ዛሬ አንድ ማስታወቂያን ተመለከትኩ

“ እስከ ….. ድረስ ‘ ይህንን ይህንን ‘ ለሚገዙ ግለሰቦች ሽልማት አዘጋጅተናል “ የሚል


ማስታወቂያቸው በርእሱ ዙሪያ የተመለከትከኩትን የዑለማእ ንግግር እንዳስታወስ አደረገኝና ጥቂት ነገርን ማለት ፈለግኩ ….

ሸቀጥን በመግዛት ለባለ እጣዎች ብቻ የሚገኙ ሽልማቶችን በተመለከተ የተለያዩ ገፅታዎች አሉና የተለያዩ ብይኖች ይኖራሉ - ዑለማእ እንደሚሉት

ለዛሬ ሁለቱን ብቻ ላውሳ ፣

1ኛው ገፅታ ፣ ለባለ እጣዎች በታሰበው ሽልማት ምክንያት በሸቀጡ ዋጋ ላይ ጭማሪ ተደርጎ ከሆነ ( ለምሳሌ ሽልማቱ ከመዘጋጀቱ በፊት 100 ይሸጥ የነበረ እቃ ከሽልማቱ ወዲህ 110 ቢገባ ) ወደ እንዲህ አይነቱ ውል መግባት የተከለከለ ይሆናል ።

ምክንያቱም ተጨማሪ ገንዘብ እየተከፈለ ያለው የሽልማቱ ባለ እጣ ለመሆን ነውና ነገሩ ሎተሪ ብለው ከሚጠሩት ቁማር የተለየ እንዳልሆነ ዑለማእ ይገልፃሉ

2ኛው ገፅታ ባለ እጣ ለሚሏቸው የተዘጋጀን ሽልማት በማሰብ ብቻ የማይፈልጉትን እቃ መግዛት ሲሆን እንዲህ አይነቱ ቅርፅም እንደማይፈቀድ ዑለማእ ያስተምራሉ ።

ለምሳሌ “ የታሸጉ የልጆች ምግቦችን ለሚገዙ እስከ ጥቅምት የሚዘልቅ ሽልማት አለ - እጣው ለሚወጣላቸው “ ቢባል ፣ እነዚህን ሸቀጦች የመግዛት ልምድና ፍላጎት የሌላቸው ላጤዎች ሸቀጦቹን መግዛትና በሽልማቱ መጠቀም አይፈቀድላቸው - የቁማር ገፅታ አለበትና ።

ምክንያቱም ፣

እኒህ ግለሰቦች ገንዘቡን እየከፈሉ ያሉት ይኖራል የተባለውን ሽልማት በማሰብ እንጂ ለሸቀጡ እውነተኛ ፍላጎት ኖሯቸው አይደለም - ሸቀጡ ለነዚህ ሰዎች የመጀመሪ ግብ ሳይሆን ትርፍ ፍላጎት ነው - ሸልማቱ የመጀመሪያ ግብ ነው !

ለዚህማ ነው ሽልማት አለ ባይባል ኖሮ እቃውን ባልገዙት ነበር !

ሁለቱም የጠቀስኳቸው ገፅታዎች ከሎተሪ ቁማር እንደማይለዩ ዑለማእ ገልፀዋል ፣

አሏህ ያውቃል



እንጠንቀቅ

https://hottg.com/Muhammedsirage
Forwarded from MuhammedSirage M.NOOR (MuhammedSirage MuhammedNoor)
የወንጀላችን ግዝፈትና ብዛት ነጅሶን በተፈቀዱ ነገሮች እንኳን መደሰት በከሰመበት ዘመን የተከለከሉ ነገሮችን በመጠቀም ደስታን ለመሸመት ማሰብ ድንቁርና ነው ።

አላህ ይመልሰን

አሏህን በመፍራት እውነተኛ ደስታና እረፍት ይገኛል !

https://hottg.com/Muhammedsirage
Forwarded from Abu reyis mohamed imam
السلام عليكم ورحمة الله وبركاته

ታላቅ ዳዕዋና ኮንፈረንስ በኢትዮጵያ

    እነሆ በአሏህ ፍቃድ ወሎ ኮምቦልቻ ከተማ አንሷር መስጅድ የፊታች እሁድ ቀን 18/03/ 2015 ጀምሮ ለተከታታይ ሶስት ቀናት በታላላቅ ከውጭ በመጡ አሊሞችና የሃገራችን አሊሞች መሻኢኾች እና ኡስታዞች ታላቅ የዳዕዋ ፣ የፈትዋ እና የኮርስ ፕሮግራም ተዘጋጅቶ ይጠብቃቹሃል... በዕለቱ  ብዙ ታዳሚ ይገኛል ተብሎ ይጠበቃል። 

በእለቱ ከሚገኙ ከውጭ ሀገር ታላላቅ ኡለማዎች መሃል
1) የተከበሩ ሸይኽ አቢ ዐማር ሙሐመድ ኢብኑ ዐብዲላሂ ባሙሳ - فضيلة الشيخ محمد بن عبد الله با موسى - حفظه الله تعالى

2) የተከበሩ ሸይኽ ረሻድ አል-ሑበይሺይ - فضيلة الشيخ  رشاد الورد الحبيشي حفظه الله

3) የተከበሩት ሸይኽ ሙሳ አሕመድ አል ቀጧኒ
فضيلة الشيخ موسى احمد القطاني

እና ሌሎችም ውድ የሰለፊያ ኡስታዞች እና ወንድሞች ከ አፋር ከአዲስ አበባ ከደሴ ከኸሚሲይ እንዲሁም ከተለያዩ ቦታዎች በአለሠህ ፍቃድ ይዘምታሉ

በዕለቱ :-

✔️ የኮርስ ፕሮግራም ይካሄዳል
✔️ የደዕዋ ፕሮግራም ይካሄዳል
✔️ በመሻኢኮቻችን ነሲሃ ይደረጋል
✔️ የፈትዋ ፕሮግራም ይኖረናል

ማሳሰቢያ :- ማንኛውም ስለማንኛውም ነገር ሹብሃ ያለበትም አካል ጥሪ ሳይደረግለትም መምጣት ይችላል በራችን ክፍት ነው ።

👌 በቂ ምግብ እና የመኝታ ቦታ ተዘጋጅቷል ... ከቅዳሜ  ጀምሮ ኢትዮጵያውያን ይህንን ውድ ፕሮግራም ለመታደም ወደ ኮምቦልቻ አንሷር መስጅድ እብድታመሩ ስንል ጋብዘናቹሃል።

ማሳሰቢያ
የሌሊት ልብስ ይዛችሁ ብትመጡ የተመረጠ ነዉ።


አድራሻ :- ኢትዮጵያ ኮምቦልቻ ከተማ ሀሰና ሀገር ክፍል ከተማ ቀበሌ ሁዳዴ በርበሬ ወንዝ አድሱ ድልድይ ተሻግሮ ደዌ ሰፈር በአንሷር መስጅድ

hottg.com/Ye_kombolcha_Ansuar_Mesjid_Jemea
hottg.com/Ye_kombolcha_Ansuar_Mesjid_Jemea
Forwarded from MuhammedSirage M.NOOR (MuhammedSirage MuhammedNoor)
የነገው ቀጠሮ

በደመቀው ሳሎን - በተዋበው ማጀት
ብትቀማጠለው ከልጅ እስከ ማርጀት

ያሻህን ብትነዳ በዝቶ ተሽከርካሪ
አለምን ብታስስ በሰማይ በራሪ

ጉድጓድ ነው ማረፊያህ የነገ ቀጠሮ
አፈር ልብስህ ሊሆን ሱፍህን ቀይሮ

ታገል ወንድሜ ሆይ ሰንቅ ለአኺራ
ፀፀት ያኔ አይጠቅምም ዛሬ ካልተሰራ



https://hottg.com/Muhammedsirage
Forwarded from MuhammedSirage M.NOOR (MuhammedSirage MuhammedNoor)
ውሸት አስነዋሪ ባህሪ ነው ። ውሸት የሙናፊቆች መለያ ነው ። ውሸት ማንነትን ከሚያረክሱ መገለጫዎች ውስጥ አንዱ ነው ። ታላቁ ነብይ ውሸት ወደ ወንጀሎች እንደሚመራ ገልፀዋል ። ውሸትን የሚዳፈር ሰው ሌሎች ትልልቅ ወንጀሎች ውስጥም ሊነከር የቀረበ ነው ። ውሸትን የሚያበዛ ሰው አላህ ዘንድ “ ውሸታም” ተብሎ ይፃፋል !!!

ባጠቃላይ ውሸት የሰዎችን ታማኝነት የሚሰባብር ቆሻሻ ልማድ ነው ።

ዛሬ ዛሬማ ይኸው ሰባራ ባህሪ ወደ አላህ መንገድ እጣራለሁ የሚለው አንዳንዱ ደፋርም ላይ የሚታይ ሆኗል - እጅጉን ያሳዝናል !! ቀደምት ደጋጎችን እከተላለሁ እያለ የሚሞግተው አንዳንዱ ውሸትን ሲያበዛ ማየት እንግዳ መሆኑ ቀርቷል !!

ጀሌዎቹን ለመስቀል ሀሰትን እንደ ጠመንጃ ይጠቀምበታል ። በጠላትነት የፈረጃቸውን ለመገንደስ ባልዋሉበት ያውላል - ያሳዝናል !!!

ሁሉም አላህ ፊት ይቆማል !

አንተ በሰዎች ላይ የምትዋሽ ሆይ ! እያንዳንዱ ተገቢ ዋጋውን በሚያገኝበት ቀን የዋሸህባቸው ሰዎች ከመልካም ስራህ እንደሚወስዱ አለያም ከወንጀላቸው እንደምትሸከም አስታውስ !! አላህን ፍራ !!

አላህን ፍሪ !!

በርግጥ ነው ለቡድንተኝነት ትግላቸው ሆን ብለው ውሸትን እንደ መሳሪያ ከሚገለገሉበት ሰዎች ጋር “ አላህን ፍሩ “ ማለት የሚያግባባ ቋንቋ ላይሆን ይችላል ….. የተባለውን ሁሉ ሳያጣሩ በየዋህነት የሚያወሩትን ግን ይጠቅማል ብየ ተስፋ አደርጋለሁ ። አላህን እንፍራ !!

አላህ ከውሸት ይጠብቀን !!

https://hottg.com/Muhammedsirage
Forwarded from ⚘ሱና የኑሕ መርከብ ናት قناة السنة سفينة نوح (كوني زوجة صالحة تقية)
#ሰለፊያ_ማለት ታላቁ የየመን ዓሊም ሸይኽ ሙቅቢል ኢብኑ ሃዲ አልዋዲኢ (ረሂመሁላህ) እንዲህ ብለዋል፦

"ሰለፊያ ማለት አንድ ሰው ሲፈልግ የሚለብሰው ሳይፈልግ ደግሞ የሚያወልቀው ካባ አይደለም ፣ እንዲያውም ሰለፊያ ማለት፦ የአላህን መፅሐፍ እና የመልክተኛውን (ሰለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም) ሱናህ በሰለፉ ሳሊሂን አረዳድ አጥብቆ መያዝ ማለት ነው።"
【ቱሕፈቱ አልሙጂብ አላ አስኢለቲ አለሓዲር ወልገሪብ】
hottg.com/Kunizewjeten2
Forwarded from MuhammedSirage M.NOOR (MuhammedSirage MuhammedNoor)
መልካሙን መልበስህ ፣ ያማረን ነገር መጠቀምህ ፣ የተዋበን ቤት መገንባትሀ‍ የሚነወር አይደለም ።

እነዚህ ነገሮች ላይ ለመድረስ የተከለከሉ ነገሮችን መዳፈርና የዱንያ ነገርህን ለማድመቅ አኺራህን አደጋ ላይ መጣል ግን ነውር ነውና እናስብበት !!

አላህ ይምራን !
hottg.com/Muhammedsirage
Forwarded from كوني زوجة صالحة تقية (كوني زوجة صالحة تقية)
قال عبد الله بن عمرو رضي الله عنهما :
(من مَرَّ ببلاد الأعاجم فصنع نيروزهم ومهرجانهم وتشبه بهم حتى يموت وهو كذلك حشر معهم يوم القيامة)

أحكام أهل الذمة 1 /723-724
hottg.com/Kunizewjeten2
Audio
ቁርአንና ሐዲስ መመሪያችን በማለት ላይ አንቆምም - ተጨማሪ ቅጥያ ያስፈልገዋል


ሰለፊ መሆን ( ቀደምቶችን - ሶሐቦችን …. መከተል ) ግድ ነው ?

ሙሐመድሲራጅ ሙ ኑር

https://hottg.com/Muhammedsirage
Forwarded from MuhammedSirage M.NOOR (كوني زوجة صالحة تقية)
ረመዷን የመጨረሻው ውስን ቀናቶች ውስጥ ነን ይህን ዱዓ እናብዛ

" اللهم إنك عفو تحب العفو فاعف عني "
" አሏሁመ ኢነከ አፉውን ቱሂቡል ዓፍወ ፈዓፉወ ዐኒ "
አላህ ሆይ አተ ይቅር ባይ ነህ ይቅር ማለትን ትወዳለህ ይቅር በለኝ!
hottg.com/Kunizewjeten2
Forwarded from MuhammedSirage M.NOOR (MuhammedSirage MuhammedNoor)
ረመዷን እስኪወጣ ሣይሆን ሩሕ እስኪወጣ ጌታህን ታዘዝ

ከረመዷን በፊት ወደነበርክበት አመፅና ወንጀል ለመመለስ በማኮብኮብ ላይ ያለህ ወንድሜ ሆይ ! አላህን ፍራ! የረመዳኑ ጌታ የተቀሩት ወራቶችም ጌታ ነው ... አሏህን ፍራ!

ፈጣሪህን በመፍራት የታዘዝከው በዚህ ወር ብቻ አይደለም ... ከፀያፍ ነገሮች መራቅ የእድሜ ልክ ግብ እንጂ የአንድ ወር አላማ አይደለም !

ሁሌም ለአላህ እጅ የሰጠህ ሙስሊም ለመሆን ታገል ...

ረመዷን እስኪወጣ ሣይሆን ሩሕ እስኪወጣ ጌታህን ታዘዝ



وَاعْبُدْ رَبَّكَ حَتَّى يَأْتِيَكَ الْيَقِينُ
እውነቱም (ሞት) እስኪመጣህ ድረስ ጌታህን ተገዛ፡፡

https://hottg.com/Muhammedsirage
ኢማምነትና ኸጢብነት ሸሪዐዊ ሃላፊነቶች ናቸው። በሸሪዐዊ ሃላፊነት ላይ በአግባቡ አማናን መወጣት ይገባል። የራስን ፍላጎት ብቻ ከመከተል ይልቅ ሰፊውን ተገልጋይ ማሰብ ይገባል። ስላሰኘህ ብቻ ማስረዘም፣ ስለ ታከተህ ብቻ ማሳጠር ተገቢ አይደለም። ኢማም ወይም ኸጢብ የሆነ ሰው አቅመ ደካሞችን፣ ባለ ጉዳዮችን፣ ህመምተኞችን፣ አዛውንቶችን፣ ፀሐይ ወይም ዝናብ ላይ ያሉ ሰጋጆችን ወይም አድማጮችን ታሳቢ ማድረግ አለበት። ነብያችንኮ ﷺ የሚያለቅስ ልጅ ድምፅ ሰምተው እናቱ እንዳትረበሽ በሚል ሶላት ያሳጥሩ ነበር።
ልክ እንዲሁ በኸጢቦች የሚነሱ ርእሶችም ማህበረሰቡ ያለበትን ሁኔታ ወይም ወቅታዊ ጉዳዮችን የዘነጉ መሆን የለባቸውም። ረመዷን ላይ አብዛኛው ደዕዋ ስለ ረመዷን ነበር። ይሄ ጥሩ ነው። ነገር ግን በዘረኝነት ስንታመስ፣ በሱስ ስንወረር፣ ነጋዴው መሀል ማጭበርበርና መካካድ ሲንሰራፋ፣ መጨካከን ሲበዛ፣ ሺርክና ቢድዐ ሲስፋፋ፣ ... ዱዓቶችና ኸጢቦች ጭልጥ ብለው ሌላ አለም ውስጥ ሊሆኑ አይገባም። አስተማሪ ማለት ልክ እንደ ሃኪም ነው። ሃኪም የውስጥ ደዌ ለማከም የቆዳ መድሃኒት አይሰጥም። ልክ እንዲሁ ለወገኑ ተቆርቋሪ የሆነ ዳዒያህ ማለት ህዝቡ ያለበትን ነባራዊ ሁኔታ እያየ ተገቢውን ህክምና የሚሰጥ ነው።
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://hottg.com/IbnuMunewor
Forwarded from MuhammedSirage M.NOOR (MuhammedSirage MuhammedNoor)
የኤሌክትሮኒክስ መሳሪያዎችን በመሸጥ የሞትተዳደሩ ወንድሞችና እህቶች ሆይ፣

በምትሸጡ ግዜ እውነተኞች ሁኑ ! ከዚህ በፊት ጥቅም ላይ የዋለን ስልክ፣ ታብሌት ... በአዲስ ስም ፣ ባልሠራ ሒሳብ ከመሸጥ ታቀቡ ! አሏህን ፍሩ ! ላመኗችሁ ታማኞች ሁኑ! የዱንያ ሸቀጥን ፣ ጠፊ ገንዘብን ለመሰብሰብ ሲባል እምነታችሁንና ክብራችሁን ለአደጋ አታጋልጡ

በውሸትና በማጭበርበር የሚገኝ ገንዘብ ዕረፍትን የሚነሣ ከመሆኑ ጋር የፍርዱ ቀን ደግሞ ኪሣራን ያሸክማል .. አሏህ ዘንድ ተጠያቂ ያደርጋልና ተጠንቀቁ ! አሏህን ፍሩ!
Forwarded from كوني زوجة صالحة تقية (كوني زوجة صالحة تقية)
Forwarded from مركز الإمام أحمد الإسلامي (ابو فركوس)
እንኳን ያንተ አይነቱ
ውሻ ቢባል ሽልማቱ


ጀግና ‘ሚባል ተሰብስቦ
ሊያከስማቸው ጥልቅ አስቦ

አንዴ ሲዘልፍ ሙሐመድን
ሌላ ግዜ ሊገላቸው ጦር ሰብስቦ አገር ቢያድን

አልሆን ብሎት አፈር በልቷል
ከነ ጀሌው ጉድጓድ ገብቷል ! 


የዛሬውም ከንቱ ውሻ …,

ምግባር ሆኖ ለከረፋው ማንነትህ

ባፍ ብትጮህ ብታላዝን እንዳባትህ …


በዋልጌ አምደበትህ እምነቱን አትገታም

አለም ቢደግፍህ በባዶ ራስ ቅልህ እኛን ከቶ አትረታም !!!

https://hottg.com/Muhammedsirage
Forwarded from كوني زوجة صالحة تقية (كوني زوجة صالحة تقية)
خرج أبو بكر رضي الله عنه صبيحة الإثنين 12 ربيع الأول سنة11هجري وقال: مات #رسول_الله_ﷺ فأظلمت الدنيا على المسلمين ،
فبماذا ستحتفلون !
hottg.com/Kunizewjeten2
HTML Embed Code:
2024/03/29 11:52:45
Back to Top