TG Telegram Group Link
Channel: አለሕግ🔵AleHig
Back to Bottom
አደገኛ ወንጀል ነው!

አለም አቀፉ የጉምሩክ ድርጅት /WCO/ ኮንትሮባንድን እንደሚከተለው ይተረጉመዋል፡፡ ኮንትሮባንድ ማለት ማንኛውም በህግ የተከለከለ አሰራር ሲሆን እነርሱም፡- ከማምረት /production/፣ ከማጓጓዝ /shipment/፣ ከመቀበል /receipt/፣ ባለቤት ከመሆን /possession/፣ ከማከፋፈል /distribution/፣ ከመግዛትና መሸጥ እንዲሁም ማንኛውም ለዚህ አሰራር ሁኔታዎችን ማመቻቸትን /facilitation/ ያካትታል፡፡

የኢትዮጵያ ጉምሩክ አዋጅ ኮንትሮባንድን <<ህጎችንና በህግ መሰረት የወጡ መመሪያዎችን በመተላለፍ ወደ ጉምሩክ ክልል ዕቃዎችን ማስገባት፣ በህጋዊ መንገድ የወጡትን በህገ ወጥ መንገድ መልሶ ማስገባት፣ መያዝ፣ ማከማቸት፣ ማዘዋወር፣ ማስተላለፍ፣ እንዲገቡ ወይም እንዲወጡ ለማድረግ መሞከር፣ እንዲሁም እነዚህ ዕቃዎችን መግዛትን፣ መሸጥንና ለዚህ ድርጊት ተባባሪ መሆንን ያጠቃልላል፡፡; በማለት ተርጉሞታል።

1. የኮንትሮባንድ ወንጀል በሀገር ኢኮኖሚ ላይ ብቻ ሳይሆን የህዝብን ጤንነት፣ የሀገርን ሰላምና ፀጥታ የሚያውኩ ዕቃዎችን በማስገባት አገራዊ ደህንነትን አደጋ ላይ የሚጥል አደገኛ ወንጀል ነው፡፡
2. ከኢኮኖሚ አንፃር የኮንትሮባንድ ወንጀል ህጋዊ ነጋዴውንና አምራቹን አዳክሞ ከገበያ በማስወጣት ምርታመነትንና ህጋዊ ንግድን ያቀጭጫል፤ ህጋዊ የንግድ ውድድርን ያዳክማል፤ የመንግስትን የገቢ ምንጭ ያደርቃል፡፡
አማራጭ የሕግ እውቀት
👉Telegram👈
https://hottg.com/lawsocieties

👉Facebook Page 👈
https://www.facebook.com/lawsocieties/

👉 LinkedIn 👈
https://www.linkedin.com/company/lawsocieties/

👉YouTube 👈
https://youtube.com/@Ale_Hig
የኢትዮጵያ የኮንስትራክሽን ሕግ.pdf
1.5 MB
የኢትዮጵያ የኮንስትራክሽን ሕግ.
የመኖሪያ ቤት እጥረትና የቤት ክራይ ውድነትን ለመቀነስ ያስችላል የተባለ አዋጅ ፀደቀ

ከግዜ ወደግዜ እየናረ የመጣውን የመኖሪያ ቤት እጥረት እና የቤት ክራይ ውድነትን ለመቀነስ ያስችላል የተባለ አዋጅ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ፀድቋል። ምክር ቤቱ ያፅደቀው አዋጅ አዋጅ ቁጥር 1320/2016 የመኖሪያ ቤት ኪራይ ቁጥጥርን እና አስተዳደር ይመለከታል።

ይህ አዋጅ ቀደም ብሎ በቃል እና በእምነት በተከራይ እና አከራይ መካከል ይደረግ የነበረው የመኖሪያ ቤት ኪራይ ውል በአዲሱ አዋጅ አንቀፅ 4 መሰረት የመኖሪያ ቤት ኪራይ ውል በፅሁፍ ማድረግን ግዴታ ከማድረጉም ባሻገር ውሉ በተቆጣጣሪው አካል ተረጋግጦ እንዲመዘገብ ያዛል ግዴታቸውን ያልተወጡ አከራይና ተከራይ ላይ የቤት ክራዩን የሦስት ወር ገንዘብ ቅጣት አዋጁ አስቀምጧል። ከዚህ ቀደም ተከራይ የሶስት እና የስድስት ወር ቅድሚያ ክፍያ ለአከራይ መስጠት ግዴታው የነበረ ሲሆን በአዲሱ አዋጅ ግን ተከራይ የሚጠበቅበት የሁለት ወር ኪራይ ቅድመ ክፍያ ብቻ ነው ።

ክፍያውም በባንክ ወይም በኤሌክትሮኒክስ የክፍያ ዘዴ መፈፀም ይኖርበታል። ይህ አስገዳጅ ህግ አዲስ የሚፈፀም የኪራይ ውል ብቻ ሳይሆን እድሳትንም ያካትታል፣ በአዲሱ አዋጅ አንድ የመኖሪያ ቤት ክራይ ውል የቆይታ ጊዜ ሁለት ዓመት ነው። በዚህ ግዜ ውስጥ አከራይ ተቆጣጣሪው ከሚያወጣው የክራይ ጣሪያ ውጭ ምንም አይነት የቤት ክራይ ጭማሪ ማድረግ አይችልም።

አዲሱ አዋጅ እስካሁን የቤት ክራይ ዋጋን በተመለከተ ፈላጭ ቆራጭ ናቸው የሚባሉትን የመኖሪያ ቤት አከራዩች እንዳሻቸው ዋጋ ከመጨመር ያግዳቸዋል። አቅምን ያማከለ የመኖሪያ ቤት እጥረት ችግር ሳቢያ የሚፈጥዕረውን የኑሮ ውድነት ጫና ለመቀነስ አይነተኛ መፍትሄ ነው ተብሏል። DW ያናገራቸው የአዲስ አበባ የቤት ክራይ ነዋሪዎች ስጋታቸውን እንዲህ ይናገራሉ አዲስ ቤት ለኪራይ የሚያቀርቡ አከራዮችን የመጀመሪያውን የቤት ኪራይ ውል ካስመዘገቡበት ቀን ጀምሮ በአዋጁ መሰረት ከሚወጡ የኪራይ ዋጋ ጣሪያ ግዴታዎች ለአራት አመት ነፃ ይኾናሉ የሚል የማበረታቻ ሲኖረው በሌል በኩል ባለቤቶች ቀደም ብሎ ሲከራይ የነበረን ቤት ከስድስት ወር በላይ ሳይከራይ እንዲቆይ ቢያደርጉ ቤቱ ቢከራይ ያስገኝ የነበረውን የቤት ኪራይ ግብር ገቢ ታስቦ በማግረግ እንዲከፍሉ ይደረጋል ይላል።

የህግ ባለሙያው አቶ ካፒታል ክብሪ ለ DW እንደተናገሩት አዋጁ በግለሰቦች ለፍተው ባፈሩት ሀብት ላይ የሚኖራቸውን መብት ለመገደቡ አሻሚ አይደለም ይላሉ።

ትክክለኛው መፍትሄ ኢኮኖሚያዊ ላይ መስራት ነው። እንደውም በጣም ጥብቅ የሆነ ህግ በወጣ ቁጥር የበለጠ አልሚዎችን በመጉዳት ችግሩን ከድጡ ወደማጡ ሊወስደው ይችላል ይላሉ።

ከፍተኛ የመኖሪያ ቤት እጥረት ባለባቸው ከተሞች የመኖሪያ ቤትን አላግባብ ከህግ ውጭ አገልግሎት ሳይሰጡ ከአንድ አመት በላይ ለሚያቆዩ ባለንብረቶች ከኪራይ ግብር በተጨመሪ የቤቱን ንብረት ግምት ተመን 25 ከመቶ እንዲከፍሉ የሚያስገድድ መመሪያ እንዲያወጡ አዋጁ ለየከተሞች መብት ሰጥቶዋል።

ምንጭ። DW ዶቼ ቬሌ።
አማራጭ የሕግ እውቀት
👉Telegram👈
https://hottg.com/lawsocieties

👉Facebook Page 👈
https://www.facebook.com/lawsocieties/

👉 LinkedIn 👈
https://www.linkedin.com/company/lawsocieties/

👉YouTube 👈
https://youtube.com/@Ale_Hig
ዳግማዊ አሰፋ (የሕግ ባለሙያና ደራሲ)

ዳጊ ስለፍትሕ፣ ስለእውነትና ስለታማኝነት የተከፈለ መስዋዕትነት ማሳያ ነው። ከዓመታት በፊት በደረሰበት አደጋ ለከፍተኛ ጉዳት ተዳርጎ ነበር። በእግዚአብሔር ተዓምር ተርፎ ይሄው ለብዙዎቻችን ትልቅ ተምሳሌትና መማሪያ ሆኖ በመጽሐፎቹ፣ በየመድረኩ፣ በመገናኛ ብዙሃንና በማሕበራዊ ትስስር ገጽ ለብዙዎቻችን የይቅርታና የጽናት ሕያው መማሪያ ሆኖን አለ።

ለዳጊ ያለንን ፍቅርና አክብሮት በተግባር የምናሳይበት እድል አግኝተናል። ዳጊ ከደረሰበት አደጋ በኋላ በብዙ የጤና ትግል ውስጥ በርካታ ስራዎችን እየሰራ ይገኛል። አሁን ደግሞ ጤናውን በተሻለ የሚያግዝ ተስፋ የተጣለበት ሕክምና ሂደት ተጀምሯል። ለህክምናውም የተጠየቀው 60ሺ ዶላር ነው። ወዳጆቼ አንድ ዶላር በ57ብር በመግዛት ለሀገር ባለውለታ ህክምና ስጦታ በማበርከት ዳጊን እናመስግነው።

ይህንን መልዕክት ለብዙዎች አጋሩልኝ!
እኔ ዘመቻውን ተቀላቀልኩ ኑ እናንተም መልካም ስራን የሰራ ሰውን አመስጋኝ ሁኑ!

አንድ ዶላር በ57 ብር ይግዙ
ንግድ ባንክ- 1000310977938
ዳሽን-5016527877077
አቢሲኒያ- 39796821

https://gofund.me/ca6e599b

ምንተስኖት መኩሪያ

አማራጭ የሕግ እውቀት
👉Telegram👈
https://hottg.com/lawsocieties

👉Facebook Page 👈
https://www.facebook.com/lawsocieties/

👉 LinkedIn 👈
https://www.linkedin.com/company/lawsocieties/

👉YouTube 👈
https://youtube.com/@Ale_Hig
Consoledated_Training_Manual_Final draft edited T + H.pdf
211.8 KB
በጠቅላላ ጉባኤ ቀርበው ከሚፀድቁ መመሪያዎች አንዱ የስልጠና መመሪያ ተለቋል::

መረጃውን #share #like በማድረግ እንድታጋሩልን እንጠይቃለን::

በሚከተለው መስፈንጠሪያ የስልጠና መመሪያውን ያንብቡ::

https://hottg.com/lawsocieties/9482

የኢትዮጵያ ፌደራል ጠበቆች ማህበር
ሚያዝያ 29 ቀን 2016ዓ.ም
አዲስ አበባ ፤

አማራጭ የሕግ እውቀት
👉Telegram👈
https://hottg.com/lawsocieties

👉Facebook Page 👈
https://www.facebook.com/lawsocieties/

👉 LinkedIn 👈
https://www.linkedin.com/company/lawsocieties/

👉YouTube 👈
https://youtube.com/@Ale_Hig
የኢትዮጵያ የፌደራል ጠበቆች ማህበር አባላት መዋጮ መመሪያ ቁጥር
………/2016

ለፌደራል ጠበቆች
-----
በአጭሩ ረቂቅ መመሪያው አንድ ጠበቃ በዓመት 8400 ብር እንዲከፍል ይገደዳል! ይህን ያልከፈለ ፍቀድ እንዳያሳድስ እና የማህበሩን ጥቅም እንዳያገኝ ይሆናል ይላል!
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
ማስታወቂያ

የፌደራል የማናቸውም ፍርድ ቤት የጥብቅና ፈቃድ ለመውሰድ መጋቢት 28 ቀን 2016 ዓ.ም ፈተና የተሰጠ መሆኑ ይታወቃል፡፡ በዚህም መሰረት የፈተና ውጤቱ ከታች አባሪ በተደረገው ሰንጠረዥ መሰረት ይፋ የተደረገ ሲሆን መረጃውን የላከው የጥብቅና ሙያ መግቢያ ፈተና ኮሚቴ ነው::
HTML Embed Code:
2024/06/12 09:01:15
Back to Top