TG Telegram Group Link
Channel: Kalid | PGI Consultant | Thinking Into Results
Back to Bottom
እርሶ ሰው በመሆኖ ብቻ ብቁ ኖት።

የሰው ልጅ ሰው በመሆኑ ብቻ በአእምሮዎዊና መንፈሳዊ ማንነቱ ውስጥ የሚያስባቸውን ቅርጽ አልባ (Formless substance) የሆኑ ጽንሰ ሃሳቦችና ምስሎች በማስረጽና በምምራት የሚፈልገውን ማንኛውም ለውጥና ነገሮች መፍጠር ይሚችል (Creative Beign) የሆነ መንፈሳዊ ፍጥረት ነው። ሀሳቦን የመቆጣጠርና የመምረጥ አቅሞን ይጠቀሙ እናም ማንነቶንና ስሜቶን ህይወቶንና ኑሮዎን ይለውጡ፡፡ ይህ ለእርሶ የተሰጦት ታላቅ ጸጋ እና እምቅ አቅሞ ነው፡፡

ሀሳቦን የመግዛትና የምምራት ጥበብን ይማሩ፡፡ በህይወቷ እና በራሷ ላይ ይሰልጥኑ! እርሶ በራሶ ከጫኑት ውስንንት ሀሳቦች በቀር ድንቅ ፍጥረት ነዎት፡፡

ለውጤት ማሰብ ይማሩ፡፡
ካሊድ ሰኢድ፤ በኢትዮጵያ የቦብ ፕሮክተር ስልጠና አሰልጣኝና አማካሪ
ምን አሰብክ ታድያ?

የምንኖርባት (Gravity Law) ወደታች እንጂ ፍጹም ወደላይ ሊሆን አይችልም። የእርሶ ምርጫና ፈቃድ ከክፍታ ላይ መዝለል ወይ አለመዝለል ብቻ ነው እንጂ አንዴ ከዘለሉ ቡሆላ ምርጫው የሚወሰነው በተፈጥሮ ህግ በቻ ነው። ንፋስና አየሩ፣ ተራራውና ግንቡ እየገፈታተሩ ወዳሻቸው ቦታ እንደየሁኔታው gravity law ወደታች መፈጥፈጦ የማይቀር ነው። እርሶም ዛሬ በህይወቶና በንሮዎ ውስጥ የሚኖሩት ህይወትም ልክ እንደዛው በተፈጥሮ ህግ የሚመራ ሲሆን እሱም በሃሳቦ ልክ ነው። በአስተሳሰቦ አይነት ልክ የሚወስን ነው። ሃሳቦን የመምረጥ ነጻነቶንና አቅሞን ይጠቀሙ

ለውጤት እናስብ፡፡
ካሊድ ሰኢድ፤ በኢትዮጵያ የቦብ ፕሮክተር ስልጠና አሰልጣኝና አማካሪ
ክረምቱ እየገባ ነው ዘንድሮስ ምን ልትዘራ እያሰብክ ነው?

በአእምሮዎዊና መንፈሳዊ ማንነቶ ውስጥ የሚዘሩትና የሚቀርጹት ጽንሰ ሃሳቦችና ምስሎች ስለራሶ ማንነትና ህይወት ውድቀት ከሆነ፣ ስላሉበት ሁኔታና ደረጃ ማማረር፣ ድክመቶንና ችግሮን፣ ጥላቻና ምሬት ከሆነ የሚያብሰለስሉት እጣ ፋንታዎም ጭንቀትና ሃዘን፣ መከራና ችግር ውስጥ የሚኖር ደካማና ተሸናፊ ሰው መሆን ይሆናል።

ሃሳቦን ወደ ውጤት ይለውጡ!
ካሊድ ሰኢድ፤ በኢትዮጵያ የቦብ ፕሮክተር ስልጠና አሰልጣኝና አማካሪ
አንተን የሚመራህና የሚቆጣጠርህ አእምሮህ ነው፡፡

አንተ ለገጠመህ ነገር ለሆነውና ለደረሰው አልያም ለሁኔታዎቸወና ለነገሮች ምላሽ የምትሰጥበት መንገድ የሚወሰነው ባለህ የአእምሮህ ዝንባሌህ (Mental Attitude) ነው::

የደረሰቦትና የሆነው ነገር ሳይሆን አእምሮ የደረሰውንና የሆነውን ነገር በሚያይበት መንገድ ነው የእርሶ ሕይወትና ኑሮ የሚገዛው፡፡ ሃሳቦን የመምረጥ አቅሞን ይጠቀሙ፡፡ የመረጡትና የሚያብሰለስሉት ሀሳቦች እርሶንና ኑሮዎን ይገዛሉና፡፡

ለውጤት ማሰብ ይማሩ፡፡
ካሊድ ሰኢድ፤ በኢትዮጵያ የቦብ ፕሮክተር ስልጠና አሰልጣኝና አማካሪ
የፈለጉትን ለመሆንና ለማድረግ የሚፈልጉበት ለመድረስ ትኩረት ተስኖታል?

ስላለፈው ስለትላንቱ ስለሆነው ስለሄደውና ስለመጣው መንገድ ላይ ሰው ስለተናገሮት ነገር ስላዩት ፊልም ስለሰሙት ሰበር ዜና ስንቱን አስበው ይችሉታል ግን?

ለእርሶ ለማይረባዎት ውስጦን ለሚያደማዎት ውስጦንና ስሜቶን ለሚረብሽና ለሚያቆሽሽ የእርሶን ማንነትና አቅም ጥያቄ ውስጥ ከሚከትቦትና እርሶንና ማንነቶን ለሚያጎድፍ ሀሳቦች አያብሰልስሉ፡፡ እርሶ ሰው በመሆኖ ብቻ ጥያቄ ውስጥ የማይገባ ብቁ ፍጥረት ነዎት፡፡

መሆንና ማድረግ መድረስ ከሚፈልጉት ለመድረስ እርሶን ሊያቆምና ሊገታ የሚችል አንድም የለም ከሃሳቦ በቀር፡፡ ሃሳቦን ይምረጡ!

ሃሳቦን ወደ ውጤት ይለውጡ!
ካሊድ ሰኢድ፤ በኢትዮጵያ የቦብ ፕሮክተር ስልጠና አሰልጣኝና አማካሪ
ግን እሱ ማን ነው?

ስለ ካሊድ ሰኢድ በጥቂቱ
ካሊድ ሰኢድ የግል ስልጠናውን በዓለም ታዋቂና ለ86 አመት በአእምሮ፣ በሰው አቅም እና ስኬት ላይ ተመራማሪና አሰልጣኝ ኤክፕርት የሆነውን የቦብ ኘሮክተርን ከፍተኛ የሚባለውን ደረጃ (Proctor Gallgher Consultant) ስልጠና በቦብ ፕሮክተር አማካኝነት በዚህ ዘርፍ ስልጠና በመውሰድ በጥር 25, 2011 ዓም ጀምሮ የቦብ ሰልጣኝ ተማሪ በመሆን የቦብ ፕሮክተር ስልጠናዎች አስልጣኝና አማካሪ የመሆንን የህይወቱን አዲስ ምእራፍ የጀመረው።

ካሊድ ከልጅነት ጀምሮ ለለውጥና እድገት በነበረው የግል ዝንባሌ ሆላም አድጎ በራሱ እና በህይወት ውስጥ ለምን የሚሉ ያለተመለሱ የውስጥ ጥያቄዎችና ጉትጎታዎች በራሱ በሚያደርገው ፍለጋዎች ውስጥ በሚያነባቸው የመጽሃፍት ንባብና ካጠናቸው ስልጠናዎች ለእርሱ አጥጋቢና የሚያረካውን በቂ አሳማኝ ምላሽ ሊያገኝ ባለመቻሉ ያላማቆረጥ ፍለጋውን በመቀጠል ሂደትና ጥረት ውስጥ ነበር ከቦብ ፕሮክተር ስልጠና ጋር ለመገናኘት የበቃው። ይህ የቦብ ስልጠና ክፍያ በዶላርና እጅግ በጣም ውድ በመሆኑ ካሊድ የነበረውን ባለ ሶስት መኝታ ቤቱን መሸጥ ግድ ስለሆነበት ቤቱን በመሽጥ ነበር ወደዚህ ስልጠና የተቀላቀለው። ይቀጥላል......
የእርሶ አለም በውስጦ ነው፡፡ በእጆ ነው፡፡

የአንተ አለም ህይወቶ ኑሮህ ከሰዎች ያለህ ግንኙነት የትዳርህ የቤተሰብህ አጠቃላይ አለምህ የሚወሰነው አንተ ባለህ ውስጣዊ ምልከታህ አእምሯዊ ዝንባሌህና አመለካከትህ ነው፡፡

የአንተ ውስጥህ እና ምልከታህ እይታህና አስተሳሰብህ ሲቀየር ዙሪያህና በዙሪያህ ያሉ ነገሮች እና ሰዎች ሁሉ ላንተ ያለቸው ስሜትና ምልከታም ይለወጣል፡፡ አለምህም ይለወጣል፡፡

አለሞ በውስጦ ነው፡ ፡

ለውጤት እናስብ!
ካሊድ ሰኢድ፤ በኢትዮጵያ የቦብ ፕሮክተር ስልጠና አሰልጣኝና አማካሪ
.......ግን እሱ ማን ነው?
ሰለ ካሊድ በጥቂቱ ከባለፈው የቀጠለ

ካሊድ ከ9 ባለይ የሚሆኑ የተለያዩ የቦብ ስልጠናዎችን በቀጥታ በፕሮክተር ጋላከር ኢንስቲትዩት ስር የሰለጠነ ሲሆን በኢንስቲትዩቱ ስር የራሱ የግል አካውንት ያለው በመሆኑ በዚህ ኢንስቲትዩት ውስጥ የሚገኙ የተለያዩ የስልጠና ማቴሪያል ጥናትና ምርምሮች እንዲሁም የውይይት መድረኮች በቀላሉ ማግኘት በመቻሉ ምክንያት ይህንን እድልና አጋጣሚ በመጠቀም ነበር ለሚፈልጋቸው ምላሾችና ጥያቄዎች ሰፋ ያለ ጥናት በማድረግ ከአራት አመታት በላይ የቆየ ሲሆነው አሁንም ድረስ በዚሁ ዘርፍ ጠለቅ ብሎ በመግባት ጥልቅ የሆኑ እውቀቶችና መረጃዎችን በማየትና በማጥናት በዚህ ሞያና ዘርፍ ያለማቆረጥ የጠለቀ እውቀትን እያካበት የሚገኝ ግለሰብ ነው። ይቀጥላል....
ግን እሱ ማን ነው? ከባለፈው የቀጠለ .... ካሊድ ቦብ ፕሮክተርን እና እድሜ ጠገብ የሆኑ እውቀቶችን ለሌሎችም ይጠቅሙ ዘንድ ሃሳቦችን በስፋት በማስታውቅ በማቅረብና በመተነትን ይታውቃል። ከዚህ አልፎ የሱ ሜንቶር (Mentor) የሆነው ቦብ በህይወት በነበረበት ወቅት በራሱ አንደበት የሚሰጣቸውን የተለያዩ የነጻ ስልጠናዎችና ሴሚራኖች በስፋት በማስተላለፍና በማቅረብ ሌሎች ከዚህ እውቀትና ሃሳብ ተቆዳሽ በማድረግ በብዛት ይታወቃል። ይቀጥላል.....
የትኛው መንገድ ለይ ነው የቆሙት?
ህይወት ያለማቆረጥ የምትጎዝባት መንገድ እንጂ አንድ ቦታና ነገር ላይ ደርሰህ ሁሉን ጨርሰህ እፎይ ብለህ የስኬት ጥግ ላይ ቆመህ የምትቀመጥባት ቦታ አይደለችም። ዛሬ ላይ በህይወትህ የትኛውም ደረጃ ላይ ብትሆን እንኮን በራሰህና በማንነትህ፣ በቤተሰብ ጉዳይ፣ በትዳርህ፣ በገንዘብ፣ በስራ፣ በንግድ፣ በማሃበራዊ ጉዳይና ግንኙነትህ፣ በሃይማኖትህ አልያም ብቻ በሆነ አንድ የህይወትህ መንገድና ክፍል ውስጥ ለውጥና እድገት መፈለግህ አይቀርም። እራሶ ላይ በመስራትና እራሶን የበለጠ በመጠቀም ብቻ ነው ለራሶና ለሌሎች መትረፍ የሚችሉት። እራሶን በተሻለ መንገድ ይበልጥ ለመጠቀም እራሶ በራሶ ላይ ይሰልጥኑ።
በቅርቡ ሹክ ልንሎት ነው ይጠብቁን...
እራሶንና ስሜቶን መግዛት እስካልቻሉ ድረስ በህይወት የሚወስዶቸውን እርምጃና ተግባራት በመቆጣጠር ለእድገትና ለለውጥ ወደፊት መራመድ አዳጋች ነው። ሃሳቦን መግዛት እስካልቻሉ ድረስ ደግሞ የሚሰማዎትን ስሜትና የሚወስዶቸውን እርምጃና ተግባሮን መቆጣጠር የማይተሰብ ነው። በአስተሳሰብ ለውጥ ሂደት ሃሳቦን የሚገዙበትና የሚቆጣጠሩበት እራሶ በራሶ ላይ የሚሰለጥኑበትን መረጃዎችና እውቀቶች በቅረብ ቀን...
ልብ ብለው አስተውለዋል ግን? ዛሬ ይህንን አደርጋለሁ ብለህ አልመህና አቅደህ ተነስተህ ያሰብከውን ነገር ከመፈጸምህ በፊት በሃሳብና በስሜት አስቀድመህ ተሸንፈህ እርምጃህና ተግባርህ ካሰብከው ፍጹም ተቃራኒ ውሎ ውለህ ብክን ብለህ የምታሳልፍባቸው ግዜያቶች ውስጥ በህይወት ብዙውን ግዜ ወደፊት ከመራመድ ይልቅ ብክን ብለን ወደሆላ እንቀራለን። ይህንን አስተውለው ይሆን ግን? ይህንን ሂደትና ሁኔታ በግልጽ በመረዳትና በማወቅ እራሶ በራሶ ላይ ለውጥ የሚያመጡበትን ሂደትና መንገድ ይፈልጉ ይሆን? በቅርብ ቀን...
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ይብዛም ይነስ ብዙ አውቀናል ብዙ ስምተናል ግን አሁንም ብዙ ግራ ተጋብተናል አሁንም መፍትሄ ያስፈልገናል ...
ወደ ፊት በመራመድ በሂደት ማድረግና መድረስ የምንፈልገውን ቦታ ለመድረስና ለማግኘት የሚያስፈልገንን ማንነት ክህሎትና ችሎታ በእምሮዎችን ውስጥ እየተገነባንና እየተቀረጽን የምንፈልገው ነገር ጋር ለመድረስ የሚያስችለንን ውስጣዊ ንቁ ግንዛቤ (Conscious awareness) ላይ ለመድረስ የሚያስችለንን ሂደትና መንገድ ማቅረብና ማመቻቸት ያስፈልጋል!!!
....እሱ ማን ነው? ከባለፈው የቀጠለ
ከዚህም በተጨማሪ ካሊድ በዋናነት ስልጠና ሚሰጥበት የሆነውን Thinking into results ስልጠና ሲሆን በዚህ ስልጠና ዙርያ ሴሚናር ሃሳብን በመቆጣጠርና በመምራት ማንነታችንን የመምራት ጥበብ ሂደት በአስተሳሰብ ለውጥ ለውጤት መስራትን የነጻ ሴሚናር ስልጠና በመስጠት በብዛት ይታወቃል። ካሊድ በProctor Gallgher Consultant ስር በቦብ የተዘጋጀውንና የረቀቀውን Thinking into results ስልጠና በካሊድ አሰልጣኝነት ስር ከቦብ ፕሮክተርና ከሳንዲ ጋላገር ጋር በጋራ በካሊድ አሰልጣኝነት በመታገዝ ለተለያዩ ግለሰቦች በግልና በግሩፕ የኦንላይን እና የአካካል ስልጠናም በመስጠት በስፋት ይታወቃል። በፌስቡክ በሚያቀርባቸው የተለያዩ ጥልቅ ሃሳቦችና እውቀቶችም በስፋት ይታወቃል። ይቀጥላል...
ዋናው ቁም ነገሩ እኛ ያወቅንውንና ማድረግ የምንችለውን ነገሮች በመተግበር በየቀኑ በህይወታችን ውስጥ በመኖር ወደ ፊት በመራመድ መሆንና ማድረግ መኖርና መድረስ የምንፈልጋቸውን የህይወት እሴትና አላማ ለመፍጠርና ለመቅረጽ ያለማቆራጥ መጎዝ የምንችልበትን አቅምና ስብዕና መገንባት ነው። ይህንን ሂደት ለመቅረጽና ለመመስረት የሚሚያግዞትን ደረጃ በደረጃ (Step by step) እውቀትና መረጃ ካስፈለጎ በቅርብ ቀን...
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ሙሉ ሺዲዮው... መድረስ የምንፈልገውን ቦታ ለመድረስና ለማግኘት የሚያስፈልገንን ልቦናዊ ማንነት ክህሎትና ችሎታ በእምሮዎችን ውስጥ እየተገነባንና እየተቀረጽን የምንፈልገው ነገር ጋር ለመድረስ የሚያስችለንን awareness ላይ ለመድረስ የሚያስችለንን ሂደትና መንገድ በማቅረብና በማመቻቸት ብቻ ነው ዘላቂ ለውጥ የሚመጣበትን መንገድ መፍጠር ይሚቻለው።
👇
https://www.facebook.com/reel/794115565536128
Music by Daddy_s_Music from Pixabay
“የሰው የለው ሞኝ ከአገሩ ከቦታው ከስፍራው ሲገኝ” አርቲስት ይርጋ ዱባለ.... ይህ ላንተ ምን መልክት ይሰጥሃል? አንት ውስጣዊ ነጻነትህን ስታጣ አመለካከትህና አስተሳሰብህ በሰዎች በሁኔታዎችና በነገሮች ስር ወድቀው ከውስጣዊ እውነተኛ ማንነትህን ጋር ተለያይተህ እራስህን አስተሳሰብህንና ማንነትህን ስታጣ ያኔ አንተ ከቦታህ ከስፍራህ ከአገርህ ወጥተሃል እናም የትም አገርና ቦታ ላንተ ባዳ ነው የሚሆንብህ። አይመስልህም? በእውነተኛ ውስጣዊ ነጻነቶና በህይወቶ ውስጥ መኖር የሚጀምሩበት ግዜው አሁን ነው! በቅርብ ቀን ይጠበቁን...
.......ግን እሱ ማን ነው? ከባለፈው የቀጠለ... ካሊድ በነዚህ ስራዎቹ ውስጥ በፈጣሪ ፍቃድ እና በግለሰቦች በራሳቸው የግል ጥረትና ፍላጎት የብዙ ሰዎች ህይወትንና አቅጣጫ ወደ ራሳቸው ማንነትና ፍላጎት በሚወዱት የህይወት አቅጣጫና መስመር መጎዝና ማደግ እንዲችሉ የሚያስችላቸውን ዘላቂና ቆሚ የአስተሳሰብ ለውጥ እድገት ለብዙሃን ሰዎች ምክንያትና መንስኤ የሆነ ግለሰብ ሲሆን ከእርሱ ተመሳስይ ፍላጎትና ዝንባሌ ያላቸውን ግለሰቦች አሰልጣኝነት የመሆን አላማና ግብ እንዲያሳኩና ወደግባቸው በመራመድ የሚወዱትን ምኞትና ፍላጎት የሆነውን የአሰልጣኝነት ስራ እንዲኖሩትና በተሳካ ሁኔታ ማሳካት እንዲችሉም ጭምር ምክንያት ለመሆን ችሎዋል።
HTML Embed Code:
2024/06/02 14:11:19
Back to Top